Friday, September 19, 2014

የዩክሬይን ክራሚያና የሩስያ ጉዳይ ስለኢትዮጵያና ኤርትራ ያልተዘጋ አጀንዳ ምን ያሰተምረናል?



 Editorial Note:-          

Democracy that allowed Secession should be barred by law in the coming Ethiopian rule of law. Secession is chaotic system. People do not demand secession; only lunatic elites full of hate do.There is no name called Democracy that allows Yes or No for Secession. It is made all by the New World Order Conspirators who wants the world into fragmented lands to control weak states. Secession has nothing link to Democracy. Ethiopians should demand "death penalty" for any party leader asked or allowed a vote for secession. Anyone demand secession in India will punished by death. It should be implemented in Ethiopia too. Secession never guarantee "Democracy and peace". It destroys society into dark and misery. Evidences are plenty. Secession is always demanded by hate mongers and lunatic elites. Democracy is a vehicle for anyone, including murderers and dictators. Democracy can be a myth and destructive- in fact,  if you do not control it,  Nazi parties can climb to power (Hitler used it) or as Muslim Brotherhood used to come to power in Egypt. Secession is a dooms day gamers and a game for demons. Look at Eritrea and others. Read below a very important paper. Getachew Reda (Editor Ethiopian Semay)

Conspirators and their Mercenaries in Algiers signing an agreement to destabilize Ethiopia

የዩክሬይን ክራሚያና የሩስያ ጉዳይ ስለኢትዮጵያና ኤርትራ ያልተዘጋ አጀንዳ ምን ያሰተምረናል?

(አክሊሉ ወንድአፈረው - የግል አስተያየት)

መስከረም 2, 2007 (ተምበር 12 2014  )



ባለፉት ጥቂት ወራት በዩክሬንና ክራሚያ ውስጥ የተቀሰቀሰው ሁኔታ እና አሁን የደረሰበት ደረጃ ከኢትዮጵያ የፖለቲካ ምህዳር አንጻር ብዙ ዕድምታዎች አሉት፡፡ እነዚህን ዕድምታዎች መመርመር  በሀገራችን ውስጥ ያለፉና የወደፊት ጉዞ ላይ የተከሰቱ፤ እና ሊከሰቱም የሚችሉ ጉዳዮችን  ከወዲሁ በግምት ውስጥ በማስገባት  ሀገራዊ ራዕያችንን የትግል አቅጣጫችንን አና አጋርና ተቀናቃኝ ሊሆኑ የሚችሉትን ሃይሎች ለይቶ ለማወቅ ያግዛል ብዩ አሰባለሁ።  ይህን ማወቁ ደግሞ በሀገራችን እና በብሑራዊ  ጥቅማችን ላይ ጉዳት ሊያስከትሉ ከሚችሉ ተግባሮች እንንቆጠብ ዕድል ይሰጠናል። የዚሀ ጽሁፍ ዓላማም በዚህ ጉዳይ ዙሪያ ውይይት ለመጫር ነው።



ለመንደርደሪያ ያህል፦ ለመሆኑ በታሪክ ክራሚያ ዩክሬን ወይስ ሩሲያ ነበረች?

ጠቅለል ባለ ሁኔታ የክራሚያን ያለፉት 200 ዓመታት ታሪክ ስንመለከት በዋናነት የሩሲያ አካል ሆና መቆየቷን እናያለን። በሌኒን የሚመራው የሶሻሊስት አብዮት ከተቀጣጠለ 1917 በሁዋላም ቢሆን ክራሚያ በሶቭየት ህብረት ዕቅፍ ውስጥ አንድ ራስ-ገዝ አስተዳደር ሆና ቆይታለች።



ክሬሚያ የዩክሬን አካል የሆነችው ባውሮፓውያኑ አቆጣጠር 1954 በወቅቱ የራሽያ ኮሚኒስት ፓርቲና ያገሪቱ መሪ በነበሩት በኒኪታ ክሩስቼቭ ሲሆን፤ እኘህም ሰው የትውልድ ቦታቸውና የፖለቲካ አጋራቸው ለሆነችው ዩክሬን በስጦታ መልክ ከሰጡ በሁዋላ ነበር፡፡ በወቅቱ ይህ ጉዳይ ለሶቭየት ፖለቲካ መሪዎችም ሆነ ለክራሚያ ነዋሪዎች አስጨናቂ ጉዳይ አልነበረም፡ ለምን ቢሉ ዩክሬን የሶቭየት ህብረት አንድ ክፍለ ሀገር (ሪፐብሊክ) የነበረች ሲሆን የክራሚያ ዩክሬን ውስጥ መግባት ለአስተዳደር አመቺነት ካልሆነ በስተቀር በጊዜው ሌላ ሰፊ የፖለቲካ እንደምታ አልነበረውምና ነው። ከዚያም አልፎ በተለይ በምስራቅ አውሮፓ ይገኙ የነበሩት ሁሉም ሶሻሊሰት ሀገሮች  በሶቭዬት ሶሻሊስት ሪፐብሊክ የበላይነት ጥላ ስር  እንዳንድ ሀገር ሆነው  (በሶሻሊስት ዓለማቀፋዊነት መርህ) ይመሩ ስለነበርም እንኳንስ በአንድ ሀገር ስር ያሉ ያስተዳደር ክልሎች በተለያዩ ሶሻሊስት ሀገሮችም መካከል ቢሆን ድንበርና ድንበርተኘነት ታላቅ ቁምነገር ያለው ተደርጎም ይወሰድ እንዳልነበር ማሰታወስ ያስፈልጋል።



የክራሚያ ነዋሪዎች በማንነት አንጻር ራሳቸውን እንዴት ይመለከታሉ?

ይህ አጅግ ወዛጋ ሬን ግጭት ውስጥ ተፋላሚ የሆ ክፍችም ግል አቌማቸውን የብዙኑን ፍላጎት እንደሚንጸባርቅ አድርገው የሚሟገቱበት ዕውነታ ነው::



በዩክሬይን ስልጣኑን የጨበጡት ክፍሎች እና ደጋፊቻቸው የክሚያ ነዋሪ ራሳቸውን የሚያዩት ከሁሉም በላይ  ከራሽያ የተለዩና ዩከሬንያዊ አድርገው ነው የሚቆጥሩት”  ሚለውን አመለካከት ሁሉም ስው እንዲቀበለው ይፈልጋሉ:: ክራሚያ የዩክሬን አካል ሆና የቆየችበትን ጊዜ በማጣቀሰም በተለይም አዲሱ ትውልድ የተማረውም ያደገውም ስለዩክሬን እየተነገረው ስለሆነ ስለ ራሽያዊነት የሚማውም የሚያውቀውም  ቅንጣት ነገር እንደሌለና ይህም በመሆኑ  ከራሽያ ጋር  የሚያገናኝው ስንሰለት እንደተበጣጠስ ደጋግመው ሲናገሩ ይደመጣሉ::



ክራሚያ ውስጥ የሚታየው የሚጨበጠው  እውነታ ግን ሌላ ነው:: 60 መታት የዩክሬን አካልነት እና 23 አመታት ሙሉ ለሙሉ መለያየት በሁዏላ የከሬሜያም ሆነ ሌላው የምራቅ ደቡብ ምሥራቅ ዩክሬ ነዋሪ የሚማችው ስሜት ግን ሩሲ ጋር ያላችው የቀደመ ስስር አንጅ የዩክሬን አካልነት ሆኖ አልተገኘም:::



ከዚህ በታ የሚታየው በቅርቡ የተካ  አንድ ጥናት  እንደሚያሳየው  70%  (ሰባ ከመቶ) የማያንሱ ክራሚያዎች ራሳቸውን የሚቆጥሩት ብቻ ሳይሆን ትስስርንም ቢሆን የሚሹት ከሩሲያ ጋር እንደሆነ ያመለክታል::




ሁኔታ የሚያሳየው ከአቅመቢሷ ዩክሬን ጋር ከመዳበል ይልቅ ሰፋና ጠንከር ካለችው ሩሲያ ጋር መሆኑ ምን ያህል ጠቀሜታ እንዳለው መገንዘብን ብቻ ሳይሆን የረጅሙ ጊዜ ትስስር የፈጠረውን ማንነትን በቀላሉ መበጣጠስም  እንደማይቻል ነው::


በዚህም ምክንያት ይመስላል ሚያዎች በተለያየ ሁኔታ በዩክሬን ውስጥ ማንነታቸውን ሊያሰከብሩ ሲጥሩ ቆይተው ሳይሳካላቸው ባሉበት ሁኔታ ዩክሬን ጓዟን ጠቅልላ በአውሮፓ ማህበረሰብ ቅፍ ስር ለመግባት ርምጃ መውሰድ ስትጀምር ሁኔታው ስላልጣማቸው ከገቡበት ፈተናና አጣብቂኝ እንድትታደጋቸው ሩሲያን የተማጸኑት።

ቀደም ሲል በምዕራቡ ዓለም ፖለቲካ ተንታኞች  ክራሚያወች ወደ መዋሀድን አይፈልጉም፤  ፍላጎታቸው ከሌ አውሮፓ ጋር ይበልጥ መተሳሰር ነው በማለት ደግመው ደጋግመው ይናገሩ ወይም ያስተጋቡ እንጂ በማርች 2014  ሬፈረንደም ሲካሄድ ግን  97%  የሆነው ህዝብ ዩክሬንን ትቶ ወደ ራሽ መቀላቀልን የመረጠው። ይህ ሁኔታ የክራሚያ ተወላጆች ሩሲ ጋር  ለረጅም ዘመናት ከነበራ የታሪክ፣ የፖለቲካ የቤተሰብ፣ የባህል፣ የስነ ልቦናና፣የማሕበራዊ ግንነት   ሙሉ በሙሉ  መለያየት ችለናል  በራሸያና ሚያወች  መካከል የነበረውን የአንድነትና የትስስር ስሜት አጥፍተነዋል  ብለው ሲያስቡ ለነበሩ ሁሉ መርዶና የራስ ምታት ነው የሆነባቸው::


ክራሚያውያን ከሩስያ ጋር መልሶ ለመቀላቀል 90 በመቶ በላያ በሆነ ድምጽ  ፍላጎታቸውን ገልጸው ደስታቸውን ሲገልጹ )  Mike Collett-White and Ronald Popeski SIMFEROPOL/KIEV Sun Mar 16, 2014 (Reuters) – Russian) SIMFEROPOL/KIEV

ባሁኑ ሰአት በክሬሚያ የሚታየው ሁኔታ ቢያ ስር የወደቀውን ህዝብ የማንነት ጥያቄ ተመለከተ ብዙ ጉዳዮችን እንድዝብ ያስገድዳል። ፉት 23 አመታት የኛ ነች; የማንነታችን   ነች; ብለው ከሚመለከቷት እና ከሚወ ኢትዮጰያ ተነጥለውና በኤርትራ ውስጥ ከነመሬታቸው ተገደው ከሚገዙት የአፋር፤ ኩናማ፤ ኢሮብ፤ የሀማሴን፣አካለጉዛይ እና ሌሎችም ወገኖቻችን ሁኔታ ጋር እጅግ ይመሳሰላል። ታላቁ የአፋር ተወላጅ የተከበሩት ቢትወደድ ዓሊ ሚራህ፣እንኳንስ ህዝቡ ግመሎቻችንም ቢሆኑ የኢትዮጵያን ባንዲራ ያውቃሉሲሉ የተናገሩት ታላቅ መሪ ቃል  ስለአፋር ህዝብ የማይናጋ ጥልቅ ኢትዮጽያዊነት በቂ ማስረጃ ነው። ከዚህም ሌላ ቅድመ ሻቢያ/ወያኔ ከኢትዮጵያዊነት ውጭ ምንም አናውቅም ብለው ስለቆሙ በሻቢያ ሰራዊት በተደጋጋሚ የተደበደቡት የኩናማ፤ የሳሆ ወዘተ ወገኖች ታሪክ  ኢትዮጰያዊነትንና የትዮጵያዊነትን ስሜት ከነዚህ ህዝቦች መለየት እንደማይቻል ወይም እጅግ ረጅም ጊዜ እንደሚወስድ ያመላክታል።

በመሀል ብዙ ቅሬታ እንደተከሰተ አጠያያቂ ባይሆንም ኤርትራን ከኢትዮጵያ ጋር ለማሰተሳሰር ስለታገሉት ስለወደቁት አርበኞች፣ልጆቻችውና ልጅ ልጆቻቸው አዕምሮ ውስጥ በአሁኑ ሰአት ምን አይነት ስሜት እንደሚመላለስ  የክራሚያ ተመክ ፍንጭ ይችላል:: በተለይም ደግሞ ክሬሚያ አዲስ ትውልድ አሁንም ከአማሪጮች ሁሉ ወደ ራሸያ ማዘንበሉን እንደመረጠ ስንመለከት አበረታች ሁኔታ ቢፈጠር በሻቢያ ስር በምትገኘው ኤርትራ ውስጥ ሊከሰት የሚችለውን ዕውነታ መገመት አይከብድም::



ክራሚያን ሁኔታና ዕውነታ ስንመለከት፤ የህወሀት መሪወች ሲሰብኩት የቆየውና አሁን ደግሞ ባንዳንድ  ተቃዋሚወች ውስጥም እየሰረጸ ያለው ኤርትራ ጉዳይ ያለቀለት ጉዳይ ነውየሚለው  አመለካከት የህዝብን ሰነልቦናዊ ጥንካሬ ወደሚቦረቡር እና ብሄራዊ ጥቅምንም ወደሚጎዳ ተግባር እንዳያነጉደን ያሰጋል። የሀገር ጥቅም የሚጠበቀው ጽናት እና ጥራት ባለው ላይ በተመሰረተ ትግል እንጂ  ጊዚያዊ ጥቅምን ለማሳደድ ሳያላምጡ በመዋጥ ወይም ደግሞ መሰረታዊ የሀገር ጥቅምንእሱን አሁን እርሱት በሚል  ራእይ የለሽ አካሄድ ከቶውንም ሊሆን አይችልም::



ሩሲያ ስለ ክራሚያ ምን ያስጨንቃታል?

ሩሲያ በኢኮኖሚም ሆን በወታደራዊ ሃይል በዓለም አቀፍ ደረጃ ተፈላጊነትና ተደማጭነት ያላት ታላቅ ሀገር እንደመሆኑዋ በቆዳ ስፋቱዋም ቢሆን አሁንም ባንደኘነት ደረጃ ላይ ትገኛለችል። ባንጻሩ ደግሞ ክራምያ በህዝብ ቁጥርም ሆነ በኢኮኖሚ ለሩስያ እዚህ ግባ የማይባል አስተዋጽ ነው የሚኖራት። በኢኮኖሚ አንጻር ብቻ ካየነው በዋናነት ተጠቃሚዋ ከራሚያ እንጂ ሩሲያ አትሆንም፡፡ ሆኖም ግን የዘር ሓረግና ታሪክ የሚገዛው ገንዘብ ብቻ አደለምና  ክራሚያ በሩስያ  (ሩስያም በክሬምያ) በታሪክም ሆነ በህዝቡ ሥነ-ልቦና ላይ እጅግ ቁልፍ ቦታ አላቸው፡፡ይህ ሁኔታ ምን ያህል መሰረት ያለው እንደሆነ መገንዘብ የሚቀጥሉትን ታሪካዊ ሁኔታዎች እንመልከት፡



·       በጊዜው በመዳከም ላይ የነበረው የኦቶማን ኢምፓየር እና ራሸያ  በኦክቶበር 1853 ውጊያ ውስጥ የገቡት በክሬምያ ጉዳይ ነበር፡፡ ውጊያው የተቀሰቀሰው ሩሲያ በክራሚያ የነበሩ የኦርቶዶክስ ክርስትና ተከታዮችን ከጥቃት ለማዳን በወሰደችው እርምጃ ነው

·       ይህን ተከትሎ 1853–1856 ባንድ በኩል በራሸያ በሌላ በኩል ደግሞ  በፈረንሳይና እንግሊዝ ጥምር ጦር መሀል የተካሄደው ጦርነት በክሬምያ ውስጥ ነበር፡፡

·       የቦልሽቪኮችን ወደ ስልጣን መምጣት ተከትሎ ነጩ ሰራዊት ( the white army) እየተባለ የሚጠራውና ሶሻሊዝምን በሚቃወሙ የምዕራብ ሃይሎች ይደገፍ የነበረው የተቃዋሚዎች ሀይል 1920 የመጨረሻው ወሳኙ ውጊያ ያካሄዱትም በዚሁ በክሬሚያ ነበር።

·       በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ከፍተኛ ደም የፈሰሰበት ጦርነት ከተካሄደባቸው ቦታዎች ውስጥ ክራሚያ አንዷና  በዋናነት የምትጠቀስ ነች።

·       የጀርመን ናዚዎች ክራሚያን ለመያዝ ባደረጉት ወረራ 170 ሽህ በላይ የሶቭየት ጦር የተሰዋ ሲሆን በወቅቱ ፋሽስቶችን እስከመጨረሻ የመከተችው ኣና የጀግኖች ከተማ በመባል ልዩ ሽልማት የተሰጣት የክራሚያ ዋና መናገሻ የሆነችው ሴቫስቶፖል ነበረች። በወቅቱ ምዕራብ ዩክሬን የፋሽስቱ ሂትለር ተባባሪ በመሆን በሽዎች የሚቆጠሩትን ጸረ-ፋሽስት ሃይሎች እንደገደሉና እንዲሰደዱ እንዳደረጉ ታሪክ መዝግቦታል።

·       በሁለተኛው ያለም ጦርነት ማጠቃለያ በሦስቱ ተባባሪ ሐያላን ሀገሮች (Allied Forces) መሪዎች ያሜሪካው ፍራንክሊን ሩዝቬልት፣ የሩሲያው ጆሴፍ ስታሊን እና የኢንግሊዙ ዊንስተን ቸርችል መካከል የተደረገው ስብሰባ የተካሄደው በያልታ ክራሚያ ውስጥ ነበር።



ይህ ሁሉ በራሽያውያንና ክራሚያ መካከ ያለውን ከፍተኛ የታሪክና  የሰነልቦና ትሰሰር  አንዱ ሌላውን ለምን እንደሚፈልግ ያሳያል::



ይህ ብቻ ሳይሆን ክራሚያ ለሩሲያ የምታስገ  ጂኦ-ፖለቲካዊና ስትራቴጂካዊ ጠቀሜታም እጅግ ትልቅ ነው። ክራሚያ ቀደም ሲል የሶቭየት ህብረት በሁዋላም የሩሲያ ፌዴሬሽን ባህር ሀይል የሆነው ብላክ ፍሊት የጦር ሠፈር ነች። በዩክሬን ውስጥ የራሽያ ፍቅር የሌለው መንግስት ሥልጣን ቢይዝ የሩሲያን ደህንነት ዛሬም ባይሆን ነገና ከነገ ወዲያ አደጋ ላይ ሊጥለው እንደሚችል ራሸያ ጠንቅቃ ታውቃለች። ይህ አደጋም አፍንጫዋ ስር ሲከሰት እጅ አጣጥፎና ምንም እንዳልተፈጠረ በማስመሰል ማለፍን የራሸያ መሪወችም አልፈለጉም። ስለዚህም ቀልጠፍና ፈርጠም  ያለ እርምጃ መውስድን አስፈላጊ ሆኖ አግኝተውታል። የራሽያው ፕሬዚደንት ፑትን በቅርቡ ለሀገሪቱ ፓርላማ ባደረጉት ንግግር ክራሚያ ለሩሲያ ምን ያህል ስትራተጂያዊ አስፈላጊነት እንዳላት ሲገልጹወደ ሜዴትራንያንና ወደ ጥቁር ባህር መሽጋገሪያችን የሆነችው ሶቫስቶፖል በባዕዳን ቁጥጥር ስር ሆና ማየት ከቶውንመ ተቀባይነት የለውምነበር ያሉት።



ከላይ ስንደረደርበት የቆየሁት አመለካከት ወዳገራችን ሁኔታ ሲመለስ፤ ኢትዮጵያሰ ስለ ኤርትራ ምን ያስጨንቃታል የሚለውን ጥያቄ ማጫሩ አይቀሬ ነው። ከዚህ አኳያ እያንዳንዱ ሰው የየራሱን ምርምር አድርጎ መደምደሚያ ላይ እንዲደርስ ያስፈልጋል ብዬ አስባለሁ። ሆኖም ግን ኢትዮጵያ በታሪክ፣ በኢኮኖሚ፣ በሀገር ደህንነት ወዘተ አንጻር እጅግ ብዙ ጉዳት እንደደረሰባት  እና ወደፊትም መገመት የሚከብድ አደጋ እንደተጋረጠባት ብዙወች በመረጃ አስደግፈው ጽፈውበታል። በኢኮኖ አንፃር ብቻ ሲታይ እንኴ የራሷን ወደብ እንድታጣ የሆነችው ኢትዮጵያ ለጂቡቲ መንግስት ለወደብ ኪራይ የምትክፍለው ገንዘብ በየቀኑ በሚሊዮ የሚጠር እንደሆነ ይታወ:: ይሀ ገንዘብ ለሀገር ልማት ቢውል ኖሮ የምን ያክል ናትን ህይወት ማዳን እንደሚቻል ምን ያህል ተጨማሪ ትምርት ቤት ጤና ጣቢያ ማቌቌም እና ህይወት ማዳን እንደሚቻል ስናስብ የሁኔታውን አንገብጋቢነት ለመገንዘብ ይረዳል::



አሁን ካለው አሀዝ ስንነሳ ኢትዮጵያ የራሷን ወደብ አጥታ ለጅቢቲ የምትከፍለው ወጪ  በያመቱ ለአንዳንዱ ወረዳ በሚሊዮኞች የሚቆጠር ተጨማሪ በጀት ለመመደብ የሚያሰችል ነው። ይህ ታዲያ ድህነትን ለመቀነስ፣ ለልማት ወዘተ ምን ያህል አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ማንናውም ጤነኛ አእምሮ የሚገነዘበው ነው።



በዚህ አንጻር ያለ ግንዛቤ ለማግኘት ለሚፈልግ ሁሉ የዶ/ ያዕቆብ ሐይለማርያምአሰብ የማን ናት የአምባሳደር ዘውዴ ረታንየኤርትራ ጉዳይ ባዲስ አባባ ዩኒቨርሲቲ የታተመውንየአክሊሉ ማስታወሻጥሩ ግንዛቤና መረጃ ሊሰጡ የሚችሉ መጻህፍት መሆናቸውን መጥቀስ እወዳለሁ።



የሶቭየት ህብረት መፈራረስ ክራሚያና ኤርትራ

የሲቭየት ህብረት መፈራረስን ተከትሎ በነበረው ያልተረጋጋ ወቅት ክራሚያም በግርግር ከዩክሬ ጋር ተደባልቃ ከራሸያ ተገንጥላ እንድትሄድ አድርገዋል የሚባሉት እንኳንስ ለሀገር ለራሳቸውም ማሰብ ይሳናቸው ነበር እየተባለ የሚነገርላቸው ፕሬዚደንት ቦሪስ ዬልሰን ናቸው:: ግለ የዚሀ አይነት ውሳኔ ሲወስኑ የክሬሚያን ታሪክ፣ ስትራተ ጠቀሜታ ወዘተ ከቁብ አላስገቡትም፣ የህዝቡንም ስሜት ቦታ አልሰጡትም ነበር። የሳቸው ሩጫ ከምን እንደመነጨ በግልጽ በማይታወቅ መልኩ ጎርባቾቭ የቀደዱት የለውጥ መንገድ በመለጠጥ ሶቭየት ህብረትን በማፈራረስ ላይ ያተኮረ ነበር፡፡ ክራሚያን በተመለከተም የሶቭየት ህብረት ታላቅ የባህር ሀይል የሆነው ብላክ ፍሊት ንብረት ሽያጭና ገንዘብ መሰብሰብ ላይ ነበር ትኩረታቸው። ያም ሆኖ  በንግድ አንጻር እንኳ እዚህ ግባ የሚባል ገንዘብ አላገኙበትም።



የክራምያን ጉዳይ መደምደሚያ ለመስጠት የተሞከረው በሶቭይት ሕብረት ባጠቃላይ እንዲሁም በራሽያና በተቀሩት  ሶሻሊስት ሀገሮች ታይቶ የማይታወቅ ቀውስ እና አለመረጋጋት በሰፈነበት ወቅት ነበር። በዚያ የቀውስ ወቅት በቂ የሆነ አማራጭና ረጋ ብሎ ለማሰብ ጊዜ ይኖር ሬፈረንደም ተካሄደና 58% የሚሆን ህዝብ ደገፈው በማለት ክራሚያ ከሩሲያ ተለይታ የዩክሬን ግዛት ሆና እንድትሄድ ተወሰነ።



ይህ ጉዳይ ግን በብዙ ዜጎች ልብ ውስጥ ቁርሾ አስከተለ፤ ጠባሳም ጣለ። የጊዜው ሁኔታ ባይመችና በወቅቱ ማድረግ ስለሚገባቸው ነገር ግራ ቢጋቡም፤ እጅግ ብዙ የክራሚያ ኑዋሪዎች ልባቸው መሸፈቱ አልቀረም፡፡ በዘሩም በታሪኩም ራሽያዊ ነኝ ብሎ የሚያምነው የክሬምያ ሀዝብ የለም ዩክሬናዊ ነህ ሲባል ጥርሱን ነከሰ። ሆኖም ግን በወቅቱ የሚዳምጠው አላገኝም። ታምቆ የቆየ  ቅሬታ  አሁን በቅርቡ አመጽ ወልዶ እነሆ የሆነ ያለውንና የሆነውን ዓለም እየመሠከረ ነው።



የኤርትራ ከኢትዮጵያ የመገንጠል ዕውነታ ከሶቭየት ህብረት መፈራረስ እና ከቀዝቃዛው ጦርነትመገባደድጋር በቅርብ የተቆራኘ ነበር፡ህዝበ ውሳኔ” (ሬፈራንደም ) የተባለው ሂደትም በሀሪቱ በከፍተኛ ቀውስ ውስጥ በነበረችበት፣ ገና ቋሚ መንግስት እንኳን ሳይኖራት ነበር። ህዝበ ውሳኔሂደት ውስጥም የኢዮጵያዊነት አማራጭ በታፈነበት ኢትዮጵያዊ ነኝ ብሎ የሚያምነውና የሆነውን የአፋርና ኩናማ፣ የሳሆ፤ .. ህዝብንም ፍላጎት ለማክበር ምንም ጥረት ሳይደረግና ውጤቱም ሳይታይ በግድ ያልሆነውንና ያላመነበትን ማንነት  ተቀበል ተብሎ የተጠናቀቀ የግርግር ሁኔታ ነው። ይህ ስለሆነም እነሆ እስካሁን የቀጠለው ቅሬታ የመሳሪያ ግጭትን ወልዶ ካንድ ቀውስ ወደሌላ በመሽጋገር ላይ ይገኛል።



የሚገርመው ከስልሳ አመት በሓላ ሩሲያ በክሩስቼቭ ጊዜ የተጀመረውን ያስተዳደር ክልል ማሸጋሸግ እና በቦረስ ዬልሲን ዘመን የተወሰደውን የረጅም ጊዜ ዕይታ የጎደለውን የፖለቲካ ርምጃ ለማረም የተዘጋጀ ድርጅትና መሪ አግኝታለች። ኢትዮጵያችን ግን በሁሉም መልኩ ሀላፊነት የጎደለውን የመለስ ዜናዊ ለሀገር ደንታ ቢስ የሆነ ውሳኔ ለማረም እና ለኢትዮጵያ ሀገራዊ ጥቅም በድፍረት የቆመ የመንግስት መሪ ገና አልታደለችም። ያም በመሆኑ መከራውም ቀጥ መፍትሄውም እየተወሳሰበ መሄዱ አይቀሬ ሆኗል።



የተባበሩት መንግሥታትየዩክሬንን ሀገራዊ አንድነት ስለማሰከበርያካሄደው የድምጽ አሰጣጥ

የክሬሚያ ነዋሪወች በዩክሬን ስር መተዳደርን አንፈልግም ብለው ማጉረምረም ሲጀምሩ ነው ታላላቆቹ የምእራብ መንግስታት ሁኔታውን ለማዳፈን መሯሯጥ የጀመሩት። የክሬምያን ህዝብ ታሪክ፣ ፍላጎትና ማንነት ጠንቅቀው የሚያውቁት ምዕራባውያን ጭንቀታቸው ያነጣጠረው በክሬምያ ላይ ሳይሆን ሩሲያ እንደገና ተጠናክራ በመውጣት ጉዳይ ላይ ስለሆነ ይህንን ለማከሽፍ፣ ባለፈው የካቲት መጨረሻ ገደማ ዩክሬን ውስጥ በዴሞክራሲያዊ መንገድ የተመረጠው መንግስት ባመጽ ሲፈነቀል ቃል ያልተነፈሱት ምዕራባውያን፤ በክራሚያ የተደረገውን ሬፈረንደም ተከትሎ ዩክሬን ተወረረ፣ ወዘተ፤ የሚለውን ከበሮ መደለቅ ጀመሩ። ከሁካታው በስተጀርባ ግን አሁን ባለው ሁኔታ ምዕራባውያኑም ሆኑ ራሱ የዩክሬይን መንግስት የክራሚያ ጉዳይ ያለቀለት እንደሆነ የተቀበሉት ይመስላል። ሩጫው ሊፈጠር የሚችለውን ሌላም ምስቅልቅል ሁኔታ ለመቀነስ ምናልባትም ራሱ የዩክሬን እንደሀገር የመቀጠል ጉዳይ አደጋ ላይ እንዳይወድቅ የመጨነቅ፣ ሰፋ ያለ የርስ በርስ ጦርነት ባውሮፓ ውስጥ እንዳይቀሰቀስ የመፍራት ጉዳይ እንጂ ክራሚያን የማስመለስ ፍላጎት አይመስልም።



የተባበሩት መንግሥታት የጸጥታ ጥበቃው ምከር ቤት (ድምጽን በድምጽ ሽሮ ጥርስ-አልባ የሆነው) እና ጠቅላላ ጉባኤውም በዚህ ጉዳይ ያስተላለፈውና ከፍተኛ ክፍፍል የነበረበት ውሳኔይህን ብለን ነበርከማለት የማያልፍ ነው። ጠንከር ያለ የማዕቀብ እርምጃ ወሰዱ የተባሉት አሜሪካና የአውሮፓ ማህበረሰብም ቢሆኑ ርምጃቸው ጥቂት ባለስልጣኖችን የሚነካ ከመሆን አላለፈም።



ቀረብ ብሎ ሲታይ ደግሞ ያፍሪካ መንግስታት በተለይም የኢትዮጵያ እና የኤርትራ መንግስታት የወሰዱት አቋም ትኩረትን የሚስብ ነው፡፡ የሁለቱም ወኪሎች  በተባበሩት መንግስታት ውሳኔ አሰጣጥ ላይ የክሬምያን ከዩክሬን መገንጠል ሳያወግዙም ሳይደግፉም ድምጽ ቅቦ (አብስቴን) በማድረግ ማለፉቸውን እንገነዘባላን።



ይህ የድምጽ አሰጣጥ ከብዙሀኑ ያፍሪካ ሀገሮች የተለየ አይደለም፤ ተባበሩት መንግሰታ ምክር ቤትየዩክሬንን ሀገራዊ አንድነት ማሰከበርበሚል ርእስ የክራሚያን መገንጠል ለመቃወም የቀረበውን ረቂቅ የውሳኔ ሀሳብ የደገፉ ያፍሪካ ሀገሮች 19 ብቻ ሲሆኑ የተቃውሞ ድምጽ ያሰሙ ሁለት (ሱዳንና ዚምባብዌ ) ድምጸ ተአቅቦ ያደረጉ ደግሞ ወደ 22 ያፍሪካ ሀገሮች ነበሩ። ከነዚህም ውስጥ ኢትዮጰያና ኤርትራ ይገኙበታል። ይህ ሶሰ ቦታ የተከፈ የድምጵ አሰ  የሚያሳየው የተባበሩት መንግሥታትም ሆነ ያፍሪካ አንድነት ማህበር በተመሳሳይ ሁኔታዎች ላይ የሚወስዷቸው አቋሞች ከሀገራቸው ፖለቲካ፣ እና ከሚያስገኝላቸው ጥቅም አንጻር እንጂ ከቋሚ መተክልና ዕምነት በመነሳት እንዳልሆነ ነው፡፡



ከዚህ ሁኔታ መገንዘብ እንደሚቻለው ለተመሳሳይ ሁኔታወች እያንዳንዱ ሀገር ስለሚወስደው እርምጃ ወሳኙ ጉዳይየተባበሩት መንግስታት ወይም ያፍሪካ አንድነት ህግሳይሆን እያንዳ ሀገር የሚያገኘው ጥቅማ ጥቅም እንደሆነ ነው። ባጭሩ የሀይል አሰላለፉን  የሚገዛው መተክል (ፐሪንስፕል) ሳይሆን በጊዜው ሀገራት የሚያገ ጥቅም እና የሀይል ሚዛን ይመስላል።



ጠቃለያ

ከዩክሬይን ክራሚያና የሩስያ ጉዳይ የሚገኘውን ትምህርት በከፊል እንደሚከተለው ላጠቃል፡



1. ሀገራዊ ራዕይና አርቆ አሳቢነት ከፖለቲካ መሪዎች (ገዠዎችም ተቃዋሚም ) የሚጠበቅ ተግባር ነው፣



2. ለአጭር ጊዜ ፖለቲካዊ ጥቅም ሲባል የሚወሰዱ ርምጃወች ጦሳቸው እጅግ የተወሳሰበ ይሆናል። ክሬሚያና ዩክሬንን በተመለከተ ፕሬዚደንት ያልሰን የወሰዱት ይህን ያመለክታል፡



3. የህዝብ ታሪክ እንደፈለጉ የሚጽፉት፤ የሚፍቁት ወይም የሚቀያይሩት ኣደለም፡፡ ክራሚያውያን ባገኙት የመጀመሪያ አጋጣሚ ወደ ራሽያ ልመለስ ማለታቸው የሚያሳየውም ይህንኑ ነው፡፡ የክራሚያ ዓይነቱ ጥያቄ በክራሚያ ብቻ አልተወሰነም። አሁን በምሥራቅና ደቡብ ምሥራቅ ዩከሬን 10 ያህል ከተሞች ውስጥ እየተካሄደ ያለውም አመጽና ጥያቄ  ባብዛኛው የክራሚያ ነዋሪዎችን ያቄ የሚያሰተጋባ ነው።



4. የሀገር መሪዎች ሀገራዊ እና ስትራተጂያዊ ጠቀሜታን ማረጋገጥ ከሁሉም በላይ ግዴታቸው ሊሆን ይገባል። ይህን ሲያደርጉ ደግሞ ዋናው መሠረት የህዝባቸው ፍላጉት፣ ታሪክና እውነታ እንጂ የባዕዳንን ጥቅምና ትዕዛዝ ከማስጠበቅ አኳያ ሊሆን አይገባውም።



5. የሀገሩን ታሪካዊና ስትራተጂያዊ ጥቅም ለማስጠበቅ የሚቆም መሪ ደግሞ የህዝብን ድጋፍ የሚያገኝ ለመሆኑ የክሬምያ ሁኔታና የፑቲን ተወዳጅነት ያረጋግጣል። ካውሮፓ፤ ካናዳና አሜሪካ የሚሰማው ተቃውሞ ቢቀጥልም የፕሬዚደንት ፑቲን የህዝብ ድጋፉ እየጨመረ በመሄድ ላይ ይገኛል፡ተጻርረው የቆሙ ደግሞ የተወገዙ ከመሆን እና  “የታሪክ ጠባሳተሸክመው ከመጓዝ ሊድኑ አይቸሉም። በቅርብ የተካሄደ አንድ ጥናት እንደሚያሳዪው 85%  የራሽያ ህዝብ ፕሬዚደንት ፑቲንን ይደግፋል  http://www.levada.ru/06-08-2014/avgustovskie-reitingi-odobreniya:: በነገራችን ላይ ጥናቱን ያካሄደው ለፑቲን ፍቅር እንደሌለው የሚታወቀው ሊቪዳ የተሰኝው የጥናት ተቌም ነው



6. ባለራዕይ መሪዎች የተለያዩ ታሪካዊ ሁኔታዎች የሚፈጥሩላቸውን አጋጣሚዎች በመጠቀም የትናንት ስህተቶችን ለማረም ቆራጥ እና ፈጣን ርምጃ መውሰድ ይኖርባቸዋል። ይህም ከፖለቲካ ቀኖናና ከአይዲዮሎጂ እሥረኛነት መላቀቅን እና ድፍረትን ይጠይቃል።



7.ድርጅ ርት በተመለከተ ያልተዘጋውን አጀንዳ  በጥልቀት በመረዳት የህዝብን ወኔ ከሚሰልብ በሽንፈትና በጨለምተኛነት ከተተበተበ አመለካከትና አካሄድ ራሳቸውን ሊያ ይገባል እላለሁ:: ወላጆቻችን አያቶቻችንና ቀደምት ትውልዶች  ጠላት የጫነባቸውን ሁሉ ያለቀለት ነውብለው በመንበርከክ ሳይሆን ሀገራዊ ጥቅምን በተመለከተ በጠራ ራእይ ላይ ተመርኩዘው በጽናት በመቆማቸው ነው ያችን ሀገር ለኛ ያወረሱን። እኛስ?



አስተያየት ቢኖርወት በሚከተለው ኢሜል አድራሻ ሊልኩልኝ ይችላሉ  ethioandenet@bell.net