Tuesday, June 23, 2015

ኢትዮጵያዊያንን ከሊቢያ እስር ቤት አስወጥታ ወደ ግብፅ እንዲሸሹ ያደረገች ኢትዮጵያዊት!

ኢትዮጵያዊያንን ከሊቢያ እስር ቤት አስወጥታ ወደ ግብፅ እንዲሸሹ ያደረገች ኢትዮጵያዊት!

                 እዝራ
   ድንቅ በሆነ ጥበብ በተሞላበት በራሷ መንገድ በተለመደው ወገኗን በምድረ ሊቢያ እስር ወጥተው ወደ ግብፅ በነፃነት እንዲሸኙ ያደረገች ውድ እና ብርቅ የሆነች ኢትዮጲያዊት ላስተዋውቃችሁ።”
 
Yeharerwerk Gashaw with President Mandela
የኢትዮጵያ-የሐረር ወርቅ ጋሻው ትባላለች። በምድረ ሊቢያ ለወገኖቿ ቀድማ የደረሰች የወገን ጠበቃ የኢትጵያወርቅ-የሀረርወርቅ ጋሻው በምድረ ሊቢያ ለወገኖቿ ቀድማ የደረሰች የወገን ጠበቃ ሰላም ለኢትዮጲያዊ ወገን በሙሉ ማን ያውራ የነበረ የወጋው ቢረሳ ያተወጋ አይረሳም እንዲሉ በሊቢያ የታረዱት ወገናችንን እንዴት ልንረሳው እንችላለን። አዎ ግፍ ፈፃሚዉ ረስቶት ይሆናል ጀግና እህታችን የኢትዮጲያ ወርቅ ግን ሀዘን ሊወጣላት ባይችልም በቀጥታ ማንም ባላሰበው ሁኔታ የሊቢያን መንግስትና የግብፅን መንግስታትን በማነጋገር ለተጨማሪ ጥቃት የተዘጋጁ ወገኖች የማይታወቅ ቦታ ታስረው ቀን እየጠበቁ መሆኑን ከማንም ቀድማ በማወቅ ደርድር ጀመርች። ይህ ዝርዝር በማያስፈልገው ሁኔታ እኔ ለታሰሩት ወገኔ ጠበቃ ነኝ በማለት ድንቅ በሆነ ጥበብ በተሞላበት በራሷ መንገድ በተለመደው ወገኗን ከእስር ወጥተው ወደ ግብፅ በነፃነት እንዲሸኙ ያደረገች ውድ በርቅ የኢትዮጲያ ወርቅ ነች።
የኢትዮጲያ ወርቅ-የሀረር ወርቅ ጋሻው የኢትዮጵያ ስደተኞች እናት እና አባት ነች። የሀረር ወርቅ አስተዋጽኦ ንግስት አስቴርን እንድናስታውስ ያደርገናል። ንግስት አስቴር ወገኖችዋን እስራኤሎችን ከመታረድ ያዳነች ቅድስት ነች። ታሪኳም በብሉይ ኪዳን መጽሃፈ አስቴር በሚል ይገኛል።

       ወገኖቼ በዚህ ሰአት በሀገራችን መንግስት በሌለበት በውጭ ያለው ወንዱም ወሬኛ በሆነበት ዘመን ለወገን ዘሎ የሚጋፈጥ ጠብቃ ማግኘት ከላይ መግቢያ ላይ እንዳልኩት የነበረው የጉዳዩ ባለቤት ያውቀዋል ኢትዮጲያ ሀገራችን የእግዚአብሄር ሀገር ነች ህዝቧም ተባርኯአል እግዚአብሄር ወርዶ ሳይሆን በሰው አድሮ ነው ስራውን የሚሰራው በሀረርወርቅ በኢትዮጵያወርቅ አድሮ ስራውን ስላየን አቅማችን ምስጋና ነው።
የሚገርመው ከማንም ግለሰብም ሆነ ድርጅት ምንም እርዳታ ሳትጠይቅ በግሏ በራሷ የፈፀመችው በመሆኑ ከምንም በላይ የሚያኮራ የሚያስደንቃት ብርቅዬ የኢትዮጲያ ልጅ በመሆኗ እንኳን ደስ ያለሸ እንበላት እኔ በቅርብ እከታተል ስለነበር ያሳየቺው ብርታትና ኢትዮጵያዊ እልኽ ለመግለጽ ቋንቋ ያጥርብኛል  
 ስደተኛው አንድም ኢትዮጵያዊ ግለሰብም ይሁን የፓለቲካ ድርጅት የደረሰልን ባለመኖሩ "ወኪላችን አድርገን የሀረር ወርቅ ጋሻውን መርጠናል" ብሎ በይፋ መግለጫ ቃልኪዳን አስሮላታል።


የሃረር ወርቅ ኢትዮጵያዊ ሰብአዊነትዋን ስናስታውስ ስመ ጥር ከሆኑ ምርጥ ተብለው ከተከበሩ የኢትዮጵያ ንግስቶች ማሕደር ውስጥ መመዝገብ ይኖርበታል። የኢትዮጵያ የሀረር ወርቅ ጋሻው፤ ስደተኞችን ከሲኦል ለማውጣት በሴትነትዋ ያሳየቺው ልዩ የሆነ ብርታትና ጥረት ኢትዮጵያዊያን በክብር ማየት አለባቸው የሚል እምነት አለኝ። ባጭሩ የሀረር ወርቅ ለአገርዋ ያበረከተቺው አስተዋጽኦ ሲመረመር እጅግ አኩሪና ሰፊ በመሆኑ የጊዜያችን ምርጥ ሴት ያሰኛታል። ስደተኞች ዘውድ የደፉላት ይህች ንግሥት መንግስት ጥበቃ የተነፈገው፤ ፈላጊ የሌላቸው፤ የተረሱትን ሞርከኞች የቀድሞው የኢትዮጵያ ጦራሃይሎች ጀግኖችን በሙርከኝነት ያሰራቸውን ኢሳይያስ አፈወርቂ እንዲፈታቸው አድርጋለች።እኛ ወንዶቹ ቁጭ ብለን ከምድረ አሜሪካን ተነስታ በጦር ሜዳ ውላለች።  በጄኔቫ ኮንቨንሽን ሕግ መሰረት ምርኮኞቹ የጥበቃ መብት እንዲኖራቸው አድርጋለች። ሙርከኞቹ መኖራቸውንም ለሚመለከተው ሁሉና ለኢትዮጵያም ሕዝብ በቪዲዮ በተደገፈ ማስረጃ አረጋግጣለች።  ማንም ሳይነግራት፤ ማንም ሳይገፋፋት፤ በራስዋ ገንዘብ ጭምር ወጪዋን ችላ የኢትዮጵያን ሰንደቅ አላማ ለብሳ፤ ኤርትራ ከኢትዮጵያ ተገንጥላለች በተባለችዋ የኤርትራ ምድር ላይ ኤርትራ ኢትዮጵያ መሆንዋን ለሙርከኛው፤ ለዓለም እና ለኢሳይያስ አፈወርቂ  አስመስክራለች።  ሙርከኞቹን ለማስለቀ ከኢሳያስ ስትደራደር ኢትዮጵያን ሰንደቅ አላማ ከፊት ለፊቷ በክብር እየተውለበለበ ነበር ድርደር ያደረገቺው
 የቀድሞውን የኢትዮጵያን ባሕር ሃይል ባልደረቦች ከእነ ሲቪል ሰራተኞቹ በየመን ሲሰቃዩ የነበሩትን ከረጂም የስደት ስቃይ በኋላ ከእነቤተሰባቸው የአሜሪካንን ምድር እንዲረግጡ አድርጋለች። ባህር ሃይሉን ወደ አሜሪካን ያስገባችው በአሜሪካን መንግስት ባላት ተቀባይነትና በጊዜው በነበሩት የአምሬካን መሪና ቤተሰቦቻቸው ጋር ባላት የቅርብ ግንኙነትና ጉዳዮችን አቅርባ የማሳመን ልዩ ችሎታዋ ነው።  ንግስት አስቴ ወገኖችዋን ከመታረድ ያዳነችው የተጻፈላት ካልሆነ በስተቀር (መጸሃፈ አስቴር) የሚገርመኝ ሴት ልጅ ወገኖችዋን ለማዳን ብቻዋን እንዲህ ግራ ቀኝ ስትራወጥዶክተር፤ ፕሮፌስር፤ የፖለቲካ መሪ፤ የሬዲዮ ጡሩንበኞች ድህረ ገጽ ቴሌቪዢን ወዘተ የታሉ የት ገቡ? ያሳዝናል። ግን ባረረው አንጀቴ ለወገኔ የማስተላልፈው ጎበዝ ገንዘባችሁን ያዙ በናንተ ገንዘብ ከብረዋል ተጠንቀቁ ብቻ ነው ማለት የምችለው።

በመጨረሻ ለሀረር ወርቅ ጋሻዉ እውነትም የኢትዮጲያ-ወርቅ!! እግዚአብሄር ለወገንሽ ጠበቃ ተቆርቋሪ እንደሆንሻቸው ላንቺምም ለቤተሰቦችሽም  እድሜና ጤና ጠባቂ ይዘዝልሽ።             

ቀጣዩን የሀረር ወርቅ  የኢትዮጲያን ወርቅ ስራዎችን ይዤ እመለሳለሁ
ቸር ይግጠመን  እዝራ። Posted at Ethiopian Semay             getachre@aol.com