Friday, June 5, 2020

የኢትዮጵያዊነት ውበት የተላበሰው የባልደራስ ፖለቲካ በድሆች ላይ ጦርነት የከፈተው ለፋሺስቱ አብይ አሕመድ ትልቅ የራስ ምታት ሆኖበታል! ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay)

የኢትዮጵያዊነት ውበት የተላበሰው የባልደራስ ፖለቲካ በድሆች ላይ ጦርነት የከፈተው ለፋሺስቱ አብይ አሕመድ ትልቅ የራስ ምታት ሆኖበታል!
ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay)
ዘመን እየቆጠሩ በተረኛነት ሥልጣንን የሚነጥቁ የሕዝብ ጠላቶች የፈለጋቸው ሲፈጽሙ ልናቆማቸው አልቻልንም። ቀጥለዋል፤..ይቀጥላሉም። አንድ ጸሐፊ እንዳሉት ‘የፈጸሙት  አልበቃቸውም’ ስለዚህም ገና ይቀጥላሉ። ባንድ ኢትዮጵያ አንድ የተለየ ጎሳ ወይንም የጎሳው አባሎች በስልጣን እና በሃብት እየተግበሰበሰ በሚከመር የዕድገት ዕርከን ወደ ሰማየ ሰማያት መስፈንጠርና የሌሎቹ ጎሳዎች ደግሞ እየተደቆሱ መኩሰስ ፤ እያደሩ መቅጨጭ ፤ብሎም በገፍ መገደል፡ ውሎ አድሮ ዛሬ ዜጎች “ምሳ” ለመብላትም ሆነ በምድር ላይ “በሕይት የመኖር” (ሕለውና) ከፈጣሪ ሳይሆን በገዢዎች ፈቃድ የሚፈቀድና የሚከለከል ሆኗል። በሚገርም ክስተት “ገዢዎች” ራሳቸውን ወደ “ፈጣሪነት” ለውጠዋል።

ትንሽ ወደ ሊት ላስታውሳችሁና ወደ ባልደራሱ እመልሳችለሁ።
አገራችን ለ27 አመት በትግሬ ወያኔዎች መዳፍ ገብታ የመወረርዋን እና የባሕር በርዋን የማጣቱ ጉዳይ ለማስረዳት ብዙ ደክመን ተቀባይ አጥተን ነበር። ዛሬ ያ እውን ሆኖ ሁሉም አምኖ ተቀብሎታል። ያለፈው የ27 አመት ክርክራችን ስንሰማው የነበረው ንትርክ “ትግራይ አላደገችም ያውም ከሌሎቹ በባሰ ደህይታለች ተጨቁናለች” የሚሉ ወገኖች (ያውም ምሁራን እና የፖለቲካ መሪዎች) ተከራክረውኛል። ለክርክራቸው የጤና፤የትምህርት፤የንግድ ባለቤትነት፤ የውጭ ኤምባሲ ተጠቃሚነት ወዘተ… እብጠቱ  ሁሉ “ምን አባትክ ታመጣለህ የነበረው ትምክሕት” በማስረጃ ፤በራሳቸው “አረንጓዴው መጽሓፋቸው” ሰነድ የሚመሰክር አምጥተን ስንከራከር ተመጻዳቂ ተከራካሪዎቻችን ግን ማስረጃ ሊያመጡ አልቻሉም። ክርክራችን ትግራይን ለምን አሳደጋችሁ ሳይሆን ሌላውን ለምን አቀጨጫችሁት ነበር ክርካራችን። ያ በማስረጃ ተከራክረን ወደ ታሪክ መዝገብ ተጽፎ ገብቷል። ዛሬም በየራዲዮኑ፤በየ ዩቱቡ ያንን የተጠቀሙት “ጥቂቶች ናቸው ሕዝብ አይደለም” ፤ “ትግራይ አልተጠቀመችም” ልፍለፋቸውን እያደመጥን ነው።

ዛሬ ደግሞ “ፈንቅል” የተባለ ትግራይ ውስጥ ተነሳ የተባለ ሕዝባዊ ንቅናቄ የአብይ አሕመድ ደጋፊዎች በቃለ አጋንኖ የሰከሩበት፡ “የብልግና” ፓርቲ የሚጠቀምበት ‘ሕብረ ቀለም’ የያዘ ፤ ከዚያም አልፎ  በሚሰቀጥጥ ሁኔታ “የጸረ አማራው እና የኢትዮጵያ ወታደሮችን ምፅዋ ላይ ያስጨፈጨ፤ በከፍተኛ ብሔራዊ ክሕደትና ወንጀል መጠየቅ የሚገባው ፤ ሙሉ በሙሉ ነብሰ ገዳይ የነበረው “ጎሰኛ እና ከሃዲ” አረመኔውና የወያኔው ጦረኛ የነበረው ሟቹ በሓዱሽ አርኣያ (ጀኔራል ሓየሎም አርአያ) “የቅጽል ስሙ መጠሪያው” በነበረው “ፈንቅል” በሚል ስያሜ የሚጠራ ፤ “ወያኔን ከምድረገጽ ገለበጥነው ፤ አንቀጠቀጥነው” ወደ እሚል “የልጆች ጨዋታ የሚመስል ቃለ አጋኖ” ገብተው በዜና ማሰራጨዎች ሲስተገቡ ሰምቼ ከመሳቅ ሌላ የምለው አልነበረም።

መገናኛ ብዙአህ የሚባሉትም “መናኛ አስተዳደራዊ” የሆነውን ጥያቄ ፤ ወያኔን ከመቃወም/ከመፈንቀል/ ፍጽም ከማይገናኝ ፖለቲካዊ ይዘት ገብተው ሲደልቁ ማየት “ለ45 አመት በትግራይ ላይ የተንሰራፋው ከባዱ “ሰብቨርዥን” እና የጎሳ ፖለቲካ ያለመረዳታቸውና የትግራይ ሕዝብ ተነስቶ ወያኔን ይጥላል የሚል ቅዠት ” ስመልከት ይህንን የሚያስተጋባ ተቃዋሚውም እራሱ በእንጭጭ ላይ የሚዳክር ብዙ የሚቀረው ይመስለኛል።

እንደዚያም ሆኖ- ዛሬ ደግሞ ኢትዮጵያ በሦስተኛው የኦሮሞዎች የወራራ ዕርከን ገበታለች። ይህ ክርክርም ከላይ ከጠቀስኩት ተመሳሳይነት ነበረው። ከብዙ አመት በፊት ከደደብ አድርባይ ኢትዮጵያውያን ምሁራን ተብየዎች ስከራከር “ሰሚ አጥቼ” ነበር። ከትግሬዎች የሥልጣን ወረራና የሉዓላዊ (የባሕር ወደብ እና ድምበር መሬቶች) የግዛት ማስደፈር ቀጥሎ የሚመጣው የውስጥ ወራሪ አካል “ኦሮሞዎች” ይሆናሉ ብየ ነበር።  ዛሬ እውን ሆኖ “ሦስተኛው የኦሮሞዎች የወረራ ዕርከን” ድርጊቱን በዓይናችሁ እየመዘገባችሁት ነው። ይህን እውነታ መጠራጠርና ለማስተባባል የሚሞክሩ  እውነታውን ለመቀበል የሚያዳግታቸው ሰዎች ካሉ “በእዬ-ዩቱብ ቴ/ቪዥን” ራሳቸውን እየቀረጹ የምታደምጥዋቸው ዜጎቻችን በሚያሳስብ የሕሊና ቀውስ የተሰቃዩ ጤነኞች የሚመስሉ ግን ሕሙማን የሆኑ፤ ወይንም የስርዓቱ ተጋሪ ባለተራ የሆኑት እና እንዲሁም የ28 አመት የጎሳ ፖለቲካ ያልገባቸው ወይንም የጥቅም ተጋሪ ድኩማን ወገኖች ብቻ ናቸው። ማስረጃዎቻችን አንድ ባንድ ይኼው ከዚህ ቀጥሎ እንመልከት።

አሁን ወደ የባልደራስ አማራር ኢትዮጵያዊ ሰብኣዊነት እና የአብይ አሕመድ ፋሺሰትነት የፈጠረው ፍጥጫ ልውሰዳችሁ።

ከዚህ ቀጥሎ የተያያዘው ቪዲዮ ብዙዎቻችሁ አይታችሁታል።  ይህ ‘የስዕለ ድምፅ’ ሰነድ ስትመለከቱ የአብይ አሕመድ “የኦሮማዎቹ ፋሺስታዊ ዕቅድ” በደምብ ታያላችሁ። መጀመሪያ ዜጎችን ከተጠለሉበት ቤቶቻቸው አባርሮ አፈናቀላቸው። የተነሳበት የዘር ማጥፋት አጅንዳውን /ዕቅዱን/ ለማከናወን እርጉዞች፤ እመጫቶች፤ ሽማግሌዎችና ህጻናት ለርሃብ ፤ ለቁርና ለበሽታ ሜዳ እንዲጋለጡ ሜዳ ላይ አፈሰሳቸው።

ይህንን ፋሺስታዊ ድርጊት ለማስቆም ቆርጠው የተነሱት የባልደራስ አመራሮች ደግሞ ፍጹም ኢትዮጵያዊነት በተላበሰ ሰብአዊ ተግባር ዜጎችን የመርዳት ሃሊፊነታቸውን ለ748 በላይ የሆኑ ተፈናቃይ ቤተሰብ (አንድ ቤተሰብ የያዘው ልጅ እና ዘመድ/ወላጅ አባዙት) ለመርዳት ከፍተኛ የገንዘብ ወጪ በማድረግ፤ ሜዳ ላይ የተጣሉ እነኚህ ድሆችን ለመርዳት ሲሉ የፋሺሰቶችን ሕግና ደምብን ሳይጥሱ ሜዳ ላይ በፋሺስቶች ጭካኔ ለተጣሉት እርጉዞች፤ህጻናት እና ሽመማግሌዎች  ምግብ ሲያከፋፍሉ “በፋሺሰቱ አብይ አሕመድ የውስጥ ትዕዛዝና እውቅና (በባልደራስና በድሆች  ላይ ለማከናወን የዛተው “ግልጽ ጦርነት” እዚህ ላይ አትዘንጉ) የታዘዙ “የፋሺሰቶቹ ቅጥረኛ ፖሊሶች” ቦታው ላይ በመድረስ በሚሊዮን ብር ወጪ እና በብዙ ድካም የተገዛውን የምግብ ዕርዳታ ለድሆች እንዳይዳረስ በማገድ የባልደራስ አመራሮችን እስርቤት አስገብተው ለቅቀዋቸዋል። አብይ አሕመድ ያፈናቀላቸው ድሆች በተጣሉበት ቦታ አለመሞታቸው ሲመለከት መሞት እንዳለባቸው ስላቀደ ምግብ እንዳያገኙ ህጻንትና እርጉዞች ባዶ ሆዳቸውን እንደገና አስራባቸው።

እኔ ይህንን የምዘግበው ዜናውን አላወቃችሁትም ብየ ሳይሆን ለወደፊቱ ሰነዶች ሲፈለጉ በዚህ ሰነድና ቀን መመዝገቡ ለታሪክ ጸሐፊዎች ለመዘከር ይጠቅመል። ፋሺሰቱ አብይ አሕመድ ልክ እንደ 1965 የወሎ እና የትግራይ ርሃብ እንዲደገም በምሉ ልቦናው እየሰራ መሆኑን እርግጠኛነት ሆኖ መከራከር እንችላለን። ሦስተኛው የኦሮሞ ወረራ ይመጣል ብየ ከብዙ አመታት በፊት የተከራከርኩትን ሰነድ አሁን እውን መሆኑን ማየት ትችላላችሁ። ብዙዎቹ የሕግ ምሁራን የፋሺቱ አገልጋዖች ሆኑ እንጂ  አብይን ለዓለም አቀፍ ፍርድቤት የሚያስከስስ የዘር ማጥፋት ወንጀል እየፈጸመ ነው። ግን የሕግ ባለሞያዎቹ በየ ኢንተርኔቱ ከመዘባረቅ አልፈው ወደ ተግባር ሄደው ሰውየውን በፍረድ መክሰስ አልቻሉም።

እኔ የምተብቀው ይህ ሰሚ ያጣው “የ28 አመት ማጉረምረምና ቁጣችን” ካልታሰበው የኢትዮጵያ አምላክ ሲወስን መለስ ዜናዊን እንዳስወገደልን ዛሬም “አብይ አሕመድ” ተመሳሳይ ዕጣ እንደሚገጥመው ዘወተር የምለው ስለሆነ ያንን መጠበቅ ነው። የተራቡ ወገኖችን በረሃብ መግደል “የፈጣሪን ቁጣ” ይቀሰቅሳል።
የባልደራስ አባላት ለኮሮና ወረርሽኝ ተጎጂዎች ምግብ ሲያደርሱ በአዲስ አበባ ፖሊስ ታስረው ተለቀቁ

አመሰግናለሁ!!
ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay)