Tuesday, June 25, 2024

ትግሬዎች የተከተሉት የባሕል ለውጥና እየተከሰተ ያለው ወንጀል በትግራይ ጌታቸው ረዳ 6/25/24 Ethiopian Semay


ትግሬዎች የተከተሉት የባሕል ለውጥና እየተከሰተ ያለው ወንጀል በትግራይ

ታቸው ረዳ

6/25/24

Ethiopian Semay

ወንጀል በባህል ላይ ተጽእኖ ያሳድራል, ባህል ደግሞ በወንጀል ላይ ተጽዕኖ ያሳድራል የላሉ በወንጀል ጥናት ያደረጉ ምሁራን፡፡ ይህ ማለት ማሕበረሰቡ እንደሚከተለው የባሕል ዓይነት ፤ ያንድ “ማሕበረሰብ ደህንነት ጠባቂ” የሚሆነበት ወይንም ‘’የደህንነት አስጊ’’ ሆኖ የሚከሰትበት ወቅቶች አሉት ማለት ነው፡፡

እዚህ ላይ “ወቅት” ብየ የጠቀስኩት ልብ እንድትሉት የምፈልገው “ባሕል የማሕበረሰቡ ደህንነት ጠባቂ ሆኖ ለዘመናት ከቆየ በላ ፤ ባንድ ወቅት ፤ የባሕል ብረዛ (ለውጥ) ሲደረግበት፤ ያ ጠባቂ ባሕል (ነባር) በአዲስ አስጊ ባሕል ይተካና ማሕበረሰቡ ልክ ትግራይ ውስጥና ኦሮሞ አካባቢ እየታዩ እንዳሉት አሰቃቂ የወንጀል ከስተቶች ምክንያት ማሕበረሰቡ አዝጋሚ ወይንም ፈጣን ሥጋት ውስጥ ይገባል፡፡

ባለፈው ሰሞን ትግራይ ውስጥ መነጋገርያ ሆኖ የሰነበተው ያንዲት 12 አመት ያላት ታዳጊ ወጣት ታክሲ ሲያመላልሳት በነበረው ባንድ ጎረትዋ ጎረምሳ ወጣት ተጠልፋ ተገድላ ከተሰወረች በ3ኛው ወርዋ ሬሳዋ መገኘቱ ይታወሳል፡፡ በዚህም መላው ሕዝብ በሁታው መደናገጡና እንት ሊሆን ቻለ? የሚል ጠያ ሲጭር ሰንብል፡፡

ኢትዮጵያ ወስጥ በተለይም ሰኑ ክፍል አብዛኛው በጥንታዊው የክርስትና መጻሕፍትና ቁርአን መመሪያ የሚከተል ማሕበረሰብ ስለነበር ከንጉሡ (ክ1966 ዓብዮት) ሞትና ክ63 ምኒሰትሮቹ ርሸና ብላ ከዚያም ትግራይ ወስጥ የተከሰተው የ1967 የዳግማይ ወያ አብዮት ያሰክተለው የባሕል ለውጥ ማሕበረሰቡ በወንጀልና በሃገር ክሕደት እንዲዋኝ አድርጎታል፡፡

የካቶሊክ፤የፕሮተሰታንት፤ የኦረቶዶክስና እስልምና መሪዎች በሙሉ በወያ የፋሺስት ፖለቲካ አስተምህሮ (ዶክትሪን) የተቀኙ በመሆናቸው፤ ፈሪሃ ውያኔ እንጂ ፈሪሃ ፈጣሪ ሆኖ እንዳይቀረጽ ሆኖ ተሰብከዋል፡፡

አትግደል የሚለው የፈጣሪ መመሪያን በመጣስ መግደል እንደባሕል ተወስዶ ወንድም እህቱን ሲገድል የጀብድ ምልክት ሆኖ እንዲታይ ፤ ልጅ የአባቱን ገዳይ እያሞገሰ መቀ ከተማ አዳራሽ ሲነገር አውድዮውን አስደምጨአችሁ እንደነበርና የሃየማኖት መሪዎች ነን የሚሉ እዛው ተቀምጠው ልጁን በጭብጨባ ሲያጅቡት መኖራቸው ትችት መጻን አሰታወሳለሁ፡፡

ወያ ጫካ እያለና መንግሥት ከሆነ በኋላ ማሕበረሰቡ ድያና ሞት ቅቡል ሆኖ እናት 3 ልጆችዋን ወደ ጫካ ልካ እስዋም ተዋጊ ሆና ልጆችዋ በማለቃቸው ምንም ቅር እንደማይላትና እንደገና ቢወለዱ መልሳ ወደ ጦርነት እንደምትልካቸው በኩራት ስትናገር መስማት፤ ከምናውቀው የእናት ሆድ ቡቡነት እጅግ የተለየ የልጆቻቸውን ሞት ደጋግመው ቢያዩ ልዩ ኩራትና ደስታ እንደሚሰማቸው የሚገልጹ የትግራይ እናቶች በርካቶች ናቸው፡፡

እንዲሀ ያሉት እናቶችና አባቶች ሞት ኩራት መሆኑን የሚያመኑ “ኡር ፋሺዝም” (Ur Fascism) የሜከተል ማሕበረሰብ መሆኑን ካሁን በፊት  Ur Fascism ኡር ፋሺዝም  የወያኔ ታጋዮች እውነተኛ መገለጫ በሚል አንድ መጣጥፍ መለጠፌ የታወሳል፡፡

የኡር ፋሺዝም (Ur Fascism) ባሕሪ ምንነት የነገረን  ጣሊያናዊው “ኡምቤርቶ ኤኮ” ነው። በትርጉም ካልተሳሳትኩ “ኡር ፋሺዝም” ዘላለማዊ ሺዝም ማለት ይመስለኛል፡፡ አንግሊዞች cult of tradition የሚሉት።ኡምቤርቶ ኤኮ << ህይወት>>  ለኡር-ፋሺዝም <<የህይወት ትግል የለም>> ይልቁንም  << ህይወት ለትግል ነው የምትኖረው>> ይላል።

<< ህይወት ዘላቂ ጦርነት ስለሆነ በጸጋ ይቀበለዋል። ይህ ግን የአርማጌዶን ስብስቦችን ያመጣል ጠላቶች መሸነፍ ስላለባቸው የመጨረሻው ጦርነት ሊኖር ይገባል ስለሚል፤ በዛው ቦግ እልም እያለ ያልተቋረጠ የጸብና የጦርነት ጫሪነት እንቅስቃሴው ሂደት ዓለምን መቆጣጠር ወርቃማ ሰላምን ማምጣት ይቻላል የሚል ባህሪ አለው>> ይላል። ነገር ግን እንዲህ ያለው ሁሉንም ተቆጣጥሮ ሰላም የሚያመጣ ተስፈኝነት የተሳካለት ፋሽስት መሪ የለም>>

በማለት የኡር ፋሺዝም ባሕሪ ርቀት ይገልጽና መጽሐፉን ሳነበው፤ ከጠቀሳቸው የኡር ፋሺዝም 14 ባሕሪያቶች ውስጥ ቀልቤን የሳበው ከርዕሴ መግቢያ የለጠፍኩት በመጀመሪያው የ17 አመት የወያኔ የጫካ ጦርነት ዘመን “አማረ ታረቀ” የተባለ የወያኔ ታጋይ በውግያው ውስጥ ግራ እግሩ በከባድ የጥይት አሎሎ ተመትቶ ተቆርጦ በመውደቁ የተቆረጠው ቀኝ እግሩ አንስቶ ወደ ሰማይ በመቀሰር የሞት ብስራቱን በጸጋ በመቀበል ወዲያውኑ ህይወቱ አልፏል።   

እንዲህ ያለ ሞት ኡምቤርቶ ኤኮ አንዲህ ሲል ይገልጸዋል።

<< … በእንደዚህ ዓይነት አመለካከት ሁሉም ሰው ጀግና ለመሆን ይማራል በእያንዳንዱ አፈ ታሪክ ውስጥ ጀግና ልዩ ፍጡር ነው ነገር ግን በኡር-ፋሺስት ርዕዮተ ዓለም ውስጥ ጀግንነትብርቅ” አይደለም የተለመደ ነው ይህ የጀግንነት አምልኮከሞት አምልኮ” ጋር በጥብቅየተያያዘ” ነው። የፈላንግስቶች መሪ መፈክርቪቫ ሙርቴ” ("ሞት ለዘላለም ይኑር!") ይላሉ። ይህ የሞት አምልኮ ባሕሪ በአጋጣሚ አይደለም ፋሺስትባልሆኑ” ማህበረሰቦች ውስጥ ግን ምእመናንሞት ደስ የማይል” አንደሆነ ይነገራቸዋል። አማኞች ከተፈጥሮ በላይ የሆነ ደስታ ላይ ለመድረስአሳማሚው መንገድ” እንደሆነ ይነገራቸዋል። በአንፃሩ የኡር-ፋሽስት ጀግናየጀግንነት ሞትን” ይመኛል፣ ለጀግንነቱሞት”ምርጥ ሽልማት” ተብሎ ይታወጃል። የኡር-ፋሽስት ጀግናለመሞት ትዕግስት የለውም””። ትዕግስት በማጣቱምሌሎች ሰዎችን” ወደሞት” ይልካል። >>

በማለት የ ኡር ፋሺሰቶች “ ቪቫ ላ ሙርቴ” - "ሞት ለዘላለም ይኑር!" እያሉ የሞት ቅድስና በመስበክ በጦርነት ወቅት እኔ ልሙት እኔ ልሙት እየተሽቀዳደሙ ወደ ጦርነት እሳት በመግባት ይሰዋሉ። ይህ የኡር ፋሺዝም ከ14 ቱ ባሕርያቶች አንዱ ሞትን በቅድስና እንዴት እንደሚያመልኩት ስንመለከት የወያኔ እና የሻዕቢያ ተዋጊዎች ባሕርይ የ ኡር ፋሺዝም ባሕሪ እንደተላበሱ ከሚዘግብዋቸው የታሪክ ማሕደሮቻቸው ለማወቅ ችለናል።ለ ነው የትግራይ እናቶቸና አባቶች ልጆቻቸውን እና እራሳቸው ወያ በሚያደረግላቸው የሞት ጥሪ ሁሉ “ሞትን” የምርጥ ትግዎች ምርጥ ሽልማት” ነውና በቅድስና ተቀበለውት እነሆ <<ኡር ፋሺዝ>> ትግራይ ውስጥ ከነገሠ ወዲህ ሞገደኛ ማሕበረሰብ ተፈጥል፡፡ ሰለሆነም ወጣቱ በታነጸበት “ሞገደኛ ባሕል” ምክንያት ራሱን ወንጀል ፈጻሚና ጉዳተኛ ሆኖ የምናየው ለዚህ ነው፡፡

ባሕልና ሕግ  የኛን “ድምበር” (ባውንድሪ) ይወስናሉ፡፡ተፈጠሮ የራሰዋ ሕግ እንዳላት ሁሉ ማሕበረሰቦች የሚከተሉዋቸው ባሕሎችም ጎልተው የተሰመሩ የቆዩ  ሕጎች መጣስ ከጀመሩ፡ መጣስ የሌለባቸው የተሰመሩ ባሕላዊ ወሰኖች ከጣስን ዋጋ እንደሚያሰከትል ትግራይ ውስጥ ያለው ክስተት አመላካች ነው፡፡ ፋሺስቶች ይህንን ሃቅ አይቀበሉትም፡፡

ትግራይ ስትከተላቸውና ሰታከራቸው የነበሩ ሃይማኖቶች፤ ሕግ፤ አገርና ሰንደቅ አላማ፤ ክ1967 ጀመሮ ተንቀው ተጥለዋል፡፡ትግራይ ውስጥ አመጽ ቅቡል ሆኖ ፤ <<እያባረርክ ግደለው ያንን ሞኝ አማራ>>  ክሚለው አመጸኛ ዘመቻና ዘፈን ጀመሮ የራሱን ጎረትና አብሮ አደግ ወንድምና እህት በጥይት ወይንም በስለት አርዶ መግደል ንቡር ሆኖ “ኡር ፋሺዝም” ቁቡል ባሕል ከሆነ ወዲህ የማሕበረሰቡን ሰላምና ደህንነት የሚጠበቁባቸው ነባር ባሕሎች በፋሺስት ፖለቲካ ተተክተው አነሆ ትግራይም መላው ኢትዮዮጵያም “ባሕል በመታመሙ” ምከንያት ሕዝቡ ችግር ውሰጥ ይገኛል፡፡ አመታዊ በዓላትና ሃየማኖታዊ ስብሰባዎች

የሚሰበኩት ፡ ስለ “ግደለው አፍነው፤አንተ ሞት አይፈ ፤ ድንጋይ አናጋሪ ፤ ተራራን አንቀጥቃጭ ባለ ልዩ ዲ ” የሚሉ ዘፈኖችና መፈከሮች የምታስተጋባ ትግራይ ነኛ ልትሆን አትችልም፡፡ ሁም ሐዘንና ሞት ይከብዋታል፡፡

ትግራይ ውስጥ ተገደለች የተባለቺው የ12 አመት ታዳጊ ውጣት ብዙ ሰዎች እንት ወደዚህ አስነዋሪ የግድያና የእገታ ባሕል ገባን? ሲሉ ከጠየቁት ካሰገረመኝ አንዱ <<ንጠላና መከፋፈል፤ ጸብ ፤ ጠላቻ ፤ ሞትና አመጽ ቅቡል እንዲሆን ከሚቀሰቅሱ <<የፋሺስት ቀሳወስትና ጳጳሳት>> አንዱ “የትግራዩ አባ ሰረቀበሃን” ነው፡፡

“ይህ ነብሰ ዳይ ከየት ነው የተላለፈብን? እውነት የትግራይ ሰው ነው ይህንን ወንጀል የፈጸመው? እንት ወደዚህ ክስተት ገባን? እያለ ተገርሞ ተከታዮቹን ይጠይቃል፡፡

ትግራይ ውስጥ ሰረቀ ብሃን የሚያመልከው “ወያ” እነ አቶ ገዛኢ ረዳ እና የ ቤተሰብ የሆኑት አቶ ገብረሊባኖስ መዝገቦ የመሳሰሉ አረጋውያንን እስከ እነ ሕይወታቸው እሳት ወሰጥ እየጨመሩ እንዳላሰቃዩዋቸውና እንዳልገደልዋቸው፤ ሰረቀ ብሃን ያንን ወንጀል ሰመቶ እንዳልሰማ (ራስ መንገሻ ወንድ አይደለህም ብለው የካዱት) ከደጅ የተወለደ ኢሕጋዊ የሆነ የራሥ ሥዩም ልጅ አታኸልቲ ሥዩም መቀበሪያውን ጉድድ አሰቆፈርው ከነ ሕይወቱ  ጉደጋድ ውስጥ ገብቶ እንዲቀበር ያደረገ የአባ ሰረቀበረሃን ብቸኛ ሿሚ እና መሪ የሆነው የወያ ወንጀል ሸሸጎ ተከታዮቹን ሰብሰቦ ያችን ታዳጊ ህጻን የገደለ ለመሆኑ ትግራዋይ ነው? እኛ ውስጥ ነው የበቀለው? እውነት የኛ ሰው ነው? እያለ እጆቹን እያወራጨ ተከታዮቹን ሲጠይቅና የትግራይ ሰው ንጹህነት ሲመጻደቅ መስማት “ከአባ ሰረቀበሃን” የመሳሰሉ አመጽና ላቻ ሰባኪ ፋሺስቶች ሲነገር በመሰማ ብገረምም በዙም አልገረመኝም፤

 (Fascism had profound archaic roots. it represented the crude transformation of Christian doctrine into slogans of political violence) (Theodor Adorno- Anti Semitism and Fascist Propaganda- (A Brief history of Fascist lies (Federico Finchelstein p/88)

<<(አመጽን አሰመለከቶ)ፋሺዝም ጥልቅ የሰደደ ነባር ሥር አለው፡፡ ነጹሁን የክርስትና አስተምህሮ ወደ ፖለቲካዊ መፈክሮች በመቀየር የፖለቲካ አመጽ ያበረታታል፡፡>> (A Brief history of Fascist lies (Federico Finchelstein p/88) ከሚለው መጽሐፍ ለዚህ ረስ ስዘጋጅ ሰሞኑን ካነበብኩት መጽሐፍ፡፡

 ትግራይ ውስጥ የምናየው አምጽ ማሕበርሰቡ የፋሺስት ተከታይ ሰለሆነ አመጽ በመለመዱ ሐዘን በመከሰቱ ለሳምንት ያጉረመርምና ክዚያ ወደ ወትሮው ይመለሳል፡፡ የትግራይ ወጣቶች በሙሉ በሚያስብል አሃዝ የፋሺስት ታጋዮች ናቸው፡፤ ለወያኔ መሪዎችና ባንራ ይሰዋሉ ፤ ተሰወተዋልም፡፡ ዛሬም  በኩራት ፤ ለመሞት ትዕግስት የላቸውም”። ሌሎች ሰዎችን በመረሸንም ሆነ ወደ ሞት ለመላክ ግድ የሌላቸው ገራፊዎችና ጨካኞች በብዛት የተበራከቱበት አክባቢ ነው፡፡

 በሁለመናዊ መልካቸው ከኡር ፋሺዝም ገንዳ የተቀዱት የትግራይ ወጣቶችና ምሁራኖቻቸው ሞትን ቅዱስ ባሕል አድርገው አሁንም እገፉበት ነው፡፡ ሞትን በማቆለጳጰስ “መስዋእት” ሉታል፡፡ ይክሩበታል፤ የጨፈሩበታል ፤ ይደሰቱበታል፡፡ ሰውን ድብድቦ አሰቃይቶ ገድሎ ቆሻሻ መጣያ ላይ መጣል በአመጽ ተወለዶ በአምጽ ያደገ ወጣት ሰለሆ መግደልና መሞት ምኑም ማለት አየደለም፡፡

ሞት ተወዳሽ በሆነበት ማሕበረሰብ የተወለደ ወጣት እንን ለጎረቱ ሕይወት ሊያዝን ቀርቶ ለራሱ ሕይወትም የማይጨነቅ  ትግራይ ወስጥ በሺዎቹ አሉ፡፡

ከላይ የጠቀሰኩትና የምታዩት ፎቶገራፍ በ17 አመት የወያኔ የጫካ ጦርነት ዘመን “አማረ ታረቀ” የተባለ የወያኔ ታጋይ በውግያው ውስጥ ግራ እግሩ በከባድ የጥይት አሎሎ ተመትቶ ተቆርጦ በመውደቁ የተቆረጠው ቀኝ እግሩ አንስቶ ወደ ሰማይ በመቀሰር የሞት ብስራቱን በጸጋ በመቀበል ወዲያውኑ ህይወቱ እንዳለፈ ወያኔዎች በኩራት ሲተርኩለትና ቅዱሰ ሞት መሆኑን ለተቀረው የትግራይ ወጣት በፈለጉ እንዲከተል ይሰብካሉ (ለሞተውም ሆነ ለቆሰሉት ቤተሰቦቻቸው ግን አይረዱም፟ የኔን ቤተሰብ ለመሳሌ)  እንዲሀ ሞትን የሚንቅ እንዲገደልና እንዲሞት ሲሰበክ ሞትን የማይፈራ ሞገደኛ ማሕበረሰብ በተለይ “ሲገድልና ሲደፍር ፤ እየደበደበ ሲመረምር የቆየ ከጦርነትና ከጫካ ወደ ከተማና ገጠር (ማሕበረሰብ) የተመለሰ የፖለቲካም ሆነ የጦር አዋጊም ሆነ ተራ ተዋጊ ሕሊናው በደም የተነከረ እንቅልፍ ሲተኛ የሚያባንነው “ድንጉጥ (ሲፍሮዘኒክ) የቀወሰ  ሰለሚሆን የሕሊና ጭንቀቱ ለመወጣት መጠጥ አልያም ያልታከመ “ነበሰ ገዳይ” ሆኖ የጎረቤቱ ለጃገርዶችና ወዳጅ ዘመድ ቢደፍርና  ቢገድል በአእእሮ ሐኪሞች የሚጠበቅ ከሰትተ ነው፡፡

በግፍ ሰለተገደለቺው ምስኪን ታዳጊ ወጣት፤ ባጭር መቀጨትዋ ቢያሳዝንም ትንሽ ብትቆይ ኖሮ እስዋም የዚያ ያልታከመ የወያ ታጣቂ ወጣት ማሕበረሰብ አባል ትሆን እንደነበር የሚያጠራጥር አይሆንም ነበር::

ትግራይ ውስጥ የተለመደ ከሰተት አለ፡፡ሰው ሲገደልና ሲታገት፤ ቶች ሲደፈሩ ውት በማያስገኘው በሰላማዊ ሰልፍ ከመቃወም ይልቅ ሰከን ብሎ ትግራይ ወሰጥ ከ48 አመት በላይ እንክብካ ተደረጎለት በቅሎ ሥር የሰደደው <<የአመጽ ሁሉ እናት>> የሆነው “ኡር ፋሺዝም” እንዲወገድና ወያ የሚባል ድርጅት ከፖለቲካ እንዲታገድ ካልተደረገ ችግሩ ከትውልድ ወደ ትውልድ እየተሸጋገረ ሞት ቅዱስ ሆኖ ቪቫ ሞርቴ” ("ሞት ለዘላለም ይኑር!") እያለች ትግራይ በማትወጣበት ከባድ ማእበልና ጸጸት ትገባለች፡፡

ታቸው ረዳ