Monday, December 6, 2021

የአብይ አሕመድ ባንዳ ትግሬዎች ሰልፍ በርእሰ ከተማዋ ጌታቸው ረዳ ETHIO SEMAY 1/6/2021

 

የአብይ አሕመድ ባንዳ ትግሬዎች ሰልፍ በርእሰ ከተማዋ

ጌታቸው ረዳ

ETHIO SEMAY

1/6/2021

ትናንት አዲስ አባባ ከተማ ውስጥ “አብይ ምን አለ አገሬን ለሰው አልሰጥም አለ!” እያሉ አምልኮተ አብይ አሕመድ እንዲሰበክ የተከናወነ አሳፋሪ የባንዳዎች መፈክር አድምጠናል አይተናል።ለመንግሥቱ ሃይለማርያምም ተመሳሳይ መፈክርና ጭፈራ ሲደረግለት ነበር። በመጨረሻ ግን አገሩን ለጠላት ሰጥቶ ሸሸ።

አብይ አሕመድም በወታደሮቹ  እጅ ወይንም በተቀናቃኞቹ ‘በአክራሪ ‘እስላማዊ’ ኦ.ነ.ግ.’ ካልተቀጨ የጊዜ ጉዳይ እንጂ የመንግስቱ ዕጣ ይደርሰዋል።

የዚህ ሰልፍ አድማቂዎች አንዳንዱም ቀያሾች የሆኑት በኦሮሞዎች የሚመራው አፓርታይዱ ወያኔን የተካው ለአዲሱ “አፓርታይዱ ለኦሮሙማው ሥርዓት” በባንዳነት የተቀጠሩ በጸረ አጼ ምኒሊክነታቸው የታወቁት ወያኔ የነበሩ እንደ እነ “ሲፍረዚኒኩ” ኮ/ል ዶክተር አብርሃም በላይ (መከላከያ ሚነስትር!)፤ ወያኔው አረጋዊ በርሀ፤ እና ነገሥታቶች እኛ ነን እንጂ እናንተ አልነበራችሁም የሚሉ የእንደርታ ገዢነት ለማምጣት ወያዎች ጋር ግጭት ውስጥ የገቡት ከዓድዋዎች ጋር ጸብ የገጠሙ እንደርታዎቹ ጸረ ሚኒሊኮቹ “ሊላይ ሃይለማርያም፤ ነብዩ ስሑል፤ እንዲሁም በስንት ጥረት እንቅልፍ አጥቼ  አሜሪካ ኤምባሲና “ዩ ኤን ኤች ሲ አር” ወደ አሜሪካ እንዲመጣ አንዲሁም ኒው ደልሂ ፖሊስ ኮሚሽነር የመሳሰሉት እየተጻጻፍኩ ችግር እንዳይገጥመው ሌት ተቀን ስራየ ብየ ወዳጆቼና አገር ወዳዶችን አስተባብሬ ፤ ቤት ክራዩ እና ምግቡን ከነ ልጁ ችለን ከሕንድ (ኒው ደልሂ) አገር ወደ አሜሪካ ያስመጣሁት፤ በእርሱ ምክንያት አንረዳህም ካሉት ጋዜጠኞች ጋር ተጣልቼ፤ ምስጋና ቢሱ “አለቅላቂው” አዲሱ የአብይ አሕመድ ባንዳው “አርአያ ተስፋማርያም እና ኢ. ቲ. ቪ’ ላይ አብራው የምታለቀልቀው የትግራይ ብልጽግና ጋዜጠኛ አበባ የተባለቺው እና የመሳሰሉ “ባንዳዎች” የተወደሰ ለአምልኮተ አብይ የቀረበ ሰልፍ አይተናል።

እነኚህ ባንዳዎች ስለ ትግሬዎች መብት አሳቢዎች ቢሆኑ ኖሮ እዛው እፊታቸው በሚኖሩበት ከተማና መንደር፤ የናዚ ጌስታፖዎች ሲፈጽሙት የነበረው ሂትለራዊ “የዘር ጦርነት” የተከፈተባቸው ከምንም የሌሉበት ትግሬዎች ጎን ቆመው ችግራቸውን በሰልፍ ማቅረብ በቻሉ ነበር።ነገር ግን ያንን ማድረግ አለቃቸውን ማጋለጥ ሆኖ ስላዩት ያንን ከማድረግ ተቆጥበው “ማሽቃበጥን” መርጠዋል።

የኢትዮ ሰማይ ድረገጽ ተከታታዮቼ እንደምታስታውሱት ከአመት በፊት የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ትግሬዎች ተመራቂዎች በምርቃታቸው ቀን የኢትዮጵያ ሰንደቃላማ ሲሰቀልና ሲዘመር ሌሎቹ ሲቆሙ ‘እነሱ ግን እግራቸውን አጣጥፈው” በመቀመጥ ልግምት በማሳየታቸው ትችት አቅርቤ መኖሬን ታስታውሳላችሁ። ዛሬም ተለጥፎ ስላለ ብትፈልጉት ታገኙታላችሁ (አንብቡት) ዛሬ ደግሞ በተቃራኒውና እጅግ በሚያሳፍር መልኩ የሕዝብ ስቃይ በመርሳት አብይ አሕመድን እያሞካሹ ሰላማዊ ሰልፍ የወጡ ትግሬዎችንም እነሆ ብዕሬን ሳሾል ልብ ላላችሁ አንባቢዎች ሚዛናዊ እንደሆነ ትገነዘባላችሁ።

በሩዋንዳ ዓይነት የዘር ፍትግያ በገባች አገር ውስጥ እየተኖረ ይህ አፓርታይድ ለመቃወም ፍትሕ እንዲሰፍን ከመታገል ይልቅ ኢትዮጵያ ውስጥ አገራችን ብለው በሚኖሩባቸው ከተሞችና መንደሮች “በትግሬነታቸው ብቻ” ተለይተው እየተደበደቡ “ከሥራ እየተባረሩ፤ እየታፈሱ ወደ ማጎርያ ሲወሰዱና ንብረታቸው ሲዘረፍ፤ ያለ ሕግ ሲደበደቡ” እያዩ ለዓለም ያለመጮህ በተባባሪነት ያስጠይቃል። ለነገሩ እንኳን ተባባሪ ሊጠየቅ የወንጀሉ ቀያሾችና መሪዎች ሕዝብ ሲጨፈጭፉ ማን ጠየቃቸው? ለነገሩ እንጂ ወንጀለኞችንስ ቢሆን አገር ወዳድ ብሎ ማሞካሸት የኛ የኢትዮጵያኖች ታሪክ አይደለምን!?   

ግፉ እኮ የት የሌለ ነው። ያውም አቅም የሌላቸውን ሴቶችን ለማንገላታት ወደ መኖርያ ቤቶቻቸው ድረስ “ኢንተርሃሙዌ ፖሊሶችንና የጸጥታ አካላትን” በመላክ እርጉዝ ሴቶችን “በእርግጫ፤በጥፊና በቡጢ” እንዲደበደቡ ትዕዛዝና መብት የሰጣቸው አብይ አሕመድን በአደባባይ በዓለም ፊት “አብይ ምን አለ አገሬን ለሰው አልሰጥም አለ!..” እያሉ የፋሺሰቶች ተክለሰውነትን መንከባከብ ከድሮ ጀምሮ ሲጨማለቁበት ካደጉበት ቆሻሻ ወያኔአዊ ገመናቸው መላቀቅ አልቻሉምና የለመዱበት የእሸክርና መንጋዊ ባሕሪ ነው።

አገር ለጠላት አልሰጥም አለ፤ የሚባለው ቅዠት እራሱ መሪያችን ብለው እያሞካሹት ያለው ንጹሃን ትግሬዎች እያንገላታ ያለው የወያኔ መንትያው ቁጥር አንድ (1) ጠላት አብይ አህመድ ነው።

አገር ማለት ተራራ ብቻ ሳይሆን ሕዝብ ነው። ሕዝብ  ያለ ምንም ሓጢያት በማጎርያ እስርቤቶች የታሰሩና እየተደበደቡ ላሉት ትግሬዎች ምንም ደንታ እና ትኩረት ሳይሰጡ መዋለል፤ በዚህ ከቀጠለ ደግሜ ደጋግሜ የተናገርኩት “ትግራይ በነዚህ ባንዳዎች ምርኩዝነት የኢትዮጵያ አካል ሆና እንደማትቀጥል ሃቁ መራራ ቢሆንም እውነቱን ተጋቱት።

 ይህንን ሃቅ በግልጽ በመናገሬ አማራዊው እና ኦሮሙማው ኢንተርሃሙዌው መንጋ ሲንጫጫብኝ ሰንብቷል። የመንጋው ጩኸት በእየሱስ ላይ ድንጋይ ሲወረወርበት እንደነበረው ዓይነቱ ድካም ስለሆነ እንደ ዕሬት ቢመራችሁም ተጋቱት።

‘ትግራይ ጥርግ ትበል’ የምትሉ እውጭ አገር በድሎት የምትኖሩ አማራዊ ኢንተርሃሙዌዎችና ሌሎቻችሁ፤ አገር ውስጥ ያሉ ቤተሰቦቻችሁ ነገ የሶርያኖች ዕደል ሲገጥማቸው የዛሬ ምክሬን ታስታውሱታላችሁ። በየጎራው የሚፎልለው ጥንታዊት አገር ለማፍረስ እየጣረ ያለው የትምክሕተኛውም የደንቆሮውም ህይወት የተመኘውን “የነ ተሎ ተሎ ቤት ግድግዳው ሰንበሌጥ” ተሰርቶ አልቆ ‘ሲመረቅ’ ለማየት ያኔ እኔ በሕይወት ላልኖር እችላለሁ።

እነዚህ ባንዳዎች አዲስ አባባ ቁጭ ብለው አለቃቸውን ለማሞካሸት እንዲጥማቸው ኤርትራኖች እና ትግሬዎችን በየመንደሩ እየሄዱ በቀሰቀሱት የባንዳ ብልጽግና ትግሬ ካድሬዎች ባደረጉላቸው ጥያቄ “ተሰለፉ ሲባሉ እምቢ ማለት የሚያስከትለው ብትር ስለሚያውቁ” እሺታቸው የገለጹና ከወያኔ ጋር ቅራኔ ያላቸው ሰዎችንም ቀላቅለው አሰባስበው “የተነፋ ባሉን አስይዘው” እንዲጨፍሩ ተደርጓል።

የትግሬዎች ስቃይ አላየንም አልሰማንም፤ እየተያዙ ያሉት የወያኔ ጀሌዎች ናቸው፤ እያለ አፉን ከፍቶ ላነድ ጋዜጠኛ ሲዋሽ ያደመጥኩት አዲስ ባንዳ ሲናገር ሰምቻለሁ። ባንዳዎች ምንም ቢሉ አብይን ከዓለም አቀፍ “የወንጀል ክስ” መከሰሱ ማንም ሃይል ሊከላከልለት አይችልም (እየሆነ ያለው ስለማውቅ ነው)። አማራዎችም ባለፉት በርካታ አመታት፤ “አማራ ተበድሏል፡ ስል “ውሸታም” ሲሉኝ ነበር እራሳቸው አማራዎቹ።እንዲህ ያሉ ባንዳ ትግሬዎችም ያንን ታሪክ እየደገሙት ነው።

ባንዳዎቹ ቢጮሁለትም የትግራይ ንጹሃን ስቃይ ዓለም እንዲመለከተው በቪዲዮ ተቀርጾ ለሚመለከታቸው እየተላከ እየታየ ባለበት ወቅት ይህ ግፍ ከመቃወም ይልቅ ሴቶችን የሚደበድብ፤ ንብረት የሚዘርፍ፤ የሚደፍር “ወረበላ ፖሊስ” የሚያሰማራውን “ወረበላው አብይ አሕመድን” መካብ ፤ አገር ወዳድነት ሳይሆን ጸረ አገር መሆን ነው።

በመጨረሻም ትግሬ ለሆናችሁ  የአብይ አሕመድ ካድሬዎችና ደናቁርት ጀሌዎች የማስተላልፈው መልእክት የሚከተለው ነው።_

“ኢንትርሃሙዌው መሪ ባጠረው አጥር ውስጥ እየተሰቃዩ ያሉ ንጹሃን ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን ድምጽ ለማፈን ብትጥሩም የተጠለላችሁበት የአፓርታይድ ምሽግ በግፉአን ሃይል ነገ ይደረመሳል”። ምርጫችሁ የናንተ ነው።

ትችቴ በኢንተርሃሙዌ መሪያችሁና ጀሌዎቹ ዘረኛነታቸውን እስኪያቆሙ ድረስ ይቀጥላል!

ጌታቸው ረዳ (ኢትዮ ሰማይ)