Friday, July 26, 2024

የጀነራል ተፈራ ማሞ የምርኮኛነት ትርጉም ግብዝ አማርኛ ወይስ ወገንተኛ ጌታቸው ረዳ Ethiopian Semay 7/26/24

የጀነራል ተፈራ ማሞ የምርኮኛነት ትርጉም ግብዝ አማርኛ ወይስ ወገንተኛ

ጌታቸው ረዳ Ethiopian Semay 7/26/24

ድሮ “የብ አ ዲ ን ተዋጊና አባል” የነበረው  ጀነራልነቱ በሽምቅ ተዋጊነት ልምድ  ወደ ሥልጣን የወጣው ፋሺቱ “ወያነ” ጀነራል ብሎ የሾሞው ጀነራል ተፈራ ማሞ ፍሺቱን ኦሮሙማው አብይን በመቃወም ወደ ጫካ ገብቶ ፋኖን የተቀላቀለው ተፈራ ወደ ጫካ ከገባ ወዲህ ግን ዝምታውን መርጦ ባለው ያዋጊና የሽምቅ ልምድ ፋኖዎቹን ከማደራጀት ይልቅ ፤ ቃለ መጠይቅ በማደረግ ለትችት እየተጋለጠ ነው፡፡

 ተቺውም እኔው ነኝ (መናለባት ሌሎችም ይኖራሉ)፡፡

ስለዚህም የሚቀርቡት ሰዎች የን ምክርና ትችን ቢያደርሱለት ለትግሉና ለራሱ ላለው ክብር ጠቃሚ የሚሆነው እዛም እዚህም እየመጣ በማያውቅበት የፖለቲካ ነገር ባይነካካ መልካም ነው፡፡

አሁን ካንድ ሳዓት በፊት ዮ_ቱብ ከፍቼ ስዳሥስ ፤ ካሁን በፊት ሻለቃ ዳዊት “የመሰረትናትን አገር ለማን ጥለን ነው የምንደው?” ብሎ መልስ የሰጣት “አማራ የራሱን አገር መመስረት አለበት” እያለች ስትጠይቅ የነበረች አንዲት ምስኪን ወጣት የምታዘጋጀው Amhara News Broadcasting Center ABC TV Amhara በሚባል ‘ሚዲያ’ ትንግርቱ ለሚባል ቃለ መጠይቅ አዘጋጅ ቀርቦ ተፈራ ማሞ የሰጠውን ቃለ መጠይቅ ሳዳምጥ ከሰጣቸው መልሶቹ አንዳንዶቹ አስደምመውኛል፡፡

ሁለት ነገሮች ልበል፡

አንዱ ምክር ነው፤ ላው ትችት ነው፡፡

በምክር ልጀምር፡፡

ወደ ጫካ የገባኸው በቅርቡ ስለሆነ ሁኔታዎችን አጥንተህ ነገሮች ሰከን እስኪሉ ድረስ እራስህንም በምታውቅበት የውግያ አመራር ተመቻችቶልህ ስትቀመጥ ያኔ በሙሉ እውቀትና ሓላፊነት ለምትሰጣቸው ቃለ መጠይቆች ምናልባትም ቢያስወቅስህም ተጨባጭ ነገሮች ማቅረብ ስለመትችል ሓላፊነቱን ትወስዳለህ (ሙሉውን መረጃ ይኖራሃልና) አሁን የመትሰጣቸው መልሶች ግን (ለመሳሌ ስለ አሰግድ ጠላት እጅ መውደቅ (መማረክ) ወይንም እጅ መስጠት ፤ ያገኘኸው ከሁለተኛ መረጃ እንጂ ከራስህ የእዝ አመራር ሰላለሆነ ራስህ መሪ ስትሆን (ወታደራዊ ጠቅላይ መሪነት ይገባሃልና) ራስህ በሁኔታው ይገባህበት በወቅቱ የራዲዮ/ ስልክ/ ግንኙነት ከአሰግድ ጋር ኖሮህ ቢኖር ኖሮ ተጨባጩን ስታውቅ እንጂ (የአሰገድ ቡድን ሲጠየቁ መልሳቸው እናጣራለን አጣርተን እንነግራችለን ነው እሚሉት) ፤ በሚሉበት ሁኔታ አንተ መጥተህ ስለ አሰግድ የሰጠኸው ግን የቡድኑ አባል ካልሆንክ በቀር አብረውት ከነበሩት ሰዎች ሰማሁ (ከሁለተኛ ሰው እንጂ ቀጥተኛ ተሳትፎ ባልነበረህ) ሰማሁ፤አግኝቻቸው እጁ አለሰጠም ብለውኛል የሚል የብለውኛል መልስ መስጠት አልነበረብህም፡፡ ያመንካቸው መረጃዎችህስ እጅ ሰጡ ሲባሉስ ሰዎቹ ተታኩሰው ነበር ያመለጡት? አሰግድስ ከላሸኑየት አደረገው? ያየነው ያረጀ ሽጉጡና የሻገቱ 7 (6) የሚሆኑ አሮ ጥይቶች ናቸው) ሰለዚህ ከእንደዚህ ያለ አወዛጋቢ ባትገባ ይመረጣል፡፡

በተጨማሪ አሁን ያለው ፋኖ ወስጥ ያለው እጅግ አስጊ የርስ በርስ በደም መፈላለግ ባለው ክስተት ሁኔታዎች እሰኪረጉ ድረስ ወሰጥ ለwስጥ የሚሰራውን አደረጃጀት እየሰራህ ዝምታን መርጠህ የብረት ትግሉን ብታካሂድ መልካም የሆናል እንጂ <<ከውጭ አገር እንደሚራገበው አይደለም> ማለት መረጃው የለህም ማለት ነው ወይንም ብስለቱ የለህም ማለት ነው፡፡

አሁን ወደ ሰጠኸው ቃለ መጠይቅ ልግባ፡

1)            የምታምነው ሚዲያ Amhara News Broadcasting Center ABC TV እንጂ ሎችን እንደማታምን

2)           አሁን ያለው የፋኖ በደም የመፈላለግ አለመጣጣም አሳነሰሀ ማየትህ

3)           ምርኮኛ ሰለሚለው ቃል ያለህ ግንዛ

 

በ1ኛው ልጀምር፦

ትንግርቱ የተባለው የፕሮገራሙ አዘጋጅ ሲጠይቅህ እንዲህ ብለሃል፦

 

ትንግርቱ፦ “ወደ ፋኖ ከተቀላቀልክ ወዲህ ቃለ መጥይቅ ለማድረግ ይህ የመጀመሪያህ መሆኑና

Amhara News Broadcasting Center መርጥኸው ትናንት እንደነገረከኝ ነው ወደኛ መምጣህ  የገለጽከው፡፡ ጀነራል ለምን የአማራን በሮደካሰትን እንደመረጥክ ብትነግረኝ..?

የተፈራ መልስ፡

አመሰግናለሁ! ኤ ቢ ሲ አማራ ብሮድካስት ቲ ቪ የመረጥኩበት መክንያት ያው መልእክቱን “ለሁሉም ያደርሳል” ከሚል ነው፤ ሌላ አይደለም፡፡ አጋጣሚ ስንከታተለው ሰለነበር መልእክቱን በዚህ ደረጃ  ያሰተላልፋል በሚል ነው፡፡

ትንግርቱ፤ አመሰገናለሁ ወደ እኛ ስለመጣህ! የላል፡፡

የትንግርቱ አነጋገር ፤ልጥቀስ << መርጠኸው ትናንት እንደነገረከኝ ነው ወደኛ መምጣህ  የገለጽከው>> ነው ትንግርቱ የሚለው፡፡ ለቃለ ምልልሱ “ስልክ ደዋዩ” ወይንም “ፈላጊው” ተፈራ ራሱ እንደሆነ ከጥቀሱ ያመላክታል፡፡ ካልሆነ <<ጠይቀንህ ትብብርህ ሰላሳየኸን እናመሰግናለን>> ነው የሚዲያው ሕግ እንጂ ፤ማንኛውንም እንግዳ በተቀሩት ሚዲያዎች እመነት ከሌለው በቀር “ለምን መረጥከን?” የሚል ሰመቼ አላውቅም፡፡

ያንን እንዲህ እንዳለ እንግዲህ ተፈራ ማሞ ይህንን ጣቢያ የመረጠበት ምክያት ሲገልጽ ደግሞ  “የጀነራሉ መልእክት የተቀሩት ሌሎቹ  ጣቢያዎች ለሁሉም አያዳርሱትም” የሚል እምነት ሰላለው “ለሁሉም ያዳርሳል” የሚል እምነት ያሳደረበትን ይህንን ጣቢያ መምረጡ የሚገርም ሆኖ አግኝቸዋለሁ፡፡ (ለዚህ ነው ዝምታን ምረጥ የምለው)

ሌሎቹ የተፍራን መልእክት ሳያዳርሱት ሊያፍኑት ሰለሰጋ ወይስ ስርጭታቸው አቅም ስፋት ሰለሌላቸው? በስርጭት ስፋትና ተደራሽነት ከሆነም  ይህ  ጣቢያ እጅግ ደካማ ከሚባሉት ሚዲያ የሚሰለፍ ነው፡፡ በ 20 ሰዓት ውስጥ 385 ሰው ብቻ ነው ቃለ መጠይቁን ያደመጠው፡፡ የአድማጭ ብዛት ደካማ ከሚባሉት ነው፡፡ ታዲያ ጀነራሉ ይህንን ደካማ ሚዲያ መርጦ ሌሎቹ ለሁሉም አያስተላልፉትም የሚል እመነቱ ማሰረጃውና ምክንያቱ ምን ይሆን?

የማዳረስ ብቃት የላቸውም ለሚላቸው የተቀሩት እልፍ አእላፍ ሚዲያዎች በምን አይኑ ደፍሮ ይሆን እነሱ ጋር ቀርቦ ለወደፊቱ ቃለ መጠይቅ የሚያደርገው?

2) አሁን ያለው የፋኖ አለመጣጣም ጠያቂው ሲጠይቅ፤ እንዲህ የላል፡

 “ሰሞኑን በሆነው ነገረ ያላዘነ ያልታመመ የለም፡ ምን ትላለህ? ምን እየተሰራ ነው?     

ተፈራ ማሞ፡

አሁን አንድ የጋራ ጠላታችን የምንለውን ለመምታት ወታደራዊ እዙን ከላይ እሰከታች እንድ የሚሆንበትን፤ አደረጃጀት የታጠቀ አቋም በወታደራዊ ውጊያ አንድ ዓይነት አስተሳሰብ የውጊያ አካሄዳችን እንዴት መሆን አለበት የሚሉ በዚህ ዙርያ ነው እንግዲህ በሁሉም ቦታ ለመነጋገር እየሞከርን ያለነው፡፡ አሁን ዋነኛው የትኩረት ማእከሉ አንድ ሆነን ይህን ጠላታችን ከዚህ ነቅለን መጣል አለብን በሚል አዙሪት ነው እየተነጋገረን ያለ ነው፡፡ሁሉም ይደግፈዋል፤ አሁን ያለው ሁኔታ በዛው እየሄድን ነው፡፡ ብዙም በከፋ መንገድ አላየሁትም፡ከውጭ እንደሚራገበው አይደለም፡፡>>

ይላል ጀነራል ተፈራ ማሞ፡፡

ጀነራሉ ወይስ እ ነኝ ጫካ ውስጥ ያለነው? እ  ውጭ አገር ሆኜ የምሰማውና በቪዲዮ የማየው <<የፋኖዎቹ የትኩረት ማእከሉ አንድ ሆነው ጠላታቸውን ከአካባቢያቸው ነቅለው መጣል እንዳለባቸው በሚል አዙሪት ሳይሆን እየተነጋገሩ ያሉት፡፡ አንድ መሆኑን ቀርቶ ዘመነ የተባለው “የጫካ ዲገላ” ኮሎል ጌታሁን የተባለውን ጎጃም ወስጥ የሚንቀሳቀስ የፋኖ አንድ ክንፍ ዋና መሪ እስክንድር ነጋን ስለመረጠ፤  “አንቃችሁ ይዛችሁ አምጡልኝ ብሎ ብዙ ጦር ልኮ ለመውጋት የኮሎሉ ትውልድ ቦታ ሕዝብ የክተት ጡሩምባ ነፍቶ ልጃችንን አናስነካም ብሎ የጎጃሙ ዲገላ (ዘመነ ካሴ) ጦር ተመልሶ ወደ መጣበት ቦታው መመለሱና ቀውሱ በዲገላው ምክንያት ወደ ደም መፈላለግ እያመራ መሆኑን ከኮሎሉ አንደበት በቃለ ምልልስ ስምተናል፡፡

 ይህ የሆነው ጀነራል ተፈራ  ከሚለው <<የትኩረት ማእከሉ አንድ ሆነን ይህን ጠላታችን ከዚህ ነቅለን መጣል አለብን በሚል አዙሪት ነው እየተነጋገረን ያለ ነው፡፡በዛው እየሄድን ነው፡፡>> እያለን ባለው ሰዓትና ቀን ነው ይህ እየሆነ ያለው፡፡

ይባስ ብሎ ሕዝብን ወደ ማዳማት የሚጭር አወራጃዊና ወረዳዊ ገጭትና መፈላለግ የዲገላው አደገኛ  አጉራ ዘለልነትና ጋጠወጥነትን እየባሰ የመጣውን “አንዱን ላንዱ” የመጠፋፋት ከፈተኛ ሙቀትን ነው፡ ጀነራሉ  <<ብዙም በከፋ መንገድ አላየሁትምከውጭ እንደሚራገበው አይደለም፡>> እያለን ያለው፡፡

ለዚህ ነው እባክህን ጀነራል ዝምታን መርጠህ ያዋጊ የበላይ ጦር አዛዥ ቦታውን ስትይዝ (ይገባሃልና) ያ በሙሉ ልቦና ያለውን ነገር ትነግረናለህ በየ የምመክረው፡፡ እስከዛው ድረስ ለእነ እስክንድርንና የመሳሰሉ ሌሎች በፖለቲካውና ግንኙነትን ልምድ ላላቸው ለበሰሉ ፖለቲከኞቹ  እንዲተቹበት ተወው፡፡ እነሱ ይወቀሱበት፡፡ አንተ ማድረግ ያለብህን ስራ እንጂ “ቀወሱን አሳንሰህ በክፍት አላየውምከውጭ እንደሚራገበው አይደለም” ማለት ያስገምታሃል፡፡

(3ኛ) ምርኮኛ ሰለሚለው ቃል ያለህ ግንዛቤ

ጀነራል ተፈራ ሰለ አሰግድ መኮንን እንዲህ ይላል፡

<እጅ ሰጠ የተባለው ውሸት ነው> ይልና  ምክንያቱንም ሲገልጽ፤

<<ወደ መርሃ ቤቴ ለመሻገር ሲል ነው ኮመቦልቻ ላይ ይህ ሁታ የገጠመው” ይላል ጀ/ ተፈራ፡፡

እንዲህም ይላል፡፡

<< አሁን እኮ መማረክ ውርደት አይደለም በነሱ ቤት፡፡ መማረክ እንደ ውርደት አያዩትም (የመንግሥት/አብይ የሚያዘው ወታደርን ነው እንዲህ እያለ ያለው) ጥዋትም ማታም እየተማረከ ነው፡፡ ጀነራሎቹ ሁለት ሦስት ጊዜ የተማረኩ ናቸው....።>>

 በማለት ወታደሮቹ ሲማረኩ “ውርደት” እያለ ሲጠራው “አሰግድ መኮንን”  ተማረከ የሚል ቃል ላለመጠቀም “ይህ ሁታ ገጠመው፡፡” በሚል በአዲሰ አማርኛ ለመግለጽ ይሞክራል፡፡

ወታደሮቹ ሲማረኩ ውርደት ሲሆን አዋጊው አለቃ አሰግድ ሲማረክ ግን “አርበኛ” አሰግድ እያለ ይጠራዋል፡፡ መማርክ የሚል  አማርኛ ቃል ወያነ ከመጣ ወዲህ ወይንም ተፈራ የታገለለትን ብ አ ዲን ከመጣ ወዲህ ያላውቅነው አዲስ ትርጉም የተሰጠው ከሆነ አላውቅም እንጂ ፤ ራሱን ላለመሰዋት መርጦ “እጅህን አንሳ” ሲባል እጁን አንስቶ ከነ ሽጉጡ የሚማረክ ተማራኪ “መርኮኛ” የባላል ፡፡ ትልቅ ጦርን የሚመራ መሪ ሽጉጡን ይጠጣል እንጂ እጅ አይሰጥም!

በተፈራ አማርኛ ግን አሰግድ ሲማረክ “አርበኛ” ይለዋል፤ ወታደሮቹና አዋጊ ባለ ማእረጎች ሲማረኩ ደግሞ “ወርደት የሚከናነቡ” የሚል አሰገራሚ ትርጉም አስደምጦናል፡፡ 

በወሎዎቹ አማርኛ ትርጉም  መማረክ “ለወገን” ሲሆን “አርበኛ” ፡ ጠላት ሲማረክ ግን “ሃፍረት የሚያከናንብ ውርደት ነው” የሚባል ከሆነ ንገሩኝ፡ ካልሆነ የጀነራል ተፈራ ማሞ የሙርኮኛነት ትርጉም ግብዝ አማርኛ ወይስ ወገንተኛ?

ጌታቸው ረዳ Ethiopian Semay