Sunday, July 7, 2019

ብያቅራችሁም አማራ ከእነ ደመቀ መኮንን የከፋ ጠላት የለውም! ጌታቸው ረዳ (ኢትዮ ሰማይ ድረገጽ አዘጋጅ- Ethio Semay )


ብያቅራችሁም አማራ ከእነ ደመቀ መኮንን የከፋ ጠላት የለውም!
ጌታቸው ረዳ (ኢትዮ ሰማይ ድረገጽ አዘጋጅ- Ethio Semay )
ብዙ የአማራ ወጣቶች፤ የአማራ “አክቲቪስቶች” እና ብዙዎቹ ደደብ የአማራ ምሁራን እና ነፈዝ ጋዜጠኞች የሚያወሩት ወሬ “አማራ አንድነቱን እንዳይፈረካከስ “ጥንቃቄ” እናድርግ የሚሉትን የነፈዘ ክርክራቸው ሳደምጥ እጅግ ይገርመኛል። እንዲህ የሚመክሩዋቸው ደግሞ የዘለፋ ግምባር ቀደም ሰንዘሪዎች የሆኑት “የኢትዮጵያዊነቱን ዘንግ ይዞ የተሰዋው፤ በቃሉ የጸናው የአማራው አርበኛ ጀኔራል አሳምነው ጽጌን” ከሃዲ እና ጡት ነካሽ፤ ያውም አጼ ቴዎድሮስ ሲዘለፉበት የነበሩባቸው ቃላቶች እየተጠቀሙ ሕሊናው የዞረበት ዕብድ” እያሉ አንድነትን የሚያፈርሱ ቃላት የሚጠቀሙት እነ ኮለኔል ደመቀ ዘውዱ እና እነ ደመቀ መኮንን እንዲሁም ወፈፌው መቶ አለቃ አበረ አዳሙ የመሳሰሉ ባንዳዎች ናቸው። ማሕበረሰቡን የሚያለያይበት ብትር እያቀበሉ፤የሚያራርቅ ዘለፋ “እየዘለፉ” ስለ አንድነት ስያወሩ ይገርመኛል።

እራሳቸው እነዚህ ሰዎች “ለ28 አመት ያደፈ ገበና ማሕደር ተሸክመው የአማራን ህይወትና የሰባ/ለም/ መሬት በጠላት እጅ ወድቆ እንዲጠቃ ሲያድርጉ የነበሩት የፋሺስቶቹ ወያኔ “አገልጋዮች” የነበሩ ዛሬ ደግሞ የኦሆዴድ/ኦነግ አሽከሮች የሆኑት እነ ደመቀ መኮንን፤  እና የባሕር ዳር ፖሊስ ኮሚሽነር ሆኖ የተሾሞው ስዊድን አገር “መነግሥታዊ ዌልፌር/ዕርጥባን” እየተረጠበለት ሲተዳዳር የነበረው ወደ ኤርትራ ከመሄዱ በፊት በወያኔ ሥርዓት “አዲስ አበባ” ውስጥ የአንድ ወረዳ “ምርመራ ክፍል ሹም” ሆኖ በብሔር ብሔረሰብ ሕዝቦች ፋሺሰታዊ ሕገደምብ’ ማሓላ ፈጽሞ ፡ ‘ጸረ ወያኔ’ ዜጎቻችንን “ሲያሳድድ” የነበረው የወያኔ አገልጋይ እና  በጸረ አማራነት የታወቀው የግንቦት 7 ድርጅት”  የአመራር አባል የነበረው “ልክፈተኛ ወፈፌው “የመቶ አለቃ አበረ አዳሙን” ልሳን ተማምነው “የአማራን ደህንነት እያስጠበቁ “አማራውን ከፋሺስቱ ሥርዓት” ነፃ ያወጡታል የሚሉ ነፈዞች እጅግ እጅግ መወገዝ አለባቸው።


እነዚህ ሆዳም አማራዎች ከአግልጋይ ባሕሪያቸው እና ለወያኔ አድረው ለ28 አመት የሠሩት ወንጀል እና ተልካሻ አድርባይ ባሕሪያቸው ተላቅቀው “የፋሺስት ሥርዓት” ይቃወማሉ ብሎ ማለት አንድም ለ28 አመት የተጓዙበት ባሕሪያቸው እና እስካሁን ድረስ ያልተናዘዙበት ወንጀላቸው ካለመረዳት የመነጨ ነው፤ወይንም በአፓርታይዱ ስርዓት መሪ ሚና እየተጫወቱ ካሉት ሰዎች ጋር ያላቸው የ28 አመት “ጓዳዊ” ግንኙነት መርምሮ ያለመረዳት የመነጨ ካልሆነ በስተቀር እነዚህን ምርጥ የአማራ ተወካዮች እና ልምድ ያላቸው ናቸው ብሎ ተስፋ ማድረግ ዛሬም ‘ውሃ መውቀጥ’ ነው።

ሌላ ቀርቶ “ የስራ ተሞክሮ ያላቸው ናቸው” እያሉ የፋሺሰቶች ባሕሪያዊ ተሞክሮ እንደ ቁም ነገር አድርገው በማየት የሚሰብኩ ሰባኪዎች ይገርሙኛል። ከልምዳቸው መማር ባልቻሉት በነ ደመቀ መኮንን፤ንጉሡ ጥላሁን  እና የመሳሰሉ የወያኔ እና የኦነግ/ኦሆዴድ ፉርጎ/ተጎታቾች ላይ ተስፋ የሚጥሉ የዋሆች የጭንቅላታቸው ብስለት ደካማ ነው።

ብዙዎቻችሁ እንደምታውቁት እኔ እነዚህ ሰዎች ለ28 አመት ታዝቤአቸዋለሁ። ለ28 አመት ብቻየን (ከጥቂት በጣም በጣት ከሚቆጠሩ ጛዶቼ ጋር ሆኜ) ለበርካታ አመታት አማራ እየተጠቃ ነው እና እባካችሁ “ተነሱ” ካልሆነም “እባካችሁ የወያኔ እና የተገንጣይ ኦሮሞዎች እና ከአክራሪ እስላም ፖለቲከኞች እያንቆለጳጰሳችሁ ከእነሱ ጋር በእየ አዳራሹ እየተሞዳሞዳችሁ የአማራን ጥቃት እንዳይደመጥ ከማድረግ ተቆጠቡ” ስል እንደነበር በጻፍኳቸው በርካታ መጻሕፍቶቼም ሆነ በየድረገጾቹ ከምለጥፋቸው እና ካደረግኳቸው ቃለ መጠይቆች ስትከታተሉኝ የነበራችሁ ወዳጆቼ የምታውቁት ሃቅ ነው።

ይባስ ብለው እኔን ሲቃወሙ የነበሩት ከወያኔ እና ከኦነግ ብሶባቸው ሲቃወሙኝ እና ሲዘልፉኝ የነበሩት በሚገርም ሁኔታ  “አማራዎቹ” ናቸው።  “አፍክን ዝጋ” ሲሉኝ የነበሩት “አማራዎቹ ናቸው”። የአማራ ወጣቶችን ወደ ጠባብ ብሔረተኛነት እንዲገቡ እየገፋሃቸው ነው እያሉ ሲከራከሩኝ ነበር።  ከዚያም አልፎ ኢትዮጵያዊ ዜጋ መሆኔን ረስተው “አንተ ትግሬ ነህ አማራ ጋር ምን አገባህ እያሉ ወገኖቻቸው ሲታረዱ፤ እርጉዞች በቢላዋ ሲተለተሉ፤ እህቶቻችን ሲደፈሩ ፤ ነብሰጡሮች ወደ ገድል ሲወረወሩ፤  ዓይነ ስውራን ብላታቸው በቢላዋ ሲሰለቡ፤ እያዩ ፤እየሰሙ ያንን ከማስቆም ይልቅ፤ እኔን በትግሬነቴ ብቻ ፡”ትግሬ ትግሬ ነው” እያሉ “የመንግሥት ያለህ የሕዝብ ያለህ ድረሱልን” እያሉ ሲጮሁ የነሱን ጩኸት ዘግተው የኔንም ብዕር ዝም ለማሰኘት ያልጣሩት ነገር አልነበረም።

አሁን ቤፌስቡኩና በየ ቴሌቪዥኑ ‘አማራ አማራ’ እያለ “ምላሱን የሚያሞረሞረ” የምታደምጡት “አማራ ነኝ ባይ” ከጥቂት አመት በፊት ‘ውሃ ውስጥ የገባች አይጥ’ መስሎ ሌሎችን ሲያደራጅ እና ሲያሞካሽ የነበረ ነው’። አረ አንዳንዱ ምሁር እማ እኛ አማራዎች “ኦሮሞውን ይቅርታ እንጠይቅ ሲል የነበረ ነው” (እኔ ከነስማቸው የማውቃቸው ዘሐበሻ ድረገጽ ላይ የተጻፈ ማስረጃ አለኝ)።

 የሚያስተዛዝቡ ንግግሮች ‘በድምፅ የተቀረጹ’ ንግግሮቻቸው እስካሁን ድረስ እኔ ጋር አሉ።  አንድ ቀን አቀርበላችሗለሁ። “ትግሬ ብሎ ስለ አማራ ተቆርቋሪ” እያሉ እኔን ‘አያገባህም’ እያሉኝ የነበሩት ዛሬ ‘አማራ ፤አማራ’ እያሉ ሳደምጣቸው ጥሩ እርምጃ ቢሆንም ወደ ሗላ ተመልሼ ሳየው “የሰው ባሕሪ ምን እንደሆነ ግን ይደንቀኛል”።

አማራዎች በጉሙዝ “ሰው በሊታዎች” ተገድለው ‘ስጋቸው’ ተቀቅሎ ‘ሲበላ’ ፤ በዚህ አስደንጋጭ ዜና ተነስቼ “አማራ ምሁራንና ሌሎች ዜጎች ተነሱ ፤ ሕዝባችን ከመጠቃት አልፎ እየተገደለ ስጋው እየተበላ ነው” ብየ ስለ አስተጋባሁ እኔን በመዝለፍ “ውሸት ነው” “ጉሙዞችን ለመዝለፍ እና ኢትዮጵያን ለማዋረድ እንጂ ዜጎች ዜጎችን አይበሉም” እያሉ “አማራዎች ነን የሚሉ የኢሕአፓ አባሎች” እኔን እያዋረዱ “የአማራን ጥቃት ሊደብቁት ያልሞከሩት ነገር አልነበረም”። በዚህ ብዙ ዘለፋ ደርሶብኛል። ስለሆነም ዛሬም ሆነ ትናንት አማራው ሌላውን ከመውቀስ እራሱ መጠየቅ አለበት የምለው ለዚህ ነው!

ለ28 አመት ሲያንቀላፋ ብቻ ሳይሆን የአማራ እናቶችና አረጋውያን  የድረሱልን “ድምጽ” እንዳይደምጥ እራሱ ምሁሩና ፖቲከኛው ሲያፍነው ነበር! ያውም “ድብቁ ኦነግ መረራ ጉዲና” ፤ “ኢንተርሃሙዌው በቀለ ገርባ” እና ‘ኦነጐችን’ እና ”ሓጂ ጃዋርን” እያንቆለጳጰሱ የአማራን ድምጽ ሲያዳፍኑ ነበር፡ ራሳቸው አማራዎች!!

“ያየናቸው አማራዎች ስለ አማራ ሳይሆን ሲጮሁ የነበሩት ከግንቦት 7 ጋር ተደራጅተው ለዩናይትድ ኔሽን ተቃውሞ በሰልፍ ሲያስተጋቡ ስለ አማራ ሕዝብ ጥቃት ሳይሆን ኢሳያስ አፈወርቂ በዓለም አቀፍ ውግዘት ሲደርስበት ‘የኢሳያስን ባንዴራ እያውለበለቡ ኢሳያስን እያሞገሱ በመደገፍ “የታቀውሞ” ባንዴራ ሲያውለበልቡ ነበር”። “እሽሩሩ፤እሽሩሩ! እያሉ! የኦነግ ባንዴራ ይዘው ከተሸለሙ አገር አፍራሽ ጠላቶች ጋር እየተቃቀፉ ፕሮፓጋንዳ ሲሰሩ እና ሲያጠናክርዋቸው ነበር! ብዙዎቹ አማራዎች ናቸው። ራሱን ያሸነፈ፤ሕዝቡን ያስበላ ፤ተወቃሹ እራሱ አማራው ነው! ቢያቅራችሁም ሃቁ ይህ ነው የምላችሁ ለዚህ ነው።
  
አማራው ባስቸጋሪ ተከታታይ ቅርቃር ውስጥ የገባበት ሰሞን ስለነበር፤ እባክህ ‘ታማኝ በየነ’ እያልኩ ስጮህ “ጠላዋ እንዳማረላት ሴት” እዚህም እዛም ሲሯሯጥ ስለ ጸረ አማራው የግንቦት ሰባቱ “አንዳርጋቸው ጽጌ” በወያኔ ደህንነት ሰዎች ስለ መጠለፍ መያዝ ክስተት ቅድሚያ ሰጥቶ ለመጀመሪያ ጊዜ በኢትዮጵያውያን የስፖርት በዓል ላይ በነበረው የሞረሽ ወገኔ የስብሰባ ጥሪ “እኔ እና ዶ/ር ጌታቸው ሃይሌ እንዲሁም የታሪክ ምሁሩ ዶ/ር ሃይሌ ላሬቦ’ አማራን አስመልክቶ ንግግር እንድናደርግ ተጋብዘን ሞረሽ በጠራው በሳንሆዜ ካሊፎርኒያ ከተማ” የታየው ክስተት በጻፍኩት ዘገባ ታስታውሳላችሁ። ታማኝ በየነ እና አበበ ገላው አማራ ያዘጋጀውን አደራሽ አይተው እንዳላዩት በጎን እያዩ አዳራሹን ረግጠው “ኢሳት-ግንቦት 7 (የራሱ ድርጅት) ወደ አዘጋጀው “አጠገቡ የነበረው አዳራሽ” ተንደፍድፈው በመግባት፤ ስለ አንዳርጋቸው ሲጨነቁ የነበረው ሁሉ የጻፍኩት “ዘገባ” የምታስታውሱት ነው። ሕዝቡ አማራዊ አዳራሹን “እየረገጠ” ወደ ግንቦት 7 አዳራሽ ነበር የጎረፈው። አንዳንዶቹ “እኔም አማራ ነኝ” ማለት አሳፍሮት “እኔ ብሄር የለኝም” እያሉ የነበሩ  ‘ከዛሬ ጀምሮ “እኔም አንዳርጋቸው ጽጌ ነኝ ፤ግንቦት 7 ነኝ” እያሉ በሚገርም ሁኔታ ሲያስተጋቡ ነበር!!

ምስጋናው ልነጥቀው የማልፈልገው አንድ ነገር ግን ‘ታማኝ በየነ’ ስለ አማራ አልጮኸም ማለት ግን አይደለም። አማራዎች ከአማራ ሕዝብ እምባ ይልቅ የግለሰቦች መታሰር ጎልቶ ሲሰተጋባ እንደነበረ እና ያንንም ስቃወም መኖሬ ላስታውሳችሁ ስለፈለግሁ ነው።

የአማራ አዛውንቶች እና እናቶች መጠለያ አጥተው በየቦታው የወንጀለኛው/ኦሆዴድ/ ታጣቂዎች መጫወቻ ሆነው የትም ሲቀሩ ‘አዲስ አበባ ቁጭ ብለው” ሲዘግቡ የነበሩ ጋዜጠኞች ሲጮሁት እና ሲዘግቡት የነበረው ስለ አማራ ሳይሆን ስለታሰሩት ጋዜጠኖች ጓዶቻቸው ነበር ቀልባቸው የተሳበው። ዛሬም ጥቂቶች ካልሆኑ ከዚያ ግብዝነታቸው የተላቀቁ አይመስሉም።

ዛሬ ለፋሺሰቶቹ ለነ አብይ እና ለነመለስ/ደብረጽዮን ሕገ መንግሥት የተምበረከኩት ድረውኑም ወያኔ ሲፈታቸውና ሲያስራቸው የነበሩ ‘ወጣቱ ከፖሊስ ጋር ሲተናነቅ’ እነሱ ግን  “መታሰር የለብንም፤አድማ አልጠራንም” እያሉ ሲሞዳሞዱ የነበሩ የዛሬዎቹ “ነጭ ባንዴራ አውለብላቢ” ፖለቲከኞች እና የኪነት ሰዎች ፤ የአማራ ሕዝብ እየተጠቃ “የመንግሥት ያለህ” እያለ ሲጮህ አንድም ቀን “ሰላማዊ ሰልፍ አልጠሩም (ኢንጂኔር ሃይሉ ሻውል ብቻ ሰላማዊ ሰልፍ ጠርተው፤የአማራን መከራ እያወሱ፤ተቃዋሚዎችና ጋዜጠኞችን እየወቀሱ፤ ስለ አማራው የቆሙ ብቸኛ ፖለቲከኛ ነበሩ !!! ነብሳቸው በገነት ያኑርልን!!!!) (አንዳንዶቹ ምናልባት ስለ አማራ ችግር ካወሱ እጅግ ኢምንት ነበር) ። ዛሬ ሕዝቡ ከድጡ ወደ ማጡ ገብቶ ከነጭራሹ ዛሬ እንደምታውቁት ችግሩ ቀጥሎም አያለ “ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ” ብቻ ካልሆነ አንድም የፖለቲካ ድርጅት ወይንም የኪነት ሰው “ሰላማዊ ሰልፍ” ጠርቶ ይህ ስርዓት አልተቃወመም፤ መግለጫ አልሰጠም። በሚያስቅ ፍጥነት ብርሃኑ ነጋ የአብይ አሕመድ ተሿሚ ከንቲባ ሆኖ አገር ጉድ እያሰኘ ነው! ተራርቀው የነበሩት የወያነ ትግራይ አመራሮች “ትግራይ ተከብባለችና እንሰባሰብ” ብለው እንደታረቁት ሁሉ፤ ዛሬም አብይ አሕመድ “የቀድሞ የወያኔ አጋሮች የነበሩት እነ ብርሃኑን” እየጠራ ለከንቲባነት ሹሞኣቸዋል ይባላል።

ሌሎች ተሻሚዎችም ሊኖሩ ይችላሉ፤ ለምሳሌ በሚገርም እና እንቆቁልሹ ባልገባኝ ሁኔታ ያ እኔ ጅግና ብየ ጽፌ በድረገጾች ሳደንቀው የነበረው አባትየው “ትግሬ ነህ” ሲሉት አይደለሁም ብሎ አባቱ ለዘረዘሩለት የትውልድ ሐረጋቸው አንዳችም የመልስ ምት ሳይሰጥ ቆይቶ (እኛ ትውልዳችን እገሌ እገሌ ሳይል) የነበረው ኮለኔል ደመቀ ዘውዱ የተባለው የድሮ የወያኔ ታጋይ በድንገት ጀኔራል አሳምነው ጽጌን “ከሃዲ” ብሎ በዘግናኝ ቃል ሲወርፋቸው መስማት እውነት የዚህ ግብዝ ሰው ውረፋ ከመጠን በላይ የማይገባ በመሆኑ ለዝርዝሩ በሰፊው እመለስበታለሁ። ይህ ዘለፋ እንደ ብርሃኑ ነጋ ኮለኔል ደመቀ ዘውዱም ሊያሾመው ይችላል የሚል ግምት አለኝ።

ይህ ግለሰብ የአማርኛ ልሳኑን ትግርኛ እስኪያሰመስለው ድረስ የወያኔ ታጋይ ሆኖ የወያኔ መዝሙር እየዘፈነ ፤ የኢትዮጵያን ወታደር ያውም “አማራውን” በጥይት ሲገድል የነበረ ሰው ለወልቃይት እታገላለሁ ስላለ ይቅርታ አድርገንለት ስናበቃ “አሳምነውን” “ከሃዲ” ብሎ በከባድ ዘለፋ መዝለፉ “ክሕደት”፡ ምን ማለት እንደሆነ ካልገባው እንደዚያ ከቀጠለ አንድ ቀን በሰፊው እመለስበታለሁ። ለዛሬ አልፈዋለሁ። ዛሬ ለስድቡ ምላሽ ስንሰጥ አርሱም ሀነ አድናቂዎቹ ቅር ሊለው/ሊላቸው/ አይገባም፡ እራሱ ለስድብ ጥሪ በር ከፍቷልና።

 “ፋሺሰት፤ ጡት ነካሽ፤ ከሃዲ፡ እብድ” የሚሉ ቃላቶች በፋሺስቶቹ እስርቤቶች ስቃይ የማቀቀው “በጣም ብልህ፤ የሚናገረው የሚያውቅ፤ ድብብቆሽ የማያውቅ፤ ግልጽ ጥርት ያለ አርበኛ እና አገር ወዳድ ወሎየው ጀኔራል አሳምነውን” አማራ ነን በሚሉ ባልተገረዘ ምላሳቸው በነዚህ ቃላት ሲዘለፍ መስማት አማሮቹ ምን ያህል ደደብነት እንዳሸነፋቸው የሚያሳይ ምልክት ነው።

አሳምነውን ገደሉት ስሰማ ምክንያቱ ባላወቅኩት ምክንያት “ስቅስቅ” ብየ አልቅሻለሁ። የገዛ ልጁ ቃለ መጠይቅ ስታደርግ ሰምቻት የንግግሯ ‘ጥንካሬ፤ ሐዘን፤ ጨዋ የሆነ የዕውቀትዋ ምጥቀትና ጥልቀት’ ውስጤን ሰርስሮ አሳዝናኝ ዳግም እምባ ተናንቆኝ ሙሉውን ለማድመጥ እያቆምኩ ነበር ያደምጥኳት።

 ይህ የብዙዎቹ የአማራ ምሁራንና እነሱን የሚከተሉ ያልተማሩት ክፍሎች የደደብነት በሽታ ዛሬ አልተጀመረም። ባለፉት አማታት በተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶች እና በዜና ማሰራጫ ድርጅቶች (ውስጥም ውጭ አገርም) የተሰገሰጉት አብዛኛዎቹ አማራዎች ነበሩ። ይባስ ብሎ ዛሬ ደግሞ አማራ ሆነው ስለ አማራ ደንታ የማይሰጠውን አብይ አሕመድ የተባለ የአፓርታይዱ አዲስ መሪ በመደገፍ “የኪነት ሰዎች” ተብየዎቹ አሰባስቦ  አሳፋሪው “ደበበ እሸቱ “ስለ አማራ መንገላታት እና መፈናቀል  ሳይጨነቅና መግለጫ ሳይሰጥ” አፈናቃዩን ስርዓት “እንደግፋለን” ብሎ “አድርባይ የኪነት ሰዎቹን” ጋብዞ ከበስተጀርባው ’’አምቧሻ ያለው የወያኔን ባንዴራ” አስለጥፎ መግለጫ ሲሰጥ እውነት ይህ ሰው “አማራ ነው?” ያስብላል።

ስለሆነም ነው አማራው ዛሬም ከራሱ ሰዎች ሌላ ጠላት የለውም የምለው። የአማራ ጣለቶች ጓዳውን እንዲሰረስሩት የበሩ መጋረጃ ገላጭ የሆኑት ሌሎች ሳይሆኑ እራሳቸው አማራዎች ናቸው። ትግሬውን አታዩም እንዴ? የራሱን በር ለሌሎች ከፍቶ የገዛ ሕዝቡን በሌላ ሲያስመታና ሲደፈር አይታችሁ ታውቃላችሁ? አማራው ግን የራሱን ሕዝብ በወረበሎች እንዲደፈር ያደረገው እራሱ አማራው ምሁር እና ፖለቲከኛው/ጋዜጠኛው ነው።ከዚያ ሳይማሩ ዛሬም እዛው ረግረግ ውስጥ እየዳከሩ እያየሁ ነው። አንዳንዱ ጋዜጠኛ ተብየው እማ በማያውቁት ሙያ መርማሪ ሓኪም ሆኖው አሳምነውን “የሕሊና ሕመምተኛ” ነው ብለው ደምድመዋል። የሚገርሙ ማፈሪያዎች! ያንን ለማሳመን ብዙ እየተሰራ ነው።

አንዳንዶቹ ከቅን እሳቤ የተነሳ “የገበያ ግርግር ለሌባ ያመቻል” እንዲሉ ነውና አማራን እንደ ‘ሣንዱዊች’ መሀል አድርገው ለማጥቃት ያሰፈሰፉ ኃይሎች ሠርግና ምላሽ ሆኖላቸዋል” ይላሉ። ያ ግን ሰርስረን ስንሄድ “ድሮውኑም” የአማራዎቹ “ክቡር ገዳም” በአማራዎቹ በራሳቸው አድርባይ ምሁራን እና ተቀጣሪዎች ተደፍሯል። የተከደነ የለም። መከደን እና መከበር እንዳለበት ሲወተውት የነበረው ጀኔራል አሳምነው ጽጌ ለዚያ ጥቃት ተጠቂ ሆኗል። በሚያሳፍር ሁኔታ አማራዎች አብይ የተባለ አጭበርባሪ “ሳዓረ መኮንን ጀግናችን ነው” ስላላቸው አማራዎቹም አርሱን አድምጠው ያ ጸረ ኢትዮጵያ የወያኔ “ጉሬላ” ጀግና ብለው ሲያሞግሱት ስሰማ ይህ ምሁር ነኝ ባይ ክፍል እና ጋዜጠኛ ተብየው ወደ ቁልቁለቱ እየሄደ እንደሆነ ማሳያ ነው። የሚገርመው አገር የገደሉት ሁላ ምንም ማስረጃ ሳያዩላቸው እነ ሳዓረ መኮንን እነ አርከበ ዐቑባይ ጅገኖቻችን እያሉ ሲያሞካሽዋቸው “ጀግና” ምን ማለት አንደሆነ በቅጡ የወላጆቻቸው “ጀግኖች” ምን ይመስሉ እንደነበሩ ታሪክ የመረመሩ አይመስሉም። ገዳዩን የሚያሞግስ ሕዝብ እንደ ኢትዮጵያ አላየሁም

በዚህ አልተገደቡም። አማራ ነን የሚሉ ሚዲያዎችም በረሃ ትግራይ ውስጥ ብዙ የሰብኣዊና ብሔራዊ ወንጀል የፈጸመና ያስፈጸመ አርትራዊው ጻድቃን ገብረተንሳይ የሕዝብ ፈዋሽ እና መካሪ አድርገው በየቀኑ ሲጋብዙት ማየት ሆድ ቁርጠት ይለቅብኛል። ትግሬው ሲታጠቅ መታጠቁን የሚያሞግስ “አማራው በአሳምነው ጽጌ ሲታጠቅ ግን፡ “የሚቃወም” ፈጣጣ ጎጠኛው” የወያኔው  ጀ/ጻደቃን ገብረተንሳይ ስለ አገሪቱ ፖለቲካ መፍትሄ ፈልግልን ብለው በየ ቲቪው እየጋበዙ ሲያሳዩን እጅግ ከመገረም አልፌ ምን እንደምል ይገርመኛል። ነብሰ ገዳዮች እና አገር ገዳዮችን ተክለሰውነት ለማቆነጃጀት እየተጓዙበት ያለው መንገድ የሚገርም ነው!!

በመጨረሻም በዚህ ልደምድም፤
የሰሞኑ የባሕር ዳሩ ክስተት ፤ ትግሉ እና ግጭቱ አስቀድሜ እንዳልኩት “በኣፓርታይድ የባንዳዎች ቡድን መካከል እና “ለ28 አመት የአማራ መከበብና ውርደት ታይቶት “አንዲት ሰኮንድም” ብትሆን ‘ይዋል ይደር’ የማይባል መራራ መከላከል ተደርጎ የአማራውን ክብር አስከብረን እያደገ ያለው የመሬት ነጠቃውና ከበባውን ማስቆም አለብን” ብሎ ባለው “ዳግማዊው በላይ ዘለቀ” መካካል የተከሰተ ጥልቅ የመስመር ልዩነት ነው። በዚህ አጋጣሚ “አብይ እና ሰዓረ መኮንን” ወደ ባሕር ዳር ሄደው “አሳምነውን ለማሰር” ሲንደፋደፉ  እራሱን ለመከላከል ሲል “የአብይ ባንዳዎችንም” አብሮ መግደሉንም ከስፍራው የነበሩ ምንጮችም ይናገራሉ። መንግሥት የሚየቦካው ብቻ መስማት አይኖርብንም። ከኔ ጋር ያለው የሳንሆዜው ወጣት የሄኖክ የሺጥላ ዩቱብ ዘገባ ብታደምጡ ጠቃሚ ነው።

ባንዳ ባለስልጠኖችም ሆኑ የነሱ አድናቂ ጋዜጠኞች እና ፖለቲከኞች “ነገሩ በውይይት፤በወያኔ ቃላት “ምይይጥ” ነገሮችን መፍታት ይቻል ነበር እያሉ “የሰለጠኑ የምይይጥ ዲሞክራቶች” አሳምነውን የምይይጥ ሰው አይደለም እያሉ እርሱን ለማጠልሸት ሲሯሯጡ ሰምተናል። አንባቢዎቼ ማወቅ ያለባችሁ “በዘር የሚያስተዳድር አፓርታይድ ስርዓት” በተለይም በዘር የተደራጀ መንግሥትና በፍልስፍናው የታነጹ የአፓርታይድ አሽከሮች “በምይይጥ” የሚሰሙ አይደሉም። በምይይጥ ነገር የሚፈቱ ቢሆን እማ አብይ አሕመድ እስክንድር ላይ “ጦርነት” አያውጅም ነበር!!

 ዛሬም ነገም ለብዙ አመት እንደተናገርነው፤ “ፋሺስታዊው አፓርታይድ” በምይይጥ/ በውይይት አያምንም። ባሕሪው አይደለም። ለዚህ ነው ምክንያት አድርጎ ዜጎች እየለቃቀመ እስር እያጎራቸው ያለው (ከዚያ በፊት 3000 የአዲስ አበባ ወጣቶች ሰብስቦ እስር ካስገባ በሗላ “አብይ አሕመድ” ስለ እነሱ የተናገረው ታስታውሳላችሁ። ከዚያ ድንፋታና ውሸት ሊወጣ ባሕሪው አይፈቅድለትም። የአብይ አሕመድ ተገለባባጭ እስስት ባሕሪው እና ውሸታም ፈቱን አላጠናችሁትም? የባሕር ዳር አሽከሮቹም ያው ናቸው።

የአፓርታይድ ፖለቲካ እየተማረ ያደገው የአማራ ምሁር “ምይይጥ” የሚባል ማሞኛ እና “ዲሞክራሲ” የሚባል ጣፋጭ ግን መርዘኛ ‘ከረሜላ’ እያኘከ “ሕሊናው” ለ28 አመት በማይጨበጥ ሕልም ተበውዟል። ለዚህ ነው እየተገለባበጠ ራሱንም ሕዝቡንም ለአደጋ እያጋለጠ ያለው። ከእስክንድር ነጋ በላይ “ለምይይጥ” እራሱን ያዘጋጀ ሰው አለ? ውጤቱ ግን ጦርነትና እስራት ነው እየተሰነዘረበት ያለው።

አማራ ሲከበብና ሲዋረድ ጀ/አሳመነውን ለማውገዝ እንዲመቻችሁ “በምይይጥ’፤ በመተሻሸት መፈታት ይችል ነበር” …ወዘተ የምትሉት የቅዥምብራሞቹ ምሁራን ቅዠት የምታስተጋቡ “ገራገሮች” ካሁኑኑ ገርዙት/አቁሙ። ከሰርዓቱ ጋር ጋብቻ የገቡ ብቻ ናቸው “የምይይጥ” ቀለበታቸው እንዳይፈርስ የሚጥሩት። እኛ ከስርዓቱ ጋር ቃል ኪዳን እና ጋብቻ እስካልፈጸምን ድረስ አማራው ጥቃት ሲፈጸምበት “በምይይጥ” የምንጓዝበት አስገዳጅ ቃል ኪዳን አላሰርንም ማለት አለባችሁ። ብዙ ምይይጥ ተደርጓል። አልሰራም። እስክንድ እንኳ ምይይጥ እንዳያደርግ ታግዷል። ለባለ ቃል ኪዳኖቹ ብቻ ነች ኢትዮጵያ የተሰጠቺው። ለኦሮሞው አብይ ያልተገዛ “ምይይጡ” እስር  ነው። ተው ተብሎ፤ ተመክሮ አልሰማም ካለ “የምይይጥ” ግዴታ የለንም እና በማንኛውም መንገድ አፓርታይዱን ማስወገድ የተፈጥሮአዊ ሕግጋት ነው። በትልቅ ፊደል ለማንበብ(ኢትዮጵያን ሰማይ ድረገጽ ጉጉል አድርጋችሁ አንብቡ Ethiopian semy) አመሰግናለሁ ጌታቸው ረዳ።