Saturday, April 23, 2022

እየሩሳሌም ተክለጻድቅ የኢትዮ 360 ሚዲያ ከፋሲካ እስከ ፋሲካ የአመቱ ምርጥ ጋዜጠኛ ጌታቸው ረዳ ETHIOPIAN SEMAY 4/24/22

 

እየሩሳሌም ተክለጻድቅ የኢትዮ 360 ሚዲያ ከፋሲካ እስከ ፋሲካ የአመቱ ምርጥ ጋዜጠኛ

ጌታቸው ረዳ

ETHIOPIAN SEMAY

4/24/22

ስለ የሰዎች “ምርጥነት” ምርጫ ሲነሳ ብዙውን ጊዜ ስጽፍ ያነበባችሁኝ ካላችሁ እንደምታስታውሱት “ጋዜጠኞች እና ድምጻዊያን” በኔ ብዕር ለማለፍ ግምል በመርፌ ቀዳዳ የማለፍ አስቸጋሪ ፈተና ይሆንባቸዋል።

የቴ/ቪዥን ጋዜጠኞች ምርጥነት ስመርጥ በድምጻቸው ወይንም በሚያቀርቡት የዜና ትንተና ብቻ ሳይሆን ለአገር ክብር ሲሉ አስቸጋሪ የህይወት ፈተናዎች ሲያልፉና ዜናዎቻቸውም ለሕዝብ ሲተነትኑ የዜናው ከባድነት በልባቸው የሚያሳድርባቸው ጫና ሳያስቡት በድንተኛ ዕምባ ሲቃ ሲተናነቃቸው ማየት ለነዚህ  ይነቶቹ ጋዜጠኞች ከፍተኛ አድናቆት አለኝ። ኢየርሳሌም ተክለ ጻድቅ የዚህ ማሳያ ጋዜጠኛ ነች።

ኢየሩሳልም እጅግ የሰው ልጅ ተክለሰውነት ያላት መሆንዋን ያየሁባት ሌላው አድናቆቴ፡ ሁላችንም የምንወደውና የምናከብረው የሥራ ባልደረባዋ ‘ሃያሲና ፖለቲከኛ’ ሃብታሙ አያሌው በጠና ታምሞ በነበረበት ወቅት ባንድ አጋጣሚ መድረክ ላይ እያለች የሃብታሙን ጤንነት ተነስቶ ሲወያዩበት ድንገት ዕምባ ተናንቋት መናገር አቅትዋት ከጉሮረዋ እና እምባዋ ጋር ትግል ገጥማ ያየሁዋት ቀን እኔም እጅግ ሆደ ቡቡ ስለሆንኩ ዕምባየ ተናነቀኝ እና ልጅትዋ ያላት ሰብአዊነት ሌላው መገለጫዋ ሆኖ አገኘሁት ።

እንደምታውቁት የምንወደውና የምናከብረው ባለቤትዋ  ጋዜጠኛ “ምናላቸው ስማቸው” ለብዙዎቻችን ግልጽ ባልሆነ ምክንያት ከኢትዮ-360 ባልደረባነቱ በፈቃዱ ሲለቅ ኢየሩሳሌም እንደ የትዳር አጋርዋና የሥራ ባልደረባነትዋ አብራው ላለመከተል ወስና አስገራሚ የሆነ የጋዜጠኛነት ሙያዋን በመቀጠል እኛን ስታስተምር ማየቴ “ወገንተኛነት፤ ትዳርነት፤ ወዳጅነት፤…”የሚባሉ ነገሮች ሳያጠቃት ለሙያዋ ተገዢ ሆና በጠበቅናት ቦታ ማግኘታችን እጅግ የላቀ ብርታት የሚጠይቅ ሰብኣዊነትዋ ሌላው መገለጫዋ ሆኖ አግኝቼዋለሁ።

“ዜናዎችን አሰባስባ ወደ ሕዝብ ከማስተላለፍ ባሻገር ኢትዮ 360 ውስጥ ያሉ እጅግ ከባድ ፤ ከባድ ሚዛን ያላቸው ዩሃያሲያኑን እና ፖለቲከኞቹን መድረክ በመምራት የተለያዩ ሃሳቦችን በማከፋፈል የሃያሲያኑን እና ያድማጮችን የማሰብ ችሎታ የሚወጥሩ ጥያቄዎችን በማፍለቅ “መፍትሄዎችንም ጭምር” እንዲያመጡ ተራ በተራ እያፈራረቀች የማወያየት ችሎታዋ የሚደነቅ ነው።” 

ስለዚህም ለ30 አመት ሙሉ ዛሬም ሕዝባችን ሰብአዊ ክብሩ ተነጥቆ ባለበት ፈታኝ ወቅት እንደ እየሩሳሌም እና አብራ ለምትሰራው ወ/ሮ/-ወ/ት “ልዩ” ለምትባለዋ የሚዲያቸው የቴክኒክ ባለሞያ (ፌቶግራፍዋ አላገኘሁትም) ጭምር  ያሳዩት አገራዊነት እያመሰገንኩ “በእኛው ምርጦች” እና “በእኛ በአመስጋኝነት” መካከል ያለውን ግንኙነት “የእስተማሪ እና የተማሪ” ግንኙት ቢሆንም እንደ እየሩሳሌም ተክለ ጻድቅ የመሳሰሉ ሴት ጋዜጠኞች በዚህ አስቸጋሪ የአሜሪካ ኑሮ “ራሳቸውን አሳልፈው በመስጠት” ኢትዮጵያዊያን ለምናደርገው የነፃነት እንቅስቃሴ ከፊት ሆነው መንገዱን እየመሩን በማየቴ ልዩ ምስጋናየ ለጋዜጠኛ እየሩሳሌም ተክለ ጻድቅ እያቀረብኩ፤ አብረው ለሚሰሩ ባልደረቦችዋ በሙሉ መልካም ፋሲካ እመኝላቸዋለሁ።

ጌታቸው ረዳ

ETHIOPIAN SEMAY