Wednesday, July 27, 2022

የአብይ ፕሮተስታንት መንግሥት እና የሂትለር ፕሮተስታንት መንግሥት ተመሳሳይነት ጌታቸው ረዳ Ethiopian Semay 7/27/2022

 

የአብይ ፕሮተስታንት መንግሥት እና የሂትለር ፕሮተስታንት መንግሥት ተመሳሳይነት 

ጌታቸው ረዳ 

Ethiopian Semay 7/27/2022

watch this video also

 

Dr Abiy Ahmed surprise to Yonatan Aklilu

https://youtu.be/M0h6MPQyUtc

ከእስልምና ወደ ፕሮተስታንት ከፕሮተስታንት ወደ ገዳነት እምነት ወደ ..እስላም መሳይነት (የራሱ ቃል ነው) እየተገለባበጠ የሰውየው እምነት ምን እንደሆነ በቅጡ ለማወቅ ቢያስቸግርም። ለዛሬው ፕሮተስታንትነቱ እንውሰደው እና በዚያው እንውሰደው።

እንግዲህ ፕሮተስታንቱ ኦሮሙማው መሪ አብይ አሕመድ ሥርዓቱ እየተጠላ በመጣ ቁጥር እና ስጋት በያዘው ቁጥር፤ የሚያደርጋቸው አስገራሚ ባሕሪዎች አሉት።  የመተቃቀፍ እና የአባባ መለዋወጥ ቀን፤የምስጋና ቀን…. እያለ ሕዝቡን “ሰለማዊ መንግሥት ነኝ” በሚል “ለማጃጃል” የሚያደረግው አሳፋሪ ባሕሪው እንደገና ዛሬ “የፀሎት ቀን፤የምስጋና ቀን ለፈጣሪያችን እንድታቀርቡ ይሁን” የሚል “በአፉ ለይስሙላ” ካንድ የፖለቲካ መንግሥት ነኝ ከሚል “ሃይማኖታዊ መንግሥት” ትዕዛዝ በማስተላለፍ  በአሽከሮቹ በኩል በየመስርያቤቶች በግዳጅ እንዲከበር እያስጻፈ ነው።

ይህ የምስጋና ቀን የሚባለው በአብይ አሕመድ ዘመን አዲስ አይደለም። ለምሳሌ የEthiopian News Agency በ2020 (ፈረንጅ ዘመን) 2012 ኢትዮጵያ አቆጣጠር) ኩለት አመት በፊት ማለት ነው፡ "የምስጋና ቀን" በአዲስ አበባ እየተከበረ ነው፤ በሚል ርዕስ እንዲህ ይላል።

"የምናመሰግናችሁ ስለሚገባችሁ ነው" በሚል መሪ ሃሳብ የጳጉሜ 4 "የምስጋና ቀን" በተለያየ መርሃ ግብር በአዲስ አበባ እየተከበረ ይገኛል።” በማለት የዘገበውን ታስታውሳላችሁ። ምስጋና የሚጋበችሁ ነው የሚላቸውን በማግስቱ ምስጋና ትርጉም የማያውቀው አብይ አሕመድ ተቃዋሚ ናቸው የሚላቸውን የብዕር ጀግኖችን ወደ እስር ቤት ጭለማ በመግፍተር ሽማግሌ፤ ወጣት፤እመጫት፤ህጻናት የሚጠለሉበት መኖርያ ቤቶቻቸውን እያፈረሰ በከረምት ወራት በዝናብ ጎዳና ላይ እንዲሰቃዩ አደረገ።

ዛሬ ደግሞ ወደ አምላክ ፀሎት እናቅርብ እያለ ንጸሃንን አስሮ፤ አምላክ ላላቸውም አምላክ ለሌላቸውም ቀኝ እጃቸው ወደ ደረታቸው (ከፈረንጆች የተኮረጀ/ የተቀዳ/ ማለት ነው) በማድረግ ፀሎት አድርጉ እያለ በባለሥልጣኖቹ በኩል ትዕዛዙ እንዲከበር እያደረገ ነው።

ይህ እጃችሁን ወደ ደረታችሁ በማድረግ ጸልዩ የሚለው ጸረ አገራዊ ባህል፤ እስላሞች እና ክርስትያኖች በፓርላማም ይሂን በፍርድቤት በመጽሐፍ ቅዱስ ወይንም በቁርአን መጽሐፍ ከመማል ይልቅ የፈረንጅ ባህል አምጥቶ የሃይማኖት ምሃላቸውንና ፀሎታቸው አግባብ አስቀርቶታል።

አብይ በኦርቶዶክስ ሃይማኖት እና በነባሩ/አገራዊ እስላምና ሃይማኖት ላይ ከወያኔዎች በባሰ  እጅግ ጥላቻ አለው። ሰውየው የውጭ ቅጥረኛ በመሆኑ እስልምናውን ትቶ ወደ ፕሮተስታንት በመዞር እዛም የወላጆችዋን ሃይማኖት ባራከሰቺዋ ማፈሪያዋ በሚስቱ በኩል ፕሮተስታንት ተከታይ አፈርቶ ኦርቶዶክስን የማፍረስ ተልእኮው ለማሳካት ያላደረገው ሴራ የለም። ሌላ ቀርቶ ህጻናት ልጃገረዶችን እየሳመ በመሃል አዳራሽ የሚማግጠው ወንጀለኛው ዮናታን የተባለው አደገኛ የፕሮተስናት ፓስተር ነኝ ባዩ አብይ አሕመድ የመንግሥትን መሬት በነፃ እየሸለመ ፕሮተስታንት ወንጀለኞችን የፈለጉት ወንጀል እንዲሰሩ ልቅ በመስደድ የሚያበረታታ አደገኛ ሰው ነው፤፡

አገራችን ውስጥ ፕሮተስታንት እንደሚታወቀው በኦሮሞዎች ልሂቃን የሚቀነቀን ሃይማኖት ነው።ኦሮሞ ልሂቃን ደግሞ ጸረ ኦርቶዶክስ እና ጸረ አማራ ፤ጸረ ኢትዮጵያ ናቸው። ኦርቶዶክስ በመክሰስ የፕሮተስታንትን መንግሥት በመትከል አሁን ደስተኞች ናቸው።ከዚህ አልፎ ኦርቶዶክስ ውስጥ የተሰገሰጉ ከእስላሞች ጋር አብረው ስጋ የሚበሉ ፤የኦነግ ፕሮተስታንት የውስጥ ልዑካን የሆኑ ኦሮሞ ኦርቶዶክስ መሳይ ቀሳውስትም እንደሚታስውሱት ከፍተኛ የማፍረስ ስራ ሰርተዋል። (ቀሲስ በላይ የታበለው ፈጣጣ ሴረኛን ታስታውሱታላችሁ)

 

እንደ አብይ አሕመድ የብልጽግና (ፒፒ) ወረበላዋ የናዚ ጀርምንም እንዲሁ የናዚ ቡድኑ ወደ ሥርዓተ መንግሥት በምርጫ ሲወጣ ከልቡ አልሞት የነበረውን ጸረ ካቶሊክ ሴራው እውን አድርጓል።

የጀርመን የፕሮቴስታንት ቀሳውስት የመጀመሪያውን የዓለም ጦርነት በካቶሊካዊትዋ ፈረንሳይ፤ቤልጂየም እና በኦርቶዶክስ ሩሲያውያዊቷ ጸረ ጀርመን ሃይማኖታዊ ጦርነት (ክሩሴድ) ነው የተካሄደብን እያሉ “ፕሮተስንታኖችን” ሲሰብኩ ስለነበር “ብሔርተኝነት እና ፕሮቴስታንት” የአንድ ርዕዮተ ዓለም / ያንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታዎች እንደነበራቸው ግልጽ ነበር።

 ልብ በሉ ኦሮሞዎች የ “ፒፒን” መንግሥት እንደ የኦሮሙማ ስርዓትም፤ እንደ አባገዳም እንደ ፕሮተስታንት እና እንደ ‘’የእስላማዊ ብራዘር ሁድ”  አቀንቃኝ መንግሥት አድርገው ያዩታል (የአባ ገዳ መሪ አቶ “በየነ ሰንበቶ” አብይ ባይመረጥ ኖሮ ሁሉ ኦሮሞ በየቤቱ ዘግቶ ‘ቢላዋ፤ቆንጨራ እና ጠመንጃ ስራ ላይ እንዲያውለው ይጠባበቅ ነበር!’ ያሉትን ልብ በሉ)።

 ጀርመን ውስጥም ይህ “ያንድ ስዕል ሁለት ገጽታ ያለው” እምነት ኢትዮጵያ ውስጥም በአብይ አሕመድ ዘመን እያየን ነው።

ስለዚህ የምስጋና ፀሎት እናድርግ እያለ ፖለቲካ እና ሃይማኖት በየወቅቱ የሚዘበራርቀው “አብይ አሕመድ” በፕሮተስታነቱ እና እስላማዊው ውሃብያው ‘ብራዘር ሁድ” ማሕበረሰብ  የሱን ስም እየተነሳ ውዳሴ እንዲደረግለት እየተማጸ ነው።

 ለመሆኑ ንፁሃንን እያሰረ ለማን ነው ምስጋና ን እናቅርብ እያለ ያለው? እሱን ለሚያመልከው ለሰይጠኑ ከሆነ የራሱ ጉዳይ ነው፡ ኢትዮጵያዊያን ግን የምናደርሰውና የምንጸልየው አገር ሙሉ ንጹሃንን እየለቀመ እስር በማስገባት የሚያንገላታ “እስላም መሳይ ነኝ እያለ የሚያታልል የዲያብሎስ አማኝ” እንደ መለስ ዜናዊ ተሎ እንዲያሰናብልን ነው ጸሎታችን።

 

ሰላም ቆዩ

ጌታቸው ረዳ      Ethiopian Semay