Tuesday, May 28, 2024

ሓሽፈራይ በተባለ “ሞቃታ የኤርትራ እስርቤት” ተደብድበው የሚሞቱ እስረኞች የሦስት ዘንዶዎች ምግብ እንደሚሆኑ ሚስጥሩ ይፋ ሆነ (ምንጭ Ethiopian Semay) ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay ድረገጽ አዘጋጅ) ኤርትራ ኤርትራ የእስረኞች አገር ወይስ የነፃነት አገር? ከቆዩ ሰነዶች THURSDAY, MAY 28, 2020

 

ሓሽፈራይ በተባለሞቃታ የኤርትራ እስርቤት”

 ተደብድበው የሚሞቱ እስረኞች የሦስት ዘንዶዎች ምግብ እንደሚሆኑ ሚስጥሩ ይፋ ሆነ

(ምንጭ Ethiopian Semay)

ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay ድረገጽ አዘጋጅ)

ኤርትራ የእስረኞች አገር ወይስ የነፃነት አገር?

ከቆዩ ሰነዶች

THURSDAY, MAY 28, 2020

የሚገርመው ደግሞ ይህ በዘልማድኣንደርእየተባለ የሚጠራው የሓሽፈራይ እስርቤት ከሥር ያሉ ጉድጓዶች ከላይ ከታች እንደፎቅ እና የታች ምድርቤት ያለባቸው የጉድጓድ ክፍሎች እያንዳንዱ የተጠላለፉ መሰላሎች አልዋቸው። የክፍሎቹ መጠሪያ ስም በኤርትራ ከተሞች ስም የተሰየሙ ናቸው። ወደ ታች ቤት ምድር ያሉአቑርደት፤ተሰነይ፤አስመራ፤ታይታኒክ..ወዘተ የሚባሉ ክፍሎች አሉ። እነዚህ እያንዳንዳቸው 100 ሰው እንዲይዙ የተደረጉ (200 እስረኞች እንደገቡበት የተደረጉ ናቸው) ከነዚህ ወደ ጎን ወደ ኋላ የተሰራ አዲሱ እስረቤት ደግሞናቕፋይባላል።

ሞቃታው ጥልቁ ጨለማ የተሰራው ናቕፋ የሚባለው የምድርቤቱ ክፍሎች እያንዳንዱ ጉድጓድ 300 ሰው እንዲይዙ ተደርገው የተገነቡ ናቸው (አሁንም እጥፍ እንዲይዙ የተደረጉ ናቸው ‘600’ ወደ እነዚህ ክፍሎች ለመግባት ውስብስብ በሆኑ 11 የጉድጓድ መሸጋገሪያ ጥልፍልፍ መሰላሎችን ማለፍ አለብህ።በነዚህ የጉድጓድ ክፍሎች  በጭቃ ስላልተለሰኑ አፈሩ እየፈሰሰ የጉድጓድ ቆላማ ትሎች እስረኞቹን ደማቸው እየመጠጡ ሰውነታቸው እየበሉ ያቆስልዋቸዋል። ስለ እስርቤቱ ቅርጽ ምን እንደሚመስል የዘረዘርዋቸውን ካሳየሁዋችሁ አሁን ደግሞ በእስር ቤቶቹ ጉድጓድ ውስጥ ሰለሚፈጸሙ እጅግ የሚዘገንኑትን ጥቂቶችን ልጥቀስ፡ -

ለሞት የተፈረደባቸው ሰዎች መቃብራቸው እንዲቆፍሩ ከተደረገ በኋላ ጉድጓዱ ውስጥ እያሉ የሳዮናይድ ውሃ በላያቸው ላይ በመድፋት ተቃጥለው እንዲሞቱ የመደረጉ ምስጢር እና በድብደደባ ብዛት የሚሚቱ ተመርማሪ እስረኞች እንዲሁም በእነተኽላይ ማንጁስእውቅና እንክብካቤ የሚደረግላቸው ሦስት ትላልቅ ዘንዶዎች ከበረሃ አጥምደው በማምጣትለማዳ እንዲሆኑበማድረግ የሞተ ሰው በሌለበት ጊዜ ቡቹላዎች/ትንንሽ ውሾች/ እንዲራቡ በማድረግ ምግባቸው እንዲሆኑ ይደረጋል። ተቀጥቅጠው የሞቱ እስረኞች ሲኖሩ ደግሞ ሬሳቸው ለነዚህ ሦሰት ዘንዶዎች ምግብ እንደሚሆኑ ከተነገሩ አሰቃቂ ምስጢሮች ይገኙበታል።

ይህ የተለያዩ የጭካኔ ድርጊቶች የሚፈጸምበት አሰቃቃ እስር ቤትሓሽፈራይይባላል።ከአንድ አመት በፊት ስትናገር ያደመጥኳትሓሽፈራይውስጥ የታሰረችነርስስትገልጽ  ሳምንት ባልሞላ ጊዜ የራስ ፀጉርህ እራሱ እንደ ሳር እየተቃጠለቡን ቡንእያለ በመርገፍ መላጣ እንደሚያደርግህ አሰቃቃው የጸጉር መርገፍ ስትናገር አድምጫለሁ። እዛ ሳሕል እና ሓሽከራይ የመሳሰሉ ሞቃታ እስርቤቶች በመርማሪዎች ተደፍረው የሚያረግዙ ወጣት ሴቶች እንዲረሸኑ የተደረጉ ብዙ እንደሆኑ እና አንዳንዶቹም በሙቀቱ እና በድብዳባ እርግዝናቸው እንዲያስወርዱ  እንደሚደረግ መናገርዋን አስታውሳሉ።

ዛሬ ደግሞ ዛራ ሚዲያ የገለጸው በዝግየብርት ኮንተይነርልብሶቹ አስወልቀው በጋለውየብረት ኮነተይነር/ቀፎ/” እራቁቱ ለሦሰት ወር የታሰረ ወታደራዊ ባለማዕረግ ውሃ ስለማይፈቅዱለት የሚጣልልትን በጣም የደረቀ ዳቦ በሽንቱ እየነከረ ይውጠው እንደነበር በሁለተኛውቪዲዮዛራ ሚዲያለአዘጋጁ ባንደበቱ በግል እንዳወያየው የተናገረውን ይዘረዝራል።

የጭካኔ ድርጊቶች በርዕሱ እንደሚመለከተው ታሪኩ የተፈጸመውሓሽፈራይበተባለ ቆላማ መመርመርያ እስርቤት በከፍተኛ ኤርትራዊያን ወታደራዊ መኮንኖች በእነ ተኽላይ ማንጁስ ዋና አዛዥነት እና ዮናስ በተባሉ የምርመራ ሓላፊዎች የሚካሄድ እስርቤት ውስጥ ነው። ይህ አሰቃቃ ድርጊት መፈጸሙ ምስጢሩ የወጣው  ነጋሲበሚባል የኤርትራ ወታደር የነበረ ወጣት  እራሱ በሚያዘጋጀው "Zara Media/ዛራ ሚዲያላይ ነው;

 የጭካኔ ድርጊት ፈጻሚዎች እነማን ናቸው በሚል ከኢሳያስ ጀምሮ እስከ ታች ጉምሩክ እና ፖሊሶች እንዲሁም ድምበር ጠባቂዎች ያለው የሙስና እና የወንጀል መዋቅር የሰዎቹን ስም በመዘርዘርየኤርትራ ባርነትበሚል 4 ቀን የሚቆይ ኢሳያስ አፈወርቅና ወታደራዊ መኮንኖቹ በሕዝብ ህይወት የሚያደርጉት አስነዋሪ ስነምግባር እና በሥልጣን መባለግ የሚፈጸሙ ወንጀሎችን የማጋለጥ ዘመቻ አሁንም 4ኛው ቀን በመቀጠል ላይ ነው።\

በዚህ ወንጀልን የማጋለጥ ዘመቻ ቀን ውስጥ ተደብቀው የነበሩ የባድመ ጦርነት ምስጢር በድርጊቱ የተካፈለ አንድ ኤርትራዊ እንዲህ ይላል፡በባድሜ ጦርነት ውስጥ ኢሳያሰና ጭፍሮቹ የወያኔ ወታደሮችመቓብር ስውዓት”(አርበኞች መቃብር”) ሆን ብሎ በማፈራረስ በሙታን መቃብር እና ሓውልት ወንጀል ፈጽሟል እያሉ ወያኔን ሲወነጅሉ አድምጣችኋል፤ ሓቁ ግን እኔ በማፍረሱ ሂደት እንድካፈል ከታዘዙት አንዱ እኔ ነበርኩ ስለዚህ ድርጊቱ የተፈጸመው በራሳችን አለቆች የሴራ ተግባር እንጂ ማንም መቃብር ያፈረሰ የለምሲል የተደበቀውን ምስጢር ይፋ አድርጎታል።

 ትግርኛ ለማድመጥ የምትችሉ ምንጩ ይኼው ልስጣችሁ። ይህ አንደኛው ክፍል ሲሆን 4 ቀን የሚደረገው በኔ አገላለጽ4 ቀን የሚቆይ ወንጀልን የማጋለጥ በዓልየተለያዩ ስዕለ ድምፆች (ቪዲዮዎች) ተለጥፈዋል።አንዱ ይኼው፤ የሚከተለው ነው።ዋና ዋናዎቹ የወንጀል ድርጊት ፈጻሚ ጀኔራሎች እነማን ናቸው? የሚል የውይይት ርዕስ የማጋለጥ ዘመቻ ይኼው

ቀንዲ ገበርቲን ሓደግቲን ሓለፍቲን ጀነራላትን ኣብ ኤርትራ / ስምኦን ገብረድንግል & / ወልደዝጊ ባህታ ካልኦትን መን እዮም

https://youtu.be/V80GSO3t40Y

አመሰግናለሁ

ጌታቸው ረዳ (ኢትዮጵያን ሰማይ Ethiopian Semay ይጎብኙ)