Friday, April 14, 2023

የአምቡላንስ ጩኸት እየሰማ የማይጠነቀቅ የአማራ ሕዝብ ጌታቸው ረዳ Ethiopian Semay 4/14/23

Death and sorrow under PM Abiy Ahmed of Ethiopia

የአምቡላንስ ጩኸት እየሰማ የማይጠነቀቅ የአማራ ሕዝብ

ጌታቸው ረዳ

Ethiopian Semay

4/14/23

ትናንት ማታ ኦነግ፤ አብይ አሕመድና አበባው ታደሰ ተቀናጅተው አማራን በሚጨፈጭፉበት አደገኛ አካባቢ ትጥቃቸው ፈትተው በሁለት ጭነት መኪና ተጭነው ወታደራዊ ልብሳቸው እንደለበሱ፤ ከመኪና ሳይወርዱ ተጭነው እየተጓዙ እያሉ አድፍጦ በቆየው የአብይና የኦነግ ታጣቂ አጣየ…. በተባለው አካባቢ አደገኛ ቦታ በጭካኔ አገዳደል መኪና ላይ ተጭነው እያሉ ቊጥራቸው ማወቅ ያልቻልናቸው በርካታ የአማራ ልዩ ሃይሎች በጥይት እንደተደበደቡ አሳዛኝ ምስሎች በየሚዲያው ተለጥፎ  አየሁ።

ይህ እንዳይደርስ  ከ4 ቀን በፊት << ትጥቅ መፍታት ያስከተለው መዘዝ ከማይ ካድራ ሊወሰድ የሚገባው ትምህርት>>፡ ጌታቸው ረዳ Ethiopian Semay 4/11/23  በሚል ርዕስ አማራዎች ትጥቅ እንዳይኖራቸው ብትር እንኳ ሳይቀር እንዳይዙ ተነጥቀው ለጅምላ ጭፍጨፋ እንዴት እንደተጋለጡ የ30 አመት ጭካኔና ከሁለት አመት በፊት ማይካድራ የደረሰው ጭፍጨፋ በቦታው የነበረው የዓይን ምስክር የሰጠው ቃል በቪዲዮ አስደግፌ አሳዛኝ ክስተት ለምን እንደተከሰተና ለወደፊቱ ከዚህ ትምሕርት ተወስዶ ትጥቅ አውርዱ ስትባሉ እንዳትፈቱ ሁለተኛ ጥፋት እንዳይደገም በማለት አስጠንቅቀን እያለን

በሚያስደነግጥ ሁኔታ ትናንትና አበባውና አብይ አሕመድን አምነው ትጥቅ ፈትተው ባዶ እጃቸው በሁለት የጭነት መኪና ወደ ሞት ተሳፍረው ሲጓዙ መርዶ መስማት በምን ቃል እንግለጸው?

እኔ በበኩሌ 30 አመት ሙሉ ሳይሰለቸኝ ኑሮኣችን ጊዜኣችን ማሕበራዊ ትስስራችን ወደ ጎን ትተን ፤ አማራ ሆይ እባክህን እራስህን ተከላከል እያልኩ እኔ እንደትግሬነቴ ለማንኛውንም ሳልወግን በኢትዮጵያዊነቴ አማራውን ለማዳን ብዙ ጨኩኝ፤ በዚህ የተነሳ ከብዙ ወዳጆቼ ተለያየሁ፤ ተራራቅኩ፤ አሁን ደግሞ ተደጋጋሚ ጥቃት በራሱ እንዝህላልነት ሲደርሰው ማየት ከዚህ ወዲያ በምን መንገድ ብንመክረው ጥቃቱ ይቆማል? ትግሉን ብናቆም ይሻል ይሆን? ትግሉን ላቁም? ብየ ከራሴ ጋር ተሟግቻለሁ። ግን ትግሉን ማቆም ጥቃቱ ይቀንስ ይሆን? ሰው ማስጠንቀቂያ እጠሰጠው ካልሰማ በምን መንገድ እናሳምነው?

ትጥቅን ማስፈታት የሚሯሯጡ መንግስታት አሳሳቢ ታሪክ አላቸው።

አንድ ሕዝብ በፋሺሰቶችና አምባገነኖች እጅ ውስጥ ገብቶ  በጠመንጃ ሥር ከወደቀ የመጀመሪያው አዋጩ “ጠመንጃን በጠመንጃ መከመከት ነው።ሰላም በጠምንጃ ይመጣል፤ ራስን ማስከበር ከዚያ ይጀምራል። በመጀመሪያ ይህ ዓለም በትርጓሜ ብንሄድበት እንደተሰበረ ሸክላ መቀበል አለበት።

ዓለም በክፉዎች የተከበበች ነች፤ ኢትዮጵያ በዚህ አደጋ በቀለብት ውስጥ በክፉዎች ጥርስ ዙርያ የገባች አገር ነች።

ኢትዮጵያ እንድትፈርስ ከተወሰነባት አገር አንደኛዋ መሆንዋን ዛሬ ሳይሆን ገና አክሱም ዘመነ መንግሥት ጀምሮ ከዚያም እየተቀጣጠለ በቱርክ፤ በግብጽ፤ በጣሊያን፤በሶማሊያ፤ በአክራሪ እስላም አገሮች በዓረቦች፤ አሜሪካኖች፤ እንግሊዞች… መልካም በማይመኙላት “በአንዳንድ” የካቶሊክ እና የፕሮተስታንቶች ሰባኪያን እንዲሁም አገር በቀል በሆኑት በትግሬ ወያኔዎችና ኦነጎች ባንዳዊ ትብብር ስጋቱ አሁን ወዳለበት ደረጃ ደርሷል።

የተሸረበው ክፋት ሲፈነዳ - ስጋቱ የግልም ይሁን የሀገር ሁላችንም ይጎዳል። የመጨረሻው ነገር ማንኛችንም ልንፈልገው የማይገባን ነገር ቢኖር መንግሥት ተብየው የመከላከል አቅማችንን እንዲያነሳልን መፍቀድ የለብንም።

ሂትለር በጀርመን፤  እስታሊን በሶቭየት ሕብረት ዜጎችን ጠመንጃ የማስፈታት ዘመቻቻው ሲጀምሩ  ያታልሉበት ንግግር ልክ ጀነራል ተብየው ቅጥረኛው አበባው ታደሰ የተባለ ማፈሪያ እንደተናገረው እኩያወ የሆነው “የጀርመን ናዚው” ሄይንሪክ ሂምለርም እንዲሁዜጎችን ከጥቃት የሚከላከል መንግስት ነው፡መንግሥት ስለሚከላከልላቸውዜጎች ጠመንጃ አያስፈልጋቸውም”። በማለት ዜጎች ትጥቅ ካስፈታ በኋላ ሕዝቡ በተለይ አይሁዶች ጽንፈኞች ቡድን እጅ ወደቁ።በሚሊዮኖች ወደ ኦሽዊትዝ ጭፍጨፋ ቦታ ተጋዙ  ለሞት እጣ ተዳረጉ።ይህ ሁሉ የተከሰተው ራሳቸውን ለመከላከል የሚያስችላቸውን መሳሪያ እያስመዘገቡ ትጥቃቸው ስለፈቱ የሞት ጽዋ ተጎነጩ።

የኛዎቹ ልዩ ሃይሎችና ፋኖዎች ደግሞ በተመሳሳይ ትጥቅ እንዳትፈቱ እያልን ባስጠነቀቅን በ4ኛው ቀኑ አብይ አሕመድና አበባው ታደሰ ወደ አዘጋጁላቸው ወደ ኦሽዊትዝ ጭፍጨፋ ቦታ ተጭነው ሞት እጣ ተዳረጉ።

አሳዛኝ ክስተት! ፈጣሪ ከመንበሩ ተነስቶ ይቀበላችሁ፤ ወገኖቼ ሆይ! አመድ ይቅለላችሁ!

አመሰግናለሁ

ጌታቸው ረዳ

Ethiopian Semay