Monday, March 5, 2012

በትግሬዎች ላይ የዘር ማጥፋት ዘመቻ ጥሪ የተሰራጨው ቪዲዮ!የንጉሥ ኤዛና የሓወልት ማስታወሻ (የወቅቱ ማስታወሻ ደብተር)

የንጉሥ ኤዛና የሓወልት ማስታወሻ (የወቅቱ ማስታወሻ ደብተር)
በትግሬዎች ላይ የዘር ማጥፋት ዘመቻ ጥሪ የተሰራጨ ቪዲ!

የሳምንቱ አንኳር ትኩረቶች
ጌታቸው ረዳ (አትዮጵያን ሰማይ ድረገጽ)www.ethiopiansemay.nlogspot.com getachre@aol.com እንደምን ሰነበታችሁ? አብዛኛዎቻችሁ እንደምታውቁት ይህ ድረ ገጽ የሚተቸው  በመንግሥትነት ተቀምጦ የጎሳ አስተዳደር ዘርግቶ ለብዙ ሺሕ ሰው የጎሳ ፍጅት እልቂት ምክንያት የሆነው በወያኔው ቡድን ብቻ ሳይሆን ወያኔን ለመተካት በተደራጁ ተቃዋሚ ቡድኖችም ጭምር የሚንጸባረቅ ጎሰኛ ቅሰቀሳ፤ውሸት፤ጸረ ኢትዮጵያ ዘመቻ ወይንም በየመድረኩ በማወቅ ወይንም አለማወቅ የሚነገሩ የተጣመሙ የታሪክ ስርጭቶች በሚሰነዘሩ ጉዳዮች ላይ በማትኮር ሕዝቡ አማራጭ ግንዛቤ እንዲኖረው የሚዘግብ ድረ ገጽ ነው።
በግለሰዎች ወይንም በቡድኖች በፖለቲካው፤ማሕበራዊ ግንኙነት እና ሃይማኖት ነክ ጉዳዮች ተንተርሶ የሚፈጸሙ ጸረ ሕዝብ እንቅስቃሴዎች  እየተከታተለ ማንኛውም ዛቻ፤ስድብ እና ጥቅም ሳያምበረክከው ለእውነት ስለ እውነት ሲል የዚህ ድረገጽ አዘጋጅ ለ20 አመት ሽንጡን ገትሮ ሁሉንም እንደየ አመጣጣቸው ታግሏል። አሁንም ይቀጥላል።
በዚህ መሰረት ለዚህ ሳምንት የያዝኩላችሁ ትኩረት የሚከተሉት ናቸው።
ሦስት ትኩረቶች አሉኝ
1)         ስብሐት ነጋ እና የአክሱም ዘመነ መንግሥት
2)           ታማኝ ስለ አፄ ምኒልክ በዋሽንገተን ንግግሩ። (ይኼኛው ረዢም ስለሚሆንባችሁ ለዛሬ እዘለዋለሁ) ከአህያ ጋር የዋለ ኰርማ እንደ አህያይቱ መጮህ ካልለመደ ፈስ መፍሳት ይለምዳል” ይላሉ ትግሬዎች ወላጆቻችን “(ምስ አድጊ ዝዋዓለ ዝራቢዕ ‘ህላ’ ተዘይለመደ ‘ጥራጥ’ ለመደ)። የ 15ኛው ክፍለዘመን የጋሞጐፋው “አባ ባሕርይ” የታማኝን የምኒልክን መስፋፋት አዲስ የታሪክ ዲስኩር ከመቃብራቸው ሆነው ሰምተውት ብቻ እንዳይሆኑ!!! ለዛሬ በዚህ ልለፈው። “አህያ እና በሬ ባንድ ከዋሉ ው ……! .......! ነው::

(3) በትግርኛ ተናጋሪ ሕብረተሰብ (ኤርትራኖች) ላይ የተሰራጨው የዘር ማጥፋት ዘመቻ ቅስቀሳ የተሰራጨው አውዲዮ ቪድዮ (ስዕለ ድምፅ) በሚመለከት፤
በሚቀጥለው አድራሻ በመጫን ሚካል ንዋይ የተባለ ወጣት በትግሬዎች እና በኤርትራኖች ላይ ያስተላለፈው የዘር ማጥፋት ዘመቻ ጥሪ ተመለከቱት። ልጁ የካረንት አፈይርስ ጉልት ነው።ከዚያ አይጠፋም፡ ለዚህ ነው ስለ እዛኛው ፓል ቶክ እና የመሳሰሉት ብዙ ጊዜ ሳስጠነቅቃችሁ የነበረው።አንግዲህ ጥቆማው ይኼው “የሕግ ባለ ሞያዎች” የመንግሥቱ መጽሐፍ ‘ስካን’ ተደርጎ፤ ኮፒው ተሰራጨ  ብላችሁ ያዙኝ ልቀቁኝ ብላችሁ ኩንታል ሙሉ ጽሑፍ የሚመዘን የወረቀት ክብደት ከመለጠፍ ወደ ቁም ነገር ግቡ እና ይህ የቤት ሥራ ሰጥተናል” ይኼውላችሁ፤ በተግባር አሳዩን እስቲ!!!!!!!
በሚከተለው ቪድዮ የምታዩት ሚካኤል ንዋይ ይባላል።ወጣቱ www.saveshewa.org የሚባል ኢንተርኔት/ድረገጽ  አለው።ሚካኤል ንዋይ ያስተላለፈው በትግርኛ ተናጋሪ ሕብረተሰብ የዘር ማጥፋት ጥሪ ያስተላለፈው ይኼው፡ እዚህ ይጫኑ
(3) የሻዕቢያው ደራሲ ተስፋዬ ገብአብ ለፍርድ ይቅረብ! (ይኼኛውም ረዢም ሐተታ/ዶኬት ስላካተተ ለሚቀጥለው ሳምንት አስተላልፌዋለሁ)።
(1)ስብሐት ነጋ እና የአክሱም ዘመነ መንግሥት
አንድ ጊዜ የሚያውቁኝም የማያውቁኝም አንዳንድ ወገኖች እየደወሉ “በርታ፤ምን እናድረግልህ?” እያሉ ያጽናኑኛል። ባለፈው ሰሞን ግን ሦስት ሰዎች  “ይህ ሁሉ ስትተች ምነው “ስብሓት ነጋ” ላይ ስትደርስ አፍህ ተለጐመ?” የሚል ትችት ጣል አደረጉልኝ። በተለይ አንደኛው ስብሓት ስለ ዓድዋ፤ዓጋመ እና አክሱም የተናገረው አሳፋሪ የታሪክ ጥላሸት ብዙ ሰዎች ትግሬዎችም ጭምር ከአገርም ከውጭም መልስ ጽፈውበታል፤ ግን ካንዳቸውም የተሰጠው መልስ መረጃቸው አላረካኝም (ድፍን መልስ ነው)። ስለዚህ ምንም እንኳ ሁላችንም ትግሬዎች ብንሆንም በተለይ  አንተ የአክሱም ልጅ ነህ፤ታሪኩን ታውቀዋለህ ብየ እገምታለሁ እና መልስ ሰጥቶበት ይሆናል ብየ ድረገጽህ ተመላልሼ ስጎበኝ ምንም ነገር የለም እና እባክህን እስቲ ከነዚህ ሁሉ ተቺዎች ያንተ የተሻለ ምልስ ከሆነ በዚህ አንጀቴን አርሰኝ? ብሎ ጠየቀኝ።
መልስ ላለመስጠቴ ይቅርታ ጠይቄ ቃል በገባሁላቸው መሰረት ለስብሃት የምሰጠው መልስ የሚከተለው የታሪክ መረጃ በማቅረብ ነው። ሁላችሁም እንደሚያረካ፤ ስበሐትም እንደ፣ሚማርበት አማናለሁ (የሚያወቅ ካለ ያስተምረኝ ብሏል እና)። የትግራይን ሕዝብ የወከልኩ ሰው ነኝ ብሎ እልፍ ኣእላፍ ሕዝብ አስሰልፎ የመራ ሰው ከኔው ተራ ዜጋ ትምህርት ከፈለገ ይኼውና  ከየኔታ ጄታቸው ረዳ ለቆሎ ተማሪው ስብሓት ነጋ የተሰጠ ትምህርት።
አቦይ ስብሐት የአክሱም መንግሥት አስተዳደር እንኳን አማራ ቀርቶ የተምቤንም ሆነ የዓጋመ አካባቢ አይጨምርም ነበር። ሲል ለቮኦኤ ጥር ዓርብ20/2004 (ካልተሳሳትኩ) በፈረንጅ ግን ጃኒዋሪ 14/20012 ትግርኛ ፕሮግራም ቀርቦ ከዶ/ር አረጋዊ በርሔ ጋር ስለ ብስራት አማረ መጽሐፍ ሲነጋገር ነበር እንዲህ ያለው። ቃል በቃሉ (የራሱ ቃል) ከትግርኛ ወደ አማርኛ ግልጽ ለማድረግ አንዳንድ ቅንፎችና መስተካክሎች አድርጌ የተረጐምኩት የስብሓት ክርክር እንዲህ ይላል፦

…….አሁን ይህ (መረጃ) የሚታየው ክፃፈው መፅሃፍ ተዛምዶ ነው። (ደራሲው ብስራት አማረ)የተወው ነገር ሊኖር ይችላል። ይህ   የታሪክ መጽሐፍ መነሻ እንደ  መሆኑ መጠን፡ ማለትም ከትግራይና ኤርትራ ውጭ ልክ አንተ (አረጋዊ በርሔ) እንደምትለው አይደለም ሲሸፍን የነበረው።
አክሱምጋምቤላና ሌላም የሚጨምር አይደለም!” ወደ ትግራይም ስንመጣ አሁን ያለው ትግራይን የሚጨምር አይመስለኝም። ተምቤን የአክሱማይት ኢምፓየር አካል ነበር ወይ? የሚል ጥያቄ አለኝ። እንዲያውም የአጋሜ እና የተምቤን አካባቢዎች የአክሱም (አካል) ነበር ወይ? የሚል ጥያቄ አለኝ።ባንድ አጋጣሚበፐሪፐለስ ኦፍ ኤርትራ” ስያሞ የሚል አየሁ። (ስያሞ ማለት ደግሞ የት ነው ብየ ብጠይቅ) በድሮ ኣጠራር አጋሜ ነው ብለውታል።እና (በ እዛው ሰነድ) የአክሱም አካል እንዳልሆነ ተገነዘብኩኝ። እና አፈ ታሪክ(ለጀንድ) ካልሆነ የተጨበጠ ታሪክ አይቼ/አንብቤ) ስለማላውቅ ስለ መፅሃፍዋ ግን እንደማስበው ተገቢ መንደርደርያ ነው እላለለሁ። የኢትዮጵያ ታሪክ እንደገና መጻፍ አለበት ብዬ ነው የማምነው። መጽሐፉ እውነተኛ ታሪክ እንዲፃፍ በር ይከፍታል።
ሲልአክሱምለአጋሜው እና ለተምቤኑ፤ለእንደርታው እና ለራያው ምኑ ነው? ሲል አሳፋሪና ያላዋቂነት ክርክር አቅርቧል:: የኢትዮጵያ ታሪክ እንደገና መጻፍ አለበት ብዬ ነው የማምነው!!!!!  ሲል አይገርማችሁም?

እሱ እንደሚለው አፈታሪክ ካልሆነ “የተጨበጠ ታሪክ/ጽሑፍ የለም” ብሏል።ስያሞ   ማለት ደግሞ   ጠራር  አጋሜ ነ ብለታል።እና የአክሱም  አካል  እንዳልሆ ተገዘብኩ” ብሏል”። ሁለቱንም በማስረጃ እነሆ።
ኤዛና ሐውልት የሚባል አክሱም ከተማ "የኢዛና መናፈሻ" ብለን የምንጠራው እኔ የተማርኩበት አብርሃ አጽብሃ ት/ቤት ፊት ለፊቱ የቆመ ሃውልት አለ። የትምህርት ጓደኞቼ ፕያሳ ፈልገውኝ እኔን አጥተውኝ የሚያገኙኝ ቦታ “ሲደክመኝ ወይንም ለማጥናት ስፈልግ” ሀውልቱ ሥር ቁጭ ብየ ደረቴን ወደ ሐውልቱ አስደግፌ ጸሐይ ስሞቅ የሚያገኙኝ ስፍራ የዘወትር መቀመጪያ ሐውልቱ ስር ወይንም  የሚገኙ የመናፈሻ መቀመጫዎች አካባቢ ነው።
ሐውልቱ “የኢዛና ሐውልት” ይባላል። ንጉሠ ነገሥት ኤዛና አብዛኛዎቻችሁ በገናናነቱ የምታወቁት ነው። የክርሰትና ሃይማኖት ያስፋፋ የመጀመርያ ንጉሥ ነው።ኢዛና የሳይዛና ወንድም ነው (የክርሰትና ስማቸው “አብርሃ እና  አጽብሃ)። (288 ዓ.ም እስከ 336 ዓ.ም.) የግዛታቸው ስፋት ሁላችሁም ተደጋግሞ እንዳንበባችሁት  ቀይ በሕር፤የመን ሱዳን (ወደ ታች እስከ ኑቢያ ድረስ(ሰሜን ሱዳን ድረስ) እስከ ሕንድ ውቅያኖስ (ሶማሌ በርበራ ሁሉ ድረስ) የተዘረጋ ስርዓት ነበር።(ሸዋ፤ሐረር,…..ጋሞጎፋ…… ቤተክርስትያን ገዳማት/ምሽጎች/ቅሬቶቻቸው ትተዋል።  አሁንም አሉ)
የኢዛና ማስታወሻ መዝገብ በሐውልት ደንጋይ ላይ ጽፎ ያቆመው መናፈሻ አትክልት ወስጥ በአጥር የተከለለ ነው። ኤዛና ያቆመው ሓውልት በ332 ዓ.ም፣ ነው የቆሞው። በሦስት ቋንቋ ተጽፎ ይነበባል። ወጣት ሆኜ በእጄም ዳስሼ በዓይኔም ትኩር ብየ ሁሌም የምመለከተውና የሚገርመኝ ድንጋይ ታምረኛ የድንጋዩ ምንነት ነበር። ግዕዙ አነበዋለሁ። ምን እንደሚል ስለ ምን እንደሚያወራ ግን ካደግኩኝ በሗላ ካልሆነ ያኔ በምን ምክንያት እንደተጻፈ ለማወቅ ፍላጎት ቢኖረኝም ( ዓይኔ ጽሑፉ ላይ አርፎ ባተኰረ ወቅት መንፈሴ ግን ዛሬም ሆነ ያኔ በማይገባኝ ሁኔታ በሽቶ፤በእጣን አና በዝማሬ በታወደ/በታጀበ የደራ/የጥንት ከተማ ያከንፈኝ ነበር) ምክንያቱ ለማወቅ እስከ እዚህ ጉዳየም አልነበረም። አሁን ተረዳሁት።በግሪክ፤በሳባ እና በግዕዝ ፊደል /ቋንቋ ነው የተጻፈው። በጣም የሚያምር፤መሰምር የጠበቀ ግሩም የጽሑፍ አጣጣል- ቁልጭ ብሎ ይነበባል።ሐውልቱ ላይ ያለው ጽሑፍ የተዘገበው ስለ ምንድነው የሚናገረው?
ንጉሥ ኤዛና ከዋና ከተማው አክሱም እየተነሳ የቤጃ ነገዶችን ለማሥታገሥ ያደረገውን ዘመቻ ነው የሚተርክ ። እንዲህ ይላል።
“ኢዛና የአክሱም ንጉሥ፤ የሒምያር የራይዳን፤ የሳባ፤ የሳለሂን፤ የሲያሞ፤ የቤጃና የካሱ ንጉሥ ነገሥት የማይሸነፈው የእግዚአብሔር ልጅ” እያለ በመቀጠል ወንድሞቹ “ሳይዛና እና ሐዳፈስን” ወደ ዘመቻው ልኮ ነውጥ አስነስተው አንገዛም ብለው ያንገራገሩትን የቤጃዎቹ "ትጥቅ ከብቶችና በጎች……የመሳሰሉት ንብረቶች" በቁጥር የሰውም የምርኮ ብዛት በመዘርዘር ለትውልድ ሐውልቱ ላይ ጽፎ የተወልን የጽሑፍ ሰነድ ነው።
እንግዲህ ስብሐት ነጋ “ስያሞ” ማለት አጋሜ መሆኑን የፐሪፐላስ ሰነድ ከነገረው፤ የኔው አያት እና የሰብሐት ነጋ ቅድመ ቅድመ …….ኣያት ንጉሠ ነገሥት ኤዛና “የአክሱም…..የስያሞ…….ንጉሠ ነገሥት ነኝ” ብሎ የተወልንን የቃል ተረት ተረት ሳይሆን ዝናብ፤እሳት፤ነፋስ፤ የማይደመስሰው “የኢዛና የሐውልት ጽሑፍ” (ሰነድ) አክሱም ከተማ ድረስ ሄዶ በዓይኑ እንዲያየው “ስበሓት ነጋ” እስካሁን ድረስ “ለጀንድ/አፈ ታሪክ" እንጂ በጽሑፍ/ቅሪት ያመላከተኝ ሰው የለም፤ አለ የሚል ካለ አስተካክሎ በመረጃ ያስተምረኝ/ይጠቁመኝ ስላለ፤ በመረጃ ይኼው ፡ጥቆማየ ይድረስህ።
አመሰግናለሁ ጌታቸው ረዳ www.ethiopiansemay.nlogspot.com     getachre@aol.com