Sunday, October 5, 2008

ከግልፍተኝነት የእንካ-ቴስታ ጸባያችን ወይንስ ከዘረኝነት ባሕሪያችን?
ጌታቸዉ ረዳ
ፍምን እፍ ብትላት ትነዳለች። ትፍም ብትልባት ትጠፋለች።ሁለቱም ከ አንድ አፍ የወጡ በመሆኑ ነዉ።…መጽሐፈ ሲራክ ም/28። ከላይ በርዕሱ የተጠቀሰ የመጀመሪያዉ ሐረግ የተበደርኩት ከጦቢያ መጽሄት ነዉ።በወያኔ እና በሻዕቢያ ተፈጥሮ በነበረዉ ያፍንጫ ለፍንጫ ደም መፋሰስ ሕዘቡ ገርሞት ለጸባቸዉ የመነሾ ምክንያቶችን ሲያፈላልግ “ከኢትዮጰያ ጠባቂዉ አምላክ ጣልቃ ገብነት አስከ ትግርኛዉ ተናጋሪዎች ደርሶ-“እንካ-ቴስታ” ግልፍተንነት ባሕሪ እንደሚሆን ምክንያቶችን ተደርድሯል…”።ከሚለዉ ካነበብኩት ትዉስታ ነበር። ህሊናቸዉ ከወገንተኝነት ረግረግ መንቀል አቅቷቸዉ ዛሬም እዛዉ የሚላወሱ ጎሳ ሙርኮኞች ገብሩ አስራትን ከኪሳቸዉ አዉጥተዉ ዋሽንግተን ድረስ አስመጥተዉ በየአሜሪካን ክፍለ ሀገሮች እያዟዟሩ ከአፈንጋጩ አፍቃሬ አንቀጽ 39ኙ እና ከተምበርካኪዉ አፈቃሬ አንቀጽ 39ኙ ከሁለት መልከ ጥፉ ዝንጆሮዎች መሃል ዛሬም ለምርጫ ዉደድር አቅርበዉልናል። አንድ ጸሃፊ እንዳሉት ሱዳኖች “ዝንጆሮዋ በእናቷ እይታ-ሚዳቋ- ናት”። ይላሉ፡ ያሉትን ነገር አስታወሰኝ እና ከመልከ ጡፉዎቹ አፈንጋጮቹ እና ከተምበርካኪዎቹ መልከ ጡፉዎች መሀል “ሚዳቋዉን” ገብሩ መርጠዉ አምጥተዉልን፤ ዛሬም ጠጥቁት ይሉናል። ከጦቢያ ጋር ፍቅር ያዘህሳ ባትሉኝ፡ “ሙሻ ዘር” በተባለዉ አምዷ ያኔ ገና ድሮ ገና ከአስራ ምናምን ዓመት በፊት የወያነዉ የኢትዮጵያ ራድዮ “ምን እንጠይቃችሁ? የሚል ፕሮግራም ልናዘጋጅ ነዉ” ብሎ ነበር መሰል። ጦቢያ ደግሞ “የጠየቅነዉ መቸ ተመለሰልንና ነዉ!” ብላ መልሳችላቸዉ ነበር። ገብሩን ጠይቁ የሚል መልክት አይቻለሁ። ከዚያም ከየት አስከ የት ባሕር ተሻግረዉ አዚህ ድረስ እኛን አክብረዉ እንድንጠይቀዎት በመምጣትዎ ምስጋናየ የላቀ ነዉ፡ እያሉ በስብሰባዉ ዉስጥ እጅ መንሳት የቀራቸዉ የዋሃንም አድመጫለሁ። መጠየቁ መች ከፋ? የቸገረዉ ነገር የቀሳዉስቱ፤ድያቆናቱ፤የ አረጋዊያኖቹ፤ትላልቅ ባላበቶች፤ አገር ወዳድ የከተማ እና ገበሬዉ ለዓመታት ያቀረበላቸዉ ጥያቄ መቸ ተመለሰለት እና ነዉ በጥያቄ ላይ ተጨማሪ ጥያቄ አቅርቡ ሚባለዉ? ምነዉ በወያኔ የተጎዱ የወያኔ ሰለባ የሆኑ ወንድም ዘመድ ወዳጅ የሉዋችሁም? በሰዉ ቁስል ላይ ግራጫ ባትሰድዱ ምናለበት? በደም መቀለድ እኮ ሃጢያት ነዉ፡ በነዚህ አን ጠየቅም ባዮች፤ የተጠለፈዉ የታረደዉ፤በእሳት የተቃጠለዉ የተገረፈዉ፤ አካለ ስንኩል የሆነዉ የነሱ ታጋይ እና ተራ ህዝብስ ምን ይለናል አትሉም? “ለሰላባዎቻቸዉ” አክብሮት ስጡ አንጂ? ፈጣሪን ፍሩ አንጂ? ከበስተጀርባ እየጨኸ ያለዉ የሙታን እና የቁም ሰለባዎች ቁጨት እና ጭሆት አስቲ ላንዳፍታ በሕሊናችሁ አስታዉስት? ዘሎ ለነገብሩ ለባለ አንቀጽ 39ኞቹ እጅ መስጠት እኮ -ለባለጌ ማራኪ እጅ ሰጥቶ የመሞትን ያህል እኮ ነዉ።ይህን እንዴት ከመቸዉ ረሳችሁት? ለባለጌዎቹ ማራኪዎች እጁን ሰጥቶ ወደ ልምና ተሰማርቶ በገዛ ራሱ አፈር ላይ የተኛዉ ለትልቁ ሰራዊት ያልሆኑትን እነ ገብሩ አስራት ለናንተ ምን ሊበጇችሁ ነዉ? ረጋ! ረጋ! ዖረ እስኪ ረጋ በሉ! እስኪ ስለ እናንተዉ የዋህ አወዳሾች ኢትዮጵያዊያን መተቸቱ ወደ ጎን ልተዉ እና ወደ ዋናዉ አርዕስቴ ልመለስ። ገብሩ አስራት ዋሽንግተን ዉስጥ ስበሰባ ጠርቶ በነበረበት ዕለት የተደመጠዉ ጉዳይ ልንነጋገርበት ነዉ የተነሳሁት።አንድ ለመናገር ዕድል የተሰጠዉ ታዳሚ፤ (ተናጋሪዉ የትግርኛ ቋንቋ ተነጋሪ አይደለም- ያአማርኛም ተነጋሪም አይመስለኝም) አቶ ገብሩ በመምጣቱ እና በእዛ መድረክ ተገኝቶ ከህዘቡ ያለዉን ጥያቄ ተቀብሎ እንዲመልስ በመጋበዙ ለጋባዦቹ እና ለገብሩ ምሰጋናዉ አቅርቦ በገብሩ ስብሰባ ላይ አትገኙ ያሉትን ወገኖች ቅስቀሳ ደግሞ ክፉኛ አዉግዞ ቁጭ አለ። ተንጨበጨበለት። ቀጥሎ ሌሎች በየተራ ተናገሩ። አንድ ታዳሚ (የትግርኛ ቋንቃ ተናጋሪ) ተራዉ ደርሶ፤ ለትግራይ ሕዝብ ያልተባለዉን ተባለ፤ እያለ ለመለስ ዜናዊ ራዲዮ ወያነ ትግራይና መሰሎቹ የሚዲያ ጡሪዩምባኞች “ፕሮፖጋንዳ” (የ እንዲህ አሉ ወሬ) ለማቀበል ብሎም አማራዉን ከትግራይ ህዝብ ጋር ለማቃቃር አስገራሚ የሆነ የነገር ማጣመም የታዘብኩት ከዚህኛዉ ሰዉ ነበር።
ሁላችሁም አንደምታስተዉሱት ጠባብ ወገንተኝነት ምን ያህል ጭፍን እና ነገሮችን ሳያጣሩ በድፍን የሚሰነዘር ሂስ ሁሉ “ሂሱ ለትግራይ ህዘብ ነዉ፤ ለትግራይ ህዝብ ነዉ” እንዲህ የምትሉት ትግራይን ለማሳጣት ነዉ ...” በማለት ልዩ ተቆርቋሪዎች ሆነዉ፤ ሌለዉ ግን ጠላት፤ ለትግራይ ሕዝብ ያለ እነሱ በቀር ሌላዉ ጎጂ አንደሆነ፤ ራሳቸዉን በጥብቅና ቆመዉለት ብዙ እሮሮ አድምጠናል(ለ17 ዓመታት ብያንስ)። ለብዙ ዓመታት በአማራዉ ላይ በህወሓት ድረጅት የተቀነባበረ ሴራ ፀረ- አማራ ቅስቀሳ እና ጎጂ እርመጃ እንደተደረገ እያወቁ፤ እነኚህ ወገኖች ሆን ብለዉ ተደርጎ እንዳልተደረገ አዉቁ እንዳለወቁ “ጀሮ ዳባ” ብለዉ የራሳቸዉን ጎሳ/ወገን በመከላከል “የነፍጠኖች” ወሬ ነዉ እየተባለ ወያኔን ለመከላከል ብዙ ዓይነት ክህደቶችና ክርክሮች ተደርገዉ አይተናል። የኮሚኒስቱ እና የአፓርታይዱ ቅይጥ ፖሊሲ የሆነዉ የወየኔዉ አንቀጽ 39 አስከ መገንጠል የተቃወመ ሁሉ እንደ ጸረ-የኢትዮጵያ ብሄረስቦችና ጸረ-ትግራይ እየተደረግን በኦነግ (ለኦሮሞ ህዝብ የመጣ መብት በማለት) እና በወያኔ ተከታዮችም (በምዕራባዊያን ተደግፎ ወያኔ ያመጣዉ ለኢትጵያ ፍቱን መድሃኒት አንቋሸሹብን በሚል) ብዙ ብዙ ተዘልፈናል። ይህ የሚቃወም ሁሉ የመጠሪያ-ስሙ’ “ነፍጠኛ- ወይም ደርግ ወይም ኢሕአፓ” አንደሆነ የምታወቁት ሀቅ ነዉ። ስለ ፓረቲዉ እና ስለ ፖሊሲዉ ግለሰዎች ሂስ ሲያቀርቡ የተባለዉን ቅሬታ በቅጡ ሳይመረምሩት፤ እራሰቸዉ ግራ አጋብተዉ የሌላዉን የዋህ ሰዉ አይዕምሮ የሚያምታቱ “ጠባቦች” መች መማር እንደሚችሉ እና ራሳቸዉን ከወገንተኝነት ነጻ ሳያደርጉ ከሌላዉ ኢትዮጵያዊ ይልቅ አነሱ ብቻ ለትግራይ ህዝብ ልዩ ተቆርቋነት ስሜት ኖሯቸዉ እንደቆሙ እየሆኑ ፤ሂስ በተሰነዘረ ቁጥር በቁጣ የሚነድዱ ቁጥራቸዉ እጅግ በጣም በርከት ያሉ የትግራይ ተወላጆች ዛሬም ድሮ ከነበሩበት ስሜታቸዉ መላቀቅ አቅቷቸዉ ሲያስቸግራቸዉ ይደመጣሉ። ለምሳሌ “አቶ ጌታቸዉ-..” (የአባታቸዉ ስም ማን እነደሆነ ያልተገለጸ) የተባሉት አድማጭ ስለ መገንጠል (አንቀጽ 39ኝን አስመልክቶ) እና ስለ ወያነ በወታደራዊ ተቁዋማቱ እና በመንግሥታዊ ዋና ዋና ሞተሮችና እስከ ታች ያለዉ መዋቅር ወገንተኛ ስለ መሆኑ በመዋቅሩ ላይ የሚታዩት (ገብሩ አስራት ሳይቀር ያመነበት) አድላዊ/ጎሳዊ ተግባሮችን በመዘርዘር ሲጠቁሙ፡ አቶ ጌታቸዉ( አባት ስም አልተገለጸም….?) የተናገሩት ሂስ በመጻረር/በማጣጣል ብቻ ሳይሆን በጥላቻ ነጉዶ እሳት እንደበዛበት ቡና በድንገት ገንፍሎ አንድ የትግራይ “ቁጡ ሰዉ” አቶ ጌታቸዉን ቀና አስተያየት አጣምሞ እንዴት አማራዉ እና ትግሬዉን ለማያያዝ እንደተጠቀመበት የሚከተለዉን ልጥቀስ።ልጥቀስ -ቃል በቃሉ“….. ያለዉ ነገር ሰምታችሁታል? አንድ የተናገረዉ መርዝ አለ።ምንድ ነዉ ያለዉ!? አማራዉን አስከ መቸ ጊዜ ድረስ ልንለምን ነዉ ብላችሁ ልትገነጠሉ ነዉ ወይ? አለን!.. Right at our face!!! How dare!? አንዴት?... እንደዚህ እየተናገርን ነዉ መለስን ምናወረደዉ?.......... አሜሪካ ዉስጥ ያለዉ ከ-----አስ.. ከ አፍራሽ ነዉ። ሕዝብ እና መንግሥት መለየት አልቻልንም!”
በማለት ነገሮችን አጣምሞ ከየት ወዴት አንዳምታተዉ የተከታተላችሁ ሰዎች ልብ በሉ። ሰዉየዉ ንግግሩን ጨርሶ ሲያበቃ የሁለቱንም ወገኖች ንግግር በቅጡ ሳይከታተሉ የዚህኛዉ ሰዉ ንግግር ብቻ ሚዛን የሰጡት “ዕዉራን ንቦቻቸዉ” በደማቅ ጭብጨባ ሲሸኙት/ሲደግፉት ይደመጣል.. ጨብ…ጨብ ጨብ!) የአቶ ጌታቸዉ…. መልስ ለመስጠት ዕድል ተሰጥቶት አሱን ለማብረራት፤ አንደሚከተለዉ ይደመጣል።ቃል በቀል ልጥቀስ “…ወንድሜ… Right at our face! አንዴት እንደዚህ ትለኛለህ ላለዉ፡ “ሚስ አንደርስታንድ” አድርጎኛል። እኔ ያልኩት አሁን ያለዉ የአቶ መለስ አገዛዝ “ስቲል” የመገንጠል አጀንዳ እንደያዘ ነዉ።ይሄነን የሚጠቁሙ አንዳንድ ነገሮች ያሉ ይመስለኛል…..።” ብሎ ይዘረዝሩ እና አቶ ጌታቸዉ በመቀጠልም “ …ይሄ መንግሥት አንቀጽ 39ኝን ትግራይን ለመገንጠል፤ ከመሃል አገር “ስልጣን ያጣ ከሆነ መጨረሻ መደራደርያየ ተከዜ ላይ ቆሜ ይህንን የኢትዮጵያ የዘረኞች ስርዓት አቆማለሁ፡ የሚልበት አስተያየት ይኑረዉ ይሆን ወይ? ከናንተ እየለመንን አንኖርም፡ ከአሁን በሓላ፤ የሚል ስሜት ይኖረዉ ይሆን ወይ? ነዉ እንጂ ያልኩት፤ ስለ ትግራይ ሕዝብ አይደለም ያልኩት። ያልኩት ስለ መንግሥት ጥያቄ ጉዳይ ነዉ”። በማለት “ትግሬዎች አማራዉን አስከ መቸ ልንለማመጠዉ ነዉ እያሉ ነዉ” ብለሃል በማለት “መርዝ” ብሎ የሰየመዉ “የራሱን መርዝ” ወደ አማራ እና ትግሬ እንዴት ለማያያዝ እንደሞከረ አይታቸሗል። ሰዉየዉ ስለ አንድነት ሲሰብክ ቆይቶ ወደ አማራ ሮጦ መርዙን ለመርጨት ደቂቃ አልፈጀበትም።
እኛ ሰዎች የጌታን ቃል እያምታታን፤ ሊቃዉንትና ሓዋርያት መጽሐፍ ቅዱስ ከተዉልን ትርጓሜ ዉጭ የየራሳችንነን ትርጉም እየፈለሰፍን ያለ ፈርሃት በድፈረት የጌታን ቃል ጠምዝዞ ተርጉሞ የመዳፈርን ባሕል ያደረግነዉ የዓለም ፍጡራን ሁሉ፡ ሰዎች በንግግራቸዉ ላይ ያልደመጠ፤ ያልወጣቸዉ ቃል ብለዋል፤ እያልን በሕዝብ ስም ማምታታችን እስከ መቸ እንደምንቀጥል ይገርማል።ይህ ግንፍል እንካ-ቴስታ ጠባያችን ይሁን ወይንም ከዘረኝነት ባሕሪያችን መታረም የምንችለዉ መቸ እንደሆነ ብዙ ሰዉ የገረመዉ ጉዳይ ነዉ። አሜሪካ ዉስጥ ገብሩ አስራት በበሰበሰበዉ የዓረና ድርጅት ስበሰባ ላይ የተገኙት “ነፍጠኞ-የገብሩ አስራት ወኪሎቹ ፡“የትግራ ህዘብ አማራዉን ስንት ጊዜ ልንለማመጠዉ ነዉ ያላሰብነዉን ፤ያላልነዉን (ስብሓት እንኳ ያረጋገጠልን ቢሆንም) እንገነጠላለን እያለ ነዉ… “ እያሉ የትግራይን ህዝብ እያሙትና እያስራቁት ነዉ፤ ኢትዮጵያዊነቱን ሊነጥቁት እየተንደረደሩ ነዉ….. ወዘተርፈ…” በማለት ወሬ የሚቀላዉጡት “የወያኔ-ትገሬዎች” እንደሚያራቡት አትጠራጠሩ።ከዚህ ሥራ/አስተዋጽዎ ሌላ ምን ከሰማይ የሚወርድለት መና ይኖራል? ፈጣሪዉ ካልፈራ፤ አንድ ነገረ ሰሪ “የወያኔ ዕዉር ንብ” የሰዉየዉን (የእሮሮዉ አቅራቢ) ቴፕ ብቻ ቀድቶ መቀሌ ዉስጥ ላለዉ “ድምጺ ወያነ ትግራይ” ቢልከዉ፤ እዉነት መስሎት “የወይን ራዲዮ” ፤ ቱልቱላዉን እያናፋ የሚፈልገዉን የማምታቱ ስራዉ ያችን የግንፍሉን ሰዉየ ቃል “ጫፍ” ይዞ መከረኛዉ ሕዝብ አሁንም አልተኝሉህም ሊሉት ነዉ። እኛ ጥቂት የትግራይ ተወላጆች የተቻለንን ለብዙ ዓመታት ዉዥምብሮችን ግልጽ ለማድረግ ሞከረናል ነዉ። ቢሆንም ክቡር ፐሮፈሰር/ዶክተር ጌታቸዉ ሃይሌ በአዲሱ መጽሃፋቸዉ በ “አንዳፍታ ላዉጋችሁ” እንዳሉት “ጎጠኛ እና ጎሰኛ በወረራት ሀገር ስለ ኢትዮጵያ አንድነት፤ ስለ ሕዝቧ ዕኩልነት የሚናገር የኔ ብጤ ጠላት ማፍራቱ ሳይታለም የተፈታ ነዉ”። እንዳሉት፤ በእኔም ሆነ እኔን በመሰሉ ኢትየያዊያን ትግሬዎች የጥላቻ እና የማግለል ዘመቻ ተደርጎብናል። ሖኖም ታሪክ የሗላ ሗላ ማንን አንደሚአገልል፤ ወደፊቱ የሚታይ ይሆናል። እስከዛዉ ድረስ ግን ብዕራችን የሚዉጥ ሃይል አይኖርም። ለትግራይ ሕዝብ አሳቢዎች እና ተቆርቃሪዎች ከኛ ወድያ ላሳር የሚለዉን ወገንተኝነት፤ተምክሕት ተጠራጣሪነት እና ጎጠኝነት፤ግንፍልተኝነት ለማስቀረት እንሞክር። አማራ፤አማራ ዪሚያሰኘን ጸረ አማራነት ስካር ለማብረድ አንሞክር።
የሚቀጥለዉ ምዕራፍ ሁለት ስለ ትግራይ በልማት ተጠቅሟል ወይስ አልተጠቀመም የሚለዉን የገብሩን አቋም በተጻራሪ የቆምኩበትን ሰፊ ሀተታ ከነ ማስረጃዉ በሚቀጥለዉ አቀርባለሁ፡ ተጠባበቁ።_ ፧-፧ አምላክ ኢትዮጵያን ይጠብቅ።’-/’- http://www.ethiopiansemay.blogspot.com/