Wednesday, November 20, 2024

ጎንደሬዋ የwelfare Queen በጎንደር ከተማ ጌታቸው ረዳ 11/2024 Ethiopian Semay

 

ጎንደሬዋ የwelfare Queen በጎንደር ከተማ

ጌታቸው ረዳ 11/2024

Ethiopian Semay

ከባልዋ አብይ አሕመድ ጋር ተጣልታ ወደ አሜሪካ በማቅናት አሜሪካ ውስጥ ውሽማ ይዛ ስትኖር ነበረች (የሴራ ዕርካብ የደም መንበር የሚለው የያየሰው ሽመልስ መጽሐፍ አንብቡ) የሚባልላት በአሜሪካና በኢትዮጵያ በግብር ከፋይ ዜጎች  የሥራ ማመልከቻ ሳታገባ ሥራ ሳይኖራት  የሚሊዮነሮች ኑሮ እየኖረች የምትንደላቀቀው welfare Queenዋ “ዌልፈር ኵዊንዋ” <<ዝናሽ ታያቸው>> ዛሬ ጎንደር ከተማ በመጎብኘት በኩሊዎቿ አስተናጋጆች በኩል ካባና ዳንኪራ ዕልልታና ሆሆታ ሲደረግላት ሳደምጥ ከሁን በፊት አዳነች አበበ በአዲስ አባባ ውስጥ በትግሬዎች ላይ የጅምላ እስራት ባጸደቀችበት ወቅት( ፎቶውን ተመልከቱት) መቀሌ ከተማ ስትሄድ የትግሬ አባ ሰላማ ቀሳወስት እየሰገዱ መስቀል ይዘው ሲሰግዱላትና የትግራይ ሴቶችም በዕልልታ እየጨፈሩ ፎቶ ላይ የምታዩት የለበሰቺው ጥንታዊ ጥለሽ የተጠለፈበት የትግሬ ዙርያ አለበስዋት። ለሺመልስ አብዲሳም እንዲሁ።

የአዳነች አቤቤ ዕድልና የሺመልስ አብዲሳ ትግራይን የመገብኘት ዕድል ሳይጎኝ የቀረው አብይ አሕመድ ነበር።እሱም ለትሕነግ መሪዎች እባካችሁ በፈጠራችሁ እለምናለሁ ትግራይ መጥቼ እንድጎበኝ ፍቀዱልኝ ብሎ ሲለምናቸው “አንፈቅድልህም አሉት” (አትሳቁ እውነት ነው - ይህ እራሱ የተናገረው ነው።በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ አንድ መሪ እራሱ በሚያስተዳድረው ክ/ሀገር ግዛት ውስጥ ለጉብኝት ፈቃድ ሲለምን እና ሲከለከል በታሪክ የመጀመሪያ ማፈሪያ መሪ ነው ብየ ካሁን በፊት የጻፍኩትን አስታውሱ።ለታሪክ እንዲዘገብ ዘግቤዋለሁ)።

ሚሰቱ ደግሞ ዛሬ ጎንደር ከተማ ስትንሞላቀቅ ዋለች አሉ።ካችአምና ይመስለኛል ባልዋ አብይ አሕመድም ጎንደር ሁለት ጊዜ ሲፈነጥዝባቸው ዳንኪራ፤ ጃኖ እና ካባ የሚያለብሱትና የሚሰግዱለት ኩሊዎች አላጣም። ያኔ ጎንደሬዎችን ስለተቸሁ ባንዳንድ ጎንዴሮዎች ስድብ ተችሮኛል።

ጎጃም ላይም እንደዚሁ ሺመልስ አብዲሳና አብይ አሕመድ እየተመላለሱ ሲጎበኙ የተለመደው ካባና ዳንኪራ ተችሮአቸዋል።

ታስታውሱ እንደሆን አብይ አሕመድ ለአማራው ዋነኛ ጠላት መሆኑንና “አኖሌ” ሃውልት ሲቆም መሪ እንደነበር ቢታወቅም ለመጀመሪያ ጊዜ ባሕርዳር ሲጎበኝ ሕዝቡ አዲስ ለውጥ አዲስ መሪ መጣ ብሎ በተስፋ አዳራሽ ውስጥ ተሰብስቦ ከተሰብሳቢዎቹ የቀረቡ የበሰሉ ያስተሳሰብ እና የአቤቱታ አቀራረብ ምጥቀት የታየባቸው ሕሊናዎች እንደነበሩ ታስታውሳለችሁ። አማራዎች ለ27 አመት በእንደዚያ ያለ ለመስማትም ለማየትም በሚዘገንን የጭካኔ ግፍ ተፈጽሞባቸው እያለ፤ ብሶታቸውንና ውስጣዊ ቁጣቸውን ተቆጣጥረው ሰብሰብ አድርገው በስሜት ሳይሸነፉ ምራቁን የወጠ ንግግሮችን እና ጥያቄዎችን ለባንዳው ለአብይ አሕመድ ሲያቀርቡለት የመለሰው መልስ ታሪክ ነውና እንደገና ላስታውሳችሁ።

እንዲህ በሎ ነበር፡

<<አማራ አማራ” የምትሉት ነገር ትቼ..የኢትዮጵያን ነገር እንዲህ እያንገበገባችሁ መልሳችሁ አማራ አማራ ስትሉ ታፈርሱታላችሁ! “አማራ አማራ የተባለውን ትቼ፤ ለሁላችን ፍትሕ ያስፈልገናል፤ዲሞክራሲ ያስፈልገናል፤ኢትዮጵያውያን በሕግ የምንዳኝበት ሥርዓት የሚል ከሆነ እቀበላለሁ። “የኛ ብቻ” የሚል እንዳይሆን።>> ሲል እንደመለሰላቸው ታስታውሱታላችሁ።

አብይ “አማራ አማራ እንዲህ ሆኗል፤ ታርዷል፤ ግፍ ደርሶበታል፤ የዘረኛው ሕገመንግሥት ዋና ኢላማ ሆኗል፤… የሚል አቤቱታ ክስ አልተመቸውም”። እነ ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያምም አማራ የሚል ስም ላለማንሳት “አሮሞ፤ትግሬ….” ይሉ እና ከዚያ አማራ ላለማለት (ሆን ብየ ስሙን ላለመጥራት የዘለልኩት) እያሉ ራሳቸው በብዕራቸው እንደሚጽፉት ሁሉ አብይ ደግሞ “አማራ፤አማራ” የምትለወዋን ስም እና ብሶት አትመቸውም ነበርና አማራ አማራ አትበሉ እያለ፤ ትናንም ዛሬም አብረው ከባንዳዋ ሚስቱ ኦቶዶክስ፤ ኦርቶዶክስ፤ አማራ፤ አማራ የሚባል ሲሰሙ ይጠሉታል፤ያቅለሸልሻቸዋል።

እንዲህ ላለ መሪና እንዲህ ላለ የአማራ ጠላት ባለቤት ለሆነቺው ባለቤቱን ነው ጎንደሬዎችም ሆኑ ጎጃሜዎች ካባና ጃኖ የሚያለብስዋቸው።

ሺመለስ አብዲሳ

ሺመለስ አብዲሳ ማነው ትሉ ይሆናል (ጊዜው ሲያልፍ እኔ ሞቼ ይህ ጽሑፍ ከመቶ አመት በሗላ ሰዎች ሲያነቡት ለማስገንዘብ ያህል)፤- ሺመልስ አብዲሳ የሸዋ ኦሮሞ ነው።ኦሮሙማ ተብሎ ወያኔና ኦነግ በሰየሙት ከሌሎች ነገዶችና አካባቢዎች የተነጠቀ ሰፊ ግዛት “ፕረዚዳንት” ነው። በሚቀጥለው ንግግሩ ይታወቃል፡

<<ነፍጠኞች የሰበሩን ቦታ ላይ ነፍጠኞችን ሰብረን ታሪክ ሰርተን የሀገሪቱን ትልቅ ከተማ ለመቆጣጠር ለደረስንበት ለተሻገርንበት ወቅት እንኳን አደረሳችሁ>> ኦሮሞዎች ኢረቻ በዓል ሲያከብሩ አደስ አባባ ውስጥ ለተሰብሳቢው የተናገረው።

በዚያው ሳይወሰን፡ሩዋንዳ ውስጥ ሁቱ በቱትሲዎች ላይ የተደረገው የጭፍጨፋ ወንጀል ዓይነት ሻሸመኔ ከተማ ውስጥም ኦሮሞ ያልሆኑት እንደ የጃማይካ ንግድ ቤቶችና መኖርያ ቤቶች፤ ጽ/ቤቶች እና በተለይ የአማራዎች ንግድና መኖርያ እንዲሁም አማራዎች እየተለቀሙ ሲዘረፉ፤በአክራሪ ኦሮሞ ቄሮዎች ሲታረዱና ሲደበደቡ የከተማው ከንቲባ የነበሩት አቶ ተማም ሑሴን ሁኔታው ከቁጥጥርቸው ውጭ ሲሆንባቸው ለሺመልስ አብዲሳ ደውለው ከተማዋ እየነደደች ነው በማለት ዕርዳታ እንደሚፈልጉ ሲደውሉለት፤

አንዲህ አላቸው፤

<<ገብተህ ተኛ አላቸው>>

እንዲህ ያለው ዘር አጥፊ (ጀነሳይደር) ጎጃም ባሕርዳር በተመላለሰበት ወቅት ዕልልታ እየተደረገለት ተደጋጋሚ የካባ ሽልማትና  የዳንኪራ ተርዒት ግብዣ ተደርጎለታል። 

ካሁን በፊት የጴንጤ ዘማሪዋ ዝናሽ ታያቸው ብምትወለድበት ክ/ሀገር ጎንደር ደርሳ በሄደችበት ወቅትም “ዳቦ በልታችሁ ባለቤቴም አክብራችሁ ፀጥ ብላችሁ በሰላም ተገዙለት” ዓይነቱ ንግግር ተናግራ መሄድዋን እናስታውሳለን።

ዛሬ ደግሞ በዘበኛዋ ተመስገን ጥሩነህ እየታጀበች ጎንደር ለሽርሽር ሄዳ  ጎንደሬዎች በሰላማዊ ሰልፍ ከተማዋን ቀውጢ ከማድረግ ይልቅ “ዳኒኪራና የተለመደው ካባ” አልብሰው ኩሊነታቸው ያስመሰከሩ ጎንደሬዎች ቪዲዮው ላይ አይቻለሁ።ላይ የለጠፍኩትን ፎቶ ተመልከቱ።

በትግሬና በአማራ ሕዝብ  ደም የጨቀዩት  የኦሮሙማ ጋንግስተሮች በጎንደርም በትግሬም በጎጃምም የሚቀበሉዋቸው ኩሉዎች አላጡም። የሕዝቡን መከራ እንዲቀጥል የሚያደርገው ሕዝቡ እራሱ ወይስ አምባገነኖቹ? እስኪ መልሱልኝ። የአምባገነን ኩሊዎችና ዳተኛው ሕዝብ በምን እንገላገላቸው?

ይህች የጎንደር ማፈሪያ አሁንም የተቸራት ቦታ ሳታከብር የአገሪቱ ነባራዊ ሃይማኖቶችን በተለይም ኦርቶዶክስ ወጣቶችን ለመበከል የነ “ሉዊስ ክርፕፍ” የሚሺኔሪዎች መዝሙር በቪዲዮ እያሳተመች ለሱቆች የምታሰራጭ ባንዳ የwelfare Queen ጎንደሬዋ ዝናሽ ታያቸው አፍረንብሻልና “አደብ ግዢ” የሚልዋት የጎንደር አረጋውያን ወዴት ጠፉ? <<ንጉሥሽ ህፃን የሆነ ፤ መኳንንቶቺሽም ማልደው የሚበሉ አንቺ ሀገር ሆይ ወዮልሽ>> ያለው ታላቁ መጽሐፍ ዛሬ በኢትዮጵያ እውን ሆኖ በህፃን ልጅ ስትመራ  አየናት።

ጌታቸው ረዳ