Wednesday, August 7, 2019

የአብይ አሕመድ ኢንተርሃሙዌዎች ጌታቸው ረዳ Ethio Semay (ኢትዮ ሰማይ)


 የአብይ አሕመድ ኢንተርሃሙዌዎች
ጌታቸው ረዳ Ethio Semay (ኢትዮ ሰማይ)
የኢትዮ ሰማይ ድረገጽ ተከታታዮች እንደምን ሰነበታችሁ? ፈረንጆች ፋታ የማይሰጥ ሰሞን የሚሉት “ቢዚ ዊክ) ወጥሮኝ ስለነበር ለዚህ ነው ያላገኛችሁኝ። ሰላም ለሁላችሁ። ዛሬ የማቀርብላችሁ ርዕስ እንደምትመለከቱት ነው። እኛ ኢትዮጵያውያን የነገሮችን የመርሳት መጥፎ ባሕሪ ስላለን የተደረጉብንን ጥቃቶች ካላስታወስናቸው ማንም እየመጣ በቃላት እየደለለ ጥቃቶች እየፈጸመ መቀጠሉ ስለምታዘብ፤ የግድ ጥቃቶችን ከሕሊናችሁ እንዳይጠፉ ላስታውሳችሁ። ማስታወስ የጥቃት ማስወገጃ አይነተኛ መሳርያ ነው እላለሁ። ስለሆነም ጥቃታችንን ደጋግሜ በሚከተለው ትችት ላስታውሳችሁ።
Ethiopian Oromo Qero Interhamwe እነኚህ ከላይ የምታይዋቸው በፎቶግራፍ የሚታዩት ወሮበላ ቡድን ሰውን ለመግደል የያዙት ዱላ ሥራ ላይ ለማዋል “ቄሮ” ተብሎ የሚጠራው የኦሮሞ “ኢንተርሃሙዌ መንጋ” ፎቶግራፍ ነው። (ፎቶ-1) ኦሮሞ ቄሮ/ኢንተርሃሙዌ)

 
Rwanda Hutu Impuzamugambi Interhamwe እነኚህ ድገሞ የሩዋንዳ ኢትርሃሙዌ ቡድኖች ከፈንሳዮቹ ወታደራዊ መኪና ጎን ለጎን ዱላ ይዘው ለጭፍጨፋ እየተጓዙ ያሉ የሩዋንዳ ኢንትረሃሙዌ ወጣት ወረበላ ቡድን ፎቶግራፍ ነው።(ፎቶ-2)ሩዋንዳ ቄሮ/ኢንተርሃሙዌ


የኦሮሞ ኢነትርሃሙዌ የቄሮ አዋጅ!
የአዲስ አበባ ኗሪዎች ዕጣን ለማጨስ ሲፈልጉ የኦሮሞ ፈቃድ ያስፈልጋል! (ፎቶ-3) የአዲስ አበባ ኦሮሞ ቄሮ ኢንተረሃሙዌ አዋጅ


ሰሞኑን አንድ ወዳጄ የጻፉልኝን ደብዳቤ ላስነብባችሁ።

“ሰለም ወንድሜ ጌታቸዉ ቁጭ ብለን የስቀልነዉ ቁመን ማዉረድ አቃተን የሚባለዉ ነገር እኛ ላይ ሳይደርስ አልቀረም። የአንድነት ሐይሉ ስለ ተዘናጋ ዛሬ እነ ሕዝቅኤል/ጁዋር/ሌንጮ/ዲማ ተኩራርተዉ አዲስ ታሪክ ፈጥረዉ ያሻቸዉን ተረት እየሰበኩ ተረቱ ታሪክ ሁኖ አዲሱ ትዉልድ ኢትዮጵያ ምንድነዉ ማለት ጀምሯል። ይሄ ነገር ከእጅ ሳያመልጥ የቀረ አልመሰለኝም ሰዉ ሀገሩን በአንድነቱ አስጠብቆ ከዉጭ ወረራ እራሱን ጠበቆ አንድነቱ በሰጠዉ ተጠቃሚ ከመሆን ይልቅ ክልል በሚሉት የልጅ ጨዋታ ተጠምዶ ይገዳደላል። ምሁር የተባለዉም ግራ ተጋብቷል የመንፈሳዊ አባቶችም ከአለማዊዉ የተለየ ክብርና እዉቅና ተነፍጓቸዋል ሀገሪቱ ከህወአት ወደነዚሀ ያደረገችዉ ጉዞ ከድጡ ወደ ማጡ ሁኗል ነገር ሳይበላሺ የቀረ አልመሰለኝም። ከኦነግ ሾልኮ የወጣዉ እንዲህ ከሆነ በዝግ የሚያደርጉት ስብሰባ ምን ሊሆን ይችላል።፡በአሁኑ ጊዜ የኦሮሞ ድርጅት በጠቅላላዉ በአንድ ጥላ ስር ነዉ ኢኮኖሚ ፖለቲካ ጦር መሳሪያ በጁ ነዉ ከህወአትም ጋር በጣምራ እየሰሩ ነዉ አሁን አሁን ሳስበዉ አብይ ወደ ስልጣን ከመምጣተ በፊት አብረዉ የገቡት ቃል እንዳለ በእርግጥ እንዳምን ሁኛለሁ።፡ለማንኛዉም ኢትዮጵያን አምላክ ይጠብቅ የመለሰ ዜናዊ ክፉ ስራ ፍሬ ሳያፈራ አልቀረም።” ይላሉ ወዳጄ።


አጥቂዎቻችን በረዢሙ የ28 አመት ጥቃት የምናስታውሳቸው በወያኔ ትግራይ እምነትና መመሪያ የሚመሩት “ትግሬዎችን ነው”፤ በአንድ አመት ውስጥ ደግሞ የ28 አመት ጥቃት ዕጥፍ አድርጎ ጥቃቱን የሰነዘረብን ኦሕዴድ/ኦነግ/ የተቀናጀ መመሪያ እየተመራ ያለው ሥርዓተ አልባው አፓርታይድ መሪው አብይ አሕመድ ዓሊ ነው። ይህ ሃቅ ደግሞ ኦሮሞዎቹ በአንድ ጥላ ስር ተሰባስበው አዲስ አባባ የኛ ናት በኛ ፈቃድ ትኖራላችሁ እያሉ ኢትዮጵያውያንን በገዛ አገራቸው ሊነጥቅዋቸው ተዘጋጅተዋል። ትግሉም በዚያ ውጥረት ውስጥ ተካርሯል። የ 5 አውራ ኦሮሞ ድርጅቶች ያወጡትን “የወረራ አዋጅ” መግለጫ እንዳነበባችሁት እርግጠኛ ነኝ (ይህንን ታስታውሳለችሁ ብየ ተስፋ አደርጋለሁ)።


ይህ ከ40 ማታት በላይ የታቀደ በ 135 ቀናት ውስጥ የተከናወነ የኦሮሞ ሊሂቃን ያቀዱት  የወረራ ፕሮጀክት/ዘመቻ ነው። ይህ ትክክለኛ የወዳጄ ግንዛቤ እውነታውን ለመመልከት በቃላሉ እንዲረዳን ከተፈለገ፤ ሥልጣን ላይ የተቀመጠው “የኦፒዲኦ” መሪው የጂማው ኦሮሞው ኮሎኔል አብይ አሕመድ እውቅና እየተተገበረ ያለው አገርን በጥበብ የማፍረስ ዘዴው ሚዛን ላይ ሲቀመጥ፤ ውድመቱ ከወያኔዎች ጥቃት እኩል የሆነ አንዳንዴም  የከፋ ግልጽ የጥቃት ዘመቻው እየተካሄደ ነው።


 ኮለኔሉ ምን ታመጡ ብሎ በኮማንዶ ወታደሮች የሚያስጠብቀውን የትግል ጓደኛው የአርሲው “ግማሽ የሸዋ አማራ ክርስትያን በግማሽ ገባሮ/ኦሮሞ” የሆነው ጃዋር መሓመድ የሚያዛቸው “ቄሮዎች” በአዲስ አበባ ከተማ እየዞሩ ኗሪዎች “ዕጣን” አንኳ ለማጨስ ከኦሮሞዎች ፈቃድ ማግኘት እንዳለባቸው እና እንዲሁም “የአማራ ቤቶች ውረሱ ተብለናል” ንዳሉ ቄሮዎች የተሠጣቸው አጀንዳ በግሃድ ያወጁትን ታስታውሳላችሁ። ከረሳችሁት ላስታውሳችሁ፦


በአዲስ አበባ ውስጥ ዕጣን ለማጨስ ፈቃድ ከኦሮሞዎች መጠየቅ እንዳለብን የተነገረን ከመግለጼ በፊት ተመሳሳይ ዘመቻ ወደ ሐረር ልውሰዳችሁ። ተመሳሳይ የኦሮሞ ቄሮ ‘ኢንተርሃሙዌ’ ሓረር ውስጥ የሆነው ከ5 ወር በፊት እንመልክት ከዚያም ወደ አዲስ አበባ ልወስዳችሁ ነኝ።


በሐረር የኦሮሞ ቄሮ ኢንተርሃሙዌ አዋጅ ፡እንዲህ ይላል፥---


 “በሓረር የአማራ ቤቶችን ውረሱ ተብለናል። ከቀበሌ 15 (ቢሳ ሠፈር ጀምሮ) እስከ ህይት ፋና ሆስፒታል ድረስ ያሉትን የአማራ ቤቶችን ውረሱ ተብለናል።” በማለት ከየት እንመጡ የማይታወቅ ቁጥራቸው እጅግ በጣም ብዙ የሆኑ በትጥቅ የታገዘው የኦሮሞ ኢንትርሃሙዌ የቄሮ ቡድን አማራዎችን እየለዩ ማጥቃታቸውን የወራት ጊዜ ማለት የ5 ወራት ትዝታ ነው። ይህ የዘር ጥቃት አብይ አሕመድ "ልቅ የለቀቃቸው" የኢንተርሃሙዌ የመንጋ ቡድን ነው።በአዲስ አባባ የኦሮሞ ቄሮ ኢንተርሃሙዌ አዋጅ ሞ እንዲህ ይላል፥--- 


“ካለ ኦሮሞ ፈቃድ አዲስ አበባ ውስጥ እጣን ማጨስ እንኳ አትችሉም!” 

ይህ አዋጅ እና ክስተት “ወራሪ ጣሊያን” ኢትዮጵያን ሲወርር እንዲህ የከፋ አዋጅ አላወጀም ። ኦሮሞች ግን መሪያቸውን በዙፋን ስላስቀመጡ እንዲህ ያለውን አዋጅ ዘርግተው በይፋ አውጀዋል። በለገጣፎ በተለይ በቡራዩ የጋሞጎፋ እና አማራ ማሕበረሰቦች በገጀራ በጥይት በቢላዋ ተጨፍጭፋዋል። ይህ የዘር ማጥፋት (ጀነሳይድ) የፈጸሙት ከየኦሮሞ ክፍለግዛት በጭነት መኪኖች ተሳፍረው በብዙ ሺሕ የሚቀጠሩ ኦሮሞ ቄሮዎች በቡራዩ እና በመሳሰሉ አካባቢዎች ተሰማርተው መሬት በደም ንድትጨቀይ አድርገው ሴቶች እና ልጃገረዶች ተደፍረዋል። ይህ የተደረገውም አብይ አሕመድ መሪያቸው በዙፋን ላይ ቁጥጢጥ ካለበት ጊዜ በወራት ውስጥ የተፈጸመ ነው። ሩዋንዳ የተፈጸመው ጭፍጨፋ አብይ አሕመድ በነገ በጥቀት ወራት ይፋዊ ጥቃት ተፈጽሟል። ጥቃቱ ለደረሰባቸው ች አብይ ሰብስቦ “ገዳዮቻችሁ ይቅርታ አድርጉላቸው” ብሎበትኩስ ሬሳ ላይ በዘናቸው ሲሳለቅባቸው የተቀዳ ቪዲዮ እኔው ጋር አለ። "ሰዎች  መግደል ይቻላል ግን ኢትዮጵያን ማፍረስ ግን አይሳካላቸውም" እያለ ዜጎች ሲጨፈጨፉ “ኢትዮጵያ” ይትባል የሕልም ዕቃ ይመስል” ሰው እና ኢትዮጵያ እየለያየ ሲራቀቅባቸው መስማት ያማል። በፊቱ ላይም ምንም የቁጣ ንዴት እና የቁጭት ገጽታ አይታይበትም። በወቅት ደርሰን ጥፋቱን ያለማቆማችን ይቅርታ ከማለት ይልቅ ሲራቀቅባቸው ማየት ሰውየው አጅግ አረመኔ አጭበርባሪ ሰው ነው።    በአፍሪቃዊቷ ሃገረ ሩዋንዳ ኢንተርሃምዌ (ትርጉሙም - “በጋራ የሚያጠቁ”) እየተባለ የሚታወቀው በዘር የተደራጀ ይህ ‘መንጋ’ በገጀራ የታጠቀ ታጣቂ ቡድን እና “ኢምሱዛሙምቢ (“ተመሳሳይ ግብ ያላቸው) የተባሉ የሁቱ የሽብር ቡድኖች በፈረንጆች አቆጣጠር (እኤአ) በ 1994 በሩዋንዳ የዘር ማጥፋት ዘመቻ ውስጥ ትልቅ ሚና የተጫወቱ ቡድኖች ናቸው።እነዚህ ሁለት የሽብር ቡድኖች ያቀፉዋቸው ክፍሎች ልክ እንደ ኦሮሞዎቹ ከምሁራን እና ወታደራዊ ክፍሎች እስከ ተራ  ሚሊሽያና ወረበሎችን ያቀፉ የ “ሁቱ” ነገድ ቡድኖች ናቸው። የዘር ፍጅት ለማካሄድ የታገዙት በወቅቱ በሥልጣን መንበር የነበረው የሁቱ መንግሥት የMRND ፓርቲ መሪዎች እገዛ እና አውቅና ነው። አስገራሚ ያደረገው ደግሞ የሁቱ ሚሊሺያ የቱትሲ ዘር ለማጥፋት ሲዘጋጅ የነበረው ቡድን ወታደራዊ አሰልጣኝ ካድሬ የነበረው በምስጢር   “ስለ የኢንተርሃሙዌ ቅድመ ዝግጅት ጉዳይ” አስመለክቶ ለቀጠናው የተባበሩት መንግሥታት ወታደራዊ ጸጥታ አስከባሪ ሃይል ልኡክ ዋና አዛዥ ለነበሩት ለካናዳዊው አርጋዴር-ጄኔራል ሮማን ደልየር ፣ የዘር ማጥፋት ዘመቻው ከመጀመሩ ከሦስት ወራት በፊት ‘ኒው ዮርክ’  ወደ እሚገኘው ዋና መሥሪያ ቤት ከተጠቀሰው አሰልጣኝ በምስጢር እንደተነገራቸው ወዲያውኑ “በፋክስ” አሳውቀው ነበር። ሆኖም የዘር ማጥፋቱ ዘመቻ እንዲካሄድ ፍላጎት ባደረባቸው ጸረ አፍሪካ ግለሰዎች ምንም እርምጃ ሳይወሰድ ቀርቶ ጥፋት ደርሷል።


በተመሳሳይ ኢትዮጵያ ውስጥም በአንድ ዘር ላይ ያነጣጠረ ጥቃት (በአማራ ማሕበረሰብ) የጀመረው እና የተፈጸመው በ1991 ከዚያም በፊት በወለጋ “የኦነግ ታጣቂ ሃይሎች” የአማራ ህጻናት ተማሪዎች ክፍል ውስጥ ተዘግተው ቤንዚን ተርከፍክፎበቸው በቦምብ ጋይተው ከ350 ጽናት በላይ  አሰቃቂ ጭፍጫፋ እንደተፈጸመ የሚታወስ ነው። ከዚያ ዘመን ጀምሮ እስከዚቺው እስከ የጂማው ኮሎኔል አብይ ዘመን ድረስ ጭፍጨፋው እንደቀጠለ ነው። እነ በቀለ ገርባ እነ እዝቄል ጋቢሳ በግልጽ የኢንተርሃሙዌ ቅስቀሳቸው አገር ውስጥ በይፋ እያስፋፉት ነው።


ኦነግ (በዳውድ ኢብሳ የሚመራ ታጣቂ ቡድን) እና ቄሮ (በጃዋር እነ እዝቄል ጋቢሳ የሚመራ) ይህ አደገኛ ጸረ አማራ ቡድን በዘር ማጥፋት ብቻ ሳይሆን አገር እንደ አገር ኢትዮጵያ እንድትፈርስ የተሰማራው ይህ ቡድን በኮለኔሉ እውቅና ተጠናክሯል።  ወያኔን ወደ ጎን ገሸሽ አድርጎ ሥልጣን  የተቆጣጠረው ኮሎኔል አብይ አሕመድ ዓሊ ውቅና እና አበረታችነቱ የጎላ ሚና አለው። በሚገርም ሁኔታ የኦነጉ ሌላኛው ክንፍ መሪ የሆነው ኡጋንዳ ውስጥ በስደት ሲኖር የነበረው ብ/ጄ ከማል ገልቱ የተባለው “ኦነግ” አገር ውስጥ ከገባ ወዲህ የኦሮሞ “ክልል” የጸጥታ ሹም ተደርጎ  አገልግሎቱ ሲያበቃ አንድ አስገራሚ ሚስጢር መናገሩን ታስታውሳለችሁ።፡በብዙ ቦታዎች ሽብር እና የባንክ ዘረፋ የተካሄደው ፤ “ጠ/ሚ ኮሎኔል አብይ አሕመድ ዓሊ” የሚመራው “ኦፒዲኦ” የተባለው ድርጅት “አማራዎችን በመጨፍጨፍ ግምባር ቀደም ታሪክ ያለው ይህ የሽብር ድርጅት እንደሆነ በ ኤል ቲቪ ቀርቦ መስክሯል።


 አብይ አሕመድ የሚመራው ኦሐዴድ የተባለ ድርጅት ባለሥልጣኖች በደብዳቤ እየጻፈ ያሰማራቸው ሽብርተኞች እንደሆኑ ለጋዜጠኞች ቢገልጽም አንድም “የፓርላማ ተብየው” አባላት ይህንን ሰምተው ጄኔራሉም ሆነ አብይ አሕመድ ወይንም ክልሉን ሲመራው የነበረው “ለማ መገርሳ” አስጠርቶ ስለጉዳዩ እንዲጣራ አላደረገም። ምክንያቱም ልክ ሩዋንዳ ውስጥ ለMRND እንደቆመ ሁሉ “ኢሕአዴግ” ብሎ ራሱን በዲሞክራሲ ስም የሸፈነው መንግሥትም “ፓርላማው የቆመው ከህወሓት ወደ አብይ አሕመድ ‘ኦሕዴድ’ አገልግሎትት የዞረ” በመሆኑ በኦነግ/ኦፒዲኦ እየተካሄደ ያለው ጭፍጨፋ ተሸፋፍኖ እንዲታለፍ ሆኗል (ለስም ሰዎች አስረናል ከማለቱ ባሻገር ይፋ የሆነ የፍርድ ችሎት አላየንም)። ለዚህ ነው በእነ በቀለ ገርባ እና እዝቄል ጋቢሳ እና ጃዋር መሓመድ በየክልሎቹ እየዞሩ አገር የማፍረስ ንግግር ዘመቻው የሚካሄደው የአብይ አሕመድ ውቅና እና አበራታችነት እየታገዘ ስለሆነ ነው።


ይህ ክስተት አዲስ ባይሆንም ኢትዮጵያ የሚከላከልላት መንግሥት ስታጣ መዳከምዋን
ሲያዩ ኢትዮጵያን ማጥቃት የኦሮሞ ፋሺስት ቡድኖች ‘ዓይነተኛ መያ’ ባሕሪያቸው መሆኑን ካሁን በፊት ብዙ ትችቶች የጻፍኩት ጉዳይ ስለሆነ ያንን በድረገጼ መመልከት ነው።ስለዚህ ኢትዮጵያ ውስጥ የኦሮሞ ኢንተርሃሙዎች እየሄዱበት ያለው አካሄድ የሩዋንዳ ቅጂ ነው። በ1994 ሩዋንዳ የዘር ማጥፋት ዘመቻ ሲካሄድ በነበረበት ወቅት የታጣቂዎች ሚና እና የመንገድ መዘጋቶች አጠቃቀም እስከ ጭፍጨፋ የተካሄደው መረጃ ልክ ኦሮሞዎች የቀዱት የሩዋንዳ ሁቱዎች ቅጅ ነው።
አመሰግናለሁ፤ ጌታቸው ረዳ (ኢትዮ ሰማይ)