Wednesday, January 18, 2012

አዲሱ ኦነግና ነባሩ ኦነግ ያልለቀቃቸው በሽታ


አዲሱ ኦነግና ነባሩ ኦነግ  ያልለቀቃቸው በሽታ

ጌታቸው ረዳ


በዚህ ልጀምር። የአዲሱ ኦነግ ጅማሮ የሚያበረታታ ቢሆንም መላቀቅ ያለባቸው ያልለቀቃቸው የድሮው በሽታ ስላለ እሱንም እንዲያርሙ አሁንም ከመተቸት አንቦዝንም። ለብዙ ዓመት ስለተቸናቸው “መሻሻል አሳይተዋል”። ትችታችን አሁን ላሳዩት ውጤት መንገድ መርቶ አሳይተዋቸዋል። “አጀንዳቸው የማይሰራ መሆኑን ስናስረዳ “በኦነጎች ቀርቶ” “የኦሮሞ ሕዝብ ጠላቶች” ተብለን  “ስማቸው በማልጠራቸው ኢትዮጵያውያን ሳይቀር ለአመታት ተዘልፈናል። እኛም እነሱም እየተተቻቸን የቀራቸው ጉዞ እንዲጓዙ ትችታችን ጠቃሚነቱን ማናናቅ አይኖርባቸውም። እና በርቱ፡ ይህ ካልኩ ዘንዳ ኦነጎች የምትወዱት/የምትጠሉት ትችቴን እነሆ ከጠቀማችሁ ተበራቱበት።ዛሬ አልዋጥ ቢላችሁ ከመረራችሁም እርግጣና ነኝ አንድ ቀን ሲዋጥላችሁ ይጣፍጣችል። ዛሬ ብዙ ነጥቦች ስላነሳሁ፤ ከደከማችሁም ሳይሰለቻችሁ እየተመላለሳችሁም ቢሆን ጊዜ ወስዳችሁ ትችቴን አንብቡት።
እንደሚታወቀው በፈረንጆች አዲስ ዘመን ዓመት አቆጣጠር በከማል ገልቹ የሚመራው “ኦነግ” ከመገንጠል ወጥቶ ኢትዮጵያዊነቱን አውጇል ብለው የድርጅቱ መሪዎች ተናግረው ብዙ ሰው ደስታውን በመግለጽ ላይ ሲገኝ አንዳንድ ወገኖች ደግሞ “እስኪ ረጋ በሉ” ሲሉ የሁለቱም “ኦነጎች” መርሃ ግብር/መመሪያ እንፈትሽ ብለዋል።
አንፈትሽ ያሉት እኔን መሰል ግለሰቦች እና እንዲሁም ኢሕአፓዎች ናቸው ተብሏል። ኩፉኛ ሲወገዙ አልፎም “ይህንን ረጋ ብላችሁ እስቲ ፈትሹ ያሉት በፈረደባቸው ‘ኢሕአፓዎች’ ላይ ወዳጄ ቀድቶ የላከልኝ “ካረንት አፈይረስ/ኦካዴፍ” የተባለው ፓል ቶክ ውስጥ “ምንም ቢሆን ኢሕአፓዎች በሙሉ ካልተገደሉ የኢትዮጵያ ፖለቲካ አይጠራም’ ያሉትን በነሱ ላይ የታወጀውን ሳዳምጥ “ከመሳቀቅ በላይ” “በኢሕአፓ ላይ የቀይ ሽብር ይፋፋም!” ስትል ኢሕአፓዎችን እና ደጋፊዎቻቸውን ያስደነገጠች የዛው ክፍል ሴትዮ፤ “ቀለቤቴን ስጧት” በሚለው በብዕር አጣጣሉ ሕሊናን የሚያነሆልል ብዕርተኛው በልጅግ አሊ በጻፈው መጽሐፍ ላይ ከኮምፒዩተር በስተጀርባ ሆና በኢሕፓዎች ላይ ቀይ ሽብር ይፋፋም” ስትል እንደ አውሬ ስትጮህ አብረዋት “በርቺ ፤አይዞሽ” የሚሏትን ከገፅ 43 ጀምሮ “ራስኮልኒኮቭ ሰዎቹን ከገደለ በላ ለምን ተጨነቀ?” ብሎ የጠየቀውን አስታወሰኝና መጽሐፉን እንደገና አንስቼ እንዚህ ሰዎች አሁንም ግድያ ለምን እንዲፋፋም እንደሚወዱ መከለስ ነበረብኝ እና መልሱን አገኘሁት። መጽሐፉን ገዝታችሁ ብታነቡ ካሁን በፊት ያላወቃችሁትን ምንነታችሁ ታገኙታላችሁ Beljig.ali@gmail.com ያ ፓልቶክ ብዙ ችግር አለበት፤ለወደፊቱ እንዴት እንደሚደመደም እግዚሔር ይቀው እንጂ “ያልበሰሉ አደገኛ ሰዎች” ያሉበት ክፍል ነውና ምሕረቱን ይስጣቸው።
ዛሬም ቀይ ሽብር በኢሕአፓ የሚሉት “የአዲሱ ኦነግ” መርሕ ካልተቀበላችሁ “ለሞት ተፈርዳችል የሚሉት እነማን እንደሆኑ ሁላችሁም የምታውቁት ይመስለኛል። እኔኑን ግራ የገባኝ ግን የሚከተለው የከማል ገልቹም ሆነ የኑሮ ደዶፋ እና የአሚን ጃንዳይ ቡድን በግንጠላው ላይ ያላቸው መልስ ነው።
ምንድነው ሲሉን የነበረው? ታስታውሳላችሁ? ካሁን በፊት ኦነግ የመገንጠል ጥያቄ ጠይቆ አያወቅም! ሲሉ ብዙ አነጋግሮናል። የኢትዬ-ሚዲያ ድረገጽ አዘጋጅ ወዳጄ አቶ አብርሃ በላይም ኦነግ የመገንጠል ጥያቄ ጠይቆ አያውቅም የሚለውን አነጋገራቸው በማድመቅ ድጋፉን በድረገጹ የመሪዎቹ ውሸት “ብሪሊያንት/አሳማኝ” ሲል ሲከተሉት የነበረውን የመገንጠል ጥያቄ አቋማቸው “በኢትዮጵያውያን ሃይሎች” የተዋሸ እንጂ የኦነግ ጥያቄ እንዳልነበረ አስነብቦናል። እኛ እንደዋሾች ተቆጠርን ማለት ነው። በዚህ ላይ ጽፌአለሁ። ታስታውሱታላችሁ? ብዙ እርግማንም ደርሶኛል።
አሁን ዋሾው እኔ ወይንም መሰሎቼ ሳንሆን የእነሱን ውሸት ያደመቁላቸው እና የከማል ገልቹ ወገኖች እና እራሳቸው መሪዎቹ እንደነበሩ “ከማል እራሱ እና በፕሮግራሙ “መገንጠልን እንዳስቀረ ተናገሯል።ሌሎቹንም የተናገሩትን አስደምጣችለሁ/ታነባላችሁ።
ለምሳሌ ኢሳት ከተባለው ስዕለ ድምፅ አዘጋጅ ከወዳጄ ሲሳይ አገና ጋር በቅርቡ ኮሎኔል ሃይሉ ጎንፋ ከተባሉ የአዲሱ ኦነግ አመራር አባል እና የአቅም ግምባታ ሃላፊ ከሆኑት ጋር  ቃለ መጠይቅ አድርጎ ነበር። ሃይሉ ጎንፋ አስመራ ውስጥ ሆነው በስልክ የሰጡትን የስልክ ቃለ መጠይቅ እነሆ።
ኢቲቪ- ሲሳይ አገና፡- “…አንግዲህ ደጋግሜ የማነሳው እንደሚታወቀው አርስዎም ሆኑ ጀኔራል ከማል ገልቹ በኢትዬጵያ ሠራዊት ውስጥ ከፍተኛ አመራር ቦታ የነበራችሁ ናችሁ። እንግዲህ በብዙ ሰው ውስጥ የሚነሳው ጥያቄ ኦነግ የኦሮምን ሕዝብ ስም ይዞ የተነሳ ነው፡ ግን ድርጅቱ ወደ 40 ዓመታት እንዳስቆጠረ ይታወቃል.. (የድርጅቱ አቋም) የኦሮሞ ኢትዬጵያዊነት ወይንም ኦሮሞ ኢትዮጵያዊ አይደለም የሚል ለመገንጠል የሚደረግ እንቅስቃሴ ስለሆነ በሌላ ኢትዬጵያዊም ዘንድ ጥቂት በማይባሉ ኦሮሞዎችም ጭምር የኦሮሞን ሕዝብ ለማስገንጠል ነው በሚል ረገድ የሚነሳ ጥያቄ አለ። ኢትዮጵያ ሠራዊት የነበራችሁ በአመራር ስትመሩ የነበራችሁ ሰዎች አሁን ተመልሳችሁ ኦሮሞን ከኢትዮጵያ ለመገንጠል ከሚንቀሳቀስ ቡድን ውስጥ ነው የገባችሁት እና አንዴት ነው ቢያብራሩልኝ?” 
ኮለኔል ሃይሉ ጎንፋ፤- “አሁን ከመነሻው ጥያቄ ያለው ስሕተት ምንድነው፤ ገዢዎች ሁልጊዜ ሕዝቦች እንዲጠራጠሩ እንዳይተማመኑ በፍርሃት እንዲኖሩ ከሚያደርጉ አንዱ የቀን ቅዠታቸው ይቃዡና ቅዠታቸው እንዲያስተጋባ ያደርጉታል።…ኦሮሞ ነፃነት ግምባር የመገንጠል ዋና አላማው አይደለም። ተገነጠለ የሚል ስም የሚለጥፉበት ሌሎች ሃይሎች ናቸው፤ገዢዎች ናቸው።…(የመገንጠል ጥያቄ) የኦሮሞ ነፃነት ግምባር አጀንዳም አይደለም።…ገዢዎች አንደዚህ ሲሉ እኛም (እነርሱ ጋር)ማስተጋባት ትከክል አይደለም። ሲሉ መገንጠል የጥቆ አያውቅም በማለት ክደዋል። (ይኼ በጣም በቅርብ ገዚ ነው።)
ካሁን በፊት ኑሮ ደዴፎና አሚን ጃንዳይ የተባሉት የአዲሱ ኦነግ አመራሮች “ኦነግ የመገንጠል ጥያቄ ጠይቆ አያውቅም” ሲሉ መልሰው ነበር። አሁንም ደግሞ ኢሳት “ትኩረት” በተባለው መደቡ ላይ “አዲሱ ኦነግ” ሜነሶታ ላይ አዲስ ራዕይ/አጀንዳ ይዤ ብቅ ብያለሁ ሲል በስልክ ዶ/ር ኑሮ ደዴፎን በስብሰባው ጠርቶ ቃለ መጥይቅ ሲያደርግላቸው፤ ዶ/ር ኑሮ ደዴፎ የሚከተለው ብለው ነበር።
ጠያቂ” ፦ ቀደም ሲል ከነበረው አቋም በምን ይለያል?በግልፅ አድማጮች እንዲረዱት ፈልጌ ነው ዶ/ር ኑሮ፡
ዶ/ር ኑሮ መልስ፦”ዌል፤-ከዚህ በፊት የነበረው (አጀንዳ) እንደሚታወቀው አብዛኛው የሚለው “የኦሮሞ ሕዝብ የገዛ ራሱን አገር የማቋቋም አላማዎች አሉት” (ነበሩበት)። ያሁኑ ጊዜ ግልጽ አድርጎ ከሌሎች ኢትዮጵያ ሕዝቦች ጋር (ለመኖር) አንድ አገር መስርቶ (ኢትዮጵያ) አሁን አንዳለው እንደ ወያኔው የውሸት ፌደራል ሳይሆን (ዓለማችን) “በፌዴራል ዲሞክራቲክ”  ለመኖር ነው።(አሁን ይዞ የመጣው (መርህ) ካለፈው የሚያሳየው ልዩነት ካለ ያሁኑ አንድ አገር (ኢትዮጵያ) የመቀበል ጉዳይ ነው።
የኢሳቱ አበበ ገላውም አንዲህ ሲል አረጋግጧል፦“Washington DC (ESAT) – The Oromo Liberation Front has announced its historic decision to drop its long-held secessionist agenda and to embrace the unity of Ethiopia under a genuine federal arrangement that must guarantee the rights, equality and liberty of all Ethiopians.” January 2nd, 2012)
እንግዲህ በዚህ መልክ አዲሱን ኦነግ ለሚመሩ የምጠይቀው ጥያቄ “ኦነግ የመገንጠልን ጥያቄ አጀንዳ የለውም” የሚለውን አንመን ወይስ “ኦነግ የመገንጠል አጀንዳውን አንስቷልን” እንመን? በዚህ ውዥምብር ስንሰደብ ለውሸታቸው “ይቅርታ አንዲጠይቁን” ማንን እንጠይቅ? ወሸታሞቹ እነሱ ወይንስ እኛ? በዚህ የውሸት ባሕሪ ተነስተን አዲሱን የኦነግ አማራር አሁንም ለወደፊተም ከዚህ ልማዳቸው ተነስተን ብንጠራጠር እንዴት ልያስወቅሰን ይችላል?
እንቀጥል፦
ፕሮግራማቸውም ብትመለከቱት ለኔ ወያኔአዊ እንጂ ምንም ልዩነት የለውም። አማርኛ ስለሚጠሉ መግለጫቸው “በእንግሊዝኛቸው” ነው የተጠቀሙት እና እኔው ራሴ ፕሮግራማቸው ወደ አማርኛችን ስለውጠው አሁንም የተጠቀሙበት የነገዶች አገላለጽ ወያኔ የነደፈው/የተከተለው “ብሔር፤ብሐረሰቦች እና ሕዝቦች” የሚለው ነው። ሕዘብን በቋንቋም እንደ ወያኔ ተንትነውታል። ይህ ትምህርት ኮሚኒስታዊ፤ሲከፋም ጣሊያኖች አገራችን ሲወሩን የተጠቀሙበት የትንታኔ ፋሸስታዊ ንድፍ ነው። እነኚህም በዛው ፈለግ ተከትለዋል።
በመሰረቱ እነዚህም የኮሚኒስቱ የዋለልኝ መኮንን ደቀመዛሙርቶች ናቸው እና ዋለልኝ የተጠቀመበትን አገላለጽ ተጠቅመውበታል። ላገራችንም አደገኛነቱ አሁንም በነዚህ የፖለቲካ ገልቱዎች መቀጠሉ ያሳዝናል።
የዋለልኝ ኢትዮጵያ አገላለጽ አስተምህሮ ምን ብሎ ነበር? እነሆ፦“Ethiopia is not really one nation. It is made up of a dozen nationalities with their own languages, ways of dressing, history, social organization and territorial entity. . . . I conclude that in Ethiopia there is the Oromo Nation, the Tigrai Nation, the Amhara Nation, the Gurage Nation, the Sidama Nation, the Wellamo Nation, the Adhere Nation, and however much you may not like it the Somali Nation.” Wallelign. ዋለልኝ መኮንን ይህ አገላለጽ ከማን አገኘው? ከኮሚኒስቶች። ኮሚኒስቶች ብቻ ሳይሆኑ ጣሊያኖችም ጭምር ነው። ለመሆኑ ዋለልኝ ይህ በጻፈ ከብዙ ዓመት በላ ኢትዮጵያ የአማራዎች አገር እንጂ እሱ የጠቀሳቸው “የኢትዮጵያ እስረኞች” ብሎ የሚላቸው (በኔ አጠራር) “ነገዶች” በሱ አገላለጽ “ራሳቸው የቻሉ አገሮች/መንግሥታት” አንዳልሆነች ከገለጸበት እና የኮሚኒስቶቹ ፖለቲካ ኪሳራ ካጋጠመው ወዲህ ዛሬ “Wallelign misunderstood his country and its people as much as the people misunderstood him”. (ዘውገ ፋንታ) ዋለልኝ በቅርብ ከሚያውቁት አብሮ አደጎችና ጓደኞቹ መካከል። ተብሏል።
ዋለልኝ ያስተማራቸው ተ.ሓ.ህ.ት እና ኦነጎች ዛሬም በዛው በከሰረው ኮሚኒስታዊ እና ፋሺስታዊ ጎዳና ሲራመዱ አጀንዳቸውን ዛሬም እንደ ተገንጣ ወያኔ እና ሌላኛው ኦነግ አስተዳደራዊ ቅርጽ አስነብበውናል። ከዛው የተነሳም ዕድሜ ለዋለልኝ የየመንገሥታቶቹ ባንዴራዎች ተሰፍተው ዋለልኝ “አሳሪ” ከሚላት ወህኔ ቤት ውስጥ ነፃ ወጥተው ባንዴራቸው ያውለበልባሉ። አገር ውስጥ የሌሉም ኢንተርኔት ድረገጽ ላይ የፈለጉትን ጨርቅና የቀለም ዓይነት መርጠው ያውለበልቡታል።
ይህ የሕሊና በሽታ መነሻው ከየት ነው? ተብሎ መመርመር አስፈላጊ ነው።መለስ ብለን (ባክ ግራውንድ የሚሉት ተንታኞች) ፋሺስቶች እና ኮሚኒስቶች በየወቅታቸው ያሴሩብንን የሴራው መነሻው ጊዜ ከናዚዎች ኢትዮጵያን ዓይናቸው ውስጥ አስገብተዋታል።
ከሚከተለው መነሾ እንመልከት፡-“The Nazis of Austro Hungary had already in the 1930's targeted Ethiopia as a threat against white supremacy, and white colonialism in Africa, in much the same way as the Bush administration talks about Iraq's "weapons of mass destruction" and threat to "Western Civilization." In the case of Ethiopia, the classic work on the subject, which we have repeatedly introduced to the Ethiopian public, myself and the Ethiopian patriotic Diaspora in Germany, was , of course, the book by the Austrian Nazi, Baron Roman Prochazka's "Abyssinia the Powder Barrel" (Vienna 1935), translated in all the major Western languages (including American English, as the following text shows) before the Italian invasion in 1936. Baron Roman Prochazka was posted for two years as Austrian Consul in Addis Ababa until his expulsion in February 1934, as we say now for activities not compatible with his job of a diplomat. The Italian translation of Prochazka's book entitled ABISSINIA PERICOLO NERO meaning “Abyssinia the Black Threat or Danger” was published in 1935, which is a year before the Fascist invasion .Starting from the first page, Prochazka alerts his white public by stating that since four years that Emperor Haile Selassie's Ethiopia, in "close co-operation with Japan," was engaged "on a life and death struggle with the white race, the consequences of which are incalculable. The targets are the colonial powers in Africa without exception. It is hardly possible to imagine a more unhappy situation of a white man than to have to live under the oppression of an Abyssinian grandee. The prevalence of this contemptuous invective is characteristic of the mentality and attitude of the natives who imagine themselves to be infinitely superior to the white race."
Strikingly, the solution proposed by Prochazka is, and that is where he brings us to to the subject under discussion, is the tribalisation of Ethiopian politics for the purpose of divide and destroy. Prochazka was the first ever to have spoken of "self determination "as the most handy instrument for the dismantlement of the Ethiopian State. Here in brief are the highlights of Prochazka's strategy:
"The numerous peoples and tribes who inhabit the territory of the Ethiopian state, and which differ in race, language, culture and religion from the ruling minority of the Abyssinians proper, would long ago have thrown off the Abyssinian yoke if they had been given the right of self-determination. Instead, they are being forcibly kept cut off from European influences and from the advantages that progressive colonization could confer upon the country.” (Origin of Tribalisation of Ethiopian Politics: From Fascism to Fascism Aleme Eshete) www.ethiopiansemay,blogspot.com Or http://www.tecolahagos.com/origin_tribal.htm
ከላይ የተመለከታችሁት ኦነጎች እና ወያኔዎች የመሳሰሉት የተከተሉት ትምህርት ከዋለልኝ ብቻ ሳይሆን ከነዚ ፋሺስቱ ከሮማን ፕሮቻስካ እንደሆነ ያመላክታል። “ኢትዮጵያ የብሔር ብሔረሶቦች እና ሕዝቦች እስር ቤት ነች” ሲሉ የአዲሱ ኦነግ አማራር አባል ከአስመራ ባለፈው ሰሞን ያስተላለፉትም ከዚህ በመነሳት ነው። የታሰሩበት ምክንያት ከአስተማሪዎቻቸው አንዱ (ፕሮቻስካ) ሲገልጽ “they are being forcibly kept cut off from European influences and from the advantages that progressive colonization could confer upon the country.” ኦነጎች (ሁለቱም) ከወያኔ ጋር የሚያምኑት ላቲን ለኦሮሞ ሕዝብ የጽሐፈት መጠቀሚያ ቋንቋ የተመረጠበት መደረጉ ምክንያት በፕሮግራማቸው እንደሚነበበው እና ካሁን በፊት 1000 ኦሮሞ ምሁራን ከወዳጃቸው ወያኔ ጋር ፓርላማ ሆነው ሲያጽድቁት የተናገሩትም “ላቲን መጠቀም በቀላሉ ከስልጣኔ ጋር ያገናኘናል፤ ምክንያቱም ላቲን የሰለጠነ የስልጡኖች መነጋገርያ ቋንቋ ስለሆነ ነው።’ በማለት ነበር ያጸደቁት። ፕሮቻስካም እንዲሁ “ከአውሮጳውያን እኩል እንዳይሰለጥኑ ብሔሮች የመገንጠል መብት ተነፍገው ታስረዋል” ብሏል።በዚህ መልክ የፋሺስቶችና የኮሚኒስቶች መመሪያ አፅም እና ቅረቶቻቸው ዛሬም በኢትዮጵያ የጎሳ አቀንቃኞች ውስጥ ህያው ሆነው እየታዩ ነው።
ለመሆኑ ከማል ገልቹ በሳምነቱ ስለ የላቲን ቋንቋ በቪኦኤ ተጠይቀው ሲያብራሩ “በአባባላቸው የተለየ አነጋገር ይጠቀሙ እንጂ” ከአቻቸው የሚለይ አመለካከት የላቸውም። ለምን እንደተገለጸ ሲገልጹም የላቲን ምቹነትን አብራርተዋል።
ለመሆኑ ግዕዝ ላለማለት “ሳባ” የሚል ቋንቋ ጀኔራሉ ተጠቅመዋል፡ ለምን? ሳባ እና ግዕዝ ልዩነት እንዳለው አላወቁም? ወይስ ብቸኛው የአፍሪቃ ፊደል “ግዕዝ ፊደል” “የኢትዮጵያውያን ፊደል” ማለት አቀበት ሆኗቸው? እኔ እየጻፍኩ ያለሁት አሁን የምታነብቡት ፊደል ሳባ ነው? ይገርማል። ለነገሩ ግዕዝ (ግዕዝና አማርኛ ኦነጎች የደብተራዎች ቋንቋ የሚሉት) ከ“ላቲን” በተሻለ ኦሮምኛን ለማገልገል እንደሚችል በመጽሐፌ የተገለጸው መረጃ ሰጥቼ ልሰናበታችሁ። ‘ቁቤ’የተባለው ኦነጎች የፈለሰፉት ሳይሆን ጸረ ኢትዮጵያ ክፍሎች የፈጠሩላቸው አንደሆነ ከኦኖጎቹ ፀሓፊዎች መረጃው እነሆ “. The early writing in the Oromo language began almost two centuries ago. It is the conquest of Oromiyaa by Abyssinia that interrupted its development into full-fledged writing instrument. Of the earliest writing was vocabulary of Oromo language in 1842 in Latin script by J. Ludwig Krapf, a German national.”
ክራፕፍ የተባለው ማን እንደሆነ የኦነጎችን ታሪከ የተከታተላችሁ እና የሚስዮናውያን ጣልቃ ገብነት ያነባበችሁ ሰዎች የምታውቁት ሰው ነው። ክራፕፍ ከራሴ ው መፅሐፍ ውስጥ የተወሰደ ጥቅስ ምን ብሎ እንደነበር ክራፕፍ  እነሆ “በሸዋ ቆይታየ ለጋሎች የተለየ ትኩረት ያደረግሁት በእግዚአብሔር ፀጋ ፕሮቴስታንትነትን ከተቀበሉ በኋላ የሠራዊት ጌታ ለጀርመኖች በአውሮጳ ላሳየው የተልእኮ መሳካትን የተመረጡ እንደሚሆኑ በመገመት ነው።"(J.Lewis Krapf; Travels, Researches and Missionary Labour During an eighteen years Residence... (London :1968), 2nd ed. p. 72)" (የወያኔ ገበና ማህደር -ገጽ 215)ብሏል።
ግን እውን ላቲን ከግዕዝ የተሻለ ነው?
አንድም የጋላ ቋንቋ ድምፅ በእንግሊዝኛ/ላቲን ፊደል የማይገለጽ የለም እንዲያውም ከኢትዮጵያዊ ፊደል ይበልጥ በተሻለ ረገድ ሊገለጽ የማይቻል የለም።"(J.Krapf: Journal of Rev. Mess Issenberg and Krapf etc. London 1843 and An Imperfect outline of the elements of the Galla -Language by Rev. J.L Krapf.
London 1840) ከሚለው የተተረጎመ።
“አንድም የጋላ ቋንቋ ድምፅ በእንግሊዝኛ ፊደል የማይገለጽ የለም እንዲያውም ከኢትዮጵያዊ ፊደል ይበልጥ በተሻለ ረገድ ሊገለጽ የማይቻል የለም።” ያለውን የኦነጎቹ አስተማሪ ሌላው ሐቀኛ ጀርመናዊ ቻርለስ ቱትሸክ የጋልኛ መዝገበ ቃላት አዘጋጅ የክራፍን ትክክለኛ ያልሆነ ሐሳብ ተቃውሞ 30 ሆሂያት ያሉት ፊደል አዘጋጅቷል። የላቲን ጐዶሎ ፊደል ለጋልኛ ይሆናል ማለቱ ምን ያህል ውሸታም እንደሆነ ያሳያል። ለመሆኑ የእንግሊዝኛ ፊደል እንደ ጰ፤ ጨ፤ ጠ፤ ኘ፡ ዠ፤ ቀ፤ ፀ፤. ወዘተረፈ፤ የመሳሰሉት ድምፆች እንደ ኦሮምኛ አሉት? ከዘረኝነት ነፃ አስተዋይ ሕሊና ያላቸው የቋንቋ ሊቃውንት ሁሉ እንደሚያረጋግጡት የኢትዮጵያ ቋንቋዎች በመሠረታዊ ድምፅ አወጣጣቸው ዓይነት ብዛት ተመሳሳይ ናቸው። ለምሳሌ አማርኛ አና ኦሮሚኛ ብንወስድ በአማርኛ ውስጥ ከሚገኙት 27 ተነባቢ ድምፆች ውስጥ 23 በኦሮሚኛም ይገኛሉ። እንደዚሁም 24 የጋሊኛ ተነባቢዎች 23 በአማርኛ ያሉ ናቸው። ይህ ዓይነት ተቀራራቢነት በቋንቋዎች መካከል ካለ አንደኛው ቋንቋ በሚጽፍበት ፊደል ሌላውን መጻፍ የሚቻል መሆኑን የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የቋንቋ መምህር ባዩ ይማም፤ ባቀረቡት ጥናታዊ ጽሑፍ ሥርዓተ ጽሕፈት ውይይት 3 ቅጽ 1 ቁጥር 1 መጋቢት (1984) ገጽ 17-38 ያመለክታል። ኦሮሚኛ ከላቲን ይልቅ ከኢትዮጵያ ፊደል ተስማሚ ድምጾች (ጰ፤ ጠ፤ ጨ፤ ) እና አጻጻፍ እንደሚቻለውአየለ በክሬ (Ethiopic An African Writing System, (Canada: 1997) ገጽ 95). (ምንጭ ይደረስ ለጎጠኛው መምህር- ደራሲ ጌታቸው ረዳ -ገጽ 228)
በተጨማሪም  በአዲሱ እና በቆየው ኦነጎች መካካል በድረገጻቸው አጀንዳ የፖለቲካ ኦሮሚያ እና ኢትዮጵያ የሚሉት አገላለጽ ኤምፓየር/አማራ የሚሉት የሁለቱ ኦነጎች ውሸት እኔ የተከራከርኩበት (ቆየት ቢልም) አንድ አገር ዋዳድ ምሁር ኢትዮጵያዊ የገለፁትን ጭምር አንብቡ OLF & It’s Group: - How Many More Raids Do Ethiopians Tolerate? by Engeda Kassa “This article is an extracted version of my 15 pages commentary article posted on the then Ethiopian Unity website in 2004, to an argument made between Mr. Getachew Redda and an OLF official Mr. Dumesaa Diimmaa on OLF’s Mission issues.” አመሰግናለሁ። ጌታቸው ረዳ www.ethiopiansemay.blogspot.com getachre@aol.com.1-