መልስ ለዩኒቨርሲቲዋ መምህርት እና
ሃያሲት ወ/ሮ መስከረም አበራ
ከጌታቸው ረዳ (ኢትዮ ሰማይ)
“ጠ/ሚ አብይ ከጋዜጠኛ መዓዛ ብሩ ጋር ያደረጉትን ቃለ-ምልልስ – መስከረም አበራ
September 17, 2019) በሚል ጽሑፍ የጻፍሺውን ሳተናው በሚባል ድረገጽ አንብቤው በሰጠሺው አስተያየት አልተደሰትኩም።
አንዳንዶቹን ባጭሩ ይኼው፡
አብይን የምትወጂለትን ሰዋዊነት
እንዲህ ትገልጪዋለሽ፦
“ከጠ/ሚው ተፈጥሮ የምወድላቸው ለህዝብ ቀረብ የማለት ሰዋዊነት” ብለሻል
ወ/ሮ መሰረት ይህ የፋሺሰት ድርጅቶች ሁሉ ሊቀመንበር የሆነ መሪ “እስር ቤት ውስጥ በሐዘን ላይ ያለችውን ነብሰጡር የሚያሰቃይ ጨካኝ ሰው “መደብ ላይ እየተኛሁ፣ኩራዝ የሚበራበት ቤት ውስጥ ያደግኩ ነኝ” ስላለ አንቺ ለህዝብ ቀረብ ያለ ሰዋዊነት” ብለሽ እንዴት እንዲህ ያለ ትልቅ ሽልማት ለማሞገስ በቃሽ? ያውም ከወራት በፊት ነብሰጡር የሚያሰቃይ ጨካኝ እያልሽ የከሰስሺውን ሰው በሚደሰኩሮው አጭበርባሪ ቃላት እና ቃለ መጠይቅ እንዴት ተሎ ተሸወደሽ “ሰዋዊ” አልሽው?!!!
እንዲህም ብለሻል፦
“ለጠያቂ ጋዜጠኛም ምቾት መስጠቱ አይቀርም፡፡”መደብ ላይ እየተኛሁ፣ኩራዝ የሚበራበት ቤት ውስጥ ያደግኩ ነኝ” ሲሉ አድማጭ ከእኛ እንደ አንዱ እንጅ ከሰማይ ዱብ ብለው ዙፋን ላይ ያረፉ አለመሆናውን ይረዳል፤ይህ አይነቱ ሰው ሰው የሚል ነገር ከመሪ አንደበት ሲወጣ አንዳች ህዝብን እና መሪን የሚያቀራርብ መስህብ አለው፡፡” ስትይ በሚገርም ሁኔታ ራስሺን አታልለሻል።
ወ/ሮ መሰረት! ኢትዮጵያውያን እንኳን ”መደብ ላይ እየተኛሁ፣ኩራዝ የሚበራበት ቤት ውስጥ ያደግኩ ነኝ” የሚል “መስህብ” (የምትይው) ቀርቶ “ኢትዮጵያ” የሚል ቃል “እግዚአብሔር” የሚል ቃል የሚናገር ሁሉ እግሩ ላይ የሚነጠፍ ተላላ ሕዝብ መሆኑን እንዴት አጥተሺው ነው አሁን ይህንን ማጭበርበሪያ ቃላት እንደ ቁም ነገር ቆጥረሽ ሕዝብ እና መሪ ያሚያቀራርብ መስሕብ ብለሽ ገለጽሺው? ወያኔዎች ከገበሬው ጋር ምን መስለው ይኖሩ አንደነበር እነ መለስ ዜናዊ ሲገልጹት የነበረውን የጫካ አኗኗር ከአብይ የመደብ እና የኩራዝ ኑሮ ለኢትዮጵያውያን የመስህቡ ልዩነት ጨዋታ ምን ልዩነት አለው ብለሽ ነው? ነገሩ ያለው ስራ ላይ የሚታየው እንጂ መደብ ስተኛ ነበር ስላለ የሚከተለው ፋሺሰታዊ ርዕዮት እና የሥራ አፈጻጸም ጋር ሲነጻጸር ከሕዝብ ጋር የሚያቀራርበው አንዳችም ነገር አይኖርም። ለምሳሌ “መደብ ላይ እየተኙ” ጅማ ላይ ያደጉት ኮለኔል መንግሥቱስ አለሉሽ አይደል? ራሳቸው የገለጹትን አታስታውሺም? ግን ያ መደብ ሥራ ላይ ሲተረጎም ምን አስከተለ?
ቀጥለሺም፦
“በዚህ ረገድ ከአብይ አለፍ ብሎ ኦህዴድ ላይ ትኩረት ማድረጉ ደግ እንደሆነ አውቃለሁና ጠ/ሚውን በግል ልከሳቸው አልሻም፡፡” ብለሻል።
ይህ ሰው ኦሕዴድ የተባለ የኣማራን ሕዝብ ዘር በማጥፋት ተጠያቂ የሆነን ድርጅት መሪ ከሆነ መሪው ድርጅቱን ካልተቆጣጠረ ኦሕዴድ በራሱ የሚዋልል መልሕቅ የሌለው “ፋሉል” (አናርኪ/ሥርዓተ አልባ) ድርጅት ነውና ትኩረት የሚደረገው በመሪው እንጂ በጭፍረቹ ላይ ማትኮር በምን ዘዴ ነው የምትለውጪው። አንድ የድርጅት መሪ አባሎቹ የሚያደርጉት ሥራ ካልተቆጣጠረ መሪ ሊሆን አይችልም። (ያውም ድርጅቱ ያለ
እርሱ እውቅና ድርጅታ መግለጫዎች ሊወጡ አይችሉም። የአብይ ድረርጅት ያሰራጫቸው የድርጅቱ መግለጫዎች “ኦሮሞ ኬኛ ጀምሮ እስከ….
የሕዝብ ስብጥር ኦሮማዊ ማድረግ እስከ… የባንክ ዘረፋ (ከማል ገልቹን ምስክርነት የአሕዴድ አጅ እንዳለበት የነገረንን አብይ በዚህ
ምንም ትንፍሽ ያለማለቱን ልብ ይለዋል).እስከ….ሁሉ.. የአብይ አውቅና የለበትም አንልም (አንቺ ብትየም/ቢዳዳሽም) ነገሩ ያለው ድርጅቱ የሚከተለው ርዕዮት እንጂ ጭፍሮቹ ከኪሳቸው ያወጡት አሰራር አይደልም። ድርጅቱ ፋሺሰት ነው እና ፋሺዝምነ ለመለወጥ መታገል ብትይ ይሻላል። ያም ካልሆነ ትኩረቱ ደግሞ በመሪው ላይ ነው መደረግ ያለበት።
የሚገርመው ደግሞ ያ የአንዳርጋቸው ጽጌን የማቆለጰጰሱን ባህሪሽን በአብይ ላይ ተመልሶ ሲያገሽቢሽ አንዲህ ብለሻል
“እንዲህ የሚል ጠ/ሚ በማግኘታችንም ደስተኛ ነኝ።”
አንቺ ሁሉም ያስድስትሻል። አንዳርጋቸውም ያስደስትሻል። ስትገለባበጪ መክረምሽ ነው። እባክሽ አንዳርጋቸውን የሚያክል አደገኛ ጸረ አማራ፤ ባንዳ “ዋሾ!!!!” ሰው አትካቢብን ብለን ብዙ ስንጮህብሽ አንዲት ካንቺ የባሰች “እየሩሳሌም ተስፋው” የተባለች ወጣት አንዳርጋቸው ጫማ ስር እየተደፋች ስታስቸግር የነበረች የግንቦት 7 አባል ሴት ጋር አብራችሁ አንዳርጋቸውን ስታቆለጳጵሱት ከርመሽ አሁን ያንን መስመርሺን ትንሽ ወጣ ብለሽ አብይን የመሰለ ስርዓተ አልባው፤ጨካኝ፤ አታላይና “ትልቁ ዋሾ” (ይግራኝ አሕመድ ታናሽ) ስትቀወሚው ደስ ብሎን ነበር፤ ዛሬ ደግሞ ባጭበርባሪ ቃላት አብይ ደለለሽ እና ፋሺሰታዊነቱን/እርጉዝ ጨለማ ውስጥ አስሮ የሚያሰቃይ ጨካኝነቱን ሰርዘሽ “ሰዋዊነቱን” መቀበል ጀመርሽ። ጸሐፊዎችና ወጣትና ሽማግሌ ነፈዝ ምሁራኖች ምን ብናደርጋችሁ ይሻላችሁ ይሆን?
የንግግር ከፍታ እና ዝቅታ ከሥራው ጋር ሲነጻጸር እንዲህ
ብለሻል።
“ከዚህ ኢትዮጵያን ከመውደዳቸው ከፍታ እስካልወረዱ ድረስ ከነቃርሚያው ተስፋ እንዳደርግ ያደርጉኛል፡፡”
ይህ እማ ያንቺ የተለየ ባሕሪ አይደለም ኢትዮጵያውያን የምንጠቃበት አስቸጋሪ ባሕሪ ነው። ለዚህም ማስረጃ ፊታውራሪ ተክለሐዋርያት ተክለ ማርያም ያሉትን ላንቺ የሚስማማ ንግግር ላቸው። እንዲህ ይላሉ ”የኢትዮጵያ ዕድልዋ መቸም ይኸው ነው፡ መታለል እና በከንቱ ማለቅ።” አንቺም የዚህ የቃላት ሰለባ እና ተታላይ ነሽ። እባካችሁ በቃላት እየተሰዋደችሁ ሕዝቡንም የባሰ ግራ አታጋቡት። ኮለኔል መንግሥቱ የመጨረሻ ንግግራቸውን ታስታዊሽያለሽ? እንዲህ ነበር ያሉት፦ “..የኢትዮጵያ
ጣለቶች የሚንቀሳቀሱት ኢትዮጵያን ለመበተን ከሆነ ለኢትዮጵያ ስል ግምባሬን በጥይት እስከተፈረከሰ ድረስ ለኢትዮጵያ ስል
ግምባሬን ለአረር እሰጣለሁ። ከዚች ድሃዋ ኢትዮጵያ አገራችን እንማለን/እንሞታለን…” ብለው በሳምንቱ ወያኔ ጅሑር ፤ሠላሌ ገባ
ሲባል፤ምስኪን ወታደሩን ካለ አመራር በትነውት “ውልቅ ብለው ወደ ዝምባብዌ” መሄዳቸውን ያየነው የጊዜአችን ታሪክ ነው።
ስለሆነም ብዙዎቹ መሪዎች ሁሌም ከምለሳቸው የሚወጣው የማር ዘለላ ሲሆን በትግባር ሲፈተኑ ግን አጥፊዎች፤ወሾች፤አጭበርባሪዎች፤ቅጥረኞች
እና ሙሾ ናቸው። ስለሆንመ በቃላት የመደለሉ ባሕሪ ብታቆሙ እና መሪዎች በሚሰሩት ስራ ብትመዝንዋቸው መልካም ነው። እንኳን
የምሁራን ዋዣቂ ብዕር ተጨምሮበት እንዳውም ተላለ ነውና ተላላውን ሕዝብ መልሳችሁ ጌኞ እንዲሆን አታስተምሩት።
አመሰግናለሁ ጌታቸው ረዳ (ኢትዮ ሰማይ) Ethio Semay
አመሰግናለሁ ጌታቸው ረዳ (ኢትዮ ሰማይ) Ethio Semay