Sunday, June 19, 2022

የኢትዮጵያ ወይንስ የኦሮምያ ንግድ ባንክ? የኦሮምያ ወይንስ የኢትዮጵያ አየር መንገድ?... ዳግማዊ ጉዱ ካሣ ይድረስ ለ“ኢትዮጵያ” ንግድ ባንክ! Ethiopian Semay 6/19/22

 

የኢትዮጵያ ወይንስ የኦሮምያ ንግድ ባንክ?

የኦሮምያ ወይንስ የኢትዮጵያ አየር መንገድ?...

ዳግማዊ ጉዱ ካሣ

ይድረስ ለ“ኢትዮጵያ” ንግድ ባንክ!

Ethiopian Semay

6/19/22



የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከፖለቲካ ሊገናኝ የማይገባው፣ ከዘረኝነትም ሊቆራኝ የማይጠበቅበት የሀገር የወል ሀብት መሆኑ ይታወቃል፡፡ በወያኔ ዘመን እንኳን ይህ ሀገራዊ ይዘቱና አገልግሎቱ እምብዝም ሳይነካ ሊቀ ሣጥናኤል ጠቅልሎ ቤተ መንግሥታችንን እስከተቆጣጠረበት እስከ 2010ዓ.ም ድረስ ቆይቷል፡፡ ባንክ ሙያተኞችን እንጂ ዘረኛና ጎጠኛ የአእምሮ ድኩማንን አይፈልግም፡፡ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በነገድና በጎሣ ሊቀፈደድ የማይገባው ቢቻል እንዲያውም ዓለም አቀፍ ይዘት እንዲኖረው ቢደረግ የማይበዛበት ትልቅ ተቋም ነው፡፡

ኢትዮጵያም ሆነች ንብረቷ የ86 ነገዶች የጋራ ሀገርና ንብረት እንጂ የኦሮሞ ወይንም የሌላ ነገድ ብቸኛ አንጡራ ሀብት አይደለችም፡፡ ይህ ዓይነቱ የተሳሳት ሃሳብ ከወያኔ ጀምሮ አሁንም ድረስ በባሰ ሁኔታ የቀጠለ፣ ነገና ከነገ ወዲያ ግን በታሪክ አሳፋሪ የሆነና በዚህ ድራማ ውስጥ የገቡ ሁሉ አንገታቸውን የሚደፉበት ትውልድን አሸማቃቂ ድርጊት ነው፡፡ በአእምሮ ሳይሆን በተለጣጭ ላስቲክ ሆድ የሚነዱ ዜጎች ነገ መግቢያ ቀዳዳ ሲጠፋቸው መፈጠራቸውን እንደሚራገሙ ማወቅ አለባቸው፡፡ ከቻሉ  ዛሬና አሁን ብዙም ሳይረፍድባቸው ከስህተታቸው ይመለሱ፡፡ ካለፈ ታሪክም ይማሩ፡፡ ማንም እንደገነነ አይቆይምና፡፡

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክን በአሁኑ ወቅት ምንም ዕውቀትና ችሎታ ሳይኖራቸው በኦሮሙማ መልማይነት ከየገጠሩ የሚሰባሰቡ ያልሰለጠኑና ከኅብረተሰቡ ጋርም በቋንቋም ሆነ በማኅበራዊ ተግባቦት ድሃ የሆኑ ኦሮምኛ ተናጋሪዎች ሙሉ በሙሉ ሊባል ጥቂት በሚቀረው ደረጃ ተቆጣጥረውታል፡፡ በመሠረቱና እንደእውነቱም ከሆነ የባንክ አገልግሎት የገንዘብና ገንዘብ ነክ ዕውቀትን እንጂ ነገዳዊ ማንነትን አይሻም፡፡ የባንክ ሥራ ሙያዊ ብቃትን እንጂ በአንድ ቋንቋ ተናጋሪነት የሚሰባሰቡ ማይማን ሰገጤዎችን አይፈልግም፡፡ ከሞራልም ከሃይማኖታዊና ባህላዊ ዕሤትም ያፈነገጡ ቁጡ ኦሮሞዎች የወረሩት የገንዘብ ተቋም ኪሣራ እንጂ ትርፍ እንደማይጠበቅበት ደግሞ ሊታወቅ ይገባል፡፡ ዘረኝነት የተጣባው እልህ የትም አያደርስም፡፡

በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሚታየው እውነት ይሄው ነው፡፡

ከዚህ በተያያዘ አንድ ሰሞነኛ መረጃ ልንገራችሁ፡፡ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ባለፈው ሰሞን የውስጥ ዕድገት ማስታወቂያ ያወጣል፡፡ ሠራተኞችም ማስታወቂያውን አንብበው ይመዘገባሉ፡፡ ምዝገባው ከተጠናቀቀ በኋላ ግን አዲስ መመርያ ይወጣና የተመዘገቡት ሁሉ ብሔራቸውን እንዲሞሉ ይነገራቸዋል፡፡ የዚህ መመርያ ዓላማ በጣም ግልጽ ነው፡፡ እንዲህ ያለ መመርያ ደግሞ በየትም ሀገር አይወጣም፤ ቢወጣ ደግሞ ዓላማው ልክ እንደኛው ሀገር ነው፡፡ ሠራተኞችን በትምህርት ደረጃቸውና በሥራ ልምዳቸው አወዳድሮ እንደማሳደግ ብሔር የተጠየቀበት ምክንያት ለሌላ ሣይሆን ኦሮሞ ኦሮሞውን መርጠው ለማሳደግ ነው፡፡ ይህን አሠራር ደግሞ በሁሉም የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች ፈጥጦ እያየነው ነው፡፡ ከቀበሌ እስከወረዳና ከፍተኛ፣ ከከፍተኛ እስከሚኒስቴር መ/ቤቶችና መከላከያ አዛዥ ናዛዦቹ ሁሉም ኦሮሞ ናቸው፡፡ ወያኔን አስከንድተው እነሱ በአሁኑ ወቅት የእግዚአብሔርንም ቦታ ለመቆጣጠር ሳይከጅሉ አልቀሩም፡፡ እኛም በዚህ ከእንስሳም በወረደ ድርጊታቸው ፈዘንና ደንግዘን ፍርዱንም ለላይኛው ሰጥተን ተቀምጠናል፡፡

ከወያኔ የበለጠ ይሉኝታና ሀፍረት የሌለው የለም ስል እንደነበር አስታውሳለሁና የወያኔ ጌታ ሚስተር ሉሲፈር ይቅር ይበለኝ፤ እነሱን ዕጥፍ ድርብ የሚያስከነዱ ደናቁርት ኦሮሙማዎች ሀገሪቱን እንደመዥገርና እንደተምች ተጣብቀው እየቦጠቦጡ ናቸው፡፡ ሁሉም አክራሪ ኦሮሞ በ“አካም ነጉማ፣ በፈያዳ ፈዩማ” እየተሰባሰበ ኢትዮጵያን ከዳር እዳር እየዋጣት ነው - ሌላው አዘጥዛጭና አሽቃባጭም አላቸው - ሊያውም ከፕሮፌሰር እስከ ዲፕሎማ፤ ከትምህርት ሚኒስቴር እስከእርሻ ሚኒስቴር፤ ከቤተ መንግሥት እስከ ፓትርያርክ ጽ/ቤት፡፡ የሚገርመው ለመሰልቀጥ ዕቅድና ፕሮግራም የተያዘላቸው “”ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች”ም ሁሉ ተስማምተው በየተራ ለመበላት ወረፋ ይዘዋል፤ ከዚያም ባለፈ እርስ በርስ እየተጨፋጨፉ የኦሮሙማን ድካም በእጅጉ እየቀነሱለት ነው፡፡

ወይ ኢትዮጵያ! እንዲህ ያለ አዘቅት ውስጥ ትግባ? ፋኖዎች ቶሎ ቶሎ በሉ እንጂ፡፡ የምን ማፈር መተፋፈር ነው፡፡ ትግሉን እዚያው ጀምሩና ብዙ ሰው ወደሚጠብቃችሁ ወደ መሀል ሸዋ ብቅ በሉ፤ በቅድሚያ ግን ሆዳምና ተላላኪ አማራን ከሥሩ የሚያጸዳ ልዩ ኃይል ይቋቋም፡፡ ….

በኦሮሞ ብቻ ከተወረሩ መሥሪያ ቤቶች አንደኛው የኦሮምያ ማነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ነው፡፡ በዚህ ተቋም ከዘበኛ እስከ ሥራ አስኪያጅ ኦሮሞ ነው፡፡ ሁሉም ሠራተኛ ኦሮሞ መሆኑ ብቻውንና በራሱ ለኔ ችግር አይደለም፡፡ ሁሉን የሥራ ቦታ ኦሮሞ ቢይዘው ደንታየ አይደለም፡፡ ችግሩ ዓላማውና የሥራ ችሎታ ሳይኖር በዘረኝነት ትብታብ ተጠልፎ ሀገርን ለማውደም የሚሠራው ግፍና በደል ነው፡፡ እንጂ ለምሣሌ ሥራውን ችለውት፣ ቅንና ጨዋ ሆነው በትህትና ማስተናገዱን ቢያውቁበት እኔ ግድ የለኝም፡፡

ሰሞኑን ሆነ ብዬ በተወሰኑ ሆስፒታሎች ዞርኩ፡፡ ተገረምኩ፤ አዘንኩም፡፡ የኢትዮጵያ ትንሣኤም በእግረ መንገድ ቁልጭ ብሎ ታየኝ፡፡ የጅብ ችኩል ቀንድ የመንከሱ ምሥጢርም ተከሰተልኝ፡፡ ኦሮሙማዎች ይደንቃሉ፡፡ ጠንጋራም ሆነ ወልጋዳ ለአንድ ዓላማ ከልብ ከሠሩ አይቀር እንደኦሮሙማዎች ነው፡፡ ከዚህ ብዙ መማር አለብን፡፡ በተለይ የኢትዮጵያ ነጻነት ተዋጊዎች ከነዚህ ጅሎች ትምህርት ቅሰሙ፤ ግን ጽናታቸውን ብቻ እንጂ ጭካኔያቸንና ጅብነታቸውን አይሁን፡፡ መጨከን ሲያስፈልግ መጨከንም ለድል ያበቃልና ጨክኑ፡፡

ወያኔ ብልጥ ነበረች፡፡ በይሉኝታቢስነትና በሀፍረተቢስነት በዓለም አንደኛ እንደሆነች ቅንጣት ሳላፍር እናገርላት የነበረችው ወያኔ አሁን ዞሬ ንግግሬን ሳጤነው ትልቅ ስህተት እንደነበር ተረዳሁ - ማንን ይቅርታ እንደምጠይቅ አላውቅም እንጂ በድጋሚ ትልቅ ይቅርታ፡፡ በሀፍረት የለሽነትና በይሉኝታቢስነት ኦሮሙማዎችን የሚስተካከል እንደሌለ ዛሬ ላይ ሆኜ በሚገባ ተገንዝቤያለሁ፡፡ ወያኔ ከአሥር ነገሮች አንድ ወይ ሁለቱን ምናልባትም ሦስቱን ለሌላ ጎሣና ነገድ ለይስሙላም ቢሆን ታካፍል ነበር፡፡ የአሁኖቹ ግን ድብን ያሉ ገገማዎች ናቸው፡፡

 ከ100 ነገሮች ውስጥ አንድ መቶ አንዱን ለነሱ ይወስዱታል፡፡ ሌላው አጨብጭቦ ሲቀር እነሱ ይምነሸነሹበታል፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ወያኔ ስትጠግብ በሚተርፋት ገንዘብ አንዳንድ ሀገራዊም ይሁን ግለሰባዊ ቁም ነገር ትሠራ ነበር፡፡ እነዚህ ገሪባዎች ግን ዕውቀትና ፍላጎት፣ ትምህርትና ልምድ፣ ጥበብና ችሎታም ስለሌላቸው ዳንኪራ ሲረግጡና ካገኟት ሴት ጋር አንሶላ ሲጋፈፉ አድረው ቀኑን ሲያፋሽጉ ይውላሉ እንጂ በቁም ነገር ቦታ አታገኟቸውም፡፡ ትልቅ አለመታደል ነው፡፡ ስሙን አስተካክለው የማይጠሩትን መኪና ይገዙና ከየግድግዳና ፖሉ እያጋጩ በሀገር ሀብት ይጫወታሉ፡፡ አምናና ታቻምና መኪና አጣቢና ተላላኪ ሆኖ የምታውቀው ኦሮሞ ዛሬ ባመቱና በሦስት ወሩ መሬት እየቸበቸበና ከፍተኛ ጉቦ እየተቀበለ ሚሊየኔር ነው፤ ወይ ኦነግና ኦህዲዶች!!

ዕድሜያቸው አጭር ነው የምንለው ለዚህ ነው፡፡ እነዚያ ብልጦች ስለነበሩ 27 ዓመታትን እንደምንም ቆዩ፡፡ እነዚህ ግን የለየላቸው ደናቁርት ስለሆኑ አምስት ዓመት መድፈናቸውንም እጠራጠራለሁ፡፡ አያያዛቸው ያስታውቃልና ዕድሜያቸው የወራት እንጂ የዓመታት አይደለም፡፡ ቱ! ምን አለ እንትና በለኝ ጥቂት ሣምንታት ቢቀራቸው ነው፡፡ እንደጉድ እኮ ነው የወበሩት!!