Sunday, July 1, 2018

የዲሲ ግበረሃይል ዱርየዎች በአሜሪካ ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay)


የዲሲ ግበረሃይል ዱርየዎች በአሜሪካ
ታቸው ረዳ (Ethiopian Semay)This fellow is the DC Gibrehayl gangster
ዲሲ ግበረሃይል እየተባለ የሚጠራ የሆነ ተቃዋሚ ክፍል እንዳለ በተለያዩ ዜናዎች አደምጥ ነበር። ይህ ሃይል ማን እንዳደራጀው ማንስ እንደሚመራው የማውቀው ነገር ባይኖርም፤ በቪዲዮ እየተቀረጹ ከዋሺንግተን ዲሲ ሲተላለፉ የነበሩት በተለያዩ ዜናዎችና ወቅቶች ያየናቸው የማውቃቸው አንዳንድ ሰዎች አይቻለሁ። ባለፉት ጊዜያት በዚህ ግብረሃይል ስም ሚጠራ በዜና ያየሁት ሰው የኢሕአፓ ራዲዮ ተነጋሪ /አዘጋጅ የነበረ (አሁንም ያለ ይመስለኛል) ዮሃንስ የተባለ ቃለ መጠይቅ ሲደረግለት በተለያዩ ጊዜያት አይቸዋለሁ። አንዳንዶቹ ደግሞ የግንቦት 7 አባላት አሉበት ይባላል (በመልክ አላውቃቸውም)

ማንም ይሁን ማን ያደራጀው ይህ የዲሲ ግብረሃይል የተባለ (ይህ ትችት የማይመለከተው ሌላ ቡድን ከሌለ በቀር) ይህ ቡድን ባለፈው ሰሞን/ አብይ አሕመድን ወደ ዲሲ ለመጋበዝ ቅድመ ዝግጅት ለማድረግተብሎ በዚህቡድን የተዘጋጀ ይመስለኛል” (ካልተሳሳትኩ) በተጠራው ስብሰባ አዳራሽ ውስጥ / ፍስሐ እሸቱ የተባሉት ኢትዮጵያዊ ዜጋ ከተቀመጡበት ወንበር ድረስ በመሄድሁለት ሰዎች ከጀርባ እና ከጎንሆነው (በስተጀርባ ጎን ቆሞ የነበረው ፀበኛ መልኩ አይታይም ሁለተኛው ከዶ/ ፍስሓ ወደ ግራ ተቀምጦ እጁን ከዶክተሩ አንገት በማጅራት በኩል አዙሮ በመጠጋት ሲያስጨንቃቸው የነበረው እጅግአግረሲቭ” (ፀበኛ) የሆነው መልኩ በደምብ ማየት የሚቻል ሞገደኛው ወጣት ዶክተሩን ከብበውበማገትእየሰደቡ የተረጋጋውን መንፈሳቸውን ሲያስጨነቁ ሲዘልፏቸው፤ሲያስፈራርዋቸው በቪዲዮ ተቀድቶ ለመላ ኢትዮጵያ ሕዝብ የተላለፈው ከሕግ ውጭ የሆነ የሚያበሳጭ፤ የሚያሳዝን እና የሕግ ሞራል የሚፈታተን፤ አንጀት የሚበላ ኢትዮጵያዊ ሰብአዊነታችንን የሚፈታተን አሳዛኝ ክስተት እንድናይ ተደርጓል።

 ይግረማችሁ ብሎ ይህ ሞገደኛ ወጣትየድፍረቱ እና የንቀቱ ብዛትይህ የዱርየነት ወንጀልእንደ ጀግንነት ቆጥሮትቪዲዮውን ያሰራጨው ደግሞ ከዚህ በታች ያለው ቪዲዮው ውስጥ የሚታየው ከሞገደኞቹ አንዱ እና ዋነኛውሞገደኛውወጣት ነው።


ሁለቱን ቪዲዮዎች ተመልክቱዋቸው። የመጀመርያው ቪዲዮ ዶክተሩን ከብበው ሲያስጨንቁት የሚያሳይ ቪዲዮ ሲሆን ፤ሁለተኛው ቪዲዮ ደግሞ እራሱ ሞገደኛው ወጣት (ጋንጉ) ስለ ግብረሃይሉ መግለጫ እያብራራ የሚያሳይ ነው። በዛው ቪዲዮ ዶክተሩንበቁጥጥር ስር” (አብዳክት) በማድረግ ለምን እንዲያስጨንቅዋቸው እና እንዲያስፈራርዋቸው  ምክንያት ሲያብራራየዲሲ ግበረሀይል ሙሉ መግለጫበሚል በቪዲዮ ቀርጾ ሞገደኛው ወጣት ለረዢም ደቂቃዎች የሚያብራራበት ቪዲዮ ነው።

ሰበር ዜና የዲሲ ግብረ ሀይል / ፍሰሀን በቁጥጥር ስር አውሎ አናገራቸውከዶ/ ፍሰሀ ጋር ያለው ፀብ ምንድነው የዲሲ ግብረሀይ ሙሉ መግለጫ ያስረዳልእንዲህ ያለ ነውርነት የወያኔ ማጅራት መቺዎች ከፈጸሙት የባሰ ነው። ያውም በሰለጠነው ዓለም፤ ለሰላም ህይወት ለምኖ፤ “መንግሰቴን በሰላም አላኖር አለኝ ተብሎ ማመለክቻ አቅርቦ” እባካችሁ አስጠጉኝ ተብሎ አሜሪካኖችን ተማጽኖ፤ በስደተኛነት ተመዝግቦ እኮ ነው ይህ ሁሉ ሞገደኛነት ዲሲ ውስጥ እያን ያለነው።

 በፖለቲካ እያሳበቡ ዜጎችን የሚያስፈራሩ ፤ የሚደበድቡ የሚገድሉ የሚያሸብሩ ግለሰቦች ፖለቲካውን እየተንተራሱ ዜጎችን የሚያስፈራሩ እና የሚያስጨንቁ ሕግ እንዲጎበኛቸው ማድረግ ተገቢ መሆኑን ከመነጋገራችን በፊት እነኚህ መጎደኞች ዶክተሩን “በቁጥጥር ስር (አብዳክት) ለማድረግ ምክንያታቸው ሲገልጽ በቪዲዮው ላይ የተዘገበው ግልጽ ነው። “ለምንድ ነው አንተ አንዳርጋቸው ፅጌ ከእስር እንዲፈታ ያልጠየቅከው…..” የሚል ነው። በጣም አስገራሚ ነው! አንዳርጋቸው ጽጌ እንዲፈታ ድምጽ ስላለሰሙ ዶከተሩ በነዚህ ጋንጎች “ቊጥጥር ስር” እንዲውሉ ተደርጓል። ለተወሰነ ጊዜ አስረዋቸዋል ማለት ነው። ብዙ ሰዎች ይህ ሞገደኛ ሰውየ የግንቦት 7 ኣባል እና ዲሲ ውስጥ ካሁን በፊት በተለያዩ ምክንያቶች ሰዎችን በማወክ የሚታወቅ ሆኖ ሌላም ጉድ ሰርቶ ሕግ ፊት እንደነበረ ይነገራል።

የሚገርመው ነገር ደግሞ ይህ ወጣት አንገቱ ላይ ያንጠለጠለው የክርሰቶስ የሰላም መስቀል ነው። ያ ብቻ እንዳይመስላችሁ፤ የዘውድ መንግሥት ሥርዓት ማሕተም እና ምልክት የነበረው የኢትዮጵያ ሰንደቃላማ በመስቀል ምልክት የተሸከመ አንበሳ መስቀል ምስል ያለበት የባሕል ልብስ የለበሰ ወጣት ነው። አንዲህ ያሉ የሰላም ምልክቶች ለብሰው ሰላማዊ ዜጎች በፖለቲካ እያሳበቡ ልክ እንደማጅራት መቺ በቀን ጸሓይ ሕዝብ በተሰበሰበበት አዳራሽ ውስጥ የፈለገው የፖለቲካ ልዩነት ዶክተሩ ቢይዙም “በቊጥጥር አሰረው/አግተው/ በአካል እና በመንፈስ ለጥቂት ጊዘያት አንዳይንቀሳቀሱ አስሮ ግራ እና ቀኝ ከለብበው ዜጋን ማገት ከፍተኛ የሕግ ጥሰት እና የሚያስጠይቅ ነው። ሕግ ቦታ ሰርቻለሁ። ሕጉን ስለማውቀው። ለመሆኑ የሕግ ባለሞያዎች ምን እያደረጋችሁ ነው? አያገባንም ልትሉ? ስራችሁ ስለማትሰሩ እኮ ነው ይህ ሁሉ የወያኔ  ገራፊ  ዘራፊና ሞገደኛ የነበረ ሁሉ እኛ ጋር እየኖረ እየናቀን ያለው።

እኔ ያበሳጨኝ አብዳክት (በቊጥጥር ስር ) ያደረጉዋቸው ሞገደኞቹን (ጋንጎችን) አይደለም ትኩረቴ፤ እኔ ቅር ያለኝ እነ ግርማ ሰይፉ የተባሉ እና የአዳራሹ አስተናጋጆች እና ለዜጎች ጸጥታ ሓላፊነት የወሰዱ አዘጋጆች ያሳዩት እጅግ አሳፋሪ  ትዕይንት ነው።

በቪዲዮው “ስክሪን ሻት” የተወሰደው ከታች እንደትመለከቱት ምስል የወያኔ ፓርላማ አባል ‘ግርማ ሰይፉ” ነው። ስለ ግርማ ልተች አይደለም; ስለ እሱ ሌላ ጊዜ መተቸት እችላለሁ። እዚህ ላይ የሚታየው ግርማ ሰይፉ እና ሌሎች ፖሊስ ጠርተው ሞገደኛውን ከማሳሰር ይልቅ (ሰለማዊ ተጋባዥ እንግዳ ሳያስበው በመጎደኞች ኣብዳክት (በቁጥጥር) በመደረጉ /ሰላማዊ ታዳሚ በሞገደኛ ወጣቶች ቁጥጥር ስር በመዋሉ) ሞገደኞችን ሲያሽሞነሙኑ ሲያባብሉት ይታያሉ።
Girma Seyfu and others comforting  the gang
አንድ ዜጋ በሞገደኞች ሲታገት ወደ ፖሊስ ማቅረብ ‘ስልክ ደውሎ’ ማስያዝ ፤ ቢያንስ ሞገደኛውን ከአዳራሹ ማስወገድ የአዘጋጆች እና የዜጎች ግዴታ አይደለም ወይ? ያውም እኮ “ለጠ/ሚ አብይ አሕመድ የሰላም የፍቅር መስተንግዶ ለማድረግ እየተከናወነ ባለበት የፍቅር (?) አዳረሽ ውስጥ እኮ ነው እኚህ ዜጋ በሕዝብ ፊት ‘በፓብሊክ’ በቪዲዮ እየተቀረጸ ሊታገቱ የቻሉት!

እንዲህ ያሉ ሞገደኞች በሕዝባዊ አዳራሾች ዜጎች ‘ማገት’ (አብዳክት) ማድረግ ከቻሉ ይህንን ስጋት በማየት ተጋባዦች መኪናቸው ውስጥ መሳርያ ይዘው በመምጣት አጋቾቻቸውን ጠብቀው ሲወጡ መግደል ሊጀመር ነው ማለት ነው። ያኔ ታጋቾቹ ግድያ ስለፈጸሙ ፖሊስ እንዲጠራ ይደረጋል። ሰው ሲገደል ፖሊስ መጥራት ሰው ሲታገት ግን ፖሊስ ከመጥራት ይልቅ ወይንም ሞገደኛውን አንቆ ከማስወጣት ይልቅ ‘አጋቾችን’ ማሽሞንመን፤ማባበል ፍጹም ከሞራልም ከሰብአዊነትም ከዜግነትም ከሃይማኖትም እጅግ የሚጣረስ ነው።

ዶክተር ፍስሃ እሸቱ በፖለቲካ መስመራቸው አልደግፋቸውም። ስለ እሳቸው አቁዋም ካሁን በፊት በምሬት ተቺቻቸዋለሁ። ሆኖም ሰብአዊ እና ዜግነታዊ ሰላመዊ እና አካላዊ መብታቸው በሞገደኞች ሲረበሽ ቆሜ የማይበት ስብእና የለኝም። ወገኖች ቪዲዮውን አይታችሁታል? ደጋግማችሁ እስቲ እዩት? የአዳራሹ “ፔቲ ቡርዣ” ታዳሚ ሁሉ ቁጭ ብሎ ይህንን “የማገት ትዕይንት” (አብዳክሽን) ተረጋግተው ተዝናንተው ተቀምጠው እያያ ‘ዶክተሩ በነዚህ ጋጠ ወጦች ሲጨነቁ ስድቡ ማስፈራሪያው ማገቱ ሁሉ ‘በትዕግስት’ ተቀብለው ሲጨነቁ’ አይቼ  ለጀመሪያ ጊዜ እምባየ በብስጭት አቅርሬለሁ። ሰው በብስጨት ተነሳስቶ ሰውን በሽጉጥ ጀሮ ግንዱን የሚያነድደው እኮ እንደዚህ ያለ ክብርን የሚዳፈር ጋጠ ወጥ ፍጡራን ሲተናኮሉ ነው።  እንዴት ዜጎች ይህንን ተመለክተው ጋጠወጦቹን ለሕግ አያቀርብም?    

ሞገዶኞቹ እንኳ “ሰበር ዜና ብለውታል” ተዳሚው እና መነኛ አዘጋጆቹ ግን እንደ ዜና ቀርቶ ምንም አንዳልተፈጸመ አልፈውታል። የሚገርመው ደግሞ የቪ ኦኤ ተብየው ሁለት ወይንም ሦስት ጋዜጠኞች እዛው ወስጥ ተቀምጠዋል። ጉድ እኮ ነው። ሞገደኛው እራሱ  የዲሲ ግብረ ሀይል / ፍሰሀን በቁጥጥር ስር አውሎ አናገራቸው” ብሎ ዜና ሲያሰራጭ ጋዜጠኞቹ ግን ጀሮ ዳባ ነበር የሉት። “አበዳክሽን” እኮ ነው! የዲሲ ግብረ ሀይል / ፍሰሀን በቁጥጥር ስር አውሎ አናገራቸው እኮ ነው ዜናው! እንዴት አንድ የሰው ልጅ ኢትዮጵያዊ ምሁር ቀርቶ  ድመት እና ውሻ ‘የእንሰሳዎች” ክብር በሚከበርበት አገር ውስጥ በሕዝብ ፊት በሞገደኞች ታግቶ ቁጥጥር ስር ሲውል፤  እንዲህ ያለ የክብር መዳፈር ሲገጥመው የአዳራሹ ሞገደኞች እና አዘጋጆች ፖሊስ ከመጥራት ይልቅ እያባባሉ ማሽሞንሞን ምን ይባላል? ውጭ አገር ያለው ፖለቲካ እና ተከታይ ወዴት እየተጓዘ ነው? በፖለቲካ ያልተስማማህን በአካል ማስፈራራት፤ መደብደብ፤ ማገት? ለምን?

የሚገርመው ደግሞ ሞገደኛው የሰላም የፍቅር ምልክት የሆነው የእየሱስ ክርስቶስ የክርስትያን መስቀል አንገቱ ላይ አንጥለጥሏል እኮ! ይህ ፖለቲካ አይደለም ፡ የማጅራት መቺ ባሕሪ ነው። ሰውን ማገት፤ በቁጥጥር ስር ማድረግ ይቅር የማይባል ነው።

ጌታቸው ረዳ getachre@aol.com (ኢትዮጵያን ሰማይ)