Wednesday, October 3, 2018

ግንቦት 7 እና የኦነግ ግንኙነት በአማራ ላይ ሲያሴሩት የነበረው ሴራ እንደገና ላስታውሳችሁ! ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay)


ግንቦት 7 እና የኦነግ ግንኙነት በአማራ ላይ ሲያሴሩት የነበረው ሴራ እንደገና ላስታውሳችሁ!

ጌታቸው ረዳ (ኢትዮጵያን ሰማይ)

የኢትዮጵያ ሃገራዊ ንቅናቄ (ENM) ተብሎ የሚጠራው ድርጅትና ያጸደቀው ሰነድ።


ከቀኝ ወደ ግራ ሙሉነህ እዮኤል (ግንቦት 7-“ኦሮሚያን ለማፍረስ መሞከር ኢትዮጵያን ለማፍረስ ብቻ ሲፈለግ የሚሞከር ክፉ ሴራ ነው።” ብሎ ጽፋል ተብሎ በወልቃይት.ካም ድረገጽ ላይ የተተቸበት ሰው) ሌንጮ ለታ (ኦነግ) ቀጥሎ ያለው (አልታወቀም የሲዳማ ሕዝብ ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ ..) ቀጥሎ ዶ/ር ኮንቴ (ዓፋር) ወደ መጨረሻ የተቀመጠው (አልታወቀም፤ አማራ እወክላለሁ ብሎ በራሱ የወከለ ግለሰብ) 2016 ዓ.ም ከታተመ)

ለአንባቢዎቼ ማሳሰቢያ

ባለፈው ሰሞን ስለ ኦሮሞዎች እና ትግሬ ልሂቃን በወጣቶች ሕሊና ውስጥ ያስሰራጩት የበሰበሰ ፖለቲካቸው ሦስት ትውልድ ድረስ እንደማይሽር ክፍል አንድ አስነብቤአችለሁ። ክፍል ሁለት በዝግጅት ላይ ነው። የምንወያይባቸው ርዕሶችም የግብረሰዶም ሰንደቃላማ ምልክቶች የታዩበት የ2011 የመስቀል ደመራ በዓል አስከፊው ገጽታ እና ኦሮሞዎች እሬቻ እና ገዳ የተባሉ ሃይማኖታዊ እና አስተዳደራዊ ባሕል ኦሮሚያ ለሚለው ፖለቲካ መጠቀሚያ እና የትግሬ ወያኔዎች አሸንዳ የሚባለው ሓይማኖታዊ ጨዋታ ወደ ፖለቲካ የመጠምዘዝ አባዜአቸው እንዲሁም “የአብይ ሻዕቢያ” ካድሬዎች በተዋህዶ ቤተክርስትያን እና በየሕዝባዊ መድረኩ ለሻዕቢያ ባንዴራ እያሳዩት ያለው ቅዠታዊ ፍቅራቸው ሃገራዊ ክህደትን እንዴት ሕጋዊ እየሆነ እንደሆነ ሲፈተሽ”  በሚል ርዕስ በሚቀጥለው ሰሞን እንመለከታልን።

በመደመር አባዜ ስም በኢሳያስ አፈወርቅ ትዕዛዝ ከኤርትራ የተባረሩት ተቃዋሚ የኢትዮጵያ ድርጅቶች አዲስ አበባ መግባታቸው ይታወቃል። ክስተቱ ለነሱ ያስደነበራቸው ቢሆንም ፤ ላንዳንዶቹ ግን ለሽንፈታቸው “አጋጣሚ ሽፋን” ስላገኙ ያልጠበቁት ከሰማይ የወረደ መና እንደሆነላቸው የታወቀ ነው (ግንቦት 7 እና ኦነግ)። አስገራሚው ግን ሲገቡም አሸናፊዎች ነን በሚል ሲመጻደቁ እና ንቃት ከጎደለው በአፍዝዝ ወ አደንዝዝ ፖለቲካ የተወናጀረው “አብዛኛው” የከተሜው ስልብ (ሃይጃክድ) ወጣት የማይገባ መስተንግዶ ሲቆለልላቸው አይተናል። የሆኖ ሆኖ ከኤርትራ “በክብር ተባርረው” በቅርቡ ከገቡት ውስጥ እና አገር ውስጥ እና አውጭ አገር ከነበሩ 5 የኦሮሞ የድርጅቶች ባወጡት መግለጫ ውስጥ “ኢሳት” በተባለው በግንቦት 7 አቀንቃኝ ካድሬ ጋዜጠኞች የታጀበ ቴ/ቪዥን ጣቢያ እና ግንቦት 7 በማለት ራሱ የሰየመ ድርጅት መሪዎች ላይ እና በኢትዮጵያ ሕልውና ላይ ያነጣጠረ የጥላቻ መግለጫ ማውጣታቸው ላልገመተ የዋህ አድማጭ በክውታ አስገርሞታል ።

አሁን ጉድ ፈላ!

ለየዋህ ዜጋ ብቻ ሳይሆን ያስገረመ ኢሳት የተባለው ቴ/ቪዥን ለኢሳያስ አፈወርቅ፤ ለግንቦት 7 እና ለኦነግ እያቀነቀነ ሲያሰለቸን የነበረው የግንቦት 7 ቀኝ እጅ የቴ/ቪዥን ጣቢያ 5 የኦሮሞ ድርጅቶች ሳይታሰብ በድንገት ፖለቲካዊ ትፋታቸው ሲተፉበት መታዘብ ለእኛም ጭምር ቅንድባችንን አስቁሟል (የተጠበቀ ቢሆንም)። በኢሳት ብቻ ሳይሆን ጣቢያው በሚያሽቃብጥበት ድርጅት በግንቦት 7 ደርጅት ላይም ተመሳሳይ ፖለቲካዊ ትፋት ተፍተውበታል።

 5 የኦሮሞ ድርጅቶች ከሚባሉት ለብዙዎቹ ኢሳትም ሆነ ግንቦት 7 ከሚገባቸው በላይ ሲያሽቃብጡላቸው እና ሲቆልሉዋቸው የነበሩ ናቸው። ዛሬ ውዝግብ ገብተው ለሰማ ጀሮ ግራ እንዳያጋባው ግንቦት 7 እና ኢሳት የተባሉት ምን  ይነት አስነዋሪ ስራ ሲሰሩ እንደነበሩ ማስታወስ አስፈላጊ ነው። የግንቦት 7 ቱ መሪ የብርሃኑ ነጋ ቀኝ እጅ ጋዜጠኛ የሆነው የኢሳቴ ፋሲል የኔ አለም የተባለው የዚህ ጣቢያ ጋዜጠኛ ነኝ ባይ ካሁን በፊት የሞረሽ ወገኔ አማራ ተወካይ አቶ ተክሌ የሻው ዶ/ር ላጲሶ በተባለ የታሪክ ምሁር ላይ ያላቸው የመልስ ምት ለማቅረብ ጣቢያው ጠይቀው በስንት መከራ ዕድሉን ካገኙ በላ “ይህ ሰው” ለላጲሶ የሰጠው ክብር መስጠቱስ ይቅር እንግዳውን እንዴት ያንቋሽሻቸው እንደነበረ የሚታወስ ነው። በዚህ የተነሳ ሲያደናቅፋቸው እና ሲያሳንሳቸው እንደነበረ የታዘበቺው ባለቤቱ እጅግ በመቆጣትዋ ከስራ መልስ ቤት ሲገባ “ተቋውሞዋን” ማሰማትዋን እሱ እራሱም በዜና መስጫ ጣቢያዎች የዘረጋው ጽሑፍ ማንበብ ጠቃሚ ነው። (በቅጣት መለክ ተቆጥታ ምሳ ወይንም እራት ነፍጋው እንደሆነም ብዙ ሰዎች ሲያሾፈበት የተነበበ ጽሑፍ አንብቤአለሁ!)።

አማራ ነገድ ነው የሚባለው ፋሲል የኔ አለም የተባለው አስገራሚ ጸረ አማራ ጋዜጠኛ ያ አልበቃ ብሎት አባ ኒቀዲሞስ አስፋው የተባሉ መነኩሴ እንግዳ ሆነው በፕሮግራሙ ሲቀርቡ፤ ኦነግ በአማራ ማሕበረሰብ ላይ የፈጸመው የዘር ማጥፋት ጭፍጨፋ የነበሩበት የዓይን ምስክርንት ለማብራራት ሲሞክሩ አፋቸው እያስዘጋ ወደ “ኦፒዲኦ/ወያኔ” ወንጀል ብቻ እንዲያተኩሩ እያስገደዳቸው እና ሲያስቆማቸው እንደነበረ ታሪክ ዘግቦታል። የመናገር መብት ስለነፈጋቸው በኦነግ የተፈጸመው ወንጅል ሕዝብ እንዳያውቀው በማድረጉ፤ ብዙ ሰዎች በዚህ ስለተበሳጩ “በሌሎች ነፃ ሚዲያዎች” ቀርበው ሰፊ ትንተና እንዲሰጡ ስለተጠየቀ እሳቸው በሌላ ሚዲያ ቀርበው ያለ ምንም አፋና ምስክርነታቸውን ሰጥዋል።እስከዚህ ድረስ ጸረ ሕዝባችን የተካተቱበት “ካድሬ ጋዜጠኞች” ኢሳት ውስጥ እና በግንቦት 7 ውስጥም ተመሳሳይ ኦነጋዊ የፖለቲካ ብከላ በሕዝባችን ላይ ሲያካሂዱ እንደነበረ ያልነቃችሁ ወጣቶች ይህንን ታሪካቸው እንድታውቁት ከወዲሁ ስገልጽ፡ ሰሞኑን ኦነግ እና ኢሳት/ግንቦት7/ እንካ ስላንትያ ገጥመው እኛ ስንለው የነበረው እና የጠበቅነው ጉደኛ ገመናቸው በሕዝብ ፊት እንደሚጠዛጠዙ የተነበይነው ሃቅ እነሆ እውን ሆኗል።

በተመሳሳይ ቪዥን ኢትዮጵያ የተባለ እና የነገድ ፖለቲካ ለማካሄድ የተቀናጁት “የኢትጵጵያ አገራዊ ንቅናቂ” የተባሉት ድርጅቶች አገራዊ ሉአላዊነት በሚመለከት ከኦሮሞ ተገንጣዮች እና በሻዕቢያ ቁጥጥር ያለቺው ኤርትራን በባርነት የያዘ ድርጅት ጋር የነበራቸው ዕይታ ምን ያህል እንደነበር ከነበረው ሆሆታ እና ጭብጨባ እንድታስታውሱት በዚህ አጋጣሚ እፈልጋለሁ።

ይህ ጽሑፍ በፈረንጆች ዘመን በ2016 (የዘሬ 2 አመት በፊት) የጻፍኩት ትችት ነው። ታሪክ የዘገበው ለመፋቅ ቢሞከርም አይቻልም እና በኔ ዘገባ የተዘገበው የታሪክ ማሕደር ምን እንደተዘገበ እንመልከት። ወደ ርዕሳችን ከመግባታችን በፊት የግንቦት 7 የጎሳ ዘራቸው በዘሓበሻ ድረገጽ ከተለጠፈው ምንጭ ያገኘሁት እንዲህ ይነበባል።

1ኛ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ————ጉራጌ G7 Executive

2ኛ ዶ/ር ታደሰ ብሩ————-,ጉራጌ G7 Executive

3ኛ አቶ ኤፍሬም ማዴቦ——–ከምባታ G7 Executive

4ኛ አቶ ንአምን ዘለቀ ———-ኤርትራና ኦሮሞ G7 Executive

5ኛ አቶ አበበ ቦጋለ————–ኦሮሞ G7 Executive

6ኛ አቶ ቸኮል ጌታሁን———–ጉራጌ G7 Higher leader Ship

7 ኛ አቶ አንድነት ሐይሉ ——–ጉራጌ G7 Council

8ኛ አቶ ሙሉነህ እዮኤል———ከንባታ G7 Council

9ኛ አቶ አበረ አዳሙ————-ኦሮሞ/ጎጃም/ G7 Council

 10ኛ አቶአንዳርጋቸውጽጌ- ፀሃፊ  = ኦሮሞ

በማለት የጎሳ ገመዳቸውን ተቺዎች በእንዲህ ይገልጿቸዋል። የሞረሽ ወገኔ ተወካይ አማራ ድርጅት እንዳይገባ መከልከሉን አስመልክተው ኦነግ እና በግንቦት 7 የሚመራው ንቅናቄ የሚከተለው ጭብጥ በውስጡ የተዘረዘሩት የስምምነት የንቅናቄው ሰነድ ምን እንደሚል እንዲህ ይዘረዝሩታል።

* የንቅናቄው ሰንድ ወያኔ እንደሚለው የኢትዮጵያን ህዝብ “ሕዝቦች” እያለ የሚጠራ ነው።


* ይህ በነዚህ በአራት ድርጅቶች የጸደቀው ሰነድ ካሁን በኋላ ሰነዱን ማንም ማሻሻም አይችልም የሚል ማሰሪያ አንቀጽ አለው።

* አዲስ ወደ ንቅናቄው የሚገቡ ድርጅቶች በአራቱ ድርጅቶች የጸደቀውን ይህንን ሰነድ እንዳለ ተቀብለው መግባት እንጂ ሰነዱ እንዲሻሻልና እንዲስተካከል የመጠየቅም ሆነ የማሻሻል ጥያቄ መብታቸው የተከለከለ ነው።


* ግንቦት 7 (G7) ና የኦሮሞ ዲሞክራሲያዊ ግንባር (ODF) ማንኛውም የአማራ ድርጅት ተወካይ ወይም በአዛጋጆች ተጋብዞ የነበረው ሞረሽ ወገኔ የአማራ ድርጅት በዚህ የንቅናቄ ስብስብ ውስጥ ሊገባ አይገባውም የሚል እገዳ ጥለዋል።


* በንቅናቄ የተገኙት የአፋር እና የሲዳማ ድርጅቶች የአማራ ህዝብ ተወካይ የሌለበት የድርጅቶች ስብስብ የትም አይደርስምና የአማራ ህዝብ ተወካይ በንቅናቄው ስብስብ እንዲካተት ከፍተኛ ድምጽ ያሰሙ ቢሆንም ግንቦት 7 እና ኦዲፍ (ODF) ግን የአማራ ተወካይ በንቅናቄው ውስጥ መገኘት የለበትም በማለት እገዳ ጥለዋል።


በዚህ አጋጣሚ የአፋርና የሲዳማ ህዝብ ድርጅቶች ሓላፊዎች ምንም እንኳ በጉልበተኞቹ በግንቦት 7 እና ኦዲፍ (ODF) መሪዎች ተጽእኖ ምክንያት የአማራ ህዝብ ተወካይ በስብስቡ እንዳይገኝ ቢደረግም እናንተ ግን እውነተኛ የነጻነት ታጋዮች በመሆናችሁ የአማራ ህዝብ ተወካይ የሌለበት ስብስብ ዋጋ የለውም ብላችሁ ያነሳችሁት ጥያቄ ለነጻነቱ እየታገለ ላለው የአማራ ህዝብ ያላችሁ ቅን ልብና ወገናዊትነት የሚያረጋግጥ በመሆኑ የአማራ ህዝብ ለእናንተ ያለው አክብሮት ከፍ ያለ መሆኑን እየገለጽን በዚህ አጋጣሚ ላሳያችሁት አጋርነት እናመሰግናችኋለን።” በማለት ሞረሽ አጸፋውን መልሷል።

አቶ ተክሌ የሻው ሞረሽ ወገኔ የአማራ ድርጅትና ሊቀመንበር እና የአማራ ህዝብ ጠባቃ “የኢትዮጵያ” ሃገራዊ ንቅናቄ (ENM) ተብሎ የሚጠራው ድርጅትና ያጸደቀው ሰነድን በሚመለከት የሰጡትን አስተያየት ከዚህ በታች ያድምጡ።ከታች የምታደምጡት አውዲዮ የድርጅቱ አገናኝ የሆነው የቭዢን ኢትዮጵያ አባል ሻለቃ ዳዊት ወ/ጊዮርጊስ አቶ ተክሌ ስልክ ደውለውለት ንቅናቄ የሚባሉት በግንቦት 7 እና ኦነግ የሚመራው ንቅናቄ አማራን በሚመለከት ለሻለቃ ዳዊት ወ/ጊዮርጊስ ምን መልስ እንደሰጡት ማስረጃውን አደምጡ። እነሆ ከዚህ በታች።

ስለ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ንቅናቄን - Ethiopian National Movement የአቶ ተክሌ የሻው አስተያየት


ለመሆኑ ስንቶቻችሁ ናችሁ “ኢሕአዴግ” ብሎ ወያኔ የሰራውን ቀዩ የፋሺሰቶች ባንዴራ አዋሳ (ሃዋሳ) የወያኔዎች ስብሰባ ላይ ብርሃኑ ነጋ ተገኝቶ ያንኑ ባንዴራ አስጨብጠውት ደረቱ ላይ ሽጦ ታቅፎት  ያያችሁ? ጉዳም በይዛ! አለች አንዲት ሳታስበው እየሳቀች የተደፈረች ትግሬ! (ምን እሚሉት የማያፍር ጉደኛ ሰው ነው ይኼ እባለካችሁ! ብላ ክስተቱን በቸልታ ያየቺው አጋጣሚ ማለት ነው)። “ሁ ኢዝ ኔክስት?/who is next?” የባለ 500 ዶላር አርበኛነት የምስክር ወረቀት የያዝክ ባለ ተራ ግባ! ማነህ?  

አመሰግናለሁ። ጌታቸው ረዳ የኢትዮጵያን ሰማይ ድረገጽ አዘጋጅ (Ethiopian Semay)