Thursday, November 22, 2018

ለጌታቸው ረዳ ኢትዮጵያን ሰማይ አዘጋጅ የተጻፈ ደብዳቤ..ጀግና ተስፋ አይቆርጥም! (ከ ፍሥሐ አንዳርጌ)


 
ለጌታቸው ረዳ ኢትዮጵያን ሰማይ አዘጋጅ የተጻፈ ደብዳቤ
 
ጀግና ተስፋ አይቆርጥም!

(ከ ፍሥሐ አንዳርጌ)
 
ለውድ ሀገርህ ኢትዮጵያ ምን ያህል ተቆርቋሪ እንደሆንክ በወሬ ሳይሆን በተግባር አሳይተሃል፡፡ የህወሓትንና ኦነግን ጸረ-ኢትዮጵያዊነት በጠንካራው ብዕርህ ተዋግታሃቸዋል፡፡ በነዚህ ጸረ-ኢትዮጵያና ጸረ-አማራ  ድርጅቶች በአማራ ህዝብ ላይ የደረሰውን ግፍ  ለመላው አለም ህዝብ አጋልጠሃል፡፡ ከዚህም አልፎ ህወሃት አማራን ለምን በጠላትነት እንደፈረጀው መጽሃፍ በማዘጋጀት እውነታው  እንዲታወቅ አድርገሃል፡፡

በሚገባ እንደምትገነዘበው ዛሬ ያ የደከምክለት ህዝብ( አማራ) ተደራጅቶ ትግሎን እያቀጣጠለው ይገኛል፡፡ ለህውሓትም ሆነ ለኦነግ  ትልቅ ራስ ምታት የሆነው  የአማራ ህዝብ መደራጀቱና  በወልቃይትና በራያ ታሪካዊ ቦታዎቹ  ላይ  የማያወላውል  አቋም ይዞ ወደፊት እየገሰገሰ መሄዱ  ነው፡፡  በስንብት ጽሁፍህ ማለትም “መልካም እድል ለኢትዪጵያ ህዝብ እመኛለሁብለህ እንደ ገለጽከው ህወሓት ይህን የአማራ ህዝብ  መደራጀት በመፍራት ነው አሁን የመገንጠል ሴራ እያራመደ የሚገኘው፡፡ ይሁን እንጅ ህወሓት ከአሁን በኋላ ከአማራ ክንድ እንደማያመልጥ ምልክቶችን  እያየን ነው፡፡ እርግጥ ነው በህወሓት መሰሪነት ምክንያት የአማራና የትግራይ ህዝብ መጥፎ የሚባል ቅራኔ ውስጥ መግባታቸው የማይቀር ነው፡፡ ለዚህም ዋናው ምክንያት የወልቃይትና የራያ የማንነት ጉዳዮች ናቸው፡፡

ይህችን ደብዳቤ ልልክልህ የተነሳሳሁት ስለ ህወሓት ጸረ-ኢትዮጵያዊነት ለማስረዳት ሳይሆን የስንብት ጽሁፍህን በማየቴና ያበሳጨህንም ምክንያት ስላነበብሁ ነው፡፡

በእርግጥ የኢትዮጵያ ህዝብ ለእንደ አንተ አይነቱ   ቆራጥ  ኢትዮጵያዊ  ብዙ ተስፋ የሚያስቆርጡ ድርጊቶች በብዛት ይታይበታል፡፡ ለሁሉም ነገር በጀምላ ማጨብጨብ፤ ለወሬኞች ምላሰ እጅ መስጠት ፤ትዕግስት ማጣት፤ በቁጥር ቀላል የማይባለው ኢትዮጵያዊ ደግሞ ለጊዜአቂ ጥቅም ሲል ሀገሩን አሳልፎ  ለጠላት መስጠት የመሳሰሉት በብዛት የሚስተዋሉ ችግሮቻችን  ናቸው፡፡ ይሁን እንጅ  በቁጥር ጥቂት ነገር ግን በሞራል እጀግ ጠንካራሆኑ ኢትዮጵያዊያን አንተን ጨምሮ በምታደርጉት ተጋድሎ እየተስተዋለ ያለው ችግር ቀስ በቀስ እየሟሽሸ  ይገኛል፡፡

ይህ ትግል  በአንተና በሌሎች መሰል ቆራጥ ኢትዮጵያውያ መቀጠል አለበት፤ ከጎንህ ብዙ ደጋፊና ታጋይ እንዳለ አትርሳ፤ጅግና ተስፋ አይቆርጥም፡፡ የሻዕቢያውን መሬ  ጎንደር ላይ የተመለከትከው የአክብሮት አቀባበል ትዕይነት  በኢትዮጵያ ላይ ሻዕቢያ  ካደረሰው ግፍ እንፃር ሲታይ እጅግ ያበሳጫል፤ ብትበሳጭ አይፈረድህብህም፡፡ ምክንያቱም ኢትዮጵያ አሁን ለደረሰችበት ቀውስ ዋናው ተጠያቂ ሻዕቢያ በመሆኑ፡፡ ህወሓትን ኮትኩቶ በማሳደግ ኢትዮጵያን እንዲያፈራርስ ያደርገው  ሻዕቢያ ስለሆነ፡፡

ይሁንና አንተም በሚገባ እንደምታውቀው ፖለቲካ እጅግ ተለዋዋጭ ነው፡፡ሁለቱ ጸረ-ኢትዮጵያ ኃይሎች ለጊዜውም ቢሆን ባላጣ ናቸው፡፡ አሁን ህወሓት ብቻውን ነው፡፡ ህወሓትን ለማስወገድ የሻዕቢያን ኃይል መነጠል እጅግ ጠቃሚ ስለመሆኑ እንተን ማስረዳት አይቻልም፡፡ህወሓት ብቻውን የትም አይደረስም፡፡ አማራና ህወሓት ወደ ጦርነት መግባታቸው የማይቀር ሀቅ ነው፡፡ ለዚህ ደግሞ ሻዕቢያን ከህወሓት መነጠሉ ተጊቢ መስሎ ይታየኛል፡፡ይህ ማለት ግን አማራም ሆነ ኢትዮጵያ ከቀይ ባህር ጋር በተያያዘ የላቸውን ጥያቄ አቆሙ ማለት እንዳልሆነ ግልጽ ነው ነገር ግን ሁሉም ነገር በቅድም ተከተል መሆን እንዳለበት አምናለሁ፡፡

ስለዚህ  ጎንዳር ከተማ  የተመለከትከውም ሆነ የአዲስ አበባው  የኢሳያስ አቀባበል ትዕይንተ ሊያበሳጭህ ቢችልም ከትግልህ  ፈቀቅ ሊያደርግህ ግን አይገባም፡፡ ጀግንነት የአንድ ወቅት ተጋድሎ ሳይሆን የእድሜ ልክ ስጦታ ነው፡ ከጀግኖች  አባቶቻችን የተማርነው ጀግንነት እስከ እለት ሞት ድረስ መሆኑን ነው፡፡

ስለሆነም የአንድ ከተማ ትዕይንት ወይም የአልነቃው ህዝብ መብዛት ከትግልህ ሊያሽሽህ አይገባም፡፡ ከአሁን ቀደምም ከሚዲያው ላለተወሰነ ጊዜ ሽሽቻለሁ ብለህ እንደነበር እስታውሳለሁ፡፡ ምን አልባትም ለሀገርህ ያለህ  አቋም እጅግ ጠንካራ ስለሆነና ከሌሎች ኢትዮጵያዊያን የምትጠብቀውን ጥንካሬ ማየት ባለመቻልህ ይመስለኛል ተስፋ እያስቆርጠህ የሚገኘው፡፡

አብዛኛዎችን ጠቃሚ ጽሁፎችህን አንብቢያቸዋለሁ፡፡ ብዙዎቻችን በመረጃነት እየተጠቀምንባቸው ነው፤ ይህ ትልቅ ነገር ነው፡፡ይሕ ደግሞ አንተ ለምትጓጓላት ኢትዮጵያ እውን መሆን አስተዋፆ እያደረገ መሆኑን ማወቅ በራሱ ተጋድሎህን እንድትቀጥልበት ያደርጋል እንጅ እንድትሸሽ አያደርግም፡፡

አመንክም አላመንክም በበኩሌ ስለ አንት ለጓደኞች ሁሌ የምናገረው ነገር አለ፤ እርሱም ስልጣን ቢኖረኝ ኑሮ በክብር ከምሸልማቸው ሰዎች መካከል አንዱና ብቸኛው ትግሬ ጌታቸው ረዳ ነው እያልሁ ነው የማዎራው፡፡ ምን አልባትም አንዲህ አይነት አክብሮት የሚሰጡህ ብዙ ይሆናሉ ብየ አምናለሁ፡፡

ስለዚህ ለእናት ሀገርህ  ከምታደረገው ትግል አትሽሽ፡፡ ብዙ አድናቂና የአንተን መረጃ ተጠቃሚ  እንዳለህ አስታውስ፤ ጀግንነት መሸነፍ ሳይሆን እስከ መጨረሳዋ እስትንፋስ መታገል ነው፡፡ ስለሆነም የስንብት ሀሳብህን እንደምትሽረው ተሰፋ በማድረግ የሚቀጥለውን ጠንካራ ጽሁፍህን  ለማንበብ  ተስፋ አደርጋሁ፡፡

ከፍስሃ አንዳርጌ