Saturday, April 20, 2019

ሻለቃ ዳዊት የደረሰበት ድምዳሜ የሚታይ የሚጨበጥ እውነታ ነው! መልስ ለባይሳ ዋቅ ወያ ጌታቸው ረዳ (የኢትዮ ሰማይ ድረገጽ አዘጋጅ)



ሻለቃ ዳዊት የደረሰበት ድምዳሜ የሚታይ የሚጨበጥ እውነታ ነው! መልስ ለባይሳ ዋቅ ወያ
ጌታቸው ረዳ (የኢትዮ ሰማይ ድረገጽ አዘጋጅ)

ለበርካታ አመታት በሻለቃ ዳዊት ወልደግዮርጊስ የነበረኝ አቋም በተለያዩ ምክንያቶች ተጻራሪ እንደነበር ትችቶቼን ስትከታተሉ የነበራችሁ ወገኖች የምታስታውሱት ነው። ሻለቃው ዛሬ እጅግ በጣም የሚያስመሰግን አቅጣጫ ይዘው ብምርምር የደረሱበት ስለ የአብይ አሕመድ “ጥገናዊ መንግሥት” አመራር ኢትዮጵያን ወደ አስፈሪ ውቅያኖስ እየቀሰፈች በሃይለኛ ሞገድ እየተንገላታች እንደሆነ ያስቀመጡት ምሁራዊ ትንታኔአቸው እና የደረሱብት ፖለቲካዊ እና አገራዊ የደህንነት ስጋት ድምዳሜ ወድጀዋለሁ።

አቶ ባይሳ ዋቅ ወያ የተባሉ ጸሓፊ ግን “ከጅብ ጅማት የተሠራ ክራር ቅኝቱ እንብላው እንብላው ብቻ ነው” (ባይሳ ዋቅ-ወያ) April 19/2019 በሚል ርዕስ በጋዜጠኛ ክንፉ አሰፋ የሚዘጋጀው http://ethioforum.org (Ethio media Forum) ድረገጽ ላይ የተለጠፈውን ትችታቸው አንብቤው ሁለቱ የማይገናኙ ጭንቅላቶች ሆነው አግኝቼአቸዋለሁ።

እንደ እነ ባይሳ ዋቅ ወያ የመሳሰሉ የኦሮሞ ልሂቃኖችና በእኛ በኩልም በርካታ የዋዠቁ ኢትዮጵያውያን ልሂቃን ጭምር የሻለቃው ጥናት እና ትችት አልተዋጠላቸውም። ሃቁ ግን ከማንኛውም ወቅት ዛሬ በለማ መገርሳ እና በአብይ አሕመድ የሚመራውበቋንቋ” አስተዳደር የሚያምን ስርዓት ለብዙዎቹ የኦሮሞ ልሂቃን የተመቻቸ ስርዐት እንደሆነ ሽንጣቸው ገትረው የቆሙለት አሳፋሪ ወቅት ነው።ይህ “የአፓርታይድ/የዘረኞች’ ስርዓት ከጽንፈኛ እስላማዊ ኦሮሞ ድርጅቶች ጀምሮ እስከ ጠባብ እና ዋዣቂ ኦሮሞ ሊሂቅ ያልተገደበ ሰፊ ምህዳር ተፈቅዶላቸው፤ እያንዳንዶቹም በብረት እየታገዙ መንግሥታዊም ሆኑ ሕዝባዊ እና ግላዊ ተቋማትን ከማፍረስ እስከ ዝርፍያ እና ቅሚያ የደረሱበት ወቅት ነው። ወንጀሎች ሲፈጽሙም  መላቅጡ ባልተረዳነው ቸልተኝነት “ቸል” ስለተባሉ የልብ ልብ ተሰምቷቸው ያለ ምንም ፍርሃት እና ተጠያቂነት በአገሪቷ ገጠሮች እና ከተሞች ሰፊ የሽብር ጥቃት በማካሄድ የሰለማዊ ዜጎችን ህይወት በማናወጥ ላይ ይገኛሉ።  

አንዳንዶቻችነን ያስገረመን ተገኘ የተባለ ደብዳቤ ባለፈው አመት በቅርቡ ወደ ሜካ (ሳወዲ አረቢያ) በመሄድ የ “ሓጂነት” ማዕረግ የተሰጠው “ሓጂ ጃዋር መሓመድ” የተባለ የቄሮዎች መሪ፤ ከእነ ለማ መገርሳ ተጻጻፈበት የተባለውን ከግል ኮምፕዩተሩ “ሃክ” የተደረገ  የተጠለፈ ደብዳቤ የሚያረጋግጠው፤ አሁን እያየነው ያለውን ሁኔታ ስንመለከት “በጃዋር በእስቄል ጋቢሳ በመሳሰሉ ጠባብ ኦሮሞ ልሂቃን ”መሪነት “የኦሮሞ የሽግግር መንግሥት/ቻርተር/ የተባለው “አገር አፍራሽ ሴራ” እንዴት እየተተገበረ እንደሆነ እና ቄሮዎችም የፈለጉት “ስርዓተ አልባ” መንገዶች እንዲፈጽሙ ለምን “ልቅ” እንዲሆኑ የሆነበት ምክንያት ተያያዥ የመነሻ ምክንያት ደብዳቤው ጠቋሚ ማስረጃ (ሊዲንግ ፋክተር) ሆኖ አግኝቸዋለሁ። ባይሳ ዋቅ ወያም ይህንን አልሰማሁም/አላነበብኩም ስላሉ ያንን ማስረጃ ከወደታች አቀርባለሁ።

ወደ ማዕከላዊ ጉዳያችን ከመግባቴ በፊት አቶ ባይሳም ሆኑ የባይሳ መሰል ቡድኖች ሻለቃው ያስቀመጡዋቸው ሃቆች ነጥቡን ለይተው ከመከራከር ይልቅ “ሳታስበው ድንገት ያለጥንቃቄ በቸልተኝነት የረገጠቺው የዛፍ ቅርንጫፍ ሊጥላት ሲል ተንጠልጥላ እንደምትጮህ የበረሃ ‘ወፍ” ይመስል “ውች! ውችውች!” እያሉ እውነታውን ለላመጋፈጥ ሲጮሁ እየሰማን ነው። አዎ ኢትዮጵያ ዛሬ “የተናጠች አገር” ብቻ ሳትይሆን “ፌይልድ ስቴት” ነች። የዜጎችዋ ደህንነት መጠበቅ ያልቻለ ደካማ ነች። ጥፋቱ ተባባሪ ሥርዓቱ ነው። ስለሆነም ሕግ የለም እንጂ በሕግ መከሰስ የሚችል ሥርዓት ይሆን ነበር። 

በዚህ የጥገና ቡድን የተመራው አንድ አመት ውስጥ (ለውጥ መጣ በተባለበት ወቅት) ‘ወንጀሉ እየተበራከተ ፤ የዘር ማጽዳት ፤ በርካታ የቤተ ጸለቶች መቃጠልን ፤ መነኮሳት እና እናቶች እርጉዞች ላይ ግፍ መፈጸምን፤ የሕግ ወጥ ጠመንጃዎችን እንዲሁም ሕገ ወጥ ገንዘቦች እና ወርቆች በጥቁር ገበያ ዝውውር መበራከትን ፤ በርካታ ባንኮችን በተከታታይ “በኦነግ እና ተባባሪ የመግሥት ታጣቂዎች” መዘረፉን፤ መንግሥታዊ ተብየ አስተዳደሮች በበርካታ አካባቢዎች እየፈረሱ በኦነግ እና በመሳሰሉ ‘ወረበሎች’ ቁጥጥር ሥር እየዋሉ መሆናቸውን እራሱ ጠ/ሚኒሰትሩ የሚያምንበት ነው። ስለዚህም ሻለቃው መከራከሪያቸው ተጨባጭ ነው።

ዘረፋዎችም ሆነ ግድያዎች ሲፈጸሙ የኦነግ መሪው ዳውድ ኢብሳ አዲስ አበባ ቁጭ ብሎ የከሚሴ ኗሪዎች በኦነግ ሠራዊቱ ከመጠቃታቸው አንድ ቀን ሲቀረው “ከዛሬ ጀምሮ” ተለያይተናል ብሎ ባለፈው ሳምንት (የውሸት መለያየት) እስከተናገረ ድረስ “በለውጡ ወቅት በአንድ አመት ውስጥ የተጠቀሱ ወንጀሎች ሲፈጸሙ” አዛዥን አመሪ ዳውድ ኢብሳ ነው።

ታጣቂዎቹ በሰላማዊ መንገድ ወደ አገር ግቡ ሲባሉም እኛ ችግር የለንም “መሪያችን አቶ ዳውድ ኢብሳ” ትጥቃችሁን ፍቱ እና ኑ ግቡ ብለው ትዛዝ ካስተላለፉልን ለመግባት ዝግጁ ነን” በማለት የምዕራባዊ ወለጋ የኦነግ ተዋጊ ሃይል የሆነው የወረበሎቹ መሪ “ጃል ማሮ” የሰጠውን የቃለ ምልልስ በየሚዲያው መለጠፉን እናስታውሳለን።  

አገሪቷ የተናወጠች መሆንዋን ማስረጃ ሌላ ማስረጃ አያስፈልግም። ኢትዮጵያ አካል የተባለቺው ትግራይ በዘመነ አብይ አሕመድ ትግራይ ከኢትዮጵያ ሕጋዊ የመነጥል አዋጅ ሳታውጅ ‘ከኢትዮጵያ ጋር “በኮን-ፌደረሺን” ዓይነት ግንኙነት እየተዳደረች ነች። ቻይናውያኖችን አውሮጳውያኖችን ልክ ራስዋ እንደቻለች አገር ወደ ትግራይ እየጋበዘች እያስጎበኘችና እየተዋዋለች ነች። የፌደራሉ መንግሥት ትግራይ እንድትተባበረው ለሚጠይቀው ጥያቄ አሻፈረኝ “አልፈጽምም” ስትል በአንጻሩ “ትግራይ የምትጠይቀው እርዳታም ሆነ ማንኛወንም ጥያቄ” የፌደራሉን እጅ በመጠምዘዝ በጉልበትዋ “ይፈጸምላታል”። ሃይል የትግራይ እንጂ ማኣከላዊው መንግሥት የደከመ “የተናቀ” አቅመ ቢስ ነው ብለው ወያኔዎች ንቀውት መሳለቂያ አድርገውታል። “ስርዐተ አልባ” ማለት “የወደቀ አገር” ማለት ከዚህ የባሰ የውድቀት ምልክት ምን ሌላ ማስረጃ አለ? መሰፍናዊ ስርዓት ማለት ከዚህ ሌላስ ምን የተለየ ክስተት ሊኖረው?

የአገሪቱ ‘የፌዴራል ቢሮ’ አስተዳደር የትግራይ ተወላጅ የሆኑ ተፈላጊ ወንጀለኞች “ትግራይ ውስጥ መኖራቸው እየታወቀ” እነሱን ለመያዝና ለፍርድ እንዲቀርቡ አፈላልጎ እንዲያስረክበው ”ለትግራይ-መንግሥት” እንዲተባበረው ሲያሳውቅ፤ ከወያኔ ባለሥልጣኖች የሚሰጠው መልስ “ዞር በል!” የሚል አናስረክብህም ነው የሚጠው መልስ። ይህ ባህሪ የሚያሳየን አገሪቱ የወደቀች “ፌይልድ ስቴት” መሆንዋን ነው። ለዚህም ነው ሻለቃው አገሪቱ በየጎበዝ አለቆች እየተመራች መሆንዋን ያሳዩት። እኔም አገሪቱ ወደ እዚህ ክስተት እንደመታመራ መጀመሪያ ገና አብይ ወደ ሥልጣን ለመውጣት ሲጣጣር “አትዮ ፓትርዮትስ. ካም “ በተባለ ድረገጽ ከስዊድን ኢትዮጵያ ራዲዮን ያደረግኩት ቃለ መጠይቅ የሰጠሁትን ትንበያና ዝርዝር ማብራሪያዎችን የሚያረጋግጥልኝ ሃቅ ነው።

ይህ ሁሉ ስንመለከት ‘ባይሳ እና እነ ፀጋዬ አራርሳም ሆነ ጃዋርን’ ሳስብ የኦሮሞ ወጣት ማሕበረሰብም ሆነ በጠቅላላ ማሕበረሰቡ በነዚህ ምሁራን ኮቴ ከተመራ የምሁር ሕሊናቸውን ባግባቡ ያልታጠቀሙበት መሆናቸውን ሳስበው ሕዝቡ ምን ያህል ረዢም መጪው ዘመን አስከፊ ኑሮ እንደሚኖር ለመገመት የሚያስቸግር አይሆንም። ብዙዎቹ አሮሞ ወጣቶች ከኦሮሞ ውጪ ወጥተው ሥራ መስራት አይችሉም። ምክንያቱም ብሔራዊ መገናኛ አማርኛ ቋንቋ የሰፋሪ አማራ /የምኒለክ/ ነው ብለው ጠባብ ኦሮሞ ምሁራን ስለሰበኩዋቸው እንዳያውቁት ደንቁረው ቀርተው ሥራ አጥ ሆነዋል። የሚያሳዝን ከስተት!!!

አቶ ባይሳ ዋቅ ወያ ካሁን በፊት “ከወያኔ ጋር መደራደር አለብን” እያሉ  ግትሩን የፋሺሰት ወያኔዎች ባሕሪ እያወቀ ከወያኔ ጋር ተቃዋሚዎች እንዲዳረዱ ሲሰብኩ የነበሩ ሰው ናቸው። ዛሬ ያለ ምንም ድረድር “በሕዝብ አመጽ” ወደ ስልጣን የመጣው እና የተሻለ ምሕዳር አምጥቷል ብሎ የሚከላከሉለትን አብይ አሕመድ እንኳ “በጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ የሚመራው ባልደራስ የተሰኘው “ሰላማዊ  እንቅስቃሴ/ጥያቄ/” ስብሰባ ለማካሄድ ፈልጎ “ሁለት ጊዜ” (እስካሁንዋ ደቂቃ ድረስ) እንዳይሰበሰቡ በአብይ አሕመድ ትዕዛዝ/ስርዓት/ ታግዷል። ያ እንዳይበቃ “ግልጽ ጦርነት” እንደሚያካሂድባቸው አብይ አሕመድ በይፋ ሳይሸማቀቅ የጦርነት ዛቻ አውጆባቸዋል።

ይህ ተለዋዋጭ ባሕሪ ያለው ጭብጨባ እና ሙገሳ ሲደረግለት ፈካ የሚል፤ በአንጻሩ ወቀሳ ሲሰነዘርበት ደግሞ ኩፍኛ በማኩረፍ ወቃሾቹንም ሆኑ ሰላማዊ የመናገር እና የመሰብሰብ ነጻነት የነፈጋቸውን ወገኖችን መብታችን ይጠበቅ ብለው ሲጠይቁት “አርፋችሁ ተቀመጡ! “አደራ ባለ አደራ፤ ምናምን፤ ምንትስ… አትበሉ ካላረፋችሁ “ወደ ለየለት ግልጽ ጦርነት ገብተን ዝም እናሰኛኋለን” ብሎ የሚል “አምባገነኑ አብይ አሕመድ” በእስስት ባሕሪያቱ እየተገረምን ባለንበት ወቅት  በሚገርም ሁኔታ “አፍሪካ ውስጥ ተጽእኖ ፈጣሪ ከሚባሉት ሰዎች” አብይ አሕመድ መመረጡን ስንሰማ በጣም ገርሞናል።

ይህ ክስተት የሚያሳየን ነገር “ሸላሚዎቹ” የሕዝባችንን መከራ እና እንዲሁም ዓለም ያደነቀው ዓለም ዓቀፍ ተሸላሚ ጋዜጠኛ እና የሰብኣዊ መብት ጠበቃ የሆነው ‘እስክንድር ነጋ’ በተሸላሚው አብይ አሕመድ አንደበት “ጦርነት ታውጆበት” ፤ የመሰብሰብ እና የመናገር ነፃነቱን” ያፈነው መሆኑን  በሚገባ ያውቃሉ። በርካታ ዜጎቻችን ከሚኖሩበት መኖርያ ቤታቸው በቡልዶዘር እንደቆሻሻ እየተጠረጉ ወደ ሜዳ መጣላቸውን ያውቃሉ። በርካታ ዜጎች ያልሰሩትን የሽብር ስራ ሰርታችኋል ተብለው (የኦነግ ባንዴራ ተቃውማችኋል በሚል የሽብር ስም ተለጥፎባቸው ክስ ተመስርቶባቸው ያለ ምንም ምርመራ እና ሓጢያት እስከዛሬ ድረስ እስር ውስጥ በስብሰው ይገኛሉ-(ኢትኦጵ ቁጥር 30 የቀረበውን የሕግ ጠበቃቸው ቃለ መጠይቅ ይመልከቱ)!! ይህ እና የመሳሰሉ በርካታ የሰብኣዊ ጥሰቶች እና የዘር ማጥፋት ወንጀሎች እየተሰራ መሆኑን ችግሩ የተቀጣጠለውም እራሱ አብይ በፈጠረው “ቅጥ ባጣ ስርዓተ አልባዊ የመደመር መርሆ” ሆኖ ‘ችግሩ ከመከሰቱም ሆነ ከተሰተ በኋላም ‘ማስቆም” ያልቻለ ደካማ መሪ መሆኑን እያወቁ ለሽልማት መብቃታቸው የሚያሳየን ነገር በዘመነ ክሊንተን ጊዜ ‘ምዕራበውያን መሪዎች ለመለስ ዜናዊና ለኢሳያስ አፈወርቂ ሲያስተጋቡት የነበረው የሙገሳ ጋጋታን እንድናስታውስ  አድርጎናል።

ወደ ሻለቃው እና የባይሳ ዋቅ ወያ ክርክር ከመግባቴ በፊት ባይሳ ዋቅ ወያ ማናቸው የሚለው ወደፊት የምናየው ሲሆን ላዛሬው ግን በዚህ አንድ ዓረፍተ ነገር ብየ ልሻገር።

ወይሳ ዋቅ ወያ በኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ አያምኑም። ዮሐንስም ሆኑ ምኒሊክ ጣሊያን ድል ሲመቱ ብቻ ሳይሆን አምደጽዮንም ከሽዋ ተነስቶ ‘ቱርኮችን ከምጽዋ/ኤርትራ” ሲያባርርም ሆነ በዘመነ ኢትኦፒስ ጀምሮ የተውለበለበች ሰንደቅ ዓላማ መሆኑንዋንም የክርስትና ሃይማኖት እምነት ሊቃውንቶች/ጸሓፍት/ የኢትዮጵያን ሰንደቃላማ ታሪክና ስያሜ ምንጩ ተንትነው ያስረዳሉ።  የሚገርመው ግን እስከዛሬ ድረስ “ባይሳ ዋቅ ወያ’ የአገራችንን ሰንደቃላማ በተለምዶ የኢትዮጵያ የምንለው ባለሶስት ቀለማት ባንዲራ እያሉ በተለምዶ"የሚለው ቃል እየተጠቀሙ፡ “የትዮጵያ ሰንደቅ  በተለምዶ እንጂ ሕጋዊነቱ ያልታወቀ በሕግ አውቅና ተሰጥቶት የተደነገገ አይደለም” ማለታቸው ከሚገረሙኝ አቁዋማቸው አንዱ ነው።

እንዲህ ይላል፦

“ለምሳሌ በተለምዶ የኢትዮጵያ የምንለው ባለ ሶስት ቀለማት ባንዲራ ያገራችን ሕዝቦች መለያ እንዲሆን የተወሰነው በሕዝቦች ተሳትፎ ሳይሆን በአጼ ምኒልክ ውሳኔ ነበር።”

በማለት ስለ የሰንደቅ ዓላማ ምንነት አፈጣጠር እውቀት የሌላቸው መሆኑን የተከበሩ የታሪክ ተመራማሪ የሆኑት አርበኛው ዶ/ር ሃይሌ ላሬቦ ይህንን “የዋይሳ ዋቅ ወያን’ ስለ ሰንደቃላማ የጻፉትን ደካማነት ሲመለከቱ  “ከታሪክ ማኅደር- ---  ለመሆኑ በሕዝብ ድምፅ የተወሰነ ሰንደቅ ዓላማ አለ ወይ?” (ኀይሌ ላሬቦ) በሚል ‘ለባይሳ ዋቅ ወያ’ የጻፉት መልስ እንዲህ ተገለጾ ነበር፡-

“በቅርቡ ማለትም በአ. አ. መስከረም ፳፰ ቀን ፳፻፲፰ ዓ. ም. ባይሳ ዋቅ ወያ የተባሉ ደራሲ፣ “በባንዲራና አርማ ዙርያ ያሉ ውዝግቦች” በሚል ርእስ የጻፉትን፣ በየድረገጹ አሰራጭተውት አየሁት። ከጽሑፋቸው መካከል ቀልቤን ይበልጥ የሳበው የሚከተለው ንግግራቸው ነው።የአቶ ባይሳ ዋና ስሕተታቸው “ዲሞክራሲያዊ የአገዛዝ ሥርዓቶች እየተስፋፉና እየተለመዱ ሲመጡ፣ የባንዲራ ምርጫም ልክ እንደ ሌሎች አገራዊ ጉዳዮች ለሕዝብ ቀርቦና ሕዝብም ተወያይቶበት የሚበጀውን ባብላጫው ድምጽ እንዲወስን ይደረግ ነበር። ዛሬም ብዙ አገራት የሚከተሉት ይህንን ልምድ ነው። “ የሚለው ንግግራቸው ነው።......

“......አቶ ባይሳ የሙያቸው መስክ ምን እንደሆነ አላውቅም። ግን የታሪክ ምሁር እንዳልሆኑ ይኸው ጽሑፋቸው ቊልጭ አድርጎ ይመሰክራል። የታሪክ ሰው ሁነው ይኸንን ዐይነት ጽሑፉ ከጻፉ ደግሞ፣ ከታሪክ ምሁራን የሚጠበቅባቸውን መሠረታዊ መስፈርት ቅንጣት እንኳን የሚታክል ሊያሟሉ አልቻሉም የሚል ግምት ያሰጣቸዋል። በአገራችን አለመስክ ገብቶ መፈትፈት የተለመደ መሆኑን የተረዳሁት የዛሬ አራት ዓመት፣ ማለትም በአ. አ. ጥር ፬ ቀን ፳፻፲፬ ዓ. ም. አቶ አበራ ቶላ የተባሉ ጸሓፊ፣ “ስለኦሮሞ መስፋፋትና ስለምኒልክ ማስገበር ጨለማው ጐን በኢትዮጵያ 1” በሚል ርእስ፣ የኦሮሞን በኢትዮጵያ ገጸምድር መስፋፋት ከአፄ ምኒልክ ማስገበር ጋር በማነፃፀር የጻፉትን ሳነብ ነበር።"

ካሉ በኋላ ፤ በመቀጠልም

“የአፍሪቃ ሰንደቅ ዓላማዎች፣ አገራቸው ከአውሮጳውያን ቅኝ ግዛት ሊላቀቁ ሲታገሉ በነበረበት ወቅት፣ ለዚህ ቅዱስ ዓላማ በአንድ ላይ ያሰለፈቻቸውና፣ እንደ አብነትና የድላቸው ዋስትና ሁና ያገለገለቻቸው ኢትዮጵያ በመሆኗ፣ ነፃነታቸውን ሲቀዳጁ፣ ከአገራችን ጋር ያላቸውን የታሪክና የሥነምድር (ጂዎግራፊ) ትስስራቸውን ለማሳየት ሲሉ፣ አብዛኞቹ የሰንደቅ ዓላማቸው ቀለማት፣ የኢትዮጵያን ያማከለ እንዲሆን መርጠዋል።.....እነዚህን ቀለማት የመረጡት የነፃነቱ ትግል መሪዎች እንጂ፣ የአገሩ ሕዝብ መክሮበት አይደለም። ከመሪዎቹ ብዙዎቹ በፈጸሙት ግፍ፣ ወይንም በመባለግ መንግሥታቸው ሲገለበጥ፣ ወይንም እነሱ ከሥልጣን ሲባረሩ፣ በሥራቸው ክፋት ምክንያት ወይንም ያንድ የተወሰነ ጐሣ አባል ስለነበሩና፣ ወገኔንና ክልሌን ስለማይወክሉ፣ ሰንደቅ ዓላማው ይቀየር ያለ አገር፣ ወይንም ሕዝብ እንዳለ፣ እስካሁን አልተሰማም።"
በማለት ዶ/ር ኀይሌ ላሬቦ መልስ ሰጥተውታል።

ስለዚህ ሰንደቃላማችንን “በተለምዶ” ከሚለው አነጋገሩ በተጨማሪ “ሰንደቅዓላማዋ የፈጠሩትም የተወሰነውም ‘በሕዝቦች ተሳትፎ’ ሳይሆን ‘በአጼ ምኒልክ ውሳኔ ነበር’።” ብለው ጻፉትከእውነታው እና ከታሪክ ውጭ የተንገጫገጨው ግንዛቤ ስለሆነ እንዲያርም የታሪክ ምሁራዊ ማስረጃ ለግሰል።

 ባይሳ ዋቅ ወያ ሰንደቅዓላማችን የሚያዩት እንደ የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ሳይሆን የሚጠሩት “የምኒሊክ ባንዴራ” ብለው ነው የሚጠሩት። አስገራሚ የሚሆነው ደግሞ የሽብርተኛው እና የብዙ አማራን ነብስ እያረደ ከነ ነብሳቸው ወደ ገደል የጣለውን የአሸባሪው የኦነግን  ባንዴራ በማነጻጸር “ሁለቱም ባንዴራዎች የድርጅቶች እንጂ ማንንም ሕዝብ የሚወክሉ ምልከቶች አይደሉም” በማለት ሲሟገት የነበሩ ጸሐፊ ናቸው። ለዘመናት የታወቀቺውን ሰንደቅ ዓላማችንን ማንንም ሕዝብ አትወክልም ሲሉ በኦሮሚያዊ መነጽ ሲተችዋት የምናውቃቸው ‘ባይሳ ዋቅ ወያ’ ማለት አኚህ ነው።

እርው “ይወክለናል” የሚሉት አርማ የትኛው እንደሆነ አናውም።

ስገምተው ግን ምናልባትም ሰማያዊ ቀለም ያረፈበት የሰይጣናዊ አምልኮት ምልክት የሆነውን ባለ ኮከብ የወያኔ/ኢሕአዴግ/ ባንዴራ የሚያከብሩ ይመስለኛል።ወቅቱ ግንቦት 7 እና ኦነግ ወደ አዲስ አበባ በገቡበት ወቅት ነው። እንዲህ ይላሉ ፦

“የግንቦት-7 ደጋፊዎች መሪዎቻቸውን ለመቀበል የምኒልክን ባንዲራ ይዘው ሲወጡ  ሁለቱም አርማዎች ወይም ባንዲራዎች የድርጅቶቹ እንጂ እንወክለዋለን የሚሏቸው ሕዝቦች ማንነት መገለጫና አርማ አለመሆኑ እየታወቀ ነው።” ይላሉ ባይሳ ስለ “ባንዴራ” ጥናት ምንም እወቀት እና ምርምር ሳይኖራቸው።

ኢትዮጵያውያን ወደ ባድሜ ጦርነት በዘመቱበት ወቅት ይዘውት የዘመቱት ሰንደቅ ዓላማ አርሳቸው “የሚኒሊክ ባንዴራ” የሚሏትን ሰንደቅ-ዓላማችን ሳይሆን የወያኔ/ኢሕአዴግ/ ፋሺሰት ባንዴራ ይዘው እንደዘመቱ ያልተወለበለውን ሰንደቅ ዓላማ ተውለብልቦ ነበር በማለት ታሪክ ለማሳሳት የሞከሩ ናቸው።

 እንዲህ ይላል፡

“ልክ በባድሜ ላይ እንዳደረገው ያገራችንን ዳር ድንበር ለማስከበር የምኒልክን ወይም የኦነግ ባንዲራ ሳይሆን፣ ይህንኑ ባለኮከቡን ባንዲራ ይዞ ዘምቶ፣ ተዋግቶ አሸንፎ ይመለሳልና ምንም ስጋት አይግባን!”

የወያኔ ባለ ኮከብ ባንዴራ ከባድሜ ጦርነት በኋላ ያውም ከቅንጅት ምርጫ በኋላ የተከሰተ (ኢንፎርስድ የሆነ) ምልክት መሆኑን ባይሳ ልብ አላሉትም። ሰራዊ

ሲዘምቱ ሲያውለብልቡት የነበረው ሰንደቅዓላማ ባድሜን እንደተቆጣጠሩ በከተማዋ መሃል በወያኔ “የነገዶች መዝሙር” ታጅባ የተውለበለበች ባለ ሦሰት ቀለም  አሮሞዎች (ባይሳም ጭምር) “የምኒሊክ ባንዴራ” የሚሏትን ውዲቷ ሰደቅዓላማችን እንደተውለበለበች “በዩቱብ የቲቪ ድረገጽ” ላይ ማየት ይቻላል። ስለሆነም ባይሳ የክስተቶች እና የታሪክ ክንዋኔዎች የማስተዋል ድካም ስላለቸው፡ አሁን እየታየ ያለው የኦሮሞዎች መንግሥት አገሪቱን ማስተዳዳር ያልቻለውን አብይ አሕመድ ሥልጣኑን ማስረከብ ይኖርበታል ብለው ሻለቃ ዳዊት የተናገሩትን ማስተዋል ብቃት ስለጎደላቸው ሻለቃ ዳዊትን “ከጅብ ጅማት የተሠራ ክራር ቅኝቱ እንብላው እንብላው ብቻ ነው” በማለት ወደ ስድብ ውርጅቢኝ አነጣጥረዋል። 

ብዙዎቹ የኦሮሞ ጠባብ ምሁራን የሚገርሙኝ ሌላው ነገራቸው ደግሞ “ሰንደቃላማችንን ምኒሊክ ስለፈጠርዋት “እንደ ሰንደቃላማችን አድርገን አንቀበልም” ይሉ እና ወይንም በምንሊክ ስም እየጠሩ “የምንሊክ ባንዴራ” ብለው  ይጠሩዋት እና ምንሊክ የገነባውን ቤተመንግሥት ፡ “ምኒሊክ-ቤተመንግሥት” ተብሎ ሲጠራ ግን “ብሔራዊ በተመንግሥት” እንጂ “ምንሊክ ቤተ መንግሥት” መባል የለበትም እያሉ ሲከራከሩ መስማት ግራ የሚያጋቡ የተማሩ ግን ካልተማረው ያነሰ አስተሳሰብ የሚያፈልቁ ምሁራን ናቸው።

አቶ ባይሳ ለሻለቃ ዳዊት መልስ ሲሉ በብዙ ገጾች የጻፉት የመከራከሪያ ነጥቦቻቸው በጥንቃቄ ደጋግሜ ባነብበውም ያ ሁሉ ዑደት ዞሮ የወደቁበት መልስ “ኢሕአዴግ የዘር ማጽዳት የሚያክል ዓለም አቀፍ ወንጀል አላከናወነም” ብለውን አርፍ! 

 ኢሓዴግን እንተው እና “የቄሮ ትውልድ” (ቄሮ ጄኔረሽን) ብለው ኦሮሞ ምሁራን ያሳደጉት ኦሮሞ ወጣት ኢትዮጵያን እጅግ አድርጎ የሚጠላ በጣም አክራሪ ሽብርተኛ ወጣት በማፍራታቸውን ሌላውን የኋላ ገመናቸውን ትተን ቢያንስ የአንድ አመት እንቅስቃሴአቸው እንኳ ምን አይነት ሽብር እንደፈጸሙ ቁልጭ ያለ ሃቅ ነው። ስለዚህ ኢሕአዴግ የዘር ማጥፋት አላከናወነም ብለው አቶ ባይሳ ሲከራከሩ ‘ኢሕአዴግ የተባለ በጣሊያን ፋሺስቶች ርዕዮተ ዓለም የተገናባ በዘር ማጽዳት ወንጀል የተካፈለ ለመሆኑ ብዙ እኛ ኢትዮጵያውያን እናውቃለን። ማስረጃዎችም ሞልተዋል።“ኦቦ ባይሳ ዋቅ ወያ” በሁለት መንግዶች ኢሕአዴግን ሲከላከሉ ተመልክተናል፦

ለሻለቃ ዳዊት መልስ ሲሰጡ እንዲህ ይላሉ፦

“እኔም እንደስዎ ኑሮዬ ከባህር ማዶ ስለሆነ የኢህአዴግ መንግሥት በኢንቬስትመንት ሰበብ “ህዝብን እንዳፈናቀለና አልፎ አልፎም እንዳሰፈረ” ባውቅም፣“ብሄርን የማጥራት” ፖሊሲ ነበረው ብዬ ለማመን ግን ያዳግተኛል። እስዎ የዘረዘሯቸው የኢህአዴግ የሰብዓዊ መብት መጣሱ ዕውነት ሆኖ እያለ ብሄርን ማጥራት” የሚያክል ዓለም አቀፋዊ ወንጀል መፈጸሙን ግን እርግጠኛ አይደለሁም እስዎም ያለዎትን ተጨባጭ ማስረጃዎችዎን ቢያቀርቡ ኖሮ ተዓማኒነትዎን ከፍ ያደርግ ነበር። ግን አላቀረቡም።”

በማለት “ኢሕአዴግ በብሄር ማጥራት የሚያክል ወንጀል መፈጸሙን እርግጣኛ አይደለሁም” የሚለው መከራከሪያ መልሳቸው የሚያመላክተን ለበርካታ አመታት ወያኔ የሚመራው ኢሕአዴግ ምን ይሰራ እንደነበርም አለማወቁ ለ27 አመት የተኼደው የዘር ማጽዳት ወንጀል ካላወቀ አሁን እየተከሰተ ያለው ተጨባጭ አደጋ ለመረዳት አቅም እንደሚያንሳቸውው ማሳያ ነው።
በኢሕአዴግ የተሰየመው የወያኔ መሪ ሃይል ‘በወልቃይት አማራ ላይ” ምን የዘር ማጽዳት ወንጀል እንደሰራ ባይሳ እርግጣኛ አይደሉም። ለምን? ምክንያቱ ለኛ ግልጽ የሆነ፤ ለእርሳቸው ብቻ ባናውቀው ምክንያት የተሰወረባቸው።

ኢሕአዴግ በቋንቋ በነገድ ሸንሽኖ ያዋቀራት ኢትዮጵያ “አፓርታይድ” መሆንዋን እና ኦሮሚያ የሚል የአካባቢ መጠርያ በታሪክ ያልታወቀውም ሆነ የኦሮሞ ነው ተብሎ 3/4ኛ ያገሪቱ መሬት “ኦሮሞ” ብሎ ራሱን ለሚጠራ ሕዝብ ያለ ምንም ሕጋዊም ሆነ ሕዝባዊ (ፓብሊክ ዲቤት) ክርክር እና እሰጥ አገባ “ለኦሮሞ ጠቀሜታ እና ብቸኛ ባለቤትነት የሰጠው የጎበጣ (የሄጂመኒ) ሕግ የዘር ማጽዳት ምክንያት መነሻ መሆኑንም አቶ ባይሳ አላወቁም ወይንም ግልጽ አልሆነላቸውም። ለምን? መልሱ እራሳቸው የሚያውቁትን ያብራሩት፡

“መሰሪው” ሌንጮ ለታ እና ‘ባንዳው መለስ ዜናዊ’ ተሰነይ ከተማ በምስጢር ተገናኝተው ተፈራርመው ያጸደቁት ‘ሕገ መንግሥት’ ተብየው ፈቅዶ “ሕዝብ ያጸደቀው ሳይሆን” ሁለቱም (ምናልባትም ኢሳያስ የተጨመረበት) ሆነው የነደፉትን ሕግ በሽግግሩ ወቅት “መጠነኛ ለውጥ ተደርጎበት” የጸደቀ መሆኑን ‘ሌንጮ እራሱ ተሰነይ የረቀቀው የወያኔ እና የኦነግ ሕገ መንግሥት እንደሆነ “ኢሳት” ላይ በሰጠው ቃለ መጠይቁ አረጋግጦልናል። ይህንን የኦሮሚያ ግንጣላ እና ገሪቱን ሚበትን ሴራ እውን ለማድረግ በወቅቱ 14 የኦሮሞ የተደራጁ የፖለቲካ ድርጅቶች ሽንጣቸው ገትረው ‘ለአፓርታይዱ ሕገ መንግሥት’ ቆመው ይከራከሩለት እንደነበሩ (ስማቸውን ለመመለክት ምጽአተ ዐማራ ገጽ 264 ተመለክት) ያመጣው የዘር ጭፍጨፋ ሕገ መንግሥቱ መሆኑን አቶ ባይሳ ለምን እየሸሹ እንደሆነ ግልጽ አይደለም። የዘር ማጽዳት እና ጸረ ኢትዮጵያነት ለዛሬ ብጥብጥ ምንጩ ከዚያ የመነጨ ነው ስንል በወቅቱ የተፈጸሙ ድርጊቶችን እና በጉባው ውስጥ በአንድ ዘር ላይ ያነጣጠረ “የነገድ ስም እየተጠቀሰ” የዘር ማጽዳት ዘመቻ መጀመር እንዳለበት ግፊት የተደረገበት ምልክትን ለማስታወስ ሃገራዊ የሆነ ሰብኣዊ ሕሊናን መገንባት ያሻል ።
በጣም የሚገርመው አቶ ባይሳ እንዲህ ይላሉ፡-


"ተለያዩ ያገራችን ክፍሎች በብሄሮች መካከል የተነሳው ግጭት“ብሄርን ለማጥራት” እንዳልሆነ የሚያሳየው፣ ለምሳሌ በኦሮሚያ ክልል የሚኖሩ በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠሩ የአማር ብሄር ተወላጆች እንኳን ከቄያቸው መፈናቀል ይቅርና አንዳችም “የባዕድነት ስሜት” ሳይሰማቸው ለዘመናት በኖሩበት አካባቢ ከጎረቤቶቻቸው ጋር እዚያው ኦሮሚያ ክልል ውስጥ በሰላም እየኖሩነው።"  ይላል ባይሳ ዋቅ ወያ!

ይህንን ስታነብቡ ጭንቅላትን በሁለት እጅ አስደግፎ “በስመ አብ!” ያሰኛል። ከተለያዩ ያገራችን ክፍሎች በብሄሮች መካከል የተነሳው ግጭት “ብሄርን ለማጥራት” ሲባል አልተከሰተም” ሲሉን ታዲያ ምን ለማጥራት ኖሯል ወደ ክልልህ ሂድ! ውጣ አገርህ አይደለም! እየተባለ በሚሊዮኖች የተፈናቀለው ዜጋ ? በተፈራ ሽጉጤ እና በመለስ ዜናዊ አይዞህ ባይነት የተከናወነው ከ70 ሺሕ የአማራ ሕዝብ የጉራ ፈርዳ ተፈናቃይ “ምን ለማጥራት ኖሯል” አማራ እንዲፈናቀል የተደረገው?

በጣም በርካታ የአማራ ሕዝብ የጭካኔ እና የዘር ማጽዳት ስራ በኦፒዲኦ ባለስልጣኖች እና በወያኔ ወታደሮች እንዲሁም በኦነግና በጃራ ጦረኞች ተረባርበው ግምባር ገጥመው “በአማራ ማሕበረስብ ላይ የዘር ማጽዳት የተከናወነበትን የኦሮሞ ክልል” “ከቄያቸው መፈናቀል ይቅርና አንዳችም “የባዕድነት ሰሜት” ሳይሰማቸው ዛሬም እዛው ኦሮሞ በሰላም እየኖሩ ነው” የሚለው የአሮ ባይሳ ዋቅ ወያ ሙግት በማስረጃ የተደገፈ አይደለም። እንዲህ ያሉ ኦሮሞ ምሁራን በዚህ ዓይነት ማስተባበያ ገብተው ሲነታረኩ መስማት ለብዙዎቻችሁ ያስገርም ይሆናል፦ ሃቁ ግን ‘የኦሮሞ እና እኔ መጣሁበት የትግሬ ነገድ ልሂቃኖች የተከተሉት የክሕደት መንገድ “ምን ያህል ርቀት እንደሚሄዱ ‘ከኦኖሌ ሃውልት’ ምስረታም ሆነ ወያኔ ይዞት ከተነሳበት የጸረ አማራ ፖሊሲው ከዘመናዊ አስተዛሰብ የራቁ የዘመነ መስፍንት አስተሳሰብ የተናወጣቸው መሆናቸውን ለምናውቃቸው ብዙም አልገረመንም።

“ለዘመናት በኖሩበት አካባቢ. ምንም ችግርየባዕድነት ስሜት ሳይሰማው….”  የሚለውን ለኔ ባልገባኝ ምክንያት “አልተፈጸመም”  በሚል ሃቁን ክዷል። ለዘመናት የኖሩት አማራ ገበሬዎች መምህራን እና ነጋዴ ሰላማዊያን ኦሮሞ ውስጥ የዘር ማጽዳት ተፈጽሞባቸው ምጽአተ ዐማራ የተባለው መጽሐፍ በገጽ 335 የዘገበውን እንድትመለከቱት አንባቢዎችን እጋብዛለሁ።

ገጽ 135 እንዲህ ይላል።

የገለምሶ ዕልቂት ብዙ ሰው አያውቀውም። በሁለቱም የሀገሪቱ ክፍል ከተደረጉት ጭፍጨፋዎች የሚያክል የለም። በቦታው ለብዙ ዘመናት የኖረውን ዐማራ በሰኔ 1984 በገለምሶ አካባቢ ባሉ ወፊ፤ ዳንሴ፤ እንጫራና ገለምሶ ከተማ ዐማሮች እና ክርስትያኖች እየተለቀሙ ተያዙ። በሀብሩ ወረዳ “ገርሶ ገደል” እየታረዱ ተጣሉ። የተገደሉት እንዳሁኖቹ “አሸባሪዎች” የራስ ቅላቸው ከአንገታቸው ላይ በሜንጫ እየተቀላ ነው።  የሰው ራስ ቅል ጭኖ የመጣ አንድ ገልባጭ መኪና ከሌላ ቦታ አምጥተው ገለምሶ አውሳይድ ወንዝ አጠገብ ካለ ጫካ ሲገለብጡ ያየ ሰው ምስክርነቱ እንዲህ ይገልጸዋል፡-

“አውሳይድ ወንዘ አጠገብ ወደ ወፍ ቆሎ ጫካ ሲገለብጡት ተደብቄ እመለከት ነበር። ሙሉ ሽበት ያለበት፤ግራጫ የመሰለ፤አልፎ አልፎ ሽበት ጣል ያደረገበት ፤ሙሉ ጥቁር ራስ በራ የሆኑ ጭንቅላቶች በገፍ ሲገለበጡ በዓይኔ አይቻለሁ። በእርግጥ የመኪናው የላ መጫኛው አልሞላም። ቢሆንም ግን ያየሁት ጭንቅላት ከሁለት ጆኒያ ይበልጣል።” (ሰረዝ የተጨመረ)
በማለት ያይን ምስክር ያየውን መስክሯል። ከሁሉም የሚገርመው ደግሞ  በምዕራብ ሓረርጌ የተገደሉ ሰዎች አብዛኛዎቹ በሜንጫና በቢላዋ ነው። ብዙዎቹም በጅምላ በአንድ ቦታና ጊዜ ታርደዋል።” ይላል መጽሐፉ።

እንቁፍቱ በደኖ ገደል ላይ ከነነብሳቸው ተገፍትረው፤ በቢላዋ ታርደው፤ ህጻናት ሳይቀር አንገታቸው በሰላ እየታረዱ የዘር ጽዳት የተካሄደባቸው የተጨፈጨፉ አማሮች  በኦነግ፤ በጃራ ራዊት፤ በኦፒዲኦ እና በወያኔ ሰራዊት እየተፈራረቁ የሰሩት የዘር ማጽዳት ወንጀል  በቪዲዮ፤በምስል፤ በጽሑፍ በቃለ መጠይቅ የተረጋገጡ ማስረጃዎች በብዛት አሉ።በሚሊዮን ማፈናቀሉን የተዘወተረ ስለሆነ አሁን፤አሁን ብዙም ሰው ቁብ አልሰጠውም።

እንግዲህ አቶ ዋቅወያ ለዘመናት የኖሩ አማሮች እንኳን ቄያችሁ ልቀቁ ሊባሉ በሰላም እየኖሩ ነው ማለቱ ሳይበቃ ዕልቂቱን ለማጣጣል ወይንም አነስተኛ ለማድረግ ወይንም “ስማቸው ሊጠቅሰልን ያለፈለገ የራሱ የምናብ ግምት የገቡ ወንጀለኞች” ስራ እንጂ በሽግግሩ መንግሥት አባሎች የነበሩ የኢሕአዴግ አባል ድርጅቶች የጃራ ፤ ኦነግ ፤ የኦሕዴድ እጅ ወይንም “ፖለሲ/ መመሪያ/ ትዕዛዝ ” በጭፍጨፋው የሉበትም በማለት "እኔ እስከ ማውቀው ድረስ የራሱን ክልል ከሌላው ብሄር ወይም ብሄሮች ለማጥራት ብሎ አንድን ብሄር ነጥሎ ያገለለ ወይም ያፈናቀለ ክልል የለም ማለቴነው።” በማለት በፖሊሲ ደረጃ የዘር ማጽዳት (በተለይ በአማራ ላይ ያነጣጠረ) ወንጀል ዘመቻ አልተካሄደም እያለን ያለው።

ሽፍንፉኑ እንዳለ በዘዴ ለማምለጥ እንዲህ ይላል፡

“…ስለዚህ ነው በክልል ባለቤትነት” ዙርያ በኢትዮጵያ ብሄሮች መካከል ግጭት አለ የሚባለውን ትርክት ለመቀበል በጣም የሚያዳግተኝ።”

 በማለት አንድ ሕዝብ በገፍ ሲፈናቀል እና ሲጨፈጨፍ የክልሉ ኗሪዎች ይብዛም ይነስ ካልተካፈሉበት አይከናወንም።ሕዝብ የሚባል የሚዳሰስ ነገር የለም። ሕዝብ ማለት ያለ ግለሰቦች የሚኖር አይደለም። ስለዚህ ግለሰቦች እንጂ ሕዝብ የሚባል ስለሌለ “ያፈጀ ያረጀ” “ሕዝብ” እየተባለ የሚተረከው የማይጨበጥ ሙግት “መሸሺያ” ሽፋን ካልሆነ በቀር “በወንጀሉ” ተሳታፊዎች የክልሉ ተወላጆች ናቸው እና የሕዝቡ አካል ስለሆኑ በፈለግከው ትርጉም ልትወስደው ካልተፈለገ “አጠቃላይ ክንዋኔው” በክልሉ የዘር ጭፍፋ ሊካሄድ ምክንያት የሆነው “ተሳታፊው” ሳይሆን ትኩረታችን “ለዚህ የዘር ጽዳት ምክንያት መነሻ የሆነው “በቋንቋ፤ በነገድ ከልልሎ አንዱ ከሌላው የባለቤትነት ጥቅም አባልጦ የሚያጋድል” የኢሕአዴግ መንግሥታዊ ፖሊሲ ነው የሻለቃውም ሆነ የማንኛችንም ክርክር።

አቶ ባይሳው ግን ኢትዮጵያ ውስጥ ጭራሽኑ “የዘር ጽዳት አልተፈጸመም” “ኢሕዴግ መንግሥት በዘር ማጽዳት አልተካፈም” ወይንም ከተከናወንም ፖሊሲው ለዘር ማጽዳት መነሻ አይደለም” በማለት ሻለቃ ዳዊትን እንዲህ ይላቸዋል።

“እስዎ የዘረዘሯቸው የኢህአዴግ የሰብዓዊ መብት መጣሱ ዕውነት ሆኖ እያለ ብሄርን ማጥራት” የሚያክል ዓለም አቀፋዊ ወንጀል መፈጸሙን ግን እርግጠኛ አይደለሁም ይላሉ አቶ ባይሳው ዋቅ ወያ።

ይህ ሁሉ በዓለም አቀፍ ወንጀል የሚያስጠይቅም ሆነ በፈጣሪ ሕግ የሚያስኮንን የዘር ጭፍጫፋ ተካሂዶ አቶ ባይሳ ግን የሚያ “የሰብኣዊ መብት ጥሰት” በሚል በማሳነስ ደረጃ ነው የተመለከቱት። ለዚህ ነው ‘የአብዛኞቹ’ የኦሮሞ ምሁራን ሕሊና ከመቸውም ጊዜ እየቀጨጨ መሄዱን ንዲህ ያለ ግንዛቤአቸውን ስናደምጥ የኦሮሞ ወጣቶች በነዚህ ሰዎች መገራቱን ከቀጠለበት  መጻኢ ዕዳለቸው ምን አንደሚሆን አሳሳቢ ይሆናል ብለን የምንለው። 

በአማራ ሕዝብ ላይ ከኦሮሞ እና ከደበቡብ ክልሎች መፈናቀልም ሆነ የዘር ጽዳት የተፈጸመበትን ወንጀል ለማንበብ ከ657 ገጽ በላይ የተጻፈውን “ምጽአተ ዐማራ ተገድሎና ተገዳድሎ የማያልቅ ተነቅሎ የማይደርቅ” በደራሲው በወዳጄ በክቡር አቶ ተክሌ የሻው የተደረሰው በሞረሽ ወገኔ ዐማራ ድርጅት የቀረበ እያንዳንዱ ሰነድ ላይ በማስረጃ የተደገፈ ይህ ታሪካዊ መጽሐፍ ሁሉም ኢትዮጵያዊ እንዲያነበውና አለም አቀፍ የዘር ማጽዳት ወንጀል በኢሕአዴግ (ወያኔ/ ኦፒዲኦ/ የደቡብ ሕዝቦች መስተዳድር ባለስልጣኖች…) አዝማችነት ቁረጠው!ግደለው!ውጣ/ እየተባለ በፖሊሲ አሰራር “በመንግሥት ትዕዛዝና በስውር” የተፈጸመ የዘር ማጽዳት ወንጅል መሆኑን ማስረጃዎቹን ለማየት እንዲረዳችሁ መጽሐፉን አፈላልጋችሁ እንድታነቡት እጠይቃለሁ።

በመጨረሻም ጽሑፌን በዚህ ማስረጃ ልደምድም። አቶ ባይሳ ለሻለቃ ዳዊት የሰጡት  የመጨረሻው መልሳቸው እንዲህ ይላል።

“The Qeros are recruited by Jawar to do the dirty work of killing,plundering and creating an atmosphere of fear in the nation”በማለትቄሮዎች ለግድያና ለዘረፋ ወንጀል በጃዋር እንደተመለመሉና የሥጋትና ፍርሃት ድባብባ ገሪቷ ላይ እንዳሰፈኑአድርገው ማቅረብዎ ደግሞ ከስዎ የማይጠበቅ ደረጃውን ያልጠበቀ ተራ አነጋገር ነው። “የዶ/ር ዓቢይን ከጃዋር ጋር ያለውን ግልጽም ሆነ ድብቅ ግንኙነት በተመለከተ ምንም ማስረጃ ስለሌኝ አስተያየት ከመሰንዘር ብቆጠብ ይሻለኛል።” ይላሉ  አቶ ባይሳ)።

ኢትዮጵያ በሁለት ምንግሥታት እንደምትተዳደር የነገረን (በቄሮ እና ኢሕዴግ) ሓጂ ጃዋር ከእነ ለማ መገርሳ በምስጢር ይጻጻፍ  ነበር የተባለው ሰነድ አቀርባለሁ። መረጃውን የመቀበል እና አለመቀበል የየግል ግንዛቤአችሁ ሆኖ በድብቅ ሲገናኝበት የነበረውን ደብዳቤው ከጃዋር ኮምፕዩተር “ሃክ” ተደርጎ “ተጠልፎ” ተገኘ የተባለው ደብዳቤ ይኼው አቶ ባይሳ ዋቅ ወያ እንዲያየው ይኼው።

“ከጀዋር ኢሜል hack ተደርጎ የተገኘ ለአብይ: ለለማ እና ለተከታዮቹ ያሰራጨው  highly classified email (በዶክተር ደመቀ ገሰሰ ከኦሮምኛ ወደ አማርኛ የተተረጎመ)

"ለኦሮሞማ እውን መሆን ከዚህ የበለጠ ጥሩ አጋጣሚ የለም። ይህንን አጋጣሚ በፍጥነት መጠቀም መቻል አለብን። አሁን ማድረግ ያለብን ዩናትድ ኔሽን አገሮችን ሲያደራድር ይዞታውን የሚያፀኑት በወታደራዊ ሃይል አሸንፎ ለተቆጣጠረው አካል ነው።

ስለዚህ በሁሉም አቅጣጫ ያሉንን የወሰን ይገባኛል ቦታዎችን በሃይል አሸንፈን መያዝ መቻል አለብን። ይህንን ማድረግ በቂ አይደለም። በሃይል የያዝናቸው ቦታዎች ላይ ሰፍረው የሚገኙ ሌሎች ብሄሮችን ከቦታው መሸኘት መቻል አለብን። የኤርትራ መንግስትም ከጎናችን ነው። ሌሎች የቅርብም፣ የሩቅም አጋሮቻችን ይህንን እውን ለማድረግ እኛን በመጠባበቅ ላይ ናቸው። ይህንን እድል በፍፁም ማጣት የለብንም። የአሜሪካ መንግስትም በዚህ ጉዳይ ላይ ችግር የለበትም።

በሁሉም አቅጣጫ የአቢሲኒያን ኤምፓየር መፍረስ የሚፈልጉ ሁሉ ከእኛ ጋር ናቸው። እነ ለማ ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ በተከታታይ ባደረግነው ውይይት ከጎናችን ናቸው። አቢሲኒያዎች ቶሎ ግንኙነት ለመፍጠር ሳይሄዱ ያለውን ክፍተት መጠቀም ያለብን አሁን ነው።"  

ይላል የጃዋር ግንኙነት ደብዳቤ ከነ ለማ መገርሳ ጋር ተደርገ የታበለ በዶ/ር ደመቀ ገሰሰ ከኦሮምኛ ወደ አማርኛ የተተረጎመ ምስጢራዊ ደብዳቤ ግንኙነት።

በመጨረሻም አቶ ባይሳ አብይ ማን አንደሆነ እና ሥርዓቱ ሥርዓተ አልባ እና የተናጋ መሆኑን “ታላቁ የፖለቲካ ቅሌት በኢትዮጵያ፤ ነጠብጣቦቹን ያገናኙና ምስሉን ይመልከቱ!” የሚል  ፀሃፊ፡- ሰርቤሳ .ተርጓሚ፡- “ሢሣይነሽ መንግሥቴ” ግሩም ጥናት ጉገል በማድረግ ለተጨማሪ ንባብ እጋብዛለሁ።

 በተረፈ በሻለቃ ዳዊት የተጻፈ (ኢትዮጵያ፤ አፋፍ ላይ የምትገኝ ሃገር – ዳዊት ወልደጊዮርጊስ April 12, 2019 -  ምንጭ – Ethiopia: A Country on the Brinks ተርጓሚ – ሚኪያስ ጥላሁን) ወድጀዋለሁ። ይህንን  ርዕስ በሚመለከት ብቻ ‘ቆቤን አንስቼ’ ለሻለቃ ዳዊት እጅ እነሳለሁ።
አመሰግናለሁ፤
ጌታቸው ረዳ (ኢትዮ ሰማይ)