Monday, January 29, 2018

“ኤች አይ ቪ ኤድስ እንድያዝ የተፈፀመብኝ ተንኮል” (ኢትዮጵያዊው ሻምበል አስረስ ብዙነህ) የሚለው እና ሰውን አልገድልም ስላልኩኝ ደሜን በቫይረስ በከሉት- የሚለው ኤርትራዊው ደ/ር ንስረዲን መንሱር ታሪክ (Ethiopian Semay)



ኤች አይ ኤድስ እንድያዝ የተፈፀመብኝ ተንኮል(ኢትዮጵያዊው ሻምበል አስረስ ብዙነህ) የሚለው እና ሰውን አልገድልም ስላልኩኝ ደሜን በቫይረስ በከሉት- የሚለው ኤርትራዊው ደ/ር ንስረዲን መንሱር ታሪክ (Ethiopian Semay)


 An Ethiopian army officer Captain Asres Bezunh accused TPLF government of Ethiopia for infected him with the deadly HIV virus while admitted in hospital after wounded in the Badme battle against Eritrea. ሻምበል አስረስ ብዙነህ_ ጎጃሜው)
Dr.Nesredin Mensure accusing the Eritrean regime for infecting him with HIV virus after refusing the order of the government to kill a wanted pry of  the government by injecting the person with HIV virus or by the deadly formalin poison.
 የትህነግ/ህወሓት መከላከያ ውስጥ የተሰራ ዘግናኝ ወንጀል፣ የሻምበሉ አሳዛኝ ታሪክ
ከአፋር ወደ ሽራሮና ወደ ሌሎች ግምባሮች በመጓዝ ብዙ ውጤታማ ስራዎችን ሰርቻለሁ። 1992 ዓም ከሻዕቢያ በተተኮሰ የከባድ መሳርያ ፍንጣሪ ቆሰልኩ። አብረውኝ የሚሰሩት አብዛኛዎቹ ሲቪሎች ስለነበሩ ደንግጠው ይመስለኛል፣ በወቅቱ እርዳታ አላደረጉልኝም። ደሜ ፈሶ አልቆ መናገር አልችልም ነበር። ራሴን ስቼ ነበር በፊልድ ሐኪሞች የተነሳሁት። ሐኪሞች አንስተው ወስደው ፊልድ ሆስፒታል ድንኳን ውስጥ አስተኙኝ።

አሁን አንባቢን የሚፈታተን የሕይወት እጣዬን ላካፍላችሁ። ……ለስልጣን ሲባል ምን ያህል ለህሊና የሚቀፍ ነገር እንደሚፈፀም አንባቢ ቢያውቀው ክፋት የለውም በሚል ነው የፃፍኩት።
በተፈጥሮዬ ማጎብደድ መጎናበስ አላውቅም። ……ስራየን ይህ ምስኪን ሕዝብ ከኪሱ አውጥቶ ለሚከፍለኝ ደመወዝ የተመጣጠነ ስራ ለመስራት እተጋለሁ።።ይህን የማደርገው በዚህ ዝብርቅርቅ አስተዳደር ነው። የምሰራው ከሚከፈለኝ ዋጋና አቅሜ በታች ከሆነም በራሴ ራሴን እከሳለሁ።

በዚህ ምክንያት የአንድ ሀገር ህዝቦች ሆነን፣በሀገር መከላከያ ውስጥ በቆየሁበት ጊዜ ከችሎታ ችሎታ፣ ከትምህርት ትምህርት፣ከአገልግሎት አገልግሎት የሌላቸው ሰዎችምርጥ ዘርበመሆናቸው ብቻ ያለ አቅማቸው ከአቅማቸው በላይ ዋጋ ሲከፈላቸው፣ በአንፃሩ ደግሞ በቂ የስራ ችሎታ በቂ የትምህርት ዝግጅት እና በርካታ አመት የስራ ልምድ ያላቸው ዜጎች ከእውቀታቸውና ከስራቸው ጋር የማይጣጣምና የማይመጣጠን ዋጋ ሲከፈላቸው ሳይ፣ቦታው ህይወት የሚያስከፍል ቢሆንም በድፍረት ተቃውሞዬን በመግለፅ እዳፈር ነበር።

በጠቅላላው የኢህአዴግ የመከላከያ ሠራዊት ቤት ጥቅምና የተሟላ ኑሮ ወደ አንድ ወገን እያደላ ሲሄድ በጣም አዝን ነበር። እኔ መፍትሄ አመጣ ይመስል አላስችል እያለኝ ፊት ለፊት ከማይነቃነቅ ድንጋይ ጋር በተደጋጋሚ ተጋጭቻለሁ። ለእውነት መቆሜ ብዙ አስከፍሎኛል።

ይሄው ባህሪዬ በመንግስቱ ኃይለማርያም መዳፍ ውስጥ ሊያስጨፈልቀኝ ነበር። ደግነቱ ቀድሜ ሸሽቻለሁ። ምን ያደርጋል፣ እድሜ ልኩን በቁም መግደል ከሚችልበት የህወሓት/ኢህአዴግ መዳፍ ውስጥ ወድቄያለሁ። ጨካኝ ካድሬዎች 1992 በሻዕቢያ ጥይት ቆስዬ ሆስፒታል ተኝቼ ሳለ፣ በተፈጠረ አጋጣሚ በየጊዜው እየተሟገተች የተዳፈረቻቸውን ምላሴን ፀጥ ለማድረግ፣ በበሽታ እንድመረዝ አደረጉ።

ዘመኑ እጅግ በተራቀቀበት ወቅት አንድ በኤች አይ ታሞ አጠገቤ ከተኛ የአስር አለቃ (የአድዋ ልጅ ነው) የደህንነት ሰራተኛ የተወጋበትን መርፌ እንስት ሀኪም ተብየዋ ረዳት ተጋደልቲ ወጋችኝ። በወቅቱ መንቀሳቀስ አልችልምና እዚያው በተኛሁበትእሪብዬ ጮህኩ። ወዲያውኑ የዋርዱ ኃላፊ ዶክተር ሳምሶን የሚባል ሲቪል ወጣት መጥቶምን ሆንክ?” ብሎ ሲጠይቀኝ፣እንዴት በሌላ ሰው መርፌ ትወጋኛለች? መርፌ ደግሞ እየቀቀሉ መጠቀም እንኳ ድሮ ቀርቷል……” እያልኩ ጮህኩ።

ይች ተጋደልቲ ሐኪም በድንገት የተሳሳተች ለመምሰል ከወዲያ ወዲህ ትሯሯጣለች አንባቢያን ሊረዳልኝ የምፈልገው በመጀመሪያ እኔ መኮንን ነኝ። አጠገቤ የተኛው ደግሞ አስር አለቃ ነው። በወታደራዊ ህግ በኩል አስር አለቃው መኮንኖች ዋርድ የመተኛት መብት የለውም። ሆን ተብሎ በእቅድ የተሰራ ነበር።

ዶክተር እንዴት እንዲህ ይደረጋል?” ብየ አለቀስኩበት። ዶክተሩ የታዘዘውን መስራት እንጅ ምንም ሥልጣን እንደሌለው እናውቃለን። በተራ ተጋዳልቲ እየታዘዘ ነው የሚሰራው። እናም የተወጋሁትን ታፋዬን በአልኮል እያጠበአይዞህ ምንም አይደል!” እያለ ሊያፅናናኝ ሞከረ። በጣም ማዘኑ ከፊቱ ያስታውቃል። ከዶክተሩ ጋር የምትሰራዋ ሌላኛዋ ሲቪል ነርስም በጣም እያዘነች ነበር። እራሷን እያረጋጋችለማንኛውም ከወር በኋላ ቸክ አድርግ!”አለችኝ። ይህች ነርስ ዛሬም በህይወት አለች። ዶክተሩን ግን ከዚያች ጊዜ በኋላ አላየሁትም። የት እንዳለም አላውቅም።
አጠገቤ ተኝቶ የነበረው አስር አለቃ ደህንነት አይኔ እያየ አጠገቤ ሞተ። ከዚህ በኋላማ ለደቂቃም አእምሮዬ ሊያርፍ አልቻለም። ውስጤ በፍርሃት እየራደ አለቀ። ነርሷ እንደመከረችኝ በወሩ ስመረመርያጠራጥራልተባለ። ቁስሌ ሲያገግም ከትግራይ ወደ አዲስ አበባ ጦር ኃይሎች ሆስፒታል ተላኩ። በሁለተኛው ወር አዲስ አበባ ስመረመርፖዘቲቭመሆኔ ተነገረኝ። ይህ ውጤት ሲነገረኝ አራት ቀን ምግብ አልበላሁም። እንቅልፍ የሚባል በአይኔ አልዞር አለ። ኒሞኒያው፣ቲቪው፣ አልማዝ ባለጭራው፣ ጉንፋኑምኑን ልንገራችሁ? በሽታ ሁሉ እንደ ንብ መንጋ የሰፈረብኝ መሰለኝ። ከሆስፒታል ወጥቼ ቤቴን ትቼ ጃንሜዳ ሜዳው ላይ 3 ቀን ዋልኩ። አደርኩ። 3ኛው ቀን ቤተሰብ ፈልጎ አገኘኝና በስንት ልመና ወደ ቤቴ ገባሁ።

ከመስርያ ቤት የስራ ስንብት ጠየኩ። ማመልከቻዬ ታይቶ ሳይፈቀድልኝ ቀረ። ያልተፈቀደልኝ ደግሞ ለኔ ታስቦ ወይም ስለምጠቅማቸው አይደለም። ከእነሱ ስላልመጣ ነው። እናም በህክምና ምክንያት ብዙ ጉዳት ደረሶብኝ ይኸው ከሞትኩ ቆየሁ።
(ታሪኩ ሻምበሉ ከፃፉት የካድሬው ማስታወሻ መፅሐፍ ላይ የተወሰደ ነው
(ሕትመት ኢትዮጵያን ሰማይ- ምንጭ ወልቃይት.ካም)

የኤርትራዊው ዶ/ር ንስረዲን ታሪክ (ባጭሩ) ትርጉም ጌታቸው ረዳ (ኢትዮጵያን ሰማይ)

ካሁን በፊት ዶ/ር ንስረዲን መንሱር የተባለ ወጣት ኤርትራዊ ሓኪም፤ በኤርትራ ባለሥልጣኖች ትዕዛዝ ስርዓቱን የሚቃወሙ  “አላይ” የተባለ የናጠጠ ቱጃር/ሃብታም/ ኤርትራዊ ነጋዴ ታስሮ ሆስፒታል ለሕክምና መጥቶ ተኝቶ ስለነበር፤  በኤች አይ ቪ ቫይረስ መርፌ ወግቶ እንዲገድለው ሲታዘዝ፤ እኔ ሰውን ለማዳን እንጂ ለመግደል ቃል ኪዳን አልገባሁም’ ብሎ እምቢ ስላለ፤ ሁለት ወር ሃሳቡን እንዲለውጥ ጊዜ ቢሰጡትም ‘አምቢ ስላለ”፡ እሺ እስኪል ድረስ ከሆስፒታሉ ርቀት አንዳይወጣ ተደረገ።በመጨረሻም “አላይ” የተባለው (እንዲገደል የተፈለገው ሰውየ) እንዲገድለው እየወተወቱት ስለሆነ፤ ‘ሚስጢሩን ነግሮት’ ‘ነብሱን” ማዳን አንዳለበት እና ከሆስፒታሉ ማምለጥ እንዳለበት ዶክተሩም አስቀድሞ ነግሮት ስለነበር፡ አላይም ጠባቂዎቹን በገንዘብ አታልሎም ይሁን በሆነ ምክንያት ‘አላይ’ በእህቱ ተባባሪነት በከረን አድርጎ ኤርትራን ለቆ ወጣ። ከዚያም ሚኬኤለ የተባለ የጸጥታ ጠባቂ ሁለት ወር ሙሉ እየተመላለሰ ዶከተር ንስረዲንን የመግደል ‘ትብብሩን’ እንዲያሳይ ቢጠይቀውም ፤ መጨረሻ በእምቢታው ስለጸና ‘ተፈለጊውም’ “ከሆስፒታሉ” አምልጦ በመሄዱ “ሚኬአለ” የተባለ የጸጥታ ባልደረባ ከሌሎች ደብዳቢ ባልደረቦቹን ይዞ ወደ ሆስፒታሉ በመምጣት “ዶ/ር ንስረዲንን” በድንገት ተረባርበው አንቀው እጆቹን ጠምዝዘው ‘በብርተ ሰንሰለት’ በማሰር ክንዶቹን ሰባብረው እንዳይላወስ በማድረግ ደብድበውት ‘ህይወቱ ስቶ’ <<ኮማ>> አስገብተው እር ቤት ውስደው ሕይቱ ከሳተ በሗላ እንደገና ደ’ር ንስረዲን ወደ እሚሰራበት “ሓሊበት” ወደ ተባለው ሆዝፒታል ወስደው “ጓል ወልዳይ” በተባለች ነርስ እና ሌሎቹ በመተባባር “የኤች አይ ቪ መርፌ” ወግተውት “አይ-ቪ” Intravenous Infusion (በደም ስር የሚሰጥ ጉልበትና የሰውነት ፈሳሽ መጠን የሚጠብቅ ፈሳሽ) ክንዱ ላይ ተተክሎበት ከእንቅልፉ ሲባንን “አልጋ ላይ ተኝቶ ባልጠበቀው ሁኔታ ሆኖ እራሱን አገኘው።” ከ2013 እስከ 2016 ታስሮ ከጊዜ በሗላ ላብ እና ድካም እየወረረው ጤናው ጉልበቱ እየዛለ ሄዶ ከእስር ወጥቶ ሕክምና ስራው እንዲሰራ ከተለቀቀ በሗላ፤ ጓደኛው ደ/ር በረከት ጋር ሓሊበት ሆስፒታል ስራቸውን ቀጥለው የጠበቀ ወዳጅነት እና አብረውም ሰራተኛ ቀጥረው ስለሚኖሩ፤ ደ/ር በረኸት ንስረዲንን የ ኤች አይ ቪ ምርምራ እንዲያደረጉ ወተወተው። ለምን ብሎ ሲጠይቀው፤ ያው ከብዙ ሰው ጋር ስለምንሰራ ምርመራውን ለራሳችንም “የዘወትር” ልማድ ማድረግ አለብን ብሎ ነጉ በጎን አግባብቶ ምርመራው ሲያደርጉ፤ ደ/ር ንስረዲን እራሱ ምርመራውን በማካሄድ ፡ኤች ኣይ ቪ” ፖሲቲቭ- ሆኖ ውጡን አነበበው። ዶ/ር በረከት ምስጢሩን ስለሚያውቅ ፤እንዴት እንዲበከል እንደሆነ እና ማን መርፌው እንደወጋው ይህ ምስጢር ስለሚያውቅ ‘ከድንጋጤው አረጋግቶ” ታሪኩን ነግሮት <ጓል ወልዳይ- የወልዳይ ልጅ) የተባለች ነርስ መርፌ ወግታ አንድትበከል ስለታዘዘች “ኤች አይ ቪ” በሽተኛ ልትሆን የሆንከው በዚህ ምክንያት ነው። ብሎ ታሪኩን ነግሮት ሁለቱም ተመካክረው ወደ ውጭ አገር በእግር አምልጠው ኤርትራን ጥለው ደ/ር ንስረዲን በእግር አምልጦ ወደ ኢትዮጵያ በመግባት መጠለያ ተሰጥቶት ወጋሕታ ለተባለ ራዲዮ ቃለ መጠይቅ አድርጓል።ጓደኛው ዶ/ር አድሓኖም እንዲያለ ወንጀል እንዲፈጽም በኤርትራ ባለስልጣኖች እንደተገደደ እና እራሱንም አምልጦ ዛሬ “ጣሊያን” አገር እንዳለ ጓደኛው ተናግሯል።  ዶ/ር አድሓኖምና ዶ/ር ንስረዲን  አብረው በደቡብ አፍሪካ (ኬፕ ታውን) በዶክተሬት ሕክምና ተምረው ሁለቱም ወደ ኤርትራ ሄደው ሕዝብ ለመርዳት ተቀጥረው ሲሰሩ የቆዩ ናቸው።

በሌላ ዜናም፡ እንዲሁም ዶር ተስፋዓለም ባራኺ የታለ ሌላ ሓኪምም ‘ሰዎች’ ፎርማሊን ውሃ ውስጥ ተጨምሮ እንዲጠጡ በማድረግ ወይንም እንዲወጉ በማድረግ ደርቀው እንዲገኙ እየተደረገ መሆኑን ይህ ሃኪም ደግሞ ሌላ ታሪክ ይዞ ምስጢሮችን በራዲዮ ቃለ መጠይቅ አድርጓል። ስለዚህ ወያኔም ሆነ ሻዕቢያ በተቀናቃኞቻው እና ደስ በማይላቸው ሰው እንዲህ ያለ ወንጀል እየፈጸሙ መሆናቸው ስንመለከት እጅግ የሚያሳዝን ድርጊት ከመሆኑ በላይ፤ እነዚህን የሰው እንሰሳዎች ጋር ተጠግተው የሰው ልጅ ደህንነት ያመጣሉ፤ወይንም ስለ ጎረቤት ሕዝብ ደህንነት ይቆረቆራዩ ብለው የሚሞግቱን ሰዎች አዝንላቸዋለሁ። ለተጠቂዎች ጽናቱን ይስጣችሁ። አልገድለም ስላልኩኝ ደሜነን በቫይረስ በከሉት-የሚለው ትግርኛ ለምትሰሙ ታሪኩ በቪዲዮ ይኼው። በጣም የሚያሳዝነው ደግሞ ተጠቂዎች ሐዘናቸውን በእምባ ሲገልጹ “እሰየው” የሚሉ በጣም የሚገርሙ የሰው አራዊት የሆኑ “ካልቶች” አሉ።

ኣይቀትልን ስለዝበልኩዎም ደመይ ብቫይረስ በኪሎሞ- ዶክተር ነስረዲን መንሱር - ካልኣይ ክፋል

https://youtu.be/-j6BBnD3YQQ

 

አመሰግናለሁ፤
 ጌታቸው ረዳ