Tuesday, January 6, 2015

ወያኔ ደደቢት በረሃ ውስጥ በስቶክሆልም ሲንድሮም ስብስቦች በመታጀቡ ፋሺስታዊ ማንነቱን ሊደብቀው አይችልም ! ጌታቸው ረዳ ኢትዮጵያን ሰማይ አዘጋጅ/



 ወያኔ ደደቢት በረሃ ውስጥ በስቶክሆልም ሲንድሮም ስብስቦች በመታጀቡ ፋሺስታዊ ማንነቱን ሊደብቀው አይችልም !
ጌታቸው ረዳ ኢትዮጵያን ሰማይ አዘጋጅ/ Editor Ethiopiansemay    getachre@aol.com

The 10 Bullets are symbols representing the future 10 Tigray Awraja Gizat. Remember Tigray had 8 Awraja. The two added are meant from Wollo and Gonder to make it 10 Awraja annexed by the power of the barrel of a gun. The promise to annex more territories from the Amhara provinces depicted on its seal is currently fulfilled.
Amhara children slaughtered by three known Ethiopian 4 Fascist Liberation Groups namely the "Tigrayan People Liberation Fromt" (the present Ethiopian Government in power  (2) Oromo Liberation Front, (3) Islamic Oromo Liberation Front (4) Oromo People Democratic Front
ባለፈው ጽሑፌ ‘ወያኔ’ ዲሞክራቲክ እንጂ “ፋሺስት” አይደለም፤ የህ ስያሜ ጠንክሮ የሚዘወትረው ባንተው ጽሑፍ ብቻ ነው፤ ብለው ያሉኝ የወያኔ ጀሌዎች እና ሌሎችም  ቢያነስ ወያኔ አምባገነን ቢሆን እንጂ “ከነ ሂትለር/ጣሊያን የሚያመሳስለው ፋሺስታዊ ገመና ስላልታየበት “አምባ ገነን” ብትለው ክርክራችን ተአማኒነት ሊኖረው ይችላል፤ ሲሉ “ክርዮሲቲ” በሚል ርዕስ” በኢመይል የጠየቁኝ አንባቢዎችም አሉ። ይህ ውዥምብር በግለሰዎች ብቻ የተወሰነ ሳይሆን፤ በአብዛኛዎቹ የተቃዋሚ የፖለቲካ ቡድኖች እና የሰላም ትግል ምንነት ተንታኞችም ጭምር (ለምሳሌ አቶ ግርማ ሞገስ በተባሉት የሰላማዊ ትግል ተንታኝ በቪ ኦ ኤዋ አዳነች ፍስሀየ ዘንድ ቀርበው በቅርቡ ስለ ምርጫና ዲሞክራሲ ማብራርያ የሰጡም ጭምር) የወያኔ አራዊታዊ ትክለ ሰውነትን “በአምባገነናዊነት ባሕሪ ብቻ” እንዲታይ በተሳሳተ ስዕል ለሕዝቡ ሲያስተምሩ አስተውያለሁ። ይህ ውዥምብር ደግሞ የትግሉን አቅጣጫ እና የትግሉ ስልት አሳስቶ የሕዝቡን መከራ ማራዘም ነው።

 ባጭሩ ላብራራ። ፋሺስት ተግባሮች እና ሥርዓቶች፤ ባብዛኛዎቹ አገሮች ተንጸባርቀዋል። ፋሺስትነት የተገበሩ አገሮች አንድ ወጥ የሆነ ባሕሪ እና አፈጻጸም የላቸውም። ባንዳንድ ሁኔታዎች ይገናኛሉ፤ ባንዳንድ ስነ ምግባሮቻቸው ደግሞ ይለያያሉ። እላይ እንደገለጽኩት ወያኔ ፋሺስት ነው፤ ብዬ ስል፤ “አምባ ገነን እንጂ ፋሺስት ሊሆን አይችልም” የሚሉ አሉ። ከኦነግ ጀምሮ አብዛኛዎቹ ተቃዋሚዎች የወያኔን ፋሺስቱ ቡድንን ፤“ይህ አምባገነን ሥርዓት” ብለው በቪኦም ሆነ በየቃለ መጠይቆቻቸው ይጠሩታል ። አንዳንድ የተቃዋሚ የዜና ማስራጫዎችም ሆኑ የፖለቲካ መሪዎች ለምሳሌ አንዳርጋቸው ጽጌ ‘ኢሳያስ አፈወርቂን’ የሚመለከተው ‘ለኢትዮጵያ ሕዝብ ደህንነት የሚቆረቆር’ ግሩም ሰብአዊ ፍጡር ብሎ ሲመለከት፤ የራሱ ራዲዮ የሆነው ግንቦት 7 ራዲዮ አዘጋጅ ደግሞ ‘የኦነጉን ዘረኛ እና ጸረ አማራ ፋሺሰቱ’ ሽማግሌው ሌንጮን “ሰብአዊነት የተላበሱ” ሲል ሰብአዊነትን አላብሶታል (ራዲዮኑ ሲመሰረት ያደረገው ቃለ መጠይቅ ያድምጡ)። ፋሺሰታዊ ባሕሪ የተላበሱ ግለሰቦችም ሆኑ ፋሺስታዊ ቡድን የሚመሩ ክፍሎች በኢትዮጵያዊያን ዓይን የግንዛቤ ጉድለት እንዳለ አመላካች ነው። ሰሞኑን ግንቦት 7 ራዲዮ ጣቢያ የኔን መንገድ በመከተል ‘ፋሺስት ወያኔ’ እያለ በተደጋጋሚ እንደ ብራንድ /አዲስ መፈክር/ በቅርቡ እየተጠቀመበት አድምጫለሁ። ይህ ደግሞ ተገቢ ስያሜ ነው። ከዚያ በፊት የዚህ ድርጅት መሪዎችና ራዲዮን አዘጋጆች ወያኔን ሲተነትኑ በአምባገነንነት እንደነበር ማሕደሮቻቸው ያመላክታሉ።

ወያኔ ፋሽስት ሊሆን አይችልም፤ የሚሉ ሰዎች ፋሺዝም ከእነ ሙሶሎኒ (ጣሊያን)፤ ሂትለር (ጀርመን) እና ፍራንኮ (ስፐይን)፤ ጃፓን (ፉሚማሮ) ቺሌ፤ ባሕሪያቶች እና ክስተቶች በማነፃፀር እየተመለከቱት አንደሆነ እገምታለሁ። ፋሺስዝም ቢያንስ በ38 አገሮች ታይተዋል።ሁሉም የተለያዩ ባሕሪያቶች አሉዋቸው።

ምክንያቱም በተለይ በጣሊያን እና በጀርመን የተከሰቱ አስከፊ ኢሰብአዊ አርምጃዎች በዘመነ ወያኔ ከታዩ ፋሽታዊ ባሕሪዎች  ስለሚለያዩ ወያኔን ፋሺስት ለማለት ይከብዳቸዋል። ግንዛቤአቸው ግን የተሳሳተ ነው።

የወያኔ ስርዓትና ባሕሪ ከሂትለር፤ከሚሶሎኑ ባሕሪዎች እና ተግባሮች የሚያመሳስላቸው ብዙ ዝርዝሮችን ካሁን በፊት ገልጫለሁ። ወንድሜ ገብረመድህን አርአያም ስለ ወያኔ ምንነት ሲገልጽ በብዙ ሺሕ የሚቆጠሩ አማራ ሙርኮኞች አጽረጋ በተባለው ‘ውስተ ምድር’ (አንደር ግራውንድ) አንደተረሸኑ ነግሮናል (በነገራችን ላይ ሌሎች ታጋይ የነበሩም ስለ ታሪኩ ሳወያያቸው ይህንኑ ታሪክ እውነትንት እንደላው አረጋግጠውልኛል። እንዳውም ብዙ ክፉ ነገሮች አንዳሉና ሊያወሱት እንደማይፈልጉ ነግረውኛል። ካናዳ የሚኖሮው በርሔ ሐጎስ የተባለ የድሮ ታጋይ እና የዛሬ የወያኔ ቀዳሽ እና አወዳሽም “ሙሴ” የተባለው የወያኔ የመጀመሪያ መሪያቸው ዓድዋ ገጠር ውስጥ አንዱን ሰው አለ ፍርድ ዓይናችን እያየን  ጠመንጃውን አቀባብሎ ሊረሽነው ሲል፤ ስየ አብርሃ ተወው ብሎ የሰውየውን ሕይወት አንዳዳነው ደጀን በተባለው ራዲዮ ጣቢያ በትግሬዎች ቴሌ ኮንፈረንስ ተናግሯል። ይህ ፋሺስታዊ ባሕሪ መቸ እንደጀመረ ማሳያ ነው)። ከዚያም አያይዞ “ቴትራሳይክሊን” በውስጡ ያቀፈውን ዱቄት በማራገፍ፤ በምትኩ፤ የሳዮናይድ መርዛማ ዱቄት በመክተት ከ45 እሰከ 60 የሚገመቱ ወታደራዊ ሙርከኞች/አማራዎች በወባ መከላከያ ሽፋን እንዲውጡት በማድረግ የጅምላ ግድያ አንደተፈጸመባቸው “ታላቁ ሴራ” በተባለው ገብረመድህን አርአያ ያብራራበት ማሕደር ላይ ተገልጿል። ይህ ፋሽስታዊ አመላካች ባሕሪን ልብ ይበሉ።

ደርግም ኢትዮጵያዊ ነዉ እናንተም ኢትዮጵያዊያን ናችሁ።ስንልከበስተጀርባችሁ የሆነ ነገር አላችሁ!” በማለት ማሰር እና መቅጣት ጀመሩን …(1500 እንሆናለን)።ወላጆቻችን ታሰሩ። የእርሻ ማሳዎቻችንም ተወረሰ። ቀንደኛ አድመኞች ናችሁ በተባልን በተወሰንን ሰዎች ላይ ከባድ ቅጣት ተፈጸመብን። 6 ወር አስከ ዓመት በእስራትና በግርፋት ተቀጥተናል። ክንዶቹ ለረዥም ጊዜ በቀጭን ጅማት ነገር በመታሰራቸዉ ምክንያት ጣቶቹ ደም አስከ ማንጠባጠብ የደረሰ ጓደኛችንም ነበረ። በግርፋት አንድ እጁ እና አንድ እግሩ ሽባ የሆነ ጓደኛየ ሃለቃ ሓዲሽ የባላል። ቢዚያን ወቅትሙሹሮችና ካህናትሳይቀሩበጾመ ህማማት’ ጊዜ ከቤተክርስትያንተወስደዉ ከሽማግሌዎች በቀር ሁሉም ታፍሶ ተወሰደ። ለመሸሽ የሞከረዉን እንደጅግራ እያሯሯጡ በጥይት ያሳድዱት ነበር። ይህ ሁሉ የተፈጸመው የካቲት ወር 1981 . ጀምሮ ማለት ነዉ።ትግራይ ነፃ ከወጣች በሗላ ማለት ነዉ ከዚያሰዉ እንደ አዉሬ በአካባቢዉ እየተበተነ በአካባቢዉ በቀን ሰዉ የሚባል አይታይም ነበር። እነሱም እንደ ጅግራ እያደኑ ይዉላሉ፤መሬታችንም ለታጋይ ቤተስብ ታድሎ የምንቀምሰዉ የምንልሰዉ አልነበረም።ከቀበሌ ወደ ቀበሌ የሚያስተላልፉ የነሱ ካድሬዎች ካዩን ጥይት ይተኩሱብናል፤..”) ድያቆን ብርሃነ ገብረህይወት (በ7 ጥይት ደብድበው ሞቷል ብለው ጫካ ውስጥ ወረወሩኝ) ምንጭ አትኦጵ/ /ሓይካማ መጽሐፍ ውስጥ በትግርኛ የተተረጐመ፤ ደራሲ ጌታቸው ረዳ)

ሕዳር 25 ቀን እንደገና ጦር ተጭኖ መጣ፣ሠራዊት ነዉ:: መትረየስ፣ክላሽ ላዉንቸር ታጥቀዋል። ቁጥሩ አይታወቅም፣ በቅጠሉ ቁጥር ነዉ።ብዛቱ ይነገር ቢባል 500 እና 600 ይሆናል።ሰዉን ይገድል፣ቤትን ያቃጥል ጀመረ።ሰላም ነዉ ብለዉ ከቤታቸዉ የተቀመጡትን ሰዎችከክልል ሦስት ነን የመጣን፣ከባሕር ዳር ነን የመጣንእያሉ ቤቱን ከፍቶ ሲያገኙት ያዉ መግደል ነዉ፣ገደሉት! ቤቱን በእሳት፣ክምሩን በእሳት አነደዱት።ሰዉን በጥይት ፈጁት። የሞተዉ ቁጥር የለዉም በሺ ነዉ። እስከ ሕዳር 27 እና 28 ድረስ ዕልቂት ነበር። ይተኩሳሉ፣ይገድላሉ፣ የተቀመጠዉን በዱላ፣የሮጦዉንም በጥይት ይሉታል። ልጅም፣ ህጣንም፣ሴትም ዱላ የበዛበትፈቀቅ ሲልበጥይት ነዉ። ወንጀሉ ይሄ ነዉ አይባልም። ጥያቄም የለበትም ከመስመር ያለዉን አማራ በጠቅላላ አጥፉ ነው የተባልነውአሉ። ወደ ድሬ ወደ ሃሮ የሚያወጣ መንገድ አለ፣ ከዚያ ወዲህ ሰባት ገበሬ ማሕበሮች ነን። እነዚያ በሙሉእንዲጠፋ ታዝዘናልይሉ ነበር። ትዛዝ ነው! አባቴንም ባገኝ አልምርም፣ሁላችሁን እናጠፋችሗለንአሉን። አጠፉን! የተቀበረም የለም፤ያለቀሰም የለም፣ንብረትም እዛው ከሰለ። ሕይወትም እዛዉ አለቀ!


ከዕልቂቱ አስከፊ ገጽታ በከፊል፣-
- (1) “ጌጣ ጌጡን አይተዉ አንቀልባዉን ለመዉሰድ በሃይል ጎትተዉ ሲፈቱት የሁለት ዓመት ሕፃን ከእናቱ ጀርባ ከሚነደዉ ቤት ደጃፍ ላይ ወድቆ በእሳት ተቃጥሎ ሞተ።

(2) “መልካሙ ዉባለም የተባለዉን ገድለዉ ምላሱን አውጥተዉ ወሰዱት፣
 (3) አስረግደው ውቡ የተባለዉን በጥይት ገድለው አንካሴ አንገቱ ላይ፣ ወገቡ ላይ እግሩ ላይ ቸክለውበት ሄዱ።
 
(4) አንድ ሴት ሦስት ልጆቿን አስከትላ ስትሸሽ፤ ወንዝ ላይ ስትደርስ በጥይት ገደሏት። ሦስቱ ልጆቹ በርረው ወንዝ ውስጥ ገቡና እዛዉ ሞተው ቀሩ።” 

(5) አባ በላይ ዋለ የተባሉትን ዓይነ ሥዉር ገደሏቸዉ፣፣ አማራ! አማራ ነዉ! ብለዉ ብልታቸዉን ቆረጡት።” 

(6) መልካሙ ዉባለም አርደዉ ገደሉትና ምላሱን አውጥተው ወሰዱት
 ማጠቃለያ፣- ፖሊሲዉ አማራን ማስወጣት ብቻ ሳይሆን አማራ እንዳይገባም ይከለክላል፣፣ ባለዉ የጎሳ ፖሊሲ መሠረት በአሁኑ ጊዜ የአማራዉን ተወላጅ እየጨፈጨፉና እያሳደዱ ከወለጋ ማስወጣት ብቻ ሳይሆን ወደ ወለጋም እንዳይገባም እገዳ እየተደረገ ነዉ

  ከአንድ ወር በፊት ወለጋ ይኖሩ ከነበሩ አማራዎች ዉስጥ ዘመድ ጠይቀዉ ለመመለስ ጎጃም መጥተዉ ነበር፣፣ የካቲት 14 ቀን 1993ወደ ነበሩበት (ወለጋ)ለመመለስ በሦስት መለስተኛ አዉቶቡሶች ተሳፍረዉ ሄዱ። ኪራሞ ላይ ሲደርሱ 10የሚሆኑ የኦሮሞ ፖሊሶች አትሄዱም ብለዉ መለስዋቸዉ። ይሁን እንጂ ከሦስቱ አቡቶቡሶች አንዱ፣ የሰሌዳ ቁጥር 3-13316የሆነዉና የአቶ ተሻለ ዓለማየሁ በተባለዉ ሾፌር የሚነዳዉ በአጋጣሚ አልፎ ሄደ። ሁለቱ የሰሌዳ ቁጥር 3-39522-በአቶ ቴዎድሮስ ዘርዓይ የሚነዳዉና አቶ አምሳሉ ወርቅነህ የሚያሽከረክሩት የሰሌዳ ቁጥር 3-13282-አቶቡሶች ሰዎችን እንደጫኑ ተመልሰዋል። ቤተሰቦቻቸዉ ወለጋ፣ እነሱ ክልል ሦስት!!!/--/  (ልዪ ጥንቅር- ጦቢያ ቅጽ 8 ቁጥር 8 1993 ምስራቅ ወለጋ ‘ የአማራዉ ሕዝብ ዕልቂትባንድ ዘር ላይ ያነጣጠረ ጥቃት’ ፤ ዘጋቢ ኦርዮን” 

ዋሺንግተን ዲሲ ኗሪ የሆነው ጠበቃ ሙሉጌታ አረጋዊ  ራዲዮ መርሃዊ ከተባለ የወያኔ ደጋፊ ትግርኛ ራዲዮ ጣቢያ ላይ ኤትኒክ ክሊንሲንግ (የጎሳ ፍጅት)“በቲ ኤል ኤፍሊካሄድ አይችልም። ይህ (ውንጀላ) ከየት እንደመጣ አላውቅም ምክንየቱም ኢትዮጵያ ዉስጥ አንድ ዘር ስለሆንንየዘር ፍጅትሊከሰት አይችልም   ኤል ኤፍ  ትግሬዎች ናቸው፤ ትግሬዎች ማንን ነዉዲፖርት/Deport” ሚያደርጉት? ማንን ነዉ ገፍተዉ የሚያስወጡት ( “ጠርገዉ የሚያወጡት”) ከኢትዮጵያ ጠርገዉ ለማስወጣት የሚመክሩትን አማራውን ነው? ኦሮሞውን ነው? ቢሞክሩስ እንደዚያ ማድረግ ይቻላል ወይ? ምክንያቱምማጆሪቲ/Majority” “ማይኖሪቲዉን/Minority ማስለቀቅ አይችልም። እራሱ አባባሉቲኦሮቲካል ዊክነስ/Theoretical Weakness” አለዉ፣፣ ነገሮችን ለማጋነን ነዉ (እንደዚህ ዓይነት ቅስቀሳ ማካሄድ) ምክንያቱም በዓለም ውስጥ እንዲሰራጭ እና ጋዜጠኞችም ዜናዉን አግኝተው እንደፈለጉት ስለሚጠቀሙበት (ሆን ተብሎ የተሰራጨ ነዉ)። ብሎ ከጥቂት አመታት በፊት በመከራከሩ ፋሸስታዊ/ናዚያዊ እርምጃዎች በወየነ ትግራይ ስነ መንግሥታዊ አስተዳዳር መፈጸሙን እና ስርአቱ  ፋሺስታዊ መሆኑን እና ጫካም ሆነ መንግሥት ከሆነ በሗለ ፋሺስታዊ ተግባሮችን በተግባር መፈጸሙን እንደማስረጃ ካቀረብኩት ጽሑፍ የተወሰደ/ ተጨማሪ ምንጭ የወያኔ ገበና ማሕደር/ደራሲ ጌታቸው ረዳ)

ከዚህ በተጨማሪ ወዳጄ አቶ ግደይ ባሕሪ ሹም “አሞራው” በተባለው መጽሐፉ እንደተጠቀሰው ‘በፋሺስቶቹ የወያኔ መሪዎችና ካድሬዎቻቸው አንዲገደል የተበየነበት ሰው መቀበሪያው ጉድጓድ ቆፍሮ ካበቃ በሗላ፤ በጠፍር እጅ እግሩ ታስሮ ከነሕይወቱ ወደ ጉድጓዱ አንዲገባ ይደርግና በቁም ተልቶ በሕይወቱ እያለ በዱቅዱቃ (ትሎች) ተበልቶ አጥንቱን ፈረካክሰው በዓይኖቹና በጆሮዎቹ ትሎች ከወጡ በሗላ በስብሶ ሕይወቱ ሲያልፍ አፈር አልብሰው ይቀብሩት እንደነበረ ተገልጿል (ለምሳሌ ሃበተ ገብረተንሳይ፤ ተኽላይ ገብረመስቀል፤ ወይዘሮ ወርቂ ምንጭራ፤ ከተማ ሸራሮ  ውስጥ የወረዳው ራፖል ጸሓፊ የነበረ  የልዑል ራስ መንገሻ ሥዩም በጐን የተወለደ (ኢሕጋዊ) ወንድም የሆነው አቶ አታክልቲ ሥዩም  እና ሌሎች ይህ ፋሸስታዊ የግድያ ድርጊት ተፈጽሞባቸዋል)። 

በመጽሐፌ የተገለጹት ቃለ መጠይቅ ያደረግንላቸው አቶ ገዛኢ ረዳ ጀኔራል አበበ ተ/ሃይማኖት (ጆቢ/ዑስማን) ጫካ እያለ እሳት ከምሮ ለብልቦ እንዴት አንዳሰቃያቸው በቃለ መጠይቃቸው ያረጋገጡትን እና ለኔም በግል ያጫወቱኝን ይመልከቱ። እንዲህ የመሳሰሉ ግፎች ወያኔዎች ከነሙሰሎኒ እና ሂትለር ባሕሪያቶች ጋር ያመሳስላቸዋል።

 በግፍ አፈጻጸም ብቻ ሳይሆን ወያኔም ሆነ ሂትለር/ሙሶሎኒ በዘር የበላይነትና በድሮ “መሲያኒክ ግሎሪ” የሗላ ታሪካቸውን በመዘከር /ባለፈው የጉለበተኛና የበላይነት ማንነት ኩራትና ወታደራዊ ጀብዳቸው ለማስመለስ ቀዳሚ የትግላቸው መነሻ ማድረጋቸውን ያመሳስላቸዋል። 

እስረኞቻቸው በቢጫ ፤በቀይ ወዘተ የመሳሰሉ የመለያ ቀለሞች….በማሰሪያ መዝገባቸው/ወይንም በልብሳቸው ለጥፈው እንሚለይዋቸው ወያኔዎችም ይህ ስልት መጠቀማቸው በገብረመድህን ተገልጿል።

ስለሆነም ወያኔ የዘመናችን እና የጥንቱ/ጀነሪክ ፋሺስዝም/ የቀላቀለ ቡድን እንደሆነ፤ ካሁን በፊት የገልጽኩትን ነው ባጭሩ ዛሬም ደግሜ ልግልጽላችሁ እየሞከርኩ ያለሁኝ።

ሰሞኑን የወያኔ 40ኛው የፋሺስት ምስረታ የደደቢት ጉብኝት


These ethno nationalist Tigrayan singers who are worshipers of the Fascists showing their will and readiness to serve the propaganda mission.
ፖለቲካ ብስለት በጐደላቸው በምቾት የተንደላቀቁ የፋሺስት ስርዓት አድናቂ ከያኒያን እና በስቶክሆልም ሲንድሮም የታጨቀ የጀሌዎች ሰብስብስብ የተቸረው አድናቆት የታየው አሳፋሪ ትዕይንት፤ በፋሺሰት የፕሮፓጋንዳ አሰራጭ ክፍል ድረገጾቻቸው በኩል አይተነዋል። ጀሌ የኪነት ሰዎች እና “ታዋቂ” ብሎ ወያኔ የሚጠራቸው በስነ ልቦና ሊቃውንት  “ስቶክሆልም ሲንድሮም” ተብሎ በሚታወቀው የሕሊና መንጠቆ የተያዙ የሕሊና በሽተኞች ደደቢት በረሃ ላይ ሄደው ስለ ወያኔ  ምንነት የሰጧቸው ገለጻዎችን ሳዳምጥ በተጠቀሰው ሲንድሮም መሰቃየታቸው አስቀድሜ ስለተገነዘብኩ አላስገረመኝም።ይህ የሕሊና በሽታ በቅጡ ያልተረዱ አንዳንድ ወንድሞቼ ሲጽፉ ለምሳሌ ይህ የደረግ ወታደር የነበረ
 X-Derg era soldier "Serawit Fikre" a patient suffering from Stockholm Syndrome  saluting his captivators postured on the top of the tank he surrendered to his captivators years in 1991
በወያኔ ተማርኮ የነሱ አድናቂ ሆኖ ባስረከበው ታንክ ላይ ወጥቶ ወታደራዊ የሙርኮ ሰላምታ ሰጥቶ መነሳቱ የተመለከቱ “
የህወሃት በዓል; ሳሞራ፣ አባዱላ፣ ንዋይ ደበበና ሰራዊት ክፍል1”  ብለው በጻፉ አንድ ጻሐፊ ቃላት አጥተው አንዲህ ሲሉ ያሉትን ልጥቀስ። “የመጀመሪያው ይህ የሰራዊት ፍቅሬ ፎቶ ነው:: ይህ ሰው የደርግ ወታደር ነበር ብዬ ለማመን ሁላ ከብዶኛል:: የደርግ የሽሬ ሽንፈትን ሲጎበኝ የህወሃት ታንክ ላይ የተነሳው ነው የራሱን ሽንፈት ሰላምታ እየሰጠ ያንቆለጳጰሰ ወራዳ ወታደር በአለም ላይ አለ ብዬም አላምንም - See more at: http://www.zehabesha.com/amharic/archives/37615#sthash.kHrpPD5x.dpuf

እንዲህ ያለ ወራዳ ወታደር በዓለም ታይቶ አይታወቅም። ለመግለጽም ቃላት አጥቻለሁ።” ሲል ዘሐበሻ ድረገጽ ላይ  የጻፈውን ስትመለከቱ፤ ሰዎች “የስቶክሆልም ሲንድሮም” ክፉ ባሕሪ ያላነበቡ ሰዎች እንዲህ ያለ እርቃኑ ያሳየ አሳፋሪ ኢ-ወታደራዊ ድርጊት ለመግለጽ ስለሚቸግራቸው፤ ባህሪውን  በቃላት ለመግለጽ ይጠበባሉ፤ አቅል ያሳጣቸዋል፤ ባጭሩ “ቃላት አጥቻለሁ” በሚል ደምዳሜ ይገልጽዋቸዋል። ሰሎሞን ተካልኝንም (እዚህ ጨምሩት) ንዋይ ደበበ  

Patient of the Stockholm Syndrome singer Neway Debebe behaving exactly from what he is suffering praising his mental captivators in Tigray.
፤ እና የመሳሰሉ ከነሳሞራ እና አብዱላ ገመዳ በጭፈራ ላይ እየተቃቀፉ ማራኪዎቻቸውን በውዳሴ ዜማ እያሞገሱ ሲጨፍሩ የሚያሳየው ይህ የስቶክሆልም ሲንድሮም በሽታ የተሰቃዩ ግለሰቦች ባሕሪያዊ ትዕይንት መሆውን ሕዝቡ እንዲያውቀው/ በተለይ ወጣቱ እንዲህ ያሉ ግለሰቦች መነሻቸው ምን እንደሆነ ሊያውቁት አስፈላጊ ነው።

These individuals are Group of patients suffering from Stockholm Syndrome. They look and act normal, but mentally suffering with the mystery of loving an abuser. “Carefully” eximine their reaction, you will understand each faces reading mystery reaction.
ስቶክሆልም ሲንድሮም ካሁን በፊት በድረገጼ ላይ ገልጫለሁ። ባጭሩ እነሆ፦

      Stockholm syndrome (disambiguation).
Stockholm syndrome, or capture-bonding, is a psychological phenomenon in which hostages express empathy and sympathy and have positive feelings toward their captors, sometimes to the point of defending and identifying with the captors. These feelings are generally considered irrational in light of the danger or risk endured by the victims, who essentially mistake a lack of abuse from their captors for an act of kindness.[1][2] The FBI's Hostage Barricade Database System shows that roughly 8% of victims show evidence of Stockholm syndrome.[3]

Stockholm syndrome can be seen as a form of traumatic bonding, which does not necessarily require a hostage scenario, but which describes "strong emotional ties that develop between two persons where one person intermittently harasses, beats, threatens, abuses, or intimidates the other."[4] One commonly used hypothesis to explain the effect of Stockholm syndrome is based on Freudian theory. It suggests that the bonding is the individual's response to trauma in becoming a victim. Identifying with the aggressor is one way that the ego defends itself. When a victim believes the same values as the aggressor, they cease to be perceived as a threat.[5]

ባጭሩ ስቶክሆልም ሲንድሮም ማራኪውን፤ጠላፊውን፤ደብዳቢውን፤ ገዢውን/ጌታውን… “አዳኙና ተከላካዩ” አድርጎ በመውሰድ “በማራኪው በመደነቅ”  ለማራኪው ጥብቅና በመቆም “ለራሱ ሳይታወቀው” እያሰቃየው ያለው ውስጣዊ የእጅ ሰጪነት/የበታችነት ስሜቱን ለመዋጋት እኔም “ወያኔ” ነኝ በማለት ከአጥቂው ጋር በመወገን የስቃዩና የሽንፈቱ ማስታገሻ በማድረግ ለማራኪው በእጅ ሰጪነት ያድራል። (ስቶክሆልም ሲንድሮም የተባለበት ምክንያት ስዊድን/ስቶክሆልም ከተማ ውስጥ ታጣቂ ዘራፊዎች ባንክ ሲዘርፉ ሦስት የባንኩ ሰራተኛ ሴቶች ተጠልፈው ሲሄዱ ፤ ከጠላፊዎቹ ጋር “ሆስተጅ” ሆነው “ታግተው” ለሳምንት በቆዩበት ጊዜ  ልቦናቸው በመሰረቁ ጠላፊዎቻቸውን በማገዝ ከተፈቱ በሗላ ጥብቅና አቁመው ተከራክሮውላቸዋል። አንዳንዶቹም በትዳር ተጋብተው አንደነበር ታሪክ ያስረዳል፡” ከዚያ ወዲህ በሽታው “ስቶክሆልም ሲንድሮም” የሚል ስም በስነ ልቦና አዋቂዎች ተሰይሟል። ሰለሆም ወደ ደደቢት ወርደው የፈሺሰት ድርጊቶችን የተፈጸመበት መሬት ድረስ ሄደው ፋሺስቶችን ማወደሳቸው ከዚህ የልቦና ሲንድሮም/በሽታ የተነሳ መሆኑን አንባቢዎች አንድትረዱት እግረመንገዴን ለመግለጽ እወዳለሁ። 

በዛው በረሃ የተፈጸሙት ፋሺስታዊ ወንጀሎችን ግን ማራኪዎቻቸው ሊያሳይዋቸው ከቶ ሞራሉም ድፍረቱም የላቸውም። ዜጎች በረሃው ላይ ጉድጓድ ውስጥ ተቀብረው ሳይሞቱ የቆላ የመሬት ትሎች በጆሮአቸው እና በዓይናቸው ቀፎ ትሎቹ እየወጡ ዓይናቸው ሲፈርጥ የሚተርክ ፋሺስታዊ የወያኔ ወንጀላቸው ለስቶክ ሆልም ስብስቦቹ ሊነግሯቸው አይችሉም። ፋሺስቶች ፈሪዎች እና ውሸታሞች ናቸው እና ሞራላቸው አይፈቅድም።  
    
ከላይ የተገለጹት ፋሺስታዊ የወያኔ ባህሪያቶች እና መሰል ትስስሮች ሌላው ከነሂትለር ጋር የሚያመሳስላቸው አንደኛውና ማዕከላዊ ስራ “የፕሮፓጋንዳ”/የሕሊና ቡወዛ ስራቸው ነው።
 

 በሂትለር ሦስተኛው ሪፑብሊክ /Third Reich- Germany/ ዘመን ሥርዓቱ በፕሮፓጋንዳ የተዋጠ (ሞኖፖላይዝድ) ነበር። የጀርመኖች ሕይወት በፕሮፓጋንዳ የተጨናነቀ ሕይወት ነበር። ከሚመገቡት እኩል ፕሮፓጋንዳውንም አብሮ በቴሌቪዥን ይቀርባል። ወያኔዎቹ ልክ አንደ ናዚዎቹ (ጸረ አይሁድነት) ከፖለቲካው እስከ ትምህርት ቤት (ሥልጠና..) እስከ ምጣኔ ሀብቱ እና ወታደራዊ ዘርፎች የሚሰጡ ትምሕርቶች “ያለፉት አማራ ሥርአቶች/ነፍጠኖች/ጸረ ብሔር/ብሔረሰቦች/ሕዝቦችን….” መብት በመጋፋት፤ ያለፈውን የትግራይ ወርቃማ ዘመን ነጥቀው፤ ከዚያም አልፈው የትግራይን ሕዝብ ወንድነት፤ጀግንንነት ታሪክ ሰሪነት አማራዎች የራሳቸው አስመስለው በመለፈፍ “ዩተነጠቅነውን ወርቃማ የትግራይ ዘመን” ተመልሰን ማምጣት አለብን በማለት ሃያልነታቸውን እንደ ናዚዎቹ እና ጣሊያኖቹ ደጋግመው ያነሳሉ። ወያኔዎች ያለፈው የአክሱም ዘመነ መንግሥት ሃያልነት የትግሬዎች ብቻ አድርገው በመመልከት የራሳቸው ብቸኛ ምልክትና “ግሎሪ” (ወርቃማ ዘመን) የሃውልት ምልክት ማህተማቸው ላይ በማድረግ፤ ሕዝቡን ቀስቅሰውበታል። ዛሬም ወያኔ በተመሰረተበት ወርሃ የካቲት (ወያኔ የካቲት 11- ዴምህት የካቲት 19) የተመሰረተው ዴምሕትም (TPDM) የወያኔዎቹን አርአያ በመከተል ያለፈውን የትግራይ “ወርቃማ ዘመንና፤ የትግሬ ሃያልነትን” በመዘከር ታጋዩን እና ሕዝቡን ወደ ራሱ ለመሳብ የሚጠቀምብት እምሮአዊ ስልት እና ባሕሪ ያው የአክሱም ሃውልት በመዘከር ነው።
ይህም ኤርትራ ምድር ውስጥ ሰው ሰራሽ ሃውልት በመትከል በዙርያው ሲጨፍሩ የሚያሳይ ፎቶግራፍ የምለውን እንዲያምኑኝ እነሆ ፎቶግራፉን  ይመልከቱ። ምንጭ  (PDM TV SPECIAL PROGRAM 13th Anniversary day founding of TPDM in Feb 19 2006 E C PART 1) ቪዲዮውኑን ለመመልክት የሰጠሁትን ምንጭ ዩ ቱብ ላይ ይጻፉ። 

 glorious past with contemporary events. Archaism--making reference to the distant past--suggests that history is not linear but rather a cycle of rebirth and regeneration, making a return to the values of a golden age possible.  በሚል መርሕ በመቀስቀስ የጀርምን/የጣሊያን ናዚዎችና የወያነ ትግራይ ፋሺስቶች በውጭም ሆነ ባገር ውስጥ የትግራይን ሕዝብ በማጃጃል ክፍተት አግኝቷል።


በዚህ የስሜት ስልት በሕዝቡ እአምሮ አንዲቀረጽ ደጋግመው በመጐንጐን ኢትዮጵያን የመሰረታችሁ ቀደምት ጥበበኞች እና ጀግኖች ዛሬ ወድቃችሗ ል፤ በማለት የሕዝቡን ቀልብ ለመስለብ ወያኔም ሆነ የናዚ ሥርዓቶች ተመሳሳይ ቅስቀሳ አድርገዋል። “great and glorious Tigray” (ዓባይን ግንንቲን ወርቃዊት ትግራይ) “ታላቁ እና ገናናው ወርቃማው የትግሬ ዘመን” (‘ወርቃዊት ደደቢት’) የሚሉ ዘፈኖች እና መፈክሮች በወያኔዎች ብቻ ሳይሆን በአውሮፓም እንዲህ ያሉ ተመሳሳይ መፈክሮች ተከስቷል። 

በጦርነት ለመካፈል ፍላጎት ያላሳዩ ዜጎችን ለመሰብ የቻይናው ማኦ ዜዶንግም ተጠቅሞበታል። ባጭሩ ወያኔዎች ልክ እንደ ናዚዎቹ፤

 (1)ብሔር ብሐረሰብ፤ሕዝቦችን በጐሳ (ዘር/ነገድ) አስተዳዳር ቀይሶ የዘር መታወቂያ/ነገድ/ጎሳ በማዘጋጀት (Blut and Boden was one of the Nazi ideologies, which focused on race/ethnicity)
 
(2) ገዳዮች እና አፋኞች በሕዝብ አንዳይተወቁ “ሰላማዊ ልብስ” በማስለበስ በምስጢር ነብሰገዳዮችን በማሰማራት ተቃዋሚዎቹን ማጥፋት፤ 

(3) የስለላ መረቦችን በየተቋማቱ በማሰማራት ሕዝቡን መቆጣጠር 

(4) ወያኔያዊ የጎሳ “አይዲኦሎጂ” በሕዝቡ ከዚያም አልፎ በጐረቤት አገሮች አንዲስፋፉ ማድረግ፤ ከናዚዎች ባሕሪ አንድ ያደርገዋል። የስብሓትም ሆነ የመለስ ዜናዊ ነግግር ልብ ይለዋል። “መስመራችን ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ለአፍሪቃም ጭምር ተሻግሮ የሚሰራ ነው” (ስበሓት ነጋ ኢትዮጵያንስ ፎረም ፎር ፖለቲካል ሲቪሊቲ ፓል ቶክ)  

ይህንን የናዚ ባሕሪ ከወያኔ ጋር ለማስተያየት የሚከተለውን እንመልከት፤ “…the superior and inferior race. what Hitler phrased, “lebensraum” or living space, the idea that Germany needed to expand its empire, which meant they needed more space to live. This contributed to dislike for the Jews, because they needed to be pushed out in order to make room for more Aryan people so that Germany could once again be restored to its former glory. 

በዚህ ቅስቀሳ በተለይ ገናናውና ታላቁ የትግሬ ዘመነ መንግሥት (አክሱምን፤ ዮሐንስን) በአማራዎች ምክንያት ተኰላሸ የሚለው ቅስቀሳ ብዙ ትግሬዎችን አሰልፎአል። ሥልጣን ከያዘ በሗላም እናንተን አፍኖ ይዣችሁ የነበረው አማራ አስወግደንላችሗል እና “ደደቢት” መሽጎ እስከ አዲስ አበባ ድረስ ገስግሶ ሥልጣን የተቆጣጠረው “የወያነ ትግራይ ሱሪ እና ጀግነንት” ተመልከቱልን ሲል ጀሌዎቹን ሰብስቦ ደደቢት ድረስ ወስዶ “ወታደራዊ ጀብደኝነት” አንዲያደንቁለት ያደረገበት ምክንያት፤ በፖለቲካው በተለይም  እሱ “ዲሞክራሲ አመጣሁላችሁ” የሚለው ፏሽስታዊ/አፓርታይድ ሥርዓት ክፉኛ አንደከሸፈበት ያውቃል።ስለሆነም ለመጪው “ምርጫ” የሚለው ፋሺስታዊ ጨዋታው እንደ አጋዥ ፕሮፓጋንዳ አንዲሆነው ማጃጃያ አንደሆነ ፖለቲከኞች የምታውቁት ይመስለኛል። Fascism--and its propaganda--is anti-rationalist in its approach. Appeals to emotion, references to cultural myths, loyalty, the national spirit and its glorious past, all circumvent rational analysis in those who want to believe. It is a "cult of action and passion free of doctrinal rules" “ሰገናት” በሚል ስያሜ የሚጠራቸው ታዳጊ ህፃናት ለፏሺስታዊ ተልዕኮው ተረካቢ ትውልድ ስለሚያስፈልገው ናዚዎቹ ‘አይሁዶቹን” በጠላትንት እንደፈረጃቸው አማራውን በፀረ ትግሬነት ፈርጆ በሰገናት ሕሊና አማራውና የኢትዮጵያ ሰንደቃላማ በጠላትንት እንዲታይ በምትኩ ፋሺስታዊ የድርጅቱ ባንዴራ “ሰገናቱ፡ አንዲታጠቁትና እንዲያውቁት አድርጎ በቂ የፋሽታዊ ርዕዮተ ኩትኮታ አድርጓል።“Toadstool”

“ሰገናት”Young  kids indoctrinated to hate Amhara.
 in German is a children’s book released in 1938 by Julius Streicher.
Hitlerjugend
often abbreviated as HJ in German
The book was aimed at “educating” Aryan children about their “sub-human” Jewish counterparts. This was propaganda that preyed on the young, and encouraged German citizens, from a very young age, to develop a deep hatred for the Jews. 


የህ በኢትዮጵያ ምን ማለት ነው? ዘርዘር ላድረገው፦

 በኢትዮጵያ የመጀመሪያው አገር አቀፍ ብሔራዊ የሕዝብ ቆጠራ የተካሄደው 1976 .. ነበር። በወቅቱ ኤርትራን እና የአሰብ አስተዳደርን ጨምሮ ጠቅላላ የኢትዮጵያ ሕዝብ ብዛት 42,616,876 ያህል ነበር። በኤርትራ እና በአሰብ አስተዳደር ኗሪ የነበሩት ዜጎች ቁጥር ሲቀነስ በቀሪዋ ኢትዮጵያ ይኖር የነበረው ሕዝብ ብዛት 39,868,572 ይሆናል። በወቅቱ በሕዝብ ብዛት አንደኛ የነበረው የኦሮሞ ነገድ ብዛቱም 12,387,664 ሲሆን፤ እንዲሁም ዐማራ በሁለተኛ ደረጃ 12,055,250 ያህል ተወላጆች ነበሯቸው። ስለሆነም በወቅቱ በሁለቱ ነገዶች ተወላጆች ብዛት መካከል የነበረው የቁጥር ልዩነት 332,414 ይሆናል ማለት ነው። የመጀመሪያው የሕዝብ ቆጠራ ከተደረገ 23 ዓመታት በኋላ፣ ማለትም 1999 .. በተደረገው ሦሥተኛው የሕዝብ ቆጠራ ውጤት መሠረት ዐማራው ቁጥሩ በአዝጋሚ ሁኔታ ወደ 19,867,817 ሲጨምር የኦሮሞዎቹ ብዛት ግን ከእጥፍ በላይ አድጎ ወደ 25,488,344 ደርሷል። ስለዚህ በኦሮሞ እና ዐማራ ተወላጆች ብዛት መካከል ያለው የቁጥር ልዩነት 5,620,527 አሻቅቧል ማለት ነው። በዐማራው እና በኦሮሞው መካከል የነበረው የቁጥር ልዩነት ተመጣጣኝነት እንዳለ እንደተጠበቀ ይቀጥል ቢባል እንኳን 23 ዓመታት በኋላ ሊኖር የሚችለው ልዩነት 664,828 አይበልጥም። በመሆኑም 5ሚሊዮን የማያንሰውን ዐማራ ዬት እንዳደረሱት የሚያውቁት የትግሬ-ወያኔዎች እና ሎሌዎቻቸው ናቸው።

ባለፉት 23 ዓመታት 4,751,333 በላይ የዐማራ ነገድ ተወላጅ የጠፋው ወያኔ ገና የትጥቅ ትግል ሲጀምር የትግራይ ሕዝብ ደመኛ ጠላት ዐማራ ነው፤” “ዐማራን፣ የአማርኛ ቋንቋን እና የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖትን ማጥፋት አለብን!” ብለው የተሰለፉ በመሆናቸው የዐማራውን ነገድ ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ በመግደላቸው ነው። በግልፅ እንደሚታወቀው ወያኔ የዐማራውን ነገድ በሚከተሉት ሥልቶች አጥፍቷል…..” (5 ሚሊዮን የማያንሰው ዐማራ ዬት ደረሰ? – ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት ቅፅ ቁጥር ) በማለት ሞረሽ ወገኔ የአማራ ድርጅት ለሕዝብ ይፋ ያደረገውን ሰነድ ይመልከቱ።

German Expansion: “Blut and Boden” የትግሬ መልክአ መሬት መስፋፋት “ዝጠፍኤ መሬት፤ ዝጠፍኤ ክብርና፤ዝዓነወ ገዛ ምሕዳስ” አድላይን መሰረታዊ ናይ ሕዝብና ዋሕስ ስለዝኾነ ኩልና ምርብራብ ንጽባሕ ዘይባሃል ቃልሲ ሐድነት እዩ” (የጠፋና የተወሰደብን መሬቶች/ደምበሮችን ማስመለስ፤ክብራችን እና የፈረሰ ወና ቤቶቻችን መልስን ማነጽ የሕዝባችን ዋስትና እና የማንንታችን መገለጫዎች ስለሆኑ ለነገ በይደር ሳይያዝ፤ ሁላችንም እጅ ለጅ ተያይዘን ወደ የጋራው ግንባታ ዛሬውኑ እንግባ”) 

መጀመሪያ የጀርምን ናዚ ርዕዮት የመለክ አምድር መስፋፋት መርሆን እንምለክት፡ “Blut and Boden”. Blut and Boden literally means blood and soil, in German. “Bloden” went along with what Hitler phrased, “lebensraum” or living space, the idea that Germany needed to expand its empire, which meant they needed more space to live. This contributed to dislike for the Jews, because they needed to be pushed out in order to make room for more Aryan people so that Germany could once again be restored to its former glory. Blut”, was the distinction between the Ubermenschen and Untermenschen, the superior and inferior race. 

የወያኔ የትግሬ ድምበር/ግዛት መስፋፋት ፋሺስታዊ ናዚኢዝም ባህሪ የተገበራቸው ባህሪዎችን እንመለከት። የጀርምን ታሪክ አንደሚያመለክትው በ1929 (ባውሮጳ አቆጣጠር) የዓለም ምጣኔ ሃብት ተንኮታኰተ። ይህንን ተከትሎ ለበርካታ አመታት የጀርምን ኑሮ አስጊ ሁኔታ ደረሰ። 6 ሚሊዮን ሥራ ፈት ሆነ፤ 20 ሚሊዮን ሕዝብ በመንግሥት የምግብ ድጎማ (ፉድ ስታምፕ) ሥር ወደቀ። ይህ ሲከሰት ሂትለር ለዚያ ውድቀት የውጭ እና የውስጥ ሃይል ተጠያቂ ማድረግ ነበረበት።

ጀርመን የአሻጥረኞች/የአይሁዶች ኢላማ ሆናለች አለ።ትግሬም ለድህነቷ እና ለትግሬዎች ‘ግሎሪ’ ውድቀት/መነጠቅ “የአማራ ብሔር” ተጠያቂ ነው አለ። የወያኔው የሽምቅ ጦር ተዋጊ ዋናው አዛዥ የነበረው ዶ/ር አረጋዊ በርሄ አንዲህ ሲል ጽፏል።

 ''More over, since the people of Tigray had the dominant Amhara as their adversary, the media had mobilized the people and united the militant forces to deal an outward blow.'' 

(ይብልጥኑ፤ የትግራይ ሕዝብ በጨቋኝ ተቀናቃኝነት/በጠላትነት/ ያስቀመጠው አማራውን ነው። ይህን ለሕዝቡ ለማስረዳት የዜና ማዕከሎቹ ሕዝብን እና የሚሊሺያን አቀናጅቶ በማስተባባር “አማራ” ወደ ተባለው ውጪአዊ ጠላት እንዲያተኩር አደረገ።” (አረጋዊ በርሄ) ትርጉም ጌታቸው ረዳ    

ይህንን መስፋፋት እውን ለማድረግም መሬት ከወሎ እና ከጐንደር ወስዶ ወደ ትግራይ ጨመሯል። የትግራይ ምልክአ ምድርም ከነበረው እጅግ አድጓል።  ለምሳሌ “የትግራይ ነፃ አውጭ ድርጅት ተከዜን ተሻግሮ እስካሁን በሃይል የወሰዳቸው የጎንደር ወልቃይትና ፀገዴ ቦታወች ወልቃይት፣ ሰቲት ሁመራ፣ ቃፍታ ሁመራ፣ ፀለምት፡ እና ከፀገዴ ከነበሩት ጠቅላላ 39 ቀበሌወች ውስጥ 25ቱን ቀበሌወች ወደ ትግራይ ወስዶ አንድ ወረዳ የመሰረተ ሲሆን ወደ አማራ ክልል ከፀገዴ የቀረው 14 ቀበሌ ብቻ ነው አካባቢው በለምነቱ የታወቀና ድንግል መሬት ያለበት ሰፊ አካባቢ ሲሆን በብዛት የሚመረቱት የአዝርዕት አይነቶች ሰሊጥ፣ ጥጥ፣ ማሽላ፣ ሩዝ፣ ስኩኣር አገዳ፣ ፍራፍሬና አትክልት በስፋት ይመረታሉ።

በዚሁ በወልቃይት ፀገዴ አካባቢ የሚገኙና ወደ ትግራይ የተወሰዱ ትላልቅ ከተሞች ሁመራ ማይካድራ ማይፀብሬ ዳንሻ ማክሰኞ ገበያ /ንጉስ ከተማ/ ዲቪዥን የተባሉ ከተሞች ተወስደዋል። የትግራይ ነፃ አውጭ ድርጅት ይህንኑ የመስፋፋት ስስቱን በማጠናከር በአሁኑ ሰዓት አንገረብ ወንዝን በመጠቅለል የፀገዴ ቀሪ ቀበሌወችን እና የታች አርማጭሆ ለም መሬትን ለመውሰድ እየተዘጋጀ እንደሆነ ያካባቢው ጭብጦች ያስረዳሉ።ህወኃት ወያኔ በወልቃይት ፀገዴ ህዝብ ላይ ተጨማሪ የዘር ፍጅት ለማካሄድ እየተዘጋጀ ነውከሚል  November 24, 2014 ወልቃይት.ካም ድረገጽ የተገኘ።
 
በወሎ ክ/ሀገርም እንደዚሁ ሰፊ መሬት ወደ ትግራይ በማስገባት አማርኛ ተናጋሪው ሕብረተሰብ ከነልጆቻቸው በግድ በትግርኛ ቋንቋ አንዲዳኙ እና እንዲማሩ በማድረግ ናዚያዊ ትእብታቸውን በግልጽ አሳይተዋል። ወያኔ አደገኛ ፋሺሰት ብቻ ሳይሆን ቅጥረኛ እና ጸረ ኢትዮጵያ ቡድን በመሆኑ ኢትዮጵያዊያን የወያኔ ፋሺስት ቡድን ስብስብ ተክለሰውነት ግንዛቤ ምንንነት ካልገባቸው ‘ወያኔ’ በስቶክሆልም ሲንድሮም ስብስቦች መታጀብ መቀጠሉ ብቻ ሳይወሰን ‘ዲመክራሲ’ እያለ በሚያጃጅልበት የማጃጃያ ጨዋታው የወያኔ ፋሺስታዊ ባሕሪ ሳይገነዘቡ ተቃዋሚ የፖለቲካ መሪዎችም አብረው በምርጫ ዳንኪራ በመጨፈር ሕብረተሰቡ እንደ 97 ዓ/ም ምርጫ ለአመጽ እንዳይነሳ ሳይውቁት ለወያኔ የመከላከያ አጥር መሆናቸውንም መቀጠላቸው አይቀሬ ነው። በ97 ዓ/ም የተሰሙ መፈክሮች እና የህዝቡ አልገዛም አመጸኛ አንዲሁም ሰለማዊ ባሕሪ በክፍል ሁለት እንመለከታለን። አመሰግናለሁ። ጌታቸው ረዳ (Editor Ethiopian Semay) getachre@aol.com