Monday, December 12, 2011

ወደ ዘረኞቹ ወደ “እናት ክፉሉ” የተመለሰው ወታደር ታማኝ በየነ
To see the page/font with a wider range, please press the key Ctrl and + sign. To view the page/font with a narrow range, please press the key CTRL and _ sign.
የሚታየው የወያኔ ገበና ማህደር አዲሱ መጽሐፍ ለመግዛት $30.00 ዶላር ሲሆን ይድረስ ለጎጠኛው መምህር መጽሐፍ ደግሞ $25.00 ወይንም ሓይካማ የሚለው የትግርኛ መጽሐፌ ደግሞ $15.00 ዶላር ብትልኩ መጽሐፎቹን ማግኘት ትችላላችሁ።Getachew Reda P. O.Box 2219 San Jose, CA 95109 getachre@aol.com Phone (408) 561 4836


ወደ ዘረኞቹ ወደ “እናት ክፉሉ” የተመለሰው ወታደር ታማኝ በየነ

ጌታቸው ረዳ (ኢትዮጵያን ሰማይ) www.ethiopiansemay.blogspot.com getachre@aol.com

አርበኛ እና ደፋር ስለው የነበረው፤ ዘፋኞችም እንዲሁ “ታማኝ የታለ” እያሉ የዘፈኑለት አዝማሪው/ቀልደኛው/የኪነት ሰው/ፖለቲከኛ/ታጋይ/የስባዊ መብት ጠበቃ…..ታማኝ በየነ ዛሬ በማያሻማ አነጋገር ማንነቱን ነገረኝ። ለዚህም አናደደኝ፤ ስለሱም አፈርኩለት።
ታማኝን በመገሰጼ ብዙ ሰዎች እዚህ በመምጣትም ሆነ በየፎረሙ/ መድረኩ ሊንጫጩብኝ ይሆናል፡ ተንጫጪዎቹ ያላወቁልኝን ነገር ካለ እንዲያውቁት የምሻው ነገር አንድ ነገር ልበል። እኔ ትግል ስጀምር ገና በጣም እጅግ በጣም ወጣት ሁኜ ነው የጀመርኩት። ከዛ ጊዜ ጀምሮ እስከዚቺው ደቂቃ ድረስ ብዙ ጠላቶች አፍርቻለሁ፤ ብዙ ወዳጆችም አፍርቻለሁ። ትግል ውስጥ ስገባ እኔ ሁለቱንም እንዳፈራ ብየ አልገባሁም። ያከበሩኝ ሲጠሉኝ የጠሉኝ ሲያከብሩኝ እንደዚሁ ሲቀያየሩ አይቻቸዋለሁ። አትኩሮቴ ሁኔታው የምመለከተው ለእኔ ኢትዮጵያ በጣላት እንደ ተከበበች ሁሉ እኔም በተለያዩ ጠላቶች እንደተከበብኩ አውቃለሁና ልምዱም ስላለብኝ ብዙም ባትንጫጩ እና እራሰችሁን ሳታበሳጩ የምለውን ብቻ በአትኩሮት አገናዝቡት። መንጫጫቱ፤ስድቡ፤ ጋጋታው ያስደነግጠዋል የምትሉ ግሪን ካርድ አመልካቾች/ አዲስ መጤ የግንቦት 7 የሽምቅ ተዋጊ ሃይሎች ካላችሁ ጌታቸው ረዳን አላወቃችሁትም ማለት ነውና ብዙ ሳትለፉ ለምሰጠው ተግሳጽ ተገቢውን መልስ መስጠት ይጠበቅባችል።
እኔ ወያኔዎችን ስቃወም ከትግራይ ሰዎች ውስጥ እጅግ ጥቂቶች ነበርን። ያኔ ሲደርስብኝ የነበረው የጎሳ ስድብ፤ የፖቲካ ስድብ፤ የማስፈራራት ስድብ በጣም በጣም ብዙ ነበር። በስሕተት ጎዳና እና በስሜት ተወጥረው ይጓዙ እንደ ነበር ስለማውቅ ጉዳይም አልቆጠርኩት። ከጊዜ ብዛት ሲሰድቡኝ የነበሩት ሰዎች ሁሉ ዛሬ አብረውኝ በመቆም የተቃዋሚ ድረ ገጽ በመክፈት ወያኔን ከኔ በባሰ ሲቃወሙ እና ሲዘልፉት ለማየት በቃሁ። ለዚህ ደግሞ እግዚአብሔርን አመሰገንኩት። አንዳንዶቹ ምን ይሉኝ፤ምን ይጽፉብኝ  እንደ ነበረም አልነገርኳቸውም። አንዳንድ ጽሑፋቸው ሳነበው ተክ ብየ እስቃለሁ። አንዳንዱ ዶክተርነቴን ይሰጠኛል አንዳንዱ ዶክተርነቴን ይነጥቀኛል። ምንነቴን ሳያውቁ ምን እያሉ ያሙኝ እንደ ነበር ሰዎች ስልክ ይደውሉልኝ እና የተናገሩትን ይነግሩኛል። ዛሬ ወያኔ ስለተቃወሙ ይቅር ብያቸው አውቄ እናዳላወቅኩባቸው በሆዴ ይዤው ከነሱ ጋር እስቃለሁ/በስልክም አወራለሁ።
ተሻሽለው ስላልተሸሻሉ ግን ”ገዛ ተጋሩ በሚባለው የሌሎኞቹ ዘረኞች ፓል ቶክ ክፍል ተጋብዞ “ኢመርጀንሲ” ከገጠማት ትግራይ አንቀጽ 39 በመጠቀም መገንጠል አለባት ያለውን የእነ ገብሩ አስራት” እና መሰል ጓዶቹ ደጋፊዎች ሆነው ብቅ ሲሉ ‘ያለኝን ሃሳብ ድረ ገጻቸው ላይ እንዲለጥፉት ስልከው “አልጣማቸው ነበርና ውጠውት ዝም ይሉ ነበር”። ሲያፍኑኝ፦ መጨረሻ የምተነፍስበት የግሌ ድረ ገጽ ከፍቼ በነፃነት አሁን አስተነፍሳለሁ። ሲያግዱኝ የነበሩትም፤የተበሳጩም፤ ያልተበሳጩም ተቃዋሚዎቼም  የማይቀወሙኝም በብዛት ከመላው ዓለም  እየጎበኙት ነው።  
ተወደደም ተጠላም “ታዋቂ ተቃዋሚ ሰዎች” ታቦቶች ናቸው እና አትንኩብን የሚሉ ካሉ  ጌታቸው ረዳ “የዘረኞች የአፍ ልፍለፋ ተዋጊ ቡድኖች ታማኝ ወይንም ኢሳት ወይንም ግንቦት 7 ተነካብን ብለው  ያሻቸው ቢቀባጥሩብኝ” መለስ ዜናዊ እንዳለው “የስኒ ላይ ማዕበል” ከመሆን አያልፉም እና ወደ ርዕሳችን እንቀጥል።  አዎ የሻይ ስኒ ማዕበል!
ቅዳሜ ዕለት አንድ የትግራይ ሰው ባለፈው ሳምንታዊ ዘገባህ ታማኝን አርበኛ ስትለው አንብቤ “ሰውየው እንዳለወቅከው” አውቄ ነበር። “አርበኛህ ይኼውልህ “የትም ዞሬ ዞሬ ትዝ አለኝ ሩሜ/ክፍሌ በማለት “እናት ክፍሌ” ብለው ከሚጠራው ለብዙ ዓመታት ከትግሬ ጋር እንዳትጋቡ’ እነሱ 5 ሚሊዮን እኛ 80 ሚሊዮን መግጠም አንችላለን” “ካንሰሮች” … ወዘተ እያሉ “ኢንተርሃሙዬ ቅስቀሳ በሚካሄድበት የጸረ ትግሬዎች ‘ካረንት አፌይርስ”ፓልቶክ  ክፍል ዘንድ በመሄድ “ሲያሞግሳቸው  አመሸልህ/ዋለልህ”  ብሎ የቀዳውን ቃለ መጠይቁ ልኮልኝ፤ ሳዳምጠው እውነትም ፡እኔም ሰው ነኝ (ወያኔዎቹ) በተለወጡ ቁጥር የኔም ስሜት በዛው ልክ ይለወጣል” ሲል ኢሳት ውስጥ የተናገረውን ትዝ አለኝ እና ፤እንዴ ለካ ይሄ ሰው የሚናገረው የሚያምነውን ነው ብየ አሁን ከሰነዘረው “ከናት ክፍሉ” ያስተላለፈውን ቃል በቃሉ ላስደምጣችሁ።
ቃለ ምልልሱ የምትመራው ሴትዮ በዕደሜ ባለጸጋ ነች ነው  የሚሏት።ዘረኛ በመሆኗ “እንደ ዕድሜዋ ስለማታስብ፤ አንቱታውን ሳልለግሳት” “ባንቺታ”ልጥራት።  በጣም ሲበዛ ድንቁርና እና ስሜት ጉራ እና ተራ ውሸት የሚያሸንፋት ጸረ ትገሬ አቋሟ በግልጽ ሳትደብቅ “ጸረ ትግሬ መሆኔን እና ከዛሬ ጀምሮ ዘረኛ መሆኔን እንድታውቁት” በማለት ሳይሰለቻት ሁሌም ደጋግማ እቅጩን በማስታወቂያ መልክ የምትናገረን “ዘረኛዋ ሙያየ ምስክር” የተባለችዋ ሴትዮ  ነበር መድረኩን/ቃለ መጠይቁን ለታማኝ በየነ እንዲህ ስትል ጥያቄዋን የምታስቀድምለት።
ሙያየ ምስክር “ወደ ኢትዮጵያውያን  ካረነት አፈይርስ የመወያያ መድረክ አንኳን ደህና መጣህ ይላሉ። አንተ ምን ትላለህ?”
ታማኝ በየነ “በጣም አመሰግናለሁ። ከረዥም ጉዞ እና አገልግሎት በላ ወደ እናት ክፍሉ ወታደር እንደተመለሰ ወታደር ይሰማኛል።በክፉ ጊዜ የማንለያይ ወገኖቼ እንደምናችሁ ብየ እጅ እነሳለሁ። እንደ ዱሮ እንደ መድረክ ሞያ ከሆነ ደግሞ እንግዲህ “ታማኝ በየነ እባላለሁ።ታማኝ በየነ ማለት ባመነበት የወሰነ፤ወስኜ የምሰራ፤ለምሰራው የማልፈራ፤ሳወራ ከሰውነት ጋራ….እላለሁ፤ እንደምናችሁ እያልኩ እጅ እነሳለሁ….።” (ታማኝ በየነ ካረንት አፈይርስ ከተናገረው የተወሰደ በከፊል 12/12/2011 በፈረንጅ አቆጣጠር)
ትዝ ይላችል “ከቅንጅት አመራር ሁለት ሰዎች እንጂኔር ግዛቸው እና ዳኛ ብርቱካን መዲቅሳ ለትግራይ ሕዝብ ይቅርታ ሲጠይቁ”? ያኔ እኔ ሁለቱም ሰዎች ይቅርታቸው መሰረት እንደሌለው ተቃዉሜ ነበር።  ቢያንስ ማፈር ነበረባቸው። አድርባይንት ወይንም ደካማ የፖለቲካ ዕውቀት……የፈለጋችሁት ስም ስጡት” ብቻ ተገቢ አንዳልነበረ አሁን አሁን የቅንጅቱ አባሎች እና አመራሮች ከኔው ጋር ተስማምተዋል። አሁን ከወር በፊት በቅርቡ እንኳ “አቡጊዳ” በተባለው ድረገጽ ላይ ስዊዘር ላንድ በሚኖር አንድ የቅንጅት አባል እና ጋዜጠኛ የተጻፈው ጥያቄ “ለጥያቄው የሰጠሁትን መልስ ይመልከቱ”።

ከአራት ዓመት በፊት እንዲሁም ለማስተዋስ እንዲመቻችሁ ስለ ብርቱካን የጻፍኩትን እንዲህ ይላል;- Why her group decided to come out with this bad publicity and communication is beyond believe. Her thoughts to apologize for Tigrayans on behalf of Kinijt is absolutely irresponsible and showed that there seems to be no potential buyer to her group if she and her supporters used such appology for cheap and temporary political gains and popularities. It is only a matter of time if I or she or her group are correct to appologize or not to appologize Tigrayans with such baseless ground of appology.”
በዚህ መልክ ሃቁ ዛሬ ምን እንደሆነ የምትረዱት ይመስለኛል። በወቅቱ ግን ብዙ ዘለፋ ተሰንዝሮብኝ ነበር (በቅንጀት ይቅርታ ጠያቂ ደጋፊ ወገኖች እና በወያኔ ትግሬዎች በኩል)።
ታማኝ በየነም በእዛው አዲስ (ዊርድ) ንግግሩ የታዘብኩት ነገር ቢኖር “”ፓወር ኮራፕትስ ፓወር” እንደሚባለው፤ ለዓመታት የገነባው ገናናነት ታማኝን “ኮራፕት” (ያበሰበሰው/ያበላሸው/ያጃጃለው” መሰለኝ። ሁሉም በኔ እጅ ነው ፤ብዙ ሰው አፍርቻለሁ፡ ሙዚቃው ለኔ ሕዝቡ ለኔ፤ዛፉ ድንጋዩ ወደ እኔ ይሰግዳል፤ያንጨበጭበልናል ወደ ሚለው “ፍጹም ዘላቂ እምነት”ራሱን እየመራ ይመስላል። ገናናነቱ እያደገ በመጣ ቁጥር “ኤምፓየርነት/ጉልተኛነት/ሃያልነት/ያበጠው ይፈንዳ/ የምን ይሆናሉ-ነት..” ስሜት በውስጥ እየተገነባ ይመጣል” ፍጹማዊ እውነታው ከሕዝቡ ሲለገስለት እና አውን ሲሆን መስመር ይዟል እና የሰው ፍጡር በመሆኑ ወደ “ዕብጠት”በመለወጥ ወደ ውሸት የመንፈስ አዘቅት ይዘፈቃል። “ስልጣን እና ታዋቂነት” ሞኛ ሞኝ ይሰሩሃል። እኛ እና እግዚአብሔር የሚለየን በዚህ ባሕርይ ነው። ለዚህም ይመስላል፤ የትግራይ ሕዝብ በሚሰደብበት እና ከትግራይ ሕዝብ ጋር ወይንም የትግራይ ደም ካለው ሰው ጋር እንዳትጋቡ; እንዳትበሉ; እንዳትጠጡ……እየተባለ በሚነገርበት “ራዲዮ ቴሌቪዚዮን ሊብሬ ዴስ ሚሌ ኮሊኒስ” የተባለው ለ1994 ቱ የሩዋንዳ የዘር ማጥፋት ዕልቂት ተጠያቂ ዘረኛ ራዲዮ  ዓይነቱ ወደ ሆነው “ኢትዮጵያን ካረንት አፈይርስ ዲስካሽን ፎረም” ወደ ተባለው ዘረኛ የፓል ቶክ ቡድን በመሄድ  “ትግሬዎች ምን ልትሆኑ ነው”በሚል ዕቡይ ስሜት ተወጥሮ መረን በመልቀቅ  “ወደ ኢትዮጵያውያን  ካረንት አፈይርስ የመወያያ መድረክ አንኳን ደህና መጣህ ይላሉ። አንተ ምን ትላለህ?” ብላ ዘረኛዋ የመድረኩ ዋና መሪዋ ስትጠይቀው
 “በጣም አመሰግናለሁ። ከረዥም ጉዞ እና አገልግሎት በላ ወደ እናት ክፍሉ ወታደር እንደተመለሰ ወታደር ይሰማኛል።”  ይህ እንዲህ ዓይነት ለእኛ ለትግሬዎች ጀሮ በጣም አስቀያሚ መልስ መስጠት የተገደደበት ምክንያት በግልጽ እንዲያብራራልኝ እጠይቀዋለሁ።
ታማኝ ገናናነቱን በገዛ እጁ እራሱ ኮራፕት/እያበላሸው/ እንዲሆን የመምጣቱ ጉዳይ ይህ ነጋሪ ምልክት ነው እላለሁ። ለተወሰነ ጊዜ ከዛው ከዘረኞቹ ምድጃ ተነጥሎ ቆይቶ አሁን ግን ተመልሶ ወደ ምድቡ በመመለሱ “ልክ ወደ እናት ክፍሉ ወታደር እንደተመለሰ ወታደር ይሰማኛል።” ሲል የታማኝ ምድብ ቦታ “በጸረ ትገሬነቱ ትግሬዎች ብቻ ሳንሆን ሌሎች ወንድሞቻችንም ጭምር ብዙ ጽፈው ያወገዙት የካረነት አፈይርስ ፓልቶክ ሩም እንደነበረ እና፤ ዛሬ ግን፤ ከብዙ ጊዜ በላ ወደ ምድብ ቦታው ወደ “ዘረኞቹ” መመለሱ በደስታ እና በኩራት ሲገልጽ “የገናናነት ብልሹነት ባሕሪ” (ገናናነትን በትዕግስት እና ባግባቡ ባለመንከባከብ) የመጀመሪያው ደረጃ ሳይሆን “ከፍተኛው የገናነነት ንቅዘት” ባሕሪ ነው።ለብዙ ሰዎች “ሥልጣን እና ገናናነት” የሚያጓጓ ቢሆንም ሁለቱም ነገሮች መጠበቅ ካልቻልክ እና ባሕሪያቸውን እና አጠቃቀማቸው ካላወቅክባቸው ንቅዘቱ እያደረ ቀስ እያለ ከጊዜ ብዛት ልክ ሰማይ የወጣህበትን ርቀት ያህል ወደ ቁልቁል ሰትወርድ አደገኛ አወዳደቅ ይገጥምሃል።
እነ ጋዳፊ እንደዚያ ሲንጨበጨብላቸው፤ ገናናነቱ ስላባለጋቸው እና አጠቃቀሙ ስላላወቁበት “ወደ ትዕቢት” በማምራት መጨረሻቸው ያየነው ነው። ታዋቂ ግለሰዎች ከዘረኞች እና ከማይገቡ ክፍሎች መደበላለቅ ካበዙ “እንዳልተከደነ ጠላ እያደሩ ይነፍሳሉ”።
የትግራይ ሕዝብ የፈለገው ቢቃወመኝ ጉዳዬ አይደለም፤ወይንም ጥቂት የትግራይ ሰዎች “ካረንት አፈይርስ ስለተቃወሙ” ወይንም “የካረንት አፈይርስ ስብስብ ዘረኛ ግለሰዎች የጠየቁኳቸውን ፍራንክ እና ሰላማዊ ሰልፍ ስለሚያዋጡልኝ እና ስለሚወጡልኝ” “ስለ ትግራይ ሕዝብ አቋማቸው ጉዳያችን አይደለም”  ስለ ዛቻው እና ቅስቀሳው ትግሬዎቹ ይቸገሩበት”……ትግሬዎች ካወገዙት ፓል ቶክ መግባት እና መልክታችንን ማስተላለፍ ሃጢያት የለበትም……..ወዘተ፣ የሚሉ ሰዎች በማወቅም ባለማወቅም ለዘረኞቹ “የዘምባባ ዝንጣፊ” እያቀበሏቸው እና “ዘረኛነታችሁ፤ ጸረ ትግሬነታችሁ ቀጥሉበት” እያሉ እያበረታቱ እንደሆኑ መታወቅ ይኖርበታል።
የሰው ልጅ የሚለካው በስብስብ፤ በሆሆታ፤ በገናናነት፤በደምጸ መረዋነት ሳይሆን “በሚከተለው መንገድ እና በሚያስተላልፈው የመልእክት ጥራት ነው” ከትግራይ ሕዝብ ጋር እንዳትጋቡ፤ አርቋቸው፤ ነቀርሳዎች ናቸው፤ ታማኞች አይደሉም፤ስልጣን ስይዙ አገር ይሸጣሉ.. “ካንሰሮች” ናቸው እና ከመለከአ ምድራችን ቀፍፈን አናሰወግዳቸው” ከሚሉ የተለያዩ ዘረኞችና ክፍሎች ጋር መተሻሸት ወይንም እጅ መንሳት ወይንም ማመስገን ፤ጣምራ ትግል ማካሄድ፤ በበኩሌ መወገዝ ያለበት ያልተቀደሰ አካሄድ ነው።
ዘረኞቹ  እነ ሙያየ ታማኝ በየነ እንዳለው “በክፉ ጊዜ የማይለያዩ ወገኖቹ” ከሆኑ እነኚህ ደንቆሮዎች ሊያመጡብን የሚመኙትን ክፉ ቀን አብሯቸው እንደማይደባለቅ ተስፋ አድረጋለሁ። እሱ እንደሚለው “ታማኝ በየነ ማለት ባመነበት የወሰነ፤ወስኖ የሚሰራ፤ ለሚሰራው የማይፈራ ከሆነ ወደ እዛው ምድብ ቦታው መመለሱ ደስ ያለው ይህ “የካረንት አፈይርስ ምድብ ወታደር” አስቦበት እና ወስኖ የተቀለቀላቸው ስለሆነ ለዛውም ምንም  ፍራቻ እንደሌለው እና ቅሬታ እንደማይሰማው ስለነገረን በገዛ እራሱ ገናናቱ ለማበላሸት “ቁልቁለት አፋፍ” ላይ እንዳለ ገናና ወታደር እንደሆነ ስነግረው በወንድማዊ ምክር ልብ እንዲለው ይህ መልእክት አስተላልፍለታለሁ። ታማኝ የትግራይን ሕዝብ ዘላፊዎች እና መጥፎ ተመኚዎች “ምድብ ቦታየ” ነው ብሎ በካረንት አፈይርስ ወታደርነት ለማገልገል “ወስኖ ከተነሳም” ትግሬዎች እንደሚሉት “ከይኮነ ለብም፤ ከይተሰብረ ጸግን” (ከመሆኑ በፊት ልባም ሁን ከመሰበሩ በፊት ጠግን”) ይላሉ። አመሰግናለሁ። ጌታቸው ረዳ (ኢትዮያን ሰማይ) www.ethiopiansemay.blogspot,com getachre@aol.com