Wednesday, August 16, 2023

ከታላቅ አክብሮት ጋር ዶክተር ሃይሌ ላሬቦን ልተች ነው ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay) 8/16/23


ከታላቅ አክብሮት ጋር  ዶክተር ሃይሌ ላሬቦን ልተች ነው

ጌታቸው ረዳ

(Ethiopian Semay)

8/16/23

ፕሮፌሰር ሃይሌ ላሬቦ ከምባታ ብሔረሰብ ካፈራቻቸው ብርቅዬ ኢትዮጵያዊያን ምሁራን አንዱ ናቸው። ፕሮፌሰር ሃይሌ ላሬቦ በላቀ ደረጃ ከማከብራቸው ኢትዮጵያውያን የታሪክ ምሁራን አንዱ ናቸው።

ፕሮፌሰር በአካል ያገኘሁዋቸው እኔ እና እርሳቸው እንዲሁም ነብሳቸው በገነት ያኑርልን ፕሮፌሰር ጌታቸው ሃይሌ በ2014 ከ9 ወይንም 10 አመት በፊት ሞረሽ ወገኔ የተባለ በውጭ አሃገር (እዚሁ አሜሪካና አውሮጳ) የመጀመርያ አምሐራዊ ድርጅት የነበረው ንግግር እንድናደርግ ባደረገልን ግብዣ ነበር የተገናኘነው።\

ፕሮፌሰሩ በእውቀታቸው ምጡቅ፤ በባሕሪያቸውም እጅግ ደርበብ ያለ ጨዋዊ ዕርጋታ ያላቸው ረጋ ብለው የሚናገሩ ከሰው ጋር ሲናገሩ በጣም የዋህ ገጽታ የላቸው በራሳቸው ሙሉ ዕምነት እንዳላቸው የሚያሳውቅ ደርባባ ገጽታ ያላቸው እንግሊዝ አገር ለንደን ዩኒቨርሲቲ የተማሩ የታሪክ


ተመራማሪ የግዕዝ ሊቅ ናቸው።   

ፕሮፌሰሩ ወቅቱ ካልተሳሳትኩ በፈረንጆች 2016 (በፈረንጅ) ኢሳት በተባለው ጣቢያ ቀርበው ስለ ኢትዮጵያ ታሪክና ስለ ጠቅላላ የብሔረሰብ ጉዳይ አስመልክተውፋሲል የኔአለምየኢሳት ጋዜጠኛ ባደረገላቸው ሁለት ክፍል በሰጡት ቃለ መጠይቅ እሳቸው እንደ የታሪክ ተመራማሪነታቸው ዛሬ ኦሮሞ ብላችሁ ጥሩን ብለው የድሮ ስማቸው ግራ በሚያጋባ ምክንያት የሚደብቁ ወገኖች ለምን ጥንታዊ ሰነዶችና የታሪክ መጻሕፍትና ተመራማሪዎች በሚጠሩን ስም ጠራኸን ብለው፤ የፕሮፌሰር ላሬቦን የታሪክ አገላለጽ በመቃወም ብቻ ሳይሆን የግል ባህሪያቸውን እና ሕዝባዊ ዝናቸውን ለማጥፋት በጭካኔ ተነሳስተው በሚያስተምሩበትሞርሃውስ ኮሌጅ አትላንታ" ድረስ በብዙ ሽሕ የኦሮሞ ማሕበረሰብ የተፈረመ ፌርማ በማሰባሰብ ከሥራቸው እንዲባረሩ ለማድረግ ከፍተኛ ምቀኛነትና ተንኮል ተፈጽመውባቸዋል።

እኛ ኢትዮጵያ ወገኖችም ፈራሚዎቹን በመቃወም በዕጥፍ የተቃውሞ ፌርማችንን በማስቀመጥ ለሚያስተምሩበት አስተዳዳር በመጻፍ ከሥራቸው እንዳይባረሩ በማድረግ እውነታውን በማስረዳት ተቋሙ በፕሮፌሰሩ ላይ የበለጠ አክብሮት እንዲኖሮው በማድረግ እንደገመትነው ሁሉ ትምህርት ቤቱ ከፍተኛ አክብሮት እንደሰጣቸው ሰምተናል።

ከሠለጠነ ማሕበረሰብ ኦሮሞ የመጣን የሠለጠንን ነን የሚሉ ተቃዋሚዎቻቸውን በወቅቱ አሳፍረን መክተናል። ወደ ርዕሴ ከመግባቴ በፊት ስለዚህ ጉዳይ አንስቼ እቀጥላለሁ፡ ፕሮፌሰሩ አክብሮት የሚገባቸው ስለሆኑ ለማታውቁዋቸውና ከጽንፈኛ ኦሮሞዎች በሳቸውና በቤተሰባቸው ላይ የስልክ ጥሪና ሕይወት ማስፈራሪያና የስድብ ፍላጻ ሲወረወርባቸው እንደነበር ለታሪክ መግለጽ አስፈላጊ ነው።

 የተቃውሞው አንቀሳቃሾች አክራሪ ኦሮሞዎች ናቸው ብያለሁ። ከነዚህ ውስጥ Ayyaantuu.com እና Opride.com የተባሉ ሁለት ጸረ አምሐራና ጸረ ኢትዮጵያ የኦሮሞ ጽንፈኛ ድረገጾች ቀዳሚ ተዋናያን ነበሩ። Ayyaantuu.com በጃዋር ባለቤት የሚካሄድ ድረገጽና (ቲቪ ?) ሲሆን፤ ይህ ድረገጽ ፕሮፌሰር ላሬቦንየከምባታነቱን ዘር የካደ (ትሬይተር) በሚል ሲዘልፋቸው፡ Opride.com ደግሞ አዘጋጁመሐመድ አዴሞ” (በአልጀዚራ ኤጀንሲ ውስጥም ይሠራልለ በቅርቡ የአብይ አሕመድ አገልጋይ ሆኖ የሕዝባችን ስቃይ ሲያስረዝም ከነበሩት አንዱ ነው) ይህ አክራሪ ወጣት የሠለጠነን ማሕበረሰብ በድሮ ስሙ ተጠራ (ተሰደበ) ብሎ ይጽፍና ከሠለጠነ ማሕበረሰብ የመጣሁ ነኝ እያለ ሲበጠረቅ የነበረ ይህ ወጣት ፕሮፌሰሩን "monkey” and “baboon” “ዝንጀሮእናየዝንጀሮ ዝርያበሚል የዘረኝነት ቃላትን ተጠቅሞ ክቡር ፕሮፌሰር ላሬቦን ከሰብአዊነት ውጭ በመጥራት አልጀዚራ ውስጥ በጋዜጠኛነት የሚሰራ ይሁን እንጂ ውስጡ ከሥልጣኔ እጅግ የራቀ አስተሳሰብ እንዳለው በማሳያት የፕሮፌሰሩን ስብእና እና ክብር በመንካት መላው ኢትዮጵያውያንን አስቆጥቶ የነበረ አጋጣሚ እንደነበረ ላስታውሳችሁ እወዳለሁ።

ስለዚህ ፕሮፌሰሩ ለታሪክ ያላቸው ክብርና ለሙያቸው ያላቸው ጽናት ከአክራሪዎች ሲሰነዘነርባቸው የነበሩትን <<የይቅርታ ጠይቅ>> ዘለፋዎችን መክተው የዘለቁ አገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ ናቸው””

አሁን ወደ ርዕሴ ልግባ፡-

መቸ እንደተላለፈ ባለወቅም ፕሮፌሰሩ በዚህ ሳምንት ከትንታጉ የፖለቲካና ሃይማኖት ተንታኝ ከማከብረው ከዘመድኩን በቀለ ጋር ያደረጉት አንዲት አጭር (ምናልባትም 4 ወይንም ከዚያ በታች አነስተኛ ደቂቃ) የተላለፈ የቃለ መጠይቅ ቪዲዮፌስቡክ ላይመረጃ ቲቪየሚል ጣቢያ አደመጥኩና እሳቸው እንደሆኑ ሳውቅ ትኩርቴን ሳበውና አደመጥኩዋቸው።

ቪዲዮውን ለአንባቢዎቼ ለማስቀረትና ለመለጠፍ ሞክሬ መቅዳት የማይቻል ሆኖ ስላገኘሁት፤ ፕሮፌሰሩ አማራ የሚል ቃል ቋንቋንና ብሔረሰብን አያመለከትም። የሕዝብ መጠሪያ ወይንም ባሕል ሳይሆን "የቦታ መጠሪያ" ነው በማለት ከተናገሩት የተስማማሁበትና ያልተስማማሁበት የታሪክ ትንታኔአቸውን ከናንተው ጋር በጽሑፍ ጠቅሼ ልጥቀሳቸውና ልዘርዝር።

እንዲህ ይላሉ፦

<<ንጉሥ ስሱንዮስ፤ ንጉሡ 'ወደ አምሐራ ምድር ሄደ' ከዚያም ቀጥሎ ወደ ጎጃም ምድር ሄደ፤ከዚያም ቀጥሎ ወደ ሸዋ ሄደ ፤ከዚያም ቀጥሎ ወደ ቤገምድር ሄደ፡ ይላል የአካባቢው ነው የሚያመለክተው እንጂ ቋንቋንና ብሔረሰብን አያመለከትም።>> ካሉ በኋላ ዘመድኩን ጣልቃ በመግባት፦

<< ይቅርታ: ምድሪቷን ልንጠቅሳት እንችላለን?>> በማለት ወደአምሐራ ምድር ሄደየምትለዋን ሐረግ ጠየቃቸው።

ፕሮፌሰሩም

<< አዎ፡ አማራ ሳይንት እንግዲህ ብዙን ጊዜ የሚጠቀሰው በወሎ አማራ ሳይትን ነው የሚጠቀሰው።በዚህ ምክንያት የጎሳ ማመላከቻ ሆኖ አያውቅም። 1983 . ህወሓት ሥልጣን ሲይዝና ከዚያም በፊት በእነ ዋለልኝ መኮንን በትልቅ ስሕተት ነው የቀዱት። አማርኛ የሚናገር ከአማራ ጋር በማቀናጀት አማራ የሚባል ጨቋኝ ነው እያሉ ማያያዝ ጀመሩት እንጂ አማራ የሚባል ማሕበረሰብ አልነበረም።ቋንቋ ግን ነበር። ይህ ቋንቋ ከአማራ ጋር ምንም ግንኙነት የለውም። ምክንያቱምእንደ ሚነገረው ከሆነየአገው ነገሥታት ናቸው የኢትዮጵያ ቋንቋ እንዲሆን ያደረጉት። ስለዚህ አማርኛ እንዲናገር አድርገውታል።…….

………..አገዎች ቋንቋቸው አገውኛ ነው፡ ግን የግዴታ ኣማርኛን ያደረጉበት ምክንያት ሰፊው ሕዝብ ሁሉም ሰው የሚናገረው ቋንቋ ስለሆነ ያንን እንዲናገርብት አድርገዋል። >> ብለዋል ፕሮፌሰር ሃይሌ ላሬቦ።

አሁን የምስማማበትና የማልስማማበትን ላስቀምጥ።

የምስማማበት፤-

ንጉሡ ወደ አምሓራ ምድር ሔደሲል ምድርን ያመለክታል ሲሉ እስማማለሁ።

ግን << ንጉሡ ወደ አምሓራ ምድር ሔደ ሲል መሬቱን እንጂ ማሕበረሰብን አያመለክትም “” ያሉበትን ልዩነቴን ላስቀምጥ።

አምሓራ ምድር ሄደ ያለበት (እስፕሲፊክ) ተጭኖ ያመላከተበት ምክንያት አምሐራ የሚባል ማሕበረሰብና አምርኛ የሚናገር ማሕበረሰብብዙ ጊዜ የሚጠቀሰው ቦታብለው እሳቸው የጠቀሱትአማራ ሳይንትብቻ አይደለም (በወቅቱ በተጠቀሰው ንግሥ ጊዜ አማራዎች ሲኖሩበት የነበሩበት ቦታ ከወደታች እጠቅሳለሁ)

እኔ ደግሞ የምለው << ንጉሡ የትኛው አማራ ምድርእንደሄደ በስም ባያስቀምጥም በመላምት /ግምታችን ግን እሳቸውም ግምታቸው ባለውቅም ምናልባት እንደሚገምቱት <<አማራዎች በብዛት የተካመቹበት ቦታ አማራ ሳይንት ሊሆን ስለሚችልአምሓራየሚለውን ቃል ንጉሡ መጠቀሙአምሐራየተባለ ማሕበረሰብ በመኖሩአምሐራየምትለዋ ቃል በማሕበረሰቡ ስም ጠቅሷታል።

ምክንያቱም ጎጃምና ቤገምድር ውስጥ ያኔም አምሐራዎች ነበሩበት። የተለያዩ ቅይጥ ማሕበረሰብ ስለመኖሩ ዛሬም እናውቃለን (ከጊዜ በሗላ ብዛት ያለው አማራ ጎልቶ መውጣቱ እንዳለ ሆኖ) “አምሐራ ምድርየምትለዋአምሐራየምትል ቃል ለምን ተጠቀመ ብለን ብንጠይቅአምሐራበዚያችየት መሆኑን ያልተጠቀሰ በአምሐራ ስም የተሰየመው ምድር ምድርአምሐራየተባለ ሕዝብ በመኖሩ ነው። <<ጎጃም የሚባል ሕዝብስ ፤ቤገምድር የሚባልስ ሕዝብ ነበር ወይ>> ብላችሁ ልትጠይቁኝ ይሆናል ለምሳሌ በዛው ወቅት ሸዋ የሚባል የግድ አምሓራ ምድር አይባልም ብንል እንኳ መንዝ ውስጥ አምሐራ ነበሩበት። በማናውቀው ትርጉም እና መጠሪያ የግድ ጎጃም ወይንም ወሎ ወይንም ቤጌምደር ስለተባለአምሐራየሚባል ሕዝብ በውስጡ አልነበረም ማለት አይቻልም።

ንጉሡ ምድር ሲልቦታ አማላካችቢሆንም ወደ እዚያ ምድር (ቦታ) የሄደበት ምክንያት አይታወቅም (ወይንም ተገልጾ ሊሆን ይችላል) ስለዚህ የዛሬ ወሎ የጥንት ስሙ << ለኮመልዛ (ካልተሳሳትኩ)>> ውስጥ የሚኖሩ የተለያዩ ነገዶች ማለትም‘’አገዎች፤ ኦሮሞዎች፤ አርጎባዎች፤ አማራዎች….‘ ይኖሩበታል፤ ግን ንጉሡ ባጠቃላይ የወሎን ምድር ሕዝብ (እነዚህን ማሕበረሰቦች) በድፍን ጎብኝቶ ቢሆን ኖሮ ልክ እንደ ጎጃም /ቤገምድር እንደጠቀሳቸው ሁሉ <<ለኮመልዛ>> ብሎ ይጠራ ነበር። ሆኖም <እስፐስፊክ> “አምሐራየተባሉ ማሕበረሰብ መጎብኘት ስለነበረበት በስማቸው ወደ እሚጠራው ምድር መሄዱንያመላክታል።

እንደሚታወቀው በተለምዶ አነጋጋር ከጥንት የመጣ አነጋጋርአገው ምድር” “ትግሬ ምድርስንል የተጠቀሱት ብሐረሰቦች የሚገኙበት ቦታ ማለት ነው።

ብዙውን ጊዜ የጥንት መጻሕፍትአረመኔ ምድርአገው ምድር” “እስላሞች አገርየኦሮሞች አገርብሎ እንደሚጠቀሱ እናውቃለን። አገር የሚለው ቦታን እና ምድርን ያመላክታል። አገሬሳይንትነው። ይላሉ። አገር ስንዘረዝረው የት ብለህ አጥብቀህ ስትጠይቀው ደግሞአማራይላል አማራ ሳይንት ማለት ግን አማራ አይኖርበትም ማለት አይደለም፤ ምክንያቱም ብዙዎቹ አማራዎች እዛ ሳይንት ውስጥ ስለሚገኙ። እኛ ትግሬዎች <<ዓዲ ምሓራ“ ( ዓዲ ኣምሓራ) ስንል << አማራ አገርአምሐራ ምድርስንል (ከጥንትም ከዛሬም አነጋጋር) አማራዎች የሚኖሩነት ምድር ማለት ነው።

ፕሮፌሰሩ ግዕዝ አዋቂና ግዕዝ ሲያስተምሩ እንደነበር አውቃለሁ። ይህ የትግሬዎች አነጋገር አያጡትም ብየ እገምታለሁ። ስለዚህምድር እና አገርበውስጠ ታዋቂ አዝሎት የሚመጣ ትርጉምየተናጠል (የአማራ አገር/ምድር ማሕበረሰብ) አጣራር ይሆናል (ልክ ንጉሡ ሔድኩኝ ባለበት የወል አጠራር እንደጎጃም እና ቤገምድር ስለዚህ ትርጉም እንደ ተርጓሚው ነው። አዝሎት የሚመጣውውስጠ ታዋቂውም ጭምር ግምት ውስጥ ካላስገባነውቀጥተኛ የቃላት ትርጉም ስንወስድ ወስጠ ታዋቂውን በመጣልስሕተት ውስጥ እንገባለን።

ሌላው ቋንቋን አያመለከትም ሲሉ ፤ምድርን እንደሚያመለክት እውነት ነው። ግን አምሐራ የሚለው የማሕበረሰብ መጠሪያ ቋንቋን የወለደ መሆኑን ካላመን ትግሬ ስንልትግርኛ አምሐራ ስንልአምሐርኛየሚለው አጠራር ከየት መነጨ? ጉራጌ፤ ጉራጌኛ፤ ከምባታ፤ከምባትኛ” (ካልተሳሳትኩ) ከየት መነጨ?

 ፕሮፌሰሩ የጠቀሱት 17ኛው /ዘመን ንጉሥን ነው። እኔ ደግሞ ወደኋላ መሄድን ትቼ ባጭሩ 13ኛው /ዘመን እንመልከት።በ12ኛውም ሆነ (ይኩኖ) ወይንም ኪዘያ በኋላ በርካታ አማራ የሚባል ሕዝብ እና ንገሥታቶች ነበሩ።

አጭር ምሳሌ ልስጥ፦

ክቡር ፕሮፌሰር ሃይሌ የሚያውቅዋቸው የዓረብ ጸሐፍት ለምሳሌአል-ማቅሪዚየተባለው የዓረብ ጸሐፊ ድሮ ሶማሌ ውስጥ የነበረው (ዛሬ ሶማሌ ላንድ ቁጥጥር ይመስለኛል) ዘይላ የተባለው ወደብ 20 አመት ሙሉ አማራዎች እንደነበሩበት ጽፏል።

/ ደረሰ አየናቸው በጻፉትሰሎሞናውያን የኢትዮጵያ መንግሥት ታሪክ (1262-1521) በገጽ 186 ስንመለከት (“አል-ማቅሪዚ በመጥቀስ) ከዚህ በታች የምትመለከቱትሰአደዲንየሚል ስም ከክርሰትያን ንገሥታት ጋር ውግያ ሲገጥሙ ከነበሩት የኢፋት እና የመሳሰሉ እስላማዊየወላሰማ ሥርወ መንግሥትመሪዎች አንዱ ነው። ከንጉሥ ዳዊት ጋር ሃይለኛ ውግያ አድርጎ በሗላ ሰአደዲን ተሸንፎ ኢፋት ለክርሰትያኑ ንጉሥ ያስረከበ ነው። ንጉሥ ዳዊት 1396 ሰአደዲን በማጥቃቱ

አል-ማቅሪዚእንዲህ ይላል፦

<< ንጉሥ ይስሐቅ ባንድ ሙስሊምና በአንድ ክርስትያን ግብጻውያን ባለሞያዎች በመታገዝ የንጉሥ ይስሐቅ ጦርና አስተዳደር በመታገዝ፤ የንጉሡ ጦር በተሻለ አቅም በመገንባቱ አጼውና አምሐራዎች ግዛቱን (ዜይላን) እና አካባቢውን ከተቆጣጠሩ በኋላ በግዛቱ ተቀመጡበት። መስጊዶቹን አፍርሰው ቤተክርስትያን ሰሩ። ለሃያ አመታትም በዜይላንና አካባቢው የሰሎሞን አስተዳደር ማደራጀት ችለው ነበር።>> ይላል አል -ማቅሪዚ

  ደራሲውም እንዲህ ያክሉበታል፤-

ለንጉሥ ይስሐቅም ክብር በጥንታዊ አምሐርኛ የተገጠመ ንጉሡ የግብጽ ጥበብ እንደነበረው ይናገራል። ይኼው ሰነድምወንበዴ ጠፋ ለድምጽሲል ንጉሡን ያሞግሳል።

ስለዚህ ቋንቋ ለብሔር ማንነት ግንባታ እና ጥበቃ ወሳኝ ሚና እንደሚጨወት ይታወቃል። አማርኛ ቋንቋ መኖሩን ብቻ ሳይሆን አምሐራ የተበለ ሕዝብና ክርሰትያነዊ ስርወ-መንግሥት ነበር።

በዚህ በደራሲው ልደምድም፡-

<< ንጉሥ አምደ ጽዮን ሥልጣን በያዘ በሁለት አመት በኋላ የወሰደው ወታደራዊ እርምጃ ግን መሠረታዊውን የኢትዮጵያን ግዛት መስፋፋት ሂደት ቀይሯል። የወታደራዊው አቅሙንም አዲስ ምዕራፍ የከፈተና የአምሐራ ሰሎሞናውያን ክንፍ ለሚቀጥለው ሁለት መቶ ሃምሳ ዓመታት የሥርወ-መንግሥቱ አስተዳዳር መሪ እንዲሆን አድርጎታል። የንጉሥ አምደ ጽዮን የወታደራዊ ድሎችና ቀጣይ አደረጃጃት ለክርሰትያን መንግሥት ትንሳኤ ሰጠው።>> ይላሉ ደራሲው።

አምሐራ የሚባል ማሕበረሰብና ንጉሥ ካልነበረየአምሐራ ሰሎሞናውያን ክንፍ ለሚቀጥለው ሁለት መቶ ሃምሳ ዓመታት የሥርወ-መንግሥቱ አስተዳዳር መሪ ለመሆንከየት መጣ? ስለዚህም ከዚያስ ንጉሥ ይስሐቅ እና አምሐራዎች ዜይላ (ሶመሌ ወደብ) 20 አመት ሲኖሩአል-መቅሪዚአምሐራ የሚለው የማሕበረሰብ ሥም (ቃል) ከየት አመጣው?

የሸዋ መንዝ በተፈጥሮ አቀማመጡ እና በቆላማነቱ ይላሉ ከላይ የተጠቀሱ ደራሲ / ደረሰ

<<የሸዋ መንዝ ግን በተፈጠሮአዊ አቀማመጥ በቆላ የተሸሸጉ የአምሐራ ክርስትያኖች በመመከታቸው ግዛቱ በእስልምናም ሆነ በኦሮሞ መስፋፋት እንደ (ቀሪዎቹ) ከኔ ከጌታቸው ረዳ የተጨመረ) እንደ ቀሪዎቹ አምሐራ ግዛት አልተዋጠም ነበረ።>>

ይሉ እና፤

ዶክተር ሃይሌ ላሬቦ ሲጠቅሱት የነበረው ንጉሥ ስሲንዮስ (17ኛወ /ዘመን) / ደረሰ አየናቸው ሸዋ ውስጥ አማራዎች እንደነበሩ ይጠቅሳሉ፡

እንዲህ ሲሉ፡

 << 17ኛው መጨረሻ ቀሪው ሸዋ-አምሐራ ግዛት ሊያንሰራራ በሚችልበት ሁኔታ ተደራጅቶ ነበረ። የመንዝ ግዛትም በየ ጎበዝ አለቃ ይመራ ነበር።>> (/ ደረሰጥቅስአስፋወሰን አስራተ ገጽ 1980)

ልጨርስ፡

 / ሃይሌ ላሬቦ ሱስንዮስን ሲጠቅሱሸዋአምሐራ ስም ማለት አይደለም ወይንም የቦታ ስም ነው፤ ብለዋል። ልክ ነው፡ ግን በወቅቱአምሐራየሚባል ሕዝብ እንደነበር ይኼው ማስረጃው ጠቅሻለሁ። አምሐራ ሳይንት ብቻ ሳይሆንአምሐራ ምድርየሚባሉ በርካታ ምድሮች አምሐራዎች ይኖሩ እንደነበር አመላካች ነው (ጎጃም፤ቤገምድር ወዘተ……እና ነገሥታቱ የገዙዋቸው ምድሮች ሁሉ አምሐራዎች ተስፋፍተውበት ነበር።

አረብ ፋቂሕ የተባለ የማናዊ የታሪክ ጸሐፊም (ከግራኝ ጋር ሲዘግብ የነበረ ዘጋቢ) ሰሎሞናውያን ነገሥታት የሰሩባቸው ብዛት ያለቸው ቤተክርሰትያናትና የትውልድ ቦታዎቻቸውቤተ አምሐራሲል ዘግቧቸዋል። ስለዚህ አምሐራዎች ነበሩ አገራቸውም ቤተ- አምሐራ ይባላል። ብሎ ዘግቦታል። ስከዚህ አምሐራ ምድር ማለት "የቦታም" "የአማራ ቤቶችም" ማለት ነው። ቤተ አምሐራ (የአምሐራ ሕዝብ መኖርያ) ማለት ነው ክርስትያንነት ባለበት ምድር ሁሉ አማራዎች አሉ አማራና ክርስትያን ያንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታ ናቸው።

ከአክብሮት ጋር

ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay)