Sunday, July 3, 2016

የደም መርገም ተካፋዮች ጌታቸው ረዳ (የ Ethio Semay አዘጋጅ)የደም መርገም ተካፋዮች
ጌታቸው ረዳ (የ Ethio Semay አዘጋጅ)
መጀመሪያ ከተለያዩ የአሜሪካ ግዛቶችና ሁለት ከአውሮጳ የካችሁልኝ ደብዳቤዎቻችሁ ደርሰውኛል። ሁለት ወንድማማቾች (እህትና ወንድም) በጋራ የላካችሁልኝ ረዢም እጅግ አሳዛኝ ታሪኮችን የሚያወሳ ልብ የሚበላ በኤርትራ ምድር ቀርተው ደብዛቸው የጠፋ ወላጅ አባታችሁ የሚያወሳ መልእክት ስመለከት ልቤ ነክቶታል። በሺዎች ምናልባትም በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሲቪልና ወታደሮች ኢትየጵያዊያን በኤርትራ ምድር ተገድለው፤ወደ ሱዳን ለመሸሽ
ሲሞክሩ በማያውቁት አስቸገሪ በረሃ ተበትነው የበረሃ አራዊት የበላቸው፤ በሃረንድዋና በራሻይዳ አረመኔ እስላሞች ተይዘው ለሊቢያ ዓረቦች በባርነት የሸጥዋቸው፤ ያረድዋቸው፤በኢሳያስ አፈወርቅ የታፈኑ፤የተረሸኑ፤ የታሰሩ፤ መውጫ አጥተው በኤርትራ ከተሞችና በአስመራ ከተማ ለማኞች ሆነው እዛው ኤርትራ የቀሩ (ከሁለት አመት በፊት ስለ ኢትዮጵያ ለማኞች በኤርትራ ውስጥ በአንድ ኤርትራዊ የትግርኛ ቃለ መጠይቅ ያዳመጥኩት ብትሰሙት እጅግ የሚያበሳጭ፤ የሚያቃጥል፤ የሚያሳዝን ነበር) ፤የሳሕል በረሃ ምሽግ ቆፋሪዎችና ድንጋይ ፈላጮችና ጥርጊያ ጠራጊዎች ሆነው የቀሩ በርካታ ዜጎቻችን፤ የጊዜ ጉዳይ እንጂ ሁሉም እንደየ ተግባሩ በፈጣሪ ወይንም በዓለም ሕግ የእጁን ያገኛል እያልኩ አሳዛኝ መልዕክታችሁን፤ ዕንባችሁና እሮራችሁ ለአንባቢዎቼ አስተላልፌአለሁ።

ሻዕቢያ በአንድ ውድቅት /ቀን/ 2000 ኢትዮጵያዊያን ሙርኮኞች ከረሸናቸው አንዳንዶቹ  በዚህ ፎቶግራፍ ውስጥ  እንዳሉ የሚነገር።የግንቦት 7 ጀሌዎች ከኢሳያስ ጀሌዎች ጋር አንድነት በመፍጠር “ኢሳያስ ለፍረድ አይቅረብ” በማለት የድጋፍ ሰልፍ ሲያደርጉ ነው።

አሳዘኙ ክስተት ግን የግንቦት 7 ባንዳዎች ኢሳያስ ወደ ዓለም ፍረድ ቤት እንዳይቀርብ ለሻዕቢያ መሪ መቆማቸው ነው። በስቃይ ላይ ያሉ ኢትዮጵያዊያን ወታደራዊ እና ሲቪላዊ ወገኖቻችን የደም ዕምባ እንዳይቆም፤ መውጫ አጥተው የነበሩ እስረኞች አርበኞች አጋጣሚውን ዕድል አግኝተው ወገኖቻችን ከታፈኑት ጉድጓድና ምድረበዳ “እንዳይለቀቁ” ለኢሳያስ ሥልጣን መራዘም ጥብቅና የቆሙት የግንቦት7 ባንዳዎች ብቻ ሳይሆኑ፤ ያለመታደል ሆኖ ኢትዮጵያዊያን የሕግ ምሁራን እና በዓለም አቀፍ የታወቁ ዲፕሎማት ኢትጵያዊያንም ሆኑ በሚሊዮን የሚቆጠሩ የፖለቲካ ተወናዮችና ሰብአዊ ነክ ባለሞያዎችም ጭምር የነዚህ ወገኖቻችን ሁኔታና ስቃይ ተረስቶ እንዲቀር አስተዋጽኦ አድርገዋል። 

በዚህ አጋጣሚ፤ ከነዚህ ሁሉ ዲግሪ የጫኑ “እንግሊዝኛ አሳምረው የሚጽፉ “አገሳሶች”
የአርበኞቻችንን ገድል ሲረ “የቁርጥ ቀን ልጅ” ብለው ወታደሮች የሚጠሯት “ሞዴል፤ የፊልም ተዋናይና የሰብአዊ መብት ተሟጋች” የሆነቺው “የሐረር ወርቅ ጋሻው” - “ኤርትራ ምድር ድረስ ተጉዛ” ፋሺስቱ ኢሳያስን የያዛቸውን ምርኮኞች ወታደሮች እንዲለቀቁ መደራደሯንና በአካልም ከታሰሩብት እስር ቤት ሄዳ እንባዋ እየተናነቃት ዜጎቻችንን ስታነጋግር የተቀዳውን የቪዲዮ ማስረጃ ስናስታውስ ታሪክ በክብር ዙፋኑ አስቀምጦ እንደሚዘክራት ተስፋ አለኝ። የሐረር ወርቅ ጋሻው የተመረቀቺው ከ Dallas Baptist University (DBU) Sociology/Business Administration, Journalism/ Broadcasting and International Business/Trade በዲግሪ ተመርቃለች።   እስከዛው ግን በቁጭትና በብስጭት እንዳንታመም ሁሉም ፍርዱን ለፈጣሪ መስጠት ነው። ታሪካችሁን ስላካፈላችሁኝ እጅግ አመሰግናለሁ።

አሁን ወደ ጉዳያችን፡፡አዎ! ዛሬም ስለ የግንቦት7 የደም መርገምቶች/ባንዳዎች/ ደግምን ደጋግምን እንነጋገራለን። አሳዛኙ የሁለተኛው ዙር ገድል ጀምረነዋል (አንደኛው በወያኔ ዘመን ሲሆን፤ ሁለተኛው ዙር ድግሞ በግንቦት7/ ኦነግና በመሳሰሉ የውጭ ቅጥረኞችና ተገንጣዮች በአማራው እና በኢትዮጵያ ሉአላዊነት ለሚያቅዱት መጪው አፍራሽ ሚና ለመታገል የተያያዝነው ፊታችን ላይ ቆሞ ያለው መጪው ፈታኝ ገድል።) ሁለቱም ዙሮች እጅግ አሳዛኝ ክህደት የተሞሉበትና በውጭ ጠላቶች የሚታገዙና የሚተውኑበት/የተካፈሉበት ስለሆነ ትግላችን ረዢምና መራራ ነው። ከዚህ አብሮ አስቸጋሪ የሚያደርገው፤የወያኔ ብትርና እስርቤት ያሰቃያቸው አንደ አን ርዕዮት ዓለሙ የመሳሰሉ ፤ ከወያኔ የመከራ ሥርዓት ሽተው ወደ ውጭ አገር በመምጣት ወንዱ “የጨነቀው ዕርጉዝ ያገባል” ሴቱ “ቆሞ ከመቀር ባናና ” ሆኖባቸው የማሰብ ሕሊናቸው በንዴት፤በስሜትና በእልክ ታውሮ፤ በየዋህነት ሰተት ብለው ወደ ግንቦት 7 በመቀለቃል የፕሮፓጋንዳ ስራ የሚሰሩ ጋዜጠኞችና ብሎገሮች ወጣቱን በማደናገር ልቦናው ስላዋለሉት ለትግላችንና አንድነታችን ተጨማሪ ዕንቅፋቶች ሆነዋል።ይህ ፎቶግራፍ ተመልከቱት።

“Riyot Alem  manupulating Diaspora youth spreading  the propaganda of Ginbot7”
ስለ እዚች ወጣት አንድ ልበልና እንቀጥላለን። ወ/ት ርዕዮት በወያኔ መሰቃየቷ እጅግ እያዘንን እና ታስራም ልቦናችን መድማቱ ከጎኗ ጋር ቆመን የነበርን ብንሆንም፤ ዛሬ ከላይ የሰጠሁት ምሳሌ ሆነባትና ተገልብጣ ጸረ አማራ ከሆኑት የደቡብ ዘረኞች (The Southeren Racists) ጋር ተዳብላ “ግንቦት 7 ድርጅታችን በፖሊሲ አይመራም…….ወዘተ” እያለች “ፈረስ በሌለው ሕልማዊ ጋሪ እየተጓዘች” በሌላ በኩል አለቆቿ እንደ እነ ዘረኞቹ “ኤፍሬም ማዴቦ” የመሳሰሉ ኦክላንድ ካሊፎረኒያ በሻዕቢያ ፈስቲቫል በመገኘት አማራውን በመዝለፍ እዚህ መድረክ የተገኘሁት ድርጅቴ ግንቦት 7ን ወክዬ ሲሆን፤ እዚህ መድረክ ላይ ቆሜ የማደርገው ንግግር ሁሉ የድርጅቴ ፖሊሲና  ድርጅቴ የሚያምንበትን ነው፤ በማለት አማራዎችን “ነፍጠኛ” እያለ ከወያኔ የተበደረውን ታጊንግ/ዘለፋ በፖሊሲ ደረጃ ሲያሰራጭ፤ እሷ ደግሞ “ገንዘብ ቀርቶ ደሜን ለድርጅቴ እሰጣለሁ” እያለች በጸረ አማራ ፖሊሲ ለሚመራው ድርጅት ቆማ መቀባጠር ጅመራለች። ከወያኔ የማይሻሉ እነዚህ ጸረ አማራ ግለሰቦች የሚመሩት ድርጅት ቆማ ለድርጅቱ ውክልና መከራከሯን ከቀጠለች እሷም “በጸረ አማራ” ፖሊሲ ከሚጓዝ ድርጅት ተመችቷት ኤፍሬም ማዴቦ መሪዬና የትግል ጓዴ ነው ብላ የምታምን ነች ብልን ድምዳሜ  ለመውሰድ እንገደዳለን። “ፍየል ከመድረሿ ቅጠል መበጠሷ!”። ሰዎች ገናና ታሪካቸውን እራሳቸው ባንድ ውድቅት እንዴት ትብያ ላይ አንደሚጥሉት ስመለከት ይገርመኛል። ግንቦት 7 ከሽፍታው ከሻዕቢያው ሎሌ “ከማዓዛው ጌጡ” ጋር ሆነው ከትግራይ ድምበር እየተጠለፉ ለእርሻ ሸቅል፤ ለትግል ምልመላ እና ድብዳባ የሚዳረጉት ‘ወርቅ ለቃሚ’ የቀን ሞያተኛ ድሃ የትግራይ ወጣቶችን በጊላነት ማሰማራቱን ስታወግዢ አልሰማናትም? ለምን? የሚል ጥያቄ አቅርበንላታል።

 ግንቦት 7 አመራር ነሽ ይባላል፤ ዜናውን፤ሁኔታውን አታውቂም? ደም አፈስለታለሁ የምትይውን ድርጅትሽ የቀን ተቀን ዘገባ አይደርስሽም? ወይንስ አንቺም እንደ መሪዎቺሽ የድርጊቱ ተባባሪ? ወ/ት ርዕዮትን ለማሳሰብ የምንፈልገው፤ የድርጅቷ መሪዎች ጸረ አማራ ለመሆን የቻሉት ከጎኑ ከቆሙት ከኢሳያስ ሻዕቢያ ፖሊሲ የቀዱት ዘረኛነት ባሕሪ እንደሆነ የ “ዋ ምፅዋ” ደራሲ መቶአለቃ ታደሰ ቴሌ እንባ እየተናነቃቸው ከካሳሁን ሰቦቃ (አውስትርአሊያ ራዲዮ) ጋር ባደረጉት ቃለ መጠይቅ ስለ ኢሳያስ ፖሊሲ እናስታውስሽ።

እንዲህ ይላሉ፤-
በተለይ ደግሞ የአማራ ብሔረሰብ የሆኑትን ለብቻ ለይተው ድንጋይ ፍንቀላና መንገድ ስራ ያሰሯቸዋል።አማረኛ ተናጋሪ ከሆንክ ለብቻ ያደርጉና እናንተ ናችሁ ለኤርትራ ጦርነት ምክንያት የሆናችሁ ይሎቸዋል።ሁሉም ሰው አማራ ላይ ይበረታል ።አማራ ብሔረሰብ ሲመዘገብ አማራ ነኝ ብሎ ስለሚመዘገብ  አማራ የሚባለው ዘር ፋይል ለብቻ አለው። ፋይሉን ለብቻ አውጥተው ነበር የሚጠቀሙበት። በአማራ ላይ ያላቸው ጥላቻ እጅግ በጣም የከረረ ፣አንድ ቃል በመናገሩ አንድ ጥይት የሚሰጡበት ሁኔታ ነው የነበረው።” ይላሉ።

ወ/ት  ርዕዮት በአሳፋሪ ታሪክ “ኢሳያስ አፈወርቂን” በመደገፍ ወደ ሌላ ምዕራፍ ብትሸጋገርም፤ ዛሬም ወደ ሕሊናዋ ለመመለስ ሰፊ ጊዜ አላት እንላለን። ይህ ሁሉ ጸረ አማራነትና ስለ ኢሳያስ ማልቀስ ተይዞ ግን አብረን ለመጓዝ ያስቸግራል።ስለ ወ/ት ርዕዮት ሌላ ቀን እንመለስበታልን። አሁን ወደ ርዕሱ ልመልሳችሁ።

የመጀመሪያው አሳዛኙ ዙር ምን ምዕራፍ ላይ እንዳስቀመጠን ከታች የሚታየው ፎቶግራፍ በመመልከት ውርደታችንን በግልጽ ማየት ትችላላችሁ።ኢትዮጵያዊያንን ከኤርትራ በማባረር፤ በማፈን፤በመግደል፤በማዋረድ፤በመዝረፍ፤ እንዲሁም በሳሕል በረሃ ምሽግ ቆፋሪዎች አድርጎ በባርነት እስከዛሬ ድረስ ቁጥራቸው በእውን ያልታወቀ እጅግ በርካታ ሰዎች አፍኖ ይዞብን ያለው  ዓለም ያወገዘው “የሳሕል ወንጀለኛው” ኢሳያስ አፈወርቅ፤ ወደ ዓለም ፍርድ ቤት መቅረብ አለበት ብለው ኤርትራኖች ኢሳያስን ሲከስሱት፤ የኛ ማፈሪያዎች ግን መከሰስ የለበትም ብለው ከጠላት ጋር ወግነው ሰላማዊ ሰልፍ ሲያደርጉ ፎቶግራፍ ተነስተው ታሪክ “በባንዳነት”  የዘገባቸው የግንቦት 7 ደጋፊዎች ሰንደቃላማችንን አርክሰው፤ የደም መርገም ተካፋዮች-ሆነው-የተነሱት-ፎቶግራፍ-ከዚህ-በታች-ያለውን-ይመልከቱ።  
Ginbot 7 cults supporting Isayas Aafewerki የግንቦት 7 ጀሌዎች ከኢሳያስ ጀሌዎች ጋር አንድነት በመፍጠር “ኢሳያስ ለፍረድ አይቅረብ” በማለት የድጋፍ ሰልፍ ሲያደርጉ
 የአይሁዶችን አርማ እመሃል ሰንደቃላማችን ላይ በማስቀመጥ ወያኔ ያበላሻት ሰንደቃላማችን፤ ከጸረ ሻዕቢያ ስደተኞች ጋር ትግራይ መቀሌ

ወጣቶቹ፤ለሰንደቃላማችን ያላቸው የአያየዝ ክብርና ደምብ ስትመለከቱ እነኚህ የግንቦት 7 ደጋፊዎች (የወያኔ ዝቃጭ ፎቶግራፍ ትታችሁ፤ከነሱ የሚጠበቅ ስነምግባር በመሆኑ) በደም የተከበረቺውን ክብርት አርማችንን፤ እንደ አልባሌ ጨርቅ “ውሻ በአፉ እንደሚያንጠለጥለው ጨርቅ” አንጠልጥለው ሲይዟት በተቃራኒው ደግሞ፤ ኢትጵያዊያን ጀግኖች ለአገራችው ሉዓላዊነት ሲሉ ከሻዕቢያ ጋር እየተፋለሙ በኤርትራ በረሃዎች ደማቸው ሲፈስስ፤ በወደቁበት ሬሳቸው ላይ ስትውለበልብ የነበረቺው የነዚህ ወንበዴዎቹ ባንዴራ በዚህ ሰልፍ ላይ ሻዕብያዎች ባንዴራቸውን እንዴት በክብር ይዘው እያውለበለቧት እንዳሉ ከፎቶግራፍ ላይ ስታነጻጽሩ በወያኔዎች ዘመን የዚህ ዘመን ወጣቶች የሰንደቃላማችንን ክብር እንደ አልባሌ ጨርቅ ሲጎትቷት (ራሳቸውን አዋርደው-ሰንደቃላማችንን ለሻዕቢያ ባንዴራ አጋርነት እንድትቆም በማድረግ አራክሰዋታል) ነገም የመለስ ቡችሎች ለፍርድ አይቅረቡ የሚሉ ለወያኔ ባንዴራ አጋር የሚቆሙ ትግሬ ያልሆኑ ሌሎች ኢትዮጵያዊያን ሊኖሩ ይችላሉ/ዛሬም አሉ!!)። 

እነኚህ “የደም መርገምት” ሰንደቃላማችን ለጠላትዋ ባንዴራ አጋር እንድትቆም ራሳቸውን ለታሪክ ውረደት ከማጋለጥ አልፈው፤ ሰንደቃላምችንን እንደ አልባሌ ጨርቅ አዘቅዝው እያንጠለጠሉ፤ “ኢሳያስ መታሰር የለበትም፤ ኢሳያስ ወንጀለኛ አይደለም፤ ኤርትራ ነፃ አገር ነች’፤ ኢሳያስ በኤርትራ ሕዝብ የተወደደ ነው፤  ሕዝቡ በኢሳያስ ደስተኛ ነው፤ ሕዝብ አልተገደለም፤ በየእስር ቤቱ እየታጎረ ድብደባ አልደረሰበትም፤ በወጣት ዘማች ሴቶች ላይ አመጾች አይፈጸሙም፤ ብዙዎቹ ኤርትራ ነን ብለው የተመዘገቡ ሰደተኞች ኢትዮጵያዊያን እንጂ ኤርትራኖች አይደሉም፤ የኩናማ፤ የዓፋር፤የሳሆ፤የከበሳ ሰዎች በኢሳያስ የዘር ማጽዳት ዘመቻ ግድያ አልተፈጸመባቸውም፣ ኢሳያስ አሸባሪ አይደለም፤ ኢሳያስ ለአልሸባብ ደጋፍና ስልጠና አልሰጠም፤ ኢሳያስና ጓዶቹ ከንቅዘት ነፃ ናቸው! ብለው ባደባባይ ከሻዕቢያ ሎሌዎች ጋር መቆማቸው እንዲህ ያለ እጅግ አስገራሚ የሆነብን ዓይኑ ያፈጠጠ ባንዳነት ታይቶ ተስምቶ አይታወቅም ። 

ማወቅ ያለብን፤ የሰላማዊ ሰልፉ ዋነኛው ትኩረትና የየተደመጡት መፈክሮች ከላይ የተጠቀሱት ጥቂቶቹ መፈክሮች ነበሩ። እነኚህ መፈክሮች በመደገፍ የግንቦት 7 ጀሌዎች አደባባይ ላይ ከሻዕቢያ አጋሮቻቸው ጋር ቆመው ንግግር ሲያደርጉ የተሳተፉበት ተልዕኮ በሻዕቢያ ቲቪ ከአስመራ ለመላ ኢትዮጵያ ተላልፏል። በሻዕቢያ ተ/ቪ ከአስመራ ወደ ኢትዮጵያ የተላለፈው የግንቦት 7 እና የምናውቀው የወያኔ አምባሳደርና አሽከር የነበረው የኦጋዴን ሶማሌው የመሓመድ ሓሰን አስገራሚ ጊላነት/ “እሽክርና” ንግግር ከኤርትራ ምድር እየተለቀሙ በግፍ እና በአሰቃቂ ሁኔታ ተፈናቅለው እንዲባረሩ የተደረጉ መስቀል አደባባይ ፈሰሰው የነበሩ ኢትዮጵያውያን፤ አዲስ አበባ ሆነው ዛሬ የተላለፈው ይህ የ ቲ/ቪ ትርኢት ሲመለከቱ ምን ተሰምቷቸው ይሆን?
 
እነኚህ የግምቦት 7 ወጣት ጀሌዎች መለስ ብልን ታሪክ እንዲያጠኑ እናሳስባቸዋለን። ይህች እንደ አልባሌ ጨርቅ በማዝረክርክ ይዘዋት እየታዩ ያሏት፤ በህይወት እንድትኖር ፤ከፍ ብላ እንድትውለበለብ ከፍተኛ ምስዋእት ሲከፈልላት የነበረቺው፤ ይህች ክብርት ሰንደቅ ወርዳ፤ በምትኳ መጀመሪያ በጣሊያን፤ ከዚያም እሷ ወርዳ፤ በምትኳ የሽፍታው የኢሳያስ ባንዴራ ኤርትራ ምድር ውስጥ እንድትውለበለብ በርካታ የኢትዮጵያ ጠላቶች የተካፈሉበት ሴራና ውጤት መሆኑን ልናስታውሳቸው እንወዳለን። 

በመሰረቱ ኢሳያስ ማን ነው? የግንቦት 7 ጀሌዎች ይህ ሰው ያውቁታል? ወይስ መሪዎቻቸው ባንዳው ንአምን ዘለቀና እና ብርሃኑ ነጋ ፤አንዳርጋቸው ጽጌና ይሁዳው ካሳ ከበደ “ኢሳያስ ለኢትዮጵያዊያን ወዳጅ እና  በጎ አሳቢ ነው” ብለው ስላስተማሯቸው ነው ይህ ሁሉ አሳፋሪ የጊላነት ጫጫታ? ( የኰለኔል ታደሰ ሙሉነህ ልጅ የህ የጫጨታ ጥብቅና ስትመለከት ምን ይሰማታል ብለው ቆም ብለው አስበውበታል?) ያንን ተቀብለው ነው በባንዳነት እየነጎዱ ያሉት? ኢሳያስ የጸረ አማራው የግንቦት 7 ድርጅት ወዳጅ እንጂ የኢትዮጵያ ወዳጅ አይደለም። ማስረጃ ልስጥ። አምስተርዳም የሚኖሮው ጋዜጠኛ ክንፉ አሰፋ ጸረ ኢትዮጵያ የሆነ የረዢም የባዕዳንን ሕልም ማን እውን እንዳደረገው በአንድ ግሩም ጽሑፍ ውስጥ ያሳሰባችሁን ቁም ነገር ላስነብባችሁ፡

“ታሪክ እንደሚነግረን ለሃያላን ሃገሮች አልንበረከክ ያለች ኢትዮጵያን ለማዳከም የባህር በር ማሳጣቱ ሴራ በባእዳን ነው የተጠነሰሰው። እሳቸውም ምስጢሩን በደንብ አድርገው ያውቁታል። ይህን ሴራ እውን ለማድረግ በቱርክና በግብፅ ከዚያም በጣሊያንና በእንግሊዝ ብዙ ተሞክሮ ነበር። የጉንደት፣ የጉራ፣ የኩፊት፤ የኮቲት እና የዶጋሊ ጦርነቶች ለዚህ ዋቢ ናቸው። ሁሉም አልተሳኩም። ይህንን የቤት ስራ በመጀመርያ ጀብሃ ከዚያ ቀጥሎ ሻእቢያ ከባእዳን ተቀብሎ መስራት ጀመረ። የነዚህ ባእዳን ህልም በመጨረሻ በኢሳያስ አፈወርቂ እውን ሆነ። 5 ሚሊዮን ህዝብ ላይጠቀምበት የሁለት ወደብ ባለቤት ሲሆን፣ 80 ሚሊዮን ህዝብ ግን ያለ ወደብ እንዲኖር ተደረገ።

እኝህ ሰው የርስበርስ ጦርነቱን አሸንፈው ኤርትራን ባስገነጠሉ ጊዜ ጀግና ነበሩ። የግዜ እንጂ የሰው ጀግና የለምና የጀግንነታቸው ጫጉላ እንዳሰቡት ረጅም አልዘለቀም።ነጻነቱንበቅጡ ሳያጣጥሙት ሌሎች ጦርነቶች ውስጥ ገቡ። ትልቁ እና ዋነኛው ጦርነት ግን ከሕዝባቸው ጋር የገጠሙት ፍልሚያ ነው። ውጤቱም ስደት ሆነ። ዛሬ የኤርትራን ምድር ለቅቆ ለመጥፋት የማይጥር ዜጋ የለም። በኮንቬንሽናል ጦርነት ጊዜ ከሚሰደደው ህዝብ የበለጠ ቁጥር ያለው ህዝብ ይሰደዳል። ከኤርትራ ህዝብ ብዛት አንጻር ሲታይም ስደተኛው እጅግ ብዙ ነው። የተሳካለት የኤርትራ ተወላጅ በረሃ አቋርጦ ኢትዮጵያ፤ ሱዳን እና ሊቢያ ይዘልቃል። ያልተሳካለት ደግሞ በየጠረፉ የሻእቢያ ራት ይሆናል። የዜጎች ኩላሊት ሽያጭም እዚያው ይካሄዳል። በኤርትራ እንደቀልድ የሚነገር እውነታ አለ። ኢሳያስ አፈወርቂ ለኤርትራ ካበረከቱት ነገር ሁሉ የኢቦላ ወረርሽኝ በሃገራቸው እንዳይገባ ማድረጋቸው ነው። ከዚያ የሚወጣ እንጂ የሚገባ ሰው ስለሌለ።
በዚህ ዘመን ከሚከሰቱት እልቂቶች ሁሉ የላቀ እልቂት እና ሰቆቃ የምናየው በነዚህ ወገኖቻችን ላይ ነው። ስንት ኤርትራውያን እንደበላች የሲሲሊዋ ላምባዶዛ ትመስክር።” ይላል ክንፉ አሰፋ።
ኮለኔል ካሳሁን ትርፌ የነኚህ ኢትዮጵያዊያን መኮንኖች ውርደት ማን ነበር ተጠያቂው? ኢሳያስና መለስ ዜናዊ

የግንቦት 7 ጀሌዎች በባንዳዎቹ መሪዎቻቸው በኩል የሚነገራቸው ኢሳያስ ለኢትዮጵያ ቀና አሳቢ ነው የሚለው ዓይን ያፈጠጠ ውሸት ክንፉ አሰፋ እንዳለው “ለኢትዮጵያ ሕዝብ የመቆርቆሩ ጉዳይ ግን የአዞ እንባ ነው። እዚያው እጉያቸው ላሉት ኢትዮጵያውያን ያልራሩ፣ መረብን ተሻግሮ ማሰቡ ግብዝነት ነው የሚሆነው።”እኔ የምተረጉመው ከዚያ በላይ ነው። የምተረጉመው ‘ግብዝነት” ሳይሆን፤ ሆን ብሎ በጥንቃቄ የተጤነ እንደ ግንቦት 7 የመሳሰሉ  ጀሌዎችን ልብ ለማማለል የተጠና ሴራ ነው። በሻዕቢያው ወንበዴ ኮለኔል ፍጹም እና በግንቦት 7 መሪውና  በማዓዛው ጌጡ ትእዛዝ ከትግራይ ድምበር እየተጠለፉ ለእርሻ ሸቅል፤ ለትግል ምልመላ እና ድብዳባ እንደሚዳረጉና ወያኔ ጀሮ ዳባ ብሎ ሰምቶ እንዳልሰማ ነገሩ ሊደብቀው አንደሞከረው ለትግሬዎቹ ሳይራራ ለሶማሌዎቹ እንደሚራራው አይነት ለፕሮፓጋንዳ (ለሌሎች ወገኖች በመቆም /ፕሮክሲ ጦርነት) በእቅድ የሚከናወን እገዛ እንደማለት ።
ደብዛቸው የጠፋው አይሮፕላን አብራሪው አርበኛው ኮለኔል በዛብህ ጴጥሮስ
ሻዕብያ በሰሓል ሐሩራማ በረሃ ውስጥ በጉልበት ሥራ ያሰማራቸው ከላይ የሚታዩ ወታደሮች ደብዛው እንዳይገኝ ግንቦት 7 ለሻዕብያ ዕድሜ ይማጸናል!

የግንቦት 7 መርገምቶች፤ ከዚህ ከይሲ ሰው ጋር ቆመው ባደባባይ ወጥተው ሰንደቃላማችንን እየጎተቱ ሲያራክሱና የባንዳ ድምፅ ሲያስሰሙ “ቲቪ ኤሬ” በተባለው አስመራ ከተማ የሚተላለፈው በሻዕቢያ ቴ/ቪዥን ታይተዋል። እንደ እሳት የሚያቃጥል ጉድጓድ ስር እና ኰንተይነር ውስጥ  ታሽገው የሚደርስላቸው ያጡ፤ ታስረው እየተሰቃዩ ያሉ ኢትዮጵያዊያን እና  ኤርትራዊያን የነዚህ ከሃዲ እና አሳፋሪ ሰዎች ድምጽና ምስል ለሻዕቢያ ጥብቅና ቆመው ድምጻቸውና ምስላቸው በሻዕቢያ ቲቪ ሲተላለፍ ቢያዩ ምንኛ አንጀታቸው እንደሚበግን ገምቱት!! እጅግ፤እጅግ አሳዛኝና አስገራሚ ሁኔታ!
ከረዢም መራራ የቀናት ቶከስ በብስጭትና በድካም አንቀላፍተው እንዳሉ ቶክስ ተከፍቶ አልጌና ውስጥ በጠላት እጅ የወደቁት ኮለኔል ግርማ ተሰማ የውቃው ዕዝ ዋና አዛዥና አርበኛ። ይህ አሳዛኝ ፎቶ ስትመለክቱ አንጀታችሁና ዓይናችሁ ምን ይፈታተናችል?
በአሜሪካኖች የስለላ ሳተላይት መረጃ እየታገዙ ወያኔና  ሻዕቢያ ባገኙት ዕድል አርበኞች ኢትዮጵያዊያን፤ወታደሮች ለሻዕቢያ ምግብ እንዲያዘጋጁ በተገደዱበት ወቅት እንጀራ ሲጋግሩ።


ኢትዮጵያ ምርኮኛ ወታደሮች ለሻዕቢያ ምግብ አቅርቦት በቆላማ በረሃ ውስ  በዶሮ ዕርባታ ያሰማራቸው አርበኞች ወታሮቻችን።
ኢትዮጵያ ወታደሮች በሳሕል በረሃ ውስጥ አትክልት እየተከሉ ፍራፍሬ በመልቀም ለሻዕቢያ ምግብ እየለቀሙ ተክል ለቀማ ያሰማራቸው ጀግኖች። 

ያጋዜጠኛ ክንፉ አሰፋ እንዳለው ለዚህ ‘ህግ፣ ፍትህ፣ ዲፕሎማሲ ምናምን የሚባሉ ነገሮች የማይገባው ሰው” ጥብቅና መቆም እኛ ትግሬዎች ኢሳያስ  በምናውቀው ሕቡእና ግልጽ ባሕሪው “ኦነጎችን” (ዝበርንዑ) “ያረረ/የተበላሸ ወጥ” ብሎ እንደዘለፋቸው ሁሉ፤ ግንቦት 7 ባንዳዎችም “ጊላቶተይ” (አገልጋዮቼ) ብሎ እንደሚጠራቸው የሚያጠያይቅ አይደለም። ክንፉ አሰፋ እንደነገረን፤ “እርግጥ ነው፤ ስለ ኢሳያስም ሆነ ስለ ኤርትራ ጉዳይ እኛ አያገባንም። አምባገነንነታቸው የኛ ጉዳይ ላይሆን ይችላል። የዚያች ሃገር ጉዳይኢትዮጵያዊ አይደለንምብሎ 99.9 በመቶ ድምጽ የሰጠው ህዝብ ጉዳይ ነው። ግና ባሰኛቸው ጊዜ እየተነሱ ቁስላችንን ሲነካኩብን ዝም የማለት ሞራል አይኖረንም። ከአሰብ በግፍ እና በአሰቃቂ ሁኔታ ተፈናቅለው ሲያበቁ መስቀል አደባባይ ለወራት የፈሰሱ ኢትዮጵያውያን ጉዳይ ከቶውንም ከአእምሯችን አይጠፋም። ኢሳያስ አፈወርቂ ዛሬ በሰራነው አንጸጸትም፣ እንዲያውም ካሳ ይገባኛል ሲሉ በድፍረት ተናገሩ። ምን እንላለን? በወገኖቻችን ላይ እየሰሩ ላሉት ግፍ ፈጣሪ ይከፍላቸዋል። ካሳቸውንም ከታሪክ መዝገብ ያገኙታል።

“በፖለቲካ ቋሚ ጠላት ወይንም ቋሚ ወዳጅ የለም።” ይላል ክንፉ፤ “የጋራ ጥቅም ግን አለ። ሰጥቶ መቀበል የሚሉት ነገር። ኢሳያስ አፈወርቂ ግን ለጋራ ጥቅም ሳይሆን ለጽድቅ እንደሚሰሩ አይነት ነው እየነገሩን ያሉት። በኢትዮጵያ ችግሮች አሉ። አማራጭ የፖለቲካ በሮች በሙሉ ተዘግተዋል። አገዛዙ ፍጹም አንባገነን ሆኗል። ኤርትራን መጠጋት እንደ መፍትሄ የወሰዱ ወገኖች ሌላ የትግል አማራጭ ስላጡ ሊሆን ይችላል። የቸገረው እርጉዝ ያገባል እንደሚባለው። ያለፉት ተመክሮዎች ግን ሻእቢያን በጥርጣሬ እንድናይ ያደርገናል። ከአስር አመት በፊት አስመራ የመሸጉ ሃይሎች አሁንም አስመራ ላይ ናቸው። አንዳንዶቹ እዚያው ሲያረጁ ሌሎቹ ደግሞ አእምሯቸውን ስተው ሲለቅቁ እያየን ነው። የእነ ኮሎኔል ታደሰ ሙሉነህ ደብዛ መጥፋት፣ 18 የአርበኞች ግንባር አባላት በድንገት መሰወር፣ አስመራን እንዳይለቅቁ እገዳ የተጣለባቸው የተቃዋሚ ሃይል አባላትወዘተ እጣ ፈንታ በኢሳያስ እጅ ላይ ነው ያለው። ስለ ኢትዮጵያ መቆርቆር ከዚህ ይጀምራል። እነዚህ ወገኖቻችንን ነጻ ካደረጓቸው በኋላ ኢትዮጵያውያንን ለውይይት ቢጠሩ አንድ ነገር ነው። በትንሹ ያልታመነ፣ በትልቁ አይታመንምና።” በሚለው የክንፉ አሰፋ ጽሑፍ እሰናበታችለሁ።

ድሮውንስ “ነፍጠኛ” እያሉ አማራን የሚዘልፉ፤ “14 ክፍለሃገር መዝሙር ዘማሪዎች” እያሉ ጸረ አማራና ጸረ ኢትዮጵያ የሆኑ ግለሰቦች የሚመሩት ግንቦት 7፤ ለጸረ አማራው ኢሳያስ አፈወርቅ ጥብቅና ባደባባይ ቆመው ቢጮሁ ምን ያስገርማል? ለማንኛውም ባንዳ (የደም መርገም) ከመሆን ይሰውረን። በሻዕቢያው ሻለቃ ዳዊት እና በሻቢያው ኰለኔል ፍፁም ትዕዛዝ፤ በማዓዛው ጌጡና በግንቦት 7 አርበኞች ግምባር ተላለኪነት የተፈጸመው የድሃ ትግሬዎ ጠላፋ ወንጀል እዚህ ላይ በመጫን ይመልከቱ።

Interview with Ethiopians who were abducted by Shabia

 Documentary - Part 1


 ጌታቸው ረዳ (ኢትዮጵያን- ሰማይ ብሎግ አዘጋጅ Ethio Semay) getachre@aol.com