Wednesday, December 21, 2022

መሳይ መኮንን የኢሳት የብለጽግናው ካድሬ የዘር ማጥፋት ጥሪው ጌታቸው ረዳ Ethiopian Semay 12/21/22

 

መሳይ መኮንን የኢሳት የብለጽግናው ካድሬ የዘር ማጥፋት ጥሪው

ጌታቸው ረዳ

Ethiopian Semay 12/21/22

ሰሞኑን እንደሰማነው ከሆነ፤ በወያኔ እና በአብይ አሕመድ  መሪነት በጦርነቱ ውስጥ የተፈጸሙ የዘር ጭፍጨፋና የጦር ወንጀል ለማጣራት ከውጭ አለም የቀረበ ጥያቄ ለሁለተኛ ጊዜ “ቦጅባጃው” አብይ አሕመድ ላላመተባበር የተለያዩ ምክንያቶች እየፈጠረ እንደሆነ ሰምተናል። ከመጠየቅ ያመልጣል ወይ? የምናየው ይሆናል።

 ኢትዮጵያን በቅኝ ግዛት ቀንበር እየገዛት ያለው የኦሮሙማው ኦሮሞዎች ሥርዓት ከወያኔ በከፋ መልኩ በ4 አመት ውስጥ ታይቶ ተሰምቶ የማይታወቅ የዘር ጭፍጨፋ፤የሃይማኖት ግጭቶች፤ ዓለም ያስደነገጠ ጦርነት፤ የፍትሕ መጓደል እና አብይ አሕመድ በአደረጃጀትና በገንዘብ ረድቸዋለህ እያለ የነገረን “ኦነግ” የተባለ ድርጅት በወንዶች ላይ ግበረሰዶምን መፈጸም እና አማራዎችን አርዶ ሥጋቸውን የሚበላ ወደ እንሰሳነት የተለወጠ አረመኔ “የኦሮሞዎች ቡድን” ያየንበት ወቅት ነው።

ይህ ሁሉ እያለ የወያኔው የትግሬዎች ፋሺሰት ቡድን በትግራይ ውስጥ ባስነሳው ጦርነት ሰበብ መነሻ በውል ያልታወቀ ከፍተኛ የሰው እና የንብረት ውድመት ደርሷል። በዚህ ጦርነት ተዋናይ የነበሩት መሪዎች ወያኔዎች እና የአብይ አሕመድ “ኦሮሙማ ብልጽግና” ቡድኖች በሁሉም ወገን የተፈጸመ የዘር ጭፍጨፋና የጦር ወንጀል ተጠያቂዎች ናቸው።

በነዚህ ተወናይ ቡድኖች ውስጥ ደግሞ በጋዜጠኛነት ስም ተሰማርተው በንጹሃን ትግሬ ቤተሰቦቻችን ላይ የዘር ጭፍጨፋ አንዲካሄድ ቅስቀሳ ሲያካሂዱ የነበሩ አማካሪዎች ብዙ ናቸው። ከነዚህ አማካሪዎች ውስጥ አንዱ “የኢሳት ቲቪ” ከዚያም ፤ “ኢ ኤም ኤስ”  ሲሰራ ቆይቶ ለመቸውም ጊዜ ከጋዜጠኛነቴ ለቅቄ  አለሁ ብሎ ሲዋሽ ቆይቶ ፤ለቀቅኩ ካለን ወራት ሳይሞሉት ዛሬ  ደግሞ  “አንከር ቲቪ” በሚል የግል ሚዲያ ከፍቶ ብቅ ያለው መሳይ መኮንን አንዱ በትግሬዎች ላይ የዘር ጭፍጨፋ እንዲካሄድ የአብይ አሕመድ መንግሥት በፌስቡኩ ሲማጸን የነበረ ነው። ማስረጃውም ተያይዞ የቀረበው ፎቶ ኮፒ ይመልከቱ።

መሳይ መኮንን ያስተላላፈው ጸረ ንጹሃን ትግሬዎች አዋጅና ቅስቀሳ በራሴ ቤተሰቦች ላይ ደርሶ በመሳይ መኮንን ቅስቀሳ ምክንያት ታስረው ተሰቃይተው፤ከሥራቸው ተፈናቅለው እስከዛሬ ድረስ ችግር ውስጥ ናቸው። ቤት ያከራይዋቸው ጸረ ትግሬ የሆኑ አማራ ባለቤት አከራዮችም የነ መሳይ መከንን ቅስቀሳ ተጠቅመው “ባሕርዳር ውስጥ” ክራይ እንዲጨምሩባቸው አድርገዋል/በሌሎች አካባቢዎችም ከተከራዩባቸው መኖሪያ ቤቶቻቸው እንዲወጡ ተደርገዋል።

ከመልዕክቱ ውስጥ አንዱን ላስነብባችሁ፤

መሳይ መኮንን እንዲህ ይላል

<< ጥብቅ መልዕክት ለመንግስት

አሁንም አልፈረደም። የትግራይ ተወላጆችን አሁንም “ከህወሓት ጋር ግንኙነት የሌላቸውም ቢሆን” በጊዜያዊ ማቆያ ጣቢያዎች እንዲሰባሰቡ ማድረግ ያስፈልጋል። አሜሪካ በሁለተኛ የዓለም ጦርነት ወቅት ወደ ጦርነቱ ከምባቷ በፊት በሀገሯ የሚኖሩ የጃፓን ዜጎች በሙሉ ወደ ካምፕ አስገብታ በው የጃፓን ወራሪንና የሂትለርን ጦር ማሸነፍ የቻለችው። ጃፓኖች በብብትዋ ውስጥ ወሽቃ ወደ ጦርነት መግባት የሽንፈት መጀመሪያ መሆኑን ተረድታ እርምጃውን ወስዳለች። ኢትዮጵያም ከዚያ ደጋ የከፋ ውስጥ ናት።የደሴው ግብግብ ዋናው ተዋናይ ከሕዝቡ ጋር አብረው የሚኖሩት የህወሓት ደጋፊዎች መሆናቸው በስፋት ታምኗል። እነሱን በጉያ ይዞ ጦርነት ማሸነፍ በፍጹም የማይቻል አይደለም።ለእነሱም ደህንነት ተብሎ እርምጃው በአስቸኳይ ሊወሰድ ይገባል። >> ሲል የዘር ጭፍጨፋው በንጹሃን ትግሬዎችም ላይ እንዲካሄድ ይፋ አዋጅ በፌስቡኩ መልዕክቱን አስተላልፎ ነበር።

     በመሳይ መኮንን ቅስቀሳ ምክንያት የፋሺሰቱ የአብይ አሕመድ መንግሥት መልዕክቱን ተግባራዊ በማድረግ በርካታ በሺዎች የሚቆጠሩ ነጹሃን ትግሬዎች በመላው ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ትግሬዎች ከመኖርያ እና ከሥራ ገበታቸው እየተለቀሙ ወደ “ማጎርያ ካምፖች” እየታፈኑ እርጉዞች፤ደም የሚያንጠባጥቡ ትኩስ እመጫቶች፤ህጻናት፤በሽተኞች እና ሽማግሌዎች እየተደበደቡና እየተገፈተሩ ወደ ማጎርያ ጣቢያዎች እየተወሰዱ ታስረው ለስቃይ እንደተዳረጉ ይታወቃል።

አንዳንዶቹም ፍትህ ተነፍገው አስካሁን ድረስ አሉ። የራሴ በተሰቦችም ባሕርዳር ውስጥ ያለምንምን ወንጀላቸው ከምንም ከምንም ፖለቲካ የማይገኝባቸው “ትግሬ” በመሆናቸው ብቻ ታስረው ማጎርያ ጣቢያና ከዚያም “ሰባታሚት” በሚባል ጉደኛ ማጎርያ ለብዙ ወራት እስር ቤት ታስረው ከፍተኛ ገንዘብ አንድያስይዙ በዋስ ወጥተው “የእጅ ስleከቸው(ንብረታቸው) እና ገንዘባቸው ሁለት አመት እነሆ ዛሬም ተይዞ ሳይመለስላቸው” የፖሊስና የዳኞች ቢራ መጠጪያ ሆኖ እስካሁን ድረስ አልተመለሰላቸውም። ፍትሕ የለም! ለማን አቤት ይባላል! አቤት ቢሉ አንደገና ለምን ጠየቅከን ተብለው ሊያስሯቸው ነው። በዚኢሀ አጋጣሚ ባሕረዳር ውስጥ የሕግ ሰው ነኝ በፍትሕ አምናለሁ የሚል ዳኛ ካለ እኔን የማነጋገር ከፈለገ ይኸው በፌስቡኬ መልዕክት ለመነጋጋር ክፍት ነው። አብይ አህመድ ሁሉም ዳኛ “ዘራፊ/የነቀዘ/ ነው” ብሎ ስለሰደባቸው፤ ያኔ ሰሞን የባሕር ዳር ዳኞች ተሰባስበው የቅሬታ ደብዳቤ አንደጻፉለትና እንደተንጫጩ በአበበ በለው መረጃ ቲቪ ሲንጫቹ ነበር የሰማሁት ፡ ያኔ ጠይቄ ነበር። ዛሬም “የያዛችሁትን “የዋስ ገንዘብና ስልክ”  ለወንድሜ እንድትመልሱለት እጠይቃቸዋለሁ። እኔን ለማነጋጋር እና ይህንን ለማድረግ ጥቁር ጋውን የለበሰ ዳኛ ነኝ የሚል የበቃ ዳኛ ይገኛል ወይ? የሚለው ጥያቄ መልስ የሚሻ ትልቁ ጥያቄ ነው።

ከላይ እንዳነበባችሁት መሳይ መኮንን ባወጀው የዘር ቅስቀሳ ቤተሰቦቼ ተሰቃይተዋል። አሁን የምጠይቀው ፤ በአማራዎች ላይ የዘር ጭፍጨፋ ያወጀው ወያኔው “አሉላ ሰለሞን” በሕግ አንዲጠየቅ የሕግ ባለሞያዎች (ደደቦቹ የሕግ ባለሞያዎች) ክስ እንዲሰመሰርቱና ለፍትሕ እንዲቀርብ ደጋግሜ እንደጠየቅኩ ሁሉ ዛሬ ደግሞ በንፁሃን ትግሬዎች ወገኖቻችን ላይ የዘር ጭፍጨፋ ሳይሰለቸው ለብዙ አማታት ደጋግሞ ሲቀሰቅስ የነበረው ጋዜጠኛ መሳይ መኮንን የሕግ ባለሞያዎች ነን የሚሉ “ትግሬዎችም አማራዎችም ከየትኛውም ነገድ” ያላችሁ ባለሞያዎች በተበደሉት ዘመዶቻችን ስም መሳይ መኮንን ወደ ፍትሕ እንድታቀርቡልን እጠይቃለሁ። በተለይ ጠረጴዛ እየደበደበ የሚውለው የሕግ ባለሞያ ነኝ የሚለን ቴድሮስ ጸጋየ (ርዕዮት ሚዲያ) እና መሰል የትግራይ የሕግ ባለሞያዎች ይህንን እንዴት ቸል እንዳሉት አብዝቶ ይገርመኛል። መልስ ካላችሁ እስክ ልስማችሁ?

ይህ እገሌ ከእገሌ ሳይባል ሁሉም ኢትዮጵያዊ የሕግ ባለሞያን የሚመለከት ነው። እዚህ ከናንተው ጋር የሚኖሩትን ወንጀለኞችን በሕግ ሳትጠይቁ አዲስ አባባ የሚኖሩትን ወንጀለኞች በሕግ አንጠይቃለን የምትሉት ቅዠት አይገባኝም።

አንባቢዎችም  መልዕክቴን ሕሊናችሁ በኢትዮጵያዊነት ብቻ እንድትበይኑት እንጂ በጎሳ ድልድላችሁ እንዳታዩት እጠይቃለሁ።

አመሰግናለሁ

ጌታቸው ረዳ  Ethiopian Semay