Tuesday, August 20, 2024

የዘመነ የጎጃም አማራ ፋኖ የሰለጠነ የፖለቲካ መሪ ያስፈልገዋል! ጌታቸው ረዳ 8/29/24

 

የዘመነ የጎጃም አማራ ፋኖ እና የምሬ ወዳጆ የወሎ ፋኖም እንዲሁ

የሰለጠነ የፖለቲካ መሪ ያስፈልጋቸዋል!

ጌታቸው ረዳ

8/29/24

በዚህ የታላቁ እስከንድር ንግግር ልጀምር፡

<< የብሄር ስም እና ማንነታችን ያገኘነው የዘር ማጥፋት ሰለባ ከሆኑ ሰዎች ነው የእኛ ትልቁ ተልዕኮ እና ራዕይ የዘር ማጥፋት መከላከል ነው>> Sep 8, 2023 ከጄፍ ፒርስ ቃለ መጠይቅ

ታላቁ እስክንድር ወደ ፋኖ የተቀላቀለበትና ግቡ ምን እንደሆነ ለእውቁ ጋዜጠኛ ለጄፍ ፒርስ የሰጠው ቃለ መጠይቅ ልጀምር፦ ሙሉውን ወደ መጨረሻ ታገኙታላችሁ::

ወደ ዋናው ርዕስ ልግባ!

ሰሞኑን በዘመነ ካሴ የሚመራው በጎጃም የአማራ ፋኖ ያስተላለፈው የትራንስፖርት እንቅስቃሴ እገዳ በሚመለከት በእስክንድር ነጋ የሚመራው የአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት በአወንታዊ ምላሽ ደግፎ ያስተላለፈው የድጋፍ ጥሪ ከሰለጠነ መሪና ከሰለጠነ ድርጅት የሚጠበቅ ጥላቻና ቅራኔ ወደ ጎን ትቶ የጋራ ችግር በጋራ የመወጣት የስልጣኔ ምልክት ሲሆን፤ በአንጻሩ የዲገላው የዘመነ ካሴ ድርጅት ግን ያንን ድጋፍ አወንታዊነቱን ተቀብሎ በምስጋናና ወንድማዊ የትግል አጋርነት በማሳየታቸው መልስ ከመስጠት ይልቅ ያንን የዲገላነት ማይምነቱን ለማሳየት መልስ ሳይሰጥ ዘግቶታል። ያ አልበቃ ተብሎ ደጋፊዎቹ በእስክንድር ሲሳለቁ በየሚዲያው መስማት የሚገርም ባርባሪዝም (ማይምነት) ምልክት የሰለጠነ አስተካካይ መሪ ያጣ “ኮሚኒቲ” መሆኑን ነጋሪ ነው።

ፖለቲካና ሥልጣኔ ምንድናቸው? ፖለቲካ ሰዎች ኑሮአቸውን ለማሻሻል የሚጠቀሙበት መወጣጫ መሰላል ነው። ስልጣኔ ግን የአረመኔነትን ተቃራኒ የሚገልጽ የዓዕምሮ ብስለት ነው። የሰለጠነ ሰው ጨዋ ነው። ትንሽዋን ቃል "አመሰግናለሁ" እንዴት እንደሚል እንኳን ያውቃል። ዲገላው ግን የሰለጠነውና ጓዳዊ የአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት ድጋፍ ትንሽዋን ቃል "አናመሰግናችለን" እንኳ ለድጋፋቸው መልስ ሊሰጥ አልፈለገም። ለዚህ ነው “የጎጃም አማራ ፋኖ” በሥልጡን ፖለቲካ የተካነ መሪ ፈልጎ ማግኘት እንዳለበት ሁሌም የምመክረው። ከተማና ገጠር ስለያዝክ አጃቢና ትጥቅ ስላከማቸህ አድካሚውና ትዕግስትና ጥበብ የሚጠየቅ ፖለቲካ መሪ ከሌለህ ትግሉ ውሃ መውቀጥና ስቃይ ማራዘም ነው።

ስለ ምሬ ወዳጆ

ምሬ ወዳጆ የተባለ ትምሕርትና ልቦና የጎደለው የወሎ ፋኖ ማይም ስለ ኮለሜል ፋንታሁን ሞሓባ እና ስለ እስክንድርና ስለ የሸዋ ፋኖ የመከታ ማሞ አመራር በማይም ቃላት ሲሰድባቸው ሰምታችሁ ይሆናለ። አንዳንዶቹን ልጥቀስ

ኮሎኔል ፋንታሁን ሙሓባ ባንዳንድ ሃይሎች ስለተጠለፈ አባርረነዋል

ስለ የሸዋ ፋኖም እንዲህ ሲል ብልግናውን ሲተፋባቸው ሰምተናል፡

<<የሸዋ ፋኖን እየመራ ያለው “አባ ዱላ ገመዳ” ነው>> ሲል ማይምነቱን በሚዲያ ገልጽዋል።

ይህ ማይም ጥይት እንዲቶክስ እንጂ የማያውቀውን ፖለቲካና የሚዲያ መድረክ መቅረብ ስለሌበት፤ አብረው የሚታገሉ ልባሞች ካሉ ይህ ማይም ከሚዲያ አስርቁት ፡ ብዙ ነገር ያበላሽባችል።

ከዚያ በፊት የጎጃም ፋኖ ቃል አቀባይ ተብየው ማርሸት ፀሃየ የተባለ ሲዋሽ ሰማይና ምድር የሚያጣብቅ ልጅ እስክንድር ከአብይ አሕመድ የኦሮሙማ አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ ጋር እየተነጋገረ መሆኑን ደርሰንበት ማስረጃው እልክልሃለሁ ሲል ለእሱ መሳይ የሚዲያ ዋሾ ምናላቸው ስማቸው የተባለ ጎጀሜው ማፈሪያ (ባለቤቱ ውድ አርበኛዋ የኢትዮ 360 ኢየሩስ ይቅርታ እየጠየቅኩ) ቃለ መጠየቅ ሲሰጠው “እየቀለድክ ነው ማስረጃው አለህ? አዎ አለኝ፡ በቃ አገሩ ይተረማመስ ላክልኝ” ብሎት እስካሁን ድረስ አንዲት ብጣሽ ማስረጃ አላቀረበም። እነጂህ ያልበሰሉ ማይሞች ከሚዲያው አስወግዳችሁ የበሰለ ትዕግሥትና የፖለቲካ ጥበብ ያላቸው መሪዎች ፈልጉላቸው።

በእስክንድርና በጓዶቹ የሚመራ የፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት በአክብሮትና በአድናቆት ቆቤን በማንሳት ክብር ይገባችኋል፤ ስላሳያችሁት ጓዳ ትሕትና እና ሥልጡን ዲፕሎማሲባላችሁበት አድናቆቴ ይድረሳችሁ!

አሁን በመግቢያየ የጠቀስኩት ቆየት ያለ የእስክንድር ቃለ መጠይቅ ቅስ ላቅርብ (አማርኛውና እንግሊዝኛው) Sep 8, 2023

Jeff Pearce: Fano and APF for that matter keep getting lazily referred to online and in news reports as ethnic extremists or militants. Western news claims Fano has killed government officials and wrecked offices. What should people know?

Eskinder Nega: The best way to describe Fano is as a historical grass roots movement of resistance for either justice or defense of country.

Over what is assumed as a very long time in Ethiopia’s history, Fano has become a pan-Ethiopian cultural phenomenon. That we now see Fano as manifest only in the Amhara region attests to the unique challenge facing the Amharas — the challenge of genocide, I should point out — not to the ethnicity of Fano.

We have an ethnic name and an ethnic organization as a byproduct to to the ongoing state-sponsored leveling, categorization, demonization, mass displacement, mass killing of Amharas. All these are well known hallmarks of genocide. In other words, we derive the ethnic name and identity from the victims of genocide. Our paramount quest and vision is the prevention of genocide. To these noble ends, we recognize the de-emphasis of identity politics is an essential goal. That is the goal we shall strive for.

ጄፍ ፒርስ፡- ፋኖ እና ኤፒኤፍ ለነገሩ በመስመር ላይ እና በዜና ዘገባዎች ላይ እንደ ጎሳ ጽንፈኞች ወይም ታጣቂዎች እየተባሉ ይጠቀሳሉ። የምዕራቡ ዓለም ዜናዎች ፋኖ የመንግስት ባለስልጣናትን ገድሏል እና ቢሮዎችን ያወድማሉ እያሉ ይዘግባሉ። በዚህ ጉዳይ ሰዎች ምን ማወቅ አለባቸው?

እስክንድር ነጋ፡- ፋኖን ለመግለፅ የተሻለው መንገድ ለፍትህ ወይም ለሀገር መከላከያ የተቃውሞ እንቅስቃሴ ታሪካዊ ሥረ መሠረት ያለው ነው።

በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ በጣም ረጅም ጊዜ ነው ተብሎ በሚታሰበው መሰረት ፋኖ የመላው ኢትዮጵያ የባህል ክስተት ሆኗል። አሁን ፋኖን በአማራ ክልል ብቻ እንደግልጽ አድርገን መመልከታችን የአማራዎችን ልዩ ሁኔታዎችና ተግዳሮች ስላሉ ነው።

የብሄር ስም እና ማንነታችን ያገኘነው የዘር ማጥፋት ሰለባ ከሆኑ ሰዎች ነው። የእኛ ትልቁ ተልዕኮ እና ራዕይ የዘር ማጥፋት መከላከል ነው። ለእነዚህ መልካም ዓላማዎች የኝኝ ባይ ብሔረተኛነትን ፖለቲካ ማጉደል አስፈላጊ ግብ መሆኑን እንገነዘባለን። እኛ የምንጥርበት ዓላማ ይህ ነው።

መልካም ሳምንት!

ጌታቸው ረዳ