እመኑኝ፣ “ኦሮምያ” የተፈጠረችበትን
ቀን ትረግማለች!
ዳግማዊ ጉዱ ካሣ
2/2/2022
ETHIOPIAN SEMAY
አነሳሴ አስደንጋጭ ነው፡፡ ርዕሴ ብዙዎችን ያስደነግጣል፡፡ የጠ/ሚኒስትሬን ብልጣብልጥ የአነጋገር ዘይቤ ልዋስና እኔም በርዕሴ እጅጉን ደንግጫለሁ፡፡ እውነቱ ግን ይሄው ነው፡፡ እውነትን መደበቅ ደግሞ ማንንም አይጠቅምም፡፡ እና እውነቴን ነው - ይህች የወያኔ ፍጡር ኦሮምያ የምትባል የአሜባ ቅርጽ ያላት ክልልም በሏት ኢምፓየር በቅርቡ መፈጠሯን ትራገማለች፡፡ አውራ ፓርቲዋን ኦነግ/ኦህዲድን የተማመኑ ባለጊዜ ጥጋበኞችም ድራሻቸው ይጠፋል፡፡ ብዛታቸው አራት ሚሊዮንም ይሁን አርባ ሚሊዮን እነዚህ የኦነግ/ኦህዲድ አባላትና ካድሬዎች አያያዛቸው ሌልኛ በመሆኑ በራሳቸው ላይ አስቀድመው ሞትን ፈርደዋልና መጨረሻቸው ከወያኔዎችም በበለጠ እጅጉን አስቀያሚ ነው፡፡ አሁን የሚሠሩትን አጥተው በዕብሪት ተወጥረው ክፉኛ ቢቅበዘበዙም በቅርቡ የዞረ ድምር ሒሳባቸውን ያወራርዳሉ፡፡ ወደድንም ጠላንም ሃቁ ይሄው ነው፡፡ ዛሬ ትግራይን ያዬ በመለሳዊ ፍልስፍና የገማ ጭቃ ውስጥ ገብቶ ምነቦጫረቅን ባልመረጠ፤ ግን ፍርጃ ነው፡፡
የወያኔ አረሆ (የሴት አዝማሪ) በዚያን ሰሞን እንዲህ ብላ ዘፈነች አሉ፡-
ፍቅር ያዘኝ ብለህ አትበል ደምበር ገተር፤
እኛም አንድ ሰሞን እንዲህ አርጎን ነበር፡፡
አዎ፣ ሀብትም ሆነ ሥልጣን በትንንሽ ሰዎች ደጅ አይለፉ፤ በቤታቸውም አይግቡ፡፡ የበታችነት ስሜት በሚያሰቃየው ሰው እጅ አይውደቁ፡፡ የበታችነት ስሜት የሚወልደው ትንሽነት የክፋት ጎተራ ያደርጋልና ከዚህ እርግማን ይሰውር፡፡ ፈጣሪን የሚያስከዳ፣ ከሃይማኖት የሚያስወጣ፣ በጥጋብ ኅሊናን የሚያሳውር፣ ትናንትንና ነገን የሚያስረሳ እንደበታችነት ስሜት ሌላ ምንም የለም፡፡ ይህ በሽታ ነው እንግዲህ ሁለት ወንድሞቻችንን ከሰውነት ተራ አውጥቶ ፊትና ኋላም አቁሞ መከራ ፍዳቸውን እያበላቸው የሚገኘው፤ ጦሱ ለኛም ተርፎ አሳራችንን እያሳየን ይገኛል፡፡ የሚያልፍ ቀን ስንትና ስንት የማያልፍ ጠባሳ አስቀምጦብን ሊያልፍ ነው፡፡ አክራሪ ኦሮሞዎች በሚያመጡት ጠንቅ እኚያ የዋሃን ኦሮሞዎች እንዳይጎዱ(ብኝ)እሰጋለሁና አንድዬ ጨለማውን ያሳጥረው፡፡
ዱሮ ለደጋግ ተጋሩ ብዙ ተናግሬ ሰሚ አላገኘሁም፤ “ምክር የድሃ ነበርሽ ማን ቢሰማሽ” እንዲሉ ሆኖብኝ ጩኸቴ መና ሆኖ ቀረ እንጂ ትግራይ ወደ ምድረ በዳነት እንደምትለወጥ የላይቴ ላይ በል ያለኝን በወቅቱ ብያለሁ፤ አሁንም ያንኑ እውነት በሌላ መልኩ እየደገምኩት ነው፡፡ እናም ደጋግ ኦሮሞዎች እባካችሁን ነገ ጊዜ የላችሁምና አሁን እነዚህን ዕብዶች የጋራ ወንድምና እህቶቻችንን ምከሩ፡፡ ነገ ጊዜ ላይኖራችሁ ይችላልና ዛሬ አስጠንቅቋቸው፤ እርግጥ ነው የዕብሪት ሞራ የጋረደው ማንንም እንደማይሰማ ቢታወቅም ከእናንተ አይቅር፡፡ ጠጋ በሏቸውና ምከሯቸው፡፡ ትራክተርም ሆነ ስንዴ ከሞት እንደማያድን ንገሯቸው፡፡ ከትግራይ የበለጠ ኃይለኛና ባለዘመናዊ መሣሪያ እንዳልነበረም አስታውሷቸው፡፡ ሤራና ተንኮል ለመለስም እንዳልጠቀመ አስገንዝቧቸው፡፡ ጀግናው ጊዜ እንጂ ሰውም እንዳልሆነ አስረዷቸው፡፡ ትዕቢት ለነሂትለርም አልጠቀመ፤ ለነሙሶሊኒም አልበጀ፤ ለነቢስማርክና ጋዳፊም አልሆነ፡፡ …. እነአቢይና ሽመልስ ልጆች ናቸው፡፡ እነጃዋርና ሕዝቅኤል ጋቢሳ ልጆች ናቸው፡፡ እነፀጋየ አራርሳና ሌሎችም በኦሮሙማ ልክፍት ተጠምደው መከራ ፍዳቸውን እያዩ ያሉ ወገኖቻችን ሁሉ ብስለት የሚጎድላቸው ውርጋጦች ናቸው፡፡ በወያኔና ሻዕቢያ የመቶ ዓመት የቤት ሥራ ተኮትኩተውና በሀሰት የፕሮፓጋንዳ ትርክት ተመርዘው በማደጋቸው አሁን የሚታያቸው ኢትዮጵያንና አማራን ማጥፋት ብቻ ነው፡፡
“ዲአምሃሪሳይዜሽን” በሚል የተሳሳተ ቀመር ውስጥ ተዘፍቀው ራሳቸውንና ኢትዮጵያን ለማጥፋት ቆርጠው ቢነሱም በቆፈሩት ጉድጓድ ለመግባት የቀራቸው ጊዜ በጣም ጥቂት ነውና ወዳጅ ዘመድ ካለ ይምከራቸው፡፡ አማራንም ሆነ አማርኛን ማጥፋት በፍጹም አይቻልም፡፡ ከስምንት መቶ ዓመታት በላይ በመላ ኢትዮጵያውያን የወል ጥረት አድጎ የጋራ ጥቅም የሚሰጥን ቋንቋ በአንዴ አጥፍቶ በሌላ መተካት የሚቻለው ሁሉንም የቋንቋውን ተጠቃሚዎች ከምድረ ገጽ ካጠፉ ብቻ ነው፤ አማርኛን ደግሞ እንኳንስ ሌላው ዘውግ፣ አክራሪ ኦሮሞው ሌላውን እየከለከለ ራሱ ቅኔ የሚቀኝበትና መጽሐፍ ሳይቀር እየደረሰ ለሽያጭ የሚያቀርብበት ሀገርኛ ሆሄ ያለው ቋንቋ ነው፡፡ በመሠረቱ አማርኛ መወደስና መሸለም ሲገባው የአንዲት ሀገርን ሕዝብ ስላቀራረበና ስላዋሃደ ሊኮነን ባልተገባው፤ ከረቂቅ ግዑዝ ነገር ጋር መጣላት ደግሞ የጤና አይደለም፡፡ ያጎረሰን እጅ መንከስ ብልግና ነው፤ ቋንቋ ባለቤት የሌለው መሆኑንም እነዚህ የኦሮሙማ ልክፍት የተጠናወታቸው ሰዎች አያውቁም፡፡ በፍላጎት ብቻ ደግሞ የሚሳካ ነገር የለም፡፡ የነቶሎ ቶሎን ቤት የግድግዳ ሰምበሌጥነት ሁሉም ኢትዮጵያዊ በሚገባ እየተረዳው ነው፡፡
በመከራ ውስጥ ሆኖም እየሳቀባቸው ነው፡፡ የሚጠብቀው የፈጣሪን ፍርድ ብቻ ነው፡፡ እሱም ቀርቧል፡፡ እነሱ ግን አያውቁትም፡፡ የተነከሩበት ንፋስ የጣለላቸው ሀብትና ሥልጣን አሳውሯቸው የሚሠሩትን አሳጥቷቸዋል፡፡ እናም ከገበያ ገዝቶ ያመጣውን እህል ቂጣ ላርግህ ብትለው እምቢ፣ እንጀራ ላርግህ ብትለው እምቢ፣ ዳቦ ላርግህ ብትለው እምቢ … እያላት ሚስቱ ስትቸገር ያዬው ሰውዬ “ዕብድ እህል ገዝቼ ሚስቴን አሳበድኳት” እንዳለው ይህ በሥልጣን ስካር ያበደ አቢይ የሚባል ልጅ እንዳሻው በሚሾማቸውና እንደእንዝርት በሚያሾራቸው የኦሮሙማ አጋፋሪዎች ሀገራችን የዕውር ድብር እየነጎደች ወደገደል አፋፍ መጠጋቷ ኢትዮጵያውያን ነን የምንል ወገኖችን አሁን ካላስደነገጠ ጤነኛ መሆናችንን እጠራጠራለሁ፡፡
ተመልከቱ! በነዚህ አራት ዓመታት ምን ያልሆነ ነገር እንዳለ ታዘቡ፡፡
እነዚያኞቹ እኮ - አሁን ላይ ሆነን ስናስበው - ትንሽ ይሉኝታ ነበራቸው፡፡ ለታይታና ለይምሰልም ቢሆን ከአሥር ተሹዋሚዎች ውስጥ
ቢያንስ ሁለቱ ከሌላ ብሔር ይሆኑ ነበር፡፡ እነዚህ ደግሞ የባሰባቸው ሆኑና ከዘበኛ አቅም እንኳ ከሌላ አይቀጥሩም፡፡ ሁለመናቸው
ታውሯል፡፡ እንደሚባለው ባንኩም ታንኩም በነሱ ቁጥጥር ሥር ከገባ ወዲህ ኢትዮጵያን እንደግል ጥገት ላም እየጠቧት ይገኛሉ፡፡ ዱሮ
በወያኔ ዘመን “ትግራይ እስክትለማሌላው አገር ይድማ” የሚል አባባል ነበር፡፡ ከዚያም ባለፈ በተዘረፈ ሀብትና ንብረት ትግራይ ልትሰምጥ
እንደሆነም ይነገር እንደነበር አስታውሳለሁ - የሚባለው ሁሉ እውነት ይሁን ሀሰት ሌላ ነገር ሆኖ ግን ብዙ ነገሮች ይባሉ ነበር፡፡ አሁን ጊዜው ተገልብጦ “ኦሮምያ እስክትለማ ሌላው
አገር ይድማ” ተብሎ በኦሮሙማ አቀንቃኞች የታወጀ ይመስላል፡፡ ደህና ነገር እንጂ መጥፎ ነገር እንዴት ይወረሳል? የአእምሮ መጫጫት
ትልቅ ምልክት ነው፡፡
መልም ነገርን ይማሯል እንጂ አስጠሊታና አፍራሽ ነገርን መማር ተመሳሳይ አስቀያሚ ፍጻሜን መጋበዝ ነው፡፡
ለኦሮምያ አሥር ሽህ ትራክተር ሲልኩ ለአማራና ትግሬ መፋጃ ወይ መተላለቂያ ደግሞ መቶ ሽህ ጥይትና በሽዎች የሚቆጠር ላውንቸር ይልካሉ፡፡ ወያኔ የቀደደው ቦይ ተመችቷቸዋል፡፡ ፊደል መቁጠር የማያስፈልገው ምድረ ደንቆሮ ባለሥልጣን ሁሉ ደግሞ ከኦሮምያ ክልል በፉጨት እየተጠራራ ፌዴራል ተብዬውንና አዲስ አበባን - ማናት እቴ - ፊንፊኔን - ሙሉ በሙሉ እየተቆጣጠረ ነው፤ የአንዳንድ ክልል ተብዬዎችን ሥልጣንና ምክር ቤትም እንደዚሁ ይዘውታል - ለምሳሌ ቤንሻንጉል ጉምዝን፡፡ ደቡብን ለሥልታቸው ሲሉ በየብሔረሰቡ እየከፋፈሉ ክልል እንዲሆን እያደረጉት ነው፡፡
ይህ ደግሞ ተራ በተራ ለመሰልቀጥ እንዲያመቻቸው መሆኑ ግልጽ ነው፡፡ ትግሬና አማራን ልክ ካስገቡ ለሌላው እንደማይጨነቁ የታወቀ ነው - በአንድ ቀላጤ “ግባ በለው” ሲሉ እንደሚገባላቸው አምነው አሁን የተያያዙት አማራና ትግሬን እርስ በርስ ማፋጀት ነው፡፡ ዕቅዳቸው ሁሉ እኮ ግልጽ ነው፡፡ “ባለድርሻ አካላት” ግን አልገባቸውም፡፡በተለይ አማራና ትግሬ በተተለመላቸው የመጠፋፋት ሤራ በማን አባት ገደል ገባ የልጆች ጨዋታ እየተፎካከሩ በስፋት ቀጥለውበታል፡፡
ትንሽዬ ትዝናኑ ዘንድ ከኢቢሲ ዜናዎች እስኪ የተወሰኑትን ላሰማችሁና ወደሌላ
ነጥብ ልሂድ፡-
- እንዲህና እንዲህ መደረጉን የመሥሪያ
ቤቱ ዋና ኃላፊ ከበደ ባልቻ ገለጡ፡፡
- እንደዚያ የማይደረግ እንደሆነ ኃላፊዋ
ጫልቱ በዳዳ ለኦቢኤን አስታውቀዋል:::
- ሰሞኑን ተመርቆ አገልግሎት እንደሚሰጥ
የድርጅቱ ሥራ አሥኪያጅ ሰርቤሣ ነገዎ ገልጠዋል፡፡
- ነገሩ እንደተባለው የተጋነነ እንዳልሆነ
የሥራ ኃላፊው ዱጋሣ ቡልቲ በስልክ አስታውቀዋል፡፡
- ይህ ነገር ፈጽሞ ሊሆን እንደማይችል
ሚኒስትሩ ኦቦጉልማ ጫላለሪፖርተራችን ሁንዱማ ሚልኬሣ ገልጸዋል፡፡
-
- በመጋላ ፊንፊኔ የሚካሄደው የአፍሪካ
ኅብረት ስብሰባ በተሳካ ሁኔታ እንደሚጠናቀቅ የፊንፊኔ ፖሊስ ዋና አዛዥ ኮሎኔል ጫልጭሣ ጭብሣ ገለጡ፡፡ የኦሮምያ ፖሊስም የተጠቀሰው ስብሰባ በሰላም እንዲጠናቀቅ የሚፈለገውን ያህል የሸኔ ኃይል ማሰማራቱ
ታውቋል፡፡
- የመግቢያ ትኬቱን በአቅራቢያ ከሚገኝ
የኦሮምያ ኅብረት ባንክ ማግኘት እንደሚቻል የትርዒቱ አዘጋጅ ኮሚቴ ሰብሳቢ ኦቦ ሂርጳሣ ገለጡ፡፡
-
- ከአሁን በኋላ የፊንፊኔ የትምህርት
መስጫ ቋንቋ ኦሮሚፋ እንደሚሆን ሚኒስትር ዴታው ኦቦ መርዳሣ ገመቹ ገለጡ፡፡ (ስንሻውን ወይም ሐጎስንና ኡጅሉን ጠብቀህ ከሆነ ሲያምርህ
ይቀራል! እነሱ በዚህ ቀልድ አያውቁም፡፡ አሃ! ኬኛ ብለው ተነስተዋላ፡፡ የምን ይሉኝታ ነው፡፡ “ካለበት የተጋባበት” ይሉሃል እንደዚህ
ነው፡፡ ኦነጎቹ በዘረኝነት ወያኔን ዕጥፍ ድርብ አስከንድተውታል፤ የሸኔያቸውን ጭካኔ የተሞላበት የሰው ዕርድ ቢያስቆሙልን እንዴት
በወደድኳቸው፡፡)
እነዚህን ጉዶች በነዚህ አራት ዓመታት ሁሉንም አየንላቸው፡፡ የሆነው ይሁን፣ ጨለማውም የፈለገውን ያህል ይክበድ ኢትዮጵያ ግን አትጠፋም፡፡ አማራም አይሸነፍም፡፡ አማራ የሌለበት የጎሣና የነገድ ዘር በኢትዮጵያ ውስጥ የለም፡፡ ከሁሉም ጋር ተዋልዷል፤ ተዋህዷል፡፡ በባህልም ሆነ በኑሮ ዘይቤ ከሁሉም ጋር ተዋርሷል፡፡ አማራ ማለት ድንች ነው - ላጥፋው ባልህ ቁጥር የሚበዛ፡፡ የአማራን ሥነ ልቦና ጠላቶቹ አያውቁትም፡፡ አጠፋነው ሲሉ ይበዛል፤ አደኸየነው ሲሉ ይከብራል፡፡ አደነቆርነው ሲሉ አእምሮው በዕውቀትና ጥበብ ይሳላል፡፡ ይህም በሌላ ጎኑ ያስጨንቃቸዋል፡፡ ከማይችሉት ጠላት ጋር መግጠማቸውን ለማወቅ ግን እንደፊተኛው ሁሉ የኋለኛውም ጎማ እስኪተነፍስ ጥቂት ጊዜ መጠበቅ ይኖርብናል፡፡ አማራ ጦሩ ብቻ ሳይሆን በግፈኞች ጭካኔ የሚያፈሰው ዕንባና እንደጎርፍ የሚወርደው ደሙ ለጠላቶቹ መብረቅ ነው፡፡“አትዋል ይዋሉብህ፤ አትምከር ይምከሩ በቆፈሩት ጉድጓድ ሳይገቡም አይቀሩ” ብሎ የሚቀኘው አማራ ተገድዶ አሁን “አማራ ነኝ” አለ እንጂ ለኢትዮጵያውያን ሁሉ እኩል አተያይና የወገንተኝነት ስሜት ያለው ከዘረኝነት አረንቋ የፀዳና ለእናቱ ልጅ እንኳን የማያዳላ ሕዝብ ነው - እኔን ዳግማዊን ወይም እሷን ታንጉትን አትይ ታዲያ፤ እኔ እምለው እንደአጠቃላይ የማኅበረሰብ መገለጫ እንጂ ጎጠኝነትና ዝምድናዊ አሠራር መጥፎ ልማድ የሆነ ግን የሰውኛ ተፈጥሮ ባሕርይ መገለጫ መሆኑን አጥቼው አይደለም፡፡ ይህ እውነት ደግሞ ከሞላ ጎደል ለሁሉም ማኅበረሰቦች - እንደአካሄድ - ይሠራል ብዬ እገምታለሁ፡፡ የምናበላሻቸው ተማርን የምንል ወገኖች ነን፡፡
በነገራችን ላይ ከፍ ሲል የተናገርኩትን የአማራና የኢትዮጵያ አሸናፊነት ስናገር አንዳንድ ሰው “በዚህና በዚያ አካባቢ እንዲህና እንዲህ እየተደረገ፣ አማራ በወያኔና ኦነግሸኔ የተቀናጀ ጥቃት እየደረሰበት ይህ ሰው ለምን በተስፋ ዳቦ ሆዳችንን ይቀበትተዋል?” ብሎ ቢጠይቅ ትክክለኛ ጥያቄ ነው፡፡ የኔ እርግጠኝነት የተመሠረተው ደግሞ ከነባራዊ እውነታ እንጂ ከጥንቆላ ወይንም ከትንቢት አይደለም፡፡ ይሁንና አማራና ኢትዮጵያ አሸናፊነታቸው የተረጋገጠ ቢሆንም የአቢይንና የሽመልስን የፖለቲካ ቁማር ለመቀልበስ የሚደረገው ጦርነት መቼ እንደሚጀምር፣ የት ላይ እንደሚጀምር፣ እነማን እንደሚጀምሩትና ምን ያህል መስዋዕትነት እንደሚጠይቅ ከአንድዬ በስተቀር ከሰው ልጅ ዕውቀት ውጪ ነው፡፡ የምለው ሁሉ የምኞትና የቀቢፀ ተስፋ ውጤት ሳይሆን እውነት ነው፡፡
ለማንኛውም ይህን ስለአማራ የምለውን እውነት ሁሉም ይገንዘበው፡፡ ለአማራ ከጉያው ጀምሮ ራሱን መሰል ጠላት ቢበጅለትም ለሁሉም ጊዜ አለውና በቅርቡ ይነሳል - አሁንም መነሳት ጀምሯል፡፡ የማይቀርለትን የሁለትዮሽ የጥፋት ዐዋጅ የተረዳው አማራ ኅልውናውን በሚገባ ያረጋግጣል፡፡ ያኔም ኢትዮጵያ ትንሣኤዋ ይበሰራል፡፡ ሞኞቹ የሀገር ውስጥ የኢትዮጵያ ጠላቶች የአማራው መዘናጋትና የተከፋፈለ መስሎ መታየት ብርታትና ወኔ ሰጥቷቸው በተለይ ላለፉት 31 ዓመታት አማራንና ኢትዮጵያን ለማጥፋት ያልፈነቀሉት ድንጋይ የለም፡፡ ከፍ ሲል የተናገርኩትን አሁንም ልድገመው - ትንሽ ሰው አያሸንፍህ ወንድማለም፤ የፈሪ ምርኮኛ አትሁን ወንድምሁነኝ፤ የፈሪ ዱላ ዘጠኝ ነው ይባላልና አንዱም አይድረስብህ፡፡
ላም በሬን ስታሸንፍ የሚፈጠረው ክስተት ሁሉ በአማራ ላይ ተከስቶ እነዚህ ትንሾች በአማራ ላይ በየተራ እየተፈራረቁና በአንድነትም ጭምር አይነጋ መስሏቸው ተሳልቀውበታል፤ አሰቃይተውትማል፡፡ አማራም የነካው ሳይታወቅ ወይንም ምናልባት የሚከፍለው የሚወራረድ ዕዳ ኖሮበት በነሰው-ልክ አያውቁ ፍዳውን ሲቆጥር ጥቂት የማይባሉ አሠርት ዓመታትን አሳልፏል፡፡አሁን ግን ሲበቃ በቃ ነውና ሊበቃቸው ዘመኑ ግድ ብሏል፡፡ እናም ኢትዮጵያ ልትነሣ ጎሕ መቅደድ ጀምሯል - ጅማሬው ለብዙዎቻችን ባይታይም ጭላንጭሉ እየታያቸው ያሉ በከፍተኛ ጸሎት ላይም ተጠምደው የሚገኙ ወገኖች አሉ፡፡ ኢትዮጵያችን በትንሣኤዋ እልል የምትልበት ጊዜ ተቃርቧል፡፡ አሜን ነው - አሜን!!
ቀላል ሥሌት፡፡ ኢትዮጵያ ማለት ትግሬ ብቻ አይደለችም፡፡ ኢትዮጵያ ማለት ኦሮሞ ብቻም አይደለችም፡፡ ኢትዮጵያ ማለት አማራ ብቻ ማለት አይደለችም፡፡ ይህን እውነት እነዚህ ሦስት ዘውጎች በተለይም ከሁለቱ ውስጥ ብዙዎቹ የዘውግ አባላት የመዘንጋት ጠባይ ይስተዋልባቸዋል - ሲመቻቸው “የኔ ዘውግ ብቻ” ሳይመቻቸው ደግሞ “ኢትዮጵያ” የሚሉ፡፡ ይህ ዓይነቱ “ከመረቁ አውጡልኝ ከሥጋው ጦመኛ ነኝ” አካሄድ ደግሞ አያዛልቅም፡፡
ልብ እናድርግ! ከተጋሩ የበለጠ ሕዝብ ያላቸው ሶማሌን መሰል ነገዶች አሉ፡፡ ከትግሬ ቁጥር የማያንሱ የአፋርን ነገድ የመሰሉ ጎሣዎች አሉ፡፡ የአማራ፣ የትግሬና የኦሮሞ ቁጥር በአንድ ላይ ቢቀመጥ የሌሎቹ ቁጥር ያመዝናል፡፡ የኦሮሙማ ክሽፈት ግማሽ ምሥጢር እዚህ ላይ ነው፡፡ ኦሮሙማዎች “አማራንና ትግሬን ካጨራረስናቸው ሌላውን በግማሽ ቀን አስገብረን የኛ ባርያና ሎሌ እናደርገዋለን፤ በሞጋሳ ባህላችንም እናኦርምመዋለን፤ እምቢ የሚሉትንም እንደመስሳቸዋለን” የሚል ነው፡፡ እንዳንረሳባቸው ዘወትር በቃልም በጽሑፍም የሚያስታውሱን ይህ አስተሳሰባቸው ባይናገሩትም እንኳን ከድርጊታቸው ለማንም ግልጽ ነው፡፡ “በጊዜ የጮኸ ጅብ አያሳድረኝም” ይላል ያገሬ ባላገር፡፡ አማራንና ትግሬን እየዋጠ የሚገኝ ኦሮሙማ ነገ ምን ሊያስከትል እንደሚችል ጉራጌው ይገባዋል፤ ጠምባሮው ይረዳዋል፤ ሶማሌው ይገነዘበዋል፤ አርጎባው ያውቀዋል፤ ሃዲያውና ደራሳውም በቀላሉ ይገምተዋል፤ … ምናለፋህ … የነዚህን የኦሮሙማ ብልጣብልጥ አካሄድ ጡጦውን ያልጣለ ሕጻንም አያጣውም፡፡ ስለዚህ ኦነግ/ኦህዲድ መቃብሩን የቆፈረው ራሱ ነው፡፡ ሌላውን መናገር አይገባም፤ አያስፈልግምም፡፡ ነገ ራሱ አንደበት አለውና፡፡
ስለራስ መናገር በባህላችን ነውር ነው፡፡ በሰለጠነው ዓለም ግን ብዙም የሚያስከፋ አይደለም - የሚነገረው እውነት ይሁን እንጂ፡፡ እናም እኔ አሁን አለሁ፡፡ ትናንትም ነበርኩ፡፡ ነገ ግን አልኖርም፡፡ ከሰኔ 12 ቀን 1982ዓ.ም ጀምሮ ስለሀገር ብዙ ጫጭሬያለሁ፡፡ ስለወያኔ ገና ጫካ ሳለች ጀምሮ በርካታ ቁም ነገሮችን በሬዲዮም በቴሌቪዥንም አስተላልፍ ነበር፡፡ የወያኔን መጨረሻ ይናገሩ ከነበሩ ሰዎች መካከል አንዱ ነኝ፡፡ ያልነው ሁሉ አልቀረም፡፡ ሁሉም በጊዜው ሆነ፡፡ ልብ አድርግ! “ከአነጋገር ይፈረዳል፤ ከአያያዝ ይቀደዳል” እንላለን - “የማይወጣ እንጀራ ከምጣዱ ያስታውቃል”ም እንላለን፡፡ ማንም ቢሆን በወያኔና በኦነግ/ኦህዲድ መንገድ ተጉዞ ኢትዮጵያን የመሰለች ታሪካዊት ሀገር ማጥፋት አይችልም፡፡ ማንም ደግሞ በሤራና በተንኮል እንደበለጠ አይኖርም፡፡ ተንኮልና ሤራ ይበልጥ የሚጎዳው ሤረኛንና ተንኮለኛን ነው፡፡ የሸፍጠኞች ድል ጊዜያዊ ነው፡፡ ይህን መናገር ደግሞ ትኩረትና ፍላጎት እንጂ ብዙም ዕውቀትና መፈላሰፍን አይጠይቅም፡፡
በመጪው ጊዜ ብዙ ችግሮች መኖራቸውን ማንም ልደብቅ ቢል የሚችል አይመስለኝም፡፡ ልደብቅ ቢል እንኳን ግመል ሰርቆ አጎንብሶ እንደመሄድ ወይም ሳል ይዞ ስርቆት ዓይነት ነው፡፡ ችግሮች በጣም የፈጠጡበት ወቅት ላይ ነን፡፡ ነገር ግን እንኳን ከፎከረ ከወረወረም የሚያድን አምላክ አላትና ኢትዮጵያ ሊበሏት ካሰፈሰፉ ታሪካዊ ጠላቶቿ ፈጣሪዋ በቅርቡ ይታደጋታል፡፡ ከሰው የሚጠብቅ በሰው ምሕረት ሥር አለ፡፡ ከፈጣሪ የሚጠብቅ ግን በፈጣሪ እጅ ውስጥ አለ፡፡ እርግጥ ነው - ሰው ነንና በምናየው ሁሉ እንደነግጣለን፤ እንፈራለንም፡፡ ያለመንግሥት መኖር፤ ከዚያም ባለፈ በከሃዲዎች ጨንገር ባልተወለደ አንጀት እየተገረፉ በስቃይ መኖር መፈጠርን ያስጠላል፡፡ አዲስ አበባን ለኑሮ አመች እንዳትሆን ሆን ተብሎ በሚሠራ የኑሮ ውድነት መንገብገብና በዚያም ምክንያት ከደሞዝ ጋር መቆራረጥ፣ ከግርጌ እስከራስጌ በሙስና በበሸቀጠና በበሰበሰ ቅጥየለሽ መንግሥታዊ ሥርዓት መገረፍ፣ ፍትህና እውነተኛ ዳኝነት በዘረኝነትና በገንዘብ በተለወጡበት ማኅበራዊ ቀውስ ውስጥ መዘፈቅ፣ አንድን ጉዳይ ለማስፈጸም ሲፈለግ አለቃና ምንዝሩን ማወቅ በማይቻልበት ጉቦኛ የቢሮክራሲ ውጣውረድ መንከራተት፣ ከትምህርትና ከዕውቀት ጋር በተጣሉ አሮሙማዎች ግልምጫና ስድብ ሠርክ መንገብገብ፣ ከእርሻና ከከብት እረኝነት በመጡ ቄሮዎችና ቄሪቶች የዕውር ድምብር አገዛዝ መሰቃየት፣ ሁለት በሚመስሉ ግን አንድነታቸው በዘር ሐረግ በጠበቀ የአንድ ዘረኛ ድርጅት አስተዳደሮች ጥምር አገዛዝ መጠበስ … እርግጥ ነው ለጊዜው መፈጠርን ማስረገሙ አይቀርም፡፡ ግን ግን ክፉውን ካላዩ ደግ አይገኝምና ይህ ሁሉ ሊሆን የግድ ነው፡፡ መቻያውን ይስጠን ወገኔ፡፡
አሁን ቄስ የለም፡፡ አሁን ጳጳስ የለም፡፡ አሁን ፓትርያርክ የለም፡፡ አሁን የበቁ አባቶች የሉም - አንድም እንኳ፡፡ ቢኖሩ ኖሮ አቡነ ጴጥሮስን እናይ ነበር፡፡ ቢኖሩ ኖሮ አቡነ ተክለ ሃይማኖትን እናይ ነበር፡፡ ቢኖሩ ኖሮ መጥምቁ ዮሐንስን እናይ ነበር፡፡ እንዳልምል ያህል አንድ አባት ከሙስሊም፣ አንድ አባት ከኦርቶዶክስ ለአብነት መጥራት እችላለሁ እንጂ ሌላው መጽሐፉ እንደሚለው ሁሉም በኃጢኣት ሥር ወድቆ ለኃጥኣን አገዛዝ ተንበርክኳል፡፡ ለምሣሌ ይህ ሁሉ ግፍና በደል በሀገር ላይ እየወረደ አንድም ጳጳስ ሀገራዊ ሱባኤ እንዲጠራ አላዘዘም - ለምን ቢባል “ከተደላደለ ኑሮየ እፈናቀላለሁ” ብሎ ይፈራላ! ሎጥ ወዶ አልነበረም የአምላክን ቁጣ ለማስቀረት ያን ሁሉ ጥረት አድርጎ ሲያበቃ አንድም ጻዲቅ ማቅረብ ባለመቻሉየጨው ዓምድ ሆና የቀረችዋን ሚስቱን እንኳን ማዳን ያቃተው፡፡
ፈጣሪ ማንን አይቶ ይማረን ታዲያ! ስለሆነም እግዚአብሔር ሁለቱንም በቅርቡ ያጸዳል፡፡ ቤተ መንግሥትንም - ቤተ እምነቶችንም፡፡ ከሞላ ጎደል ሁሉም በሚባል ደረጃ ከበጎው መንገድ ወጥተው በክፋት የሰይጣን መንገድ እየነጎዱ በመሆናቸው ዋጋቸውን ሊያገኙ ፋይሉ ከፅርሃ አርያም ወጥቶ ወደኃያል መላእክት እጅ ገብቷል፤ ጊዜውን ግን ከፍ ሲል ለመግለጽ እንደሞከርኩት በዚህ ወይ በዚያ ዓመት ብሎ መናገር የሚችል የለም፡፡ የጊዜ ቀመር በፈጣሪና በሰው መካከል እጅጉን ስለሚለያይ በዚህ ዓመት እንዲህ ይሆናል በዚያኛው ደግሞ እንዲህ አይሆንም ማለቱ ለትዝብት ከመዳረጉም በተጨማሪ ሰውን በከንቱ ማጓጓትና የፈጣሪን ሥራም መቀማት ነው፡፡ እኔ አጭበርባሪ ባህታዊ አይደለሁም፡፡ በቀጨኔም ሆነ በአራት ኪሎ አልገኝም፡፡ እኔ የጩፋይዝምና የእሥራ-ዳንሳይዝም የሣጥናኤል አቀንቃኝ ወይም ተከታይ አይደለሁም፡፡ እኔ እኔነቴን ለገንዘብ የምሸቅጥ በሃይማኖትና በፖለቲካም የምነገድ ዜጋ አይደለሁም፡፡ ከአንዲት እንጀራ ለማታልፈው ሆዴ ብዬ ሀሰትን የማራግብ ሳልሆን የሚሰማኝንና ትንሹ እግዚአብሔር - ኅሊናየ - የሚነግረኝን ለሚሰሙኝ የማስተላልፍ ምስኪን ኢትዮጵያዊ ነኝ፡፡ ፈጣሪየ ግን ከምለው ነገር አጉድሎ(ብ)ኝ አያውቅምና ዘወትር አመሰግነዋለሁ፡፡ዘመኑ የሃሳውያን መሲሆች ዘመን መሆኑን ደግሞ ጠንቅቄ እረዳለሁ፡፡
ከደፈረሰው ባህር ማዶ፣ ከሚያዳፋው ማዕበልና ወጀብ ቀጥሎ አሰስ ገሰሱ
በተነቃቀለላት ግሩም ዐውድ የምትመሠረት ኢትዮጵያ ከምትታያቸው በጣም ጥቂት ወገኖች መካከል መሆኔን ስለምገምት ዕድለኛ ነኝ ብዬ
አምናለሁ፡፡ ተዓምሩ የማያልቀብት ፈጣሪ ፀጋውን አብዝቶልኝ ለዚያ ወርቃማ ዘመን እንዲያበቃኝም እጸልያለሁ፡፡ ሆዳሞችን ግን፣ ሀገር
ሻጮችን ግን ፈጣሪ የሥራቸውን እንዲሰጣቸው ለርሱ ድንቅ የፍትኅ ሚዛን እተዋለሁ፡፡ እግዚአብሔር ሀገራችንን ከገባችበት ማጥ በፍጥነት
አውጥቶ ትንሣኤዋን ያሳየን፤ አሜን፡፡