Thursday, July 9, 2020

ለአብይ አሕመድ ደብዳቤ ለጻፋችሁ ምሁራን ሆይ! ከጌታቸው ረዳ (የ Ethiopian Semay ድረገጽ አዘጋጅ) July 10, 2020


ለአብይ አሕመድ ደብዳቤ ለጻፋችሁ ምሁራን ሆይ!
ከጌታቸው ረዳ
(የ Ethiopian Semay ድረገጽ አዘጋጅ)
July 10, 2020
በደብዳቤው ውስጥ የተካተቱ ምሁራን አንዳንዶቹ የቅርብ ወዳጆቼ ቢሆኑም እዛው ደብዳቤ ውስጥ ስማቸው ስለተጠቀሰ እነሱንም የግድ አብሬ ከሌሎቻችሁ ጋር የሚከተሉት ጥያቄዎችን መልስ እንድትሰጡበት እጠይቃለሁ።

ለፋሺሰቱ መሪ ለኮለኔል አብይ አሕመድ ዓሊ የጻፋችሁትን ቀኑ እና አመተምሕረቱ ያለተገለጸ ደብዳቤአችሁ በመጽሐፈ-ገጽ (በፌስ ቡክ) ሲንሸራሸር አነበብኩት። ደብዳቤው ላይ ቅሬታየን ላስምርበት።

1ኛ- ቀንና አመተምሕረት የለውም (ወይንም ድረገጽ ላይ የለጠፉት ሰዎች ቆርጠውታል- ስለዚህ ማወቅ አልቻልኩም)። ደብዳቤው የተወሰኑ ኢትዮጵያውያንን የፖለቲካ መሪዎች እና አባሎች ብቻ ሲጠቅስ፤ ልክ እንደ ትንታጉ “ልደቱ አያሌው” የሽብርተኞችን ፖለቲካ እራቁታቸውን የሚያስቀራቸው ትንታጉና ጨዋው  እንጂነር ይልቃል ጌትነትን እስር ቤት ታስሮ መኖሩንም ሆነ የደረሰበት ግፍ ፍጹም አልጠቀሳችሁትም። ለምን የሚለው ጥያቄ ጭሮብኛል። ደብዳቤው የተጻፈው እነ እስክንድር ሲታሰሩ በቀጥታ ያኔውኑ የተጻፈ ከሆነ እና ይልቃል ከመታሰሩ በፊት የተጸፈ ከሆነ ይቅር እላችሗለሁ፡ ካልሆነ ግን ለምን ተረሳ? የሚለው ጥያቄ መልስ ስጡኝ።

2ኛ፤- እንዲህ ያለ ድብዳቤ ስትጽፉ ብዙዎቻችሁ የመጀመሪያችሁ  ሳይሆን ካሁን በፊትም ተመሳሳይ የሚመስል ደብዳቤ ሰትጽፉ አውቃለሁ። ቅሬታየም እነሆ፦-- ለምን የፋሺሰቶቹ መሪ ለኮለኔሉ ደብዳቤ ጻፋችሁ ሳይሆን ቅሬታየ፤ ዋናው ደብዳቤ ለራሱ ብትጽፉም “ሁለት አመት ሙሉ” ኢትዮጵያን በማታውቀውና ባላየቺው በመደመር “ጥቁር ገመድ” አስሮ ምድር ለምድር እንድተጎተት አድርጎ፤ ተደጋጋሚ ጭፍጨፋዎች በመንግሥት አካላት ሲፈጸሙ ‘ምንም ባለማለቱ ብቻ ሳይሆን “እኔ የቀበሌ መሪ አይደለሁም፤ እኔ ጠ/ሚኒስተር ነኝ ፤ሥራየም ከሚገባው በላይ እያከናወንኩ ነው ስለዚህ አልጠየቅበትም!!!” እያለ ምዕመናንን እና ዜጎች ቅሬታቸውን ሲያስተጋቡ እና ሲጠይቁት ይህንን ሃለፊነት የጎደለው የሕጻን መልስ ሲመልስ እንደነበረ ታውቃለችሁ።

ያ እንዳይበቃው “አልቃሽ ሕዝብ ይዤ እናንተ ስታለቅሱ እንደ አመላችሁ እኔም መሃረም (“ናፕኪን” የተጠቀመበት የራሱ ቃል) ይዤ መቅረብ ነው’። ‘ታምሜአለሁ፤ ደሞዝ አነሰኝ’ የሚል አልቃሻ ሕዝብ እስካለ ድረሰ እኔም “እኔም ‘ታምሜ መታከም አልቻልኩም፤ደሞዝ አንሶኛል” እያልኩ መልስ እሰጣችሗለሁ”…    እያለ ለሚያሾፍ ግለሰብ የምክር ደብዳቤ መጻፍ አልነበረባችሁም።

ይህንን እናንተም አድምጣቸሁታል።  “ሽብርተኞችን አታስገባ ብለን ስንጮህ እምቢ ብሎን ሲመግባቸው ሲንከባከባቸው” ለነበረው የሴራው “ግፋ በለው ተባባሪው መሪ”  ሳይሆን መጻፍ የነበረባችሁ; ለዓለም አገሮች መሪዎች፤ ለአፍሪካ መሪዎች (እርባና ቢሶች ቢሆኑም) ለተባበሩት መንግሥታት፤ ለዓለም ፍርድ ቤት እና ለኖብል ሽልማት ሸላሚዎቹ “ቢያንስ” “በግልባጭ” ለኮለኔሉ ማስታወቅ ሲኖርባችሁ፤ በቀጥታ ለተጠያቂው ወንጀለኛ መሪ ደብዳቤ መጻፋችሁ የያዛችሁት ከፍተኛ የትምሕርት እውቀት የሚያስገምት ሥራ  ነው።

ፋሺስቶች ከጥፋታቸው በደብዳቤ ምክር የመታረሙ እማ ቢሆን  ወያኔን ስንት ጊዜ ነበር ስለ ኤርትራ ጉዳይም ሆነ ስለ መብት ጥሰት የጻፋችሁለት”? ተመለሰ? አደመጣችሁ? አላደመጠም! ይባስ ብሎ እየከፋበት ሄደ። አብይም አሕመድም እንዲሁ ሁለት አመት ሙሉ ደብዳቤ ስትጽፉለት እየባሰበት ሄዶ አሁን ኢትዮጵያን ጎትቶ ወደ ገደል አስገባት፡(ጫፍ አትበሉ - አገሪጧ ገድል ውስጥ ነች ያለቺው። ለናንተ ጫፍ ገድል ላይ ነች ትሉ ይሆናል፤ ለሞቱት እና ንብረታቸው ለተዘረፈ እና ለጋየባቸው ዜጎቻችን ግን “ኢትዮጵ  ለነሱ “ገደል ውስጥ ገብታለች”)። ስለዚህ ገደል ውስጥ ላስገባት ወታደራዊና ፋሺስታዊ ብሐረተኛ የሆነን መሪ ብዙ ጊዜ ወንጀሉን እንዲያስተካክል መክራችሁት፡ አልሰማችሁም! እና ዛሬ ይሰማናል ብላችሁ እንዴት አሰባችሁ?

አሁንም ደብዳቤአችሁን ከሥልጣን እንዲለቅና በወንጀል እንዲጠየቅ ለተባበሩት ለዓለም መሪዎች እና ፍርድ ቤቶች እንዲሁም ሰባዊ ነክ ተቋማትን አቤቱታችሁን አስሰሙ እላለሁ።
ምርጥ ምርጦችን አስገባለሁ ብሎ ‘ምርጥ ምርጥ ሽብርተኞችን አስገብቶ’ ‘ምርጥ ምርጥ ቅርሶቻችን እና ምርጥ ዜጎችን አስጨረሰብን!
አመሰግናለሁ
ጌታቸው ረዳ (ኢትዮጵያን ሰማይ ድረገጽ አዘጋጅ)