አገር
ያቀፈቻቸው ብዙሃን ሕዝቦችዋ ደናቁርት እስከሆኑ ድረስ የሰቆቃው ህይወት ማቆሚያ ሳይኖሮው አንዱ ሲያባራ ሌላው ይቀጥላል!
ጌታቸው ረዳ
(ኢትዮ ሰማይ Ethiopian Semay)
Friday, July, 17, 2020
በተቃዋሞ ሰልፍ ተሰላፊዎች ላይ የታዘብኩት ቅሬታዎችና ምስጋናዎች ትንሽ ልበል።
ቱርካዊው የህይወት ትወናዎች
ልበወለድ ደራሲና ፈላስፋው ታዋቂው ወጣቱ “መሕመት ሙራት ኢልዳን” እንዲህ ይላል። “In a country where
ignorant millions are in majority, nightmares never end! When one nightmare
finishes, another one starts!” ― ይላል። ትርጉሙ ከላይ በርዕሱ ላይ የተጠቀሰው ነው። እንዳውም የብዙሃኑ ደንቆሮነት መሆን
በታሪክ የታዩ አሰቃቂ ክስተቶች ሲደግፉ እራሳቸውንም የክስተቱ ተዋናዮችና ደጋዎች ሆኖው ሰቆቃው እንዳይቆም አስተዋጽአቸው የላቀ
መኖሩን ሲገልጽ እንዲህ ይላል፦*
በአንድ ወቅት ሚሊዮኖች
ለአዶልፍ ሂትለር አድናቆት አሳይተዋል፤ እንዲሁም ደግፈዋል ፡፡ አላዋቂ የሆኑት ብዙሃኑ ብዙውን ጊዜ ቀላል እውነቶችን ማየት
አይችሉም ፣ እና በግልጽም ግልጽ የሆኑትን ጫፎች የማየት ችሎታ የላቸውም! የታወቁት የብዙዎች ሞኝነት በታሪክ ውስጥ በሺዎች
የሚቆጠሩ ጊዜያት ተረጋግጧል! እያንዳንዱን ጊዜ የተሳሳተውን መሪ ሲከተሉ በመጨረሻ ላይ እራሳቸውን ቆሻሻ ማጠራቀሚያ በሆነው
የመዋኛ ገንዳ ተዘፍቀው ያገኙታል!” ይላል።
ወደ ጭብጤ የሚወስደኝ “አላዋቂ
የሆኑት ብዙሃኑ ብዙውን ጊዜ ቀላል እውነቶችን ማየት አይችሉም ፣ እና በግልጽም ግልጽ የሆኑትን ጫፎች የማየት ችሎታ
የላቸውም!” የምትለዋን ሓረግ ስትመለከቱዋት፤ እኛውኑን ኢትዮጵያዊያንን የምትገልጽ ሐረግ መገለጫችን ነች። በተደጋጋሚ አገራችን
ውስጥ ከ1966 ዓ.ም ጀምሮ እስካሁንዋ ደቂቃ ድረስ ወደ ሥልጣን የሚወጡ ግለሰቦችን እኛን ሲገርፉ የዋሁን ንጹህ ዜጋ
ሲያሰቃዩና ለስደት ሲዳርጉን ከሥልጣን እንዲወገዱ ከማስገደድ ይልቅ (አገሪቷ መንታ መንገድ ላይ ነች በሚል የጥገና ለውጥ
አራማጆች በሚያጠልቁላቸው ማጃጃያ ጭምብል በማጥለቅ” ይልቅ የድንቁርናቸው ብዛት “ ፎቶግራፎቻቸውንና የስታቀፉዋቸውን ባዕድ
ባንዴራዎችን እያውለበለቡ፤ ሴረኞች የሰጡዋቸውን የተቆረጠ አገራዊ መልክኣምድር/ካርታ/ እራሳቸውንና ከናቴራቸውን በማስዋብ፤
ንግግሮቻቸውን በጥቅስ እያስተጋቡ ሲደበቁና ሲያንጨበጭቡላቸው፤ ይባስ ብሎ አማራጭ የለንም እና “እርሱ” ሥልጣን ላይ ይቆይ
እያልን የአገራችን ሕዝብ ስቃይ ቀጣይነት እንዲኖሮው አሳፋሪ ባህሪያችንን ዛሬም በመከተል ላይ እንገኛለን።
ለብዙ አመታት አምባገነኖችን
ላለማቆላመጥ ሕዝብን ለማስተማር ያልጻፍነው፤ያልተናገርነው ክርክርም ሆነ ትምህርት ያለተተነተነ አንድም አልቀረም። መባል
ያለበትን ሁሉ ተናግረናል። ከ1966 ዓ.ም ጀምሮ በሚልዮኖች የሚቆጠር ሕዝብ “ጋጠወጥ” መሪዎችን ለማስወገድ ብዙ መራራ
መስዋዕት ተከፍሏል፤ ዛሬም ስቃዩ እየባሰ ታይቶ በማይታወቅ የሕዝብ እልቂት ተሸጋግሯል።
እንዲያም ሆኖ ትናንትም ሆነ
ዛሬ ኢትዮጵያን በማያባራ እልቂት እየገፏት ካሉት የትግሬና ኦሮሞ ፖለቲከኞች ዛሬ ሥልጣን ላይ የተኮፈሰው “የኦሮሞዎቹ ትልቁ
አሳማን” ላለማስወገድ ብዙ ኢትዮጵያውያን በተለይም አማራዎች ምክንያቱ በማይገባኝ ምክንያት ሕዝባዊ ተቃውሚ ሲደረግ “አብይ
መሪዬ ነው” በሚል እጅግ ዘግናኝና አሳፋሪ በሆነ ባህሪ ከሥልጣን እንዳይወገድ ቆሻሻ ፖለቲካን የሙጥኝ ብሎ እየዳከረ ካለው
“ትልቁ አሳማቸው” ጋር ሲኖጉዱ ማየት እጅግ የሚገርም ነው።
“አሳማዎች የቆሸሹ ናቸው ፣
ነገር ግን ከአሳማ የቆሸሹ ፍጡራንን እነግርሃለሁ፤ - “ውሸታሞች ይባላሉ” የሚያስተጋቡበት ልሳናቸው እውነትነት ስለሌለው አሳማ
ከሚንደፋደፍበት የበሰበሰ ቆሻሻ ይበልጥ ይሸታሉ።” ይላል ወጣቱ መሕመት። ኢትዮጵያውያን ይህንን ውሸታም “መሪዬ ነው” እያሉ
በተቃውሞ ሰልፍም ሆነ በየፌስቡኩ የሚያስተጋቡና የሚያሰራጩ ደናቁርቶች በብዛት እስካሉ ድረስ የኢትዮጵያ ፀሐይ ባልተገባ “እኩለ
ቀን” ላይ እየጠለቀች ባለችበት ባሁኑ ሰዓት ማዳን አይቻልም።
ትናንት ሐሙስ እና ዛሬ አርብ
ኢትዮጵያውያን የተለያዩ ሰላማዊ ሰልፎችን አስተጋብተዋል። በሦስት ቡድን ተከፍለዋል። የኦነግ (ሸኔ) የዳውድ ኢብሳን ባንዴራ
ይዘው ወጥተው ስለጃዋር መክተዋል። ሌላው ቡድን ስልጣንን እንደፈለገው እያደረገ እና ሻዕቢያን፤ ጃዋር እና ኦነጎችን ወደ አገር
አስገብቶ፤ አማራዎች፤ጋሞዎች ጉራጌዎች፤ወላይታዎች፤ ወዘተ… እንዲታረዱና ክርስትያኖችንም እንዲፈጁ” ያደረገ ወንጀለኛው
የኦሮሙማው ትልቁ አሳማ አብይ አሕመድን “መሪዬ ነው” በሚል መርህ የተከናወነው በመሪነት የተካፈለበት ሌላ ሰው ሳይሆን ልጅ
ተክሌ የተባለው ካናዳ ውስጥ የሚኖሮው ነው።ልጅ ተክሌ ማለት ፡ጎንደር ጎንደር የሚለው አስደናቂው የቴዲ አፍሮ ዘፈን የተቸ፤
“የአማርኛ ዘፋኞች ሰልችተውናል በምትካቸው ኦሮሙኛ ዘፋኞች ይዝፈኑ” የሚል፤ “ኤርትራኖችን በጀግንነት የሚያወድስ አማራ እና
የኢትዮጵያ ሰንደቃላማ በእሳት ቢጋይ ችግሩ ምንድነው?! ይቃጣላ! ፤ቅር አይለኝም” በማለት የሚታወቀው “ኦሮሞና ትግሬ እንጂ
አማራ የሚባል ወደ ሗላ መቀመጥ እንጂ ስብሰባም መምራትም ሆነ ሥልጣን ላይ መውጣት የለበትም” በማለት የሚታወቀው በብዙ
የመጠሪያ ስም የሚታወቀው “ልጅ ተክሌ (ኢሳት ውስጥ ጋዜጠኛ የነበረ ዛሬ የስደተኞች የሕግ ጠበቃ)” የተካሄደው ሰልፍ ነው።
ሰልፉ ኦሮሞዎች፤ ሻዕቢያዎች
(እኔ የማውቃቸው በቪዲዮ ያየሗቸው) የተካፈሉበት፤ በሚገርም ሁኔታ እስክንድርን ይልቃልን፤አስቴርን እና ብዙዎቹ ንጸሑን
በሰላማዊ ሰልፋቸው “ስማቸው እንዳይጠራ” የተፋለመው ማፈሪያ ቡድን የተሰባሰበበት” የነ አብይ አሕመድ ደጋፊዎች የገነቡት የነ
ልጅ ተክሌ ሰልፍ ነው፡
ሦስተኛው ቡድን ስለ እነ
እስክንደር ነጋ መታሰር አስመለክቶ ባስቸኳይ እንዲፈቱ የሚጠራ ሰልፍ ነው። ስለ አማራ መጨፍጨፍ እና ግፍ መብዛት አስመለክቶ
ጨፍጫፊ ወንጀለኞች ወደ ሕግ እንዲቀርቡ የሚጠራ ሰልፍ ነው። እነዚህ ምስጋና የሚገባቸው እውነተኛ ወገኖቻችን የሆኑት ኢትትጵያዊ
የአንድነት ሃይል ናቸው። ሀኖም በነዚህም ላይ ቅሬታየን ላስተጋባ።
አለቅላቂው ታማኝ በየነ
እንደሰማነው ከሆነ ዋሺንግተን አካባቢ የሚኖሩ 27 እውቅ ዜጎች ስለ አገራችን ሁኔታ እንዲመክሩ ጠራቸው። ከነዚህ ውስጥ
ኦነጎችና የአብይ አሕመድ አለቅላቂዎችም የተጠሩ ነበሩበት (አትገረሙ)። በዚህ ላይ አለቅላቂው “እኔ 2 ሳምንት በሚያስቸኩል
ስራ ስለምጠመድ አልገኝም ልተዋችሁ ነኝ” ብሎ አለቅላቂው ስርኣት ሳያስይዝ ጥሏቸው “ውልቅ፡ ብሎ ሄደ። መከፋፈል ተጀመረ፡
ስድብ ተወረወረ፡ ለሁለት ተከፈለ የሚል ዜና ሰማን። አለቅላቂውም በዚህ አንገብጋቢ ሰልፍም ላይ እራሱ አልተገኘም። ለምን?
አትበሉኝ፡ ምክንያቱም አለቅላቂው የማን ጫማ ላይ ወድቆ ሁለት አመት ሙሉ የማን ደጋፊ እንደነበረ አይታችሁታል።
ስለዚህ ስለ አለቅላቂው ብዙ
አመት ስለተናገርኩ እዚህ ላይ አቁሜ፤ ስለ ሰለማዊው ተሰላፊ የማይስማማኝን የዘመኑ አዲስ ፈሊጥ “በምንወደው እንደግፈዋለን
በምንቃወመው እንዲያርም ማሳሰቢያ እንለግሰዋለን” የሚለው ተቃውሞ ሰልፉም ላይ ሆነ በየፌስ-ቡኩና በየሚዲያው የሚነገረው “ወያኔ
የተወላቸውን ፈሊጥ” የምቃወመው መሆኔን ልግለጽ።
አብይ ሁለት አመት አገራችንን
ወደ ከፍተኛው የዘር እልቂት አሸጋግሯታል። በዚህ እንተማመን። የኔን ክርክር ካመናችሁ እንዲህ ያለው ሰው ሥልጣን ላንድ ቀንም
ቢሆን የሚፈቀድለት አይደለም። መጀመሪያ ሥልጣን የተረከበው በሕዝብ ደምጽ አይደለም። ስለዚህ አምባገነን ነው።ያለፈው
የአፓርታይድ የወያኔ ቅሪት ነው። አልሰማ ስትሉት የንቀቱ ንቀት “ሕገመንግሥቱን እንከባከባለሁ፤ብዙ ደም ከፍለንበታል” ብሎ
ነግሯችሗል። ጥገናዊ እንጂ መሰረታዊ ለውጥም አላመጣም ብሏል። ከዚህ እልቂት ወዲያ ምን ለማግኘት ነው የምትመክሩት? የሚለው
ጥያቄ ልጠይቅ ነው።
ልቦናችሁ በጎ አሳቢ ቢሆንም
ለምንድ ነው “በሞቱት እና ጡታቸው በተቆረጡት፤ እንዲሁም በታፈኑት፤ በተጠለፉት ልጃገረዶች እና ንብረታቸው ቤተጸሎቶቻቸው
በተቃጠለባቸውና ሚስቶቻቸው በተደፈሩባቸው ዓይን አይታችሁ ይህንን መሪ ከዚህ ወዲያ የሚፈይደው ምንድነው ብላችሁ ማየት እንዴት
አቃታችሁ?
ልነግራችሁ የምፈልገው፤
ጉዳተኞቹ ከዚህ መሪ የሚጠብቁት እራሱ ፍርድ ቤት ቆሞ በፍትሕ እንዲጠየቅ ነው! አደለም እንዴ? ለመከራ ዳርጓቸዋል እና አንድም
ቀን ፊቱን ለማየትም ሆነ፤ ሥልጣን ላይ እንዲቆይ ፍላጎት የላቸውም። ህይታቸውና ንብረታቸው ገዳዮችን አስገብቶ “መዘዝ”
ሆኖባቸዋል። ታዲያ ለምንድነው እናንተ ግን “አብይ ከሥልጣን ይውረድ” ማለት ትልቅ ተራራን መውጣት የሆኖባችሁ?
“አብይን እየደገፍን
በሚያደርገው ስህተት እንዲታረም እየተቃወምን አገር እናሻግራለን” የምትሉት ድንቁርና ቀድሞም “መለስ ዜናዊ ሲያሰራጨው የነበረ
የደናቁርት ምላስ ማስተጋቢያ እንዲሆን የተቀረጸ “ሰዘብቨርዠን” (ፖሌካዊ ብከላ) ነው።
አብይ ጃዋርን ስላሰረው አብይን
እንደግፋለን፡ ብላችሗል። አብይ ጃዋርን ያሰረው ስለ ሬሳ ማንገላታት እና ወቅታዊ የሥልጣን ሽኩቻ እንጂ “እስክንድር ነጋ”
አብየት ብሎ ሁለት አመት ሙሉ ለዓለም ያስተጋባው ክስ አስመክቶ አይደልም። እስክንድርንማ “አክራሪውን ቄሮና ጃዋርን በመቃወሙ”
“ጦርነት እንገባለን” ብሎ ጦርነት ከፍቶበት ይኼው አስር ውስጥ ከተተው። ይህ አደጋ እያንዣበበብን ነው ፤ካሁን እናስቁም ስላለ
ጀግናውን አሳምነው ጽጌን አሳረደው። ታዲያ ዛሬ “በምንስማማበት እንስማማ በማንስማማበት እየመክርን አገር እናሻግር” የሚለው
ወያኔ ትቶላችሁ የሄደው የደንቆሮዎች ምግብ አሁኑኑ ካላቆማችሁ፤መቸውንም ቢሆን አምባገነኖች የኢትዮጵያን ሕዝብ አበሳ ከማባባስ
አይመለሱም።
ራሳችሁን ለፖለቲካ ፍጆታ ስትሉ
ጥላ ሥር አትሸሸጉ። ለፖለቲካ ፍጆታ ስትሉ ራሳችሁን ጭምብል ውስጥ መደበቅ፤ የፈሪዎች እንጂ የጀግኖች ባህሪ አይደለም።
መሞዳሞዱ፤ኮምፕሮማይዙ ለ29 አመት የትም አላደረሳችሁም። ጸሓይዋ ፊታችሁ ላይ ታብራ፤ ሁሉም እንዲያየችሁ አድርጉ። ለማትጨብጡት
ሕልም አትገዙ።
አብይ ከሥልጣን ይወገድ ለማለት
አትሸማቀቁ! አሁኑኑ በዓለም ፍርድ ክስ ተመስርቶበት ለፍርድ ይቅረብ ማለት በሞራልም በሕግም በፈጠሪም የሚደገፍ ነው!
ልሳኖችን አስታወሱ እንጂ “የሙታኖች እና የተጠለፉት ልጃገረዶች ልሳን እያስተጋባ ያለው “አብይ ሥልጣን
ላይ ይቆይ ሳይሆን ለዚህ ግፍ ዳርጎናልና አሁኑኑ ለፍረድ ይቅረብ ይላሉ! በዚህ እንግባባ።
ጌታቸው ረዳ (ኢትዮ ሰማይ Ethiopian Semay)