Thursday, October 1, 2015

መስፍን ወልደማርያም-ዋለልኝ መኮንን ሁለት መንትያዎች ጌታቸው ረዳ (Getachew Reda - Editor Ethiopian Semay) Septemeber 28/2015



መስፍን ወልደማርያም-ዋለልኝ መኮንን ሁለት መንትያዎች
ጌታቸው ረዳ (Getachew Reda - Editor Ethiopian Semay)
Septemeber 28/2015
ወደ ዋናው የመነገገርያ ርዕሴ ከመግባቴ በፊት ባለፈው ሁለት ሰሞን  ጉሙዝ ላይ አማራዎች በደረሰባቸው የጎሳ ጥቃት፤ ኢሕአፓን በሚመለከት አስመልክቼ በደመፍላት የጻፍኩት ትችት እንደነበር ይታወሳል። አንዳንድ ሰዎች በኢሕአፓ ላይ በጻፍኩት ትችት፤ በተለይም ስም ጠቅሳችሁ “ሃማ ቱማ (ታጋይ እያሱ አለማዮህን) አስመልከቼ አንደጻፍኩት አድርጋችሁ በመደሰታችሁ የላካችሁልኝ ደብዳቤ እጅግ ከልቤ አዝኛለሁ። ላንዳንዶቻችሁም መልስ ጽፌላችሗለሁ። ይኼውም ፤ ሃማ የኔ አርበኛ እና የግል የትግል ጓዴ ስለሆነ ከቶውንም ሃማን ለማሳዘን፤ በሃማ ቱማ ባትመጡብኝ እጅግ አመሰግናለሁ።  

ስንተታች ፖለቲካውን አስመልክተን እንጂ ለጥል ለግል ሽኩቻ አንዳልሆነ እንድታውቁልኝ አሳስባለሁ።ይኼ ደግሞ ሁሌም የምናደርገው ነው። ዩኒክ/ልዩ የሚያደርገንም ይህ ባሕሪያችን ነው።  የኔን መነሻ እያደረጋችሁ በየፓልቶኩ ኢሕአፓን ስትዘልፉ አድምጫለሁ። ኢሕአፓን ወይንም እያሱን ቀዳዳ ተገኘ እያላችሁ፤ በየፓልቶኩ የምትዘልፉ ሰዎችም ከዚያ አንድትርቁ አደራ እላለሁ። በተረፈ ኢሕአፓ አለመታደል ሆኖ “ብዙ ባንዳዎች” ትግሉን እየበረዙ አበላሹት አንጂ “ኢሕአፓ” የሚስተካከል ነገር አስተካክሎ፤ የተበተኑትም አባሎቹን አሰባስቦ ባንድነት ትግሉን ቢመበራው፤ ወያኔ ይኸኔ ይገረሰስ አንደነበር በሙሉ ልቦና ነው የምላችሁ። ወደዳችሁትም ጠላችሁትም ፤ ኢያሱ ዓለማዮህ/ሃማ ቱማ አሁንም የትግል ጓዴ እና እጅግ የማከብረው አርበኛ እና ጋዴ መሆኑን በዚህ አጋጣሚ ወዳጆችና ጠላቶች ልነግራችሁ እፈልጋለሁ። Hama! the Hero, an author, poet, rare icon and the only revolutionary student leader of our time left on this earth. Viva Hama! Head up my brother!

አሁን ወደ ርዕሳችን እንግባ። ሰፋ ያለ ትንታኔ ስለሆነ ጊዜ ወስዳችሁ አንድታነብቡት ይሁን።ለማንበብ የምትደክሙ “አጭር ተጓዠ ደካሞች” ካላችሁ ወደ አጫጫር ዜና አቅራቢዎች ሂዱ። ወዳጆች ሆይ እኛ ጻሐፊዎች ለታሪክ ሰነድ ለማስቀረት የምናደርገው ጥረት ድካም እና የጊዜ መጣበብ የምናደርገው ግብግብ ብትረዱልን እንዴት ደስ ባለን። በዛሬው በዚህ ርዕሠ ጽሑፍ የተመለከቱ በሁለት ታላቅ ኢትዮጵያዊያን ምሁራን ላይ እተቻለሁ።

በቅድሚያ  ምሁሩ ፕሮፌሰርና እና እውቅናቸው የገነነው  መስፍን ወልደማርያምን እተቻለሁ።ከዚያ ወደ ዋለልኝ አመራለሁ። ከዚያም\\ በሚቀጥለው ሳምንት ልዑል ራስ መንገሻ ሥዩም “ፈጣሪ የወያኔ ዕድሜ ወንድሞቻችን ሥርዓት ዕድሜው ያርዝምልን” ፡ በማለት፤ የአማራን ዘር ማንዘር በማጥፋት ላይ የሚገኘው ፋሺስቱ የወያኔ የትግሬ መንግሥትን የመረቁበትን አንደበታቸው እተቻለሁ።

ከዚያም ቦታ ካልጠበበ ጋዜጠኛ ነበረች የሚባልላት በእስተ እርጅናዋ በፀረ አማራዎች በዘረኞቹ በእነ ኤፍሬም ማዴቦ የሚመራው “ግንቦት 7 ካድሬና ”የኢካዴፍ/ካረንት አፈይርስ አስተባባሪ የሆነቺው ወ/ሮ ብዙ ወንድማገኘሁ/የፓልቶክ ስሟ “ሙያዬ ምስክር” ስለ አማራ መደራጀት ጥላሸት የመቀባትዋ ጉዳይ የተናገረቺውን ከነፎቶግራፍዋ በመለጠፍ እተቻለሁ። ከዚያም ቂጣ ራስ በማለት እራስዋን የምትጠራ “ኦሮሞ ነኝ” ብላ ባንደበቷ የነገረችን፤ ሻዕቢያን እያወደሰች ትግሬውን የምትዘልፍ፤ ለሻዕቢያ ያደሩትና፤ አማራን ሲዘልፉ በቴፕ የተቀዱ፤ በጸረ አማራነታቸው የታወቁት የግንቦት 7 መሪዎችን በመከላከልና በማድነቅ፤  “መርማሪያዋ” ተብላ በብዕር ስም የምትጠራ፤ እጅግ ሲበዛ አውቀቷ፤ለዛዋ እና በመረጃ የተደገፈ ብርቱ የሆነ የመልስ አሰጣጥዋ የሚያረካ፤ ደምጸ መራዋ ኢትዮጵያዊት ታጋይ፤ ይህችን “ትንሽዬ ሕሊና ያላት ቂጣ ራስ” ሴትዬ ምን ብላ ታስተምራት አንደነበር አባ መላ ያወያያቸውን ውይይታቸውን እንመለከታለን። ይህ ለሚቀጥለው ይሆናል። ለዛሬ ግን ይህንኑ ከታች ያለውን እንመለክት።

ፕሮፌሰር መስፍን፦

በተለያዩ ምክንያቶች አክብሬአቸዋለሁ። አሁንም አከብራቸዋለሁ።ባለፉት በርካታ አመታት እሳቸውን ለመከላከል ስል ከዘለፉዋቸው ከብዙ ጸሐፊዎችም ጋር ተጋጭቼአለሁ። ለሰሯቸው ብዙ በጎ ነገሮችን አሁንም አክብሮት እየሰጠሁ፤ ግልጽ ያልሆኑልኝ፤ የሚጎረብጡ ስለ አማራ ማሕበረሰብ የሰነዘርዋቸው አንዳንድ አስተሳሰባቸው ግን የአማራው ሕብረተሰብም ሆነ ሌላው ዜጋ አንዲያውቀው ማድረግ እንደ ዜጋ ጠቃሚ መከራከሪያ ሆኖ ስላገኘሁት በዚህ እንወያያለን።

ባለፈው ሁለት ሰሞን በሞረሽ ሊቀመንበር በአቶ ተክሌ የሻው የተጻፈ በኢትዮፓትርዮት እና በወልቃይት.ካም ድረገጾች፤ ኢትዮጵያዊያን ለፕሮፌሰር መስፍን  ጥያቄ አንዲያቀርቡላቸው የዘረዘርዋቸው ጉዳዮች አንብቤ ፕሮፌሰሩ በአንደኛው መጽሐፋቸው ውስጥ ስለ አማራ እና ኦጋዴን ሶማሌዎች የሻከረ ግንኙነት የጻፉት ነገር በሚመለከት አትኩሮቴ ስለሳበው ይህ ትችት በፕሮፌሰሩ ላይ ለማቅረብ ነው።

አንቱ የተባሉ እኚህ ምሁር እና የተከበሩ አዛውንት የሕብረተሰብ አስተማሪ የመሆናቸውን ያህል ስለ አማራ ማሕበረሰብ ያላቸው ግንዛቤ ሙሉውን መረጃ ያጠራቸው ይመስላሉ፤ ወይንም ባልታወቀ ምክንያት የሳሳው ግንዛቤአቸው የተዘጋ ይመስላል። 

ብዙ ምሁራን ኤሊቶች/ሊሂቃን እርስ በርስሳቸው በፖለቲካም/ሃይማኖትም ሆነ ባንዳች ምክንያት ሳይግባቡ ሲቀሩ፤ ያንን ቁርሾ/አመለካከት/እምነት ተሸክመው  ብዙውን ቅርያኔአቸው በገበሬው ማሕበረሰብ ጫንቃ ላይ ይጥሉታል። ማሕበረሰቡም ሊሂቃኖቹ በሚያስተምሩት መንገድ ወይ ተጠቂ ይሆናል፤ ወይ ተከታይ ይሆናል። በስሙ ይነገድበታል፤ ወይንም ይወቀስበታል። ባልሆነ መንገድ ገብቶም ለጥቃት ይጋለጣል።

ማሕበረሰቡ እራሱን የሚገልጽበት የራሱ ግንዛቤ እና አረዳድ ቢኖሮውም፤ የራሱን መጠሪያም ሆነ ግንዛቤ ‘ነጥቀው’ “ሊሂቃኖቹ” በሚሰጡት ስምም ሆነ የአካባቢ ግንዛቤ እንዲታጠር ያደርጋሉ።ይህ ድርጊት የሚፈጸምበት ምክንያት ለፖለቲካ፤ለሃይማኖትና ለስልጣን መቆናጠጫ ሲባል የሚከሰት ክስተት ነው።  

የአማራን ደህንነት/ሴክዩሪቲ/ሴፍቲ የሚጻረሩ ሃሳቦች፤ ለሌሎች ጎሳ ሊሂቃኖችን በማቀበል፤ በማስረጃ ያልተደገፈ ፕሮፓጋንዳ  ለጠላት  በማቀበል ስማቸው የሚወቀሱ አማራዎች መሃል (አማራ አይደለሁም ቢሉም፤ ያንኑ አከብራለሁ) አንዱ ፕሮፌሰር መስፍን መሆናቸውን አዝኛለሁ።

ፕሮፌሰሩ አማራን በሚመለከት ሲተነትኑ፤አማራ የሚባል የለም ይላሉ። ለዚህ ደግሞ በቂ ትንትና ሲሰጡ አልሰማሁም፤አላነበብኩም። አማራ የሚባል የለም እያሉ ለኢትዮጵያዊያን እና ለዓለም እየገለጹ ሲከራከሩ ቆይተው፤ “የለም” ሲሉት የነበረው “አማራ” የተባለ ማሕበረሰብ ደግሞ ከሃምሳዎቹ ዓ/ም ጀምሮ “አማራ” የሚባል ማሕበረሰብ እንደነበር ሳይታወቃቸው የራሳቸውን ሙግት እንደገና እራሳቸው ሲያፈርሱት “አቶ ተክሌ የሻው፤ ፕሮፌሰሩ” የጠቀሱት ማስረጃ ለማረጋገጥ ብዬ መጽሃፉን ገልጬ ሳነብበው እውነትም ፕሮፌሰሩ ሲሞግቱበት የነበረውን የእራሳቸው ነጥብ ተመልሰው ሲያፈርሱት ይታያል።  

ፕሮፌሰሩ እንዲህ አይነት እራስን በራስ የመገራጨት/የመቃረንን ነገር የአፍ ወለምታ ነው እንዳይባል፤ በብዙ ገበሬ አነጋግሬአለሁ፤ማስረጃ አለኝ እያሉ ነው የጻፉትና የሚከራከሩት። ይህ የራስን ትንታኔ በግልፅ ያለመተንተን አቋም ሌላውን ውዥምብር ውስጥ የመክተት አባዜ በእርሳቸው የተወሰነ አይደለም። የፕሮፌሰሩን የተምታታ ሐረግ እየመዘዙ፤የእሳቸውን ኮቴ እየከተሉ እራሳቸውን አምታትተው ሌለውን የሚያምታቱ የፕሮፌሰር ተከታዮች ብዙ ናቸው። 

ለምሳሌ ከላይ የጠቀስኳት፤ ድሮ አገር ውስጥ ማሕበራዊ ነክ የቴሌቪዥን ጋዜጠኛ ነበረች የሚባልላት ዛሬ በእስተእርጅናዋ “ከልጆች” ጋር የጠላ ቤት ወሬ የሚመስል በፓልቶክ ክፍል ውስጥ  ዘረኝነትን ስታቀማጥል፤ ወሬን እንደ እሳት እየሞቀችበት “እኔም ከዚቹ ቀን ጀምሮ ዘረኛ መሆኔን አንድታወቁልኝ” እያለች በካረንት አፌይረስ/ኢካዴፍ ፓል ቶክ ውስጥ አዘጋጅ ሆና የትግራይን ማሕበረሰብ በመዝለፍ የምናውቃት የግንቦት 7 “ካልት” የሆነቺው ወ/ሮ ብዙ ወንድማገኝ የተባለች ሴትዮ፤ “አማራ የሚባል የለም” ከሚሉት የፕሮፌሰሩ ተከታይ ነች።

የለም የማለት መብቷ ቢሆንም፤ የለም፤ወይንም አይደለሁም በሚለው ተወስና ዝም ብትል እኮ ባልከፋ፤ ሆኖም “አማራ አለ፤ ስለሆነም ተደራጅተን አማራን ከጨርሶ ጥፋት እንከላከል” ብሎ የተደራጀውን “ሞረሽ ወገኔ” የተባለው ፤ ’ሲቪክ’ ድርጅት፤ በመዝለፍ፤ አማራ የሚባል አለ የሚሉ ሁሉ ‘ለስልጣን ጉጉታቸውን ለማርካት ሲሉ ሊጠቀሙበት የተደራጁ ሰዎች እንጂ፤ የሌለን አማራ ለመከላከል እያሉ፤ በከፋ መልኩ ሊያስጨርሱት ነው” እያለች የሞረሽን መሪዎች እና ተከታዮች ባልታረመ አንደበቷ እየዘለፈች ስትወነጅል ትደመጥ እና፤ ደቂቃ ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ምላስዋን አጥፋ “እኔ ብመረመር ጥርት ያልኩ አማራ ነኝ ከጥፈሬ እስከ እራሴ” ፤በማለት እርስ በርስ የሚምታቱ አቋሞች ልክ እንደ ፕሮፌሰሩ የሚያንጸባርቁ ሰዎችን አድምጠናል። “የለም” ሲሉ ቆይተው አንደገና “አዎ አለ” ይሉናል። የቱን እንያዝ? 

የህች ጋዜጠኛ ነበረች የምትባል ሴት የተናገረቺው አንደበቷን በሚቀጥለው ሰሞን እራሱ በቻለ በትችት መልክ እመለስበታለሁ። ስለሆነም የፕሮፌሰሩ የተሳሳተ ትምሕርት እንደ ወ/ሮ ብዙ ወንድማገኘሁ በብዙ ሺዎች ሰዎች እርስ በርስ የሚምታታባቸው ተከታዖችን አፍርተዋል። 

ጊዜው መቸም ቢሆን ጊዜው ለአማራው በከፋ መልኩ ነው እያንገላታው ያለው። ፕሮፌሰሩ የተምታታ አቁዋማቸው አይደለም ዋናው ትኩረቴ። አለ፤ የለም አይደለም። ትኩረቴ፤ ሕዝብን የማቃቃር ጽሑፋቸውን ላይ ነው ትኩረቴ። ልብ ማለት ያለበን፤ አማራ ነኝ የሚልም ሆነ አማራ አይደለሁም ብሎ እራሱን የካደ አማራም ሆነ ሌላው ወገን በአማራው ሕብረተሰብ ጥቃት ሲደርስ ዝምታን መምረጡ አሌ የሚባል አይደለም (ባለፈው ሰሞን ስለዚህ ጉዳይ በስፋት ገልጫለሁ) ከሊቅ እስከ ደቂቅ አማራ በልጆቹ የተከዳ ማሕበረሰብ ነው። ፕሮፌሰሩ ሰብአዊ መብት ተሟጋች ስለነበሩ በጎ ስራ ሰርተዋል። ወቀሳው እሳቸውን አይመለከተም (እኔ እስከተረዳሁዋቸው ድረስ)። ከወቀሳ ነፃ ያላደረጋቸው ግን አንድ ነገር አለ። ወደ ታች እንመለከታለን።  

በዚህ በወያነ ትግራይ ዘመን ለ24 አመት አማራው ጥቃት እየደረሰበት ይገኛል። ፕሮፌሰሩ “አማርኛ ተናጋሪ እንጂ አማራ አይደለሁም” ወይንም እየተጠቃ ያለው አማርኛ ተናጋሪ እንጂ አማራ አይደለም። አማራ የሚባል የለም፤ እያሉ ስለ አማራ ሕብረተሰብም ሆነ ስለ እራሳቸው ማንነታቸው የሚናገሩት “ሂፕክሪት/ዶግማ/ ግትር” ክርክራቸው እንደተጠበቀ ሆኖ ፤ አማራ የተባለ ማሕበረሰብ አማራ በመሆኑ ብቻ እየተጠቃ ፤እየተባረረ መሆኑን እሳቸውም በውስጠ ሕሊናቸው የሚክዱት አይመስለኝም።

አማራን ለማጥፋት ”በኦጋዴን ሶማሌ ክልል” ውስጥ አማራን በሚጠሉ ሶማሌዎች እየተሰነዘረ ያለው አማራን የማባረርና የመግደል ወንጀል” ከመመከት ይልቅ “ወያኔዎች፤ኦጋዴን ነፃ አውጪዎች፤ኦነጎች……የመሳሰሉ የፋሺስት ድርጅቶች” አማራን ለማጥፋት የሚፈልጉት ብትርና መሟገቻ ሃሳብ በማቀበል ለፋሽሺስቶቹ በማወቅም ሆነ ባለማወቅ “አማራን በሃላፊነት የሚያስጠይቅ፤ የሚጎዳ ጽሑፍ”  ወያኔ ከገባ በሗላ ጽፈው ለጠላቶች አበርክተዋል። ያውም በመጽሐፍ ውስጥ ታትሞ የሚነበብ! ይህ ለምን ሆነ?

ከፕሮፌሰሩ ጋርም አብሮ፤ አማራው ገበሬ ዛሬ በአማራነቱ ብቻ ለመጠቃቱ ክስተት መነሻና ቆስቋሽ ሰበቦች የስታሊናዊ/ የማኦ/የማርክስ/ሌኒን የፖለቲካ ንዳድ ያበሰለው “ጫፍ የረገጠ/አክራሪ/አልትራ/ኤክስትሪም” ግራ ዘመም አቀንቃኝና በአማራው ማሕበረሰብ ላይ ከፍተኛ ዘመቻ ሲያካሂድ የነበረ የ70ቹ የተማሪ ማሕበረሰብም አብሮ ተጠያቂ ነው።

ይህንን ስናነሳ በግምባር ቀደም የሚታወሰው ሟቹ የቀ/ሃ/ዩኒቨርሲቲ ተማሪ ዋለልኝ መኮንን ነው። ወጣቱ ዋለልኝና ፕሮፈሰሩ በአማራ ላይ ሲመሰክሩ፤ ከአንድ እናት የወጡ “መንትያዎች” ይመስላሉ። ትግርኛው “ክናናን- ምናናን” ይላቸዋል። መንተያዎች ማለት ነው። 

በቅርቡ በሞረሽ ሊቀመንበር በአቶ ተክሌ የሻው የቀረበው ./ ለፕሮፌሰር መሥፍን የመጽሐፍ ምረቃ ታዳሚዎች እና ለእርሳቸው አድናቂዎች በሙሉ፣………… የሚል ለፕሮፌሰር መስፍን ያቀረቡት የጽሑፍ ጥያቄ፤ ፕሮፌሰሩ መልስ መስጠት ይጠበቅባቸዋል። አቶ ተክሌ የሻው ፕሮፌሰር መስፍን ከላይ በተጠቀሰው መጽሐፍ ውስጥ የጻፉትን ጥቅስ መነሻ ያደረጉትን ልነሳ፡
“ ፕሮፌሰር መሥፍን ወልደማርያም፦

«ሥልጣን፣ ባህልና አገዛዝ፤ ፖለቲካዊ ምርጫ» በሚል ርዕስ በ2003 ባሳተሙት መጽሐፈዎ ገጽ 120 ላይ እንዲህ ብለዋል።

«ኅዳር 1951 ዓም ከአጼ ኃይለሥላሴ ጀምሮ እስከ ታላላቆቹ ባለሥልጣኖች ባሰራጨሁት የጥናት ጽሑፍ ስለኦጋዴን የሚከተለውን ብየ ነበር።  «በጠቅላላው የአማሮቹና የሱማሌዎቹን ግንኙነት ላስተዋለው፣ አማራዎቹ የሚያሳዩት የበላይነት መንፈስና በሱማሌዎቹ ላይ ያላቸው ንቀት፤ ሱማሌዎቹ በበኩላቸው ያላቸው ኩራት በአማራዎቹ ንቀት እየተነካባቸው የሚሰማቸው ስሜት በአንዴ ይታወቃል። ``ቆሻሻ ሱማሌ``በያለበት የሚሰማ ነው። በዕድሜም ሆነ በክብር ከፍ ያሉትን ሱማሌዎች እርሰዎ እያለ የሚያነጋግራቸው በቁጥር ነው።---እንደዚህ ዓይነቱ የሌለውን የአማራ የበላይነትና የሱማሌ የበታችነት በግልጽም በድብቅም የሚያሳይ መንፈስ የሱማሌዎቹን ልብ በጣም እንደሚያሞክረው የሚያጠራጥር አይደለም። ሱማሌዎቹ ልክ እንደአማራዎቹ መሆናቸውን ሁሉ የተገነዘቡት አይመስሉም፤ ሱማሌዎቹም ሁሉ የሚውቁት አይደለም።» ………………………………………………”

( መስፍን  ወ/ማርያም «ሥልጣን፣ ባህልና አገዛዝ፤ ፖለቲካዊ ምርጫ» በሚል ርዕስ በ2003 ባሳተሙት መጽሐፈዎ ገጽ 120)

አቶ ተክሌ እንዳሉት ፕሮፌሰሩ ከምን ጥናት ነስተው ነው ዛሬ አማራ በጅምላ እየተገደለ ባለበት ወቅት እንዲህ ያለ ውንጀላ ሊወነጅሉት የተነሱት በምን መነሻ ነው? የሚል ጥያቄ ይቀሰቅሳል። አሁን አማራው በገፍ እየተገደለ ባለበት ጊዜ እውን ከአንድ ምሁር የሚጠበቅ ነው? አማራው ብትር በበዛበት ሰዓት መወንጀሉ ጥቅሙ ምንድ ነው?
ሸመገሉ እንዳልል፤ ኣእምሮዎ ከወጣት አእምሮ በተሻለ የሚሰራ መሆኑን የሚያጠያይቅ አይደለም። ቢያምኑትም ባያምኑትም፤ ወያኔም ሆኑ ሶማሌዎቹ አማራን ለማዋከብ የእርስዎን ድጋፍ በእጅጉ ይፈልጉታል።ዋለልኝን እንደ አርበኛ የሚቆጥሩት ወያኔዎች፤ሻዕቢአዎች፤ ኦነጎችና ኦጋዴን ሶማሌዎች ይህንኑ አርስዎ የሰነዘሩት ውሸት እየዋሸ አማራውን መሰረተ ቢስ በሆነ ክስ በመወንጀሉ ነው የሚያከብሩት። ዋለልኝም ሆነ እነኚህ አገር በቀል ፋሺስት ግልገሎች፤ጣሊያኖች ያቀበሉዋቸውን የሃሰት መረጃ ነበር ተቀብለው አማራውን ሲወነጅሉ የኖሩት። ለርስዎ አይንት ሊቅ የተደበቀ ታሪክ አይደለም።  
 
በአማራው ላይ የጥላቻ ትኩረት እየተደረገበት፤ ሂደቱ እያደገ የመጣው፤ ከውጭ በኩል በውጭ ጠላቶች የተነዛ አገር ማፍረሻ መረጃ፤ ከአገር ውስጥ ደግሞ ዋለልኝና መሰሎቹ ያደለቡት ውሸት ሥር ሰድዶ ‘አማራ’ ለዚህ ጥቃት ተጋልጣል። እርስዎ ለሶማሌ ኦጋዴኖች በሰጡዋቸው ምስክርነትዎ እና ዋለልኝም  ደግሞ “ብሔር፤ብሔረሰብ….ሕዘቦች” ብሎ አገር ለመበተኛ እንዲያመች በኮሚኒስት አጠራር ለሰየማቸው የኢትዮጵያ ነገዶች በጸረ አማራ ሃይላት ምስክርነታችሁ ቢሞገስም፤ በማይፋቀው የታሪክ ማሕደር “መንትያዎች” ሆናችሁ ተመዝግባችሗል። 

በትግርኛ አንድ ምሳሌ አለ፡ “አድጊ ተማህሊላ በላዒዓ አምጺኣ” ( አህያ ጮሃ ጮሃ የሚበላትን ጅብ አመጣች)፤ እርስዎ አማርኛ ተናጋሪ እንጂ አማራ አይደለሁም ቢሉም፤ ወያኔም ሆነ የወያኔ ሎሌዎች በየፓልቶኩ እርሰዎንም የሚያየውና የሚጠራው በነፍጠኛነት ነው። ወያኔ አማራን በሚመለከትበት መነፅር እርስዎንም አብሮ ያይበታል። ስለሆነ እርስዎም በሞላ ጎደል የወያኔ ተጠቂ እንደሆኑ የሚካድ አይደለም (ስለ እርስዎ ወያኔ ትግሬ፤ ጸሃፊዎች በትግርኛ ቋንቋ የሚጽፉት እና በራዲዮናቸው የሚንዘላዘሉበት ባለጌ ምላሳቸው ቢያነቡና ቢያደምጡ ኖሮ፤ ምንኛ በአማራ አንደተመደቡ ያውቁት ነበር)። እስኪ የእርስዎን እና የዋልልኝን የሃሰት ፕሮፓጋንዳ ለሶማሌ ኦጋዴኖች ያቀበላችሗቸው ብትር ስራ ላይ ውሎ ተተርጉሞ ፍሬ አፍርቶ ምን ውጤት አንዳሰስገኘ ከዚህ በታች ያለውን እንመልከት፡

ክቡር ፕሮፌሰር ሆይ! 

ወያኔ ከትግራይ በረሃ ገስግሶ አዲስ አበባን ተቆጣጥሮ የሽግግር መንግስት ተብየው ሲመሰርት፤ የተሰነዘረን ንግግር እርስዎ አይስቱትም። ለአንባቢዎቼ ላስታውስ “አማራና ኦርቶዶክስን እንዳያንሰራራ አከርካሪውን ሰብረነዋል” በሦስቱ ቀለማት መሃል  ነጭ መስመር ሆኖ ከመሃሉ ጥቁር ቀለም ይሰመርበት!”… “ጠላታችን ከባንዲራው በስተጀርባ ያለው ክፍል ነው” .... “ነፍጠኛው ይህንን ባንዲራ እያውለበለ...” “ይህ ጨርቅ!...” እያሉ በዕብዶች አዳራሽ ላይ ዕብዶች በብሔራዊ ሰንደቃላማችንና በአማራው ላይ የሰነዘሩትን ንግግር ምን ይሉ አንደነበር ሰምተናል።

ዛሬ ደግሞ በቅርቡ ከአንድ አመት ተኩል በፊት ማለትም በ2014 ዓ.ም እንደ ጎርጎርዮስ ዘመን አቆጣጠር ቅድመ አያቶቻቸው የኖሩበት፤ እንዲሁም ባለፉት አርባ እና ሐምሳ አመታት በጅጅጋ ከተማ ሲኖሩ የነበሩ የጅጅጋ የአማራ ማሕበረሰብ ኗሪዎች ለኢሳት የጻፉትን ደብዳቤ ልጥቀስለዎት፦

እነኚህ ማሕበረሰቦች በሶማሌዎች እደረሰባቸው ያለውን የማባረር ዘመቻ እና ሌሎች የግፍ ተግባሮች እየተከታተለ አገር ውስጥ የሚያስተጋባላቸው የጋዜጣም ሆነ የራዲዮ ድርጅት ወይንም የፖለቲካ ተቃዋሚ ባለመኖሩ ፤ በ2014 እንደ አውሮጳ አቆጣጠር የጅጅጋ ኗሪዎች የሆኑት አማራዎች፤  ዋሺንግተን (አሜሪካ) እና አምስተርዳም (አውሮጳ) ውሰጥ ለሚገኘው በውጭ አገር ሃይላት የገንዘብ ዱጎማ ለሚንቀሳቀሰው “ኢሳት” ለተባለው ሻዕቢያዊው የግንቦት 7 ራዲዮና ቴ/ቪ የጻፉትን ደብዳቤ እንዲህ ይላል።

( “ ቤታችን እየተነጠቅን ለጎዳና ተዳዳሪነት ተጋልጠናል። እስካሁን ድረስ በከተማዋ ውስጥ የነበሩት የአማራዎች ዋና ዋና የንግድ ተቋማትን እየተነጠቁ ለሶማሌ ተወላጆች እያስረከቡ ስለተደረገ አብዛኛዎቻችን ከተማውን እየለቀቅን ወደ መሃል አገር ሄደናል።

ተወልደን ያደግንበትን አገራችን አንለቅም ያሉትንም ፌደራላዊ ጫናዎች እየተደረጉ ከተማዋን ለቅቀው እንዲወጡ በደብዳቤና በቃል ትዕዛዝ ተነግሯቸዋል።

የአንድ ቤሔር የበላይነት በሰፈነበት መልኩ “አማራ ወይንም ሐበሻ”  የሚል መጠሪያ ተደርጎልን፤ እነሆ ከህጻናት  እስከ ትልቅ በመንገድ  በቢሮም እየተሰደብን መኖራችነን ሳያንስ፤ አሁን ደግሞ ያለምንም  ልዋጭ ቤቶቻችን ተቀምተን ሜዳ ላይ ተጥለን እንገኛለን።

 የኛ ልጆች አንደልብ መንገድ ላይ መሄድ አይችሉም፤ ሱሩ የለበሰች ሴት  ‘አማራ ነች’ እየተባለ በፖሊስ በዱላ ትደበደባለ፤ች። ማን ፖሊስ ማን ሃላፊ እንደሆነ በማናውቀው ሁኔታ የ “ሸሪዓ ፍርድ ቤት”  ተቋቁሞ ቤቶቻችን እንድንለቅ እየተደረገ ነው። ተወልድን ባደግንበት አገር  አንደ ሁለተኛ ዜጋ  እንደ ቆሻሻ እየታየን ነው ብለዋል።”
 አንድ ስማቸው እንዲገለጽ ያልፈለጉ የከተማዋ ኗሪ በከተማዋ የመኖር ስሜታቸው እየተሟጠጠ መሄዱ ደግሞ በስልክ እንዲህ ሲሉ ተናግረዋል።

 “በዚህ አካባቢ የመኖር ስሜታችን ተሟጥዋል።  ያፈራነውን ያለንን ነገር ለቀቅቀን ለመውጣት እየተዘጋጀን ነው። ሰላሳ እና አርባ አመት እና ከዚያም አመታት በላይ የኖርክብትን ቦታ ለቅቀህ ስትሄድ ዝም ብለህ ወፍ አይደለህ፤ በርረህ አትሄድም። አንዳንድ ያፈራሃቸው ነገሮች ሊኖሩ ይችላሉ፤ ልጆች ይኖራሉ..አንዳንድ ንብረቶች ይኖሩሃል… እነሱን ጥለህ አትሄድም፤ አጋጣሚና ዕድል ይገኝ እንደሆነ ብለን፤ አንዳንዶቻችን ያንን እንደምንም ብለን እያስተካከልን ብለን ነው እስካሁን እየተንገዳገድን ያለነው። የወደፊት በዚህ ከታማ የመኖሩ ተስፋ እንኳን እንጃ!..እንጃ!” ) 

ሲሉ አማራዎች እንደ ሶማሌ እስላም “ሸሪዓ ፍርድ ቤት” ቀርበው ንብረታቸው እያስረከቡ ወደ አገራችሁ ሂዱ እየተባሉ እንዲባረሩ ሲወሰንባቸው; ልጃገረዶች ልጆቻቸውም “ሱሪ” ታጥቃ ስትሄድ አንደ ሳውዲ አረቢያ “ሰፋጢን” ተብለው በሚጠሩ የሃይማኖት ፖሊሶች “አማራ/ሐበሻ” እየተባሉ በዱላ ይደበደቡ እንደነበር አማራዎች በጅጅጋ የደረሰባቸውን ግፍ አስረድተዋል።

ከዚህ ሌላ የኦጋዴን ሶማሌ ክልል ፕረዚዳንት ተብየው ጸረ አማራ ዘመቻ በማካሄድ፤ የአካባቢው ስማግሌዎችን ሰብስቦ፤ አማራ የሚባል ጠላታችን ነው “ትግሬዎች” ወዳጆቻችን ናቸው፤ እያለ ሶማሌዎች አማራውን እንዴት ማባረር አንዳለበትና፤ ማጥቃት አንዳለባቸው የቀሰቀሰበትን፤ በአውዲዮ ቪዲዬ የተቀረጸውን ማስረጃ ይህንን ይመልከቱ’-

 TPLF puppet Somali president secret video exposed TPLFs hate against Amhara May 8 2013
https://youtu.be/Kj2sNJ5B2j0

እንግዲህ ክቡር ፕሮፌሰር መስፍን ይህ ግፍ ሲፈጸም በመጽሐፍዎ የዘገቡት በመረጃ ያልተረጋገጠ አማራውን የመወንጀል ዘመቻዎ የአካባቢው የፖለቲካ የፋሺስት ግልገል ድርጅቶችና እና የአካባቢው አክራሪ እስላሞች በአማራው ሕብረተሰብ ላይ ያነጣጠረ የተቀነባባረ ጥቃት ልክ አንደ እነ “ታምራት ላይኔ” ንግግር ለዛሬው ግፍ የእርስዎ ምስክርነት ተጨማሪ ብትር አላቀበልኩም ሊሉ ይችላሉ?
ዋለልኝ መኮንን
 
ይህ ፎቶግራፍ በዋናነት የተዘገበውና ድረገጽ ላይ እንዲሰራጭ ያደረገው በቅድሚያ ስያትል ለሚኖረው ለዋለልኝ ጓደኛ ለአቶ ዘውገ ፋንታን አመሰግናለሁ (በሁለታችን መሃል የከረረ ቅራኔ ያለን ቢሆንም ንብረቱ ነውና ምሳጋና አቀርብለታለሁ)። ይህ ካልኩ ዘንድ፤ ይህ ወጣት እጅግ መረን የለቀቀ ግራ ዘመም ፍልስፍና ያጠቃው፤በራሱ ላይ እና እሱን በፈጠሩ የአማራ ማሕበረሰብ ላይ መሰረተ ቢስ ውንጀላ በመሰንዘር፤ የኢትዮጵያን አንድነት ለመበተን፤ የዘር ጽዳት ለማካሄድ ታጥቀው የተነሱ አክራሪ ሃይላትና በታኝ/ኒሂሊስት ቡድኖች እንዲሁም እንደ እነ ወያኔና ኦነግ የመሳሰሉ ግልገል ፋሺስቶች፤ የዓላማቸው መሪ ተዋናይና ታላቅ ሰማዕት አድርገው በክብር የሚያዩት ወጣት ነው።

የዚህ ወጣት ታሪክ በጓደኛው በዘውገ ፋንታ የተዘገበው ዘገባ የሚያመለክተው (የወቅቱ ወጣቶች አብዛኛዎቻችን ዋለልኝ በወቅቱ
 ማን መሆኑን የምናውቅ ብንኖርም) ዋለልኝ በአዲስ አበባ
ዩኒበርስቲ ማህበርና (USUAA) በብሔራዊ የኢትዮጵያ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ማህበር (NUEUS) ከፍተኛ አመራር አባል ሆኖ ።የወቅቱ ማርክሳዊና ሌሊናዊ ግራ ዘመም የፖለቲካ አቀንቃኝ ዋና ነበር። ዋለልኝ ከነ ማርታ እና ጀብሃ ከላካቸው አንዳንድ ሰዎች ጋር ሆኖ በ1965 ዓ.ም ወደ ውጭ አገር አይሮፕላን ጠልፎ ለመውጣት ሲሞክር በጸጥታ ሃይሎች በጠለፋው ግብግብ ሰማይ ላይ እንዳለ ሕይወቱ አልፏል።
ለጠለፋው መነሻ ጓደኞቹ እንደሚሉት “ጀርመን በርሊን ውስጥ የኢሕአፓን ስብሰባ ለመካፈል ወይንም በዛው ለመቀላቀል፤ ከአገር የሚወጣበት መንገድ ስላጣ አማራጭ ስላልነበረው አይሮፕላን ጠልፏል። ሲሉ ሃሳባቸው ይገልጻሉ። ሆኖም እኔ ከኤርትራ የጀብሃ ፋይሎች እንደተረዳሁት ግን ፤ የጠለፋው ቀስቃሽ ፕላን የተቀነባበረው በኤርትራኖች አንደሆነ ነው። ከነ ዋለልኝ እና ማርታ መብራቱ…..በጠለፋው የተሳተፈው  “ራዲዮ” እየተባለ በጀብሃ የቅጽል ስም የሚታወቅ ሕጋዊ ስሙ “ሳሙኤል ዮሃንስ” ቢሆንም ስሙን በመቀያየር ታደሰ መሐመድ፤ዑስማን መሓመድ በመባልም ይታወቃል፤። ይህንን ለማወቅ እኔ በኢትዮፕያን ሰማይ ድረገጽ በጻፍኩት፤ ከዚህ በታች ልጥቀስ፤-

ወደ ሊቢያ በተካሄደዉ ጠለፋ ተሳታፊ ኖሮ እንደገና ለሁለተኛ ጊዜ ከገረግር -ሱዳን በረሃ የአይሮፕላን ጠለፋ ለማካሄድ ታዝዞ፤ ወደ አዲስ አበባ ተመልሶ በመሄድ በንግድ ሥራ እየተሰማራ የሚኖር በማስመሰል ዋለልኝን በፍቅር ያኖሆለለችዉን መልከመልካምዋፍያሚታ-ጊላይ” (በማርታ መብራህቱ) በኩል ዋለልኝን ለጠለፋዉ ስራ እንዲስማማ እና ጃንደረባዎቹም እንዲቀላቃሏቸዉ በማድረግ የተገንጣዮቹን የጠለፋ ስራ ለኤርትራዊያኖች ጥቅምና ተጨማሪ ሃይል እንዲሆኑ አድርጓል።ጠለፋዉ ከተከናወነ ከጥቂት  ሰዓታት በሗላ  ጠላፊዎቹ እነማን እና ለምን አላማ እንደነበር ተገንጣዮቹ ባስተላለፉት የራዲዮ መልዕክት በወቅቱ ተገልጿል። አማኑኤል ዮሃንስ ለማን እየተጋለ እንደነበር ማን እንደላከዉ ከዛ በፊት በሊብያዉ የጠለፋ ተልእኮ የተሳተፈ መሆኑን በጠለፋ ስራ መሰማራቱን ዋለልኝ በሚገባ ያዉቃል።ሃሎ!!!!ኵሩሩር!!!! 

በዋለልኝ ዙርያ የነበሩ ኤርትራዊያን ጃንደረባዎቹ አብዛኛዎቹህዝባዊ ሓይልታት (ቡድን 2) ተብሎ የሚታወቀዉ የኢሳያስ ተከታዮችና ተዋጊዎች ነበሩ።በጠለፋዉ ወቅት የተሰማሩት 3 ኤርትራዊያኖች እና 4 ኢትዮጵአዊያን ነበሩ።ማርታ መብራህቱ፤ አማኑኤል ዮሃንስ ( “ራድዮ”) እና ዮሃንስ ፍቓዱ። በዚህ በኩል ደገሞ ዋለልኝ መኮንን፤ጌታቸዉ ሃብቴ ፤ተስፋየ ቢረጋ፤ታደለች ኪዳነ ማርያም። ነበሩ።….አማኑኤል ዮሃንስ (በሁለተኛዉና በሦስተኛዉ ዙር ጠለፋ ከነ ዋለልኝ የተሳተፈዉ ነዉ)ደበሳይ ገብረስላሴ፤ ሙሴ ተስፋሚካኤል፤ ዮሃንስ ስብሃቱ፤ ሙሴ ተስፋሚካኤል (አይሮፕላናችንን ጠልፈዉ ሊቢያ የገቡ ናቸዉ)።ዮሃንስ ስብሃቱ እና ሙሴ ተስፋሚካኤል 1973 (ፈረንጅ) በተነሳዉ የዉስጥ አመጽ/እንቅስቃሴ (መንካዕ- ተብሎ በሚታወቀዉ የኢሳያስ የአፈና አርምጃ እነደተገደሉ ይታመናል።)” 

ዋለልኝ ከነበረው እውቀትና ገናናነት እና ማርክሳዊ ርዕዮት ከጸረ አማራዎቹ  ከኤርትራኖቹ ጋር ሚስጢርም ሆነ ግንኙነት በግሌ የሚያውቀው ነገር የአልነበረውም ማለት አይቻልም። ምክንያቱም የእጅ ቦምብና ሽጉጥ የመጣው ከአስመራ በኤርትራኖች በኩል እንደሆነ አንዳንድ ምንጮች ያመላክታሉ።” መረሳት የሌለበት ማርታ ኤርትራዊት ነች፡ የጀኔራል መብራህቱ ጎይተኦም ልጅ ነች። እስከዛሬ ድረስ ወንድሟ የሻዕቢያ ተሞዳሟጅ ነውም ይባላል።” (ምንጭ የራሴው/ኢትዮጵያን ሰማይ)

እሷም እንዲሁ በዛው ወቅት የለችበትም ማለት ትንሽ የዋህነት ያሰኛል። ግንኙነቱ ምናልባትም በማርታ በኩል ዋለልኝን ማሳመን ሊሆን ይችላል። የቅርብ ጓደኛ ስያትል የሚኖሮው ወለየው ዘውገ ፋንታ ስለ ጓደኛው ዋለልኝ አንዲህ ሲል “Martha was a beautiful woman, but extremely uptight. She was the only person I could not break into laughter. If Wallelign walked to the bathroom or to the kitchen, she would stand and look. The first day I saw her with Wallelign, I asked him if she were his girl friend. He smiled and said: “Ziga.” በጽሁፉ ነግሮን ነበር።

ስለዚህም ዋለልኝ በአማራ ላይ ያሳደረው የተዛባ አመለካከቱ፤ ከሴት ጓደኛው ከማርታ ጋር የነበረው ንኪኪ ሳይጎትተው እንዳልቀረ እገምታለሁ። በወቅቱ ክስ ሲመሰረት፤ ማርታ በወቅቱ የቀ.ሃ/ሴ ዩኒቨርሲቲ ሕክምና  ኮለጅ ተማሪ እንደመኖሯ ሁሉ፤ አይሮፕላን በመጥለፍ ለኤርትራ ነፃ አውጪዎች በሕክምና ፈቅዳ ለማገልገል እንደነበር፤ የታሪክ ምንጮች ከተከሰሰችበት ማሕደር ያገኙትን ይጠቅሳሉ። ልብ ማለት የሚኖርብን በረራው ከተጠለፈ በሗላ የኤርትራ ነፃ አውጪ ድርጅት ወኪል የጠለፋው ምክንያት ለኤርትራው ቡድን ድጋፍ ለመስጠት እንደነበር ከሊቢያ መግለጫ ሰጥቶ መኖሩን ልብ በሉ።

ያም ሆነ ይህ፤ ኤርትራኖች ዛሬም አሽከር አላጡም። የኢሳት ጋዜጠኞችም ሆኑ ግንቦት 7 የተባለው ድርጅት ሻዕቢያን ለማሞገስ በወያኔ እግር ለመተካት ብቅ ብሎ ወገቡን አለጥልጦላቸዋልና ከጠላት ጋር የመሞዳሞድ ክስተት ለታሪክ ማሕደር እንተወው።አሁን ኤርትራ ምድር ውስጥ ሆኖ የእነ “ፍረወይኒ” የቡና ጣዕም በማድነቅ እየጻፈ ያለው፤ ኤፍሬም ማዴቦ፦ “ነፍጠኞችን ቁጥጥር ሥር አድርገንላችሗል” ብሎ ለሻዕቢያ “ፈስቲቫል” ተሰብሳቢዎች ኦክላንድ ካሊፎረኒያ ውስጥ በአንደበቱ አረጋግጦላቸዋል። ይህች ቡቹላ ካሁኑ እንዲህ የጮኸች ስትድግ …….!!!!! ምን አንደምታደርግ  አያሰኛችሁም?

ይህንን እንለፈው እና፤ ዋለልኝ አማራ ሆኖ አማራውን በጅምላ የሚወነጅል እጅግ አደገኛ “አልትራ” (ያልተገራ) ርዕዮት ሲያስፋፋ የነበረ unfairly/ ከምክንያታዊ ውጭ በሆነ መንገድ አማራን የወነጀለና ጥላሸት የቀባ ወጣት ነበር።

ምኒሊክ ሳልሳዊ ተባለ የግንቦት 7 ጸሐፊ እንዲህ ይላል።

ዋለልኝ መኰንን በአንዳንድ ግለስቦች እንደ ተራ አውሮፕላን ጠላፊ ቢታይም በኢትዮጵያ የተማሪዎች እንቅስቃሴና ለኢትዮጵያ ሕዝብ ነፃነት በተደረገው ትግል ታሪክ ውስጥ ያደረገው ግንባር ቀደም ተሳትፎውና የብዕሩ ለዛ ሚዛናቸው የደፋ ነው።”  ይላል።

እርግጥ ዋለልኝ ጠንካራ ጸሐፊ ነው። ለዛነቱ ምን ላይ እንደሆነ ባይገባኝም፤ ዋለልኝ ሲጽፋቸው የነበሩ ጽሑፎች ከትምህርቱ ደረጃ አኳያ እጅግ የመጠቁ እንደነበሩ አይካድም። ከጽሑፎቹ መካካል አንዱን በምሳሌ ብንወስድ ለዛ ያለው ሳይሆን ለዛ ቢስ የሆነ አማራውን ሕብረተስብ የሚወነጅል፤ለዛሬው የአማራ ሕብረተሰብ ስቃይ ከፍተኛ ብትር ያቀበለ “አናካሽ” ጸሐፊ ነበር (ነብሱ ይማረው፡ ከይቅርታ ጋር! ታሪክ ትቶልናል እና እንነጋገርበታለን። እየተነጋገርን ያለነውም ከእርሱ ጋር ሳይሆን የሱን ማሕደር የተሸከሙትን እና በመንገዱ የተከተሉትን ሻዕቢያዎች፤ወያኔዎች፤ኦነጎችን እና ወዘተ…ድርጅቶችን ነው)።

አማራን በመዝለፍ የታወከቀው የወያኔው አማርኛ ተናጋሪው ክፍል የብአዴን ድርጅት አመራር አባል “አለምነው መኮንን” የተባለው ሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን ሳይጨርስ ወደ ወያኔ አሽከር ወደ ብአዴን ድርጅት ተቀላቅሎ፤ ዛሬ ስልጣን ተሰጥቶት አማራውን “አማራ በባዶ እግሩ እየሄደ በስንፋጭ ትምክሕት የታጀለ መርዝ ንግግሩን እስካሁን ድረስ ማቆም ያልቻለ፤ትምክህት እየተመገበ ያደገ፤……እያለ  “የብአዴን ሁለተኛ ሰው” የሆነው ባሕርዳር ውስጥ ተቀምጦ የተናገረው ዘለፋ፤ በእኔው ድረገጽ በኢትዮጵያን ሰማይ ላይ “የአመቱ ባለጌ ሰው ተብሎ” የተሰየመው አለምነው መኮንን እና  ዋለልኝ መኮንን እንደ አጋጣሚ ሁለቱም “ወሎየዎች” ናቸው። ባለመታደል ሆኖ አንዳንድ ጊዜ ልጅ አባቱን ይዘልፋል፤ ይክዳል የሚባልበት ውቅት አለ። እነኚህም ለዚህ ምሳሌ የሚመቹ ናቸው።

 የነ አለምነህ መኮንን አማራን የመዝለፍ የቅጥረኛነት ባሕሪ ሲሞገስ ሰምተናል። “ሲሳይ መንግሥቴ አዲሱ” የተባለ የብእዴን ታጋይ የነበረ ዛሬ በወያኔ ሥርዓት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ የሕግ እና የፌደራልዝም መምሕር የሆነው ግለሰብም፤ ዘለፋው “ወርቅ የሆነ አባባል” ሲል አማራን መስደቡን ደግፎታል።

ወደ ዋለልኝ ስንመለስ፡ ሕዳር 10/1961 በታታመው “ታገል በሚባለው ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች መጽሔት ላይ ‘የብሔረሰቦች ጥያቄ በኢትዮጵያ’ (On the Question of Nationality in Ethiopia) አማራውን ክፉኛ ወንጅሏል። ባገሪቱ ውስጥም የመድብ ትግል ሳይሆን ዋነኛው ጥያቄ የብሔር ጥያቄ ችግር ነው፤ በማለት ማርክሳዊ አመለካካቱን በማስፈር ጨቋኛምአማራ ብሔርነች ሲል ይከራከራል። 

ይህ በዚህ የተሳሰተ አባባሉ ሳይገታ ዋለልኝ የገዛ አገሩ “ፌክ ኢትዮጵያ፤የአማሮች ኢትዮጵያ…..”  ይላታል። እርሱ አማራ ሆኖኢትዮጵያን የአመሮች ንብረት ነች! ኢትዮጵያዊ ለመሆን መታወቂያዉ አማራን ስም መያዝ ነዉ” ፤ካልሆነ ዜግነትህ አይከበርም፤ አይታወቅልህም” እያለ የነዛዉ ጸረ-አማራ ዉዥምብርና የውሸት ፕሮፖጋንዳዉ ከኤርትራዊያን ተጨምቆ ወደ እሱ ተላልፎ እንደ ራሱ ቅባት ሲጠቀምበት የነበረው ጸረ አትዮጵያ አፍራሽነቱ መረን የለቀቀ ነበር። 

በጽሑፉ እንደተነተነው ግን የኤርትራኖች ትግል እንደ ኮለኒ የተመለከተው አልመሰለኝም። እሱ ሚለው የብሔረተኛ ትግላቸው በወዝ አደርና ዓለም አቀፋዊ እይታ ያላቸው ሰዎች ሳይሆን በከበርቴዎች እና በአካባቢ ባለርስቶች የተመራ ስለሆነ ትግላቸው ከእኛው ጋር አይሄድም፤ ስለሚል ስለ ኤርትራ ግልጽ አቋም አላስቀመጠም። እንደተረዳኝ ከሆነ።

ዋለልኝ ብርቱ አንጎል እንደነበረው በምንም መልኩ የሚካድ አይደለም። ሆኖም ያ ብርቱ አንጎል አማራ ላይ ሲደርስ ፍርስርሱ የወጣ ብቻ ሳይሆን አማራን በሃሰት በመወንጀሉ እጅግ አስገራሚ ክስተት ነው። ምናልባትም ወደ እዛው ሊያመራው ያስቻለው መንገድ ብዬ የምጠረጥረው ማርታ ግንኙነት ይሆን? ትግሬው የፍቅርን ምንነት ሲገልጽ “ፍቕሪ ዑውር” ይለዋል (ፍቅር ዕውር ነው) ፍቅር የወንድ እቅጣጫን ያሳስታል፡ መጽሐፍ ቅዱስም ተናግሯል።ሃይለኛ ፖለቲከኛ እና ሽፍታ በሴት ይማረካል።  ሌላ ምክንያት ይኖሮው ይሆን? መልሱ ለታሪክ እንተው እና፤- 

On the Question of Nationality in Ethiopia- by Wallelinge Mekonnene Arts IV, HSIU Nov. 17, 1969 ብሎ ሳላመነታ ለክርክር (ፕሮቨኬሺን) አቅረቤዋለሁ ያለለትን ወረቀቱ እንዲህ ይላል፦  “አደራ የምላችሁ ከጽሁፌ ውስጥ ሐረግ /አረፍተ ነገር በመምዘዝ ከዋናው ተልእኮ በመነጠል የማይሆን ትርጉም ከመስጠት ተቆጠቡ” ይላል። ዋለልኝ ይህን ይበል እንጂ በአማራ እና የኢትዮጵያ ሕዝብ ምንም ባስተዳዳር ቢበደልም መስዋእት ለመሆን ሲሽቀዳደምላት የነበረው ሕዝቧ “ኢትዮጵያ ብሔራዊ ስሜቱ የውሸት ነበር” “ምንም አልነበረውም” ሲል  የሰነዘረው መሰረተ ቢስ ውንጀላው ሐረግን በመምዘዝ መተርጎምና መጠምዘዝ አላስፈለገኝም። መልዕክቱ ቀጥተኛ እና ግልጽ ስለሆነ ስለ አማራ እና ኢትዮጵያ ምን ብሎ አንደጻፈ/እንደተከራከረ አሳያለሁ። ላሰምርብት የምፈልገው ጉዳይ ግን “ዋለልኝ አገሩ አይወድም” የሚል ክርክር አይደለም እየተከራከርኩ ያለሁት። እያልኩ ያለሁት ጠንካራ አገር ወዳድ ሆኖ እያለ፤ ዘመናይ አስተዳዳርና ፍትሕ ፈላጊ ቢሆንም፤ ስለ አማራ እና በገዛ አገሩ የነበረው ግንዛቤ የተበረዘና ጠንከር ባለ ቃላት ልጠቀምና “አገሪቱን ለብጥብጥ የሚያነሳሳና የተመረዘ” መርዘኛ እና በታኝ አቅጣጫ የሚያራምድ ነበር ነው አባባሌ።

ፕሮፌሰር መስፍን እና ዋለልኝ ልዩነታቸው “ፕሪፌሰሩ“ አማራ የሚባል የለም ሲሉ፤ ዋለልኝ ደግሞ አማራ የሚባል አንደነበር ነው በወቅቱ ግልጽ ያደረገው። ያ ካልሆነ አማራን በመወንጀሉና ጥላሸት በመቀባት ረገድ ልዩነታቸው ብዙም አይራራቁም።
 ዋለልኝ አንዲህ ይላል፡

…. the Question of Nationalities-some people call it ridiculously tribalism-but I prefer to call it nationalism.”

“….What are the Ethiopian people composed of? I stress on the word peoples because sociologically speaking at this stage Ethiopia is not really one nation. It is made up of a dozen nationalities with their own languages, ways of dressing, history, social organization and territorial entity.


And what else is a nation? It is not made of a people with a particular tongue, particular ways of dressing, particular history, particular social and economic organization? Then may I conclude that in Ethiopia there is the Oromo Nation, the Tigrai Nation, the Amhara Nation, the Gurage Nation, the Sidama Nation, the Wellamo [Wolayta] Nation, the Adere [Harari] Nation, and however much you may not like it the Somali Nation.”

የነ “ፋኖን” መጽሐፍ በማንበብ በስሜት የተወነጨፈው ወጣቱ ዋለልኝ  “አገር ማለት አንድ የቋንቋ ልሳን፤ አመጋገብ፤አለባበስ፤ አንድ የተሳሰረ ማሕበራዊ፤ምጣኔ ሀብታዊ፤ እና ተመሳሳይ የጋራ ታሪክና ድምበር፤ ሲኖረው ብቻ ነው አገር/ብሔር ወይንም አንድ ሕዝብ ሊባል የሚቻለው፡ ካልሆነ ግን ኢትዮጵያ የብሔሮች ስብስብ እንጂ፤ ይህንን ያላሟላች ባሁኑ ጊዜ እራስዋ የቻለች አንድ ወጥ የሆነች አገር አይደለችም”። ይላል። ብሔር በትክክለኛ ትርጉሙ “አገር ማለት ነው”። ዋለልኝ የሚለን ደግሞ ኢትዮጵያ የተለያዩ አገሮች ያቀፈች ብሔር/አገር ነች ይለናል። አገሮች የሚላቸው ደግሞ ሲተነትን ኦሮሞ ነሺን/ ብሔር/አገር አማራ ነሺን/አገር/ብሔር ሲዳማ ጉራጌ ነሽን/ አገር ወዘተ…ወዘተ. የተባሉ አገሮች በኢትዮጵያ ውስጥ አሉ። ይላል። 

የፋኖን መጽሐፍ አንባቢው ዋለልኝ ሊቃጣው የፈለገው “ኢትዮጵያ የተጠቀሱትን አገሮች/ብሔሮች ኮሎኒያሊሰት ነች” ለማለት ነው።
እንደ አገር ሳይሆን አንደ ጭቃ ተጠፍጥፋ አማራዎች እና ትግሬዎች
ያገጣጠሟት አሁንም የሚገዝዋት “የውሸት ስራ የሆነች አገር በመባል የምትጠራ “ፌክ ኢትዮጵያ” የምትባል በአማራ ገዢዎች የሚቀሰቀስ ኢትየጵያዊ ስሜት እንጂ በውስጧ የሚኖሩ ኗሪዎቻ ኢትዮጵያዊ ብሔራዊ ስሜት የሌላቸው የውሸት አገር ነች” ሲል ይወነጅላል። ዓድዋ፤ ማይጨውና የመሳሰሉ ኢትዮጵያዊነት ስሜትን ለዓለም ያስመሰከረ ሕዝብ  “በውሸት ስሜት” የሚነዳ ሲል ሕዝብን  ይዘልፋል። ስለ አገሪቱ ብሔራዊ ስሜት የመሰከሩ የውጭ የታሪክ ሰዎችም አብሮ ይገርፋቸዋል። 

PREVAIL – THE WAR IN AFRICA THAT CHANGED THE WORLD [Book Trailer]
https://youtu.be/iN3wCyfDbwY

በምንሊክም፤ በሃይለስላሴም ዘመን ጠላት አገሪቷን ለመውረር ሲመጣ፤ ኦሮሞ፤ አማራ፤ትግሬ፤ጉራጌ፤እስላም ክርስትያን ሰይል ባብዛኛው ፤በብሔራዊ (ሃጋራዊ) ስሜት ተነስቶ ጠላት ድል በመምታት፤ ሊደርስ የነበረው ውርደት ቀንሶ አንዳንዴም ጭራሽኑ
ዓለም በሚያስገርም ጀብዱ ተዋግቶ ጠላትን አሳፍሮ መልሶዋቸዋል። እነኚህ  ልባቸው፤ቀ፤ቀባቸው፤ ሕሊናቸው አካላቶቻቸው ሁሉ ባገር ፍቅር፤በብሔራዊ ስሜት የተገነባ ነው።
ያውም በተደጋጋሚ! እነ ዋልልኝ “ፌክ’ኢትዮጵያ፤ “ስሜተ ቢስ ዜጎች፤ እያለ ያዋረደው ሕዝብና አገር።ዋልልኝ ያ ሁሉ ጀግንነትና ጀብዱ፤የገዢ መደቦች ብሔራዊ ስሜት ያነሳሳው፤የገነባው እንጂ ሐቀኛ ሃገራዊ ስሜት የተንጸባረቀባት አገር አይደለችም፡ ይላል።  ከላይ የሰጠሗችሁ የመጽሐፍ/ቪዲዮ ማስታወቂያ፤ ጣሊያን ሲወጋን፤ ብሔራዊ ስሜታችንን ለመግደል ሲዘምትብን፤ እንኳን ኢትዮጵያዊያን ቀርቶ፤ የውጭ ዜጎችም (ዋለልኝ ተጓዦች/ጎብኚዎች ይላቸዋል ሲያሳንሳቸው) ብሔራዊ ስሜታቸው ከኢትዮጵያዊያን ጋር አብሮ ስለነጎደ ፤ስሜታቸው ተጋግሎ በመላው ዓለም ያደረጉት ሰላማዊ ሰልፍ በቪዲዮው እዩት። የዋለልኝ ስሕተት በግልጽ ይታያችሗል።

አገራዊ ስሜት ሽማግሌዎቹ ብቻ ሳይሆኑ ወራሪ ሲመጣ ወጣቱም በእንዲህ ያለ አገራዊ ስሜት ተገንብቶ ነበር ጠላትን ያርበደበደው፤


ከእነዚህ ከላይ በፎቶግራፍ ከተመለከትናቸው የአገር አርበኞች የተላላፈ ብሔራዊ ስሜት፤ የትግራይ ፋሺስት ግልገሎቹ ከትግራይ ገስግሰው በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ላይ ሰላማዊ ሰልፈኞች ላይ የወደብ ጉዳይ እና የኤርትራ ግንጣላ የሴራና የባንዳዎች ውሳኔ ነው ብለው የግራዘያኒ ጥይት እሩምታ ሲያወርዱባቸው፤ የኢትዮጵያ ፈጣሪ ይመስገን  “ኢትያዊ ብሔራዊ ስሜት” አልጠፋም ነበር። ይህንን ታሪካዊ እና rare/ የማይገኝ እግዚሄር እራሱ ያነሳው ታአምራታዊ የአምላክ ስራ/ፎቶን” አብርን እንመልከት። አሌፍ በተባለው መጽሔት ታትሞ ነበር። እነሆ፤


 ዋለልኝ፤ “There is of course the fake Ethiopian Nationalism advanced by the ruling class and unwillingly accepted and even propagated by innocent fellow travellers. ይላል።

ዋለልኝ በህይወቱ እያለ የሕዝቡ ኢትዮጵያዊ ስሜት እንዴት ግሎ እንደነበርና “በአገርና በሚስት የለም ዋዛ” ብሎ መመሪያው ያደረገ “አንድ” ሕዝብ፤ እንዴት እንዳልገባው ባይገባኝም፤ በሃገራችን የታዩ ተደጋጋሚ ጀብዶች (ከጦርነት እስከ ስፖርት) የገዢ መደቦች የፈጠሩት ከሆነ፤ ከሕዝቡ ይልቅ ለገዢዎች ግርማ ሞገስ መስጠቱ የዋለልኝ ግምገማ ለእኔ አስገርሞኛል።

ገዢዎች መመስገን የሚገባቸው ቦታና ክብር ፣መስጠት ያለ ነው፤ ምክንያቱም ሃገራዊ ስሜቶች መሪዎች ናቸው የሚመሩት፤ከዚያም ሕዝቡ ሆ ብሎ ይከተላል።ሆኖም የተገኙት ድሎች ያለ ብሔራዊ ስሜት የተገኘ ነው ብሎ የሚያምን ምሁር ሁሉ “ያስተሳሰብ ችግር አለበት ማለት ነው። የዓለምን ኢምፔሪያሊሰት ወራሪ ፋሺስት  ዓድዋ ተራሮች ላይ “ማማ ሚያ!!!!እማዬ ሆይ! እማዬ ድረሺ!” እስኪል፤ በእምብርክኩ ያስኬደው ኢትዮጵያዊ ብሔራዊ ስሜት የት ሊደበቅ ነው? የሕዝቡ ኢትዮጵያዊነት ብሔራዊ ስሜት ያመነጨው ድል ካልሆነ ምን ተብሎ ሊጣራ ነው?

የመጠቁ የተመነደጉ ተማሪዎችና አንዳንድ የወቅቱና የዛሬ ምሁራን አማራ ስለሚጠሉ፤ አማራን በገዢ መደብ ስለሚመድቧቸው፤ መሪዎችን እየዘለፉና ያሳነሱ እየመሰላቸው የሕዝቡን የጀብዱ ተሳትፎ፤ ከሕዝቡ ነጥቀው “የአማራ ነው” የገዢ መደብ ነው” እያሉ እራሳቸውን ያስገምታሉ። ጥላቻ እስከዚህ ድረስ የሕሊናን ሚዛን ይጋርዳል።

የላይኛው ክርክሬን ለማጠቃለል፤ ዋለልኝ የሚለን፤ ኢትዮጵያ አንድ አገር አንድትባል፤ አንድ ቋንቋ፤ባሕል፤አለባበስ፤አመጋገብ፤ስነሉቦና፤ባሕል ሲኖራቸው አንጂ የተለያዩ ቋንቋዎች፤አለባበሶች፤ባሕሎች፤አመጋገቦች ያሉባት አገር “አንድ አገር/one nation” ልትባል አትችልም። ሲል በመላ ዓለም one nation/ አንድ አገር/ አንድ ሕዝብ ተብለው እንደ አገር የሚጠሩ አገሮች በሙሉ በውስጣቸው የተለያዩ ቋንቋዎች፤ባሕሎች፤አመጋገቦች እና አስተሳሰቦች ያላቸው መሆናቸውን ለምን አንዳልተረዳው ለኔ በጣም ግራ ይገባኛል።

ሰው ተብሎ የሚጠራ ሁለት ፆታ ይዟል *ሴት* እና ^ወንድ*። ነገር ግን ሲጠሩ በጥቅል/በጋራ መጠሪያቸው ሰው ተብለው ነው የሚጠሩት።አገርም የተለያዩ ጎሳዎች ፤ቋንቋ፤ቀለም፤ቁመና፤አለባበስ፤ባሕል….ይኑራቸው እንጂ በአንድ አገር የሚኖሩ፤ የአንድ አገር ሕዝብ ናቸው።

የተለያዩ ዛፎች ሲሰበሰቡ፤ ምን ተብለው ይጠራሉ? *ጫካ”። የኢትዮጵያ ሕዝብም ‘ትግሬ፤አማራ፤ጉራጌ፤ሶማሊ ጋምቤላ ኦሮሞ….” ይባሉ እንጂ እንደ ተሰበሰበው እያንዳንዱ ዛፍ ‘ጫካ’ ተብሎ  አንደሚጠራ ሁሉ የተለያዩ የእነዚህ ነገዶች ስብስብም በጥቅል “የኢትዮጵያ ሕዝብ” ይባላል። ምከንያቱም ፡ግለሰብ” ሲሰበሰብ “ሕዝብ” ስለሚሆን። ሆኖም፤ የሚታየው ሕዝብ ሳይሆን ፤ሰው ነው፤ ግለሰብ። ሕዝብ ቁጥር እንጂ ምንም ማለት አይደለም። ሰው ፤ግለሰብ ግን የሚዳሰስ የሚጨበጥ “እውነታ” ነው።

የማርክሲስቶች “ብሔር፤ብሔረሰብ” የሚባል “የግሩፕ” መብት “ለስልጣን መወጣጫ፤ለግንጣላ” የተሴረ እንጂ “ብሔር/ብሄረሰብ” የሚባል መብት የለም። ሰው፤ሰው በመሆኑ ብቻ እንጂ “ነገድ/ሕዝብ/ክምችት/በቡድን” ስለሚጠራ አይደለም መብቱ የሚከበረው። ስለ እኩልነት እና መብት ስንነጋገር “የግለሰብ” መብት ብቻ ነው ያለው። ያለ ግለሰብ ምንም ነገር የለም። ዛፍ እንጂ እውነታው፤ ጫካው አይደለም። የሚታየው ዛፍ እንጂ ጫካ የዛፍ ስብስብ ነው። ዋለልኝ የሚለን፤ የብሔር/ብሐረሰብ መብት (የግሩፕ መብት ነው) እንጂ የግለሰብ መብት አይደለም የተከራከረው። እንደ ሰው ሳይሆን እንደ ብሔር ነው መብትህ መከበር ያለበት ይላል። ይህ ደግሞ “ብዙሃን ለጥቂቶች ይገዙ ነው”። ዲካቶሪያል ዲሞክራሲ የሚባለው ማለት ነው። 

በሌላ መልኩ የዋለልኝ “ዲሞክራሲ” ሰው/ለግለሰብ/ መብት እየጣሰ 
 ‘ግሩፕ/ብሔር/ብሔረሰብ’ ለሚባል ጨቛኝ “ቡድን” ነው የሚሰጠው። ይህ ደግሞ “ዲሞክራሲ/ፋሺዝም/ማርክሲዝም/… ርዕዮት እንጂ “ብዙሃን በጥቂቶች” ወይንም “ጥቂቶች በብዙሃን“ የመብት መረገጥ የሚጻረረው “ሪፓብሊካዊ” ርዕዮት  አይደለም መስፈን ነበረበት ብሎ የተሟገተው “ዲክታቶሪያል ሞክራሲ” ነው እየሰበከ የነበረው። የአሁኑ ወያኔዎችም ሆኑ ኦነጎች “ይህንኑ ብዙሃን/የቡድን” መብት ነው እያካሂዱ ያሉት። ኮሆርዥን (ማስገደድ) ነው መበት የሚሉት። ጥቂቱ ወይንም ብዙሃን ይመውኡ/ዲሞክራሲ፤ እያሉ ግለሰብ እንዲረገጥ ይፈቅዳሉ፤ በሕግ ይደነግጋሉ። ዲሞክራሲ በመሰረቱ “እኩልንትን የሚያስከብር ስልት አይደለም። በብዙ መልኩ የብዙሃን መብት አስከባሪ ሆኖ የጥቂቶች ረጋጭ ሆኖ የሚከተልበት ወቅት አለ። 

የአማራን የግለሰብ መብት መረገጥ በኦሮሞ፤በሶማሌ እና በሲዳማ/ወላይታ…በመሳሰሉ አካባቢዎች “ብዙሃኖቹ ኗሪዎች የጥቂቶችን የአካባቢ ነዋሪዎች የመርገጥ መብት ስለ ተፈቀደ ነው”። የቡድን መብት ውጤት የግለሰብን ወይንም የጥቂቶችን መብት በመርገጥ መብት (እኩልነትን) ይጻረራል። ዲሞክራሲ እራሱ በጥልቅ ስንመለከተው “ኮሆርዥን ነው/አስገዳጅ” መብት ነው።የነ ዋለልኝ ብሔር ብሔረሰብ የራስ ገዝ/አስተዳዳር እስከ….ወዘተ የሚሉት ይህንን የግለሰብ የመብት ረገጣ ስልት እውን ለማድረግ  ነው።     

ዋለልኝ፤ አላዋቂ እንዳይባል፤ ከሊቅነትም በጣም ሊቅ እና ብልሕ ነው። ነገር ግን ለዚህ ድንቁርና ድምዳሜ ሊያደርሰው የቻለው “ምን አንደሆነ የታሪክ/የስነ ሉቦና/ ኣኢምሮ ሊቃውንት ሊፈትሹት ይገባል።

የላይኛውን አስተሳሰቡ ግልጽ ሲያደርገው ደግሞ እንዲህ ይላል፦ 

“This is the true picture of Ethiopia. There is of course the fake Ethiopian Nationalism advanced by the ruling class and unwillingly accepted and even propagated by innocent fellow travelers. What is this fake Nationalism? Is it not simply Amhara and to a certain extent Amhara-Tigre supremacy? Ask anybody what Ethiopian culture is? Ask anybody what Ethiopian language is? Ask anybody what Ethiopian music is? Ask anybody what the "national dress" is? It is either Amhara or Amhara-Tigre!! To be a "genuine Ethiopian" one has to speak Amharic, to listen to Amharic music, to accept the Amhara-Tigre religion, Orthodox Christianity and to wear the Amhara-Tigre Shamma in international conferences. In some cases to be an "Ethiopian", you will even have to change your name. In short to be an Ethiopian, you will have to wear an Amhara mask (to use Fanon's expression). Start asserting your national identity and you are automatically a tribalist, that is if you are not blessed to be born an Amhara. According to the constitution you will need Amharic to go to school, to get a job, to read books (however few) and even to listen to the news on Radio "Ethiopia"
unless you are a Somali or an Eritrean in Asmara for obvious reasons.

አንድ ኢትዮጵያዊ ዜጋ “አማራ” ካልሆነ በቀር ወይንም “የአማርኛ ስም ከሌለው” የስራ ዕደል “አያገኝም” መሰረት እና በማስረጃ የማይደገፍ ጽሑፍ በትኗል። ስራ ለማግኘት አማራን መምሰል አማርኛን መናገር ያስፈልጋል ይላል። ትንታኔውን ከላይ በጥንቃቄ አንብቡት። 

አንባቢዎቼ  ሆይ፤ የመንግስት ስራ ለመቀጠርም ሆነ ፤ ሕዝባዊ ተቋማትን በሚያገለግሉ የግል ተቋማትም ሆነ ተዘዋውሮ ንግድ ለመነገድ ብሔራዊ የመገናኛ ቋንቋ ከሌለ በምን ይግባባል?  አይደለም እንዴ? የጋራ መገናኛ ሆኖ  በታሪክ አጋጣሚ በሁሉም ቦታዎች የተንሰራፋው ደግሞ “አማርኛ” ነው። ታዲያ አንድ ኢትዮጵያዊ “አማርኛ” ካልቻለና ካልተማረ፤ በምን ቋንቋ ተግባብቶ ንግድም ሆነ በመንግስት አገልግሎት ተቀጥሮ  ባገሪቱ ቦታዎች ተዘዋውሮ ሊያገለግልና ከሕዝቡ ጋር ሊግባባ ይፈለጋል? አሁን እየታዬ ያለው የወያኔ የትምህርት/በደምብ ያልተጠና የጅብ ችኩል ቀንድ ይነክሳል ውጤት እያየን ነው።

“በ69 በሶማሌ ወረራ ጦርነት ጊዜ ወደ 300 ሰልጣኝ ሰራዊት ታጠቅ ጦር ሰፈር ለስልጠና የገባው አንዳንዱ  ሰልጣኝ፤ አንድ ወጥ የሆነ የመገናኛ ቋንቋ የነበረንን “አማርኛ” መረዳት ስለማያውቅ፤ለወታደራዊ ስልጠና  “ግራ ቀኝ” የሚለውን “ሀ” ብሎ ሰልፍ ሲማር “ቃርያና ድንች በግራና በቀኝ እጁ እንድይዝ ተደርጎ ነው “ቃርያ፤ ድንች” ፤ “ቃርያ ድንች” እያሉ ጀምረው በሦስት ወር ወታደራዊ ስልጠናው አጠናቅቆ መሰረታዊ የመግባቢያ ቋንቋ አማርኛ ተምሮ “ሰራዊቱ” አንድ ሆኖ ትዕዛዝ ማክበርና በማድመጥ ባስደናቂ ሁኔታ በጠላት ላይ የዘመተው” ይላሉ አቶ ተክሌ የሻው።

። በታሪክ አጋጣሚና በገበያ ዕድል የገጠመው አንድ ቋንቋ የሕዝብ መነጋገሪያ ሆኖ መገኘት በኢትዮጵያ የተደረገ አይደለም። መላው ኣለም በዚህ ስልት ነው የሄደው። ሁሉም ቋንቋ መነጋገሪያ ማድረግ አይቻልም። ዓለምም አላደረገው ኢትዮጵያም ላድርግ ብትል አትችለውም። ይላሉ የሞረሽ ፕረዚዳንት አቶ ተክሌ የሻው።

 አቶ ተክሌ አያይዘውም እንዲህ ይላሉ፦

 “አማርኛ በታሪክ አጋጣሚ የወታደር መነጋገርያ ሆኖ ሲፈጠር በመላ አገሪቱ ወታደሩ ሲዘምት እየተግባባ ያመረተው አማርኛ ገበያተኛ አገኘ። የመገበያያም ሆነ የመንግሥት ሥራ መግባቢያ አማርኛ ይሁን እንጂ፤ ከላይ ስርአቱን የመሩ መሪዎቹም ቢሆኑ ከጉራጌ፤ ከአፋር፤ከትግሬ፤ ከወላይታ፤ ከአማራ፤ ጉራጌ የተገኙ ናቸው።
በአጼ ምኒሊክም ሆነ በሃይለስላሴ ዘመን መረጃውን ልጀምርልህ፤ ይላሉ አቶ ተክሌ፡-

ተማሪው አመርኛ ቋንቋ የመገናኛ ቋንቋ በመሆኑ ብቻ አማራ በላይነት ተቀዳጅቷል፤ በማለት አማራን ወንጅለውታል። የተሳሳተ ነው! አማርኛ ሕዝብን እያግባባ ጠቀመ እንጂ አልጎዳውም። ባይሆንማ በምኑ ይግባባ ነበር? እስቲ አሰቡት? አማራው ደረቱን ለጦር፤ እግሩን ለጠጠር አድርጎ ለኢትዮጵያ አንድነት ሲሞት፤ ሲገብር ነው የኖረው። የረባ አንድም ነገር ለራሱ አላደረገም። ሲንከራተት ነበር የኖሮው፡ ለዚህ ነው አገር ሲያቀና አይተውት “ነፍጠኛ የሚሉት”። ማቅ ለብሶ እኮ ነው የመንዝ ሰው የሚኖረው ዛሬ! የመርሃ ቤቴ ሰው እኮ የአመት ቀለብ፤ የአመት ልብስ የለውም እኮ! ጫማ እኮ የለውም፤ ብረድልብስ እኮ የለውም። ወያኔዎች እንኳ  አማራ በሚኖርበት አካባቢ ሲያልፉ “ትግሬው በኑሮው ይሻላል፤ ይህንን አይተናል” ብለው እራሳቸው መስክረዋል (ስብሓት ይህንን በቃሉ መስክሯል፡ አውድዮው አለን።) አማራ ከሌላው የተሻለ ነው የሚሉት ስልጣን ለመቆናጠጥ ሲመኙ ነው። መለስ ዜናዎ የትግራይን ሕዝብ ያሞኘው “አማራ እንዲህ አደረገህ” እያለ ትግሬ እንዲከተለው ያደረገበት ስልት ይህንን የዋለልኝን ትምህርት በመከተል ነው። 

ያንን የሚሉ ሰዎች  የአማራውን ኑሮውን ወደ ሗላ እመለስበታለሁ። የውጭ ጠላቶች ኢትዮጵያን ለመቆጣጠር ሲሉ አገሪቱን ለረዢም ጊዜ ያስተባበረና አንድነቷን የገነባው “አማራን፤ዘውድን፤ኦርቶዶክስ ሃይማኖትን/ተከታዮቿን” ማፍረስ ነው ብለው ተነሱ። ይህንን ቅስቀሳ የውጭ ጠላቶች ይህንን ለወያኔ እና ለሻዕቢያ አስተላለፉለት። ተማሪው ሳይገባው “አያ በሬ ሆይ ሳሩን እያየህ ገደሉን ሳታይ….”  በሚል የኢትዮጵያ ታመሪዎች የዚያ ቅስቀሳ ሙርኮኞች ሆኑ። ዘውዱን አፈረሱት። ቤተክርስትያኒቱ ሃይልና ስልጠን አጣች፤ተከታዮቿ እና መሪዎቿ ተበተኑ። ማን ቀረ? አማራ የሚባል! ይህንን የቀረው ደግሞ መለስ ዜናዊ የትግሬን ሚሊሺያ ተዋጊ ይዞ ገባ እና ሕዝቡን አሳስቶ “አማራውን ከተከተው”።

 ቀደም ሲል በመደብ ትግል፤ በሗላ ጸረ ፍጠኛ ትግል፤ከዚያ የብሔር ብሐየረሰብ ጨቛኝ ትግል…. እያሉ ጨፈጨፉት። የዋልልኝ ተከታዮች እነ ወያኔዎች እኮ “አክሱም ለጉራጌው፤ለሃዲያው፤ ለአማራው ምኑም አይደለም” ብለው ተናገረዋል; የወያኔው የእስር ቤቶችና የስለላ አቀናባሪ የነበረው ብስራት አማረም ያንኑ ደግሞ “ፍኖተ ገድል” የሚል መጽሐፍ ጽፏል።

ስልጣንክን ‘አማራ’ ስለያዘው ነው፤ የሸዋ አማራ ስለያዘው ነው” ሲሉ ዋሽተዋል። ንጉሦሱ እንውሰዳቸው፦ በንጉሡ ጊዜ ማን ነበር ሥርዓቱን የመራው? አማራው በብቸኝነት ሥልጣን ይዞ አያውቅም።
የሸዋ አማራ የሚባል አባባል አላቸው ተማሪዎቹ፡ ማንን ነው? የሸዋ አማራ የሚሉትን እንመለክት እስቲ? ቀ/ሃይለስላሴ አማራ፤ ጉራጌ ኦሮሞ ናቸው/ትግሬም እንወለዳለን ብለዋል። ቀ/ሃይለስላሴ መኮንን፤ መኮንን ጉዲሳ ናቸው። እናታቸው የሺ እመቤት፤ የሺ እመቤት ጋንዶሎ ጉራጌ ናቸው። ከሃያ በላይ ኤርትራኖችና ትግሬዎች በንጉሡ ዘመን ከፍተኛ ሥልጣን ነበራቸው፤ (ኢትዮጵያን ሰማይ አዘጋጅ ጌታቸው ረዳ ባለፈው አመት ባንድ ጹሑፉ ላይ በጥቅስ ያስቀመጠው በንጉሱ ዘመን  ኤርትራኖችና ትግሬዎች የሆኑ የባለስልጣኖች ስም ዝርዝር ይመልከቱ)። እንዴት ነው ነገሩ! ስለ ሃቅ በሃቅ እንነጋገር እንጂ!

የምንሊክ መንግሥትስ? ዓለም የሚያውቃቸው ዓለም አቀፍ ቄሳርን ያምበረከኩ አፄ ምኒሊክ፤አማራ ብቻ አይደሉም።  እናታቸው እጅጋየሁ አድያቦ ጉራጌ ናቸው። በየት መጥቶ ነው አማራ ነገሰ የተባለው? የጦሩ ገበሬው እኮ  ገበየሁ እኮ ኦሮሞ ነው፤  ባልቻ አባ ሻፎ እኮ ኦሮሞ ናቸው፤ ደጃዝማች ወልደጊዮርጊስ ዲነግዴ (አባ መላ) እኮ ኦሮሞ (?) ናቸው።  እነዚህን አስተባብረው ድልን ‘ስልጣንን የገነቡ ዓለም ያደነቃቸው ቅይጥ ነገዶች ናቸው። ዝርዝር ውስጥ ብንገባ አማራ የሚባል ስልጣኑን ያልተጋራ መሪ አልነበረም። መዋሸት ይብቃ። ሃቁን እናፈርጠው!

አሁን ደግሞ ወደ ደርግ ጊዜ ልውሰድህ
 
“እግረኛ ወታደሩን ተመልከተው። የትኛው ነው አማራ ብቻ የሆነው ወታደር? ስለጣን ላይ ያሉትንስ? መንግስቱ ሃይለማርያምን ብትመለከት አማራ፤ኦሮሞ ናቸው።እነ ደበላ ዲንሳ ምንድናቸው? እነ ተካ ቱሉ ምንድናቸው? እነ ተስፋዬ ገብረኪዳን ኦሮሞ እኮ ነው፤ ተስፋዬ ገብረኪዳን ስለተባለ ትግሬ ይመስለዋል ሰው። ዉብሸት ደሴ ኦሮሞ እኮ ነው፤ አየር ሃይሉን የተቆጣጠሩት እነ መርዕድ ንጉሴን እነ ጀኔራል ረጋሳ ጅማ እኮ ኦሮሞዎች ናቸው፤ ስንቱን ልቁጠርልህ፡ ‘ኦሮሞዎች” ናቸው። ስለዚህ አማራ ስልጣኑ ተቆጣጥሯል፤ ወይንም አማራ አደገ ብትለኝ፤ እነ ቡልጋ፤ሽንኮራ፤እነ ፋርጣ፤ጭልጋ፤ አጣቃላይ ጎጃምን ውሰደው፤ ወሎ፤ የተሻለ ት/ቤት፤ጤና፤ አግኝቶ ቢሆን ኖሮ አደገ ፤አድልዎ ተደርጎ አማራው አድጎ ነበር እንል ነበር፤ ያ ግን አልሆነም።ከየት መጥቶ?” ሲሉ የሞረሹ አቶ ተክሌ የሻው  መረጃቸውን አቅርበው በሚገባ በእርግጠኛነት በኩራት ይከራከራሉ።

ዋለልኝ አማራ ሆኖ መወለድ ዕድለኛ መሆን ነው ይላል። ይህ አባባሉ ግን ፍጹም የተጋነነ ነው። አማራው አይደለም ወይ በወሎ ድርቅ የተገረፈው? የጎጃም አማራ አልነበረም ወይ በንጉሱ ቦምብ የተደበደበው? “ጥሩ ኢትዮጵያዊ ለመባል የአማርኛ ሙዚቃ ማድመጥ አለብህ” ይላል ዋለልኝ። ምን እሚሉት ደንቁርና ተጠናውቶት ነበር ዋለልኝ እንዲህ ሊል የቻለው? ሙዚቃ እኮ  ወገን ፤ጎሳ፤ዘር አይለይም። ዓለም አቀፍ ነው። እንኳን ሰውን ‘ሙዚቃ’ የአራዊትን ስሜት ሳይቀር ይቀሰቅሳል። 

የአማራ ሙዚቃ ደግሞ ካፈጣጠሩ በሽተኛን ከአልጋ ቁራኛነቱ የሚያስነሳ፤ ምናልባትም የሞተንም ሰው የሚቀሰቅስ፤ ጣእም ያለው፤ሽማግሌንም ሳይቀር የሚያስጨፍር፤ የሚያስተክዝ፤አንሰቅስቆ የሚያስለቅስና ከተቀመጥክበት ወደ ማዶ አሻግሮ ልብሕን ሰርቆ እንደ ወፍ ወደ አገርህ ወደ ፍቅረኛ የሚያከንፍ፤ ሴትም ወንድም ማራኪ፤ በአንዳች ነገር የተቀመመ፤ አደንዛዥ የሆነ የፈጣሪ ስራ መሆኑን እንዴት ዋለልኝ የወላጆቹን ሙዚቃ ምንነት ሳይረደው እንደቀረ ሳስበው ለኔ ለጌታቸው ረዳ ግራ ገብቶኛል።

የአማራዎች ሙዚቃ እንኳን ዜጎች ቀርቶ ዛሬም እንኳ ኤርትራኖች አማራን በሃሰት ተበክለው ባወገዙበትና በጠሉበት ወቅት ከአማርኛና ሙዚቃ ሌላ ሙዚቃ አያዳምጡም። አማርኛ ቋንቋና እና አማራና አማርኛን ኩፉኛ የሚጠላ ኢሳያስ አፈወርቅ አንኳ ጥላሁን ገሰሰ ሲሞት ለጥላሁን ሙዚቃ  ያለው አክብሮት የተናገረው ምን አንደሆነ ምስክር ነን። ጥላሁን ደግሞ የታወቀባቸው ሙዚቃዎቹ  አብዛኛዎቹ “አማርኛ ናቸው”። አማርኛ ሙዚቃ ሕዝቡ ሲያደምጥ የነበረው አማራ ለመምሰል ሳይሆን ፤ በስልቶቹ ቃና እና እስከስታ አመታቱ ስለተማረከ ብቻ ነው። እውነታው ይኼ ነው።

ዛሬ ወያኔ ያንኑ የዋለልኝ “አማርኛ ይጥፋ፤ አማርኛ ጨቋኝ ነው፤ኢትዮጵያ የምትባል “ፌክ” አገር ነች” ወዘተ ..ወዘተ.ወዘተ ,፣ ስብከቱን የተከተሉት የዛሬዎቹ ወያኔዎች፤ አገሪቱ “ባቢሎን” አድርገዋት ዜጎች እርስ በርሳቸው እንዳይግባቡ አድርጎ ፤ ባዕድ ሆኖ እንዲተያይ እርስ በርስ ሲባላ እያየን ነው። ለዚህ ሁሉ ተጠያቂው ዋለልኝ ሕዳር 10/1961 “ታገል በሚባለው ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች መጽሔት ላይ ‘የብሔረሰቦች ጥያቄ በኢትዮጵያ’ (On the Question of Nationality in Ethiopia) ያሰተመው ጽሑፉ ለዛሬ ባቢሎናዊ ምስቅልቅል የወያኔ ግራ ዘመም ፋሺስታዊ አስተዳደር አስተዋጽኦ ከፍተኛ ድርሻ አለበት የሚል አምነት አለኝ። 

ስለሆነም ነው ወያኔዎችም ሆኑ ኦነጎች እና ኦጋዴኖች “ዋለልኝን እንደ አርበኛቸው የሚመለከቱት”። በአማራው ላይ ከዚያ ጊዜ ጀምሮ የተለያዩ የአገሪቱ የውስጥም የውጭም ጠላቶች አማረውን ጥርሳቸው ውስጥ በማስገባት ጊዜ ጠብቀው ብትር በመሰንዘር “ነፍጠኛ” የሚል ቅጽል ስም በመስጠት ከደቡብ ከምስራቅ፤ከምዕራብ፤ እንዲሁም በሰሜን ኢትዮጵያ እየተገደለ፤ ከኑሮው እየተፈናቀለና እየተባረረ ወደ አገርህ ሂድ ለመባል የበቃው።

በሕይወት የሌለው ዋለልኝ ስለ አማራው እንዲህ አጣምሞ ተማሪውን ሲቀሰቅስ፤ በሕይወት የሚገኙት ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም ሶማሌ “ክልል” ውስጥ አማራዎች እንጂ ትግሬዎች ጠላታችን አይደሉም እያሉ የክልሉ አስተዳዳሪዎች በግልጽ ለመናገር የበቁት ፕሮፌሰሩ አስተዋጽኦ የለበትም ማለት ይቻላል? ይህነን እስኪ በዩ ቱብ ስዕለ ድምፁን በዓይናችሁ እና በጆሮአችሁ እነሆ አድምጡ።
TPLF puppet Somali president secret video exposed TPLFs hate against Amhara May 8 2013

በሚቀጥለው ሰሞን ደግሞ ስለ ልዑል ራስ ስዩም መንገሻ ወይንም ስለ ጋዜጠኛዋ ወደ ብዙ ወንድማገኘሁ በሚቀጥለው ሳምንት እንመለከታለን።
 አመሰግናለሁ፤
ጌታቸው ረዳ
(Editor Ethiopian Semay) getachre@aol.com