አብይ ኢትዮጵያን ሊገነጣጥላት በሚችል ራዕይ እየተጓዘ ነው!
ጌታቸው ረዳ
(Ethiopian Semay)
በመጀመሪያ ሰላምታየ በተለያዩ መንገዶች እኔን አግኝታችሁ ወደ ትግሉ እንድመለስ ያበረታታችሁኝ ወገኖቼ የከበረ አክብሮት
ይድረሳችሁ። ውድ ወንድሜ አቶ ፍስሃ አንዳርጌ “ ጀግና ተስፋ አይቆርጥም” በሚል ርዕስ ጽፈው የኔን አመለካካት እና
ትችት ለሕዝብ እንዲዳረስ በሚተባበሩኝ ድረገጾች ላይ በመለጠፍ ከትግሉ
የመሳብ ውሳኔየን እንደገና ለመግታት ያቀረቡልኝ ጥያቄ ተመልክቼዋለሁ። እኔም የወንድሜን ጥያቁ በማክበር ውሳኔየን ስቤዋለሁ። ስላከበሩኝ
የኢትዮጵያ አምላክ ያክብርልኝ። አመሰግናለሁ።
ከትችቶቼ ጋር ትውውቅ ያላችሁ ወገኖች እንደምታውቁት የምተችባቸው ትችቶች በቸልተኝነት የሚታለፉ በጣም ወሳኝ እጅግ አስፈሪ
የሆኑ በመንግሥትነት የተቀመጡ ባለሥልጣናትም ሆኑ እንደ ታቦት መነካት የለባቸውም ተብለው በተከታይ “ካልቶቻቸው” የሚሽሞነሞኑ የተቃዋሚ
ድርጅቶች መሪዎች የሚሰነዝርዋቸው “ተጠያቂነት የጎደለው” ንግግሮቻቸውን ፤ በተለይ የፖለቲካ ተቃዋሚ ነን ብለው “ላስጠጋቸው አገር
ምን ላቅርብ በሚል በአድርባይነት ጠባይ በመነሳት ያስጠጋቸው አገር በኢትዮጵያውያን ህይወት ላይ ያደረሰው ወንጀል በመሸፈን
ሰለባዎችን የሚወነጅሉ “ዋሾ” የተቃዋሚ ድርጅት መሪዎችን በማጋለጥ፡ እንዲሁም የታጋዮቻቸውን ሰብአዊ መብት በመጣስ ‘ከመሰወር፤ከመደብደብ እና እስከ
መግደል ድረስ የሚደርስ ሰብአዊ ጥሰት ያደረሱ የተቃዋሚ ድርጅቶች እና ይህ ወንጀል ለመሸፈን ተባባሪ የሚሆኑትን ደጋፊ የዜና ማሰራጪያዎቻቸው
እና ጋዜጠኞች” ሕዝብ እንዲያውቃቸው በማድረግ የመሳሰሉ ላይ
የሚያተኩሩ ትችቶች ስተች መኖሬ ይታወቃል። ከሌሎች ተቺዎች ለየት የሚያደርገኝ ይህ አተቻቸቴ ነው። ዛሬም ነገም ትችቴ በዚሁ ይቀጥላል።
በሚቀጥለው ሰሞን
የምንነጋርባቸው ጉዳዮች፡
ብርሃኑ ነጋ አዲሱን ለውጥ ኢሳያስ አፈወርቂ እና ግንቦት7 ናቸው ያመጡት ነው; አለ!
ሲል “ድ.ሰ.ደ.ኤ” የተባለ ኢሳያስን የሚቃወም ተቃዋሚ
ድርጅት በትግርኛ ያወጣው ሃተታ አውነትነቱን ካጣራሁ በኋላ በሚቀጥለው ሰሞን እምለስበታለሁ። ከዚያም በማያያዝ ኢሳያስ ምፅዋ ወደብ በሚገኘው የባሕሩ
የመሬት ደንደስ ውስጥ በመቆፈር የሞለቲ ፋብሪካ ባለቤት የገነባው
“ጥንታዊ ህንጻ” አፍርሶ ጣሊያኖች የኑክልየር አተላ አንዲቀበር አድርጓል፡ የሚለው በአንዲት ጀርመናዊት የሻዕቢያ አቀንቃኝ የነበረች
እና ከብዙ አመት በፊት በጣሊያን አገር አምባሳደር የነበረ “ወዳጁ” የነበረች ላንድ ኤርትራዊ ጋዜጠኛ የነገረቺው ምስጢር እራሱ ኤርትራዊ ጋዜጠኛው የዘገበው ሰነድ እና እንዲሁም ኢሳያስ እና አብይ ከተፈራረሙባቸው
ሰነዶች አንዳንዶቹ በሚቀጥለው ሰሞን እንነጋገርባቸዋለን።
ወደ ርዕሴ ከመግባቴ
በፊት ይህንን ልበል።
በማንኛቸውም የትግል ስም እየተጠሩ ‘በነፃነት፤ በግምባር፤ በእንቅሳቀሴ፤ በፓርቲ… መጠሪያ የሚጠሩ በጠመንጃ ትግል ሲታገሉ
የቆዩ የድርጅት መሪዎች “በታጋዮቻቸው ላይም ሆነ በማንኛውም ዜጋ ላይ ጫካ ውስጥ ሲንቀሳቀሱ ያደረሱት የሰብአዊ ጥሰት”
ሓላፊነት ሳይወስዱ አጋጣሚውን ተጠቅመው አብይ በሰጣቸው
የግቡ የምህረት ጥሪ ምክንያት ተጠቅመው በመደመር ጥሪ
“አመልጣለሁ” ብለው ተንደላቅቀው ወንጀል ሰርተው እንዳልሰሩ፤ ክራባት አሳምረው ሱፍ ለብሰው ‘ሰው መስለው’ “የሚደበቁ ካሉ” ፍትሕ
አንዲጠይቃቸው ይህ ጸሓፊ ይታገላል።
በተለይም በወንጀል የተሳተፉ ተቃዋሚ መሪዎች ቅጣታቸውን ሳያገኙ ወደ ሥልጣን እርካብ ዛሬም እንደለመዱት በሽፍንፍን እንቀጥላለን
እያሉ ስለሆኑ እነዚህም እንቃወማለን። ሰሞኑን ያየነው የኦነግ
መስራች አንዱ ከሆነው በጸረ አማራ የታወቀው የኦሮሞው ናዚው “ሌንጮ ለታ” የሚመራው በአዲስ የሽፋን መጠሪያ ስም የሚንቀሳቀሰው
‘ኦሮሞ ዲሞክራሲያዊ ግምባር’ (‘ኦዴግ’)፤ የዘር ፖለቲካ ከሚያቀነቅነው አብይ አሕመድ እና ለማ መገርሳ
ከሚመሩት የኦሮሞ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኦዴፓ) ውህደት/ግምባር/አንድነት
መፍጠራቸውን ሰምተናል። አብይ እና ሌንጮ ውሕደት ከፈጠሩ
የዘር ፖለቲካውን አቅጣጫ የሚመራው “የኦሮሞ ኬኛ /ጂፒ ኤስ/ ምህዋሩ” ወዴት እየገሰገሰ እንዳለ በግልጽ
ይታያችኋል። በጥላቻ እና በአማራ
ዘር ወይንም በሌሎች ነገዶች ላይ ዘር ማጥፋት ወንጀል የተሳተፉ እንዲሁም የገፋፉ ወይንም አስተዋጽኦ ያደረጉ ወንጀለኞች/ ድርጅቶች/
ጋር ውህደት የፈጸሙ ሁሉ ለተፈጸሙ ወንጀሎች ደንታ ቢሶች መሆናቸውን ስለሚያሳየን እነሱንም መቃወም ይጠበቅብናል። ይህንን ስንል
የለመድናቸው “ተሞዳሟጅ ሊሂቃን እና ሚዲያዎቻቸው” በእርቅ ስም “አፋችንን ለማስዘጋት” እንደሚጥሩ እናውቃለን። ሆኖም አገራችን
እንደገና በወንጀለኞች ላለመመራት ጥቅጥቅ ያለው የጭጋግ ፖለቲካው እስኪጠራ ድረስ ትግላችን ቀጣይ ነው።
ማንነትህን እንድነግርህ ከማን ጋር እንደምትሄድ ንገረኝ (tell me with whom you consort
with and I will tell you who you are)(posted at Ethiopian Semay)
በዚህ ትችት ላይ አራት ርዕሶችን ባጭሩ እንመለከታለን።
1)
ዶ/ር ኮለኔል አብይ አሕመድ “የመገንጠል ጥያቄ” (አገር የማፍረስ ጥያቄ)-
2)
ሶሲያል
ሰክዩሪቲ/ኤልክትሮኒክ መታወቂያ
3)
-
አንዳርጋቸው ጽጌ የተባለ የግንቦት 7 መሪ ኤርትራ በነበረበት ወቅት ፡የኢትዮጵያ አርበኞች ግምባር መሪ/መስራች/ (?) በነበረው
ኮለኔል ታደሰ ሙሉነህ የእስር መነሻ የተናገረው ውሸት።
4)
ጥገናዊ
ለውጥ የሚያራምዱት ኦሮሞዎች በወንጀል የተጨማለቁት የትግራይ ሊሂቃን ብሔረተኞችን በቁጥጥር ስር ከማዋል ይልቅ እሽሩሩውን ተያይዘውታል።
1) ዶ/ር ኮለኔል አብይ አሕመድ “የመገንጠል ጥያቄ” (አገር የማፍረስ ጥያቄ)-
በአሁኑ ወቅት በኦሮሞዎች የሚመራው ጥገናዊ ለውጥ ኢትዮጵያን ወደ እሚበታትናት
ማዕበል ቀስ በቀስ እያስጠጉዋት ነው። እራሱ አብይም “ኢትዮጵያ አስፈሪ መአዝን ላይ ነች” ሲል እንደተናገረ ዜናዎች አሰራጭተውታል።
አሁን በቆመችበት አስፈሪ መአዝን ላይ ገፍትሮ ፍርክስክስዋን የሚያደርሰው የመጨረሻው “ግፊት” ደግሞ አብይ እራሱ የሚከተለው “ወያኔአዊ ፖለቲካዊ መስመሩ ነው”። አንድ ነጥብ ላስጨብጣችሁ። ዶ/ር ኮለኔል አብይ አሕመድ “የመገንጠል ጥያቄ” (አገር የማፍረስ ጥያቄ) የሚያቀርቡ
ሁሉ አገር የማፍረስ መብታቸው “በዲሞክራሲው ዓለም” የተፈቀደ ዲሞክራሲያዊ መብት ስለሆነ “በሕዝብ ድምጽ አገር ላፍረስ ካለ መብቱ ነው”
የሚለው ባለፈው ሰሞን ለተቃዋሚ ድርጅቶች (በአዲሱ የማዕረግ ስማቸው “ተፎካካሪዎች”) የተናገረውን ታስታውሱ ይሆናል የሚል ግምት
አለኝ።
እንዲህ ያለ ወያኔአዊ
መስመር የቸከን፤የገማ፤ ጊዜው ያለፈበት የጠነባ አክራሪ ግራ ዘመም ፖለቲካዊ መስመር “ዲሞክራሲያዊ ሳይሆን” (ዲሞክራሲ
የሚለው የውሁዳን መጨቆኛ፤ የ mob ስልት ማለት መሆኑን ያዙልኝ ) በቅኝ ገዢዎች ተይዘው የነበሩት
አገሮች ወይንም በዚያው መልክ የተገነቡ አገሮች እንጂ እንደ ኢትዮጵያ ሕዝብ አይነቱ የሚመለከተው መብት አይደለም። እንደ አብይ አሕመድ፤
እንደ ወያኔዎች እንደ ኦነጎች እና ኦብነጎች የመሳሰሉ “የተማሩ
ከብቶች” ከካናዳ፤ ከእንግሊዝ ከመሳሰሉት ጋር ኢትዮጵያን
እያቆራኙ በተለይም “ተገንጣይ ወያኔአዊ ኦሮሞዎች እና ትግሬዎች” ኢትዮጵያን ስለጠሉ ‘የኢትዮጵያ ሕዝብ ግንኙነትና ቁርኝት
ከተመሰረተ ዕድሜው 100 አመት ብቻ ነው። ምኒሊክ ያገናኛቸው ናቸው” እያሉ “የውጭ አገር ቅጥረኞች” በሚነዙት
ፈጠራ እንጂ ገሃድ የሆነ አገር የማፍረስ ጥያቄ ከዲሞክራሲ ወይንም ከዜጎች መብት ጋር የሚገናኝ መብት አይደለም። የነገሩ
ማሰሪያ በዲሞክራሲ ስም “አገርን በማፍረስ” ሕዝብን ላማፈናቀል እና ለማተራመስ “ወንጀል” ለመፈጸም የታቀደ የወንጀለኞች
መብት ነው።
አብይ የተባለው በዲሞክራሲ
መብት ስም የግንጠላ “በር ከፋች” ኦሮሞዎች ጋር ሲሄድ የሚናገረው ኦሮሚኛ ሲሆን እዛው የተናገው እና አማርኛ በሚናገሩ ዜጎች አካባቢ
የሚናገረው ስለ “ኢትዮጵያ እና ስለ ኦሮሞ’ አማርኛዊ ንግግሩ ደግሞ የተለየ እንደሆነ ምሁሩ ወጣት አቻም የለህ ታምሩ
በሚገባ ምንነቱ ገልጾታል። አቻምየለህ የሚከተለው የተናገረው በቴድሮስ ፀጋዬ ራዲዮ/ቲቪ/ ላይ አቤ ቶኩቻው ከተባለ የሚቀርብለት
ክርክር “በችኮነት/በሂፒከሪት አመል” እየተነዳ፤ “በግለት ‘ፀጉሩ ይቆም’ እና ሲከራከር ቆይቶ” እራሱ
ሲሰራበት በነበረበት ‘ኢሳት ቲቪ’ ላይ የተላለፈውም ሆነ በ ኢቲቪ ወይንም በመሳሰሉ የተገኙ ‘ማስረጃዎች ሲቀርብለት ላመቀበል የሚንገዳገድ
አመል ያለው) “ጋዜጠኛ’/ተቺ/ ነኝ” የሚል ጋር
ስለ አብይ አሕመድ ሲከራከሩ ያደመጥኩት ማስረጃ ነው።
አቻም እንዲህ ይላል፡
“ሰውየው (አብይ)
ካን አርቲስት ነው (con artist) (የማታለል ባሕሪ) አለው የምልበት ምክንያት ላቅርብ። ጠ/ሚኒስቴር ሆኖ በተሾመበት ቀን
የኢትዮጵያን መሪዎች እያነሳ በጥሩ ነገር ሲናገር ሰምተነዋል። እንዳውም ስለ አጼ ምኒሊክ ሲነሳ ከሌሎቹ ኦሮሞ ብሔረተኞች በተሻለ
እንዳውም ብልህ ናቸው እንዲህ እያለ በአማርኛ በበጎ ቃላት እያነሳቸው ሲናገር ሰምቸዋለሁ። ጅማ በተካሄደው
የ ‘ኦሆዴድ’ ጉባኤ ግን እንዲህ ብሎ በኦሮምኛ ተነግሯል ፡
እጠቅሳለሁ፤
“ በጊዜ ሂደት ውስጥ
(የኦሮሞ ሕዝብ) ጥንካሬው በመላላቱ እና የነበረው ሕብረቱ በመፍረሱ
በጠላት እጅ ሊወድቅ ችሏል” ይላል። እንግዲህ በጠላት እጅ የሚለው “አጼ ምኒሊከን ነው።
ከዚያም ‘ሂፒከሪቱ’
አቤ ቶኩቻው በለመደው “ችኮነት”አመሉ ላለመቀበል በሚል ተነሳስቶ “ምኒሊክ” የሚል የምኒሊክን ስም ጠቅሷል? ብሎ አቻምን ይጠይቀዋል።
የራዲዮው አስተናጋጅ እና አዘጋጅ ቴድሮስ ፀጋየም እንዲህ በማለት እመሃል ገብቶ አቤን ለማስረዳት ይሞክራል፦
“ታስታውስ እንደሆነ
ጠ/ሚኒስትሩ እዚህ መጥተው እያለ ‘እርስ በርስ ተሸናነፍን የሚል ቋንቋ ትክክል አይደለም፤ ያሸነፍነው ጣሊያንን ነው። አሸንፍን/ተሸናናፍን/የሚለው
ቃል ለጠላት እንጂ ዜጎች አርስ በርስ በሚያደርጉት ፍትጊያ /ውግያ/ የሚገባ ቃል አይደለም” ብለው ሲሉ በደምብ አስታውሳለሁ።” ሲል
ያስረዳዋል።
አቻምየለህም እንዲህ
ይላል።
ይህ ትራንስሌሽን በኢ
ቲ ቪ (ቴ/ቪዥን) የተላለፈ ከኦሮሞኛ ወደ አማርኛ በኦፊሲየላዊ ትርጉም የተላለፈ ነው። በኦሆዴድ አማርኛ የተላለፈው መግለጫ ደግሞ
“የመደብ እንጂ የማንነት/የብሔር ጭቆና” የለም ብለው ተናግረዋል።
ይህ እንደተነገረ፤ አብይ እንዲህ ይላል፡ በኦሮምኛ፤-
“በጭቆና እና በባርነት መኖር ብቻ ሳይሆን (ኦሮሞ ሕዝብን ነው) ማንነቱ እንዲያጣ
ተደርጓል። ቋንቋው እና ታሪኩ ባህሉ እና ማንነቱ ተረስቶ ከሰው በታች የመኖር ዕድሉ ሆኖ ቆይቷል።” ይላል። ይኼ አርሱ አብይ የተናገረው ነው። ከዚያም ቀጠል ይል እና
‘በፀረ ጭቆና ትግል ውስጥ እነ ሃይለ ፊዳ እና ባሮ ቱምሳ አላማቸውን ከግብ ከማድረሳቸው
በፊት በጭቆና አገዛዝ ሊቀጩ ቻሉ” ይላል። አቻም አብይን እንዲህ ይተቸዋል።
“Infact ሰውየው
እማያውቀው “ባሮ ቱምሳን የገደለው ደርግ አይደለም (የጭቆና አገዛዝ ስርዓት አይደለም) ባሮ ቱምሳን የገደለው “ኦነግ’ ነው። በሃይማኖት
ተነሳ ኦነግ እራሱ ነው የገደለው።
አሁንም ሂፒከሪቱ አቤ
ቶክቻው “ግዴታ እኮ.. ግዴታ የጭቆና እንቶኖች እኮ... ደርግ ነው ወይንም ….” እያለ አቤ ቶክቻው በለመደው “አጉል ችኮነት” ላለመቀበል
ችክ ሲል ጋዜጠኛ ቴድሮስ ጸጋየ እመሃል ገብቶ እንዲህ ይላል፡
“አቤ አድምጠኝ… ነገሩ
እኮ ባሮ ቱምሳ የተገደለው በአገዛዙ ስለ ተቀጩ” ስለሚለው ነው ” ሲል ያስረዳዋል። አቤ ማምለጫ ሲያጣ “እሺ.. እሺ”
ብሎ ተቀበለ። አቻምም “በአገዛዙ ስለሚል ነው” ሲል ያጠናክርለታል። እና “እንዲህ ያለ “የካን አርቲስት” ገጸ ባሕሪ ያለው ሰው
ሆኖ ሲጫወት ስላየሁት ነው በዚህ የገለጽኩት። የሚናገረው እና የሚሰራው በኦሮምኛም ሆነ በአማርኛ ሲናገር ይለያያሉ። እንደ አገር መሪ ሓላፊነት የሚሰማው ሰው መሆን
ነበረበት። ባያምንበት እንኳ “ኢነተግሪቲውን” አንደ መሪ ለመጠበቅ መቻል አለበት። ኢትዮጵያዊ ጠላት የለም፤አሸናፊ ተሸናፊ የለም
ሲል ቆይቶ ፤ኦሮሞዎች ጋር ሲሄድ ደግሞ ኦሮምኛን ሰው አይሰማም ብሎ “የኦሮሞ ሕዝብ በጠላት አጅ ወድቋል ይላል።” አቻም።
እንግዲህ ከላይ የሰጠሁዋችሁን
ማስረጃ እና በዚህ ሰውየ መሪነት ሰብሳቢነት የተካሄደ የተቃዋሚ መሪዎች ስብሰባ “መገንጠልን” ከመብት አንጻር፤ አገር ማፍረስን
ከመብት አንጻር እያገናኘ “በዲሞክራሲ ሽፋን የራሱን ኦሮሞዎች እና ሶማሌ ተገንጣዮችን ወደ አገር በማስገባት “አገር ማፍረስ
እንፈልጋለን ብላችሁ ብረት ያነሳችሁ ብረቱን ተውት እና ሕዝቡን አታልላችሁ አገር ማፍረስ ትችላለችሁ። ብሎአቸዋል። ያ መብታችሁ
ነው!” ሲል ምን ማለት ነው?
ሕዝብን መሰበክ “ማታለልን
ይጨምራል”። የፔንጤ አታላዮች ወታደራዊ ኮማንዶ አጃቢዎች እና በመቶዎች የሚቆጠሩ ሕጋዊ ወታደሮች የደምብ ልብስ ለብሰው በሰብከት
ተጭበርብረው
ናላቸው ዞሮ እየጨፈሩ በቪዲዮ ተሰራጭቶ “ኢትዮጵ ወታደሮች የዓለም ማሰቂያ ሆነው ያየንበት ምክንያት” ውጤቱ ማታለል (ካን አርቲስትነትን) የገበያ ስልት ስለሆነ ነው። አገር ማፍረስ በዲሞክራሲ ስም ተጠልላችሁ ኑ በማለት አብይ ሲፈቅድ በተዘዋዋሪ አነጋገር “የምትችሉበት ማጭበርበሪያ ስልታችሁ ተጠቅማችሁ ሰውን ማታለል ከቻላችሁ እኔ እስከ ፈቀድኩላችሁ ድረስ ድረስ በምርጫ ስልት “አገር ገንጥላችሁ ሰውን አተራምሱ አገር አፍርሱ የሚል “አረንጓዴ መብራት አብርቶላቸዋል። ለዚህ ነው ኦሮሞ ጋር ሲሄድ “ምኒሊክ ጠላታችሁ ነበር! ጠላታችሁ ምኒሊክ እጁ ስር ወደቃችሁ ነበር” የሚለው። ሌላው ጋር ሲመጣ ደግሞ “ምኒሊክ “ብልህ’ ነበሩ’፤ ያውም መሸንፍ እና ማሸነፍ ለዜጎች የሚገባ ቃል ሳይሆን ላሸነፍናት ለጣሊያን የምንጠቀምበት ቃል መሆን አለበት’ እያለ ዥዋዥዌ ይጫወታል።
ናላቸው ዞሮ እየጨፈሩ በቪዲዮ ተሰራጭቶ “ኢትዮጵ ወታደሮች የዓለም ማሰቂያ ሆነው ያየንበት ምክንያት” ውጤቱ ማታለል (ካን አርቲስትነትን) የገበያ ስልት ስለሆነ ነው። አገር ማፍረስ በዲሞክራሲ ስም ተጠልላችሁ ኑ በማለት አብይ ሲፈቅድ በተዘዋዋሪ አነጋገር “የምትችሉበት ማጭበርበሪያ ስልታችሁ ተጠቅማችሁ ሰውን ማታለል ከቻላችሁ እኔ እስከ ፈቀድኩላችሁ ድረስ ድረስ በምርጫ ስልት “አገር ገንጥላችሁ ሰውን አተራምሱ አገር አፍርሱ የሚል “አረንጓዴ መብራት አብርቶላቸዋል። ለዚህ ነው ኦሮሞ ጋር ሲሄድ “ምኒሊክ ጠላታችሁ ነበር! ጠላታችሁ ምኒሊክ እጁ ስር ወደቃችሁ ነበር” የሚለው። ሌላው ጋር ሲመጣ ደግሞ “ምኒሊክ “ብልህ’ ነበሩ’፤ ያውም መሸንፍ እና ማሸነፍ ለዜጎች የሚገባ ቃል ሳይሆን ላሸነፍናት ለጣሊያን የምንጠቀምበት ቃል መሆን አለበት’ እያለ ዥዋዥዌ ይጫወታል።
የመጫወቱ ስልት መነሻው
“አገርን በስልት ለማፍረስ እየሄደ ያለው መንገድ ነው”። ፋሺሰት እና ናዚ ትግሬዎች ኢትዮጵያን ካልገዛን ኢትዮጵያ ትፍረስ ሲሉ
፤ በሌላ መንገድ ደግሞ ኦሮሞዎች ፍንፍኔን ካልወሰድን ኢትዮጵያን ካላስጨነቅን /ካልገዛን/ አቢሲኒያ ትፍረስ” የሚሉ ጋጠወጦችን
በዲሞክራሲያዊ መብት ሽፋን ስም ‘ስርኣተ አልባ’ ንግግሮችን ስለፈቀደ “ብሔራዊ ክብሯን” የሚጠብቅ ቆራጥ መሪ ነው ማለት ያስቸግራል።
አገር ወዳድ እየተባለ
ብዙ የሚደሰኮርለት ለማ መገርሳም ከተመሳሳዮቹ እነ
ሌንጮ ግምባር ፈጥሮ ግስጋሴው እያቃና ነው። ሌንጮ ማን ነው? መልሱ ብዙ ሰነድ ስላለ ያንን መመርመር ነው። እውን ለማ ከሌንጮ
ጋር የማበር ሞራል ይፈቅድለታል? የሚለው ጥያቄ መልስ ለማግኘት ከራሳቸው
ከእነ ለማ እንጠብቃለን። እነ ሌንጮ እነ በቀለ ገርባ ወዘተ.. ወዘተ…ደግሞ ፍንፍኔ (አዲስ አበባ የሚለው መጠሪያ ‘አማርኛ’ ስለሆነባቸው
አማርኛን ላለመንካት የሚጠቀሙበት አዲስ ‘የኮድ ስም ነው’) “ትናንትም፣ ዛሬም፣ ወደፊትም የኦሮምያ አካል ናት። በፍንፍኔ ውስጥ
የሚኖሩ ኢትዮጵያውይን ኗሪዎችም በኦሮሞዎች ፈቃድ ይኖራሉ።” ብለው በይፋ አዋጅ ያወጁ ናቸው። ታዲያ ለማ መገርሳ ከነዚህ ጋር በምን መመዘኛ ግምባር ለመፍጠር ተቃቀፈ? ለሚለው መልሱ ግልጽ
እስካላደረጉልን ድረስ የኔ መልስ ‘መመዘኛቸው/ ፖሊሲያቸው/ ተመሳሳይ
ከሆነ’ መልሱ በዚህ ጽሑፍ የተመለከተው አብይ ርዕስ ለማጠናከር ነው ማለት ነው።
አገር በዲሞክራሲ አልተመሰረተም
፤ አይመሰረትም ፤ ተመስርቶ አያውቅም፤ ሆኖም አገር በዲሞክራሲ ስም ሲፈርስ ግን አይተናል። ያ ሴራ ወደ እኛ እየተጓዘ ነው ብቻ
ሳይሆን “ዙፋኑ ላይ ከተቀመጠ 27 አመት ሆኖታል”። ለመፍረስ ከታቀዱት አገሮች ውስጥ ጅቡቲ (ያው የአፍሪካ ማፈሪያ ተብላ ስም
የወጣላት መንደር ስለሆነች አሉ የሚባሉ የዓለም አጋንንትን (666) በሙሉ ማህጸንዋን ከፍተው እየተጫወቱባት
ስለሆነ፤ የአፍሪካን ቀንድ ለማፍረስ የሚጠቀሙባት ምድር “ጂቡቲ” መሆንዋን አያነጋግርም፡ (ያው ሳትፈርስ በቁሟ
የተወረረች የፈረሰች መንደር ነች ማለቴ ነው)።
ኤርትራ/ኢትዮጵያ እንዲሁም
‘ሶማሊ’ ቀጣይ ባለ ተራ ናቸው። ያው ሶማሊያ ጀምራዋለች -የተገነጣጠሉ ሶማሌ ጎሳዎችን ተመልከቱ) ሱዳንም ምዕራፉን ጀምራዋለች፡
ግማሽ ቁመናዋ ረግረግ /አዘቀት/ ውስጥ ገብቷል። ኢትዮጵያ በባህል ተበክላ ማንነትዋን ጥላለች፤ አገር በቀል ‘ብሐየራዊ ፊደሎችዋ’
በላቲን ፊደል እንዲተኩ ተደርጓል፡ ግብረሰዶም፤ ሹሻ፤ጫት እጽ ተበራክተዋል። ያም ሆኖ ኢትዮጵያ ለማፍረስ 27 አመት ተንገዳግደዋል።
የተጠቀሱት ቀጣይ ባለ ተራ አገሮች በተለይም ኢትዮጵያ ለማንበርከክ እና ለማፍረስ ሕዝቧን ለመቆጣጠር የሚከተለው እቅድ ታቅዷላታል።
2) -ሶሲያል ሰክዩሪቲ/ኤልክትሮኒክ መታወቂያ ማደል።
ይህ የሶሺያል ሴክዩሪቲ
መታወቂያ እደላ ዕቅድ የታቀደው መለስ ዜናዊ በነበረበት ወቅት ነው። ደስታውን በመግለጽ ዜናውን የዘገበው ደግሞ (እንደ ልማታዊ
ዕርምጃ /ስልጣኔ/ ተወስዶ ማለት ነው) አይጋ የተባለው ድረገጽ ነው። በወቅቱ እኔ ቅሬታየን የገለጽኩበት ጽሑፍ ነበር። የት እንዳስቀመጥቁት
ላገኘው አልቻልኩም። ዛሬ እንደ አዲስ ጉዳዩ ተነስቶ የ666 ኢሉሚናቲ ገዢዎች እነ አብይ አሕመድ እና የተሰገሰጉ ነባር እና አዳዲስ
ወኪሎቻቸውን በማነጋጋር ይህ አዲስ ክስተት እውን ለማድርግ ኢሉሚናቶቹ ተነስተዋል።
እነ አብይ የሚሰጡዋችሁ
ምክንያቶች ለሕዝብ ብዛት ቆጠራ አመቺነት በሚል ስም፤ እንዲሁም ለዲሞክራሲ ተአማኒነት ያለው ምርጫ እንዲኖር ለማገልግል እንዲሁም
የቆላ እና የደጋ ተላላፊ በሽታዎች እንዲሁም ስራ አጥ እና የመሳሰሉ የግብር ክፍያን ቁጥጥሮችን ለይቶ ለማወቅ፤ ወንጀለኘን ለመያዝ
አመቺ እና በቀላሉ የሚያገለግል የሰለጠኑ አገሮች የሚጠቀሙበት አሰራር ነው በሚል ሽፋን” የኢሉሙናቲዎችን መታወቂያ አገራችን
ውስጥ ለማስገባት እየጣሩ ነው።
ሶሺያል ሴክዩሪቱ መታወቂያ ብዙ እንደሚወራለት የተሰወረን ‘ወንጀለኛን” ለመያዝ
ይረዳል ይባላል። ሆኖም ብዙም የታወቀ እና የተረጋጋጠ አይደለም። በቀላሉ ሌላ የሃሰት ቅጂ መስራት ይቻላል (ልክ አንደ ዶላር እና
ብር የሃሰት ኖት እንደሚባዛ) መጠንቀቅ ያለባችሁ ግን ከሶሲያል ሴክዩሪቲ መታወቂያ ቀጥሎ የሚመጡ የራዲዮ አክቲቭ/ጨረሮች/ እና
ኤሌክትሮኒክስ ዴቨይስስ/ማይክሮ ቺፕስ/ የመሳሰሉ መታወቂያዎች በሰው ገላ ውስጥ ለመቅበር የሚመጣው ቀጣዩ እርምጃ ነው የሚያሳስበው።
ይህ ማይክሮ ችፕስ ግዝፈት “የሩዝ” ያክል ደቃቃ ነች። ከሰውነትህ ጋር ሲቀበር መንግሥት የት እንዳለህ እንቅስቃሴህ ያውቃል። በውሾች
ላይ ተሞከሮ ዛሬ በበርካታ ሰዎች ገላ እየተሰራበት ነው። በዚህ መልክ ሕዝብ/ዜጎች ነፃታቸውን አጥተው “መንግሥት” በተባለ “ሞንሰተር/አስፈሪ”
ቁጥጥር ውለው ዓለምን በሚገዙት ኢሉሚናቲዎች ባርያ
ሆኖ ይኖራል።
በነዚህ ቡድኖች የሚተላለፈው ትዕዛዝ የማክበር ግዴታ አለብህ። ካልፈጸምክ በቀላሉ ከሥራ ትገለላለህ። ባንክ አያወቅህም፤ ገንዘብም ‘የወረቀት ኖት’
ስላለሆነ (ብር/ኖት ቀስ በቀስ ሊያጠፉት ነው) በብዙ ገበያዎች ካርዶች ቴሌፎኖች ውስጥ የተተከሉ ማይክሮ ችፕስ የሚያስከትለው ጦስ በማያወቁ “ስልጣኔ የመሳለቸው ተጠቃሚዎች/ሰለባዎች” መገበያየት
ተጀምሯል። ቀስ በቀስ ዓለምን ካዳረሰ የምታፈራቸው ሃብቶች በዛቺው ክንድህ ላይ በተቀበረችብህ ማይክሮ-ቺፕስ አማካይነት
ብቻ ነው ገንዘብም ሃብትህም ማንቀሳቀስ መውረስ፤ማስተላለፍ መግዛት መገበያየት የምትችለው።
ለኢሉሙናቲዎቹ አልገዛም ካልክ የምትመገበው ምግብ ከግሮሶሪ መግዛት አትችልም፤ ምክንያቱም
ገበያ ስትወርድ ያቺው ክንድህ ላይ የተቀበረችብህ ማይክሮ ቺፕስ ወደ ሰው አልባ ‘ሂሳብ ተቀባይ’ መሳሪያ ተጠግተህ ማስነበብ
አለብህ። መንግሥትን \መታዘዝ ስላልቻልክ፤ ወዲያውኑ የተተከለብህ ቺፕስ “ፍሪዝ ስለሚሆን” ምግብ መግዛት አትችልም።
ባጭሩ ህይወትህ በቁጥጥር ስለሆነ አማራጭነትህ ጌቶቻችን የሚሉንን
መፈጽም እንጂ ‘አሁን እንምደሚዋሹት” ዲሞክራሲ፤መከራከር፤መብት ፤ነፃነት ‘የሚባል ተረት ተረት ሆኖ ይቀራል።
ለዚህ ነው በአንዲት የአማራ ታዳጊ ወጣት ገላዋ /እጅዋ ላይ/ ተተክሎባት በስቃይ እንደምትገኝ ከሃኪሞች
የተለጠፈው ትችት በወልቃይት ዳት ካም እና በመሳሰሉ ድረገፆች ተለጥፎ ያነበብነው። በሚቀጥለው ትችቴ ርዕሱን ይዤ እመለሳለሁ ታነቡታላችሁ።
ስለሆነም አብይ እና ከዚህ እየተንደፋደፉ በተቃዋሚ ስም ወደ አገር የሄዱ ምሁራን እና ፖለቲከኞች በዚህ ጨዋታ እና አገር አጥፊ
የምዕራባዉያን ኢሉሙናቲ መታወቂያ “ሴራ” አገራችን እንዳትገባ አደራ የምለው። አገር በሶሲያል ሰክዩሪቲ መታወቂያ አልኖረችም፤
የግድ አስፈላጊ አይደለምም። የዜጎች ነፃነት ለማስነጠቅ ከሆነ ትግላችሁ ከነ አብይ ጋር መጨፈር መብታችሁ ቢሆንም፤ መብታችሁ ግን
የሕዝባችንን መጻኢ ዕደል ወደ ዘመናዊ ባርነት እና በ666 ባለሀብቶች እጅ እንዳትወድቅ ያለንን ተቃውሞ ለሕዝባችን ለማሳወቅ እንጥራለን።
እነ ብርቱካን መዲቅሳ አደራ የምንለው የምርጫ ቦርድ ስም “ኤሌክትሮኒክ መሳሪያዎች እና ዴቫይሶች ሶሺያል ሴክዩሪቲ
የመሳሰሉ ወደ አገራችን አንዳይገቡ ዜጋዊ ግዴታችሁ እንድትወጡ አደራ እያልን፡ የኢሉሙናቲ ተገዢዎች ከሆነችሁ ግን ታሪክ ይፋረዳችኋል።
የኤሌክትሮኒከ የምርጫ ሳጥን መቆጣጠሪያ መሳሪያዎች በቀላሉ ማበላሸት/ ማጭበርበር/ ማኮላሸት ስለሚቻል፤ በዚህ የውሸት ሳጥን አምናችሁ የ666 ኡሉሚናቲዎች ሴራ አስፈጻሚዎች ብትሆኑ በድጋሚ ታሪክ ይፋረዳችኋል።
የኤሌክትሮኒከ የምርጫ ሳጥን መቆጣጠሪያ መሳሪያዎች በቀላሉ ማበላሸት/ ማጭበርበር/ ማኮላሸት ስለሚቻል፤ በዚህ የውሸት ሳጥን አምናችሁ የ666 ኡሉሚናቲዎች ሴራ አስፈጻሚዎች ብትሆኑ በድጋሚ ታሪክ ይፋረዳችኋል።
ዜጎች አንዴ በኤሌክትሮኒክ
መረጃ ማሕደር ውስጥ ከገቡ እነዚህ ፋይሎች የሚቆጣጠርዋቸው ኢትዮጵያውያን ሳይሆኑ የውጭ አገር ኤልክትሮኒክ ኮረፖረሺን ናቸው። እነዚያም የያገራቸው መንግሥት አይቆጣጠራቸውም።
ምክንያቱም እራሱ መንግሥት በነዚህ ኮርፖረሺን ሥር እና መረጃ በሚሰጡት ስልት ነው የሚንቀሳቀሰው። እነዚህን ፋይሎች መንግሥት ሳይሆን
የሚቆጣጠረው የየአገሪቱ የሕዝብ ደህንነትና መራጃ ክፍል ነው። ይህ መረጃ ክፍል ከመንግሥት ቁጥጥር ውጭ ነው።ለምሳሌ
በአውጭ አገሮችም ሆነ በአገራችን ሲነገር የምንሰማው አጉል ፕሮፓጋንዳ “መንግሥት የደህንነቱ እና የመራጃው ክፍል ሥራ ይቆጣጠራል/ያወቃል
ይባልል። ይህ ውሸት ነው። መንግሥት የሚንቀሳቀሰው የደህንነቱ ክፍል በሚሰጠው መረጃ እንጂ መንግሥት ለደህንነቱ በሚሰጠው መረጃ አይመራም።
ስለዚህም ዜጎች በመንግሥት ስር ሳይሆኑ የኮርፐረሺኖች እንዲሁም የመንግሥት
የደህንነት ሹሞች/ክፍሎች ስር ያሉ ነፃ የሚመስሉ ግን ነፃ ያልወጡ ባርያዎች ናቸው። መንግሥትን ስለ አንድ ዜጋ መረጃ ሊያሳስቱ
ወይንም አዛብተው ወይንም ሰውረው ሊያቀርቡ ይችላሉ። ብዙውን ጊዜ ያውም በሰለጠኑ አገሮች ኮርፖረሽኖች የዜጎችን የግል
ማሕደር/እንቅስቃሴ አሳልፈን አንሰጥም የሚሉበት ጉልበት አላቸው።
ሰለዚህ ዜጎች በኮርፐሬሽን ስር/ምሕረት ከወደቁ ህይወታቸው ኮርፖረሺኖች እንጂ መንግሥት
አይቆጣጠረውም ማለት ነው። እነዚህ ደግሞ ሲፈልጉ ስለ እንተ ያላቸው መረጃ ለመሸጥ፤አሳልፎ ለመስጠት ሙሉ መብት ወይንም አቅሙ አላቸው።
አብይ ወደ ስልጣን ሲመጣ ሲናገር ከሰማችሁት ነገር አንዱ እሱ ከያዘው ዕቅድ አንዱ ታላላቅ ብሔራዊ አሴቶቸ ”ስልክ/መብራት፤ባንከ፤አየር
መንገድ…. ለውጭ ባለሃብት ወይንም ለአገር ውስጥ ሃብት ለመሸጥ ነው። ይህ ስልት ደግሞ ዞሮ ዞሮ ወደ ታቀደው ዜጎች በባለሃብቶች
ቁጥጥር ስር ‘አውሎ” ለኢሉሙናቲዎች ባበርነት ለመዳረግ የታቀደ ስልት ነው።
ይህ ሲሆን ለዜጋ የሚቆም
የለም። ምክንያቱም መንግሥት እራሱ በነዚህ ሥር ነው። ወደ ኢትዮጵያ እማ ከመጣ ጭራሽኑ “የጥቃቅን መረጃ ኮረፖረሺኖች መጫወቻ’
ሆኖ ዜጎች ለከፍተኛ ጥፋት ይጋለጣሉ። ስለዚህ ነው ሶሺልስ ሰክዩሪቱ እናመጣለን እያሉ የሚሰብኩዋችሁ። ይህ ሴራ እነ
መለስ ዜናዊ ወይንም የአሁኑ አብይ የነማን ልዑካን እንደሆኑ ማስረጃ ሊሆናችህ ይችላል። በዘመናዊነት አሳብቦ አገር ማፍረስ፤ በዲሞክራሲያዊነት መብት አገር ማስገንጠል፡ የመሳሰሉት ሁሉ የውጭ አገር “ሳብቨርሲቭ”/የሴራ/ ወጥመዶች ናቸው።
ስለሆነም ሶሺያል ሰክዩሪቱ ለዜጎቻችን እንዳይታደል እንቃወማለን።
(3)- አንዳርጋቸው ጽጌ እና ታደሰ ሙሉነህ፤
አንዳርጋቸው ጽጌ የተባለ
የግንቦት 7 መሪ ኤርትራ በነበረበት ወቅት ፡የኢትዮጵያ አርበኞች ግምባር መስራች አባል በነበሩት የአየር ሃይል በረራ አሰልጣኝ
ኮሎኔል ታደሰ ሙሉነህ የእስር መነሻ ምክንያት የተናገረው ውሸት ዛሬ ኮለኔሉ እግዚሃር ከሞት አውጥቶአቸዋልና ታደሰ ሙሉነህ
ባልሰሩት ወንጀል ‘በመፈንቅለ መንግሥት ምክንያት ነው የታሰረው’ በማለት ኮለኔሉ የታሰሩበት ምክንያት በማዛባት ለሕዝብ ስለተናገረ
ኮለኔሉ እና ቤተሰቡን ይቅርታ መጠየቅ አለበት እላለሁ። ኮሎኔሉ ከኤርትራ ምድር የሲኦል እስር ቤት ተለቅቀው ከወራቶች በፊት ሲለቀቁ
“አከላታቸው ሽባ ሆኖ መራመድ ስለማይችሉ” በተሽከርካሪ መጓጓዣ ወንበር ሆነው በሰው እየተገፉ አዲስ አበባ ሆስፒታል ተኝተው በመታከም
ላይ ይገኛሉ።
በዚህ ጊዜ በጋዜጠኖች ለመታሰራቸው ምክንያት ተጠይቀው ሲመልሱ “ምክንያት የለኝም፤ የተነገረኝ ወይንም የተጠየቅኩበት ወይንም የተወነጀልኩበት የክስ መዝገብ ወይንም ምርምራ አልተነገረኝም፡ ፍርድ ቤት አልቀረብኩም፤ እንዲሁ ነው የታሰርኩት፤ስፈታም የተነገረኝ ነገር አልነበረም።” ሲሉ ስለታሰሩበት ምክንያት ምንም እንደሌለ ገልጸዋል። ዛሬ አንዳርጋቸው ጽጌ እራሱ ከእስርና ከሞት በመውጣቱ እግዚሃር አድኖታል እና ሞራሉ ካለው ለእኚህ ኮለኔል ይቅርታ መጠየቅ አለበት። አንዳርጋቸው በይቅርታ የሚያምን ከሆነ አኒህን ሰው እና ቤተሰቦቻቸው ይቅርታ መጠየቅ አለበት።
በዚህ ጊዜ በጋዜጠኖች ለመታሰራቸው ምክንያት ተጠይቀው ሲመልሱ “ምክንያት የለኝም፤ የተነገረኝ ወይንም የተጠየቅኩበት ወይንም የተወነጀልኩበት የክስ መዝገብ ወይንም ምርምራ አልተነገረኝም፡ ፍርድ ቤት አልቀረብኩም፤ እንዲሁ ነው የታሰርኩት፤ስፈታም የተነገረኝ ነገር አልነበረም።” ሲሉ ስለታሰሩበት ምክንያት ምንም እንደሌለ ገልጸዋል። ዛሬ አንዳርጋቸው ጽጌ እራሱ ከእስርና ከሞት በመውጣቱ እግዚሃር አድኖታል እና ሞራሉ ካለው ለእኚህ ኮለኔል ይቅርታ መጠየቅ አለበት። አንዳርጋቸው በይቅርታ የሚያምን ከሆነ አኒህን ሰው እና ቤተሰቦቻቸው ይቅርታ መጠየቅ አለበት።
(4)- ጥገናዊ ለውጥ የሚያራምዱት ኦሮሞዎች በወንጀል የተጨማለቁት የትግራይ ሊሂቃን ብሔረተኞችን
በቁጥጥር ስር ከማዋል ይልቅ እሽሩሩውን ተያይዘውታል።
ትግሬዎች ኢትዮጵያን በጠመንጃ ሲቆጣጠርዋት በመላዋ የአገሪትዋ መለክኣምድር ውስጥ ትግሬዎች በተለያዩ
ዘርፎች በማሰማራት በፖለቲካው በወታደራዊው፤በምጣኔ ሃብቱ፤ በሃይማኖት ተቋማት፤በኮንትሮባንዱ ወዘተ…..በብዛት ትግሬዎች ለዓይን በሚታይ በግብር በሚጨበጥ
መንሰራፋት እና ቁጥጥር አድርገው ሕዝብ ሲያሰቃዩ መኖራቸው በሰነድ የተደገፈ ዓለም ያወቀው ሃቅ ነው። ዛሬ ለጥገናዊ ለውጥ አመጪዎች
ምስጋና ይግባቸው እና (በዚህ ምስጋናቸውን አልነፍጋቸውም) በጥቂቱም ቢሆን የወያኔ ገበና ማሕደር ለሕዝብ በማሳወቅ ፋሺሰቶቹ የተሸፋፈነበትን
የሌብነት ነጠላቸው ተነጥቀው እርቃናቸው ወጥቷል። አዎ አፍረዋል፡ አዎ ወያኔ!! አጎምብሶ በሓፍረት ተሸማቋል። ለሁሉም ጊዜ አለው!ደስ ይላል!!!!
እርምጃው የሚያስመሰግን ቢሆንም፤ ጥገናዊ ለውጥ እያተራመዱት ያሉት ኦሮሞዎች በወንጀል የተጨማለቁት
የትግራይ ሊሂቃን ብሔረተኞችን በቁጥጥር ስር ከማዋል ይልቅ እሽሩሩውን ተያይዘውታል። እርምጃው የሚያስመሰግን ቢሆንም፤ ጥገናዊ ለውጥ እያተራመዱት ያሉት ኦሮሞዎች በወንጀል የተጨማለቁት የትግራይ
ሊሂቃን ብሔረተኞችን በቁጥጥር ስር ከማዋል ይልቅ እሽሩሩውን ተያይዘውታል። የትግሬ ወንጀለኞች እጃቸውን ለጥገናዊው አራማጅ መንግሥት
እጅ ላለመስጠታቸው “የትግራይ ሕዝብ እንዳይቆጣ” በሚል ከሆነ ግን ይህ ሽፋን ስለማይሆን የትግሬ ወንጀለኞች ባስቾኳይ እጃቸውን
ለመንግሥት ተላልፈው መሰጠት አለባቸው።
ካልተሰጡ እና በትግራይ ሕዝብ ስም
ትግራይ ውስጥ ተንሰራፍቶ በፍትሕ እየቀለደ ያለው የእነ ደብረጽዮን መንግሥት ከመአከላዊው መንግሥት ጋር ትብብሩን ካላሳየ፤ የትግራይ
ሕዝብም እነዚህ ወንጀለኞች ተላልፈው እንዲሰጡ ወያኔዎችን ካልገፋፋ ወይንም ካልተባበረ/ካልጠየቀ/ በክፍለ ሃገሩ ላይ አስቸኳይ የኢከኖሚ
ማእቀብ መደረግ አለበት። ክፍለሃገሩ የኢትዮጵያ ግዛት ከሆነ በመሃል አገር የተቀመጠው ማዕከላዊ መንግሥት ለጥያቄ የሚፈልጋቸው ሁሉ
አሳልፎ መስጠት አለበት።
ካልሆነ፤ ትግራይ የራሱ መንግሥት አውጇል እና ማዕከላዊው መንግሥት ፍትሕን ለማሰከበር የበጅትም ሆነ የኢኮኖሚ ማዕቀብ
ማድረግ አለበት። ተገንጥለናል ብለው ከሆነም ይፋ ይሁን እና እራሳቸው ችለው ወንጀለኞቻቸው እሽሩሩ ይበሉዋቸው።ካልሆነ ደብረጽዮን
ወደ አዲስ አበባ ተጠርቶተፈላጊዎችን ላለማስረከብ እምቢተኛነቱ ይግለጽ እና እርሱም በተባባሪነት ፍትሕን
በማዘግየት በቁጥጥር ሥር ይዋል። ካልሆነ እንዲህ ያለ ፉከራ
እና ቀልድ መቀጠል የለበትም።
ብዙ ሰው ለ27 አመት ኑሮው ተመዛብሎ ክብሩ ተዋርዶ፤ደህይቶ ግብረሰዶም ተፈጽሞበት፤ ሴቶች እህቶቻችን
እስር ቤት በጋጠወጥ መርማሪዎች ተደፍረው አይሆኑ ሆነው፤ ተዋርደው በብስጭት አሳልፈውታል። አሁን የፍትህ ጊዜ ነው ከተባለ አብይ
ቆራጥ እርምጃ በማሳለፍ ደብረጽዮንም ሆነ የወያኔ አመራሮች ለፍትህ እንዲገዘ ማድርግ ሓላፊነት አለበት። እሽሩሩ የወንጀለኞች ሰነድ
የሚደብቁበት እና የውጊያ
ስልታቸው የሚቀይሱበት ጊዜ መስጠት ስለሆነ ‘አስቸኳይ ትኩረት” ይሰጠው!!
ደብረጽዮን ወንጀለኞችን ወክሎ እዛው ሆኖ “ታውቁናላች እኮ” እያለ ጊዜ ያለፈበት የሕገ -አራዊት
ሕሊና ‘የጫካ ስካር” የቦወዘው ሕሊና ተሸክሞ “የማያዛልቀው ፉከራ እየፎከረ ጠረፔዛው ላይ ተቀምጦ አረፋውን በመድፈቅ ላይ ነው”። ለውጥና ወንጀለኛ በእሽሩሩ
አይመጡም።
ትግሬዎች ሲጠቀሙበት የነበረው ኦጋዴኑ ሶማሌው “አብዲ ኤሌ” በካቴና ታስሮ በቴ/ቪዥን እና በፎቶ ዜና ተቀርጾ ሲታይ
ምንም ያላሉ ዛሬ እነ ደብረጽዮን ደርሰው የትግሬ ሌቦች ሲያዙ ‘ወርቆች’
ስለሆኑ በካቴና ታስረው ወደ ፍትሕ መቅረብ “በትግሬ ላይ ያነጣጠረ ጥቃት ነው” እያሉ መስማት አለማፈራቸው የሚገርሙ ፍጡራን ናቸው።
ክንፈ ዳኘው በመታሰሩ የትግራዋይነት ማንነት የሚያሳንስ ነው የሚሉ ከሆነ ለምንድ ነው ታላቅ ወንድሙን አጽብሃ ዳኘውን የገደሉለት? ነብሰ ገዳይ ሁላ አሁን
ደርሰው ስለ የሰው መብት እና ነፃነት ጠበቆች ሆነው ማየት የሚገርሙ ናቸው።
ስርዓቱ ወይ ይውደም ወይ ይቀጥል! አጓጉል ጥገና እና ማወለወል ለለሌባ ማምለጫ ያመቻል። በቃ ማለት በቃ ነው! በቃችሁ መባል አለባቸው!!! በፍጥነት!!!! ካልሆነ ወያኔዎች ኢትዮጵያዊ ብሔረተኛነት ስሜት በውስጣቸው ስላልታነጸ ይችን አገር አውድመዋት ይወድማሉ። ስለ አገር ስሜት የሌለው በጫካ ሕሊና የሚጓዝ “ደደብ ቡድን” ደግሞ መጨረሻው አውድሞ እራሱም መውደም ነው። አጥፍቶ የሚጠፋበት ስልት ሳያጠና በወቅቱ መቅጨት ነው። ለዚህ ነው እነ ደብረጽዮን በፍትሕ ላይ አረፋቸውን እየተፉ ያሉት።
“ገራፊዎችን አሳልፌ እሰጥም” ማለቱ የሚጠበቅ ነው። ምክንያቱ ደህንነቱ ሰውን ሲያፍን ወይንም ሲገርፍ እና ሲገድል እንደ ጫካው አሰራራቸው “በቡድና በፓርቲው ተጠንተው የሚወሰኑ እርምጃዎች ናቸው ደህንነቱ እርምጃ የሚወስደው”” ሃይለማርያም ደሳለኝ ለዚህ ነው መረጃ የለኝም ሲል የነበረው። ወያኔ ራሱ የቻለ መንግሥት ስለ ነበር ነው። የተቀሩት ‘እጀታዎች’ (መሳሪያዎች) ናቸው።
የተቀረው ያገሪቱ ሕዝብ ከጨቋኞቻቸው
ጋር ጉሮሮ ለጉሮሮ እየተናነቁ ፍትሕ ፍለጋ ሲዋደቁ ‘ትግሬዎች የሚያሳዩን ሰልፍ ‘ለህይወታችን ስለምንሰጋ ከኢትዮጵያ
ት/ቤቶች ወጥተን ወደ ትግራይ እንድንማር ይደረግ” ነው ስልፋቸው። ሕጋዊ ወላጆቻቸው ሲያውለብለቡዋት የነበረቺው የጥንትዋ
ሰንደቃላማ እንኳ ማውለብልብ አልፈቀዱም። ለምን እንዲህ አንደሆነ ግን ግልጽ አንዲሆንላችሁ እፈልጋለሁ። ብሔረተኝነት መጥፎ ነው።
በዚህ ላይ ወያኔ ትግሬውን ከሌላው በበለጠ በደልዳላ ቦታ እና ኢኮኖሚ አስቀምጦአቸዋል። እየዛቀ እየነጠቀ የተቻለው አድርጓል። ለም አርሻዎች እና ጫካዎችን ከአማራዎች እየነጠቀ
ትግሬዎች በበላይነት አንዲኖሩ አድርጓል። ትግሬዎች እራሳቸው የወያኔን ስርዓት በትግሬዎችም ሆነ በሌሎች የሚደርሰው ግፍ ወያኔዎችን
ተጠያቂ ሲያደርጉ አልሰማንም (እስካሁን ድረስ። በጣት የምንቆጠር ተቃዋሚ ትግሬዎች ቁጥር ውስጥ አታስገቡን)።
የትግሬ ብሄረተኛነቱ ከሌላው አለም የሚለየው ከላይ እስከታች ከበረሃ ተያይዞ ተጋብቶ ተዋልዶ ተዛምዶ ወደ ከተማ የመጣ ተጋይ
ይበልጥ የትግራይ ብሄረተኛ ጸባዩ እና ዝምድናዊ ትስስሩ በረሃ ከመውጣቱ በፊት ከነበረው “ደማዊ እና አጥንታዊ ትስስሩ” ሰላጠናከረው
“ትግሬነት ማለት የትግርኛ ቋንቋ የሚናገር ቤተሰባዊ ትስስር ጋር የሚያያዝ ልዩ “ባለቤትነትና የበላይነት ኩራት ነው” ብሎ ስለሚያምን
“ኢትዮጵያዊ አገራዊነቱ በሁለተኛ ዐይን ነው የሚመለከተው። ከበረሃ
መልስ እርስ በርሱ ተዋልዶ ተጋብቶ ከመምጣቱ ባሻገር፤ እያንዳንዱ የትግራይ ሰው ለወያኔ ልኮ ወይንም ተገድዶ ያላታገለ/ወይንም ያላታገለ
ትግራይ ሰው (ከኔ ቤተሰቦች ጀምሮ) አይገኝም። በዚህ የተሳሰረ ጠብቅ የብሔረተኛነት ልጓም ተቀፍድዶ ተይዟል። ስለዚህ ትግሬዎች
የወያኔ ተባባሪዎች ናቸው ስንል ይህንን ታሳቢ በማድረግ ነው። ወያኔን የማይቃወሙበት ምክንያት ፍራቻ ሳይሆን “ብሔረተኛ ልጛማቸው
ስለሚጎትትቸው ነው”።
በመጨረሻም አንድ ጥያቄ ልጫር እና ልሰናበታችሁ፡ “ትግሬዎች ደርግን ያክል አስፈሪ ስርዓት ታግለው ከጣሉ ዛሬ ወያኔ “የትግራይ ሕዝብን ከማንኛውም ብሔር በበበለጠ ከደርግ በባሰ ጊዜ ዛሬ የተጨቆነ ነው” የሚባል ከሆነ ወያኔን ለመጣልም ሆነ በግፍ እና ባንድነት ለመቃወም አሁን ካለው አመቺ ጊዜ የበለጠ አጋጣሚ መቸ እንዲመጣ እየጠበቁ ነው? ከዛሬ የበለጠ መላው አገር በተነሳበት አመቺ ወቅት ክልተነሱ ትግሬዎች መቸ ሊነሱ ይችላሉ ብላችሁ ትነግሩኛላችሁ? ተወያዩበት።
በመጨረሻም አንድ ጥያቄ ልጫር እና ልሰናበታችሁ፡ “ትግሬዎች ደርግን ያክል አስፈሪ ስርዓት ታግለው ከጣሉ ዛሬ ወያኔ “የትግራይ ሕዝብን ከማንኛውም ብሔር በበበለጠ ከደርግ በባሰ ጊዜ ዛሬ የተጨቆነ ነው” የሚባል ከሆነ ወያኔን ለመጣልም ሆነ በግፍ እና ባንድነት ለመቃወም አሁን ካለው አመቺ ጊዜ የበለጠ አጋጣሚ መቸ እንዲመጣ እየጠበቁ ነው? ከዛሬ የበለጠ መላው አገር በተነሳበት አመቺ ወቅት ክልተነሱ ትግሬዎች መቸ ሊነሱ ይችላሉ ብላችሁ ትነግሩኛላችሁ? ተወያዩበት።
አመሰግናለሁ።
ጌታቸው ረዳ ( Ethiopian Semay)