Friday, February 20, 2009

በሰማእታትና በሕዝብ ደም የፖለቲካ ቁማር (ካነበብኳቸዉ ) ክፍል 1 ከጌታቸዉ ረዳ
በቅርቡ ያስነበብኳችሁ የወያኔ ሰለባ የሆኑት ፊታዉራሪ ገዛኢ ረዳ እና የቤተሰባችን አባል የሆኑት በወያኔ ድብደባ እና በእሳት ተቃጥለዉ ጉልበታቸዉ በመድከሙ መንቀሳቀስ ባለመቻላቸዉ በእነ ሌ/ል ጀኔራል አበበ ተክለሃይማኖት (“ዑስማን” በመባል በሜዳ ስሙ ሚጠራ ፤ ወያኔ ስልጣን ከያዘ በሗላም ያለ ምንም ልምድ “የአየር ሃይል አዛዥ” አድርጎ ከሾመዉ በሗላ “ጆቤ” በመባል የሚጠራዉ የወያኔ ታጋይ ባሁኑ ጊዜ ያዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሕግ መምህር ሆኖ በደም የጨቀየዉ እጁ “ጠመኔ” ይዞ ሕግን በማስተማር ላይ ያለዉ ፤ለወደፊቱ በሕግ የሚፈለግ ወንጀለኛ እና አብሮት በግድያዉ እና እስረኞችን በማሰቃየት የሚታወቀዉ በሜዳ ስሙ “አዉዓሎም ወልዱ” ትከክልኛ ስሙ “ትኩእ ወልዱ” (የመለስ ታማኝ “የዓባይ ወልዱ/የሜዳ ስሙ “ዓባይ ዴራ” ታላቅ ወንድም የሆነዉ ወያኔ ኤርትራን ሲያስገነጥል “የኤርትራ አምባሳደር” በመሆን ተሹሞ በነበረበት ጊዜ ኢትዮጵያዉያኖች በሻዕብያ ግፍ ደረሰብን ብለዉ ሲጮሁ የአባቱ አገር የሆነችዉን “ኤርትራ” እንዳትወቀስበት በማዳላት ተስፋ ኣስቆራጭ መልስ ይሰጣቸዉ የነበረዉ ‘ዘረኛ እና ደሞቶራዉ” ግለሰብ ፤ ከወያኔ ተገንጥሎ… በቅርቡ ደግሞ “ዓረና” በመባል ሚታወቀዉ ያዉ የወንጀለኞች ሰብስብ “አረጋሽ አዳነን ጨምሮ” (ስለ አረጋሽ ካሁን በፊት በ7 ጥይት ተኩሰዉ ጫካ ዉስጥ ጣሉኝ ብሎ ወያኔን ያጋለጡ “ድያቆን ብርሃነ ገ/ሕይወትን በተያያዘ ጉዳይ ያቀረብኩትበን ሳትዘነጉ) የስበሓት ነጋን ምኞት እና የወያኔ ማኒፌስቶን በተግባር ለማዋል አንቀጽ39ን ቀዳሚ ፖሊሲዉ በማድረግ ከመሰረቱት ከእነ ገብሩ አስራት ጋር በመሆን ተቀዳሚ ምክትል ሊቀመንበር በመሆን በአንዳንድ ግራ በተጋቡ እና ተስፋ በቆረጡ ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን አይዟችሁ ባይነት ሽር ጉድ በማለት ስለዲሞክራሲ እና ስለ የትግራይ ሕዝብ መብት እና መጨቆን የበላይነት ሲሰብክ የሚደመጠዉ ግለሰብ ምክንያት ቤተሰቦቻችን በእነዚህ ግለሰቦች በእሳት እየተጠበሱ ለሞት አና ለአካለ ጎዶሎነት መድረሳቸዉ ያቀረብኩት ማሕደር ይታወሳል። ሆኖም ካለ “ዘሓበሻ” የተባለዉ የድረገጽ ጋዜጣ (ድሮ የመዲና አዘጋጅ የነበሩት ግሩም ኢትዮጵያዊ የሚዘጋጅ ) እና እንደዚሁም ኢትዮሜድያ እና አዲስ ድምጽ ራዲዮ እና ስሙን አሁን ለዘነጋሁት አትላንታ የሚገኝ ራዲዮ ጣቢያ በስተቀር “በተቃዋሚ ነት” የቆሙ 47 የዌብሳይት ባለቤቶች ዜናዉን ሰምተዉ እንዳልስሙ ገሸሽ በማለታቸዉ “ያልጠበቅነዉ” –“ወገናዊነት” የሚያንጸባርቁበት ጊዜ በማየታችን እጅግ ቅሬታችን ለማስተላለፍ እንፈልጋለን። ሌሎቹም የፓርቲ መሪዎቻቸዉ አና እዉቅ ዘፋኝ በወያኔ ስለታሰረባቸዉ መድረኩን 24 ሰዓት በማጨናነቅ ነጋ ጠባ ስለ እነሱ ብቻ ሲነግሩን ሌሎቹ በዝና ወይንም በመድረክ ያልታወቁ “ተራ” የትግራይ ኢትዮጵያዉያን ዜጎች እና አረጋዉአን ግን ለአንዳፍታ እንኳ በወያኔ የደረሰባቸዉ ግፍ በጨረፍታ እንደዜና በመድረካቸዉ ለማቅረብ አልተጨነቁም። ለምን? ለሚለዉ ጥያቄ የሚመልሱት ወግንተኞቹ ሲሆኑ መልስ ለመስጠት ይጨነቃሉ ባንልም በታሪክ ጉዞ ነን እና ዳመናዉ እየጠራ ሲሄድ አብረን መልሱ የምናዉ ይሆናል። ሌላ ቀርቶ “የሕግ ባለሞያተኞች ነን” “ሕግን እናስተምራለን” “ለተበደለዉ ለተጠቃዉ ወገናችን እንቆማለን፤እንከራከራለን፤ሃሳብ እንሰጣለን እናማክራለን” “ስለ ፍትሕ እንጮሃለን…..” በማለት ነጋ ጠባ ስለ ብርቱካን እና ስለ ተዲ አፍሮ ሕግ ማጣት ከገጽ ወደ ገጽ ከድረገጽ ወደ ድረገጽ መድረኮቹን በማጣበብ የሚጥፉ “የሕግ ምሁራን ኢትዮጵያዉያን” በዚህ አሰቃቂ በደል ደረሰባቸዉ የትግራይ ዜጎች ግን “ትነፍሽም” አላሉ! ለምን? የሚለዉ ጥያቄ መልሱን ለማግኘት ለወደፊቱ አብረን የምናየዉ ይሆናል። እነኚህ ወገኖቻችን ስለ ሕግ ሲጽፉ ለማን ነዉ የቆሙት? ለተራዉ ዜጋ፤ ወይስ ለታዋቂ እና ዝናን ላተረፉ ዜጎች? ወይስ ለማንም የተበደለ ዜጋ? የፓርቲ ፈቅር እና ሰብአዊ መብት በሕግ ፊት የተለያዩ መሆናቸዉ ሕግን ለተማሩ እና ሕግን ለሚያስተምሩ የሕግ ሰዎች ፤ -እኛ ሕግ ያልተማርነዉ ዜጎች ድክመታቸዉን ስናስረዳ “ሕግ” የተባለዉ ሰዉ ምንኛ ይታዘባቸዉ ይሆን? “ለዝናብ ደመና፤-ለሰዉ ልጅ ጤና” የተባለዉ የአበዉ ብሂል አለና ጤና ሰጥቶን ሁላችንም የመጨረሻዉ አቀበት ስንወጣ እንዘክረዋለን። በዚህ የፓርቲ እና ወገናዊነት ሩጫዉ ከቀጠለ “አቶ ወያኔ” ከመንበራቸዉ ይነሳሉ ማለት “የሚታሰብ” አይደልም። ጅቡ ከምሽጉ ሳይንቀሳቀስ ተቀምጦ እራቱን የሚበላበት ወቅት ያፋጥነዋል የሚል እምነት አለኝ። ለዛሬ በዚህ ልሰናበት እና ፣ከላይ የጠቀስኩትን “በሰማእታት እና በሕዝብ ደም የፖለቲካ ቁማር” የተሰኘዉ የወያኔ ባዓል “የካከቲትን” አስመልክቶ ሰሞኑን እንቃኛለን። ደህና እንሰንብት። getachre@aol.com http://www.ethiopiansemay.blogspot.com