Tuesday, November 9, 2021

ጸረ ትግሬ አማራዊ ኢንተርሃሙዌ የለም ብላችሁ ለጠየቃችሁ ወገኖች ጌታቸው ረዳ (Ethio Semay) ዕለተ ማክሰኞ 11/9/2021

 

ጸረ ትግሬ አማራዊ ኢንተርሃሙዌ የለም ብላችሁ ለጠየቃችሁ ወገኖች

ጌታቸው ረዳ

(Ethio Semay)

ዕለተ ማክሰኞ

11/9/2021

ይህች የምትመለከትዋት የትግራን ማሕበረሰብ ስትሰድብ የሚያሳይ ሲሆን  በሁለተኛው ፎቶግራፍ ላይ ትግሬዎችን በዝምብ መግደያ ፍሊት ረጭተን መግደል አስፈላጊ ነው እያለች በዩቱብ ጥላቻን ስታሰራጭ ከቀዳሁት መዝገብ ነው። 

ዘረኛ አማራ በጣም ብዙ ነው። አማራ “ኢንተርሃሙዌ” የለም ለምትሉ ሰዎች ሳታውቁም ሆነ በማወቅ ዘረኘነትን “በአንድ ሰው ወይንም ጥቂቶች” ብቻ ናቸው በሚል ለማጣጣል የምትሞክሩ ሰዎች ታዝቤአለሁ። በመንግሥት ደረጃ ጎንደር፤ ጎጃም ወሎ ሸዋ…. ንጹሃን ትግሬዎች እየተለቀሙ እስር እየተወረወሩ ነው። ከሥራ ተባርረዋል፤ ቤተሰቦቻቸው አስተዳዳሪዎቹ ስለታሰሩ ለችግር ተጋልጠዋል።

የድሮ ወዳጆቻቸው እንደ ድሮ በበጎ እየተመለከትዋቸው አይደሉም። አንዳንድ ቦታ ላይ ሰላምታቸውን አቁመዋል። በዘረኞች የተገደሉ ሰዎች አሉ። በየፌስቡኩ እጅግ በርካታ የሆነ “አማራዊ ኢንተርሃሜዌ” እና “ትግራዊ ኢንተርሃሙዌ” በዘረኛ ቃላት እና ዛቻ ሲጠዛጠዙ እናነባለን። አንዳንዶቹ በዚህ ፌስ ቡኬ እየመጡ የሚጽፉትን አንብቡ።

እኔ አማራዊ “ኢንተርሃሙዌ”ቡድን መታገሉ የጀመርኩት ዛሬ አይደለም። በጣም ቆይቷል። ለምሳሌ እጅግ መረን ለቅቆ የነበረበት በ2014 ከ7 አመት በፊት የጦፈ ትግል አድርገን አርፈው ነበር። ቤተ አማራ የተባለው “አማራዊ ኢንተርሃሙዌ” ምን ያሰራጭ ነበር? መርምሩ! በርካታ የሆኑ የተለቀቁ ዘፈኖችን አድምጡ። የትምክሕቱ ጠረን የት የሌለ ነው።

ይልቅኑ ፤ ሁለቱንም ዘረኞች መታገል ማሕበረሰቡ ተረጋግቶ እንዲኖር ሰለሚረዳ ፤ በዚህ ጥላቻ የሚታዩ ሰዎች በቁጥር  “አንድ ነው” “ጥቅቶች ናቸው” የሚለው ማጃጃያ ባንለምደው ጥሩ ነው። እነ “የሱፍ ኢብራሂም” እና “መሳይ መኮንን” እንዲሁም በርካታ አማራዊ ኢንተርሃሙዌች ብዙ ተከታይ አላቸውና ዘረኛነታቸውን ማውገዝ ‘ለሁሉም’ ደህንነት ይበጃል። ይልቁን ፋሺሰቱ አብይ አሕመድ”ብድሩ እስኪያገኝ” ድረስ  “ጸረ ንጹሃን ትግሬ አፋሳውንና ማስጨነቁን እንዲያቆም” ድምጽ ሁኑን።ታሪኩ ጋንጊሳ የተባለ የዋህ የሰላማዊ ሰላም ዘፋኝ እንዴት እንደወረዱበት ሰምታችሗል አደል? ኢንተርሃሙዌው ማንም ይሁን ማንም በመንገዱ ካልሄድክ ወደ አራዊትነት ይለወጣል።

ከአማራዊ “ኢንተርሃሙዌው ቡድን ጋር ትግሉን የጀመርኩት ዛሬ ሳይሆን በ2006 እና በ2014 ያደረግኩዋቸው ቃለ መጠይቅ ብዙዎች ታስታውሱ ይሆናል (የኔ የድሮ ተከታዮች) ። “ኢካዴፍ” የተባለ የግንቦት 7 አቀንቃኝ የነበረ “ቃሌ” በሚባል የፓልቶክ ክፍል ሻዕቢያ እና ጽንፈኛ አማራዎች በጋራ በመቀናጀት በትግሬው ላይ የሩዋንዳ ራዲዮ ያክል የጥላቻ ቅስቀሳ ሲያሰራጩ ይፋ የሆነ ውይይት ሲያደርጉ የተቀዱ አውዴዎች አሁንም ከኔ ጋር አሉኝ።

አንድ ጋዜጠኛ የጻፈፈልኝን ልጥቀስ;

““…ሐቁ ይህ ሆኖ ሳለ ነብሰ ገዳዩ የወያኔ ቡድን አማራ ክልል በሚኖሩ ትግሬዎች ላይ ጥቃት ተፈጽሟል እያለ መሠረተ ቢስ አሉባልታ እያወራና እናንተም ይህንን በሬ ወለደ አታስተጋቡ። …አማራ ማሕበረሰብ ሲፈጠር ዘረኞች አልበቀሉበትም” ይላል።የአማራ ዘረኛ የለም። እያለ ነው። ይኸ ዕብደት ብቻ ሳኢሆን “ትምክሕት” ነው” በረዢም የፖለቲካ ትግል ዘመኔ ብዙ እያወቁ የመሰላቸው  ደንቆሮዎች አየሳቅኩ የታዘብኳቸው በርካታ ናቸው። ግማሾቹ አሁን የፋሺስቱ አብይ ደጋፊዎች ሆኖው ሳያቸው ከትንሽየ ሕሊናቸው አንጻር ሳስበው አልገረመኝ። 

 ከአማራ ቤተሰቦች የተወለደ አማርኛ መናገር የማይችል ኢትዮጵያዊ ካናዳዊው ወጣት “በየዋህነቱ ወደ አብይ ደጋፊ አማራዎች ተቀላቅሎ “አብይን ሲያወግዝ” ሰምተውት “ሰክዩሪቲ፤ፖሊስ ጠርተው ሁለት ፖሊሶች መሬት ላይ ጥለው ጉሮሮውን አንቀው ደረቱን ደፍጥጠው ሊገድሉት እንዴት እንደቃታቸው ትዝ ይላችሗል (ያኔ በማርች 24/2021 በፌስቡኬ የጻፍኩትን እዩት። ተያይዞ በቀረበው ቪዲዮ “በግንቦት 7 /አብይ አሕመድ ደጋፊ ኢዜማ” ቡድን እና “የአማራ የዘር ጭፍጨፋ ለዓለም እናሳውቅ” በሚሉ ቡድኖች መካከል ልጁ ጸረ አብይ በመናገሩ አሰቃዩት።) 

ለወገናቸው ያልራሩ እነዚህ “የኦሮሙማ ፓወር” አስቀጣዮች ”ኢዜማ ውስጥ የተሰገሰጉት እነ መሳይ መኮንን ‘አማራዊ የአብይ ኢንተርሃሙዌ’ ቡድኖች” ካልሆኑ ምን ሊሆኑ ይችላሉ? ለወገናቸው ለዚህ ህጻን ያልራሩ ለትግሬው ምን ይራራሉ ብላችሁ ታስባላችሁ? 

ዘሬ ደግሞ አገርሽቶአቸዋል። ኢንተርሃሙዌው የሚለቀው ዘለፋ በርካታ ነው። “በትግራይ ሕዝብ ፎቶግራፍ ላይ “ዝምብ የሚገድል “ፍሊት” እየረጩ” ፎቶግራፎች እስከማሰራጨት  ጀምሮ “ከቅማላም ጀምሮ እስ “ቁልቋል በሊታ” እና “አጋሜ” “አገርህ ግባ” የሚሉ ቅስቀሳዎች ከሁቱ የ አርቲ ኤል ኤም ቅስቀሳዎች አይተናነሱም። ይህ ጥላቻ በብዛት ተሰራጭተዋል። ጀነሳይድ በአንድ እና በጥቂት ሰዎች ነው የሚጀምረው። ጀርመን የተጀመረው በአንድ ሰው ቀስቃሺነት ነው፤ ሩዋንዳም “በአንድ ራዲዮ ጣቢያ” ቀስቃሺነት ነበር የጀመረው። ስለዚህ ረጋ ብለን እናስተውል።

ፍረዱ እንግዲህ ምንም ወንጀል ያልተገኘበትን ወንድሜ 5 ወር አስረው አሰቃይተው፤ ከሥራው ተፈናቅሎ፤ መጨረሻ ማስረጃ አላገኘንበትም ብሎ ፍርድ ቤት ያሰናበተው፤ አሁን በጅምላው እስራት አርሱንም መላው ቤተሰባችንም ሰብስበው አስረዋቸዋል (ፖለቲካው ውስጥ ምንም የሌሉበት) ። በዛሬይቱ ኢትዮጵያ መኖር ይቅርና መሞት አልቻልንም የሚለው ወዳጄ አምባቸው ደጀኔን ጽሑፍ አላነበባችሁም? ንጹሁን ትግሬ የሚጨምር የጅምላ እስራት አሁን ለንጸሃን ትግሬዎች ኢትዮጵያ ሳውዲ አረቢያ ኦናባቸዋለች። 

ጌታቸው ረዳ (Ethio Semay)