Sunday, June 25, 2017

አሳፋሪው ቴድሮስ አድሓኖም ምርጫውን “በመለስ መንፈስና” በወያኔ “የቆረጣ ስልት” ነው ያሸነፍኩት! አለ ጌታቸው ረዳ (ኢትዮፕያን ሰማይ አዘጋጅ Ethiopian Semay)



አሳፋሪው ቴድሮስ አድሓኖም ምርጫውን “በመለስ መንፈስና” በወያኔ “የቆረጣ ስልት” ነው ያሸነፍኩት! አለ
ጌታቸው ረዳ (ኢትዮፕያን ሰማይ አዘጋጅ Ethiopian Semay)

Tigrayan youth in Addis during the brainwashing process by the TPLF cabals
ትችቴ፤ በሌላ ጉዳይ ልጀምር።መጀመሪያ ለሻለቃ ዳዊት ወ/ጊዮርጊስ ይቅርታ እጠይቃለሁ። ባንድ ወቅት አንድ ሰው ወላጅ አባቱን አውቃቸዋለሁ፤ “ባንዳ ነበሩ” ብሎ ብዙ ነገሮች ስላጫወተኝ እኔም ሰውየውን አምኜ የዳዊት ወላጅ አባት በዛው አስቀምጬአቸው እንደነበር አስታውሳለሁ። በኋላ ግን ከሻለቃ ዳዊት አንደበትና ቃለ መጠይቅ ሳደምጥ ወላጅ አባቱ የተከበሩ አገር ወዳድ እንደነበሩ ስረዳ ከተነገረኝ ጋር ታሪካቸው አብሮ መጣጣም ስላልቻለ። የሻለቃ ዳዊት ቃል ስላሳመነኝ፤ ለስሕተቱ ከፍተኛ ይቅርታ ሻለቃ ዳዊትን እጠይቃለሁ። የፖለቲካ ልዩነታችን ግን እንዳለ ሆኖ፤ ይህንን በሚመለከት ብቻ ከኢትዮጵያዊ ጨዋነት አንዱ ‘ይቅርታ’ መጠየቅን አኩሪ ባሕላችን ስለሆነ፤ በስሕተት ስለነበር ይቅርታ እጠይቃለሁ። ለወላጅ አባታችን የኩሩ ዜጋነት፤አገር ወዳድነትና አርበኛነት ክብር እና ምስጋና አቀርባለሁ።

አሁን ወደ ዋናው ርዕስ ልግባ። ዛሬ ላቀርበው ያሰብኩትን ትችት በቴድሮስ አድሓኖም ጉዳይ ሊቀርብ አልቻለም። ትናንት ላንድ ማሕደር ፍለጋ የወያኔዎችን ማሕደሮች ስጎበኝ፤ ቴድሮስ አድሓኖም እና ደብረጽዮን የተባሉት የወያኔ የፖለቲካ ወፍጮዎች የፈጩትን ዱቄት በየቦታው ሲቦን አይቼ እጅግ ስለገረመኝ ትግርኛውን ተርጉሜ ለናንተው ለምወዳችሁና ለምትወዱኝ አንባቢዎቼ ላካፍላችሁ ወሰንኩ።

“መሬት ሲያረጅ የጃርቶች መጫወቻ ይሆናል” ይላል አማርኛው። እነኚህ “እነሱ እና እኛ” በሚል የጥላቻ መስመር የተካኑ ትናንሽ ሰዎች (ሊትል ሜን) ከጊዜ ወደ ጊዜ  ሥልጣን ላይ በቆዩ ቁጥር የባሰውኑ የማሰብ ችሎታቸው እጅግ እየወረደ መምጣቱ ስመለከት የመጪዋ የአገሪቱ ዕጣ ፈንታ የነበረችንን ትንሽ የተስፋ ስመለከት፡ ትንሽዋ ጭላንጭል የሚዘጋና የሚያጨልም መሆኑን ከምንገምተው በላይ በጣም አስጊ ሁኔታ እንዳለች የምናረጋግጥበት ምልክት አንዱ ይህ ትእዝብት ነው። የዚህ ሰውየ አርቆ አሳቢነት ያልበሰለ የጫካ ንግግሩ ወደ ጨቅላነት ደረጃ የመለወጥ ክስተት የትግራይ ሊሂቃን የምሁርነት ምጥቀት አሳፋሪ ደረጃ መድረሱንም እንድታዩት በሚል ነው።

ከርዕሱ የተመለከተው “ቃል” ቴድሮስ አድሃኖም ወደ ዓለም የጤና አጠበበቅ ዳይሬክትርነት ማዕረግ “በቆረጣ” (በስልት) መመረጡን ለማበሰር በብዙ ሺ ለሚቆጠሩ የቴድሮስ አድሃኖምን “ስዕል” የታተመበት “ከናቲራ” ለለበሱ ለአዲስ አበባ ኗሪ ወጣት ትግሬዎች ‘መይ 20/2017’ (ግንቦት 20/2009) የወያኔ ንግሥነት (ሄጂመኒ/ጎበጣ) ለመዘከር በተደረገው ስብሰባ በትግርኛ ያደረገው ንግግር ነው።

የባሕር ወደቦቻችንን ለዓረቦች አሳልፎ የሸለመ በባንዳው መለስ ዜናዊ አምልኮ የሰከረ፤ የፖለቲካ ብስለቱ ያላሰፋ ይህ ሰው፤ የመለስ መንፈስ እንዳስመረጠው ለነገራቸው ወጣቶች እና የወያኔን ኮቴ/መሰመር/ ተከታዮች በሆኑ የትግሬ ዘፋኞች በርካታ ሙገሳና የሙዚቃ ፊልሞች (ቪዲዮ) ተሰርቶለታል። ለቴድሮስ አድሓኖም ክብር በሚል የተዘፈኑለት በርከት ያሉ በቪዲዮ ተቀርጸው የወጡ ሙዚቃዎች አሉ።በጣም አስገራሚ ነው። ከነዚህም አንዱ ካሁን በፊት ለመለስ ዜናዊ ሞት መዘክር የዘፈነለት ዛሬም ለቴደሮሰ አድሓኖም ገብረየሱስ ሙገሳ የዘፈነው ካናዳ አገር የሚኖሮው ፤በቀልድ ነጋሪነት እና በሙዚቃ” ሥራ የታወቀው ትግሬው ሲሳይ ሕሸ (በቅጽል ስሙ መሪጌታ ሕሉፍ) በሚባለው በሙያው በቶሮረንቶ ከተማ የኢምግሬሽን የጥብቅና ሥራ የሚሰራ ግለሰብ የዘፈነለትን ቪዲዮ “አንበሳ በረኻ” (የበረሃው አንበሳ) የሚለውን እና ሌሎች አወዳሽ ሙዚቃዎች ተቀርጸው ተዘፍነውለታል።Dr. Tedros Adhanom / Anbessa Bereka / New Tigrigna Music 2017 / Sisay Hishe      https://youtu.be/WQX9HbV4OPo

ሌሎችም እንዲሁ “ዉቑር ወልዱ (መላኺ) የተባለው ትግሬ በአማርኛና በትግርኛ የተደባለቀ ሙዚቃ የዘፈነለትን እና የመሳሰሉ በዙ የሙገሳና የትምክሕት መግለጫ ጋጋታዎች ተሰርተውለታል። የውቑር ወልዱ ሌላው ጉደኛ “የደስ ይበልን” ጭፈራ የተካተቱበት የትግራይ ሕዝብ ምስሎች በትእግስት ተመልከቱ፤ Mukur Weldu | Des Bilonal | ደስ ብሎናል ( Dr.Tedros Adhanom) New Ethiopian Music 2017 https://youtu.be/xBp4G5J9no4  


ይህ ውቕሮ ወልዱ የተባለ ወጣት ሙዚቀኛ፤ የቴድሮስ አድሓኖም ወደ ዓለም አቀፍ የጤና ጉዳይ መመረጥ አፄ ምንሊክ ከፋሺስት ጣሊያን ወራሪዎች የተዋደቁበትና የተቀዳጁትን ከዓድዋ ጦርነት ድል ጋር በማያያዝ የዓድዋ ጦርነት ድል ታሪክ በቴድሮስ አድሓኖም ተደግሟል ይለናል። ወገኖቼ እንዲህ ያለ እጅግ የሚያስደነግጡ፤አስፈሪ የሆኑ፤ ምንም የማያውቁ ወጣት ሙዚቀኞች የዓድዋን ጦርነት ከቴድሮስ አድሓኖም ጋር መመረጥ እንዴት ሊያገናኙት እንደቻሉ ለኔ እጅግ እንቅልፍ አሳጥቶኛል።ሌሎች ዘፈኖቻቸው ብንፈትሽ ምን እንደሚሉ ከመረመርን እጅግ አስፈሪና አስገራሚ ግጥሞችን እናገኝ ይሆናል (እኔ በግሌ ያደመጥኳቸው ብዙ አሉ)። በሚገርም ሁኔታ በጣም በርካታ የጎሳ ፖለቲካ ሰባኪያን “ሙዚቀኞች” ብዙ ስራዎች ለቴድሮስ አድሓኖም ሙገሳ አሳትመዋል። 

ሌላው ያስገረመኝ ሙዚቀኛ ደግሞ በድምጹ ቃና ከትግራይ ሙዚቀኞች ሁሉ በግምባር ቀደም የማስቀድመው ሙዚቀኛው “ሲሳይ ሕሸ’ ነው።(ፋሺስታዊ የወያኔ ፖለቲካዊ መስመሩን ወደ ጎን ትትን ማለት ነው- ስለ ወያኔ ፖለቲካ በኢመይል አጠር ላሉ ጊዜያት በማስረጃ አስደግፌ ላስረዳው ተለዋውጠን ነበርና፤ የትግርኛ መጽሐፌንም እንዲያነበው ልኬለት ነበር፤ ሆኖም… ‘አውቆ የተኛ ሰው ሆኖ ስላገኘሁት’ ቢነቀንቁት የሚነቃ እንዳልሆነ ታዝቤዋለሁ! ፍራንዝ ፋኖን Cognitive Dissonance-የሚለው-ዓይነት) ።

ይህ በፎቶግራፍ የሚታየው “ሲሳይ-ሕሸ”አንበሳ በረኻ /“የበረሃ አንበሳ”/ ሲል ለቴድሮስ አድሓኖም የዘፈነውን ነው። ከስንኞቹ አንዱ በትግርኛ እንዲህ ይላል።
“ንስኻ እንተለኻ ምሳና፤
ዝሳገራ የለን ሩባና”
አንተ ከኛ ጋር እስካለህ ድረስ፤
 ደፍሮ የሚሻገር የለም እወንዛችን ድረስ! 

 ይህ ስራ ከቴድሮሰ አድሓኖም “የቆረጣ መርጫ’ ጋር  ምኑን ከምኑ እንዳገናኘው ስትመረምሩ የጎሳ  ፖለቲካ “በእኛ እና በእነሱ” አጥርና ውዳሴ እንዴት እንደከተተን ዓይነተኛ ጠቋሚ ስራ ነው። ይህ ሁሉ “ከአምበሳነት ሙገሳ እና ከዓድዋ ጦርነት ድል” ጋር የማያያዝ ባሕሪ የሚያሳየን መመርምር ያለበት ትልቅ የቤት ስራ እንደቀረን እና የትግራይ ከያኒዎችና ወጣቶች የፖለቲካ ንቅዘት ምን ያህል ጥልቀት እንደቦረቦራቸው ከነዚህ ሙዚቀኞች መረዳት እንችላለን።

ከሌሎች ጎሳዎች በተለየ በትግሬ ወጣቶች (የቴድሮስና የመለስ እና መቀሌ ውስጥ የተተከለው የወያኔ ተጋዮች ሃውልት ያለበት ስዕል የታተመበት ከናቲራ መልበስን) እና የኪነት ባለሞያዎች ሰውየውን ‘በአንበሳ በረሃነት’ እና ‘በዓድዋ ጦርነት ድል” ማነጻጸርንና ማወደስን እንዲህ ያለ ጋጋታ ለትግሬው ቴድሮስ አድሓኖም ለምን ተከሰተ? ብለን ብንጠይቅ መልስ ማግኘት አንቸገረም።ሁልጊዜ በማንኛውም አገር “የጎሳ ፖለቲካ” የሚከተሉ ማሕበረሰቦች የሚያርፉበት የመጨረሻ ምዕራፍቸው’ ‘የሚከተሉትን ድርጅት ወይንም የድርጅቱን መሪ “በመንፈስነት/በመለኮትነት” በማምለክ፤ ድርጅታቸውን ወይንም መሪያቸውን የሚቃወመውን ሁሉ “በእኛና በእነሱ” ሚዛን መዝነው፤ በእዛው አጥር ውስጥ ታጥረው አንዱን ‘አንበሳ’ ሌላኛው ‘ፈሪ’ በማድረግ መስመር በሚሉት ‘የሕሊና አጠባ ስልት’ እንደ ከብት መንጋ (herds) በአንድ መስመር  እየተመሙ ከሰውነት ባሕሪ ውጪ በማድረግ የታወቀ ‘የፋሺስታዊ ጎሰኛነት ፖለቲካ’ ስለሚከተሉ ነው። “ዘር”፤ “ጎሳ”፤“መስመር”፤“የወንዝ ልጅነት” ቁርኝት ያስከተለው የክልላዊ ፖቲካ ውጤት ነው። ፈጪውም አስፈጪውም አንድ አካል ነው። ጎሰኝነት!     

የቴድሮስ አድሓኖም አስገራሚና አሳፋሪ የጫካ ሰው “ንግግር” ከመመልከታችን በፊት ቴድሮስ እንዴት ተመረጠ? የመለስ መንፈስ ማለትስ ምን ማለት ነው? ቆረጣስ ምን ማለት ነው? ቴድሮስ አድሓኖም “የመለስ መንፈስ ቆረጣ ተጨምሮበት ነው የተመረጥኩት! ምክንያቱ ገባችሁ ምን ማለት እንደሆነ?!’ ብሎ ወጣቶችን ሲጣይቃቸው ምን ለማለት እንደፈለገ ውስብስቡን ፖለቲካ ለተከታተልነው ምን ማለቱ እንደሆነ ግልጽ ነው።

 የመለስ ዜናዊና የኢሳያስ አፈወርቅ ወደ ሥልጣን መምጣትና በሥልጣን ላይ የሰሩት ወንጀልና ምዝበራ በዓለም ፍርድ ቤቶች እንዳይጠየቁ ግምባር ቀደም ተከላካይ እየሆኑላቸው ያሉት እነማን መሆናቸው የምናውቀው ነው። አይደለም እንዴ? የሊቢያን እና የሶርያን ሕብረተሰብ ወደ ሲኦል ሕይወት የዳረጋቸው ‘ኦባማ’ የሚባላው ሌላው ‘ኡሉምናቲ’፤ አዲስ አበባ ላይ መጥቶ ፤ አሽከሮቹን (ፕሮክሲ ወኪሎቹን) በሕዝብ የተመረጡ (ዲሞክራቲካሊ ኢሌክትድ ጋቨርንመንት) ብሎ ያለንን እናስታዉሳለን። አደለም-እንዴ? ታዲያ ቴድሮስ አድሓኖም ‘በቆረጣ’ የተመረጠበት ዘዴ ብንፈትሽስ?

ታሪኩን እንፈትሽ። ኢትዮጵያ በማን እጅ ነች? በውጭ ጋር ሃያላን መዳፍ ውስጥ ነች። ወያኔዎችስ ምንድ ናቸው? ፕሮክሲ/የውጭ ሃይላት ሥራ አስፈጻሚዎች ናቸው። አዲስ አበባ መዲናችን ላይ እነማን ናቸው ያሉት? ከወያኔ የሲኣይኤ ቅጥረኞች ውጪ እራሳቸው ሲአይ ኤዎች አዲስ አበባ ውስጥ አሉ። ተደላድለው ተቀምጠዋል። ጅቡቲም አዲስ አበባም! 

ፎቶው ላይ ከቴድሮስ አድሓኖም ጋር የምታዩዋቸው ሁለት ጉደኞች ናቸው። ብርጭቆ ውሃ ይዞ ቴድሮስ አድሓኖምን ትኩር ብሎ እያነጋገረው ያለው የዓለም ሕዝብ በተለይ የአፍሪካ ሕዝብ ካለበት ቁጥር እንዳያድግ የወሊድ ቁጥጥር (በድብቃዊ ስልት ‘ዩጀኒክ’ በሚባል የሕዝብ ጠረጋ/ ጽዳት/ ‘ሾቭል’ ብላችሁ ጥሩት!) ዘመቻ ውስጥ የገባው ቢል ጌት ነው። ይህ ሰው ባተረፈው ገንዘብ ስለተጨናነቀ እሱ እና ብሉምበርግ የተባለው ሌላው ሴረኛ ቢልየነር ጋር ሆነው ያገኙበትን ገንዘባቸው እበጎ ተግባር ከማዋል ይልቅ ‘የሚያከማቹበት ስላጡ’፤ በተለይ ቢል ጌይት የወላጅ አባቱን ፈለግ በመከተል፡ እናቶች መምከን አለባቸው ብሎ፤ ‘በኡሉሙናቲው/ሰይጣናዊ’ አጀንዳ ተነስሳስቶ፤ የዓለም ሕዝብ በተለይ አፍሪካ እና የመሳሰሉ ድሃ አገሮች እናቶችን በማምከን በመርዛማ ክትባት ዘመቻ ተሰማርቶ የሕዝብ ቅነሳ ዘመቻ እያካሄደ ነው።

 ብዙ ሺዎች ህጻናት ሕንድ ውስጥ ‘ድውያን’/ /አካለ ስንኩላን/ ሆነው እንዲወለዱ ስላደረጋቸው በፍርድ ቤት የተከሰሰ ሰው ነው። ብዙ መሰሪ ተግባሩ ብሱ እናቶችን በማምከን ዘመቻ በመሰማራቱ እና ህጻናትንም ስንኩላን እንዲሆኑ በስራው ክንዋኔ ስለታዬ (ለነዚህም ሃዘኔታ ባለማሳየቱ) ብዙ ሃያስያን ቢል ጌትን የሰይጣን በር ብለው ይጠሩታል።

ቀጥሎ በቢል ጌትስ እና በቆረጣ የገባው ቴድሮስ አድሓኖም እማሃል ላይ ቆማ እጆቿን አጣጥፋ ያለቺው ጆሮው ላይ የጉትቻ ቀለበት ያንጠለጠለ ወንድ የሚመስለው ነጭ ሴትዮ ጌይል ስሚዝ ነች። የህች ሴት ማነች ? ጌል ስሚዝ ኢትዮጵዮጵያ ውስጥ በበጎ አድራጎት (ዩ ኤስ ሲ ኣይ ኤስ) ስም የወያኔ ቀኝ እጅና አማካሪ የነበረው ከዚህ ዓለም በሞት የተለው ‘ሲኣይ ኤው ‘ፖል ሄንዝን’ የተካች ነች። የድሮ ባልዋ የኢሳያስ አፈወርቅ ዋና ፕሮፓጋንዲሰት የነበረ ፤ ጋዜጠኛ ተመስሎ የገባው ኢሳያስ ጋር ሳሕል በረሃ የኖረው የሲአይ ኤው Dan Connell ባለቤት የነበረች ነች። “ይህች ሴረኛና ጉደኛ ሴት የመለስ ዜናዊ የቅርብ አማካሪና የወያኔው የየማነ ጃማይካ ውሽማ የነበረች ነች። 

ቀንጨብ አድርጌ ላስነብባችሁ፤-

  once the mistress of a Marxist guerilla fighter in the Horn of Africa, today Gayle Smith is a senior advisor to Barack Obama in the White House, USA.

Gayle Smith started her career in service to the American Empire as an undercover CIA operative posing as a journalist in the Horn of Africa in the late 1970’s. Taking her duty seriously, she became the mistress of a guerilla fighter known by the nom de guerre of “Jamaica” in the Marxist-Leninist-Enver Hoxha-ite Tigrayan Peoples Liberation Front (TPLF), then fighting for independence from the Soviet Union supported Mengistu regime in Ethiopia.

As a close confidant to the leadership of the TPLF, Gayle Smith would spend the decade of the 1980’s as the liaison between the CIA and Meles Zenawi, the leader of the TPLF who was to become the Prime Minister of Ethiopia after the defeat and overthrow of the Mengistu regime by the Eritrean independence movement in 1991.” እያለ ይቀጥላል። (Guerilla Mistress To Obama Confidant; The Life And Crimes Of Gayle Smith By Thomas C Mountain 01 December, 2010 Countercurrents.org   ቶማስ ማውንቴን አስመራ ውስጥ የሚኖር (አውስትራሊያዊ ወይንም አሜሪካዊ/ የሻዕቢያ ቡችላ ነው። እሱም እንደ እነ ዳን ኮኔል ስራውን እያከናወነ ነው የሚል አምነት አለኝ።

እነዚህ እና የመሳሰሉ ኢሉሙናቲ ድርጅቶች እና ግለሰቦች ናቸው በቴድሮስ አድሓኖም የቆረጣ ምርጫ ገብተው ከውስጥ ያስመረጡት። የዓለም ብጥብጥ ቀያሾችና የብዙ አገሮች ሕዝቦችን ደም ያፈሰሱና የጨፈጨፉ ፤ ግብዞችና የዓለም ‘ጸረ ሰላም’ የሆኑ እነ ‘ቢል ክሊንተን’ እና እነ ‘ቡሽ’ የመሳሰሉ በበርካታ የሕዝቦችን ሕይወት ማጥፋት ወንጀል ሴራ ተጠያቂ የሆኑ እነዚህ ማፈሪያዎችም በቆረጣው ሴራ ምስክርነታቸውን ለቴድሮስ ድጋፍ ሰጥተዋል። ሳይጠሩዋቸው አብየት ሳይለኩዋቸው ወዴት የሚሉት በቂቼዎቹ “እኛም ጨምሩን ‘ጥልቅ ብየ’ የኛዎቹ የአፍሪካ ማፈሪያዎችም” በዚሁ ቪድዮ ለወያኔው ቴድሮስ አድሐኖም በማያውቁት አገር (ኢትዮጵያ) ገብተው ‘ጥብቅና’ ቆመው ሳይቸግራቸው ‘አረፋቸውን ሲደፍቁ’ ታደምጣላችሁ። Presidents Clinton, Bush and World Leaders Speak About Dr. Tedros Adhanom https://youtu.be/LotD_Mo5FEo

የወያኔው ቴድሮስ አድሓኖም የጤና አስተዳዳሪነት ብቃት ለ7 አመት ሙሉ የኢትዮጵያ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ሆኖ ሲሰራ የብዙ አማራዎች፤ሶማሌዎች፤ጋምቤላዎች እና ኦሮሞዎች እንዲሁም ሌሎች ዜጎቻችን የጤና ውድቀትና “የሕዝብ የጅምላ ጭፍጨፋ” ሲካሄድ እንደነበር ከተለያዩ ተሟጋቾች አንብበናል/አድምጠናል። እንኳን ለዓለም ጤና ድርጅት ይቅርና በራሱ መስርያቤት እንኳ በብዙ ሚሊዮን ዶላሮች ንቅዘት/ምዝበራ ሲካሄድ እንደ እቃ ተቀምጦ ሲያየው የነበረ እና ብቃት ያልነበረው ‘ጉልቻ’ ሰው መሆኑን የሚከተለው የሳዲቅ አህመድ ራዲዮን ቃለ መጠይቅን አድምጡ። Professor Mohammed Tahiro on Tedros Adhanom https://youtu.be/bcDWPkpEkhY

 የብዙ ነብሳትን ህይወት ያጠፋና ያፈናቀለ፤ በዘር ማፅዳት ወንጀል የሚከሰስ የፖለቲካ ድርጅት ውስጥ በአመራር አባል የሚሰራ ሰው፤ የሕክምናው ፈቃድ ከመንጠቅ ይልቅ፤ ለዚህ ዓለም አቀፍ ስራ መመደብ የአሜሪካን መሪዎችና ትላልቅ ከበርቴዎች ድጋፍ ሰጥተው በቆረጣ እንዲመዘዝ፤ ለምን እንደተደረገ መገመት አያስቸግራችሁም። እነ ቢል ጌት እና እነ ጌል ስሚዝ በሕዝባችን ላይ የሚደርሰው በክትባት ሽፋን ፤እናቶችን ማምከን፤ የአካል ድውይነት/በፖሊዮ ክትባት ሽፋን/” የሚፈጸመው ወንጀል እንዲቀጥል ምቹ ሰው መምረጣቸው እንደሆነ ለኛ ግልጽ ነው። አሜሪካኖች አፍሪካ ውስጥ መሪዎችን ስያስቀምጡ በእነሱ ፖሊሲ እና ፕላን የሚጓዝ ታዛዥ ሰው ነው የሚያስቀምጡት። እምቢ ካለ ፤ያስወግዱታል። አይደለም እንዴ? ሳዳም ሁሴንን አይተናል! በሽርን እያየን ነው! የኮሎምቢያው ኢማኑኤል ኖሬጋን ምን እንዳደረጉት አይተናል። አይደለም እንዴ?
ጌይል ስሚዝ ያለ ቦታዋ ገብታ በቅርቡ በቁቤ የላቲን ፊደል ኦሮሞ ወጣቶች ያሳዩትን ዕድገት (ድንቁርናውን ዕድገት ብላዋለች) ያስተላለፈቺው ዘገባ በአንድ ኢትዮጵያዊ ሊቅ በጥያቄ ተወጥራ መልስ እንዳላገኘችበት የምናስታውሰው ነው። የአሜሪካኖች ሴራ በጤና ብቻ ሳይሆን በፖለቲካውም እጃቸው ሰፊ መሆኑ በቅንጅት ምርጫ ጊዜ አይተናቸዋል! አይደለም እንዴ? 

አገራችን ተወርራለች። ተደፍራለች። ዓረቦች ከብበውናል። ይህ ደግሞ የወያኔ መስመራዊቆረጣ ሴራና ‘ሲኣይኤ’ የተሳተፉበት እጅ ነው። ‘ቴድሮስ አድሓኖም’ ወጣቶቹን ‘መስመር!መስመር!’ እያለ “የመለስ መንፈስና” “ወያኔአዊ መስመር” እንከተል ሲላቸው ምን ማለቱ እንደሆነ ግልጽ ነው። ለውጭ ሃይላት ከተምበረከክን፤ ስልጣን በእጃችን ይገባል፤ ለምንሰራው የዘር ማጽዳት ስራ ወንጀልም ‘ሸፋን’ ይሆኑናል’ ነው የቆረጣውና የወያኔ መስመር መልዕክት። ቴድሮስም ለዚህ ምቹ ምልምላቸው ነው። ለዚህ ነው በመለስ መንፈስ እና በቆረጣ ነው የተመረጥኩት ብሎ ለትግራይ ወጣቶች አዲስ አበባ ውስጥ ሰብስቦ የነገራቸው።

አሳፋሪው የቴድሮስ የትግርኛ ንግግር ወደ አማርኛ ልተርጉምላችሁ። በቪዲየው ውስጥ  የታየው ትዕይንትና የሚወጣው ድምፅ ቴድሮስ አድሓኖም  በሚናገራቸው በያንዳንዱ ሐረጎች ውስጥ፤ ወጣቶቹ በሕሊና የጎሳዊ ዕውርነት ስሜት እየተነዱ፤በጭብጫባና በአደንቋሪ ‘ፉጨት’ አጅበውታል። የምተረጉመውም እናንተ እንደትጠቀሙበት፤ለታሪክ ጸሐፊዎች እና የፖለቲካ ምሁራን እንድትመረምሩት በሚል እሳቤ ነውና ድካሜን ከንቱ ሳታደርጉት ለትንታኔአችሁ ተጠቀሙበት። የሰውየው ንግግር ታሪክ ውስጥ መመዝገብ ያለበት እጅግ አሳፈሪና ጠባብ ቡድንተኛነት፤ተንኮል፤ ሴራ፤ ክህደት፤ ድንቁርና፤ ትምክሕትና ጉራ ያካተተ አስገራሚ ንግግር ነው።  እንዲህ ይላል፤-

{ “በጣም  ነው የማመሰግነው፤ አመሰግናለሁ! ይህ የዓለም ጤና ጥበቃ ሹመት እንዴት ተገኘ ብላችሁ አጭር ጥያቄ ልታቀርቡ ትችሉ ይሆናል።ላጭር ጥያቄ አጭር መልስ አለኝ።ውስጠ ምስጢሩ የድርጅት መንፈስ በውስጥ ስለነበረበት ነው። የመጀመሪያ ነገር በዘመቻው ላይ የተጠቀምንበት “የመለስ ዜናዊ ፋውንዴሽን” ነው። ትርጉሙ ተረድቶአችል? እንግዳውስ ከተረዳችሁ፤ከመነሻው የመለስ መንፈስ ይዤ ነው ለዘመቻው የተነሳሁት።ታውቁታላችሁ “የመለስ-መንፈስ!”፤“የውድባችን/የድርጅታችን መንፈስ!”፤“የይቻላል-መንፈስ!”፤“የሕዝባዊነት መንፈስ!” “የትዕግስት መንፈስ!”፤“የመስመራችን መንፈስ መከተል! ነው። ይኬው ነው ትርጉሙ።…
‘….ስለዚህ ‘የመለስ መንፈስ’ በምንልበት ጊዜ፤ የመስመራችን መንፈስ ማለት ነው። በእዛው ላይ ልጨምርላችሁ… ያ መንፈስ ምን ይዞ እንዲጓዝ ያደርጋል? መልስ ስጡኝ!? የሚሰጠን መልስ ከቶ አንንበረከክም! አንሸነፍም! እንደዚያ አይደለም እንዴ ሙዚቃችን/ዘፈናችን/መዝሙራችን የሚለው?! ….

መንፈሱ ላይ ሕዝባዊነት ተጨምሮበት! እሱ አልነበረም እንዴ የድርጅታችን መነሻ? ሕዝባዊነት! ታውቁታላችሁ አይደል!? ከመጀመሪያ ጀምሮ ድርጅታችን ከጥላቻ ነፃ የሆነ ነው። ስለነበርም ነው አሸናፊነታችንን እያረጋገጠ የመጣው። እኛ “እነሱ” ወደ ወረዱበት የጥላቻ ደረጃ መውረድ ነበረብን? አልወረድንም ፤ለወደፊቱም አንወርድም! ወደ ላይ ነን የምንወጣው!  እንደነሱ ወደ ታች አንዘቅጥም! መስመራችንን ነው የምንከተለው! መስመራችን ነው የሚያዋጣን! የሕዝብ ፍቅር ነው የሚያዋጣን! እኛ የአንድ ክፍል አካሎች (ጎሳ) ስለሆንን ሌለውን የሚጻረር ተግባር አናደርግም፤አድርገንም አናውቅም። ሁሌም መያዝ ያለብን ምክንያታዊ መስመራዊ መሆን አለበት። ሕዝባዊነት ከተከተላችሁ ሁሌም በማንኛውም ግጥሚያ አሸናፊዎች ናችሁ። መስመር ያመነ አይሳሳትም፤ ያም ስለሆነ ነው ውድብና/ድርጅታችን/ እዚህ ደረጃ የደረሰቺው።…

‘… በግልጽ ላስቀምጥላችሁ… የተደረገው “ውግያ” የድረጅታችን መስመር ስለተጠቀምን፤ (ኢቭን) እንዲያውም ዘመቻው ሲካሄድ “ቆረጣ” ነበረው! ያ ደግሞ የአገራችን ኢትዮጵያ ነው። ያ ቆረጣ ይዛ ነው ለ26 አመት ከ irrelevant ወደ relevant በሁለም ደረጃ ለውጥ ልታመጣ የቻለቺው። ያ የድርጅታችን መስመር የመላ ኢትዮጵያ ሕዝቦች መስመር ሆኗል። ያም ስለሆነ ነው መስመራችንን ለመስበር ከውስጥም ከደጅም እየፎከሩብን ያሉት። የጥንታዊ ስልጣኔአችንን ሳንጠቅስ፤ ኢትዮጵያ እኛ በተከልነው መስመር ምክንያት ከብዙ ሺ ዘመናት አንገትዋን ካቀረቀረቺበት ወጥታ ለመጀመሪያ ጊዜ ነች አንገትዋን ቀና ማድረግ የቻለቺው።

እነዚህ ዛሬ እየተቃወሙን ያሉት ከ26 አመት በፊትም ሆነ ዛሬ ምን ያደርጉ እንደነበርና ምን እያደረጉ እንዳሉ እናውቃቸዋለን።ወደ ፊት መስመራችንን ይዘን ለመቀጠል ከፈለግን እነሱ ወደ ወረዱበት ደረጃ መውረድ የለብንም።መስመራችን-እንዳንለቅቅ፤ድርጅታዊነታችን እንዳንስት። በበላይነት/ ከፍ ብለን ከታገልናቸው መስመራችን ሕይወት ያገኛል፤ ሁሌም ተሸናፊዎች ናቸው።ጠባብነት፤ወይንም ትምክሕትነት እኛ ውስጥ ማቆጥቆጥ ከጀመረ አደገኛ ነው። ያንን ማስጠጋት የለብንም።ነውር ነው። ከዚያ መራቅ አለብን። መስመራችን ከአፈጣጠሩ እንደተከተለው ኡኩልነትን ነው፤ እንከተል። ከማንም ነገድ ያለፈ ድርሻ አልጠየቅንም፤አልወሰድንም፤ አንወስድም። ሁሉም ሲያልፍለት እኛም ከሌሎቹ ኢትዮጵያ ሕዝቦች አብረን ከአማራው፤ከአሮሞው… እኩል እንድናድግ ነን የምንፈልገውና የምንታገለው። እኩል!
ሌላ ነገር ፈልገን አልታገልንም። በመጨረሻ የመለስ መንፈስ እንንከባከብ! የውድብ/የወያኔ/ መንፈስ እንንከባከብ! ነገሮችን ከፍ እንጂ ዝቅ አድርገን አንመልከት! ወደ ላይ እንውጣ! ወደ ታች አንውረድ! የመለስ መንፈስ ነው ለድል የሚያበቃን! መስመር ነው ሃይላችን! አሸናፊዎች ነን! አመሰግናለሁ!” }

በማለት ንግግሩን ከደመደመ በኋላ ‘አበበ አርአያ’ በተበለው እዚህ አሜሪካ አገር የሚኖሮው የድሮ የወያኔ ታጋይ “እምበር ተጋዳላይ” (እውን /አስደናቂ/ ታጋይ) የሚለውን ዘፈኑን በስሜት የሚጋልቡት በሺዎቹ የሚቆጠሩ አዲስ አበባ ውስጥ የሚኖሩ በሺዎች የሚቆጠሩ (እኔ እንዲህ ያለ የትግሬ የወጣት ብዛት መዲናዋ ውስጥ መኖሩ እጅግ አስገርሞኛል) የወያኔ ትግሬ ተከታዮች እና የወያኔ ወታደር ታጋይ ልጆች እና ዘመድ አዝማድ የወለዳቸው ወጣቶችን በማስጨፈር ለ26 አመት የግንቦት 7 የወያኔ መሳፍንቶች የንግሥና ዘመን የእንኳን አደራሳችሁ እና የቴድሮስ አድሓኖም የደስ አለህ ምረቃ አከባበር ተደመደመ።

እኔም የወያኔዎች የሽምቅ /አሽሙራዊ/ የቋንቋ ውርወራቸውን ተርጉሜ ለወገኖቼ ለናንተው ለማስነበብ ላበቃኝ አምላክ አመስግናለሁ። ሳምንት እንገናኝ።ትዝብቱ ለናንተ።ጨረስኩ!  ጌታቸው ረዳ (Editor Ethiopiaan Semay) getachre@aol.com






1 comment:

Unknown said...

ይህንን የፃፍኩት ሲሳይ ሕሸ ነኝ። እኔ እንኳ የፈለግኩትን የማለት ነፃነቴ ማንም እንዲሰጠኝና እንዲነፍገኝ አልፈቅድም። በዚህ ፅሁፍ ዙሪያ ያስገረመኝ ግን የዛሬ አራት ዓመት የወጣውን ለኢትዮጵያ አርበኞችና ሁሉም ጀግኖች ማሞገሻ ዘፈን ማንነቱ የማላውቀው ሰው ከዶክተር ቴዎድሮስ ድል ጋር mix አድርጎ ተጠቀመበት እንጂ እኔ ለዶክተር ቴዎድሮስ የገጠምኩላቸውም ሆነ ያዜምኩላቸው ዘፈን የለም። ለዶክተሩ ያለኝ ከበሬታ እንደተጠበቀ ሆኖ እኔ ብሳሳትም እንኳ በስልጣንና በሃብት ላይ ላለ ሰው አልዘፍንም። እንደዛ ማድረግ ሰው አምላኪነትን ስለሚያስከትል እንጂ መሞገስ ያለበትን ላለማሞገስ ፈልጌ አይደለም። የኔ ግጥምና ዜማ ለሃገሬ ከራስ ካሳር እስከ ራስ ዱሜራ ከጎዴ እስከ ኣኮቦ ለተሰዉላት ሰማዕታት እንጂ ለተከበሩት ዶክተር ቴዎድሮስ ያዜምኩት አይደለም። የዛሬ አራት ዓመት ጀምሮ ያለ ነው። ግጥሙ በደንብ ለሰማውም ከሳቸው ታሪክና ማንነት ጋር ምንም ዓይነት ግንኙነት የለውም። ፀሃፊው የተገደበ ዕውቀትና ካለምንም ማስረጃ የሚናገሩ ስለሆኑ ብዙም ባይገርመኝም እሳቸው በራሳቸው ጠባብ ዓለም ውስጥ ስለሚኖሩ ሁሉም እንደሳቸው ጠባብ አመለካከት ያለው ስለሚመስላቸው ነው እንዲህ ያለ ያልተገራ ልሳናቸውን የለቀቁት። እኔ ለአንድ ሰከንድም ቢሆን ትግራይ መሆንን እንጂ ሌላ መሆንን መርጬም ተመኝቼም አላውቅም። የኢትዮጵያዊነት ትልቁ ስዕል የሚጀምረው ከራሴ ማንነት ስለሆነ ነው። ለማንኛውም የሳቸው መፅሃፍም አንብቤዋለሁ። ከዚያ ውስጥ የሚስማማኝ ሊኖር ይችላል የማይስማማኝም ሊኖር ይችላል። በጥላቻ ላይና ራሳቸውን አግዝፈው ከማየት አባዜ ጋር ተያይዞ ሰለሚኣቀረሻቸው እሱን የመጥረግ ስራ የራሳቸው እንጂ የኔ ሊሂን የሚችልበት ሎጂክ የለም። እየተነሱ ሰውን ከፍ ዝቅ የሚያደርጉበት የራሳቸው ድረ ገፅ ስላላቸው ብቻ ያሻቸውን ለጊዜው ቢፅፉም ቀኑ ሲደርስ ግን በህግ የሚጠየቁበት መድረክ መኖሩንም ቢያስቡ መልካም ነበር። ለማንኛውም የስንቱን ታላላቅ ኢትዮጵያውያንን ስም በግብታዊነት እየተነሱ ባጎደፉበት ልሳናቸው እኔንም ለማሳነስ መሞከራቸው አይገርመኝም።
ላሁኑ ስህተታቸው ግን ልቦና ካላቸው አንባቢዎቻቸውን ይቅርታ ቢጠይቁበት መልካም ነው።