Saturday, April 27, 2019

ለማኙ አብይ አሕመድ እና ደፋሩ ሓቢብ ቡርጊባ ጌታቸው ረዳ (ኢትዮ ሰማይ)



ለማኙ አብይ አሕመድ እና ደፋሩ ሓቢብ ቡርጊባ
ጌታቸው ረዳ (ኢትዮ ሰማይ)
ለረዢም አማታት ትችቶቼን የተከታተላችሁኝ ሁሉ ፈረንጆችቦልድየሚሉትፈጣጣትችቶችን የምተች ተቺ መሆኔን ታውቃላችሁ። በዚህ ባሕሪየ ብዙ ጠላት አፍርቻለሁ።ደፋር እንጂ አጎብዳጅ አለመሆኔን እጅግ ደስ ይለኛል። በኢትዮጵያ ማሕበረሰብ ተወዳጁና ተጠቃሚው አጎብዳጁ እና አጭበርባሪው ክፍል እንጂ ደፋር እና ቅን ተወዳጅም ተሞጋሽም እምብዛ አይደለም። ይህንን አውቃለሁ። ታሪካችንም ይህንን ይነግረናል።

አጼ ቴዎድሮስ በደፋርነታቸው ብዙ ጠላት ተገንብቶባቸው መጨረሻ እርሳቸውን/ንጉሡን/ ያጠቁ መስሎአቸው አገሪቷ በወራሪው እንግሊዝ እንድትደፈር ተባባሪዎች ሆነውእርሳቸውም ቅርሶቻችንም እና የንጉሡን ባለቤት እንዲሁም ልጃቸው ለሕልፈተ ሞት ለመዳረጋቸውየቴዎድሮስ ጠላቶች ዋነኞቹ ተጠያቂዎች ነበሩ።ንጉሡ ያቀዱት ሰፊ ዕቅድም ባጭሩ ተቀጨ።

በትግሬነቴ ስለ ትግራይ ማሕበረሰብ ያለኝን ትችት ከሌሎቻችሁ የተለየ መሆኔንም ታውቃላችሁ። የትግራይ ሕዝብ እራሱ ነፃ ለማውጣት ሳይፈልግ ታፍኗልና እኛ ነፃ እናውጣውእያሉ የሚፏክቱ ምሁራን በጣም በርካታ ናቸው (98%ማለት በሚያስችል) ለዚያ ሕዝብ ምን እናድረግለት? እያሉ ሕዝቡ ነፃ አውጡኝ ብሎ ሳይጨነቅ ስለ ሕዝቡ የሚጨነቁ ሰዎች ገጥመውኛል። በፖለቲካ ወቅቴ ውስጥ እንዲህ ያለ አስቂኝ ገጠመኝ (አስተሳሰብ) ያስገረመኝ የለም።

በንጽጽሩ እኔም እንደ አጼ ቴዎድሮሰ ጠላቶቼ እኔን ያጠቁ መስሎአቸው የምጽፋቸው ሃገራዊ ትችቶች በየሚዲያው ለሕዝብ እንዳይሰራጩ የተቻላቸውን ያህል ለበርካታ አመታት በማገድ ጥረዋል። አንዳንዶቹም ሲነሽጣቸው ሊንክ ያደረጉትን (ያያዙትን) የድረገጼ ማስፈንጠሪያቸው ሰርዘው ከድረገጻቸው ማስፈንጠሪያ ሊስት (ዝርዝር) በማስወጣት ከድረገጻቸው ያጠፉታል። ከሚያስቁኝ ብቻ ሳይሆን የሰዎች ትንሽነት ምን ያህል መሆኑንም ከሚገርመኝ አንዱ ከትግሎቼ ዘመን ገጠሞቼ ያየሁት ክስተት ነው።

 ይህ ክስተት ኢትዮጵያውያንን በደምብ የሚገልጽየቂመኛ የድንቁርና እና የግልፍተኛ ባሕሪመለያ ነው። ኢሳት የተባለውታማኝ በየነበበላይነት የሚያስተዳድረው ጣቢያ በቅርቡ በሁለት እውቅ ጋዜጠኞች ማለትም በቴዎድሮስ ጸጋየ (የርዕዮት ሚዲያ አዘጋጅ) እና የኢሳትዋ ጋዜጠኛ / ርዕዮት አለሙ ላይ የፈጸመው የመናገር መብት አፈና ጉልህ ማስረጃ ነው። በታማኝ በየነ”!በታማኝ በየነ”!  “በታማኝ በየነ”! ስተዳደር!
ከዚያ አስታክኮ በጉራጌው ምሁር በዶ/ በዕድሉ ዋቅጅራ እና እርሱን በሚመስሉጠባብ ብሔረተኞችበቴድሮስ ጸጋየ ላይ የተሰነዘረውዘረኛ ዘለፋየሚያሳየን ክስተትኢትዮጵያውያንከቂም፤ ከዘር እና ከአጎብዳጅነት ባሕሪ ገና ያልወጣን መሆናችንን የሚገልጽልን ክስተት ነው።

ለዚህ ነው እኔም ለረዢም አማታት በዛው በአፈና ብትር እየተቀጠቀጥኩ የዘለቅኩት። 27 አመት ያየነው የምሁራን ውድቀት ደጋግሜ፤ ደጋግሜ ስለተቸሁበት ለአንባቢዎቼ አዲስ አይሆንባችሁም። ምሁራኖች እና ድንገት የተከሰቱ የአገሪቱ መሪዎች የሚረባረቡት አፍ መፍቺያቸው ያደረጉት በሞጉእ መውቀጫ አገሪቱን መውቀጥነው። ወጣቱም በዚያ ወረርሺኝ ተበክሎታሪኳን ባሕልዋን ሃይማኖትዋን ማንኳሰስ ነው።
ካንዱ ሃይማኖት ወደ ሌለ ሃይማኖት መገለባበጥ ታሪክ ለፖለቲካ ፍጆታ ማጣመም ሰንደቃላማን ማርከስየተለመደ ሆኖ በደናቁርት ሥልጣኔ ወረርሺን ተበክሏል።

ዛሬም እንዳለፈው በብልጣብልጡ አብይ አሕመድአሳሳች ስብክትከድጡ ወደ ማጡ ተጃጅለን ሕዝባችን ባልተጠበቀ የድረሱልንእሪታ ውስጥ ከትተነዋል።

አብይ አሕመድ የሚመራው የአናርኮ ፋሺስቱ ስርዐት አወዳሾች እና ጠበቃዎች የስርዓቱ ወንጀሎች እንዳይጋለጡበአወዳሽነትበመተባበር እንቅፋት እየሆኑ እንደሆነ ጥቂት ሃገራውያን ተቺዎች ጥቂት ቢሆኑም ብርቱ ማስረጃቸውን ይዘው ቢከራከሩም በራሱ በአብይ አሕመድም ሆነ በደጋፊ ጋዜጠኞቹ እና ምሁራኖቹ ተባባሪነት እውነት እየታፈነ ይገኛል።

ሃገራውያኖቻችን እየደረሰባቸው ያለው የማስፈራራት ውርጅብኝ ሁሉም ያደመጠው ሃቅ ነው። እስክንድር እና አዲስ አበቤዎችን፤ቴድሮስ ጸጋየን፤ የኢሳትዋ ርዕዮት ዓለሙን….እና አገር ውስጥ በሚኖሩ ሃገራውያን ላይ እየደረሰባቸው ያለው ወከባ ዘለፋ እስራት ዛቻ እና አፈና ማየት የወቅቱ የተለመደ ክስተት ነው። የአናርኮ ፋሺሰቱ ሥርዓት አስተዳዳር ያልተጠበቁ ክፉ ክስተቶችን በደበቃቸው ባሕሪዎቹ ሳያስበው ድንገት እየፈነዱበት ይፋ እየወጡ ነው። በጣም በርካታ ክስተቶችን  እያሳየን ነው።

ስለ አዲሱ የአማራአፓርታይድ አስተዳደር/ክልል/ መሪው ከታች ስለምጠቅስ አስቀድሜ ይህንን ልበል። ሰዎች ስርዓቱንም ሆነ አድርባይ ምሁራኖችንበስድብ መግለጽነውር ነው ይሉናል። ስድብ ዝምብሎ አልተፈጠረም። መጽሐፍ ቅዱስም፤ ቁርኣንም ስድብ ይጠቀማሉ። ስድብ የተፈጠረው ለጉዳይ ነው። ጥፋት እየፈጸሙ፤ ተው ተብለው ሳያርሙ መልሰው አንተኑን የሚዘልፉ፤ ሕዝብን እያሳሰቱ አገረቱ በምትዋዥቅበት ምንገድ እንደትሄድ አስተዋጽኦ የሚያደርጉ የአምባገነን ደላሎችን ለመግጽ የተፈጠረ የመገለጫ መንገድ ነውና በዚህ እንስማማ። ቅዱሳን መጻሕፍትን አንብቡ! የስድብ ተቀባይነቱን ታያለችሁ።

 አማራውን በአዲስ መንፈስ እመራለሁ ብሎ ምሎ ተገዝቶ የመጣ አጎብዳጁአምባቸው መኮንንየሰሞኑን አስገራሚ ንግግሩን ሰምታችል። እርሱና አቶ ንጉሱ ጥላሁን የተባሉ እነኚህ ሁለት አማራዎች ሕገ ምንግሥቱ አግላይ ነው፤ አንዱ ባለቤት ሌላው እንደ የእንጀራ እናት የሚያይ  ሕገ መንግሥት ነው እያሉ ሲኮንኑና ሲመጻደቁ ተራማጆች መስለውጉራቸውንሲነዙ ከርመው ቀስ በቀስ ከምላሳቸው የሚደመጠው አድርባይነትን ስትመለከቱ የሚገርሙ ሰዎች ናቸው።

ልክ እንደ አብይ አሕመድ እነዚህ ሰዎችም የደበቁት ባሕሪያቸው ሳያስቡት ድንገት ከውስጥ ፈንድቶ ሲደመጥ ማንነታቸውን ሲገልጹልን ሰምተናቸዋል። በቅርቡ / አምባቸው  መኮነን የተባለው የአማራክልልፕረዚዳንትአዲስ አባባን በሚመለከትተጠይቆ የኦሮሞን ልዩ ጥቅም ለማስጠበቅ እስከመጨረሻ እንታገላለንብሎን ቁጭ!  

ሙሁራኖቻችን ማሕበረሰብን በአግባቡ መምራት የሚያስችል የትምሕርት ክምችት ቢኖራቸውም፡ ምክንያቱ ባልተፈተሸ ባሕሪያቸው ምክንያትለመጣ አዲስ ገዢ  እያጎበደዱ ያልነቃውን ማሕበረሰባችን ከድጡ ወደ ማጡ እየከተቱት የጠየቅነውን ፍትሕ የማንገሥን ጥያቄ እንዲዘገይ ጎታች ሃይል ሆነዋል።

አብይ አሕመድ የተማረ ነው። ስትመለከቱት ግን 14 አመቱ ጀምሮ አስካሁን ድረስ ለወያኔ ሥርዓት በማገልገል ያደገ ወጣት ነው። ልዩ የሚያደርገው የዚህ ወጣት መሪ ባሕሪ ግን በራሱ አንደበት የነገረንየአመራር ብቃት ችሎታሳይሆን የልመና ችሎታ ከፈጣሪው እንደተሰጠው ነው ሳይሸሽግ የነገረን። ስለሆነም ሰርዓተ አልበኞቹ የሕዝብን ህይወት ሲያናጉ በሽብር አገሪቷን ሲበጠብጡ የደቡብ ሕዝባችን እስከ 80 ሺሕ የሚቆጠር ሕዝብ ከመኒኖሩበት ቦታ በአንድ ሳምንት ውስጥውጡ!” ተብለው ተባርረው እየተደበደቡ እየሞቱ እየተፈናቀሉ እያየ (800 ሺሕ የሚቆጠር) ምንም አርምጃ አልወሰደም።

ሁኔታው እንዲቀጥል እና እንዲባባስ የመሆኑ ምክንያት የአብይ አመራር የብቃት ማነስማሳያ ነው። እርሱ የሚያምነው ሽብርተኞችን አለመቆጣጠር ማለት ትርጉሙ፤-
በግጭት የማያምን ቀና እና ሽብርተኞችንም እንደ ሰላማዊ ዜጎች በእኩል ዓይን የሚያይ አባብሎ ለምኖ ዝም የሚያሰኛቸው አምባገነን ያልሆነ ዲሞክራቲክ መሪ ነው ያስብለኛል በሚል እምነት የተቃኘበት ስልቱ ነው። ስለሆነም ባንክ ዘራፊዎች እና አፈናቃዮችንበተሰጠው የልመና ችሎታለምኖ ለማስታገስ እየጣረ ያለውም ለዚህ ነው።

ሽብርተኞችን ለምኖ ወደ አስመራ ሄዶ አስመጥቶ ሲያበቃ ሽብርን በከፋ መልኩ በሕዝባችን ህይወት ላይ አፋፋመ። ለማኙ መሪሰርዓተ አልበኞችን ማስቆምአልቻለም። የተካነበት የልመና አስተዳደርም አልሰራም! ከቶውንም እየለመኑ ማስተዳዳርቅዠትእንጂ ከዘመኑ ጋር አይሄድም።አገር በድፍረት እና በሕግ እንጂ በልመና አይቀናም።መሰራት ያለበትን መስራት፤መደፈር ያለበትን ንግግር በድፈረት ተናግሮ የመሪው አቁዋም ማንነት ማሳወቅ የመሪ ዋና መመሪያው መሆን አለበት።

ሳይሸሽገን ደፍሮ የነገረን ደብቆት የቆየ አንድ ባህሪው ግን ነግሮናል። እርሱም በጦርነት አላምንም ሲለን ቆይቶአስክንድር ነጋን ለማሸማቀቅ በሓሰት ወንጅሎ መፈንቅለ መንግሥት ሊያርግብኝ እየዶለተ ነው ብሎ ግልጽ ጦርነት አውጅበታል:: ይህ ሳይሸሽግ የማንነቱ ባሕሪ ባፈጠጠ መልኩ ሕዝብ ፊት መናገሩ የድፍረቱ   ዓይነት ቢያስደነግጠንምስሜቱን ሳይሸሽግ ዛቻ መዛቱን ግን አዳራሹ በነበሩማሃይማን ጋዜጠኞችተጨብጭቦለት አድናቆ አትርፏል። ታሪክም ለመጪው ትውልድ የሚታወስ ትውስታነክሶእንደማይለቅ በመዝገቡ ዘግቦለታል! ይህ ግን ድፈረት ሳይሆን መሪዎች የሸሸጉት ባሕሪያቸው ሳያስቡት በድንገተኛ ቁጣ የሚያፈነዱት ድብቅ ማንነታቸው ያፈለቀው ድፍረት ነው።

ይህ አንድ ነገር አስታውሶኛል። ሊደፈሩ የማይችሉና ዋጋ የሚያስከፍሉ ግን ጠቀሜታ ያላቸው ለአገር ጠቀሜታ ተብሎ በድፍረት ሃቁን የዘረገፉ በቁርጣኛነታቸው የሚታወሱ ጥቂት መሪዎች ታሪክ ዘግቦአቸዋል። ለአገር ሲባል የማይደፈርን ድፍርት ደፍረው ራሳቸውን ለአደጋ የጋረጡ መሪዎች አሉ። በዚህ የምጠቅሰው ምሳሌ ያነበብኩት አንድ መሪ ትዝ አለኝ። 1956 የመጀመሪያው የቱኒዚያ መሪ!

  1956 . ነፃ የወጣችው የመጀመሪያው የቱኒዚያ መሪ የነበረው ሓቢብ ቡርጊባ ይባላል። የእስልምና ተከታይ የሆነውን የቱኒዚያን ሕዝብ ያልተጠበቀቦልድ” “ፈጣጣ ውሳኔወስዶያደርገዋል ተብሎ ያልተጠበቀ አስገራሚ እርምጃበሕዝቡ ላይ ተቀባይነት አግኝቶ እስከዛሬ ድረስ ሲታወስ ይኖራል።

ምንድ ነው ያደረገው? ከገዛሁት አመት ሆኖኝ አንብቤ ሳልጨርሰው በመጀመር በማስቀመጥ ላይ ያለሁት መጽሐፍ Conflict, Culture, and History (regional Dimensions) የሚል በአምስት ደራሲያን የተጻፈ መጽሐፍ ሳነብብ በእስልምና እምነት ተከታዮች ጭንቅላት ውስጥ የገባበትን አስተሳሰቦችን የመለወጥ ጥበቡ የሚገርም ነበር።

አገሪቷ በቅኝ አገዛዝ ስትማቅቅ ኖራለዘብ ያሉ እስላማዊ ሃይላትንያቀፈ፤አክራሪ እስላሞችን የተቃወመ መሪ ነበር። አስገራሚው ውሳኔው ቱኒዚያ ድህነት ስላጠቃትበሮመዳን ጾምበቴ/ቪዥን ቀርቦ የብርቱካን ጭማቂ የያዘ ብርጭቆ በመያዝፉትእያለ ለሰከንዶች ቃል ሳይተነፍስ አፍጥጦ ተመልካቾቹን ያይ ጀመር፤ ወቅቱየሮመዳን ጾምነበርና የብርቱካን ጭማቂ የመጠጣቱን ትዕይንት ተመልካቾቹበድንጋጤተውጠው ይመለከቱት ጀመር።

እንዲህም አለ፦

ወቅቱ ሮሞዳን መሆኑን አውቃለሁ። ብዙዎቻችሁ ስራ ከመስራት ተቆጥባችሁ በየመስጊዱም ሆነ በየቤቶቻችሁ አጥልላችሁ አርፋችሁ ተቀምጣችሁ አያለሁ። ሆኖም ሸሪዓ በሮማዳን ወቅትአትስሩ’ ‘እረፉአላለም። ሸሪዓ ሥራን አይቃወምም። የገባንበትን አስፈሪ ድህነትበጂሃድ መመታት እንዳለበት ሸሪዓ ያዝዛል። ሕዝባችን በድህነት እየማቀቀ አጋዥ አቅም ሳይኖሮው ድህነትን ማሸነፍ ከቶ አይቻለውም። ጂሃድ ሰይፍ አንስቶ በጦርነት መሳለፍ ብቻ አይደለም፡ስራም ጂሃዳዊ ግዴታ ነውስለዚህም አቅም ሊሰጠን የሚችል አጋዥ ሃይልሳንኮንንየገባንበትን የምጣኔ ሃብት ግንባታ ተሎ ካላፋጠንን የባሰውን ጭንቅ ውስጥ መግባታችን አይቀሬ ነው! በማለት እዛው ቁጭ ብሎ የሚታየውን የሸሪዓውን እውነታ እንዲመለከቱት አዘናጊውን የአስተሳሰብ ዘይቤን በገንቢ አስተሳሰብ መዝዞ ለመለወጥ ወቅቱ የሚጠይቀውን ፈተና መጋፈጥ ምን ያህል ቆራጥ ድፍርት እንደሚጠይቅ ከሓቢብ ቡርጊባ ታሪክ ሳንብብ በጣም ተመሰጥኩ።ይህንን በማድረጉ በአክራሪ እስላሞች ምን ያህል አስጨናቂ ፈተና እንደሚደርሰው የውቃል። ሆኖም እውነታውን በድፍረት መጋፈጥ ያንድ መሪ የመርሕ ባሕሪ ነበርና ያንን አድረጓል።

ቡርጊባ ለማለት የፈለገው፤ በጂሃድ ጦርነት ውስጥመግደፍይቻላል። ሳትበላ ከባዱ ጦርነት ላማካሄድ አቅም ያንሳሃል፡ ስለሆነም መግደፍ ይፈቅዳል። ድህነት እና አገር ግናታምሌላው ጂሃድ ጦርነት ስለሆነ አቅም ሊሰጣችሁ የሚችለውን ሁሉ ሳትኮንኑ እና ሳታርፉ ድህንትን መዋጋት ሸሪዓ ይፈቅዳልና ድህነትን ተዋጉ ማለቱ ነው። ባጠቃላይ ሊደፈር የማይቻለውን አውነታ ደፍሮ በተግባር ማሳየት ካንድ መሪ የሚጠበቅ አስገራሚ ክስተት ነው። ያውም እስላማዊ አገር መሪ ሆኖ!

አብይ ብዙ ጋጠወጦችን አስፋፍቶብናል (አንዳንዶቹ አልፈጠራቸውም አንዳንዶቹ ግን አዲሶች ናቸው) ለምሳሌ ጋጠወጡና አሸባሪው ኦነግ ለምኖ ሲያስገባውሽብር ሲፈጽም/ሚኒሰትሩተው አቁም!” የማለት ድፍርት አጥቷል። ይባስ ብሎ የታጠቀ የኦነግ ሃይል የለም ብሎን ቁጭ ነው ያለው። ሆን ብሎ እነዚህን ሃይላት በድፍረት ማስቆም ከተከታዮቸው ድጋፍ ያስሰጠኛል ስለሚል በወላዋይ ባሕሪ ድፍርት አጥሮት ሕዝባችንን ለኦነግ ታጣቂዎች አጋልጦ ለመከራ ዳርጓል። 

 አብይ አሕመድ የሚመራው ሰርዓትአናርኪነው። ምክንያቱም ስርዓተ አልባዎቹ በብዙ ገጠሮች እና ከተሞች ሕዝብን በመንገዳቸው እያስተዳደሩት ነው (እንደ የአልሸባብ ዓይነት አስተዳደር) የሽብር ቁንጮዎች የምንላቸው የወያኔ መሪዎችን ሊደፍራቸው ቀርቶ ለምኖ ያስገባውን ኦነግ እንኳ ሳይቀርተውሊለው ድፍርት አጥሮት ልቅ ለቅቆታል። ለዚህም አናርኮ ፋሺስቶችን አሳድጓል። አናርኪ ማለት ደግም ይህንን ትርጉም ይሰጠናል፡

  Anarchy is a state of disorder due to absence or nonrecognition of authority. Lawlessness, nihilism, disorder, stateless society... ይላል። አጠቃላይ ትርጉሙ የወረበሎች መንጋ የሚፈነጩበት መንግስት አልባ ክስተት ማለት ነው።ይህ ከመዋቅሩ በሽብር ያደገ በሽብር የታነጸ ሕገ መንግሥት እና በወንጀል የተጨማለቁ ሰዎች የሚመሩት ስርዓት ሕግ አልባዎቹን መቆጣጠር ይችላል ወይ? የሚለው ጥያቄ መልሱ አይችልም ነው።

 ምክንያቱም በአገሪቱ የደረሰው እና እየደረሰ ያለው ስርዓተ አልባ ክስተት የማስቆም ችሎታም ፍላጎትም ድፍረትም የለውም። ዋናው ፍላጎትየለውም የሚለው ነው ለኔ ዋናው መሰረታዊ መልሱ። ምክንያቱም የፋሽስት ኦሮሞ ፓርቲዎች አንዱ ፓርቲ ከሚመሩት አንደኛው ኦነጉ /ጄነራል ከማል ገልቹኤል በተባለ /ቪዥን  ጣቢያ የሰጠው ቃለ መጠይቅ አብይ የደበቀብንን ምሰጢር አጋልጦ ሃቁን ነግሮናል።

እራሱ ከየኦሮሞ ጸጥታ ሃላፊነት ሰሞኑን መባረሩን አስመልክቶ በቃለ መጠይቁ እራሱ የነገረን ሃቅግድያና የባንክ ዘረፍየተደረገው የአብይ አሕመድ ፓርቲ ኦፒዲኦ (አዴፓ) አድርግ እያለ በደብዳቤ እየጻፈ ለሽብርተኞቹ ያስፈጸመው እራሱ መንግሥት ነው ብሎ ምስጢሩ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ተናግሯል። ይህ ምስክርነት ይፋ ሲሆን ሕግ ቢኖር ኖሮ የሃገሪቱ አቃቤ ሕግ እና የፍርድ ቤቶች ጠቅላይ ፕረዚዳንት ተብየዋ ወዲያውኑጉዳዩእንዲጣራ ፋይል እንዲከፈት ማድረግ ትችል ነበር። ሌላ ቀርቶ ፓርላማ ተብየውም ልዩ ስብሰባ አድርጎ ሰውየውን (ብ/ጄነራል ከማል ገልቹ) ጠርቶ በፓርላመው ፊት ጥያቄና መልስ ሰጥቶ ሕዝቡ እውነቱን ማግኘት ማደረግ ነበረበት ግን አናርኮ ፋሺሰት (ፋሺስታዊ ስርዐተ-አልባ) መንግሥት በራሱ ላይ ምርምራ እንዲካሄድ አይፈልግም። (ልጁ ቀማኛ አባቱ ዳኛ!)

የከማል ገልቹ አስገራሚው ምስክርነቱ ደግሞ አሸባሪው ኦነግ ታጣቂዎች (ብዙዎቹ የኦዴፓ ታጣቂዎች ናቸው ይላል) በመንግሥት እውቅና ነው የሚንቀሳቀሰው ብሏል በኦሮሞ አካባቢ ሲፈጽሙት የነበረውን ሽብር ረገብ አድርጎ ወደ ሌሎች አካባቢዎች በማስፋት ወደከሚሴ እና የመሳሰሉሄዶ እዛውም ሽብር እንዲፈጽሙኦዴፓአዝዞት ነው ብሎ ተናገሯል፡ (ኋላአብንየሚባል አማራ ድርጅት ነው ብሎ አስቀድሞ ራሱን በራሱ የመሰከረውን የሚምታታ ወደ አማራው የሚያላከክ ንግግር ቢሰነዝረም)

በዚም ምንጭ አውነት ከሆነ ለማም ሆነ አብይ የራሳቸውን ኦዴፓ ፓርቲ መቆጣጠር ችሎታ እና አቅም የላቸውም ወይንም ደግሞ ሆን ብለው ሽብሩ እንዲስፋፋ አድርገዋል ማለት ነው። ከሁለቱ አንዱ። ሰውየው  ብይ ሚመራው ዴፓ የተባለው ድርጅት (አብይ ባያዝዘውም) ኦነግ ባንኮች እንዲዘርፍ የጻፈው ደብዳቤ አለ‘’ ሲል መስክሯል። አስገራሚው ደግሚ ከሚሴ ውስጥ ያሉት የራሱ የከማል ገልቹ ኦነጋዊ አባሎች ናቸው ሲል ነግሮናል። ለግጭቱ መነሻም ሲነግረንየኢትዮጵያ ሰንደቅአላማ ከተማ ውስጥ ይዘው የታዩት ኢትዮጵያውያን ላይ የመንጠቅ ዘመቻ በማድረግ ይህ ሰንደቅአላማ እንደታሳዩን ብለው ነው ግጭቱ የተቀሰቀሰውብሎ አስገራሚ እና ግልጽ ጸረ ኢትዮጵያ ጦርነት እንደተካሄደ ተናግሯል። (ከማል ገልቹንቤቲ/ቤተልሄም ታፈሰየተባለቺው ኤል / ጋዜጠኛ ብትጠቀው ኖሮ የተሻለ ምስጢር ይወጣ ነበር የሚል ግምት አለኝ። ሆኖም ጋዜጠኛው እንደወትሮው ለስላሳ ስለነበር ብዙም አልገፋውም):

ለዚህም ነው አብይ  ሊደፈር የማይቻለውን ክስተት  ለመድፈር እንደ ሓቢብ ቡርጊባደፍር ሃሞትም ሆነ ፍላጎትየለውም ያልኩት። እራሱ አብይ አሕመድ እንደነገረን ችሎታውልመናነው። በመለመን ይሳካልኛል ብሎናል። ሥርዓትን በልማና ማስከበር ደግሞ የታየ የታሪክ አጋጣሚ አላነበብንም። መጽሐፍ ቅዱስም ሆነ ቁርአንም ይህንኑ አያሳዩም። የአብይ ፍልስፍናአናርኮ ፋሺዝምንባስደንጋጭ ፍጥነት  ማስፋፋት ነው። እባቡና ጫጩቱ ገዳይ እና ተገዳይ ወንጀለኛው እና ሰላማዊው እንዳቅማቸው ይዋጣላቸው ብሎ ነጠላው አፉ ላይ ከድኖ የጎረምሶችን ትግል ለማየት ሙርኩዝን ተደግፎ እንደሚያይ ሽማግሌአህያና ጅብ ተገዳድለው፤ ተፈነቃቅለው ተቦጫጭቀውሲደክማቸው እራሳቸው ይከስማሉየሚል ስርዓተ አልባዊ ታዛቢ ስርዓትእንጂሕግ አስከባሪ ስርዓት አይደለም

ስለሆነም አዲስ መንግሥታዊ ሕገ መንግሥትም ሆነ አዲስ መሪ መለወጥ የግድ ነው። አንድ አመት ሙሉ ተንጨብጭቦለት ሰላም እንዲያሰፍን ህይወት እንዲያረጋጋ ዕድል ተሰጥቶት በሚገርም ሁኔታከድጡ ወደ ማጡአሸጋግሮናል። ይህም አልሰራም። ሌላ መሪ መፈተሽ የግድ ነው!
ጌታቸው ረዳ (ኢትዮ ሰማይ)