Friday, August 21, 2015

ሰላም ውድ የኢትዮጵያን ሰማይ አንባቢዎች!ሰላም ውድ የኢትዮጵያን ሰማይ አንባቢዎች!

መጀመሪያ ሰላምታየን አቀርባለሁ። በዚህ ድረገጽ ገብታቸህ የተለያዩ መልክቶችና ጥያቄዎች እንዲሁም ምሳግናችሁ ለላካችሁልኝ እና ስልክ ለደወላችሁልኝ ወገኖቼ እጅግ አመሰግናለሁ። ድረገጼን መጎብኘት ስላልቻልኩ በወቅቱ መልስ መስጠት አልቻልኩም። ይቀርታ እጠይቃለሁ። 


ባለፈው ሁለት ሳምንታት የግል ኢመይል አድራሻዬን በድረገጽ ወሮበሎች ሃክድ/ ተጠልፎ ስለነበር፤ በዚህም ምክንያት ሌቦቹ፤ ፍልፒን በተባለ አገር እንዳለሁ በማስመሰል፤ እዛውም እንዳለሁ፤ በሌቦች ገንዘቤን ተቀምቼ እንደነበር እና ለዚህም እርዳታ እንድትልኩልኝ የሚል የማጭበርበሪያ “ያሁ ኢመይል” ለመላ ወዳጆቼ እና አንባቢዎቼ በየኢመይላችሁ ልከው ለማጭበርበር ሞክረው ስለነበር፤ የድረገፅ አጭበርባሪዎች የላኩት የማታለያ ኢመይል ስለሆነ ፤ ገንዘብ አንዳትልኩ አሳስባለሁ። የማጭበርበሪያው ኢመይላቸው ደግሞ “ያሁ” ኢመይል ነው። ለማንኛውም ኢሜይሌ አልተለወጠም፤ ስልኬም አልተለወጠም።

ዌብ ብሎጌም ቆልፈውት ስለነበር፤ አሁን አስከፍቸዋለሁ። ለተባበሩኝ ወገኖች አመሰግናለሁ። በዚህ አጋጣሚ ላንባቢዎቼ ችግሩን ለመንገር እንድትለጥፉልኝ የላኩሁላቸው ድረገፆች ትብብራቸው ስላላሳዩኝ ቅሬታየ እየገለጽኩ። ድረገፆቹ ይቅርታ እስካልጠየቁ ድረስ፤ የኔን ጽሑፍ በእነሱ ድረገጽ አይለጠፍም። አንባቢዎቼ ከእንግዲህ ወዲህ የኔን ትችት ለማንበብ ስትፈልጉ እዚሁ ኢትዮጵያን ሰማይ መጎብኘት ይኖርባችሗል። 

በዚህ ሳምንት ፦፦ በቤንሻንጉል/ጉምዝ ከነ ነብሳቸው ታርደው “ስጋቸው እና ጉበታቸው እየተጠበሰ” ስለተበሉ አማራዎች ሰፊ ሃተታ ይቀርባል፤ ተከታተሉ። ተቃዋሚ ሚዲያዎች እና የፖለቲካ ተቃዋሚዎች የሚባሉትም ይህ እግዚኦ የሚያሰኝ ክስተት ሰምተው አንብብው ጀሮ ዳባ በማለት ስለ ራሳቸው ቡድን “ስለ ግንቦት 7”  “ስለ ብሎገሮች እና እሳላመዊ ወኪሎች” ለአመታት በማትኮር፤ አማራው ሲጠቃ ጀሮ ዳባ በማለት ፤ አንዳንዶቹም (አንደ ግንቦት 7) አማራውን “ነፍጠኛ” እያሉ በመሳለቅ እና በመዝለፍ የጥቃት ተባባሪዎች (ሳብቨርሲቭ) ሆነው ለአመታት ዘልቀዋል። እዚህ ላይ ተዋናዮች ሆነው ሕዘብ አንዳይነሳ፤ የግለሰቦች/ኤሊቶች መታሰር እና መሰቃየት እያጎሉ የሕዝቡን ስቃይ እንዴት እየገደሉት አንዳሉ አቀርባለሁ።
ጌታቸው ረዳ getachre@aol.com