Tuesday, April 20, 2021

ነጥሎ ማልቀስ እንቃወማለን በሚሉት በታማኝ በየነ እና በቴድሮስ ፀጋየ (ርዕዮት ሚዲያ) ያለኝ ተቃውሞ፡- ጌታቸው ረዳ ኢትዮ ሰማይ Ethio Semay 4/19/2021

 

ነጥሎ ማልቀስ እንቃወማለን በሚሉት በታማኝ በየነ እና በቴድሮስ ፀጋየ (ርዕዮት ሚዲያ) ያለኝ ተቃውሞ፡-

ጌታቸው ረዳ

ኢትዮ ሰማይ Ethio Semay

4/19/2021



ሁለቱም ማለትም ታማኝም ሀነ ጋዜጠኛና የሕግ ምሁሩ ቴድሮስ ፀጋየ ለኢትዮጵያ አገራቸው ያላቸው ፍቅር ወሰን የለውም። ይህንን እንደማውቅ እወቁልኝ። ይህን ካስረገጥኩኝ የሚከተሉዋቸው አንዳንድ መስመሮቻቸው ለይ ግን ቅሬታዎችና ልዩነቶች አሉኝ።

 

እነኚህ ሁለት ታላቅ ዜጎች እራሳቸው በነገሩን መሰረት በነገዳቸው ትግሬና አማራ ነገድ ናቸው። እነዚህ ወንድሞቼ የሚሉት “እየታየ ያለው ነጥሎ የማልቀስ ባሕሪ” ሁላችንም ከምንመራበት ኢትዮጵያዊ እና ሰብአዊ መርሆ (ፕሪንሲፕል) ውጭ ስለሆነ ባንድነት እንጩህ” ባይ ናቸው።

 

 ‘ነጥሎ ማልቀስ’ ስለሚሉት ወይንም ‘እየነጠላችሁ ለእገሌ እናልቅስ እያላችሁ ስለ እገሌ ግን አታለቅሱም’ የሚሉት አባባላቸው “በአማራ የዘር ማጽዳት እየተካሄደ ነውና ይቁም” ብለው ሰላማዊ ሰልፍ ለሚሰለፉት “አማራዎችን” ነው “በዋናነት” እንዲህ የሚሉት። በስሕተት ተርጉመኸዋል/ተረድተኸዋል ካላሉኝ በቀር “በአማራ የዘር ማጽዳት እየተካሄደ ነውና ይቁም” ብለው ሰላማዊ ሰልፍ ለሚሰለፉት “አማራዎችን” አጥብቀው “መንጋዎች” በማለት መጠሪያ ተሰጥቶአቸው(ታግ) ተደርገዋል። (ይህ አባባል “ታማኝን” ሳይሆን  በርዕዮት ሚዲያና በርዕዮት ሚዲያ ታድመው በሚመጡ አንዳንድ  ቋሚ ታዳሚዎች የሚሉትን ይመለከታል)

 

በግልጽ አማርኛ ሳስቀምጠው።  “አማራ” ብቻውን አይደለም የዘር ጽዳትና ጥቃት እየተካሄደበት ያለው’ የሚል ነው መልዕክታቸው። እዚህ ላይ የመጨረሻው መልዕክታቸው ሃቅ ቢሆንም፤ እኔ እያልኩ ያለሁት ደግሞ “አማራዎች አሁን የጀመሩት የብቻ እንቅስቃሴ ሕጋዊ አና ትከክለኛ ነው” እላለሁ።

 

መጀመሪያ የሁለቱም ታዋቂ ሰዎች ንግግር በቅንፍ ላስቀምጥ እና የኔን ሃሳብ አብራራለሁ፤

 

መጀመሪያ በቴድሮስ ፀጋየ (ርዕዮት ሚዲያ አዘጋጅ) ልጀምር፦ አንባቢዎች እንዲረዱልኝ የማሳስበው እኔም በነገዴ እንደ ቴድሮስ ፀጋየ “የትግሬ ነገድ” መሆኔን ለማታውቁ ላሳውቅና ልዩነታችንን ላብራራ””

 

እንዳልኩት ቴድሮስ ብዙዎቹ 99.9% ትንታኔዎቹ ይስማሙኛል። ግን በተጠቀሰው ርዕስ ላይ ልዩነት አለኝ።

 

ቴዲ እንዲህ ይላል፦

 

“እየመረጥን ኣናልቅስ” ይላል ቴዲ። “አሁን ኢትዮጵያ በ4 መአዝኖች በእሳት እንደተያያዘ ጎጆ ነው የምመለከታት፡ ማንም እየመጣ ክርቢት የሚለኩስባት፤……. የሰው ልጅ መጨፍጨፍ ፤ የሰው ደም መፍሰስ የሚያሳዝነን ከሆነ “እየመረጥን ኣናልቅስ” ሁኔታውን በመርህ ላይ ተመስርተን ልንቃወመው ይገባል።..” ይላል ቴዲ።

 

ይህ ሃቅ ነው። በመርህ ደረጃ ልክ ነው። ግን “ፕሪንሲፐል” (መርህ) 30 አመት ሙሉ ከዚያም በፊት ለአማራው አልፈየደለትም ወይንም ተግባራዊ አልሆነም። ትንሽ ላብራራ። አማራው ሲጠቃ የተቃጣበት ጥቃት እራሱን ከመከላከል ይልቅ ያውም እራሱ መቆም ሲችል “በአንድነት ስም” የጥብቅና መብቱን ለሌሎች ልቅሶ ቅድሚያ በመስጠት “ውክልናውን አሳልፎ” በመስጠት “የአማራ አድን ጥሪ” “በዲሞክራሲ እናምጣ ልቅሶ” ተተብትቦ የጥቃቱ ሰለባ እንዲብስ ተደርጓል።

 ያ ጠለፋ በረቀቀ ስልት በመከናወኑ ጭፍጨፋው ማስቆም አልተቻለም። ጥሬ ሃቁ ይህ ነው! አርሱ ስለ አገር አንድነት ሲጮህ ከስሩ እሳት ያነዱበት ነበር። ያንን ማየት አልቻለም።

 

አማራው “ፕሪንስፕል” በሚባሉት ዓለም አቀፋዊም ሆነ አገራዊ መርሆዎች በሁሉም እየገባ ሞክሮታል። መፍትሄ አልመጣም። ችግሩ ‘እራሱ በራሱ የጉዳይ “ጠበቃ” ሳይሆን የጠበቃዎቹ “ደምበኛ” ሆኖ ውክልናው አሳልፎ በመስጠት “ሞረሽ! ሞረሽ! አማራ አለህ ወይ!?” የሚል ጩኸት ሲሰተጋባለት “ጀሮ ዳባ ብሎ  የሻዕቢያን ባንዴራ በሙዚቃ አጅቦ “ይኼ ነው ባንዴራው” እያለ ጥቃቱ እራሱ ሲያፋጥን ቆይቷል። ሃቁ ይህ ነው። ይህ ጅልነት አገር ውስጥም ውጭ አገርም ታይቷል።

 

በዚህ ሁለት ወር ውስጥ ግን ከተጠለፈበት ከደምበኛነት ወጥቶ ወደ ራሱ ጥበቅና ተሸጋግሯል። በወኪል እና በእኛ እንጨሁልህ ጠበቃዎች መካካል የተፈጠረው አለመስመማት ሌላ አማራጭ መፍትሔ እንዲፈልጉ ስለተገደደ አሁን የታየው “አንድ አማራ ለመላ አማራ፤ መላ አማራ ለአንድ አማራ” ከመርሆ ያፈነገጠ ቢመስልም ስለ አማራ መጮህ ብቸኛ አማራጭ ይኸ ነው። አዝናለሁ፤ ግን አማራጭ የተባሉተት መንገዶች ሁሉ ሁሉ በሙከራ ወድቀዋል።

 

ስለ ትግሬው እልቂት ቴድሮስና እንግዶቹ በስፋት ተናግረዋል። አልቃወምም። ግን አማራ እንጂ ትግሬው ጯኺ አላጣም። ስላላጣም “በትግሬዎች እና ኦሮሞ ተሰላፊዎች መጠን የሚባል መለኪያ ካለ “ከመጠን በላይ” በትግሬዎች እየደረሰ ላለው ጥቃት ለመላው የዓለም የዜና ማሰራጫዎች እና የተባበሩት መንግሥታት ጀሮ ደርሶ ከአማራው የ30 አመት እልቂትና ጥቃት በበለጠ የትግሬዎች ልቅሶ ተደምጧል። ትግሬው ብዙ አፈቀላጤ አግኝቷል።

 

ትግሬው በአንድ ደምጽ ስለ ሕዝቡ ይጮሃል; ስለ አገር ግንጣላ ይጮሃል። አማራው ግን “በአንድ ድምጽና መርሆ ባለመጮኹ” ከትግሬዎች በላይ የተጨፈጨፈው አማራ “አልቃሽ” አላገኘም። ዛሬ ጉልበት ለመግንባት ሲጅመሩ ቅጽል ስም ሰጥቶ “ታግ” በማድረግ “መንጋ” ማለት ጭራሽ ነባራዊውን ሁኔታ አይገልጽም።

 

አንድ ድምጽ አንድ የተጠናከረ ጉልበት አማራው ሲገነባ ያኔ የመደራደር አቅሙ ከሌሎችጋር ይኖረዋል። ተበታትኖ “ቢጮህ’፡ግን ሰሚም ውጤትም አያመጣም! “እየተጠለፍክ ኑር” ማለት ልክ “ዝናቡ እየዘነበ” ሁሉም ወደ “መጠለያው ሲገባ”
አገር ለመጠበቅ “አማራው ደጅ ብቻውን ቆሞ” በዝናብ በስብሶ “ዛሬም” ከውሽንፍሩ ለመዳን “ወደ ቤቱ ሲገባ” “እዛው በስብሰህ ቁም” ማለት “የፕሪንሲፕል” ግጭት አለ።

 

አማራው አንድነት ፈጥሮ ሲጮህ ‘ወያኔ” ትግሬዎች ወደ ሰላማዊ ሰልፉና ወደ አማራ ሬስቶራንቶች በመምጣት ሲያውኩት ታይተዋል። ለምን? የሚል ጥያቄ ብትጠይቁ መልሱ “አማራው አንድ ሆኖ ከተባበረ ‘ለጥቃት አይመችም’። የወያኔ ትግሬዎች፤ ኦነጎች እንዲሁም የእነ ተስፋየ ገበረአብ ሻዕቢያዎች አማራን ማጥቃት መመመሪያቸው ስለሆነ፤ አማራው አንድ ሆኖ ከጮኸ ግን ነጣጥለው አይበሉትም፤ “ይጠቃሉ” እንጂ “አያጠቁትም”። የጅቦቹ ፍራቻ ይኼ ብቻ እና ብቻ ነው!

 

ቴዲን ለቀቅ ላድርገውና በዛው በቴዲ ሚዲያ የዘወትር ተወያይ የሆነው የሕግ ምሁሩ ክፍሉ ሁሴንም እንዲህ ይላል። እርሱም ስለ አገር ያለው ፍቅር እንደ እነ ቴዲ ነው። ግን የሚሰነዝራቸው ንግግሮቹ አይጥሙኝም። እንዲህ ይላል፦

 

“እዚህ ውጭ አገር ያሉት አማራ ሊሂቅ በሚያደርጉት “መዳራት” አገር ውስጥ ላለው ሚስኪኑ አማራ ለማለቅ እንዴት አስተዋጽኦ እንዳደረጉ (ግልጽ ነው)።” ይላል።

 

አቶ ክፍሉ እዚህ ውጭ አገር የሚኖር አማራ ሊሂቅ ከማን ጋር እየተዳራ እንደሆነ ግልጽ አላደረገውም። አማራን እየጨፈጨፈ ያለ አብይ አሕመድና ስርዓቱ እና እንዲሁም አሮሞ ነጻ አውጪ ብለው ራሳቸውን አገር ለመገንጥል በሚጠሩ የተለያዩ አክራሪ የኦሮሞ ድርጅቶች የጣምራ ሥራ ነው። እዚህ ውጭ አገር የሚኖሩ ሊሂቃን በስም አልገለጽልንም እንጂ ቢገልጽልን ኖሮ ከጨፍጨፊዎች ጋር የሚሰሩት ስራ ካለ መቃወም እንችል ነበር።

 

ቀጥሎ ክፉሉ ሑሴን እንዲህ ይላል፤

 

ውጭ ያለው ወጣት ሁሉም አይነት መረጃ የማግኘት ዕድል በሚገኝበት አገር እየኖረ …………ትግራይ ሕዝብ ላይ እየተደረገ ያለው ጭፍጨፋ በማያሻማ መረጃ፤ የተለያየ መረጃ ተመሳክሮ የቀረበለትን ሊክድ ይሞክራል። “ጀነሳድ” በቪዲዮ በምን ምን በማስረጃ እየታየም ቢሆን “አማራ አለቀ ተብሎ ገና አንድ ቪዲዮ ሲወጣ፤/ሲለቀቅ/ ግን” “አማራ ጀኖሳይድ፤ ልቅሶ!! ብካይ (እየየ) ነው!”

 

……በየሚዲያው ላይ” አመራ ጀኖሳይድ ተብሎ ለብቻ ይወጣል፤ ትግራይ ጀኖሳየድ ተብሎ ለብቻ ይወጣል። ፍሪ እስክንድር ነጋ ለብቻ ይጣል፤ ፍሪ ጃዋር መሓመድ ለብቻ ይጣል፤ ግን “ትራቬስቲ ኦፈ ጀስቲስ” የሚፈጽመው “ዘ ሴም ካንጋሮ ኮርት” ሲስተም ነው። ይሄን የሚያወግዝ የለም። መንጋው ይህን ሊነገረው ይገባል። ወጠቶቹ ክሪቲካል መሆን አለባቸው። አማራ ሲሆን ግን በቃ እየየ ልቅሶ ነው በቃ!”

ይላል ከፍሉ ሑሴን።

 

…………ትግራይ ሕዝብ ላይ እየተደረገ ያለው ጭፍጨፋ በማያሻማ መረጃ፤ የተለያየ መረጃ ተመሳክሮ የቀረበለትን ሊክድ ይሞክራል። “ጀነሳድ” በቪዲዮ በምን ምን በማስረጃ እየታየም ቢሆን “አማራ አለቀ ተብሎ ገና አንድ ቪዲዮ ሲወጣ፤ሲለቀቅ ግን” “አማራ ጀኖሳይድ፤ ልቅሶ!! ብካይ (እየየ) ነው!”

 

አሁንም ለቴዲ ከላይ ከሰጠሁት መልስ የተለየ አይደደለም። አማራው ለ30 አመት የራሱን ጀነሳይድ ጀሮ ዳባ ብሎ ስለ ትግሬው አገር (ኢትዮጵያ) ደህንነት ስለ ኦሮሞው ስለሶማሌው ስለ ጉራጌው ስለ ጋምቤላው ወዘተ, ፣ ወዘተ……. አገራዊ አንድነት ሲሰብክ ጥብቅና ሲቆም ቆይቷል። ይባስ ብሎ ስም ሰጥተውት “ደርግ፤ ነፍጠኛ፤ የትምክሕት ሃይል እያሉ ብዙዎቹ ትግሬዎችና ኦሮሞዎች ሲያንኳስሱት ኖሩ። አሁን ስለ እራሱ መከራ ለመጮህ ሲደራጅ “መንጋ”  “ከሃዲ” “ብካይ አስተጋቢ” እየየ ልቅሶ!! የሚል ቅጽል ስም መስጠቱ ምን የሚሉት ፕሪንሲፕል ነው?

 

በትግራይ ሕዝብ ላይ እየተደረገ ስላለው ጭፍጨፋ የሚጮህለት አልታጣም። “ኢትዮጵያ ታሸንፋለች” ሳይሆን “ትግራይ ታሸንፋለች” ጩኸት ብዙዎቹን እንዲርቁ አድርጓል። ሌላ ቀርቶ “የትግራይ ትዕወት” “ትግራይ ታሸንፋለች” መፈክር ፈካሪዎች የኢትዮ ሚዲያው ድረገጽ ባለቤት እነ “አብርሃ በላይም” ይህንኑ ጩኸት መሪ መፈክራቸው አድርገው በማስተጋባት ላይ ናቸው። ችግሩ በወያኔ ታሊባን ሙጃሃዲኖች እየተመራ ያለው የትግራይ ነፃ አውጪ ተዋጊ ቡድን እና በታሊባን ሙጃሃዲን አወዳሽ ተከታዮች የትግራይ ሕዝብ ነጻ ሊወጣ ይቻለዋል ወይ? ነው ጥያቄው። ይህ “ትግራይ ትዕወት” ቡድን የሚያምነውና የሚያራምደው መርህ “ውግያው በትግሬ እና በአማራ” መካከል ነው የሚሉ እንደ አብርሃ በላይ የመሳሰሉ ትግሬዎች ከአማራዎች ጋር ግምባር ፈጥሮ ውጭ አገር ሰላማዊ ሰልፍ ማድረግና ቆመው መወያየት ይቻላል ወይ?

 

ለዚህ ነው መሬት ላይ ያለው ሃቅ እናንተ “ፕሪንሲፕል” ከምትሉት “ፕሪንሲፕል” አብሮ አይሄድም የምለው። መሬት ላይ ያለው ሃቅ የኼ ነው። ሊሂቃን የነገድ አሸናፊነት ገመድ ጉተታ ገብተው “በትግራይ ታሸንፋለች” እና ውግያው “በትግሬዎች እና አማራዎች” ነው ብለው ራሳቸውን በነገድ ከተተበተቡ ትገሬዎች ጋር “የጋራ ጩኸት” ማድረግ አይቻልም። አማራው በዚህ መውቀስ ይቻል ይሆናል፤ ግን የ30/45 አመት “ፍራሰትሬሽንም” ደግሞ መረዳት ያስፈልጋል።

በ30 አመት4 አንዲት ቪዲዮ ተለቅቃለት ከሆነ ቢጮህ ችግሩ የት ላይ ነው? ለመሆኑ የ30 አመት ጭፍጨፋ ሰንት ቪዲዮ ተለቀቀለት? እንደ ጥቃቱ ብዛት ስንቶቹ ነበሩ ዜና ሰርተው እንደ አጣዳፊ ዜና አድርገው የሰሩበት? ስንቱስ “የዲሞክራሲ ታጋይና ጫሂ” ጆሮ ሰጠው?

 

 ወደ ታማኝ በየነ ልሂድ፡

 

ታማኝ ስለ አማራዎች በአመራነት ሳይሆን በኢትዮጵያዊነት ብቻ መደረጀት እንዳለባቸው ብዙ ጊዜ በብዙ መድረኮች አማራዎች ሲያነጋግር ተደምጧል። ለምሳሌ “በአማራ ስም የተደራጃችሁ የፖለቲካ ድርጅቶች፤ በኦሮሞ ስም የተደራጃችሁ ድርጅቶች፤ በሌላም፤በሌላም የተደራጃችሁ የፖለቲካ ድርጅቶች በእውነት ይኼን ሕዝብ የምትውዱት እና የምትደክሙለት ከሆነ ከራሳችሁ ኢጎ/Ego/ ዝቅ ብላችሁ መነጋገሪያ ሰዓቱ ዛሬ ነው!” የሚለው ንግግሩን ላስታውሳችሁ።

 

ታማኝ ይህንን ሲናገር ተሰብሳቢውም በተለመደው ስሜት ጭብጨባውና ፏጨቱ አስተጋብቷል።

 

ምክሩ ክፋት የለውም፡ አቃቂር አይወጣለትም። ችግሩ ግን ሁኔታውን እና ጊዜው ያላገናዘበ ምክር ነው። በወቅቱ ታማኝ ይህንን ካለ ወዲያ በማግስቱ ይህንን የሚከተለው ጽፌ ነበር።

 

“አማራና ኦሮሞ እንዲሁም ሌሎቹ የተደራጁበት ዓላማ አንድ አይደለም። አማራው የተደራጀው (ስለ ድርጅት ሳወራ የሞረሽ ወገኔን ነው፤ስለ ሌሎቹ አላውቅም።) ከሃያ አምስት አመት ሰቆቃና እንቅልፍ በሗላ የተደራጀ ድርጅት ነው። ሞረሽ ወገኔ ምስጋና ይድረሰውና፤ በክቡር አቶ ተክሌ የሻውና የድርጅቱ አባሎች ምክንያት ከውስጥ አገር ከሚገኙ የአማራ መገፋት ያስቆጣቸው ግለሰቦች ጋር ተገናኝተው ጥቃቱ “ይቁም” ብለው አማራን ከጨርሶ መጥፋት ለመታደግ የተነሱ እነዚህ ድርጅቶች አቶ ታማኝ “ኦሮሞ እና ሌሎች ድርጅቶች” ከሚላቸው እስከ መገንጠል ድረስ እና “የኮሎኒያል ጥያቄ” ከሚያነሱ ወደ “ራሳቸው ያተኮሩ” ሰልፍ ሰንተርድ/ “ኢጎዎች” ጋር “አማራን” ልክ እንደ ወያኔ ትግሬዎች በነፍጠኛነትና በትምክሕተኛነት ከሚዘልፉት ድርጅቶች ጋር ፈርጆ ፤ “ሰልፍ ሰንተርድ/ኢጐይስቲክ” መስመራችሁ ውጡ ማለት ምን ማለት ነው?” ብየ ጠይቄው ነበር።

 

በወቅቱ ጋምቤላ ውስጥ ሰው የመሰሉ የጉሙዝ አራዊቶች አማራዎችን ገድለው ሥጋቸው በልተዋቸው በነበረበት አስጨናቂ ወቅት ነበር። ወቅቱ ኦሮሞዎች ሊያለቅሱለት ቀርቶ አማራ በገዛ ልጆቹ የተከዳ ማሕበረሰብ የነበረበት ወቅት ነው። ስለዚህ ጥቂቶች አማራዎች ይህንን ግፍ “ይብቃ” ብለው በመነሳታቸው ታማኝ በወቅቱ “ከራሳችሁ ኢጎ/Ego/ ዝቅ ብላችሁ መነጋገሪያ ሰዓቱ ዛሬ ነው!” ብሎ ማለቱ መሬት ጋር ካለው እውነታ የማያገናዝብ ነው። ዛሬም ይህንን እውነታ እንዳለ ነው።

 

ለመሆኑ ኦሮሞዎቹ እና አማራዎቹ ሲነጻጸሩ በራሱ ማሕበረሰብ ላይ ያተኮረ ሊሂቅም ሆነ ማሕበረስብ እንደ ማህበረስብ ማን ነው ተብሎ ለምርምር ቢቀርብ መልሱ አማራዎች ወይንስ ኦሮሞዎች? መልሱ እራሳችሁ አታጡትም ብየ አምናለሁ።

 

ኦሮሞዎች ለ27 አመት (አሁን 3 የአብይ አሕመድ ኦሮሙማ ሥርዓት ጨምሩበት ኦሮሞ “ክልል” ውስጥ ጎረቤት ጎረቤቶቻቸውን ሲገድሉ የታየበት ዘመን ተጠቂዎች የሰጡትን የቅርብ ሳምንታት ምስክርነታቸውን አትርሱ) ውጭ አገር ያሉትም ሆኑ አገር ውስጥ ያሉ ኦሮሞዎች ኢትዮጵያዊነትን እና ኢትዮጵያ ከልባቸው አውጥተው የራሳቸው ምናባዊ ኦሮሚያ የሚባል አገርና የላቲን ፊደል እንዲሁም ሦስት ዓይነት የመለያ ባንዴራ ይዘው፤ ጭራሽ ልጆቻቸው አማርኛ እንዳይናገሩ ተደርጎ ካለው ማሕበረሰብ እና ‘ዝንተ ዓለሙን’  “ኢትዮጵያ” ወይንም “ሞት” እያለ እስካሁንዋ ደቂቃ ድረስ አንገቱን “በጽንፈኛ ዋሃቢስት ኦሮሞዎች” እና “የኦሮሙማ ነፃ አውጪ ነብሰገዳዮች” የቀን ተቀን “ሐዘንተኞች” ሆነው የሚጮሁ አማራዎችን “በሰልፍ ሰንተርድ” መውቀስ አይገባም። ብዙዎቹ አማራዎች በዚህ በኢኮቲስቲክ የሚወቀሱ አይደሉም።

 

ታማኝ ዛሬ ምን እየሰራ ነው?

 

መጀመሪያ በወያኔ መውደቂያ መቃረቢያ ጊዜ የተናገረውን ንግግሩን ልጥቀስ፡

እንዲህ ይላል፤-

“አንድ ነገር አለ! በአሁኑ ሰአት በሃገራችን እየሆነ ያለው ነገር በጣም የሚያስፈራ ነው፡፡በተደጋጋሚ እገሌ ከዚህ ክልል፤እገሌ ከዚህ ክልል ውጣ እየተባለ ሕዝብና ሕዝብ እየተቀያየመ እንዲሄድ እየተደረገ ነው፡፡ ይህ ደግሞ በጣም ያስፈራል፡፡…..የህክምና ባለሙያ ባልሆንም አንድ ዶክተር ወደ ካንሰር ሊለወጥ የሚችል በጣም ከባድ የጤና ችግር ያለበትን በሽተኛ በአግባቡ መርምሮ ዘለቄታዊ መፍትሄ ይፈልግለታል እንጂ ህመም አስታጋሽ (ፔይን ኪለር) የሚሰጠው አይመስለኝም፡፡ የሃገራችን ወቅታዊ ጉዳይም ከዚህ ጋር ተመሳሳይ ነው። ዛሬ አንድ ዘላቂ መፍትሄ ነገር ካላደረግን ችግሩ ሊድን ወደማይችል ካንሰርነት መለወጡ አይቀርም።በማለት ታማኝ ሕዝቡን እና መንግሥትን ያሰጠነቀቀበትን አስታውሳለሁ።

 

 ሃቁ ግን ከታማኝ የተለየ ነው፡ ዛሬ!!!! የተወለድንባት ምድር ኢትዮጵያ በታሪኳ ውስጥ ታይቶ ተስምቶ በማይታወቅ ብሔራዊ ሐዘን ውስጥ ተወጥራ በምትገኝበት በዚህ አብይ አሕመድ በሚያስተዳድራት አገራችን በየቦታው ባሰማራቸው ተባባሪየሰው ጅቦችበአማራው ላይ የዘር ማጽዳት/በጀነሳይድ ጥቃት ከመቸውም በተጠናከረ በስፋት በከፍተኛ ሂደት እየተስፋፋና እየተፈጸመ ነው። አሁን ታማኝ በየነ ምን እየሰራ ነው? ሥራው አብይ አሕመድ ሕዝብ እየፈናቀለ ሲቀጥል ታማኝ ደግሞ እየለመነ ተፈናቃዮችን መመገብና ማልበስ አዲስ ትግል አድርጎ እያየንለት ነው። ይህ ሥራ ካሁን በፊት መፍትሄ አስመጪ እንዳልሆነ የተናገረውን ዛሬ እራሱ ደግሞታል።

እርሱ

 አንድ ዶክተር ወደ ካንሰር ሊለወጥ የሚችል በጣም ከባድ የጤና ችግር ያለበትን በሽተኛ በአግባቡ መርምሮ ዘለቄታዊ መፍትሄ ይፈልግለታል እንጂ ህመም አስታጋሽ (ፔይን ኪለር) የሚሰጠው አይመስለኝም፡፡” ያለውን አሁን ከሚሰራው የተፈናቀሉትን ለመፈናቀላቸው መርምሮ ዘለቄታ መፍትሄ ከመፈለግ ይልቅ “ስንዴና ማሽላና አስፕሪን” ይዞ መሮጥ ዘለቄታ መፍትሄ የሚያመጣ ነው ወይ?

 

አማራው ሲት ፕያ የሚል አስፕሪን ሰጡት ፤ ዋጠው፡ ግን አላሻለውም። አማራው ስለ ኢትዮጵያ ስንት አመት ያልቅስ? 30 አመት አለቀሰ ፤ ግን ተጨፈጨፈ። ኢትዮጵያ ብሎም አላለምም “ሞቱ አልቀረለትም” ። አንዴ በጠላት ተፈርጆ እንዲገደል ተበይኖበታል። አማራዎች የሌሉበት ድርጅት የለም። ግን የአማራን ሞት ሊያቆሙት አልቻሉም። ስለ አማራም ሊጮሁለከት አልፈለጉም።  እራሱን ለመከላከል አማራ ብሎ ሰላማዊ ሰልፍ የወጣ ጥቂት አማራም “እየለዩ ማልቀስ” የሚል ስም ተለጥኦቸዋል ወይንም “ጠባቦች” ተብለው ወይንም “ሰልፍ ሰንተርድ” ተብለው ተፈርጇል። የአማራው መገደል ለብዙ ኢትዮጵያዊያኖች ስሜታቸውን ኮርኩሮት ደምፅ ሊሆኑለት አልቻለም። ጥቂቶች ወጥተው ስለ አማራ ስለጮኹ “ታግ/መለያ’ ሊለጠፍባቸው አይገባም። አማራዎች ስለ ትግሬዎች፤ ስለ ኦሮሞዎች፤ስለ ኢትዮጵያ አንድነት ለ30 አመታት ጮኹ፤ አማራ ከመገደል ከመፈናቀል ግን አልቆመም።ታዲያ መፍትሄው ምንድ ነው?  ከእነ ማንስ? የት እና ምን እያለስ ይጩሁ?

ጨርሻለሁ።

ሕዝብ እንዲመለከተው ልቅሶአችሁ እንዲደመጥ ሼር አድርጉ።

ጌታቸው ረዳ

Ethio Semay