Monday, September 26, 2016

በትግራይ ምድር ላይ ጠጅ ሲንቆር ሐዘን እምባ ሆኗል በአማራ ምድር! ጌታቸው ረዳ (ኢትዮጵያን ሰማይ ድረገጽ አዘጋጅ Ethiopian Semay)


በትግራይ ምድር ላይ ጠጅ ሲንቆረቆር
ሐዘን እምባ ሆኗል በአማራ ምድር!

ጌታቸው ረዳ (ኢትዮጵያን ሰማይ ድረገጽ አዘጋጅ Ethiopian Semay)
Ethiopian Semay- The ugly face of Ethnocentric
በፋሺሰቱ ዘረኛ ‘የወየነ ትግራይ’ ድርጅት የተመራው የትግራይ ብሔረተኛነት፤ ለኢትዮጵያ ሕዝብ “የሳዮናይድ” መርዝ ሆኖበት ለሃዘን፤ለብጥብጥና ለዘር ፍጀት ዳርጎታል።  በመጀመሪያ ሰላም ለሁላችሁ እንደምን አላችሁ? ወደ ርዕሱ ከመግባቴ በፊት እንደተለመደው አንድ ሁለት አስተያየቶችን ለመሰንዘር እሻለሁ።


በቅድሚያ ለ25 አመት የተደበቀው በአማራ ሕዝብ የደረሰው ሰቆቃና የዘር ጽዳት ጥቃት ገሃድ እንዲሆን በተጨባጭ ማስረጃ አስደግፎ ገሃድ ያደረገው “የጥፋት ዘመን  ከ1983 እስከ 2007 ዓ.ም በዐማራ  ሕዝብ ላይ የተፈጸመ  ዘር ማፅዳት” መጽሐፍ ደራሲ የዘመኑ ምርጥ ጋዜጠኛ (ዲቴክቲቭ ጆርናሊስት) ሆኖ በኢትዮጵያን ሰማይ አዘጋጅ የተመረጠ ወጣት ጋዜጠኛ ሙሉቀን ተስፋ የኢትዮጵያ ታሪክ በክብር ዙፋን እንዲመዘግበው ለኢትዮጵያ ሕዝብ በተለይም የአማራ ሕዝብ ቀን ወጥቶለት ብርሃን ሲወጣለት ሙሉቀንን የክብር/የኖብል/ሽልማት እንዲሸልመው አሳስባለሁ። ከዚህ ተያይዞ ደራሲው እንደገለጸው በክቡር አቶ ተክሌ የሻው የሚመራው “ሞረሽ ወገኔ” ድርጅት ኢትዮጵያ ውስጥ ‘ባስቸጋሪ ሁኔታ’ ጥናቱ ሲካሄድ አስፈላጊው የገንዘብ ወጪ እና ምክር በማድረግ በስተጀርባ ሆኖ ጥናቱ እንዲከናወን ቀዳሚው ሚና የነበረው “የሞረሽ ወገኔ” ድርጅት እና ሊቀመንበሩ ምስጋና እና ሽልማት ይገባቸዋል። በመጽሐፉ ዙርያ የተዘገቡት አሰቃቃ የዘር ፍጅት ወንጀሎች ለወደፊቱ እምለስበታለሁ።

ቀጥሎ ለማለት የምፈልገው ሌላ ጉዳይ፤ ሰሞኑ ዋሺንግተን ውስጥ የተካሄደው የኢትዮጵያዊያን ሰላማዊ ሰልፍ ለመጀመሪያ ጊዜ በአዘጋጆቹ እና በሰልፈኞቹ እጅግ እንደኮራሁ እና እንደተደሰትኩ ለመግለጽ እወዳለሁ። ለምን ለመጀመሪያ ጊዜ? የሚል ጥያቄ ሊቀርብ ይችላል። ሰልፈኛው ያሸበረቀበትና ያስተጋባው መፈክር “ካሁን በፊት ስተችበት የነበረው ዝብርቅርቅ ያለ የጠላቶቻችን ባንዴራዎች፤ የኦነግ (የግብፅ/ዐረቦች ባንዴራ የያዘ ቀለም)፤ የሻዕቢያና የኦብነግ ባንዴራዎች ከኢትዮጵያ ሰንደቅዓለማ ጋር እያዳቀሉ  ኢትዮጵያዊነት እና የኢትዮጵያ ሰንደቅዓላማን ክብር የሚያንኳስስ ለበርካታ አመታት ሰላማዊ ሰልፍ ይደረግ እንደነበር ባለፈው ሰሞን ክፍል ሁለት (ሳብቨርዥን/ብከላ) በሚል የጻፍኩትን ትችቶቼና ፎቶግራፎችን በማሳየት ‘አምርሬ በተደጋጋሜ ለበርካታ አመታት መቃወሜን ታስታውሳላችሁ።” ዛሬ የኔን ትችት እና ምሬት ሰምተው ለመጀመሪያ ጊዜ የጠላቶች ባንደራዎችን በማስወገድ “ኢትዮጵያዊነት እና የኢትዮጵያ ሰንደቅዓላማን ክብር ብቻ ከፍ አድርጎ ያንጸባረቀ ሰላማዊ ሰልፍ በመደረጉ እጅግ ደስ ብሎኛል።” ለመጀመሪያ ጊዜ የጠላት ባንዴራ እንዳይቀላቀል አግዳችሁ የሚያኮራ አሸብራቂ ኢትዮጵያዊነትን ስላንጸባረቃችሁና ምሬቴን ስላዳመጣችሁኝ አዘጋጆች አጅግ አመሰግናለሁ።

ሌላው በድረገጾች የተዘረጋው መነበብ ያለበት ጽሑፍ ልጠቁማችሁ። ካሁን በፊት ስማቸው ሰምተናቸው የማናውቅ አዲስ መጤ ጸሐፊዎች ተወሽቀውበት ከነበረው የምቾት ማማቸው ወጥተው በረካታ ጽሑፎችን ለዓይናችን ንባብ እያበረከቱ ነው። ጠቀሚ ትችቶም ናቸው። ሆኖም አጠንክሬ አንባቢዎቼ እንድታነቡት የምመከራችሁ በጣም አስፈላጊና የወደፊቷ ኢትዮጵያ መከተል ያለባት አስተዳደርና የመፍትሄ ሃሰባች ከሰነዘሩት ጠቃሚ (እኔ የወደድኩት) ጽሑፍ ‘ገለታው ዘለቀ’ የተባሉ ጸሓፊ የኢትዮጵያ የፌደራል ሥርዓት ችግሮችና አማራጭ መፍትሄዎች- እንደመግቢያ - ገለታው ዘለቀ”  የጻፉትን ጽሑፍ ብታነብቡ ብዙ ቁም ነገሮችን ታገኙበታላችሁ ስለሆነም እንድታነብቡት እጠቁማለሁ።

እንዲሁም፦ ወያኔ የመኢአድን አባላት እና አመራሮች ሲያፍን ኢሳት ደግሞ መኢአድ ላይ የሚደርሰዉን የግፍ በደል ያፍናል። በመላዉ አለም እንዲሁም በኢትዮጵያ ያለዉ ሕዝብ ስለ መኢአድ ተጋድሎ መረጃ እንዳያገኝ ሆን ብሎ የምንልክለትን መረጃ ሁሉ ወደ ቅርጫት ይወረውረዋል።” በማለት አምርሮታቸው በሻዕቢያ አሞጋሹ ‘ኢሳት’ ቲ/ቪ እና ራዲዮ ወቀሳቸውን የሰነዘሩት የመኢአድ የህዝብ ግንኙነት /ሀላፊ አቶ ለገሰ /ሃና በምሬት ኢሳትን አምርረው  የወቀሱበትን ሰነድ ለማንበብ “ኢሳት ቴሌቪዥን ጣቢያ ከመላዉ ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) አመራሮች ከፍተኛ ወቀሳ ደረሰበት” የሚለውን ዜና  ለማንበብ  
ወልቃይት.ካም welkait.com ድረገጽ በመግባት http://welkait.com/?p=6227 በመጠቆም ያንብቡ።

አሁን ወደ ርዕሳችን ንግባ።
ሄንሪክ ሄደን የተባሉ ሊቅ እንዲህ ይላሉ፦ “እንደሰው የሚያስብ አህያ እንኳን አይቼ ባላውቅም፤ እንደ አህያ የሚያስቡ ሰዎች ግን አጋጥመውኛል” ይላሉ። ይህ አባባል የዘመናችን አስገራሚ ሰዎችን የሚያመላክት ነው። ባሕላችን፤ይሉኝታችን በ25 አማታት እንዴት አንደተበከለ ባለፈው ከፍል ሁለት (ክፍል ) ኢትዮጵያዊያኖች ‘በዘረኛነት ባሕር እየዋኙ ነው’! ይህ እንዴት ሊከሰት ቻለ? ጌታቸው ረዳ የኢትዮጵያን ሰማይ ድረገጽ አዘጋጅ  Ethiopian Semay)  በሚል የተቸሁበት ትንታኔ ስታጤኑት፤ ዜጎቻችን ይሉኝታን ጥለው ከሰብአዊ አስተሳሰብ ውጭ በሆነ መንገድ ወገኖቻቸው በፋሺስቶቹ አረመኔአዊ የወያኔ ጥይት ሲቆሉ፤እናቶች በልጆቻቸው ሬሳ ላይ ተጋድመው በወረባላ አረመኔ የወያኔ ‘ጎስታፖ’ ፖሊሶች በዱላ ሲደበደቡ ደንታ የማይሰማቸው ወገኖች እያየን ነው።ይህ ደግሞ  ኢትዮጵያ ውስጥ የታየ ነው። 
The Tigre Fascism & the suffering of the Amhara  Ethiopians- Ethiopian Semay
የአማራ መሕበረሰብ ለ25 አመታት እጅግ አሳዛኝ በሆነ የዘር ማጽዳት ሲከናወንበት ቆይቶ በመጨረሻ በቅርቡ፤ ‘በቃኝ ብሎ’ በአጥቂዎቹ ላይ ሲያምጽ የትግራይ ወያኔ ‘ጎስታፖ’ ነብሰገዳዮች፤ “የአማራን ወጣቶች፤ታዳጊ ህጻናት እና አዛውንቶች” በጥይት እየቆሉ የተቀሩትም ማታ ማታ ወደ እየመንደሩ እየሄዱ በጭለማ እያፈኑ ብዙ  አማራዎችን እያጠፉ ባለበት ወቅት፤ ትግራይ ውስጥ ለቅዱስ ዮሐንስ እና ለመስቀል በዓል አከባብር ጠጅ እየተንቆረቆረ፤ ሽግ በርቶ፤ ከበሮ እየተነተረ ፤ቀጤማ ተጎዝጉዞ፤ ነጭ ልብስ ተለብሶ እስክስታ ወርዶ፤የትግራይ አደባባዮች በዕልልታ ሲቀልጡ ማየት አጅግ አሳዘኝ ክስተት መሆኑን እኔ እንደ ትግሬነቴ እጅግ አሳፍሮኛል፤ አሳስቦኛል። ይህ መወገዝ ያለበት እጅግ አስገራሚ ክስተት የትግራይ ማሕበረሰብ ለወደፊቱ ከተቀሩት ወገኖቻችን ያለንን ቁርኝት ወዴት እያመራ እንዳለ በጥሞና እንዲያጤኑት አሳስባለሁ። ብሔረተኛ ይህን ተሎ የሚገነዘብ አይመስለኝም። ታረክ ነፃ እንዲያጣን ግን እያሳሰብን ነው።

ዜጎች በጥይት እየተቆሉ፤ ከየቤታቸው እየታደኑ መግቢያ መውጫ አጥተው ባሉበት ወቅት ‘አረመኔ’ የወያኔ መሪዎች ካድሬዎቻቸው፤የዜና አውታሮቻቸው እና አዝማሪዎቻቸው ሌሊቱ ሙሉ እስከንጋቱ የሚቆይ የጭፈራ፤የደስታ እና የጥጋብ ማስታወቂያ እየዘረጉ ይጨፍራሉ፤ አማሮች ሌሊት ሙሉ እስከንጋቱ የሃዘን እምባ ያቀርራሉ። ይህ አሳዛኝ ክስተት ለመግለጽ የሚያዳግት ክስተት በታሪካችን ይከሰታል ብሎ የገመተ ይኖር ይሆን?
Partying and dying the outcome of  TPLF Fascism in Ethiopia
የሰሞኑነን የሰማነው እና የነበብነው አናቋሪ የወያኔ ሴራ እልከት።
የትግራይ ወላጆቻችን፤ወንድሞቻችን እና ዘመዶቻችንን ሳት እና በዘይት እየጠበሰ፤ ሰውን በማሰቃያት ሲባልግ የነበረ ደም የጠማው በጎስታፖ ቅኝት የተገነባ ድረጅት መሆኑን በተደጋጋሚ በብዙ ማስረጃዎች ተነጋግረንበታል። ወያኔ “ክርስትያን/ አማራ/ነፍጠኛ/ ትምክሕተኛ..” በማለት የመደበው የአማራ ማሕበረሰብ ወያኔ ወደ አዲስ አበባ ሲገባ ወደ ሥልጣን ጎበጣው/ሄጂመኒ ለማድረግ በሽግግሩ ወቅት ያደረገው አክራሪ ‘ሶማሌና ዓፋርን” በፓርላማው ውስጥ አሰባስቦ ወደ እየካባቢቸውም ባለሥልጣኖችና ካድሬዎቻቸውን በመላክ በአማራ ሕዝብ ላይ ጭፍጨፋ እንዲካሄድ ያደረገው ቅስቀሳ፤ ‘በማሕደረ በቪዲዮና አውድዮ’ የተቀረጹ ዘገባዎች አሉ። አማራው ለሶማሌው፤ ለዓፋሩ፤ ለኤርትራው ሰቆቃ፤ግድያና መከራ ተጣያቂ አድርጎ በውሸት የፕሮፓጋንዳ ዘመቻ በማካሄድ “አማራ ወክለዋል፡ ብሎ እራሱ ያደራጃቸው “ባንዳ ግለሰቦችን” በማሰማራት ወደ ኤርትራና ወደ ሶማሌ እንዲሁም ዓፋር እና በመሳሰሉ ቦታዎች በመላክ “በዐማራ ማሕበረሰብ ስም” ይቅርታ እንዲጠይቅ ማድረጉ የሁላችንም የቅርብ ትዝታ እና በቪዲዮ ተቀርጾ ለታሪክ የተመዘገበ የወያኔዎች “ቆሻሸ’ ባሕሪ ሁላችሁም ታስታውሱታላችሁ። 

ዛሬም አማራው ሲገደል፤ እነዚህን ማሕበረሰብ ወክለናል የሚሉ ሰዎችን አሰባስቦ ያንኑ የለመደበትን ሕዝብን ከሕዝብ የማለያየት  ‘ሰይጣነዊ ሥራው’ አገርሽቶበታል (ሶማሌዎች እና ዐፋሮች ለትግራይ ተፈናቃዮች ይህ ለገሱ……እያለ የዋሃን ሶማሌዎች እና  ፋሮችን በለመደው የሕዝብ ማናቆር ፋሺስታዊ ተንኮሉ ለጎሰኛ ፕሮፓጋንዳው ሰለባዎች እያደረጋቸው ነው)። ችግሮችን ለመፍታት የወያኔ የጫካ እውቀቱና አቅሙ ያ ብቻ ነው። የተካነበትና የሚያውቀውም ያው ሕብረተሰብን ‘ማናከስ/ማቀያየም/ማፋጀት’ ነው። ፋሺስቱ የወያኔ ድርጅት በአማራ ማሕበረሰብ ላይ የትግራይ ማሕበረሰብ ሲያደራጅ በዓለም የታዩ ፋሺስቶች ያደረጉት፤ወያኔም ያንን ባሕሪ አድርጎታል። ወያነ ትግራይ በአማራ ማሕበረስብ ላይ ፋሺስታዊና የጅምላ ፍጅት ሲያካሂድ፤ “ወያኔ ማለት ትግራይ ሕዝብ ማለት ነው” በሚል መርሕ ተደግፎ ወያኔ ትግራይ በአማራ ላይ ያንጸባረቀው ባሕሪ ዶ/ር አሰፋ እንዲህ ይገልጸዋል።

“በዓለም ላይ የተካሄዱ የጅምላ ፍጅቶች ሁሉ የሚያመሳስሏቸው ነገሮች አሉ። ከእነዚህም አንዱ የጅምላ ፍጅት የሚያካሂዱት ወገኖች የፍጅት ሰለባ የሆነውን ነጥለው ከለዩ በላ በማንንቱ ላይ የሥነ ሉቦና ዘመቻ ማድረጋቸው ነው። የሥነ ሉቦናው ዘመቻ ግብ አንድን ለጅምላ ፍጅት ሰለባነት የታጨን ሕዝብ ማንነት በሰይጣንንት ምስል መሳልና ጥላሸት መቀባት ነው። የሥነ ሉቦና ዘመቻ የጥቃት ሰለባ የተዳረገው ሕዝብ ራሱን እንደ በደለኛ አድርጎ በመቁጠር ጥቃቱን ንዲቀበል ሲያደርግ፤አጥቂው ወግን እና ራቅ ብለው ይህንኑ ጥቃት የሚያዩትን ወገኖች ፍጅቱን እንደ ተራ ነገር እንዲመለከቱት እና ለተጠቂው ማሕበረሰብ አንዳችም ዓይነት የርህራሄ አመለካካት እንዳይኖራቸው ያደርጋል።…..” (ስርዝ የተጨመረ- የኔ) ይላል ደ/ር አሰፋ  የጥፋት ዘመን ከ1983 እስከ 2007 ዓ.ም በዐማራ ሕዝብ ላይ የተፈጸመ ዘር ማጽዳት” በሚል በወጣት ሙሉቀን ተስፋው የተጻፈ ወያኔዎችና ኦሮሞ ነፃ አውጪዎች ንዲሁም የመሳሰሉት “በአማራ ማሕበረሰብ ላይ” የተፈጸመው ፍጅት በጻፈው መጽሐፍ የቀረበ የመጽሐፉ ጀርባ።

ሶማሌዎች ትግራይ ወደ ትግራይ በመጓዝ በሚሊዮን የሚገመት ብር ለትግራይ ተፈናቃዮች ለግሰዋል የሚለው ዜና ፤ ስታደምጡ እጅግ የሚያስገርም የወያኔ ፋሺስታዊ ተንኮል ምን ያህል ተራምዶ ሶማሌዎች በአማራ ማሕበረሰብ ‘ፍጅትና ሐዘን’ ምንም ደንታ እንደሌላቸው “አማራው” በሶማሌው እና በዓፋሩ ቂም እንዲይዝ ለማናከስ የለኮሰው “ተንኮል” መሆኑን በቃላሉ የሚታወቅ ቢሆንም፤ ሶማሌው ከአማራው ማሕበረሰብ ፍጅት ይልቅ የትግሬዎች መፈናቀል እንደቆረቆረቆረው ለማሳየት ያልጣረው ፕሮፓጋንዳ የለም።

ሆኖም ይህ ሶማሌዎች ናቸው የሚባሉት ሰዎች የሶማል ወያኔ ያደራጃቸው ካድሬ ስብስቦች እና ባለስልጣን ሶማሌዎች ያሰባሰቡዋቸው ናቸው። እነዚህ ደግሞ እማን እንደሆኑ በቪዲዮ የተቀረጸው በድጋሚ ለማሕደራችሁ ይህንን አድምጡ፤Somali region president hate statements about Amhara https://youtu.be/6lpronBiUZ4 እዚህ ላይ ግልጽ የሚሆነው ነገር፡ ሶማሌዎች ትግሬዎችን እንደ ወዳጅ “አማራ ማሕበረሰብ” ግን የሶማሌ ጠላት ነው ሲል የሶማሌ ክልል መሪው ሲናገር ታደምጣላችሁ። ስለሆነም ሶማሌዎች ወደ ትግሬ ተጉዘው ለትግሬ ተፈናቃዮች ሚሊዮን ብር ለገሱ፡ ሲለን ወያኔ፤ ሶማሌዎች የአማራውን ፍጅት እንደተደሰቱ እየነገረን ነው። ሶማሌዎችም ያረጋገጡልን ይህንኑ መሪያቸው የነገራቸውን ነው። ታሪክ እራሱን ባስከፊው ገጽታው ሲደግም ዛሬም እያየን ነው!

ዛሬ እየታየ ያለው ትግራይ ውስጥ፡ጭፈራ እና ቀረርቶ ዕልልታ፤ አብሮነትን የሚያደፈርስ ፤እየከፋ በመምጣት ላይ ያለው እየሻከረ ያለው የትግሬና የአማራ ማሕበረሰብ ግንኙነት የትግራይ ማሕበረሰብ በብረቱ አጢነው የወያኔ እና ካድሬዎቻቸው የሚደሰኩሩላቸው የደንቆሮዎች ፋሺስታዊ እና የሚያፋልስ የፕሮፓጋንዳ ዘመቻ “ሳይቀበሉ” ወያኔ በአማራ ላይ እያካሄደው እና የፈጸመው የሚገኘው ፍጅት/እልቂት/ዘር ማጽዳት ወንጀል ‘አቁም’ ብላችሁ ትብብራችሁ ለአማራ ሕዝብ ካላሳያችሁ፤ የወደፊት አብሮነት እንደማይጥም እና ኢትዮጵያም እንደ ኢትዮጵያ እንደማትቀጥል ማወቅ ይኖርባችሗል።

 የወያኔ ፖሊሲ ጎሳዎችን የመለያ መታወቂያ አድሎ እንደ ሩዋንዳ ለማፋጀት ያቀደ፤ የውጭ ትልዕኮ እና የማደፍረስ፤የማበጣበጥ፤የፍጅት ወንጀል ይዞ የመጣ መልዕክታኛ መሆኑን ለ25 አመት በክርስትያኑ በአማራው፤ በሉዓላዊ መሬታችን እና ባሕራችን እንዲሁም ሰንደቃላማችን የፈጸመው ወንጀል እና ክሕደት አውቃችሁ አደፍራሽ እና ፋሺስታዊ ዘመቻው ባስቾኳይ እንዲቆም ጥሪ አንድታቀርቡለት ጥሪየን አቀርባለሁ። እኛ እየነገርን ነው! ወያኔን የምንቃወም እኛ ጥቂት የትግራይ ተወላጆች ነገ ታሪክ ነፃ ያወጣናል። ታሪክ እናንተም ከኛ ጋር ነፃ እንዲያወጣችሁ አስቸጋሪውን የሕሊና ተራራ መውጣት ይጠበቅባችል። ወጣትነት፤ውበት፤ገንዘብ፤ሃብት፤ፍቅር፤ ሥልጣን ፤ፎቅ፤እስክስታ፤ዳንኪራ ጊዜአዊ ናቸው፡ የታሪክ ጉልበት ነው እና ታሪክን ማገድ ስለማይቻል፤ ባንድ ወቅት ባንድ የታሪክ መድረክ፤ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ በታሪክና በጊዜ ቅይይር “በተራቸው” ይሰወራሉ። እኛ ሰዎች ነን፤ እንደ አህያ ሳይሆን እንደ ሰው ማሰብ ይጠበቅብናል። እንደ ሰው ካሰብን፤ አማራዎች ሐዘን ላይ ሲቀመጡ እኛ የምንጨፍርበትን ሕሊና መቆጠጣርን ይጠበቅብናል።

አመሰግናለሁ፡

ጌታቸው ረዳ(ኢትዮጵያን ሰማይ ድረገጽ አዘጋጅ Ethiopian Semay)getachre@aol.co