Saturday, August 15, 2020

የፌስ ቡክ “እስርቤት” ዕገዳ እና ውሳኔ” የቂመኞች ማርኪያ ሜዳ ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay) Friday, August 17, 20202



የፌስ ቡክ “እስርቤት” ዕገዳ እና ውሳኔ” የቂመኞች ማርኪያ ሜዳ
ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay)
Friday, August 17, 20202

በቅርቡ ወዳጄ ሰዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው ለ 20 ሰዓታት ከፌስ ቡክ አግደውት ነበር። ሲያግዱት ደግሞ እንደ አምባገነን እንደ “ኢትዮጵያ አምባገነን ፖሊሶች”  “ታግዳሃል/ታስራሃል” እንጂ የማሳገጃው ምክንያት አይሰጥም። ፌስቡክ በሚሰጠው አጭር ውሳኔ ብዙ “ወቀሳ ቢደርስበትም” በዶላር ብዛት የታሸገው ጀሮው ወቀሳዎችን ከመጤፍ አይቆጥራቸውም። ከዚያ አልፎ የማን አለብኝን “የሪፓቢካኑ ተከታይ የኢምፔሪያል ሕሊና” ያሳበጠው ቢሊዮነሩ “ፌስቡክ” የፌስቡክ ተሳታፊዎችን “ፕሮፋይል” እና “ሱታፌ” ለተለያዩ ድርጅቶች እና ለመንግሥት አሳልፎ በመስጠት በመብት ረጋጭነቱና ሰላይነቱ ይታወቃል። ፌስቡክ “ፕራይቬሲ” አያውቅም፤ የመጻፍ ነፃነት ቢፈቅድም ባንዳንድ ባሕሪዎቹ “የተወጣለት አምባገነን” ነው።

የፌስቡክ ተሳታፊዎቹን ሱያግድ ማብራሪያ ካለመሥጠቱ የተነሳ እገዳ የተጣለባቸው ሰዎች ለምን አንደታገዳቸው “በመዋዠቅ” ለመታገዳቸው ምክንያት ፍለጋ እንዲኳትቱ የሕሊና ጫና ይጥላባቸዋል። ይህ “የፌስ ቡክ እስርቤት” በስፋት ያልተፈተሸ አምባገነን ነው።

ሰዓሊ አምሳሉ በፌስቡኩ ላይ የጻፈው ሰፊ የቅሬታ ትችት ሳነብብ ለምን እንዳገዱትም አይገልጽም። ይህ እጅግ በሰለጠ ዓለም መወገዝ ያለበት አምባገነናዊ ባሕሪ ማቆሚያው የት ይሆን የሚል ጥያቄ ይጭርብኛል። ከፌስ ቡክ  ዓለም መወገድ ያለባቸው ሰዎች የሉም አልልም። ግን ሲወገዱ ምክንያት መገለፀጽ አለበት። በደፈና የፌስቡክ ሕግ ተላልፈሃል እና ታግደሃል የሚል ውሳኔ ከሕግም ከሞራልም ተቀባይነት የለውም። ሰው ገድላሃል፤ ስለሆነም ዕድሜ የፍታሕ ተወስኖብሃል’ ስትለው፤ የት የገደልኩት ብሎ ሲጠይቅ “መልስ ካልተሰጠው” በምን መልኩ ነው ይህ ፍትሕ ነው ተብሎ ቅቡልነት የሚኖሮው?

አምሳሉንም እንዲሕ ነው ያደረጉት። ፌስ ቡክ የአምባገነኖች መንግሥታት ቡችሎች እና የፖለቲካ ቂመኞች የማጥቂያ መንግድ እያደረጉት ነው። ካሁን በፊት ገጣሚ ሔኖክ የሺጥላ ለአርበኛው ብ/ጄኔራል አሳምነው ጽጌ እናት እና ታዳጊ ልጆችን መጦርያና የሓዘን መደበሻ ገንዘብ እንድናዋጣ (የጎ ፋንድ ሚ) የመረዳጃ ጥያቄ በፌስቡክ ለጥፎት ወዲያውኔ የፖለቲካ ምቀኞች ለፌስቡክ ጽፈው ለተወሰነ ወቅት አሳግደውት ነበር። ይህ በጣም የሚያስቀይም የኢትዮጵያውያን ባሕሪ በፌስቡክ ላይም እየተንጸባረቀ አስቸጋሪ እየሆነ ፌስቡክም አምባገነናዊ ባሕሪውን እየተጠቀመ ምን ሳያጣራ እና የማሳገጃ ምክንያት ሳይገልጽ በዘፈቀደ “እያገደ” የሰዎችን መብት እየጣሰ ነው። በአምሳሉ ገብረኪዳን ላይም የሆነው ይኼው ነው።

በቅርቡ አብይ አሕመድ ከመጣ ጀምሮ የሱ ደጋፊዎች እና ሌላ ቡድንም ብቅ ብሎ “ክምንም ፖለቲካ ያልወገንን ነን” የሚሉ ቀባጣሪ የሕግ እና የ “አይ ቲ” (Internet Technology) ኢንጂኔሪንግ ሙያ አለን የሚሉ የአገራችን ሁኔታ ምን እንደሆነ በቅጡ ያልገቡበት የቀለም አዋቂዎች ግን “የፖለቲካ ማሃይሞች/ደናቁርት” እነሱ የማይወዱት አንድ ቃል ባዩ ቁጥር፤ ወይንም አንድ ሓረግ ባነበቡ ቁጥር “የፍጹም ሞራል ባለቤቶች” በመመስል ወደ ፌስ ቡክ እየጻፉ የሰዎችን የመጻፍና የመናገር መብት ያሳግዳሉ። የውሾች በሕሪ በቅንነት የተመሰረተ ሳይሆን “ውሻ ላመሉ “ሊጥ” ይልሳል ነው።

ይህ ደግሞ ኢትዮጵያውያኖች በፖለቲካ ሰብበ ሰውን የሚገድሉ ምቀኝነትና ተንኮል የተካኑ ስለሆኑ፤ የፖለቲካ ድርጅት ደጋፊዎችና እንዲሁም የፖለቲካ መሪዎች ነን የሚሉ በሚደግፉዋቸው  ምሁራኖቻቸው በኩል የሚቃወሙዋቸውን ሰዎች ከፖለቲካው ሜዳ ለማስወጣት “እርስ በርስ ተጠራርተው ተመራርጠው በመደራጀት” ወደ “ኢመፔሪያሊያዊው ፌስ ቡክ” የማይመችዋቸውን ሰዎች ክስ እየጻፉ እነሱን ለማስወገድ ተደራጅተው አንዳንድ ሰዎች በማሳገድ ላይ ናቸው። ይህ ደግሞ “ጥላቻን በሚሰብኩት” ላይ ብቻ ነው የምንዘምተው ሲሉ ታደምጧቸዋላችህ። የሚገርመው ግን፤ ምን አንደሚሰሩ ወይንም ማንን እያሳገዱ እንደሆነ፤ለምንስ እንዲያሳግዷቸው እንደፈለጉ ‘ተጨባጭ” ምክንያታቸውን ለሕዝቡ “የጽሑፍ ይፋ ዘገባ” አያቀርቡም። ለፌስቡክ የጻፉትን የማሳገጃ አቤቱታም በማን ላይ ውሳኔ እንደተሰጠ በድረገጾች ላይ ለሕዝቡ ይፋ አያደርጉትም።

ሊያደርጉት የማይፈክጉበት ምክንያትም በምቀኝነት የተካኑ፤ግልጽነት የሌላቸው በመሆናቸው ያንን ይፋ አድርገው ውሳኔ የተላለፈበት ሰውም መብቱ ተጠብቆለት የመከከራከሪያ መድረክ አይከፍቱለትም። በምንግሥቶቻችን የለመድነውን ባሕሪ በቡድንም እየተላለፈ ነው። ለዚህ ነው በዚህ ዘመቻ የተሰማሩት አንዳንዶቹ ማንነታቸው የምናውቃቸው ቢሆንም ጥርጠሬ የሚጭርብን።ለምን አንደተመሰረቱ በሚዲያ ሲጋበዙ  “የጥላቻ ንግግር ለማስወገድ ተቋቁመናል” ብለው “ይለፍልፉ”  እንጂ ለፌስ ቡክ የሚጽፉት አቤቱታ በማን እና ለምንስ ምክንያት እንደሆነ ግን በይፋ ለሕዝብ አያቀርቡም። ትልቁ ነጥብ እዚህ ላይ ነው!

ኢፔሪያሊያዊው ፌስቡክም የሰው መብት አክብራለሁ ብሎ ቢወዛወዝም “ብዙ ሰዎች ከፌስ ቡክ የተወገዱ አሉ”። ግን ምክንያት “አይገለጽላቸውም።” የሚገለጽላቸው ምክንያት አስቂኝና አምባገነናዊ በሆነ ዓረፍተ ነገር “የፌስ ቡክ” ሕግ ተላልፈሃል” የሚል አጭር ፤ ድፍን ያ፤ “የአምባ ገነኖችን” ውሳኔ ብቻ ይለጥፍልሃል። የተላለፈከው ሕገ ደምብ የቱ ነው? ብልህ ስትጠይቅ መልስ አይሰጡም።

ይህ ውሳኔ የሚሰጡት ዳኞች የሕግ ብስለት የሌላቸው የአይ -ቲ ባለሞያ የፖለቲካ ደናቁርት ናቸው።ይህ ዴፓርትመንት “User Operation” በመባል ይታወቃል። አንዳንዴም በሚገርም ሁኔታ ለምን እንደታገድክ ጠይቀሃቸው ከረዘመ አመት "ተሎ" ከመጣ በ5 ወራት መጠበቅ አለብህ። ያ ሁሉ ጠብቅህም የሚሰጥህ መልስ

“ Your account was disabled in error. We have reactivated it and you should be able to access it again. We sincerely apologize for the inconvenience. Please let me know if you have any further questions or issues.
Thanks for contacting Facebook,”

 የታገድክበት ምክንያት በስሕተት ነው ብሎ መለስ ይሰጠሃል። ይህንን መልስ ለማግኘት አመት ወይንም ወራት መጠበቅ አለብህ። ብዙውን ጊዜ መልስ የሚሰጥሕ “ሮቦት” ሰው ሰራሽ “ባምቡላ” ነው መልስ የሚሰጥህ፡ ዕድለኛ ከሆንክ ደግሞ ወራት ጠብቀህ ከላይ የምታነቡትን መለስ ታገኛላች።

ለማንኛወም ማገጃ ተሰጥቶህ ወደ ፌስቡክ ዕስረቤት እንድትታሰር/እንድታታገድ የሚያደርገዋችሁ ምክንያቶች ብዙ ቢሆኑም “ፌስቡክ” ኢትዮጵያ ተቃዋሚዎችን ለማጥቃት ምቹ የአምባገነኖች ጫካ እየሆነ ነው።
ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay)