Wednesday, December 24, 2008

ከወያኔ የገበና ፋይል-ክፍል 2 ካለፈዉ የቀጠለ

ከወያኔ የገበና ፋይል-ክፍል 2 ካለፈዉ የቀጠለ የወያኔዉ ጀነራል ሓየሎም አርአያ ግድያ እና የአብዱል መጂድ የግድያ ሙከራ በመቶ አለቃ አበረ አዳሙ መኮንን በፖሊስ የሞያ እይታቸዉ የደረሱበት ድምዳሜ፦ ጌታቸዉ ረዳ www.Ethiopiansemay.blogspot.com
ባለፈዉ ሰሞን ከመቶ አለቃ አበረ አዳሙ መኮንን የተገኘ ቃለ መጠይቅ የመጀመሪያዉ ክፍል የወያኔ ያገሪቱ ከፍተኛ የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነረሮች፤ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽነሮች እና የአገሪቱ የደህንነት ሃለፊዎች እና የወንጀል መከላለክል እና የምርመራ ክፍል ሹሞች ከተራ ሌቦች እና ከግምጃ ቤት ዘበጆች ጋር በመመሳጠር ሕዝቡን እንዴት ይዘርፉት እና ያሽሸብሩት እንደንበር፤- እንዲሁም ወያኔ የመንግሥስልጣነ መንበር ከሕዝብ ነጥቆ የወንጀል መከላከል እና የምርመራዉ ሕግ ክፍል በ ቁጥጥሩ አድርጎ፤ ለግል ፖለቲካና ለማህበራዊ ጠቀሜታዉ እንዴት ይጠቀምባቸዉ እንደነበር አንብበናል። እነ ተስፋይ አብርሃ እና እነ ረዳኢ ገብረአነንያ የተባሉት የወያኔ ፖሊስ ኮሚሽነሮች እና ህዝብ ደህንነት ባለስልጣኖች በስማቸዉ የተመዘገዉን መሳሪያ ሌቦች እና ዘራፊ አሸባሪዎችን እያስታጠቁ ዝረፍያዉ እና ሰላማዊዉን ሕዝብ እንዴት ያሽሸብሩት እንደነበር አይተናል።ይህ ሁሉ ሲሆን -አንዳቸዉም እንኳ ለፍርድ አልቀረቡም። እዛዉ ክፍል እያለን፤ በይቀጥላል በአዳሪ ተሰናብተን ነበር።
ለቀጣዩ አቀርብላችሗለሁ ብየ የነበረዉን የአገሪቱ የመንገድ ሥራ ባለስልጣን መ/ቤት ባለስልጣኖች በተራ ዝርፍያ እና ንብረቶችን ማለትም ቡልደዘሮች፤ ትራክተሮች፤ ትላልቅ እና ትናንሽ የመንገድ እና የህንጻ አጋዥ መኪናዎች የመሳሰሉት በእነ መለስ ዜናዊ ትዕዛዝ በእነ አቶ ተስፋየ ናሁ ሰናይ (የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን ዋና ሹም) ተባባሪነት ዕቃዎቹ ከዉጭ አገር በግዢ ወይንም በመሳሰሉት ዕርዳታ የተገኙ ንበረቶች በመርከብ ተጭነዉ ከጅቡቲ ወደብ ላይ ተመዝግበዉ እንዳረፉ ፤- ከጅቡቲ ግምጃ ቤት በቀጥታ ወደ ትግራይ አንዲተላለፉ እንዴት ይደረግ እንደነበረ ሙሉ ታሪኩ እና ነገር ግን ቡልደዞሮቹ እና ትራክተሮች እና የመሳሰሉት ከባድ ንብረቶች ከመነሻዉ ለግዢ ወይንም በ እርዳታ መጠ ይቅ ሲመዘገቡ በሌሎች ክልሎች ስም የግዢ ቅጽ ይሞላ እንደነበር እና፤ ከተገዙ በሗላ ግን በቀጥታ ወደ ትግራይ እንዲመዘገቡ ተደርጎ እንዴት ወደ ትግራይ ይተላለፉ እንደነበር እና እነዚህ ሰዎች ያገሪቱ ትላልቅ መስሪያቤቶች እና የሕግ ክፍሎች ለግል መጠቀሚያ ያደርጉት የበነበረዉን የማጭበርበሪያ ስልቶችን የገለጹበት ክፍል ነበር።
በአጋጣሚ ቴፑ የት እንዳኖርኩት ማግኘት ስላልቻልኩ ላቀርበዉ አልቻልኩም። ለዚህም ይቅርታ እጠይቃለሁ። ቴፑ ያላችሁ ሰዎች ብትልኩልኝ ቀሪዉን ማስነበብ ይቻላል።ካገኘሁት ለወደፊቱ አስነብባችሗለሁ። እስከዛዉ በእዛዉ ፈንታ ያገኘሁት ሦስተኛዉን ክፍል አቀርብላችሗለሁ።
አሁን በቀጥታ ከላይ በርዕሱ ወደ ተጠቀሱት ሁለት አበይት ጉዳዮች የመቶ አለቃዉ በሞያቸዉ የደረሱበት መደምደሚያ ለጥያቄዉ የሰጡትን መልስ እና ሌላዉ በርዕሱ መርዘም ምክንያት ያልጠቀስኩት፦ ድሮ የወያኔ ታጋዮች ነበሩ - በሗላ ወያኔ ራሱ “ሞቡላይዘሽን/መልሶ ማቋቋም፤- የሚለዉን የመልሶ ማቋቋሚያ መመሪያዉን/ፕሮጀክቱን ሲያካሂድ የተከናወነዉን አድልዎ እና አናስፈጽምም በሚሉ አንዳንድ በአዲስ አበባ ፖሊስ ጽ/ቤቶች እና በአዲስ አበባ መስተዳድር (ከተፈራ ዋልዋ ጋር) የተደረጉትን ጠቦች እንመለከታለን። ሦስቱም ጉዳዮች እነሆ።
ጥያቄ- ከሙያስ አኳያ ወ ያኔ በተጨባጭ አብዱል መጂድን ለመግደል ሙከራ አደረገ ለማለት ነዉ የፈለጉት? “..ከሙያ አንጻር መመለስ ይቻላል ይህነን ጥያቄ ። ወያኔ አብዱል መጂድን ለመግደል ሙከራ አድርጓል አላደረገም ከማለቴ በፊት እስቲ አንዳንድ ነገሮችን ማለት ልቻል። ወንጀል ሲፈጸም ወምጀል መንስኤ የሚባል ነገር አለ። በወንጀል ተመራማሪ ሊቃዉንቶች መሰረት የወነጀል ሦስት የወንጀል መንስኤዎች አሉ። አንዱ ማህበራዊ ጉዳይ ነዉ፤ሌላዉ ኢኮኖሚአዊ ጉዳይ ነዉ።ሌላዉ ደግሞ ፖለቲካዊ ጉዳይ ነዉ። ከነዚህ ሦስቱ ተተቀሱት ነገሮች ዉች አስካሁን ድረስ ሌላ የታወቁ መንሲኤዎች የሉም። ወደ አበዱል መጂድ ሑሴን የግድአ ሙከራ ስንመጣ፦በቀትታ ሙከራዉ “ፖለቲካዊ ነዉ”። አብዱል መጂስ ሑሴንን በማህበራዊ ጉዳኢ ሚፈልጋቸዉ ሰዉ የለም፦ “የተጣሉት ጎረቤት የላቸዉም፤ ወይም ያደረጉት የእምነት ማጉደል ወንጀል የለም”። አብዱል መጂድ ሚኒስቴር ነበሩ። በቀጥታ የመግደል ሙከራዉ ሙከራዉ በቀትታ የተያያዘዉ ከፖቲካ ዩዳይ ነዉ።
ምናልባት እሳቸዉን በመግደል ወይም በእርሳቸዉ ላይ የመግደል ሙከራ በማድረግ ወያኔ ሊያገኘዉ የፈለገዉ ፖለቲካዊ ጠቀሜታ ነበረ። ስለዚህም ይህነን ጉዳይ ያደረገዉ ራሱ ወያኔ ነዉ የሚል ብዙዎቻችን በተለይም በሙያዉ ላይ የበሰሉ ከእኔም በላይ አስከ ዉጭ አገር ድረስ ሄደዉ የተማሩ ባለሙያዎች በዚህ ጉዳይ ተነጋግረን የደረስንበት ድምዳሜ አለ። ለጊዜዉ ስማቸዉን መጥቀሱ ስለማልፈልግ ነዉ። በቀጥታ በአብዱል መጂድ ላይ የተፈጸመ የመግደል ሙከራ በራሱ በኢሕአዴግ ነዉ። ምክንያቱም ኢሕአዴግ ባይሆን ኖሮ እነዚህ ሰዎች ማምለጥ አይችሉም። ቅድም በጠቀስኩልህ ቦታ መኪና አስቁመን እዛዉ ፖሊስ እያለ፤ ያዉም የአብዱል መጂድ አጋሮች አብረዉ እያሉ ቢያንስ አንድ ሰዉ እንኳ እንዲመታ አልተሞከረም። ይሄ በጣም ፤በረቀቀ መንገድ እራሱ ወያኔ ነዉ የፈጸመዉ የሚል ነዉ በሙያችን የደመደምነዉ። እኔ ብቻ ሳልሆን ከእኔ በላይ በምርመራ ስራ ለ10 ዓመታት ከዛም በላይ ለሰራ ዉጭም አገር ሄደዉ የዉጭ አገር የአመራመር ስርዓት፤ትምርት እና ስልት ብዙ ልምድ ካላቸዉ መኮንኖች ጋር አብረን ይሄነን ጉዳይ አንስተን ነበር ስንወያይ የነበረዉ። ስለዚህ በአብደል መጂድ ሑሴን ላይ የተደረገዉ የመግደል ሙካራ እራሱ ወያኔ ነዉ የሚል ነዉ በእኛ በሙያችን ግንዛቤ ላይ የደረስንበት።
ከዚህ ሌላ ወያኔ በአመራመር እና በፍርድ አፈጻጸም ለፖለቲካ መጠቀሚያዉ እንዴት እንደሚያዉለዉ ልጥቀስልህ። ለምሳሌ ጀሚል ያሲን የተባለ ጀኔራል ሓየሎምን ገድሏል።በእርግጥም ገድሏል። ያ የተረጋገጠ ነገር ነዉ። አገዳደሉ እንዴት ነበረ? በጀሚል ያሲን የተሰጠዉ ፍርድ ዉሳኔወ እና ጀሚል ያሲን ጀኔራል ሓየሎም ለምን እንደገደለዉ እንዴት እንደገደለዉ እና የነበረዉ የወንጀል አፈጻጸም ዘዴዉ፤ ከተሰጠዉ የፍርድ አፈጻጸም ጋር በፍጹም የማይጣጣም ነበር። ብዙ ባለሙያዎች አስተያየታቸዉን ይሰጡ ነበር።
“አገዳደሉ እንዴት ነበር?” በመሰረቱ እኛም ወደ እዛዉ እንድንጠጋ አልተፈለገም። ለምሳሌ መቶ አለቃ አድያምሰገድ የሚባል ነበር ( ለማስታወሳችሁ -ከጌታቸዉ ረዳ- መቶ አለቃ በሗላ ሻምበል አድያም ሰገድ የተባለዉ ትዉልዱ አክሱም ሆኖ በቀ/ሃይለስላሴ ዘመነ መንገሥት ጀምሮ በ ወህኒቤቶች እና በፖሊስ ሰራዊት ያገለገለ ነበር በሗላም በደርግ እንዲሁም ም በወያኔዉ ዘመን ያዲስ አበባ ፖሊስ የምርመራ ሹም ነበር። ወያኔ ከተጠቀመበት በሗላ ሌሎችን እንዳደደርገዉ ሁሉ ‘ከደርግ ጋር የተየያዘ ወንጀል ፈልስፎ በሃሰት ከስሶ ለአመታት አስሮ መቀሌ ወህኒ እያሰቃየዉ እስካሁን ድረስ እሮሮዉን እያአሰማ መቀሌ ወህኒ /እስር ቤት የሚገኝ ነዉ) - በእዛዉ ጊዜ የአዲስ አበባ ፖሊስ የወንጀል መከላከል እና መርመራ ክፍል ሃላፊ የነበረዉ Even እሱንም እንኳ ወደ እዛዉ እንዲጠጋ አላደረጉትም። ጀሚል ያሲን ጀኔራል ሓለፎም አርአያን እንዴት እንደገደለዉ ለማጣራት የክልሉ ፓሊስ ኮሚሽኑ ረዳት ኮሚሽነር የነበረዉ መቶ አለቃ አድያም-ሰገድ እንኳ ወደዛዉ እንዲጠጋ አልተፈቀደለትም። በመጨረሻ እንዲያዉም አራንሺ ገብረተኽለ ራሱም እንዳይጠጋ ተደርጓል። አራንሺ ገብረተኽለ የክለልሉ ፖሊስ ኮሚሽነር የነበረ ነዉ። እንዲያዉም ከኮሚሽነርነቱ ያወረዱት ከዛ ጋር በተያያዘ ምክንያት ነዉ። እነዚህ ሰዎች ብያንስ ሓየሎም አርአያ በጀሚል ያሲን እንዴት እንደተገደለ First hand information ቀጥተኛ የሆነ ማስረጃ ነበራቸዉ። ያ ቀጥተኛ “ፈረስት ሃንድ ኢንፎርሜሽን” ያልተበረዘ ያልተከለሰ ማስረጃ ስለነበራቸዉ፤ያንን እንዳትተነፍሱ ተብለዉ ከሃላፊነታቸዉም ወርደዉ ምርመራዉን በቀጥታ ወደ “ተስፋይ አብርሃ ” ቢሮ ነዉ የተወሰደዉ።
ግልጽ ነዉ ከአካባቢዉ የሰማነዉ ፤-- የያሲን እና …. (በደምብ ያልተሰማ የሰዉ ስም ይጠቅሳሉ) መጠጥ ቤት ነበሩ፦ በመጠጠጥ አልተግባቡም ፤- ተነጋገሩ-፤ከዚያም ሓየሎም አርአያ ተነስቶ ጀሚል ያሲንን መታዉ፤ “በካልቾም በጥፊም”- ከዚያ በሗላ የስካር መንፈስ ነበር በሁለቱም ላይ። የማይካድ ነዉ። ስካራቸዉ እዚያዉ አብረዉ የነበሩት ሰዎች የሚያዉቁት ጉዳይ ነዉ።
አንድ ወንድ ልጅ “በጥፊ ሲመታ” “በካልቺ ሲመታ” ራሱን ለመከላከል የሚወስደዉ እርምጃ አለ። ሕጉም ይላል። ራስን ለመከላከል። አልሞት ባይ ተጋዳይ ነዉ የሚለዉ።ሕጉ አለ እኮ! ሕጉን ያሰስተማሩኝ እኮ ሌላ አይደለም፦ ሕጉን ያስተማሩኝ- ዛሬ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽነር የሆኑት ሻለቃ ፈቃዱ ቶሌራ ናቸዉ። እሳቸዉ ይሄንን ቢጠየቁ ምን መልስ እንደሚሰጡ አላዉቅም! ዛሬ ኮሚሽነር ሆነዋል ሲባል ሰምቻለሁኝ። እኔ እያለሁ አልነበሩም፡ ራሰቸዉ ከስርአቱ ጋር ችግር ነበረባቸዉ፦ ባንድ ወቅት ላይ”። ዛሬ ምን ተገኝቶ ነዉ ኮሚሽነር የሆኑት እንግዲህ አሳቸዉ የሚመልስት የሚያዉቁት ነዉ የሚሆነዉ።
ስለዚህ በእንደዚህ ዓይነት የተፈጸመን ወንጀል፤ እንደ ግፍ አገዳደል ተብሎ በጀሚል ያሲን ላይ የስቅላት ብያኔ ሲበየን ያላዘነ ፖሊስ ያላዘነ ዳኛ አልነበረም። የፍትህ ሰዉ/አካል አቃቤ ሕጎች ፍረድ ቤቶች ራሳቸዉ ሳይቀር! እንዴት በስካር መንፈስ የተፈጸመን ወንጀል ወደ ፖለቲካ ይላከካል ?……..
የቅጣት ማቅለያ እና የቅጣት ማክበጃ የሚባል አንቀጽ አለ። ለጀሚል ያሲን ሊጠቀስለት የሚችል ሕግ “የቅጣት ማቅለያ” ነዉ። ሰዉ ገድሏል ወይ? በእርግጥ! ወንጀል ፈጽሟል ወይ? አዎ ተፈጽሟል! ለምን ተፈጸመ ለሚለዉ እንነጋገርበት። ጀኔራል ሓየሎም አርያ እና ጀሚል ያሲን በወዳጅነት የተሳሰሩ ሰዎች ነበሩ ወይ? ጠብ ነበራቸዉ ወይ? ጀሚል ያሲን ሓየሎም አርአያን ለመግደል ሆን ብሎ ነዉ ወይ? -ተዘጋጅቶ ነዉ ወይ? አስቦ ነዉ ወይ? እነዚህ ነጥቦች ሁሉ እዛ የሕግ ክፍል ዉስጥ ስንገባ አይሟሉም።
አንድ ወንጀል በትከክል ተፈጽማል ለማለት እና ያሰዉየ በትከክል ሆን ብሎ መፈጸሙን ለማረጋገጥ እነዚህ ጥያቄዎች መመለስ አለባቸዉ። አቶ ጀሚል ያሲን ሆን ብለዉ ተዘጋጅተዉ ነዉ ወይ ሄደዉ ሓየሎም አርአያን የገደሉት? በቂም በቀል ነዉ ወይ? እነዚህ ሁሉ የሉም። ምንም ቂም አልነበራቸዉም። ጠጥተዋል፤ ሁለቱም ሰክረዋል። ሁለቱም ከጠጡ ደግሞ መስከር አለ።መስከር ካለ ደግሞ -የሰዉ ሕሊናዉ ትከክል አልነበረም ማለት ነዉ።
የሃሳብ ክፍል የሚባል የአይምሮ ክፍል አለ። ወንጀል ለመፈጸም ሦስት ነገሮች መሟላት አለባቸዉ የሚል የሕግ ደፍኒሽን definition /ትርጉም አለ። አንደኛዉ የሃሳብ ክፍል ነዉ -“እእምሮአችን ማለት ነዉ”” አንድ ሰዉ ወንጀል ፈጽሟል ለማለት አእምሮዉ ጤነኛ መሆን አለበት። የሃሳብ ክፍል የሚባለዉ ይሄ ነዉ። ሁለተኛ የህግ ክፍል የሚባል አለ። አታድርግ ወይንም አድርግ የሚል ድንጋጌ መኖር አለበት።ያ ድንጋጌ ተጥሷል ወይ? ያ መታየት አለበት። ሦስተኛዉ “የድርጊት ክፍል” የሚባል አለ። ድረጊቱ “Action” ኑ “ድረጊቱ ተፈጽሟል ወይ?” ተፈጽሟል ማለት አለበት። በነዚህ ሦስት ነገሮች በጀኔራል ሓየሎም የተፈጸመዉ አገዳደል ብንሄድባቸዉ፤-ሕግ አለ? አዎ ሕግ አለ።- አትግደል የሚል ሕግ አለ። ነገር ግን “ሕግ” ተጥሷል። ምክንያቱም “ግድያ ተፈጽሟል”። አታድርግ የሚል ክፍል ደግሞ አለ። ድረጊረት ተደርጓል። ምክንያቱም የድርጊቱ አፈጻጸም በጥይት ግድያ ተደርጓል። ይሄ አክሽኑ ነዉ -ድርጊቱ ማለት ነዉ።
ወደ ሃሰብ ክፍሉ ወደ ሦስተኛዉ ክፍል ስንመጣ ነዉ እንግዲህ የምንከራከረዉ። አቶ ያሲን ጀሚል ጤነኛ ናቸዉ? አዎ ጤነኛ ናቸዉ።በወቅቱ ግን ጠጥተዋል። አንድ ሰዉ ጠጥቶ ወይ ይሄ ድራግ/አደንዛዥ እጽ የሚባለዉ ወስዶ ወይም በደም ፍላት ተነስቶ ደሙን የሚያፈላ ነገር ከተፈጸመበት Cause and Effect “መንስኤ እና ዉጤት” የሚባል ነገር አለ። እነዚያ ነገሮች በሕግ ዉስጥ ሲተነተኑ የሕግ ባለሞያዎች ከኔ ይበልጥ ይተነትኑታል። እነዚያ ነገሮች በአቶ ጀሚል ያሲን አእምሮ ተሟልተዉ ነበሩ ዎይ?የሚለዉ የሕግ ጥያቄ ስንመልስ - አቶ ጀሚል ያሲን ጠጥተዉ ነበር። ሐየሎም አርአያም ጠጥተዋል።አንድ ሰዉ ሞቅታ ላይ ነዉ፤መጠጡ ሰዉየዉን ተቆጣጥሮታል- በተጨማሪም በላዩ ላይ ጥፊ ሲጨምርለት፤ካልሲ ሲጨምርለት ከመጠጡ ላይ በባሰ እንዲናደድ፤ደሙ የባሰ እንዲፈላ የሚያደርግ ነገር ነዉ። በዚህ ሁኔታ የተነሳ አንድ ሰዉ ወንጀል ቢፈጽም፦ ይህ ሰዉ ወንጀሉ ለምን ፈጸመዉ ወደ ሚል እንመጣለን። በደም ፍላት እና በስካር መንፈስ። በደም ፍላት እና በመጠጥ መንፈስ ወደ እሚል ከመጣን ደግሞ ወደ ሕግ አንቀጽ ስንሄድ ወደ ቅጣት ማጥርያ ነዉ የመንሄደዉ። ያ የቅጣት ማጥሪያ ሲጠቀስ ደግሞ “ሰዉ የገደለ ሰዉ ከ5 ዓመት አስከ ሞት ነዉ እሚለዉ ገደቡ”። 5/22 5/26 ወዘተ የሚሉ ህጎች አሉ (Actualy አሁን አላስታዉሳቸዉም የህግ አንቀጾቹን ቁጥሮቹን- የሕግ ባለ ሞያዎች ያዉቁታል ይሄንን) የትኛዉ አንቀጽ ሊያስጠቅስ እንደሚችል የቅጣት ማጥሪያ ጠቅሶ ነዉ በዚህ ሰዉየ ላይ አቃቤ ህግ ክስ ሊመሰርት የሚችለዉ።
በአቶ ጀሚል ያሲን ላይ ግን የተወሰደዉ የህግ አሰጣጥ የህግ ዉሳኔ ሁሉንም ያላገናዘበ ግን ከጀነራል ሓየሎም አርአያ ለወያኔ ወይንም ለስርአቱ አስፈላጊነት ጋር የተያያዘ ነዉ።
እኔ የጀነራል ሓየሎም አርአያ ስም እና ክብር መንካት አልፈልግም። በትግሉ ወቅት ብዙ ነገር አድርገዉ ሊሆኑ ይችላል። አደርገዋልም “ለወያኔ”። ጀግና ሊሆኑ ይችላሉ፡ አሟሟታቸዉ ግን ከነበራቸዉ ክብር እና ከነበራቸዉ ማዕረግ ሲታይ መጠጥ ቤት ሞቱ።ሰዉ ተማትተዉ ነዉ የሞቱት።ሰዉን በጥፊ መትተዋል።ሰዉ በጥፊ መምታት እኮ ሰብአዊ መብት መርገጥ ነዉ።መሳደብም ሰባዊ መብት መርገጥ ነዉ። ትግሉ የታገሉት ደግሞ”ሰብአዊ መብት ለማሰከበር ነዉ የታገልነዉ ነበር ሲሉ የነበረዉ ካድሬዎቻቸዉ”። ከእዛ አንጻር ሲታይ ወያኔ የተጠቀመበትን ጀሚል ያሲንን በመስቀል የቀጣዉ አቀጣጥ ዘዴ ግን አጠያያቂ ነዉ ። ራሱ የጀሚል ያሲን አሰቃቀል-በስቅላት እንዲቀጣ ሲደረግ ጀሚል ያሲን ኤርትራዊ ነዉ ሲባል ነበር የምንሰማዉ። ናቸዉ አይደሉም ‘እኔ የማዉቀዉ ነገር የለም’ እርገጠኛ አይደለሁም። በወያኔ እና በኤርትራ መካከል ግጭት ተፈጥሮ ጦርነት ሊካሄድ ነዉ በሚባልበት ሰዓት ነዉ ጀሚል ያሲንን የሰቀለዉ። ምክር ቤቱ ‘ኤርትራ ወረረን” ብሎ በቴሌቪዥን መግለጫ አወጣ። በሁለተኛዉ ይሁን በሦስተኛዉ ቀን ደግሞ የጀሚል ያሲን በስቅላት የሞት ቅጣት ደግሞ ያ ቴለቪዥን መልሶ ነገረን።
የጀሚል ያሲን ስቅላት ከኤርትራ ወረራ እና ከወያኔ ጦርነት ጋር የሚያያይዘዉ ነገር የለም! ያ ተራ ወንጀል ነዉ!ተራ ወንጀል ነበር! ነብስ ግድያ ነዉ የተፈጸመዉ።ነብስ ግድያ ደግሞ “ማሕበራዊ ነዉ”። ቅድም የጠቀስኳቸዉ ማሕበራዊ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ የወንጀል መንስኤዎች ብየ ከገለጽኳቸዉ ዉስጥ ነዉ። ሌሎች ሰዎች “ፖለቲካዊ” ነዉ ሊሉ ይችላሉ። እኔ በሙያየ የደረስኩበት ግን አፈጻጸሙ አካሄዱ “ሞዳስ ኦፔራስ” የሚባለዉ ግን “ማህበራዊ ነዉ”።መጠጥ ጠጥተህ ከተገዳደልክ “ማሕበራዊ” ነዉ “የወንጀሉ መንሲኤዉ”። የማሕበራዊ ግጭት ነዉ።
ስለዚህ ያ ዓይነት አገዳደል ከአገር መወረር እና ከሉአላዊነት ጋራ አያይዘዉ የትግራይ ሕዝብ ሓየሎም አርአያ ይወድድ ስለነበር፡ እስካሁንም ይወዳቸዋል፡ እኔም አከብራቸዋለሁ፤ ነገር ግን ያንን የትግራይን ሕዝብ ለማነሳሳት፤ ሌላዉንም የኢትዮጵያ የዋህ ሕዝብ ለማነሻሻነት ለመጠቀም “ኤርትራ ባድመን ሲወርር -እኛ ደግሞ እዚህ ጀሚል ያሲንን ሰቀልነዉ” በማለት ለመቀስቀሻነት ነበር የተጠቀሙበት። ይህ ማጭበርበር አስከመቸ ድረስ ነዉ ሕግን እና የፖሊስን ሃይል እየተጠቀሙ ህዝብን ማታለል እና መዋሸት የሚቻለዉ? የሚል የራሳችን ድምዳሜ ደረስን። በሙያችን አዘንን፤ተክዘናል።ምክንያቱም ሕግ ሲረገጥ ይከነክናል፤ያበሳጫል፤ዕረፈት ሰላም ይነሳል። ባጠቃላይ ለባለሞያዎቹ ለኛ ይህ አሰራር የሚያሳየዉ ኢሕአዴግ ያገሪቱን ፖሊስ ሃይል ሕግ እና የወንጀል ምርማራ ዘርፎችን ለመቀስቀሻ ለፕሮፖጋንዳ ህዝብን ‘ሞቢላይዝ’ ለማድረግያ እንዴት በተካነ ጥበብ እንደሚጠቀምበት ለመግለጽ ነበር ይሄነን ለመግለጽ የሞከርኩት።
ጥያቄ፦የመቶ አለቃ አበረ አዳሙ መኮንን- እስኪ የሕግ የበላይነት “Rule of Law” የሚባለዉ እና የሰብአዊ ጉዳዮች ሁንታ በምን አይነት መልኩ ነዉ የሚመለከቱት በሙያዎ አኳያ? ወደ ሚለዉ ጥያቄ በሚቀጥለዉ መልሳቸዉ በቀጣዩ 3ኛዉ ክፍል በመግባት በመልሶ ማቋቋም ያሰማራቸዉ የወያኔ የድሮ የበረሃ ታጋዮች በአዲስ አበባ ከተማ የንጋዴዉ ሕብረተሰብና ሰላማዊ ዜጎች ሱቆቻቸዉ አና ዉድ ዉድ የሆኑ ቤቶች በተፈራ ዋሉዋ አስፈጻሚነት በመለስ ዜናዊ እና ጥቂት የምስጢር ጓዶቹ ባወጡት ማንም የላጸደቀዉ እና ያላወቀዉ ምስጢራዊ አዋጅ “ቀጭን” ትዕዛዝ እያስተላለፉ እየነጠቁ እንዲኖሩበት እንዴት እንደተደረገ እና ይህ ሕገ ወጥ እና አድልዎ ያለበት አሰራር አናስፈጽምም ባሉት በአንዳንድ የአዲስ አበባ የፖሊስ ወረዳ ጸ/ቤቶች እና የከተማዉን አስተዳደር ሲመራ በነበረዉ በተፈራ ዋሉዋ መካከል የታየዉ ጠብ በሚቀጥለዉ 3ኛዉ ክፍል ይቀርባል። ተከታተሉ:: www.ethiopiansemay.blogspot.com