የአብይ አሕመድ የማሰብ ችሎታና የዓዕምሮ በሽታው
ከጌታቸው ረዳ
ETHIOPIAN SEMAY
1/25/2022
ሁለት ዕብዶች እያስጨረሱት ያለውን ሕዝባችን በቅጡ ስላልተመረመረ እንጂ መንስኤው የሥልጣን ሽሚያ ቢሆንም ዋናው ሞተሩ ግን የሰዎቹ የጤንነት ሁኔታ ነው። የትግሬዎቹ ዕብደት ማየት የሚቻል እና ለ30 አመት ያየነው የዝሆን ያህል ትልቅ ዕብደት ስለሆነ የእነሱን ዕብደት ትተን “አብዮት” ወደ እሚባለው አዲሱ ዕብድ እንመልከት።
አብይ ወደ ሥልጣን ሲመጣ በቪዲዮ ተቀርጾ ያየነው አባቴ ነው የሚላቸው አባቱ እና ወንድሞቹ እንዲሁም የልጅነት ጓደኞቹ ነን የሚሉ የአብይ አሕመድ ጓደኞቹ ቃለ መጠይቅ አይተናል። በዛው ቪዲዮ የቅርብ ጓደኞቹ ነበርን የሚሉ የጅማ በሻሻ ጓደኞቹ ቢነግሩንም፤ አብይ አሕመድ ግን “አንድ ነገር መናገር የምፈልገው በልጅነቴ ዘመን አንድም ጓደኛ አልነበረኝም” ሲል ያለ ጓደኛ ማደጉን ሳደምጥ የበሽታው መንስኤ ያለ ጓደኛ ማደጉ ይሆን የሚል ጥርጣሬ አለኝ። ሰው እንዴት ያለ አንድ እንኳ ጓደኛ አይኖሮውም? ለመሆኑ እነዚያ እንዲያ ሲያደንቁት የነበሩት አብሮ አደጎቹ ጓደኞቹ ከምን ተነስቶ ነው ጓደኞቼ አልረነበሩም ብሎ የከዳቸው? እውነትም ከሃዲ ነው።
አንዱ ያም ይሆን ወደ ሥልጣን ሲመጣ ዕልል ብሎ ያከበረው የኢትዮጵያ ሕዝብ በመክዳት የሕዝብ አደራ ከድቶ ሰው እያሰረ እያስደበደበ እና እያስገደለ ያለው? ንግግሮቹ ሁሉ እጅግ የተምታቱ የአታላይ ሰው ንግግሮች ናቸው። ንግግሮቹ እንኳ ስትመዝንዋቸው እርስበርሱ የሚታቱበት ጤናው የቀወሰ መሆኑንም ማሳያ ምልክቶች ናቸው። ኦሮሞ ያለመሆኑንም በሚሰድቡት ስድብ የተነሳ እኔ ኦሮሞ አይደለሁም ይልና እንደገና ኦሮሞ ነኝ እያለ መከራከሩ ስናደምጠው የሰውየው የሕሊና ተጽእኖው ከፍተኛ መሆኑን እናያለን።
ንግገሮቹ ሁሉ ስንፈትሻቸው የምር ብቃት የሌላቸው ብቻ ሳይሆኑ፤ ፍፁም ከደደብ ሕሊና የሚመነጩ በውብ ቃላት የታጀቡ ፍሬ ከርስቺ እና አታላይ መሆናቸውን ያሳያል። አብይ አሕመድ ሥልጣን ላይ ከወጣበት በነዚህ 4 አማታት ጊዜ ጀምሮ ነገሮችን አስቀድሞ ሊተነብይና መውጫ ስልቶች (ኤክዚት \እስትራተጂ) መቀየስ የማይችል ‘ከውስጡ ለሚረብሹት የማንነት ቀውሶች መፈወሻ የሚሆኑት የአትክልት እና የአበባ መናፈሻዎች ሲኮተኩትና ሲያሳምር ተዘፍቆ ከርሞ “ቸል ሲላቸው” የቆዩ ነገሮች አድገው ድንገት አስፈሪ ሆነው ፊቱ ላይ ቆመው ሲደቀኑበት “የሚደናበር” በሽተኛ ሰው ሆኖ አይተነዋል።
ይህ የውሸት፤የመደናገርና የማታለል ባሕሪው፤ ከሞላ ጎደል የፖለቲካ ህይወቱን ስንዳስስ ፤ ገና በ14 አመቱ ብረት ታጥቆ የኦነግ ታጋይ ከዚያም ኦፒዲኦ ካድሬ ሆኖ በወያኔ ሥርም “እየዋሹ ሰውን በሚጎዱበት” መስርያቤት ውስጥ ተቀጥሮ “ሲዋሽ ሲያታልል፤ ሲሰልል፤ንፁሃን ሲያጠቃ እና ሲያሳስር በመኖሩ” እንዲሁም ያለ ጓደኛ ማደግና “የማንነት” ቀውስ በፈጠረበት ጠማማ የጤና መዛባት ምክንያት አገሪቱ ምስቅልቅሏን አውጥቷታል።
የኢትዮጵያ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር ከሆነበት ጀምሮ በዓለም ፊት የስልጣን ደረጃውንና የስልጣኑን ስፋትና የውስጥ እና የውጭ ጉዳዮችን ባለማወቁ “ኢትዮጵያ” ጠላት የላትም ሲል ቆይቶ ከሰዓት በሗላ ባንድ አዳራሽ ተገኝቶ ጥዋት ረፋዱ የተናገረውን ረስቶ “ኢትዮጵያ ብዙ ጣለቶች ያላት አገር ናት” ብሎ ያፈርሰዋል።
አደገኛ የሆነው ባሕሪው “የኢትዮጵያ መሪ ሆኖ” የሕዝብን አደራ እጠብቃለሁ ብሎ “ንጉሥነቱን በይፋ በተቀባ ጊዜ” ሕዝብ ከጠላት እንዲጠብቅ የማለለትን ሃላፊነት ረስቶ “የሕዝብ ዋነኛ ጠላት ለመሆን በቅቷል” (በተለይ ለአማራ ማሕበረሰብ)። በዚህ ምክንያት ያየነው የሰውየው የሕዝብ ጠላትነት “ዘፍጥረት” ሥር ሰድዶ እነሆ በዚህ ጦርነት ውስጥ አማራውን እያስቀየመ ትግሬ የሚባል በሙሉ ደግሞ ሰብስቦ “ማጎርያ ቤት አስሮ” ሽማግሌና ህጻናት እንዲሁም እርጉዞች ጭምር ሲያሰቃያቸው ይገኛል። በዚህም ምክንያት፣ ባለፉት ዓመታት፣ የሰውየው የማስተዳዳር ችሎታ ማነስ የሕሊና በሽታ ተጨምሮበት ሰውየው ወደ ለየለት የራስ ወዳድ “ናርሲሰትነት” እና “ስኪዞፈሪንያነቱን” በገሃድ ማየት ችለናል።
በዚህ “ሲንድረም” ምክንያት የተነሳ የመንግሥት መሪነቱን “የፖለቲካ መቀመጫው” ወደ “የበሽተኛ ሶፋ መቀመጫ” ቀይሮታል። ህመሙ ከባድ ስለሆነ በአእምሮ የሕክምና ሊቃውንት ሊታከም እንደሚገባው ምንም ጥርጥር የለውም። እንደ አለመታደል ሆኖ፣ በሙያዊ ምልከታ ታካሚ “ከመገለል” ይልቅ የአንድን ሀገር ኑሮ የመምራት ፍፁም ስልጣን ተሰጥቶት እነሆ አገሪቱ ከድጡ ወደ ማጡ ወስዷታል።በሁሉም በየሚኒሰትሮቹ ሥራ መስኮችና መስራቤቶች ድረስ እየሄደ ውስብስብ እነ ሁለገብ ችሎታ ያለው ለማስመሰል ራሱ ለራሱ በቴ/ቪዥን ፊት ቆሞ ገለጻ ሲያደርግ አይተው የተማረኩለት የዋሃን ዜጎች “ውስብስብ እውቀት” አለው እያሉ ሲያንጨበጭቡለት አይተናል። የእሱ ውስብስብነት ግን ፍጹም ቅጥ ያታ የታመመ ሰው ተግባር ነው። ጥልቅ የሆነ የበታችነት ስሜት ስላለው “ህመሙን ለማስታገስ” የሆነ ቦታ መሸሸግ ነበረበረትና ወደ “ሶማሊያ፤ ሱዳን፤ ኤርትራ፤ ኬኒያ እና ወደ አፍሪካ እንዲሁም ዓረብ አገሮች ሄዶ ልዩ መሪ ለመምሰል “ሲዘባርቅ” ከርሞ “የወርቅ ሃብል ተሸልሞ’ መጨረሻ “የኤርትራ የውጭ ጉዳይ ሆኜ እንዳገለግል ክቡር አቶ ኢሳያስ አፈወርቂ በዛሬው ዕለት ሹመት እንደሰጡኝ ስገልጽ በኩራትና በደስታ ነው” እያለ “የባዕድ አገር የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር መሆን “እንደሚያስከስስና ከሥልጣን እንደሚያስባርር” በሽተኛ ሕሊናው ባለማወቁ “የታላቅ ታላቅነት ሹመት” መስሎት እራሱን እና ኢትዮጵያን አዋርዷል።
የሱ ራዕይ “የኢትዮጵያ መሪ ሆኖ እንደገና “የኤርትራ የውጭ ጉዳይ ሚኒሰትሬር” መሆን የበታችነት ስሜቱ እንዴት እንደሚፈውሰው የሚጮኽበት ስልት ነው። የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት መንግሥት የነበሩት ጃንሆይ “የኤርትራ የውጭ ጉዳይ ሚኒሰቴር ነኝ ቢሉ ወይንም ሌ/ኮ መንግሥቱ እንዲሁ ቢሉ ምንኛ ውርደት እንደሚሰማን ገምቱት። የዚህ ሰውየ ግን በመሪነት ደረጃም ስለማናየው “ቅሌቱ” ምንም አልመሰለንም።
በዚህም የበታችነት ስሜቱ “የኤርትራ አሻንጉሊት” እስከመሆን ደርሳል። የበታችነት ስሜቱን ለማከም የአማራውን (ኢትዮጵያዊ) አርበኛ “ጀኔራል (ፊልድማርሻል) አሳምነው ጽጌን” በማስገደል የመጨረሻውን የዕብደቱን ማሳያ ለመፈፀም የግድ ጀኔራሉን ገድሎ እንደገና የጀኔራሉን እርጉዝ ባለቤቱን አስሮ እርግዝናዋን እንድትወርድ ከሆነ በሗላ “አሳምነውን ከእስር የፈታሁት እኔ ነኝ” ብሎ ገና ወደ ሥልጣን ሳይመጣ የተፈታውን ሰውየ “ፈታሁት” ብሎ የሕሊና በሽተኛ መሆኑን አሳየን።
በሚገርም ሁኔታ አሳምነው ሲገደል አንዳርጋቸው ጽጌ የተባለው “አጭበርባሪ” “መሰሪ” በሳምነቱ ወደ ቶሮንቶ ካናዳ ሄዶ ሕዝብ በተሰበሰበበት አዳራሽ “ማን ማንን እንደሚገድል አስቀድሜ በዝርዝር ለጠ/ሚኒስተሩ አሳውቄ ነበር” ብሎ ተናግሮ “ፓርላማ ተብየው” ይህንን አስገራሚ የወንጀል ምስጢራዊ “ሴራ” ይፋ ያደረገልን ንግግር በሽተኛው ጠ/ሚኒሰትሩም ሆነ አንዳርጋቻው ጽጌን ጠርቶ ጉዳዩ እንዲጣራ አላደረገም። ለምን ማለት አይቻልም፤ በሽተኛ የሚመራው አገር ፓርላማ ብሎ ነገር የለም-ማ!
ወያኔ በጫረው ጦርነት እስከ ደብረሲና ድረሰ መጥቶ ዓፋር ሕዝባችን እና አማራውን ሕዝባችንን ሲያወድም ‘በሽተኛው’ ፓርክ ላይ “ሕመሙን ሲያናፈስ” ነበር፤ በዚህ የተበሳጨ ሕዝብ ሲጮህበትና ወያኔ እየገሰገሰ መምጣቱ ሲመለከት በድንጋጤ ተውጦ ፤ እራሱ ወደ ቦታው ሄዶ ግማሽ ቀን እየቆየ በሄልኮፕተር በመመላለስ ‘አስመሳይ’ እርምት በማድረግ ጫፍ የደረሰው ወያኔ ‘ወደ ሗላ’ እንዲገፋ ተደረገ። ከጦርነቱ በኋላ፣ አሸነፍን ብሎ በውሸት ሲቧርቅ፤ ጮማ ሲቆርጥ፤ የዋሆችን ሲያስጨበጭብ ፤ ሽልማት ሲሸልም ፤ ጦር ሜዳ የተዋደቀው ብዙ ተዋጊ በመጸየፉ፣ ለማንኳሰስ ሞክሮ “የወደፊት አደጋ ናቸው የሚላቸውን አካባቢዎች ለይቶ” ድሕረ ጦርነት የሚል ሴራ ጠንጥኖ ካለው የጭንቀት በሽታ ሌላ በከባድ የመንፈስ ጭንቀት ውስጥ ገብቷል።
በርካቶች ለጦርነት የሚደረገውን ድጋፍ በተለያዩ መንገዶች እስከ መግለጽ ደርሰዋል። ሁላችንም እንደምናውቀው ግልጽ የሆነ ድል ወደ ተጨባጭ ሁኔታ አልደረሰም። ሰሞኑን አሽከሮቹን ሰብስቦ ከወታደራዊ እስከ ስቢል ሰዎችን ሰብስቦ እንዴ ሙያቸው ሲሸልም “ጦርነቱ እንዳለቀና “ኖ ሞር” የሚለው እንቅስቃሴ አቁሙ ብሎ ጦርነት የለም ብሎ የቦተለከው አብይ አሕመድ በተለይም የትግሉን ሃይል ከድቶ በፈሰሰው ደማቸው በተቀጠቀጠ አጥንታቸው እርከን ሜዳ ላይ የተገኘውን የመጨረሻ ሽልማት በመንፈግ ነው ሰሞኑን ሲቦርቅ ያየነው።
በሽተኛው እየተከተለው ያለው መንገድ የተቃወሙትን ሁሉ ፤ ጤንነቱን የተጠራጠሩት ሁሉ ወደ እስር በማስገባት የወያኔ መንገድ በከፋ መልኩ እየሰለጠነበት ነው። ኦሮሞ ወክሎናል ብለው ወደ ሥልጣን የተቆናጠጡት እነዚህ አዳዲስ አረመኔዎች እየለዩ የሚወነጅሉት ዜጋ ከጀርባው ያለው ገበያ ይዞት የሚመጣ መዘዝ አላወቁትም።
ጠንከር ያሉ እና ጠንካራ አስተሳሰብ ያላቸው መንፈሶች እየታሰሩ በስርዓቱ ተጨፍልቀው ሌሎች አድርባዮች ደግሞ ወደ አሳፋሪ ጥገኛ ደም ሰጪነት ተለውጠዋል። በሽተኛው ገዢ ሙሉ በሙሉ ባለማበዱ ሞኝ-ሞኙን እና የለየላቸው “የ-ዩቱብ ዕብዶችን” እየፈለገ በጥቅም እየደለለ እርስ በርስ እንዲጣላ ያደርጋል። ከዚያ በሗላ ዲያስፖራ የምትኖሩ ሁላችሁም ‘አማራ ትግሬ ኦሮሞ..’ አትባባሉ “ኢትዮጵያዊያን ናችሁ”፤ ሲል በመ፣በራሱ ግዛት ግን “ኦሮሞ ትግሬ አማራ….ነኝ” እንዲል አዳዲስ “ፓርታይ ክልሎች” እንዲከለሉ በማድረግ ላይ ነው። በሽታው ይህን ያህል ጥልቀት አለው (አክዩት አይደለም/ ክሮኒክ ነው)።
ሁሉም ነገር ከተነገረው እና ከተሰራ በኋላ የኢሳያስ አፈወርቂና የኦነግ አጀንዳ ለማስቀጠል ብቸኛው ብቃት ያለው ሃይል “ከጋሼ አበይ አሕመድ” ሌላ ሰው ማንም አይደለም። አብይ አሕመድ ለኢትዮጵያና ለአማራ ያልተገባ ወደር የለሽ ጥላቻ እንዳለው አትርሱ። የቀረው የድጋፍ ቦታ ኦነግ (ኦነግ ሸኔ “የሽፋን ስም”) እና ኤርትራ ብቻ ነው። በግልጽ እንደሚታየው፣በኢትዮጵያ ሰማይ ጥላ ሥር ጀሮአችን እየሰማ በኦነግም በወያኔና በአብይ መካከል እኛ በማናውቀው ከፍተኛ ደረጃ ንግግሮች እየተደረጉ ነው (ካሁን በፊት - ኤርትራ ጋርም ሆነ ኤርትራ ውስጥ ከነበሩት ኦነጎች ምን ስምምነት እንደተደረገ እንኳ ሕዝቡም ሆነ ፓርላማ ተብየ አያውቅም) ። ይህ ምስጢር ስለዚህ ሰውየ ባሕሪ ብዙ ይናገራል።
በከባድ ጫና ውስጥ ያሉት የኢትዮጵያ ዜጎች ከዚህ በፊት ታይቶ የማያውቅ ዘረፋ በማሸማቀቅ ድብደባ፤ ሞት እና እስራት ላይ ነው። በዚህ ታሪካዊ ወቅት በርካታ ማህበረሰባዊ-ታሪካዊ ዳይናሚክሶ-ች እርስ በርስ እየተጠላለፉ ይገኛሉ። በህዝቡ አልገዛም ባይነት በአዲስ ተቃውሞ “በጫና አስጨንቆ” ሌላ “አገራዊ የሆነ መሪ” እስካልተካ ድረስ የሀገሪቱ የዛሬ ችግር ብቻ ሳይሆን የወደፊት ዕጣ ፈንታ ከባድ ችግር ውስጥ ይወድቃል።
አርቆ አሳቢ መሪ ለማግኘት ከበፊቱ ወንጀሎች ነፃ የሆነ ንክኪ የሌለው ቅን ሰው መሆንና ቅድመ ሁኔታው የፖሊቲካ ፍላጎት በአገር ፍቅርና ሉአላዊንተንና “ተጠያቂነትን” ማመን ያስፈልጋል። አብይ በተጠያቂነት አያምንም፡ የሀገሪቱን ደኅንነት ግድ የለውም፡ አማራ ሕዝብ ኦሮሞና ጉምዝ ሲታረዱና ሲባረሩ “አታካብዱት” ይላል። ሰውየው ከአገሪቱ ጋር ያለው ግንኙነት ለምክንያታዊ አእምሮ የማይታወቅ በሁሉም ዓይነት አለመግባባቶች የተሞላ ነው።
በጠቅላላው የስጋትና እና የጨለምተኝነት መፈልፈያ ሰው ነው። ሕመሙ የበረታ ስለሆነ የስነ-ልቦና ባለሙያዎች ስለሰውየው መተቸት ወደ እስር እንደሚዳርጋቸው ሰግተው ካልሆነ በቀር የሰውየው በሽተኛነት ሊጠፋቸው አይችልም። ባለፉት ዘመናት እንደዚህ ያለ በመሪነት ያለ መሪ በሕሊና በሽታ የታማ ቢኖር በጥቂት ሰዎች ነው። ይህ ግን በብዙዎቻችን በሽተኛነቱን አርግጠኞች ሆነን መናገር ችለናል። በመወያያ የዜና ማሰራጫና የውይይት መድረኮችም በሕሊና ጤንነቱ ብዙ ውይይት ተደርጓል።
እኛ የሚያስፈልገን ያልተበረዘ ኢትዮጵያዊ መሪ እንጂ የኤርትራ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እንዲያስተዳድረን አይደለም።
አብይ እና ተከታዮቹ በኦሮሙማ ስልቀጣ ስልት ኦሮሞ የተባለች “ዲፋክቶ አገር” መላዋን ኢትዮጵያ መግዛት አለባት ብለው በጥልቅ ያምናሉ። እኛ በስልጣን ላይ እስካለን ድረስ መላ አገሪቱ እና ህዝቦቿ በተግባራዊ መልኩ ለሁሉም ዓይነት ብዝበዛ የተዳረገ ዜጋ “በኛ ፈቃድ የሚንቀሳቀሱ” የእኛ አገልጋዮች ናቸው ብለው ያምናሉ። አብይ “ባሌ” ሄዶ ለሽማግሌወች የተናገራቸው ይህንኑ ነው ።
በሽተኛው መሪ በጦርነቱ ወቅት ለሀገራዊ ታማኝነት “የከንፈር አገልግሎት” በመስጠት ጠላትን ለመዋጋት ከፍተኛ ድጋፍ ማሰባሰብ እንችላለን ብሎ ያምናል። በሰላም ጊዜ በመንገዳችን ላይ የሚቆምን ሁሉ ለመናድ የተነደፉ ህጎችን እንፈጥራለን ይላል። የጨዋታው ስም ሥልጣንን ማካበት ነው (የበሽተኛው አማካሪ ሌንጮ ባቲ የተናገረውም ይህንኑ ነው -ለ3000 አመት እንገዛችሗለን ብሎናል አማካሪ ሆኖ እያለ አዲስ አበባ ከተማ ቃለ መጠይቅ ተደርጎለት- ዛሬ የሳውዲ አምባሳደር ነው)።
አብይ የጥቃትና የአጥቂ ሞኖፖሊነት አለን ብሎ ያምናል። የጥበቃ ወጪውን ለኦነግና ለኦፒዲኦ እስከሰጠን ድረስ ማንም አይደፍረንም የማዘዝ ብቸኛ ሥልጣን አለን ብሎ ያምናል። አምቢ ካላችሁ “ትግራይን” አስገንጥየ “ኦሮሞ” አገር እንዲመሰርት አደርጋለሁ እያለ እንደ በውሰጠ ሴራ እየነገረን ነው (አክራሪ እስላማዊ ኦሮሞ በከንቲባነትም ሆነ በፓርላማ ውስጥ እንዲሰገሰጉ የማድረጉ ምስጢሩ የኼው ነው)። “ኢትዮጵያ ውስጥ ጥበቃና እንክብካቤ የሚደረግለት ብቸኛ ሕዝብ አለ፡ እሱም “ኦሮሞ” ይባላል።በዛው “ክልል” የሚገደል ሕዝብ አለ፤ እርሱም “አማራ” ይባላል። በክልሉ የሚኖሩ አማራዎች እና ክርስትያኖች ቢገደሉ ተጠያቂ የለም። ጠያቂ ካለም “አርፈህ ተኛ!!!” የሚል አጭር ማስጠንቀቂያ ይሰጠዋል።
አሁን አብይ አሕመድ በኢትዮጵያ የፖለቲካ ምኅዳር ውስጥ እየተፈጠረ ያለውን ማዕበል በእርግጥ ማሰስ ይችላል? የአብይ አሕመድ የማሰብ ችሎታና የዓዕምሮ በሽታው አሳሽ (ኮምፓስ- ጂ ፒ ኤስ) አስይዘህ ችግሩ ብታሳያውም ሊገባው የማይችል ቀውስ ውስጥ ነው። ጽሑፉን ላላወቁ ለማሳወቅ
ተቀባበሉት።
አመሰግናለሁ
ጌታቸው ረዳ ETHIOPIAN SEMAY