Isayas Stoog Amanuel Beidemariam |
ውራጅ ፖለቲካ በኢሳት ቲቪ
Email getachre@aol.com
በአማርኛ ቋንቋችን ‘ተጠግቶ የሚያጠቃ’ ነብስ « ተውሳክ » ይባላል። አረቦቹ ‘አልጀዝማ ‘ይሉታል። እንዳውም የዓረቦቹ አጠቃቀም እኛ ‘ተውሳክ’ ከምንለው በበለጠ ያብራራዋል። የተጠቂውን የሰውነት ክፍል አካል ተመስሎ በመጣበቅ ተጠቂውን ‘ቀስ’ እያለ የሚያጠቃ እንደሆነ ነው የዓረብኛው ትርጉም ተውሳኮችን በበለጠ የሚያብራራው። የሰው ተውሳኮች ደግሞ አልጀዚሞችን በጥልቅ ለመግለጽ ሲፈልጉ ‘ጃሱስ’ ይሏቸዋል፤ (በኤርትራዊያን
የናቅፋ የበረሃ ቋንቋ ደግሞ (ጃንዳ/አገልጋይ) « ሰላይ » ማለት ነው። በዚህ ቃል ብንረጋ ፤ እራሱ ሻዕቢያ እና የሻዕቢያ ሰላዮች በተቃዋሚ ድረገጾች ፕሮፓጋንዳቸውን እንዲነዙ አንዳንድ ተቃዋሚ ድረገጾች ለብዙ አመታት ሲተባበሩ መቆየታቸው ማስረጃ ማቅረብ አይቸግርም።
‘ኢሳት’ የተባለው በበጎ አድራጊዎች (እራሱ እንደሚነግረን ከሆነ) የሚተዳደር ጣቢያ ጋዜጠኞች ናቸው ብሎ ያሰባሰባቸው አንዳንድ ጋዜጠኞቹ የሚነዙት የኢትዮጵያን ሉአላዊነት እና ክብር በሚያሳንስ መንገድ ዛሬም እየቀጠለበት ይገኛል። ከዚህ በተጨማሪ ይህ ጣቢያ በጸረ ትግሬ ቅስቀሳ የታወቀው « ECADF/ድረገጽ » ወይንም Ethiopian Current
Affairs የተባለው ፓል ቶክ ጋር በመተባበር (የብዙ ኢትዮጵያዊያን
ጽሑፍ እና ቃለ መጠይቅ ሕዝብ እንዳያዳምጣቸው/ እንዳያነባቸው እያገዱ) የየሻቢያ ወኪሎች እና ጃንዳዎቻቸውን የሚናገሩት እና የሚጽፉት
ጸረ ኢትዮጵያ አጀንዳ ያለ ምንም ገደብ ያስተናግዳሉ።
ሰሞኑን እንዳያችሁት ሦሰት የሻዕቢያ ሰላዮች እና ወኪሎች በነዚህ “የኢትዖጵያ ተቃወሚ ድረገጸች” እያሉ ራሳቸውን የሚጠሩ ድረገጸች እና ቴቪዢን ጣቢያ ሲስተናገዱ ታዝበናል። ለምሳሌ ከነዚህ ውስጥ ሶፍያ ተስፋማርያም ፤ አማኑኤል በእደማርያም እና ተስፋየ ገብረአብ ናቸው። እነኚህ ሁለቱ ኤርትራዊያን ሶፍያ እና አማኑኤል ‘ለአለም አቀፍ ኮንቶሮባንዲስቱና ባርያ ፈንጋዩ ለኢሳያስ አፈወርቅ” ያደሩ የታወቁ “ጅንዳዎች” ናቸው። የማንነት ፍለጋ ውስጥ ገብተው ማንነታቸውን ማግኘት የተሳናቸው እነዚህ ሁለቱ “ጃንዳዎች” ሕሊናቸው በማንንት ፍለጋ ሲጋጭ “ወጣት ኤርትራዊያን ሴቶችና ወንዶች እየታፈሱ ኢሳያስ አፈወርቅ ባዘጋጃቸው “የሻዕቢያ ጠላፊ ቡድን/ጐስታፖ” እየተጠለፉ “ጭለማ እስር ቤቶች ውስጥ” እየተቀጠቀጡ መላው አከላታቸው ‘ተልቶ እና ቆስሎ’ በሚገማው ሽታ የሚመረቅኑ “በወገኖቻቸው ስቃይ እና እምባ” የሚደሰቱ’ የአረመኔ መንጋ ቡድን አገልጋዮች ናቸው።
ውጭ አገር ከሚንቀሳቀሱ የኢትዮጵያ ተቃዋሚ ቡድኖች ብለው ራሳቸው ከሚጠሩ ከእነ “ንአምን ዘለቀ እና ግንቦት 7” ጋር በመተባበር የሻዕቢያ ወኪል አማኑኤል ባእደማርያም የተካፈለበት’ “Ethiopia & the Horn of Africa Conferenece on Governance, Peace, Security and Sustainable Development” በሚል የመወያያ ጉዳይ በApril 9 እስከ 11 / 2010 (አውሮጳ አቆጣጠር) አርሊንግተን ቨርጂኒያ ውስጥ ከላይ የተጠቀሱ ኢትዮጵዊያን አድርባይ ቡድኖች ከሻዕቢያ ጋር ሕብረት በመፍጠር ‘የሻዕቢያ’ አውሬነት የማናውቅ መስሏቸው ዛሬ ደግሞ የሰውነት ባሕሪ ለማላበስ ሻዕቢያ የሰው መብትና የስነ መንግስታዊ አስተዳደር ተምሳሌ ይመስል አማኑኤል ባእደማርያምን ከአዘጋጆቹ ጋር በመመካከር ኢትዮጵያ አገራችን መግባ፤ በነፃ አስተምራ ለዚህ ያበቃቺውን ኢትዮጵያን በኮሎኒያሊሰትንት እየከሰሰ የዘለፈበትን ሰፊ መድረክ አንደሰጡት የሚታወስ ነው።
ከዚህ በተጨማሪ “ሶፍያ ተስፋማሪያም” ያዘጋጀቺውን የሻዕቢያ ማንነት የማያውቁ እንደ እርሷ የመሳሰሉት ውጭ አገር ያደጉ “የሻዕቢያ ወጣት ማሕበር በማሰባሰብ ”የዓለም ሕብረተሰብ በኢሳያስ እና በነብሰገዳይ አገልጋይ ወታደራዊ አሽከሮቹ የጣለውን ማዕቀብ በመቃወም የተዘጋጀው “ሻዕቢያዊ ሰላማዊ ሰልፍ” ንአምን ዘለቀ እና መሰል ‘ጃሱሶች’ ተቃቅፈው አብረው ተስልፈው ይጨሁ እንደነበረ በሚያሳፈር ሁኔታ የተነሱት ዩቱብ ቪዲዮው ካሁን በፊት አሳይቼአችሁ እንደነበረ ይታወሳል። ተስፋየ ገብራብም በደምብ ስለምታውቁት ብዙ መዘርዘር አያሻውም። ኢትዮጵያ ወታደር እንጂ አምላክ አያድናትም ሲል እየተሳለቀብን ቆይቶ፤ ይህ ብሎ በጻፈ እኔ በተቃወምኩት መሰሪ ምላሱ “የኢትዖጵያ አምላክ” ትንግርታዊ ስራው ለማሳየት “የድሮ አለቃው “መለስ ዜናዊ”ን መንቅሮ ወሰደው። ተስፋየ ሻዕቢያም ምላሱ ቀርጥሞ አምላክ እንዲያፍር አደረገው ።
«ሁለቱ የፋሺስቱ ኢሳያስ» ወኪሎች የተለያየ ጸረ ኢትዮጵያ ክብር የሚያዋርድ ቅስቀሳ በድረገጻቸው እና በተለይ ሰሞኑን በኢሳት ቲቪና በራዲዮን ጣቢያው ጋብዞ ሻዕቢያዊ ተልዕኮ
ሲያስተላልፉ መስማት ለአገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያን እጅግ መራራ እሬት ነው።
ዛሬ አገራችንን በከባድ ፈተና ተወጥራ እንድትያዝ ያደረጉት የሕዝባችንን ክብር፤ታሪክ እና አንድነት ለማፍረስ በጠላትንት የፈረጅናቸው እና የፈረጁን ኦነጎች እና ሻዕቢያዎች የመሳሰሉ ብቻ አይደሉም። በተቃዋሚነት የተሰለፉ አንዳንድ አድርባዮችም ጭምር የጠላቶቻችን ፕሮፓጋንዳ መሳሪያ ሆነው ሲያገለግሏቸው የታዘባችሁ አገር ወዳዶች እንዳላችሁ በሚደርሱኝ ደብዳቤዎች ማወቅ ችያለሁ።
ተመችቶአቸው ወደ ተቋሚው ጎራ ሰርገው በመግባት ብቻ ሳይሆን የፖለቲካ ሴራቸውን የሚያራምዱት ተቃዋሚም እራሱ ለጊዘያዊ ጥቅሙ ሲል ከነዚህ ጸረ ኢትዮጵያ አሸባሪዎች እና ነብሰገዳይ ወሮበላ ቡድኖች ጋር በመሞዳሞድ አንዳንዱም እስከ ኤርትራ ምድር ድረስ በመሄድ ኢትዮጵያዊነቱን/ትግሬነቱን ክዶ « ኤርትራ » የሚባል ምንነቱ የማይታወቅ « ማንነት » በመፍጠር በጸረ ኢትዮጵያ ስራው የታወቀው ኢሳያስ አፈወርቂ ጽ/ቤቱ ድረስ በመሄድ አርዳታ እንዲያደርግላቸው የተማጸኑ ኢትዮጵ ውያን በጃሱስነት እያገለገሉ ለኦነግ እና ለሻዕቢያ መጠቀሚያ እየሆኑ ሕዝባችንን ለማወናበድ በግልጽ እየተንቀሳቀሱ እንደሆነ በሚያሳዩት ትብብር መረዳት ችለናል። ተክለሚካኤል አበበ ወይንም « ተክሌ » እያለ ራሱን የሚጠራ በቅርቡ ወደ ኢሳት ቲቪ የተቀላቀለው የኢሳቱ ጋዜጠኛ በሚያካሂደው በጸረ ትግሬው « ኢካድ ፎረም/ካረንት አፌርስ » ድረገጹ ዛሬ የተለጠፈው ደግሞ ካናዳ ውስጥ የሚኖሩ አንድ ኢትዮጵያዊ (የትግራይ ተወላጅ) ጳጳስ፤ ኤርትራ ጠላት መንደር ውስጥ ድረስ ሄደው « ለ21 አመት የኤርትራ ድምበር ጠባቂ » ሆነው እያገለገሉ ያሉት የተለያዩ ሻዕቢያ ያስታጠቃቸው ‘ምስኪኖች’ ኢትዮጵያዊያን (ከዚህ ጋር የተያያዘ አሰና.ካም
በተባለዉ የሻዕብያ ተቃዋሚ ራዲዮ ጣብያ ሮብዕ መጋቢት 23 ቀን 2001 ዓ.ም በፈረንጅ March 24/2009 ባስተላለፈዉ የዜና
ዘገባው ኢሳያስ ያስተላለፈላቸው ትዕዛዝ በኢትዮጵያ ሰማይ ብሎግ ዝርዝር መቅረቡ ይታወሳል) ታጣቂዎች በረሃ ድረስ ሄደው ያነጋገሩበትን አስገራሚ ቪዲዮ እንደተመከታችሁ ተስፋ አለኝ።
አባ ጰውሎስ ወዲዚያው ዘልለው ኢሳያስን አነጋግረው ነበር፤ ከተቃዋሚም እኚህ ጳጳፓስ ማን እንዳሳሳታቸው አላውቅም ኢሳያሰን ሄደው አነጋግረዋል (እስረኞች ሊያስፈቱ ሄደው ካልሆነ በቀር ድርጊቱ ለታጣቂዎቹ ለጉብኝት ከሆነ አስገራሚ ነው)። የነዚህ ምሰኪን ኢትዮጵያዊያን ወጣቶች በሻዕቢያ መንደር መታገል አሳዛኝ ገጽታው ቢሆንም፤ ያሳቀኝ ነገር ግን ‘ቪዲዮው ላይ አንዳርጋቸው ጽጌን ተመልክታችሁ የዚህ ጉደኛ ጸረ አማራ ተክለሰውነት እና የሻዕቢያን ተክለሰውነት የምታውቁ ሰዎች ስታዩ እንደኔ የሳቃችሁ ሰዎች ስንት ትሆናላችሁ ? እስቲ እጃችሁን አውጡ ! ወይ አገሬ !)

ዛሬ ሁለት ጉዳዮችን እነካካለሁ። ተቃዋሚው ክፍል እና ሚዲያው በሚመለከት። ተቃዋሚውም ሆነ ሚዲያቸው (ሁሉም አይመለከትም) የሚዘባርቁት ውሸት፤ ወገንተኝነት፤ አሳሳች ቅስቀሳም ሆነ አገርን እና ሰንደቃላማን በሚከዳ እና በሚያዋርድ መንገድ ሲጓዙ እየታዘብን ብንተቻቸው የጋራ ጠላታችን እንዳይጠቀምበት፤ጠላት ደስ አይበለው፤ እስቲ ዛሬስ እንታገሳቸው እያልን መተቸት የሚገባንን ትችት ጠልቀን ከመተችት የተቆጠብንበት ወቅት ብዙ ነው።
« ላይ ላዩን » ብቻ እየነካካን ከዛሬ ነገ ይሻላቸው ይሆን ስንል እያደሩ ቃርያ በመሆን ‘ማአዛ’ እያጡ መኮምጠጣቸውን ቀጥለውበታል። ለድክመታቸውም ሆነ አውቀው ለሚሰሩዋቸው አስነዋሪ ኢትዮጵያዊ የማንነት ክብር የሚያናንቅ ቅስቀሳ ሲያሰራጩ ሰምተው እንዳልሰሙ፤አንብበው እንዳላነበቡ የመቀጠሉ የይሉኝታ ባሕሪ ከእንግዲህ መቀጠል የለበትም።
በዚህ ርዕስ ተጠቅሜ ትችቴን ላነጣጥርበት የፈለግኩት ክፍል፤ እዚሁ ውጭ አገር አሜሪካ ውስጥ የሚገኝ « ኢሳት ቲቪ » ብሎ ራሱን በሚጠራ በዜና አውታር ላይ ነው።ወደ ርዕሱ ከመግባታችን በፊት ግን ስለ ሰሞኑ የወያኔ ተክለሰውነትን አንድ ብየ ወደ ዋናው ርዕስ
እሻገራለሁ።
የመለስ ሞት ተከትሎ የመጣው “የሙት ሹሞት ወራሽ » ሁላችንም እንደገመትነው ወያኔዎች ከሗላ « ቻዕ !!! ያዓውሽ !!!« እያሉ ከሚነዷቸው አጋሰሶቻቸው ውስጥ አንዱ እንደሚሆን የታወቀ ነበር። እንደተገመተው የመለስ ዜናዊ ቦታ «በመያዝ » ከድሮ በበለጠ ለወያኔዎች ጭነት ወገቡን አለጥልጦ በማመቻቸት ፈቃደኝነቱን ገልጾ የተቀበለው ሃይለማርያም ደሳለኝ ነው። ወያኔ ጫካ ውስጥ በነበረበት ወቅት « ደሳለኝ » የሚባል ከባድ ጭነት የሚሸከም፤ የአህዮች አለቃ ተብሎ “ብፃይ ደሳለኝ” በሚል ማአረግ የተሾመ ከወያኔ ታጋዮች ጋር አብሮ የሚጓዝ
‘ሲቆሙ የሚቆም ፤ ሲቀመጡ የሚንጋለል፤ ጠላት ሲመጣ « በማናፋት » ምልክት የሚሰጥ፤ ስናር አህያ ነበራቸው (ይህ አህያ አስገደ ገብረስላሴ ነው በወቅቱ በ $45 ብር ገዝቶ ወያኔ ገና እግር ሲተክል ለድርጅቱ መጓጓዣ እንዲሆን ያበረከተው) ። አጋጣሚ ሆኖላቸው ወያኔዎች ዛሬም ስልጣን ላይ ከወጡ በሗላ ‘የጫካው ደሳለኝን’ የሚተኩ በርካታ « የክልል ደሳለኞችን» አፍርተዋል። ጥላሁን ገሰሰ እንዳለው በመፈንቅለ መንግሥት በመገዳደል የመጡ እንደ « ሦስቱ አልማዞች » (ጀኔራል ተፈሪ ባንቲ፤ ኰሎኔል አጥናፉ አባተ እና ኰሎኔል መንግሥቱ ሃይለማርያም) ሳይሆኑ ‘የብፃይ ደሳለኝን‘ ቦታ ለመተካት ወገባቸው አለጥልጠው ለጭነት ከታጩት «የየክልሉ ደሳለኞች » ወስጥ ‘ብፃይ ደሳለኝን’ የሚተካ ወያኔዎች እና የወያኔ ጀሌዎች በትግርኛ እያቆላመጡ «ወዲ ደስ ደሳለኝ» የሚሉት የደሳለኝ ልጅ ማግኘታቸው በጣም አስገራሚ አጋጣሚ ነው።
ሦስቱ አልማዞች
አልማዝን አይቼ አልማዝን ሳያት
ሦስተኛዋ አልማዝ ብትመጣ ድንገት
ሁለቱም አልማዞች ብቅ ቢሉብኝ
ምርጫዬ ከምርጫ ተበላሸብኝ።
ሦስቱም አልማዞች ባያቸው ባያቸው
ይችም ያቺም አልማዝ ሁሉም አልማዝ ናቸው።
አልማዝን ከአልማዝ መምረጥ አቅቶኝ
ምክራችሁ ለግሱኝ ምርጫው ቸገረኝ።
(የግጥሙ ደራሲ አቶ ተስፋዬ ለማ ፤ ሙዚቃውን የተጫወተው ጥላሁን ገሰሰ)
ተብሎ የተገጠመው ለካ ‘የዝንጀሮ ቆንጆ’ ምርጫ ውስጥ ተገብቶ ለሕሊና የሚያስቸግር እንደዚህ ዓይነቱ ጉደኛ ዘመን ስላጋጠመ ነበር።
«በዚያኛው ተገርመን ብዙ ሳንቆይ
የዚህኛው መባስ አያስቅም ወይ ?
ይኸ ሁሉ ነገር ስንት ዘመን ኖሮ
በጣም ያስገርማል ጉድ አየን ዘንድሮ»
እንዲህ ያሉ የኪነት ባለሞያ ሰዎች ነበሩን። አሁን ያሉት
« አጋሰስ አዝማሪዎች እና ጋዜጠኞች» ከነዚያ ደፋሮች ጋር ስናወዳድር እነዚያ ድንቅ ከያኒዎች በተጠሩበት ሙያ መጥራት በጣም ይቀፋል።
በዛው ቆራጥ ትውልድ ያለፍን ቆፍጣና ትውልዶች የዛሬዎቹ ተቃዋሚዎች፤ከያኒው
ጋዜጠኛው….. (ሁሉም እንኳ ባይሆኑ) አብዛኛዎቹ በዚህ ፈታኝ ወቅት ፈተናውን ማለፍ አቅቷቸው ራሳቸውን በአጓጉል ትንተናዎች ሲሸፋፈኑ ማየት እጅግ ተስፋ አስቆራጭ ነው። የጣሊያን አስተዳደር ፖሊሲ (ሊገ ኦረጋኒካ/መሠረታዊ ሕግ/በሙሶኒ አገላለጽ) ተግባራዊ በማድረግ በቋንቋ/በጐሳ ከልሎ እያንዳንዱ የራሱ ብሔራዊ
« ባንዴራ » እንዲኖሮው ያደረገ «ግልገል ፋሺስቱ » መለስ ዜናዊ ሞተ ሲባል ተቃዋሚ ነኝ የሚለውም ሆነ በአጋሰስ ዓለም የተሰለፈው የኪነት ሞያተኛ ሁሉ ግማሹ ልቡ በሐዘን ሲታጠፍ፤ግማሹ ደግሞ በፍቅር ሰግጣ ይዛው የነበረቺውን ፍቅረኛው ድንገት ገፍትራ እንደተለየቺው
እስከሚመስለው ድረስ የመለስ ሞት ሰምቶ « ልቡ » ባዶ ክፍል ሆኖበት « ጭር » ባለ የናፍቆት ዓለም ተውጦ ሲተክዝ ፤ ለሐዘኑ መግለጫ ቃላት እስኪያጥራቸው
ሐረግ እና ቃላት ፍለጋ ዓይኖቻቸው ሲያማትሩ አስተውለን የኪነት ባለሞያዎች የታዘብንበት የሚገርም ዘመን ደርሰናል። የዘመኑ ጉደኛነት (ዊርድ ኢፖች/ ይሉታል ፈረንጆቹ) ለመግለጽ ቃላት ሊገልጸው አይችልም። የሚመቸው የጥላሁን ዜማ ነው።
«በዚያኛው ተገርመን ብዙ ሳንቆይ
የዚህኛው መባስ አያስቅም ወይ?»
በዚያኛዎቹ በመለስ ዜናዊ ሰበካ የተጠለፉ ምስኪን የኪነት ሰዎች እና ጋዜጠኞች ልቅሶ እና አሳፋሪ « ዋይታቸው »
ተገርመን ብዙ ሳንቆይ፡ በተቃዋሚው ጎራ የቆሙት የኛ ብለን የምንላቸው የዚህኛው ጎራ የኪነት እና የፖለቲካ ሰዎች በፋሺስት ግልገል መለየት ሰመመኑ ብሶባቸው ከመገረም አልፈን፤ሕዝብን
ከማሳወቅ አልፈን ምን እንበል ?
እውነትም ይኸ ሁሉ ነገር ስንት ዘመን ኖሮ፤ በጣም ያስገርማል ጉድ አየን ዘንድሮ» የሚለው ዜማ ለዛኛው ዘመን ብቻ ሳይሆን ለዚህኛው ዘመንም ገላጭ ስንኝ ሆኖ አግኝቼዋለሁ።
በየአዳራሹ ላንቃው እስኪታይ ድረስ ስሜተኛውን ታዳሚ እያስጨበጨበ የሚለፈልፈው
« ፍየል ተቃዋሚ »
በዚህ ጉድ ተይዞ ሲጋለጥ ማየት ‘ተቃዋሚ ነው ማለት አያስደፍርም’ ። በጣም የሚገርመው ግን ይህ አሳፋሪ ሞራል በውስጣቸው ዘንድ ሲከሰት እርስ በርሳቸው በሚዲያቸው አይወቃቀሱም። የዜና አውታሮቻቸው በወያኔ አልቃሽ ደጋፊዎች ብቻ ሲተቹ ይደመጣሉ። ተቃዋሚውም በወገንተኛነት/ቡድንተኛነት (ጎሰኛ) በሽታ የተለከፈ መሆኑንም ማስረጃ ነው።
የዜና እና የሐተታ ድረገጽና ራዲዮን አገልጋዮችስ ? ሻዕቢያ የወያኔ እንጂ የኢትዮጵ ጠላት አይደለም ብለው በመደምደም ከሻዕቢያ ጋር እየተሞዳሞዱ ሳያፍሩ በግልጽ የሕብረት አጀንዳቸውን አሳትውቀዋል።እስኪ እንፈትሻቸው።
ከላይ በመግቢያዬ የጠቀስኳቸው እነዚህ ቡድኖች/ግለሰዎች ከሻዕቢያ ጋር የተለያዩ ግንኙነታቸውን እንደተጠበቀ ሆኖ ፤ ሰሞኑን ደግሞ በጣም አድርጎ ያስገረመኝ ያበሳጨኝ
እና ያወከኝ ነገር ላውጋችሁ። ኢሳት የሚባል « የስእለ ድምፅ » የዜና አውታር (ተቃዋሚ እንዳልለው እራሱ
« ገለልተኛ የዜና አውታር ነኝ ስለሚል ፤ « የተቃወሚዎች የዜና አውታር « ብየ ልጠራው አልችልም እና «ገለልተኛ የዜና አውታር ልበለው»። ሆኖም ይህ የዜና አውታር እርሱ እንደሚቀደደው
« ገለልተኛ ነው ? » መልሱ በኔ እይታ « ወገንተኛ ነው »። ወገንተኛነቱ ለማን ነው ? የሚያናፋው ቱልቱላ በጥንቃቄ የተከታተልን ሰዎች የታዘብነው ነገር ቢኖር ብዙ ጊዜ ለኢትዮጵያ ጠላቶች ፕሮፓጋንዳ ስራ ሲሰራ በተጨባጭ አይተናልና ይህ ጣቢያ ‘ውሸታም፤ አድርባይ እና ለጊዜአዊ ጥቅም ብሎ የጠላት ፕሮፓጋንዳ ወደ ኢትዮጵያ ሕዝብ ጀሮ የሚያደርስ ጣቢያ ስለሆነ አገር ወዳዶች ጣቢያው አደብ እንዲገዛ
« ሀ » በሉት።
ተክለሚካኤል
አበበ/ተክሌ የተባለ የኢሳት ባልደረባ; ዓለም ያወቀው የሻዕቢያው ወረበላ መንግስት አጨብጫቢት ሶፊያ ተስፋማርያምን
በመጋበዝ የፕሮፓጋንዳ ስርጭት ማስተላለፉ ብቻ ሳይወሰን አዘጋጁም ከእንግዳው ጋር በመወገን የኢትዮጵያን ክብር እና ሉአላዊ መንደርን ለሻዕቢያ በሚወግን መልኩ ድጋፍ በመስጠት የአገራችንን ሉአላዊነትን የሚዳፈር ከወያኔ ቱልቱላ የማይለይ ለኤርትራዊያኖቹ
የሚደግፍ አጉዳፊ ቅስቀሳ አድርጓል። ይህንን ለማዳመጥ ESAT Insight Mrs Sophia
Tesfamariam 05 September
2012 (http://youtu.be/J2Yyj1GsZ7Q)
አድምጡ። ዝግጅቱ ስካሁን ድረስ 30 ሺሕ ሕዝብ አድምጦታል። አዘጋጁ እና ጣቢያው ምን አንድናገኝ ተብሎ ይህች በወንድሞቿ እና እህቶቿ ኤርትራዊያን ስቃይ የምትመረቅን የኢሳያስ ጃንዳ ወደ ጣቢያው ጋብዞ እንዳመጣት ባይገባኝም፤ ኤርትራ ድረስ እየሄደ እና እየመጣ ተከታቹን የሚያታልለው የግንቦት 7ቱ አንዳርጋቸው ጽጌ ፤ በበርሃኑ ነጋ አማካይነት ጣቢያው የሻቢያ ወዳጅነቱን ለማሳየት ያዘጋጀው መጥፎ/treasenous መድረክ ነው።

ብርሃኑ ነጋ የሚጨፍርበት ወደ 3000 የሚጠጉ ‘ምሰኪኖች’
ኢትዮጵያዊያን በየወሩ $20.00 እያዋጡ ያካሂዱታል የሚባለው ይህ ጣቢያ ያቀፋቸው ሰዎች (ሁሉንም አይመለከትም- አንዳንዶቹን
ነው) ለጊዜአዊ ጥቅም ሲሉ የአገራቸው እና የሕዝባቸውን አንድነት ቁም ነገር
ሳያስገቡ በጠላቶች ፕሮፓጋንዳ ተጠምደው ጠላቶች የሚነዙትን
ቅስቀሳ ተቀባይ እንዲኖሮው ወደ ሕዝባችን በአጎብዳጅነት ጸባይ ያስተላልፋሉ (የ ኦነግን፤የ ሻዕቢያን፤ ኦጋዴን፤…..ውሸቶቻቸውን፤ባንዴሮቻቸውን….እያውለበለቡላቸው
በስርጭቱ ይደሰኩራሉ/ይተባበሯቸዋል)። አጐብዳጆቹ ለአጎብዳጅነታቸው ሽፋን ሲሰጡ የሚሰጡት መልስ ”ጠላቶቻችን ናቸው አንበላቸው፤
እናስጠጋቸው፤ የጠላትን ቅስቀሳ በፕሮቮክ መልክ ደግፎ ማስተላለፍ ነውር የለውም፤…" በማለት በፖለቲካ የሽፋን መጠሪያ ስሙ “ፕሮቨካቲቭ ፖለቲካን መፍራት የለብንም” ይላሉ።
በመሰረቱ እንዲህ ያለ የሉአላዊ ክብርን በፕሮቮካቲቭነት ስራ ውስጥ የሚጠመዱ ሰዎች እና ቡድኖች/የዜና አውታሮች የቅጥረኛነት እና አጎብዳጅነት እንግሊዞች “ኮላቦራቶር” የሚሉት ባሕሪ ነው። ኮላቦራቶርም መብት ነው የሚሉ አሉ። ልክ የኢሳቱ “ፖለቲከኛ/አክቲቪሰት” እና “ተራቢው” ‘ለመለስ ዜናዊ ለምን አዘንክ ተብሎ ሲጠየቅ፤ ለምን አዘንክ ብለው ቅሬታና/እግዚኦታ ያስሰሙ ክፍሎች ልነግራቸው የምፈልገው ሌሎች የማልቀስ መብታቸው እንደሆነ ሁሉ እኔም ካለቀሱት ጋር አብሬ የማዘን መብቴ የተጠበቀ ነው” ምን ትሆኑ (የሌባ ዐይነ ደረቅ መልሶ ልብ ያደርቅ!) እንዳለን ሁሉ (ESAT Tamagne Beyene September 2012 http://youtu.be/xxE-v_t-Z-0 ) እና ሌሎቹ ባለመብቶችም “ምንም ቢሆን እንጀራ ቢያምራችሁም በየሱቁ እየሄዳችሁ የወያኔ እንጀራ አትግዙ!” እያሉ በራዲዮናቸው የሚቀሰቅሱ፤ ነገር ግን“አንድ ሚሊዪን ተኩል ብር የሚፈጅ ያማረ ቪላ አዲስ አበባ ውስጥ ማስራት አማረኝ” ብለው አዲስ አበባ ውስጥ የናጠጠ ቪላ ወኪሎቻቸውን “በወያኔ” አየር መንገድ (በጀርመን በጣሊያን በዓረብ አየር መንገድ እንጂ በወያኔ አየር መንገድ ወደ አገርቤት እንዳትጓዙ ብለው ቢቀሰቅሱም) እየተጓዙ ቪላ ማስገንባትም መብታችን ነው እያሉ እንደሚሉን ሁሉ “ኮላቦራቶሮችም” የጠላትን ወኪሎች ወደ መድረካችን ስንጋብዝ “ኩራት” ይሰማናል ማለትም “መብታችን” ነው ይላሉ። ('ወይለየኸ! ለካ ተሸሚምና ኢና' አለ ትግሬ/ እንዴ.. እንዴ! ይህ ሁሉ የመብት ጥበቃ ሲካሄድ ለካ ጀሮና ዓይናችን ተሸፍኖ ነበር፤ ወሬውም የለንም! ማለት ነው)።”እውነት እውነት እላችሗለሁ” አለ እየሱስ ክርስቶስ። ለካ ይሄ መብት የሚባል የማይታይ “ዓንደ ረቢ/ጐስት” ሁሉንም በየፈርጁ የሚያገለግል እምቢታ የማያውቅ ሁለገብ ዘበኛ ነው። እሺ ይሁን! ለመሆኑ “ኮላቦራቶር/ተባባሪ” ምንድነው?

‘ከሳንሆዘ’ ሲሰራጭ የነበረው ተወዳጁ
የኢጵያዊያኖች “ኢታር/ER” መጽሄት አጎብዳጅነት/አባሪ ተባባሪ ማለት ‘የዘቀጠ ፖለቲካ አድርባይነት ማለት ነው’ ይላል።
“Collaborationism is the worst form of political opportunism in which the
collaborator/s willingly participate in the destruction of their country….”
Collaborators can only aspired can become politically sub servant foot soldiers
for the enemy bent on annihilating
Ethiopia, and yet because of their block aspirations, their unscrupulous morals
and their convoluted conscience, they will do anything to achieve their fifteen minutes of fame.” ይላል።
ይህ ትንተና ሥልጣን ካለው ሃይለኛ ቡድን ጋር በመሞዳመድ ጊዜያዊ ጥቅም ለማካበት በአድርባይ የሚያታየው ባህሪ ነው። በሌላ
መልኩ ግን አንድ ደካማ የፖለቲካ ተቃዋሚ ድርጅት ወይንም ግለሰብ ደካማ አቅም ኖሮት ለማጥቃት የሚፈልገው ቡድን ማጥቃት ሳይችል
በሚቀርበት ወቅት ከሱ የበለጠ ጉልበት ያለው ሌላ ተቀናቃኝ ሃይል በመፈለግ (የጠላቴ ጠላት ወዳጄ/ከሰይጣንም/ከጠላትም ጋር ቢሆን
በሚል የኮሚኒስቶች ስልት እነ አርበኞች ግምባር እና ግንቦት 7….ከሻዕቢያ ጋር እንደሚሞዳሞዱት ዓይነት) ጥገኛ ሆኖ አገሪቷ ያስቀመጠቻቸው
መሰረታዊ መርሆዎች ለድርድር በማቅረብ፤ (ባያቀርብም) የተጠጋበትን ቡድን መርሆ እና ቅስቀሳ በማራገብ ወዶም/ሳይወድም ወደ አገልጋይነት
በመለወጥ፤ አገሬ ብሎ ወደ እሚጠራት አገር የሚኖር ሕዝብ ስለ እዛው ቡድን (ጠላት) በጎ ባሕሪ ወይንም የተለያዩ አጀንዳ የያዙ
የሰበካ ዘመቻ መልእክቶችን በማስተላለፍ በቀጥታ (እራሱ ጥገኛው) ወይንም በተዘዋዋሪ የተጠጋበትን የዛው አገር/ቡድን ጠላት “አፈቀላጤ”
በመጋበዝ ያለ አንዳች “ቁጥጥር”/ቻለንጅ ወደ አገሩ (ኢትዮጵያ) በማስተላለፍ በእኩይ ስራ ውስጥ ይሳተፍል።
የህች ማንነቷ ከድታ ጣሊያን የሰጣትን
‘ኤርትራ’ በሚል የዜግነት መጠሪያ ተቀብላ “ኤርትራዊት በሉኝ” የምትል የዞረባት ፍጡር፤ ምስኪን ኢትዮጵያዊያን የፈረንጅ ወለል
እየጠረጉ ባጠራቀሙት የገንዘብ መዋጮ በሚካሄደው በኢሳት ቲቪ ተገኝታ ስትነሰንሰው የነበረው ጸረ ኢትዮጵያ የውሸት ክምር ‘ማረም
ቀርቶ’ የክፍለ ጊዜው ዋና አስተናጋጅ የሆነው “ተክለሚካኤል(ተክሌ)አበበ የተባለው “ጸረ አማራ” (መረጃው ወደ ታች አቀርባለሁ)
የቅስቀሳዋ “ተባባሪ’ በመሆን የሻዕቢያ እምባ ጠራጊ እና አናፋሽ መሆኑን ‘የኢሳትን ግዴለሽነትና ላልበሰሉ ጋዜጠኞች መድረክ መለገሱ
አስገራሚ ነው።’
ይህች የሻዕቢያ ‘ገለባ” ዘሯን
ለማታውቁ ሰዎች ሁሉ የማን ዘር መሆኗን ብነግራችሁ በጣም ታዝናላችሁ። ይች ሴት የጀግናው ኢትዮጵያዊው የሓማሴኑ ተወላጅ “የዘርአይ
ደረስ” የቅርብ ስጋ (የእናትዋ አባት እና ዘርአይ ደረስ ወንድማማቾች ናቸው) ነች። አማርኛውን ስተረጉም ተሳስቼ እንዳልሆን በእንግሊዚኛው
ትርጉም ዘርአይ ደረስ “ግራንድ አንክል” ማለት ነው።ከዚያ ኢትዮጵያዊ የጀግና ሐረግ የተፈጠረች “ዘርና አገር አሰዳቢ” ግለሰብ
ነች። ዘርአይ ደረስ ማን መሆኑን እና ለኢትዮጵያዊነቱ ቀናኢነት እና በፋሺስቶች ላይ ምን ዓይነት አቋም እንደነበረው ታላላቅ ምሁራን
እና ሮማ ውስጥ በአካል አግኝተው ያነጋገሩት ኢትዮጵያዊያን የዘገቧቸው የታሪክ ምስክርነት ያነበባችሁ ሰዎች ስታገናዝቡ፤ ዛሬ “የፋሺስት
ባሕሪ የተላበሰው፤ ባሕረ ምድር/ኤርራን ወደ ወታደራዊ መደብር በመለወጥ የኤርትራ ወጣቶች በባሪያ ስርዓተ ማሕበር “አፍኖ” በመያዝ
ስደት፤እስራት፤ ጦርነት፤ ሞትና ሽብር በመዳረግ አዲስ የስቃይ ህይወት የፈጠረ ወንጀለኛው የኢሳያስ አፈወርቂ ስርዓት ተጣበቂ ሆና
ስትቀርብ በጣም አሳዛኝ ክስተት ነው። ያውም “ከ21 አመት” ነፃነትም በሗላ መሰረታዊ የተባሉት እንደ መብራትና ውሃ ለሕዝቡ መለገስ
እቅቶት በፈረቃ የሚከፋፈልበት ጨለማ አገር!!!!!
ታዲያ ለይህች ሴት ነች ተክለሚካኤል
አበበ በመደነቅ የሽፍቶች አገርና የራሷን ተቃዋሚዎች
አንድ ያላደረገች; ኢሳየስ 7 ገጠራማ አውራጃዎች ማስተዳደር አቅቶት የሌሊት መብራት እንኳ የሌላት ጭለማ “አገር”፤ ለኢትዮጵያዊያን እርዳታ እንድትለግሰልን ተክሌ ያለ ሐፍረት የጠየቃት። ያውም ከሷ ጋር መነጋገሩ ኩራት ተሰምቶት
“በኢሳት ቴ/ቪዥን አንችን ለቃለ መጠይቅ በማቅረቤ ከፍተኛ ኩራትና ክብር ይሰማኛል” በማለት ከሻዕቢያ አገልጋይ ጋር መነጋጋሩ
“ክብር” ተሰምቶት፤ወጣቱ ከድሰታው የተነሳ ከሻዕቢያ ማሕበረሰብ ጋር በመተባበር ለወደፊቱ የጭፈራ “ፈስቲቫል” እንደሚያዘጋጁ ምኞቱን
እና ፍላጎቱንም ቃል ገብቶላታል።
ይህ ተክሌ የተባለው ወጣት ማን
ነው? ካለይ እንደገለጽኩት (ካረንት አፌርስ ዋና አዘጋጅና
የኢሳት አዲስ ጋዜጠኛ ከመሆኑ ሌላ) ግለሰብ በተለያዩ ወቅቶች የሚጽፋቸውና በየራዲዮኑና/ፓልቶክ ሰለ የኢትዮጵያ ሉኣላዊነት የሚጻረር ቅስቀሳዎቹን በአገር ወዳዶች መፈተሽ አስፈላጊ ነው። ኦፖርቱኒዝም/አጎብዳጅነት (ኮላቦራቲዝም) በትከክለኛ ትርጉሙ ኢሳት ውስጥ በዚህ ወጣት ተንጸባረቋል።እኛ ሻዕቢያን የሕዝባችን ጠላት; ወገኖቻችንን የጨፈጨፈ ብለን ስንፈርጅ እነ ተክሌ እና ኢሳት ግን “ከሻዕቢያ ጋር የጋራ ፈስቲቫል” ለማዘጋጀት ምኞታቸውን ገልጸዋል።

ይህ ልጅ ኢሳት ውስጥ ተጠግቶ ለሻዕቢያ
እና ገንጣይ ቡድኖች ማቀንቀኑ ሰንደቃላማን ማንኳሰሱ ………ወዘተ…..ወዘተ ስንመለከት ብዙ ታሪክ ሸፋን ስለሚያስፈልገው ከሶፊያ ተስፋማርያም
ጋር ያደረገው ቃለ መጠይቁን አንብባችሁ ፍረዱ:: ይህ ልጅ ከላይ እስቀድሜ “በጸረ አማራነት” ለምን አንደፈረጅኩት እና ማን እንደሆነ
አሁን በአፕሪል 2011 ዓ.ም (በአውሮጳ ዘመን አቆጣጠር) (ቅንጅት ስዊዘርላን ከተባለው በቅርቡ የፋሺስቱ ወያኔው መሪ የመለስ
ዜናዊ አፈቀላጤ ወደ መሆን የተለወጠው ፓል ቶክ ክፍል)እና “ዓድዋ ለአረጋሽ አዳነ” በሚል ለወያኔዋ አረጋሽ አዳነ ነፃ እንድታወጣን በምትመረጥበት አውራጃ የሚረዳት የገንዘብ እርዳታ
እናድርግላት በማለት የጻፈውን እና ከአንደበቱ የተገኘ ጸረ አማራ ንግግሩን አስነብቤአችሁ ልደምድም።
የወጣት ተክለሚካኤል አበበ እና የወያነ ወይንም
ትግራይ ጠባብ ብሔረተኞች አጀንዳ እና ቅስቀሳ እንዴት እንደሚመሳሰሉ ለማነጻጸር እንዲመቻችሁ፤ መጀመሪያ በ60ዎቹ አካባቢ የትግራይ ብሔረተኞች ሲቀሰቅሱት የነበረው የአማራ ስም
ጥላቻ ምን ይሉ እንደነበረ በትግራውያን ልጀምር እና ከዚያ የተክሌን አባባል እወስዳችሗለሁ።
"...የትግሬ ጠቅላይ ግዛት
ትምህርት ቤት መምህራን እና ተማሪዎች የትግራይን ሕዝብ ብሔራዊ ማንነት የሸዋ አማራ ገዢ መደቦች አካሄድ እና የአገሪቱን አጠቃላይ
ጭቆና ለሕዝቡ በማሳወቅ እና ብሔረተኝነትን በማቀንቀን ዋነኛ ተዋናዮች ነበሩ። በተለይ ትምሕርት ቤት አካባቢ የባህል ክበባትን በማቋቋም
ተማሪዎች እና አልፎ አልፎ ወላጆች ስለ ትግራይ ብሔረተኝነት ስለ ሸዋ አማራ ልሂቃን አካሄድና አድልዎ በትግርኛ መናገርና መጻፍ
ምን ያህል የሕዝቡን ማንነት እንደሚያጠናክር እና እንደማያሳፍር...ወዘተ ይቀሰቅሱ ነበር። የአማርኛ ስም ለልጆች መሰየም እና መጥራት
መቅረት እንዳለበት ሕዝቡን እያዋዙ ይቀሰቅሱ ነበር።" (ጋላህቲ ሠጊ ገጽ 42)(ምንጭ የወያኔ ገበና ማህደር-
ደራሲ ጌታቸው ረዳ መስከረም 1/ 2004 ዓ.ም)
ተክሌ ደግሞ ያንኑን መፈክር በመድገም እንዲህ ይላል፡
““ግዛቸው፤ሃይላቸው፤ጌታቸው፤አለባቸው....የሚሉ አማራ ቀመስ ስሞች ከአመራር አስወግደን ይልቁንስ “አብርሃ ፤አጽብሃ፤ነመራ፤መረራ፤ነጋሶ…..”
የሚሉ ስሞችን የያዙ ወደ አማራር መተካትና ማምጣት አለብን”
(ተክለሚካል አበበ - የቀድሞ የአዲስ
አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ቦረድ ሰብሳቢ የነበረ ዛሬ በሰሜን ሜሪካ ኢሳት በተባለው ቲቪ ጋዜጠኛ፡ (የተናገረበት ቦታ እና
ወቅት ኤፕሪል 2011 ቅንጅት ኔዘርላድ ፓልቶክ ቃለ መጠይቅ ከተደረገለት የተገኘ)።
ሌሎች የተክለሚካል አበበ (ርዕሶቹ) ጽሑፎቹስ ምን
ይላሉ?
(1) “
የተሸነፍነው በትግራይ ነው፤ የምንድነውም በትግራይ ነው። አረጋሽ
ለአድዋ ፤አድዋ ለአረጋሽ….”(ዣንጥራር ተክሌ (ከቫንኩቨር ካናዳ)
(2) የምንድነው
በኤርትራ በቀር የኢትዮጵያ መዳን በማንም የለም! (ኢትየጵያን የምታድናት ኤርትራ እንጂ ኢትዮጵያ እራሷን የመዳን አቅም የላትም)
(3) አረጋሽ
አዳነ ጣይቱ ቡጡልን ብትሆንስ? ሚያዚያ 2000 ዓ.ም ምንጭ ኢትዮ ፎረም) ሰፋ ባለ ግልጽ ጽሑፉ እንዲህ ሲል ለኢትዮጵያ ሕዝብ
መልእክቱን እንዲህ ያስተላልፋል:
“የዛሬዋ መቶ አስራ አራት አመት አካባቢ ምኒሊክ ጣሊያንና ባንዳውን ሲረቱ ባለቤታቸው እቴጌ ጣይቱ ቡጡልም ጦር እየመሩ የድሉ ተካፋይ ነበሩ። እነሆ ዛሬም ታሪክ ራሱን ሊደግም ነው። ያኔ በታንክ ነበር አሁን ግን አረጋሽ በሾኬ ብላለች። ታንኩንም ቢሆን ገና በሃያዎቹ እያለች እኩያዎቿ ከተማ ውስጥ ሲዳሩ እሷ በጫካ አስኪዳዋለች። (አረጋሽን) ያልደገፈና ለብሩ የሰሰተ እጁንም አፉንም ይሰብስብ”። በማለት አረጋሽ ዳግማዊት ጣይቱ ለኢትዮጵያ መጥታለች እልል!! እልል!!!! በሉ ብሎናል።

ዛሬም ይህ የኢሳት ወጣት ጋዜጠኛ
'የኢሳያስ ተቃዋሚ ኤርትራዊያን ቡድኖች “የጭራቆች ፈስቲቫል” ብለው
በሚጠሩት በየአመቱ ሲዘጋጅ እየሄደ በሻዕቢያ ፈስቲቫል በመገኘቱ ደስታውን በመግለጽ የሻዕቢያዋ “ሶፍያ ተስፋማርያም” እና “አማኑኤል
በእደማርያም” ለተባሉ የኢሳያስ አረመኔ ግፍ ደጋፊዎች እያጎበደደ፤ ኢትዮጵያ እራሷ የመዳን አቅም ስሌላት ኤርትራ የምትመጸውተንን
የመዳኛችንን ምክር ጠይቋታል።
እንግዲህ ወዲህ እንደ እነ ተክሌ የመሳሰሉ በአፍቃሬ ሻዕቢያ ወኪሎች የተላለፈላችሁ ምክር በተለይ ደግሞ የአማርኛ ስም ያላችሁ ኢትዮጵያዊያን ትግሬዎችም ሆናችሁ ሌሎች ወደ መሪነት ወይንም ወደ መንግስታዊ ስለጣን እና ስራ ፍላጋ የምትፈልጉ ወጣቶች ካላችሁ በቅድሚያ ስማችሁ “ጐይተኦም፤ አብርሃ ፤ሐጎስ፤መረራ፤ጊዳዳ፤ፈሪሳ፤ደነቹ፤ፈይሳ……ወዘተ..” ወደ መሳሰሉት ስሞች ተሎ ካልቀየራችሁ የመምረጥ እና የመመረጥ ወይንም የመምራት መብታችሁ “በጠባብ ብሔረተኞች” ኮታ እንደሚታገድ ካሁኑኑ እንድታውቁት የድሮ የአዲስ አበባ ተማሪዎች ማሕበር መሪ የነበረው የዛሬው የኢሳት ጋዜጠኛ “ወጣት ተክለሚካል አበበ” አስታወቆአችሓል። አንለውጥም የምትሉ ካላችሁም ዓረብ አገር ሄዳችሁ “ስዒድ፤ጃዋር.ዓሊ፤ሙስጦፋ…” የሚለው የስም የለውጥ ግዳጅም ስለማይቀርባችሁ፤ መቀየር መቀየሩ ላይቀር እዛው አገራችሁ ባገራችሁ ልጆች ስም ወደ አብርሃ፤አጽብሃ እና ፈሪሳ ጊዳዳ እና ደነቹ ወደ ሚለው ቀይሩ። አማራ እና የአማራ ስም ካሁን ወዲህ “አይፈቀድም” ብሎ ወያኔ እንዳወጀው፤ በአባቴ የኦሮሞ ደም አለኝ የሚለን ተክሌ በሚመራት የወደፊቷ ኢትዮጵያ ከእንግዲህ ወዲህ ቦታ አይኖራችሁም።ውራጅ ፖለቲካ አገሩን አጥለቅልቆታልና ለወደፊቷ ኢትዮጵያ እዘኑ።የወያኔ አማርኛ እና አማራ ስም መጥላት አንዳይበቃን አነኚህ አዲስ መጤ ፖለቲከኞች በስማችን እንዲህ ሲያሴሩብን አይገርምም? አሁን አሁን በነዚህ ጅላጅል ተቃዋሚዎች እና ጎሰኛ ቡድኖች ፖለቲካው ተስፋ እያስቆረጠኝ ስለሄደ ሕሊናየ በግድ ነው እየነዳሁ እየመራሁት ያለሁት። በጣም ይገርማል። በነኚያ ስንገረም እነኚህ ደገሙን።

ተብሎ የተገጠመው ለካ ለዋዛ አልነበረም።
አመሰግናለሁ ጌታቸው ረዳ (ኢትዮጵያን
ሰማይ)www.ethiopiansemay.blogspot.com
Email getachre@aol.com