ካለፈው የቀጠለ ክፍል -2 -የአብይ አሕመድ የአእምሮ መቃወስ
ከጌታቸው
ረዳ
ETHIO
SEMAY
1/29/2022
ዛሬ በ “ቲ ኤች ኤም” ዩ ቱብ ዜና መድረክ ሳደምጥ አመስግኜው የማላውቀውን
የፕሮግራሙ አዘጋጅ “ስታሊን” ን አመሰገንኩት። ከዚህ ቀጥሎ የምጠቅሰው ረስቻቸው ከነበሩት የኣኢምሮ በሽተኛው የአብይ አሕመድ ንግግር
“ስታሊን በሚገርም ቅንብር አዘጋጅቶ አስደምጦናል”።
ንግግሩ በቪዲዮው የምታዩት ሲሆን ስለ የአእምሮ በሽተኛው “አብይ አሕመድ” መጽሐፍ ለምትጽፉ ደራሲያን እና የአእምሮና የሕሊና ተመራማሪዎች ለጥናት እንዲመቻችሁ በጽሑፍ ዘግቤ አቅርቤላችኋለሁ።
(-1-)-ኢትዮጵያዊያን ለመጓጓዣ “መኪና” መጠቀም እንደሌለባቸው እና
ሓጢያት መሆኑን
(-2-)- ሌላው ደግሞ ስለ ህዳሴ ግድብ አስመልክቶ የዓባይን ውሃም ሆነ
ሌሎች የወንዝ ፈለጎች ውሃውን ገድበን “ዕርሻ እና ለኤነርጂ” ማዋል የፈጣሪ ቁጣ ስለሚያስከትል መጠቀም እንደሌለብን ይመክራል።
የበሽተኛው ንግግር ቃል በቃል ይኸየው እንዲህ ይላል።
“እያንዳንዳችን እንድንሄድበት እንሮጥበት ዘንድ እግር ተሰጥቶን ስያበቃ እግራችንን መጠቀም ትተን መኪና መጠቀም ፈጣሪ ጋር እምያጣላ ነገር ነው። የተሰጠን እግር እያለ ለምን መኪና መጠቀም ተገድደን ብለን መጠየቅ ያስፈልጋል።” (አብይ አሕመድ- የቪዲዮ ጽሑፍ ኢትዮ- ሰማይ)።
“ውሃም እራሱ ህዳሴ ግድብን ጨምሮ መገደብ ስሕተት ነው የሚሆነው። ምክንያቱም ውሃው “ኮርሱን ጠብቆ” እንዳይሄድ በየመሃሉ እያቆሙ ከዋናው ከተፈጥሮው መንገድ እያወጡ ለእርሻ ማዋል ለኤነርጂ ማዋል ከተፈጥሮ ጋር መጋጨት ነው።”
ይህ ንግግር አንባቢዎች እንድተነትን አይጠበቅብኝም። ምክንያቱም ግልጽ ነው። የሰው ልጅ በእግሩ መሄድ አለበት እያለ እራሱ ግን በመኪና ይሄዳል። የሰው ልጅ መኪና የሚባል መጓጓዣ መጠቀም የለበትን ሌላ ቀርቶ በቅሎም ፈረስም አያስፈልግም ይላል። በእግር ብቻ መጓዝ አለባችሁ እያላችሁ ነው። ጤነኛ ሰው እንዲህ ይላል? እንዲህ የሚል ሰው በዚህ ዘመን እእምሮው የቀወሰ ሰው ብቻ ነው። መኪና መጠቀም ያበረታቱን አጼ ምኒሊክ ሲሆኑ፤ በዚህ ዘመን የተወለደው በአእምሮ ቀውስ እየተሰቃየ ያለው የጂማው በሻሻ ዕብድ ደግሞ በእግር ሂዱ እያለን ነው።
የሚገርም በሽታው ደግሞ “የህዳሴ ግድብም ሆነ ማንኛውም የወንዝና የሃይቅ ፈለጎች” ጠልፈን ለእርሻም ሆነ ለመብራትና ለኢንዳስትርያል አግልግሎቶች ማዋል አይገባም። ሓጢያት ነው ፤ፈጠሪ ጋር ያጣላናል እያለ በፕሮተስታንት ፓስተርነቱ የቀወሰው ሕሊናው ድንገር አገር የመምራት ሎተሪ ሲደርሰው “ዕብድነቱን” መሸሸግ አልቻለም። ይኼው ኢትዮጵያ በአንድ የቀወሰ ሰው ጉድ ውስጥ ገብታለች። ሓኪሞች የለታላችሁ!?
እናንተን እንኳ አልወቅሥም፤ ምክንያቱም ተመርቃችሁ ሥራ እንዳታገኙ በረንዳ
ላይ እንድትተኙ እያደረጋችሁ ስለሆነ (ትናንት የለጠፍኩት የአንድ ዶክተር አሳዛኝ ቃለ መጠይቅ ለጥፌዋለሁ ያንን ተመልከቱ)። ስለዚህ
ሓኪሞችን አምርሮ የሚጠላበት እና የሚሰድባችሁ ምክንያት በዚህ በሽታው እንደሆነ ጥርጥር የለውም።
ለማንኛው የውጭ አገር ሐኪሞች እባካችሁ ይንን ቀውስ ወደ ጀኔቫ አስራችሁ
አሳክሙልን። ወይ ኢትዮጵያ አገሬ ምን ጉድ ውስጥ ገባሽ?!
ጽሑፍን ተቀባበሉት
አመሰግናለሁ
ጌታቸው ረዳ