Tuesday, April 10, 2012

የወያኔ አስካሪስ “አማራዎች ተባረሩ” ማለቱን ፈርቶ “ተፈናቀሉ” ቢልም ከዘረኛ ወንጀሉ ነፃ አያደርገውም! The above  photo is one of the Ethiopian well known mafia and corrupt criminal official and puppet of Meles Zenawi of Ethiopa  Mr. Shiferaw ShiguTe who is wanted for Amhara Ethnic Cleansing in Ethiopia by the International Human Rights Agency & Concerned Ethiopians all over the world 
The above photo is Mr.Meles Zenawi the ringleader of the Ethiopian mafia criminals who hate Amhara society

Ethiopian ethnic Amhara elderly man crying with horror for losing his family who were pushed alive to die to a cliff by the criminals Oromo Liberation Front and the criminal Tigray Liberation Front in Ethiopia.
የወያኔ አስካሪስ “አማራዎች ተባረሩ” ማለቱን ፈርቶ “ተፈናቀሉ” ቢልም ከዘረኛ ወንጀ ነፃ አያደርገውም!
ጌታቸው ረዳ
(408) 561-4836

በእራሴው እና በፕሮፌሰር አስራት ወልደየስ ጥቅስ ጽሑፌን ልጀምር። (በዛሬ ጽሑፌ ውስጥ በጣም ጠቃሚ መረጃዎች ስላቀረብኩላችሁ በጥሞና አንብቡት)።

የዘመን አቆጣጠራቸው እና የቀን ሰዓታቸውን በጌቶቻቸው በጣሊያኖቹ በፈረንጅ ዘመን የሚቆጥሩ የኤርትራ ባንዳዎችን “የውሸት ነፃነታቸውን” /መገንጠላቸውን/ የተቃወሙትና የከፋ ጦርነት ይቀሰቅሳል ብለው በትንቢታቸው የፈሩትን የኤርትራና የኢትዮጵያ ሕጋዊነት የሌለዉ ፍቺ አገሪቱን ባስጨነቀበት ሰዓት፤ ፕሮፌሰር አሥራት ወልደየስ በርካታ ዓመታት ባገለገሉበት ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል በወያኔ እስር ቤት ቁጥጥር አልጋ ላይ ታመው ተኝተው ሲተክዙ፤ ፕሮፌሰር አሥራት ወልደየስ ለፈረንጆች የሰጡትን ቃለ ምልልስ በማስታወስ ፤ “ወያነ ትግራይ” በማለት ራሱን የሚጠራ ይህ የሙሶሎኒ ተማሪ “የጎሳ ፌደራል አስተዳደር” ብሎ ያዋቀረው የጣሊያኖች መስተዳድር ቅርጽ በማቺ ማንጂ ውስጥ አማራው ለጥቃት የዳረገው ምክንያት የአስተዳደሩ አወቃቀር ፖሊሲ እንደሆነ የፕሮፈሰሩን ቃለ መጠይቅ ቀንጨብ አድረጌ በማስተዋስ  ጽሁፌን  ልጀምር።

“The foundation of federal structure is a nation divided along linguistic, ethnic, and religious lines in the name of democracy. We believe that a federal structure of regional administrations that are based on national unity, sovereignty, equality, economic and social benefits, and popular consent will be useful for advancement. But installing a federal government without foundation and especially at a time Ethiopia is being wrecked is like constructing a house in the midst of a violent earthquake. Even the much-lauded American federal system of government had to engage in civil war to ensure national unity…” (Professor Asrat)
“ዘረኞች ሕዝብን የሚያታልሉበት ዓይነተኛ መንገድ “ውሸት”ነው። ሲዋሹ እንደ ተራ ሰው ሳይሆን ዘረኞች ሲዋሹ እስስቶች ስለሆኑ ውሸታቸው እንዳይታወቅባቸው የሚሰፍሩት ውሸትና እውነት እንደ አድማጮቹ ባሕሪ የመለዋወጥ ባሕሪያቸው ያስተካክላሉ። የዋሹትን እና የተሳደቡትን ዘረኛ ስድብም ይሁን ወንጀለኛ ፖሊሲአቸው በሌሎች ላይ በማስታከክ የገዛ ራሳቸወን ወንጀል የመጫን ችሎታቸው የላቀ ነው። ስለሆነም አድማጮች የትግል እና የንባብ ልምድ ከሌላቸው በቀላሉ የነዚህ ሰለባ ይሆናሉ።……..”    
(ዘመን ይለወጣል ዘረኞች ትተውት የሚሄዱ አሻራ ግን አይለወጥም! ጌታቸው ረዳ Septemeber/11,2011) http://ethiopiansemay.blogspot.com/2011/09/blog-post_11.html

ከላይ የተመለከተው ጥቅስ በተመለከተው ርዕስ በተጠቀሰው ቀን እና አመት ስጽፍ እንዲሁ ለምክንያት አልነበረም።ካሁን በፊት መለስ ዜናዊን ዘረኛ ፖሊሲ የተቃወሙ ኢትዮጵያዊያንን ለይቶ በስማቸው እና በቀለማቸው  “ጐሳቸውና እና የቆዳ ቀለማቸው” ጠቅሶ በድረገጹ ለፖለቲካ መጠቀሚያ በማድረግ በካርቱን እና በጽሑፍ የለጠፈ የመለስ ዜናዊ  አገልጋይ ድረገጽ የሆነው “ዓይጋ ፎረም” ተብሎ የሚጠራው፤ ስለ አማራዎች ከቤንጂ ማጂ  ደቡባዊ ኢትዮጵያ ግዛት መባረር (መፈናቀል ይለዋል ወያኔ) ጉዳይ አስመልክቶ “ከጉራፌርዳ ወረዳ በሺዎች የሚቆጠሩ የአማራ ክልል ተወላጆች እንደተፈናቀሉ ተደርጎ የሚናፈሰው ወሬ መሰረተቢስ ነውhttp://aigaforum.com/news/no-one-has-been-uprooted.php በሚል ርዕስ ዛሬ ጥዋት ‘ጌቶቹ” የዋሹበትን የውሸት መግለጫቸው ለሕዝብ እንዲነበብ ለጥፎታል። ቻይና ወይንም ጀርመን ወይንም ሂላሪ ክሊንተን ከመለስ ዜናዊ ጋር “ተጨባበጡ” አርዳታ ተለገሰልን…….ወዘተ ማለቱ በድረ ገጻቸው ለጥፈው እጅግ የሚያኮራቸው አስቂኝ የአሽከርነት ፕሮፓጋንዳ የሚያራግቡ ራዲዮኖቻቸው እና ተመሳሳይ የሆኑ የትግራይ ወያኔ አንጨብጫቢ  አሽከር ድረገጾች ሁሉም ከጌቶቻቸው የተላከላቸው የውሸት መግለጫ “ከክርስቶስ’ የተላከ ከሰማየ ሰማያት የተላከ እውነት ያዘለ መግለጫ መስሎአቸው ለጥፈውታል/አስተጋብተውታል ። 

ወያኔ የተጠቀመበት የአማርኛ ቃላት “መፈናቀል” የሚል ነው። መፈናቀል ማለት “በመሬት መንቀጥቀጥ፤ እሳት፤ሃይለኛ ነፋስ፤ጐርፍ፤ድርቅ እና ጦርነት” ምክንያት ከሚኖሩበት አካባቢ ወይንም ቤት ተፈናቅለው ለድህንነታቸው ሲባል ወደ መጠለያ ለሚወሰዱ ግለሰቦች/ማሕበረሰብ የሚገልጽ ቃላት ነው። ወያኔ የሲ.አይ.ኤን የጦርነት የስላላ ሳተላይት እርዳታ እና ምክር ተጠቅሞ ባገኘው ድጋፍ ከሕዝብ በነጠቀው መንግስታዊ ስልጣን ተጠቅሞ እነ ኸርመን ኮኸን የሰጡትን መንግስታዊ ስልጣን “

(የኢሳቱ አበበ ገላው የሲ አይ ኤው መኮንን አይሁዳዊው “ሚሰተር ኮኸን ኸርመን” ቃል አምኖ “ሲ አይ ኤ”  ወያኔ ወደ ስልጣን እንዲመጣ እጅ የለበትም፤አልተካፈለበትም ብሎ በየእሁዱ ክ/ጊዜ ኢሳት ቲቪው ቢቀደድም። ከመንግስቱ ሃይለማርያም ወደ ዝምባቡዌ በሰላም መሸጋገርን ጀምሮ እስከ ህወሓት ስልጣን መረከብን መርዳት የሲ.አይ.ኤ. እጅ  እንደነበረው ብዙ ጌዜ ሰነዶችን እና የተላያዩ አገሮች ያደረጉትን ስብሰባዎች የተደረጉበት ቦታዎችን በመረጃ ካሁን በፊት አቅርቤአለሁ።የብስራት አማረ መጽሐፍም አንብቡት።ወያኔ የመንግስቱን መሄድ ዝግጁነት ከ6 ወር በፊት እንዴት አውቀውት እንደነበረ አንብቡት።የአሜሪካን ሲ አይ.ኤ. ኰለኔል መንግስቱ ወደ ዝምባብዌ ከመሄዱ በፊት ቀለቡን እና መኖርያውን በሚመለከት ለሮበርት ሙጋቤ ምን ብለው ቃል ገብተውለት እንደነበር የሙጋቤ ቃለ መጠይቁን አስታውሱ።)

አማርኛ ተናጋሪ የሆኑትን “ቤንቺ ማጂ” ተብሎ ከሚጠራ የኢትዮጵያ ግዛት እንደፈናቀሉ ብቻ ሳይሆን “እንዲባረሩም”፤ ሲወጡ ደግሞ “ተደብድበው” "ንብረታቸውን ተነጥቀው" ነው። የወረበላው መንግስት አገልጋዮች ሌላው ዘዴአቸው ደግሞ ከመባረራቸው በፊት እየተደበደቡ እና እየተሰደቡ በብስጭት በፈቃዳቸው እንዲለቁ ተንኮል ይጎነጉን እና እንደገና ተቋቁመው የቆዩት ደግሞ በጅምላ ያባርር እና እንደገና ምስጢሩ ለመደበቅ ሲል አለፍ በገፍ/በጂምላ እንዳይባረሩ እና ወንጀሉ እንዳይጋለጥበትም የራሳቸው “ተከላካይ ጠበቃ” ሳያቆሙ “እን በእን በየተራ” በራሱ ፍረድ ቤት እየጠራ በራሱ ዳኛ እና ፌርማ፤ ንብረታቸውን ተነጥቀው፤ ጡት የሚጠቡ ህፃናት ጭምር እንዲወጡ አድርጓልማወቅ ያለብን በመፈናቀል እና በመባረር ልዩነት አለው። የተፈጥሮ አደጋ ሳይሆን ያፈናቀላቸው፤ “መንግስታዊ ጉልበት” የተጨመረበት፤ትዕዛዝ ተሰጥቶ ነው እንዲፈናቀሉ ምክንያት የሆነው።


Read on my new book what the above TPLF magazine talks about Amhara society. Then you will be able believe and compare why the BenjichMaji Amhara deportation is all about.
ወያኔ አማራውን እንደ ዓይነተኛ እና ደመኛ ማዕከላዊ ጠላት አድርጐ በፖሊሲው፤በዘፈኑ፤በትያትሩ፤በፓርላማው ስብሰባ እና በመጽሐፍ መልክ እየታተሙ ጸረ አማራ ዘመቻ እና ጥቃት የተካሄደው 37 አመት ሆኖታል።። የቅርቡ የቤንቺ ማጂ ከጉራፌርዳ ወረዳ  የተባረሩ አማራዎች ጉዳይ “በሕጋዊ ዜጋ እና በሕገወጥ ዜጋ” የቃላት ጨዋታ ገብቶ ወንጀሉን ለመሸፋፈን ቢጥርም ከተባረሩት አማራዎች ቃል እና እሮሮ፤ ከደረሰባቸው ጥቃት፤ድብደባ እና ዘረኛ ስድብ ምንጩ፤ዓይነቱ እና የግፉ ክብደት ለማወቅ ከገለልተኛ የዜና መረጃዎች እና በወያኔ ሚዲያ ውጭ የተላለፉት መረጃዎችን ልዩነታቸው እና የአዘጋገብ ጥልቀታቸው መመርምር ያስፈልጋል። የተባረሩት አማራዎች ለነጻ ዜና ዘጋቢዎች የሰጡት ቃል፤ “ለዘረኛ ፖሊሲ የሚመጥን፤ በአማረው ላይ ያነጣጠረ ጥቃት” መሆኑን በሕግ ፊት ማስረገጥ ይቻላል። እንኳን እና የሕግ ምሁራን ቀርቶ እኛ ተራ ዜጎችም ቃላቶቹ እና የደረሰባቸው የሕሊና ጫና እና የአካል ድበደባ፤የንብረት ዘረፋ፤ እንዲሁም የተባረሩት ሰዎች አያያዝ፤ ከሕግ አኳያ “የዘረኛ ፖሊሲ ውጤት” መሆኑን በግልጽ ማየት ችለናል።

““ከጉራፌርዳ ወረዳ በሺዎች የሚቆጠሩ የአማራ ክልል ተወላጆች እንደተፈናቀሉ ተደርጎ የሚናፈሰው ወሬ መሰረተቢስ ነው” የሚለው የወያኔ መግለጫ ስታነብቡ ምን ትዝ አላችሁ? “የወያኔ ገበና ማህደር” ከሚለው አዲሱ መጽሐፌ  ለታሪክ እንዲሆን ያሰፈርኩትን መረጃ ወደ ቀድሞ የወያኔ ተመሳሳይ የውሸት መግለጫ አንዴ ልውሰዳችሁ እና ያ ውሸት እና ይህኛው እንዴት እንደሚመሳሰል ላስረዳ።

በትግርኛው ምሳሌ ልጀምር፤- “አናፍራ ቆቓሕ ዘይፈልጥ አይሃዳንን” (“ቆቅ እንዴት እንደ እምትበር የማያወቅ አዳኝ፤ “አዳኝ አይባልም” ) ይላሉ ትግሬዎች። ሃያ አመት ሙሉ የወያኔ ከወንጀል የማምለጫ  ዘዴውና ተከታታይ የውሸት ባሕሪውና መግለጫዎቹ ያላጠና ዜጋ “ወያኔ ማን መሆኑን” ሊያውቀው አይችልም። ካሁን በፊት ኢትዮጵያውያን ከኤርትራ ሲባረሩ ዋናው ባንዳ መሪያቸው ምን ብሎ ነበር? ባንዳው የሚመራው ‘መንግስት’ ተብየው የሰጠው መግለጫስ ምን ብሎ ነበር?” የስነ አእምሮ ተመራራማሪዎችና የሕግ ባለሞያዎች እንዲሁም ተራ ዜጐች ከዚያ የውሸት መግለጫው ከቤንቺ ማንጂ የተባረሩት አማራዎች ተማሳሳይ መንግስታዊ ውሸት ምን መገንዘብ እንደምትችሉ ይኼው ላስታውሳችሁ?
ግፋ እያሉ በመሃል አገር አካባቢ የሚናፈሱ ጎጆ አስማሚዎች ተበራክተዋል። የኤርትራ ጊዜያዊ መንግሥት የወሰደው እርመጃ አሉባልታዎች በመዛመት ላይ ይገኛሉ።"  (ልብ በሉ! የተፈጸመው የግፍ እርምጃአሉባልታ” ብሎታል።)

"1983 ዓ.ም. በኤርትራ በነበረ ሁኔታ የመንግሥት ለውጥ ሲደረግ የኤርትራ ሕዝብና መንግሥት በተለይም ሻዕብያ እዚያ የነበርነው ኢትዮጵያውያንን በከፍተኛ ግፍና በደል ነው ያባረረን። ይኸውም በጥይትና በዱላ እየጨፈጨፈ ነው ከሀገሩ እንድንወጣ ያደረገን። “ኤርትራ ለኤርትራውያን!” “ኢትዮጵያውያን ከአገራችን ይውጡ!” “እስከዛሬ የተቀመጣችሁት ይበቃል” ፤ “በሀገራችን ላይ ሀብትና ንብረት አፍርታችል”፤ “ጆንያ እንኳን መያዝ አትችሉም።” በማለት እየጠፈጠፉና እየደበደቡ ነው ያስወጡን። ትንሽም ንብረት የያዘውን ሰው ቪድዮ እያስነሱና መኪና ላይ ከተጫነ በረሃ ላይ ሲደርስ አውርደው ባዶ እጁን ነበር የሚያባርሩት። እና ባገራቸው ላይ ከውስጥ ብረት ከላይ ጎማ በለበሰ ዱላ ነበር የሚጨፈጨፉን። “አህያ የጦር ሠራዊት ልብስ አልብሰውየጦር ሠራዊት ጫማ አድርገውለትቼ’ውሽ’ እያሉ ለኛ ለኢትዮጵያዊያኖች አሕያውን እያሳዩን ነበር የሚደበድቡን። …”

·… እና በግፍ በመከራ በሞት ነው የወጣነው። በአሁኑ ሰዓት ተርፈን ያለነውን ነው እዚህ የምታዩን። በዚያ ሰዓት የተሰራው ግፍ ይህ ነው አይባልም። ያለ ቀለብ ሦስት አራት ቀን ሜዳ ላይ እንድንቀመጥ ከተሰቃየን ነበር እየጨፈጨፉ የሚያባርሩን። ስለዚህከዱላና ከጥይትየተረፈው መንገድ ላይ እየንተጠባጠበ እንዲሞት የሚያዳክሙበት ዘዴ ነበር። ሕዝቡ አየዘፈነበስድብ በዱላእየደበደበን፤ የ10 ዓመት ልጅ የወደቀ ክላሽ አንሥቶ ነበር ሰው የሚገድለው።
እና በዚህ ሰዓት እናት አባት ልጅ እህት ተለያይተው በየሜዳው ላይ ነው የቀሩት። እናት ህፃን ልጇን ታዝላ ስትሄድ ከመንገድ ርቀትናአሳሩ ከምሬቱ የተነሣልጇን እንደ እንሰሳ እዚያው ጥላ” ከበረሃ በስቃይ ነው የወጣችው። እና ብዙ፣ ብዙ ግፍ ነው የተሰራው።


በተለይም የጦር ሠራዊት ቤተሰብ ከሆነ ከተማ ውስጥ እያዞሩ ላው ህጻናቶች እየዘፈኑ ምራቅ እየተፉበት እየተዋረደ በዱላ እየተደበደበ ነበር የወጣው። ከሰው ልጅ የማይጠበቅ ከእንሰሳ ያልተሻለ አስተሳሰብ የነበራቸው ያን ጊዜ ነው። ሲማቱ አንገት እግር እጅ አይሉም ዝም ብለው ነው ያገኙበትቦታ ላይ ብቻ "አድጊ" ትግሬውን "ቅማላም" አማራውንአህያ” እያሉ ነበር።  በዚያ ሰዓት አርምጃው ሁሉም ኢትዮጵያዊ ላይ ነበር፡በተለይም በመጀመሪያው ወቅት። በተለይ ትኩረት ተሰጥቶት የነበረው በአማራው እና በትግሬው ቤተሰብ ላይ እንዲሁም በሠራዊት ቤተስብ ላይ ነበር። አጋሜዎች አውጡልን! ነው ያሉት ገና እንደመጡ። ከፍተኛ ጥላቻ ነበራቸው። ጥላቻቸው ደግሞ ከሻዕብያ አቀራረጽ የመጣ ነው። ሕዘቡ ተቀርጿል። በተለይም ወጣቱ ክፍል። ወጣቱ ክፍል ገና ሻዓብያ ወደ ከተማ መምጣቱ ሲቃረብ ነው ጥላቻው የታየው። ምፅዋ ከተያዘ ጀምሮ ጥሩ አመለካከት አልነበራቸውም። የጅምላ "ውጣ!" ነበር።” (ከኤርትራ የተባረሩ ኢትዮጵአዊያን፤በተለይ \አማራዎች ከሰጡት ቃለ ምልልስ ከሪፖርተር ጋዜጠኛ ዘገባ የተገኘ ፤ በራሴው የወያኔ ገበና ማህደር መጽሐፌ ለታሪክ ዘግቤ ያሰፈርኩት መረጃ የተገኘ)

የባንዳዎቹ መሪ የመለስ ዜናዊ ግን የፖለቲካ ውሽማው የነበረው የኢሳያስ አፈወርቂን በአማራውና መሰል ኢትዮጵያዊያን የፈጸመው ዘር የማጥፋት ወንጀል ለመሸፈን ሲል፤ ትንሽ እንኳ እንደ አገር መሪነቱ ስቅጥጥ ሳይለው፤ሳያፍር፤ እንደ ሻዕቢያ አፈቀላጤ ተወክሎ በእናቱ አገር በኤርትራ ሕዝብ ላይ ወንጀል እና ግፍ የፈጸሙ፤ የእናቴን አገር ኤርትራን የዘረፉ ቀማኛ ወንጀለኞች ብቻ ናቸው የተባረሩት ብሎ  ለሚወነጅላቸው አረጋዊያን ፤ህጻናት እና ግፍ የተፈጸመባቸው ኢትዮጵያዊያን ቤተሰቦች እንዲህ ሲል ወንጅሏቸው ነበር።  ይሄው አድምጡ፡

 "የኤርትራ ጊዜያዊ መንግሥት ከሰብአዊነት ውጭ የሆነ እርምጃ እንደወሰደባቸው አስመስለው አቅርበዋል። በኤርትራ ውስጥ በደርግ ሥርዓት ተልእኮዎቹን ሊያስፈጽሙ በተላኩ ሃይሎች በሕዝቡ ላይ (በኤርትራኖች) የደረሰውንበደል” ወደጎን” ትተው ብዙ ሰው ከጥፋቱእንዲድን” ተብሎ የተወሰደውን  በጎ እርምጃአጥላልተው” አቀርበውታል።"

“"ከኤርትራ ወደ ኢትዮጵያ የመጡት ወታደሮች የደኅንነት ሠራተኞችና የተስፋ /ኪዳን የማፍያ ቡድኖች እንደመጡ የመጠለያ እና የምግብ ችግር ለጥቂት ጊዜ አጋጥሟቸዋል።"
"አብዛኛዎቹ ከደርግ ሥርዓት ጋር ባንድ ወይም በሌላ መልኩ የተነካኩ ስለነበር ደርግ ይሰራበት የነበረውን ፖሊሲ በእምነትም በግድም ተቀብለው የቆዩ ናቸው። የደርግ ተልእኮ ለማስፈጸም ተንቀሳቅሰውበሕዝቡ ላይ በደል ያደረሱ ናቸው”። ይህ እርምጃ በተወሰደበት ጊዜም ምናልባት ተባረርን የሚሉ አንዳንዶቹሕጋዊ ባልሆነ መንገድከሕዝብ ላይ የወሰዱት” ሀብት ንብረት ቀርቶባቸዋል። ባንድ ወይም በሌላ መልኩ የኤርትራ ጊዜዊ መንግሥት ያባረራቸው የኤርትራን ሕዝብ የበደሉ ብቻ ናቸው" (መለስ ዜናዊ የወቅቱ የወያኔ ድርጅት እና የወያኔ የሽግግር መንግሥት ሊቀመንበርና ፕረዚዳንት- በወቅቱ ለራሱ ጋዜጠኞች ከሰጠው ቃለ መጠይቅ የተወሰደ። ምንጭ የወያኔ ገበና ማህደር - ደራሲ ጌታቸው ረዳ)

ቅማላም አጋሜ"፤ "አድጊ-አምሓራይ" እየተባሉ ግፍ የተፈጸመባቸውን በሺዎች የሚቆጠሩትን ግፍ የፈጸሙ ወንጀለኞች ወይንም "ዘራፊዎች" ብሎ ዜጎቹን ሲሰድብ፤ የኢትዮጵያ ሕዝብ ምን ይለኛል የማይል፤ “ስድ አደግ’ “በጣም ሲበዛ ዋለጌነቱ መረን የሌላው” “የወላጆቹን ባሕል ያለ ገደብ የሚያንቋሽሽ፤ አረጋዊያን እና እናቶችን የሚዘልፍ”፤ ያጫካ ሕሊና ያሳበደው፤ ይህ ጋጠ ወጥ ሰው፤ ያውም ለኢትዮጵያ ሕዝብ ደህንነት ለመጠበቅ ጥብቅና ለመቆም ቃል ገብቻለሁ ብሎ  ከሚል ፤ ኢትዮጵያዊ መሪ ወይንም “መንግሥት ነኝ” ብሎ ከሚናገር እንዲህ ያለ ንግግር የሚናገር “የጠላት ጠበቃ”፡ የኛ ወገን ነው ብሎ አምኖ ለማለት በጣም ያስቸግራል። በታሪካችንም ይሁን በተቀረው የሌሎች አገር ታሪኮች ዜጎቹን በእንዲህ የሚዘልፍና የሚወነጅል ከጠላት ጋር የሚያብር መንግሥትና መሪ ታይቶ ተሰምቶም አያውቅም። በዓለም ታሪክ ውስጥ ያልተሰማ አዲስ ክሥተት ነው። (ምንጭ እንደላይኛው)።

የተባረሩት ዜጎች ደግሞ ለባንዳው ስርአት ባለስልጣኖች እና ለመለስ የሰጡት መልስ እንዲህ ሲሉ በምሬት እውነቱን አጋልጠው እንዴት ይዋሽ  እንደ ነበር የሚከቴለውን አንብቡ፡
“ኤርትራ ከኢትዮጵያ ጋር ፍቅር በነበረችበት ወቅት ኢሳያስ አፈወርቅ አዲስ አበባ መጥተው በነበረበት ወቅት ኤርትራ ያፈናቀለችው ሰው የለም፡ ሲሉ የኛም ባለሥልጣኖችምትክክለኛ ናቸው’ ብለው ነበር ያረጋገጡላቸው። ለምን ይዋሻሉ? ሲፈልጉ የሰው አገር ልትዘርፉ ነውሄዳችሁት ይሉናል። ሲፈልጉ ወራሪዎች ናችሁ ይሉናል። ትላንትና አንድ የነበረ አገር ነው። ቪዛ የማይጠየቅበት ፤ ፓስፖርት የማይጠየቅበት አገር ለምን ሄዳችሁ እንዴት እንባለላን? እና በጣም ነው የሚያሳዝነው።”  {ኤርትራ ነፃ አገር ከተባለች በኋላ ኢትዮጵያውያን ይውጡ ተብለው ከኤርትራ የተባረሩት ኢትዮጵያውያን ካሰሙት እሮሮ የተቀነጨበ። ምንጭ የወያኔ ገበና ማህደር ገጽ 346 ደራሲ ጌታቸው ረዳ}

“ኤርትራ ከኢትዮጵያ ጋር ፍቅር በነበረችበት ወቅት ኢሳያስ አፈወርቅ አዲስ አበባ መጥተው በነበረበት ወቅት ኤርትራ ያፈናቀለችው ሰው የለም፡ ሲሉ የኛም ባለሥልጣኖችምትክክለኛ ናቸው’ ብለው ነበር ..” የምትለዋ ሐረግ እና  ከበንቺ ማጂ ውጡ ተብለው የተባረሩ አማራዎች የወያኔ መግለጫ ስታስተያዩት ከወረዳው የተፈናቀለ ሰው እንደሌለ አቶ ሽፈራው መግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል ከሚለው የክሕደት መግለጫ ጋር ተመሳሳይነቱን ተመልከቱት። የሚከተለውን ጉድ ደግሞ ተመለክቱልኝ፦
የመለስ ዜናዊ ‘ጭራና ጀንጥላ” ያዥ የሆነው ዓይጋ ፎረም የተባለው ድረገጽ እንዲህ ሲል የጌቶቹን የዘር ማጥፋት ዘመቻ ወንጀል ለመደበቅ ከጌታው ከመለስ ዜናዊ ያገኘውን ትምህርት ቃል በቃል የተማረውን እንዲህ ሲል ተከላክሎለታል።The usual media outlets that will leave no stone unturned to defame the Ethiopian government have been fanning the issue like there is no tomorrow!” ጌታው መለስ ዜናዊ ደግሞ ምን ብሎ ነበር? አንብቡት

ግፋ እያሉ በመሃል አገር አካባቢ የሚናፈሱ ጎጆ አስማሚዎች ተበራክተዋል። የኤርትራ ጊዜያዊ መንግሥት ከጥፋት ለመከላከል የወሰደው በጐ እርመጃ አሉባልታዎች በመዛመት ላይ ይገኛሉ።”"የኢትዮጵያ የሽግግር መንግሥትና የኤርትራ ጊዜዊ መንግሥት የሚወስዷቸው ገንቢ እርምጃች የሚያጥላሉበት ጉድለት ቢያጡባቸው በበሬ ወለደ ቅጥፈት ተሰማርተዋል።"
(እዚህም ልብ በሉ፡  የኤርትራው ህዝባዊ ግምባርና ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ መንግሥቶች ሰማይ እና ምድር ተሸክሞ የማይችለውን የገዛ ወንጀላቸውን ደብቀው “እንከን/ጉድለት የለሽ” መንግሥት ብሏቸዋል።)  በተባረሩት ሰዎች አንደበት የተደመጠውን እሮሮ ተቃዋሚዎች የፈጠሩትና ያስወሩት ወሬ ነው በማለት መንግሥት ተብየው ተቃዋሚዎቹን ውሸታሞች ብሎ እየከሰሰ የሻዕቢያን ወንጀል ለመሸፈን የጣረበት መንግሥታዊ መግለጫው ነበር ከላይ የተመለከታችሁት።   ተቃዋሚው መንግሥት ለማጥላላት ሲባል ያልፈነቀሉት ድንይ የለም:: ሲል ከኤርትራ የተፈናቀለ የለም  ብሎ ዓይን ያወጣ ክህደት ጭልጥ አርጎ እንደካደና ተቃዋሚውን እንዴት እንደወንጀለን  የምታስታውሱት የውሸት ባሕሪው ነው” (የባድሜ ጦርነት ከመጀመሩ በፊትም፤ እንዲሁ ተቃዋሚው "ያልሆነ የመንደር:የመሸታ ቤት ወሬ" እያወሩ እንከን የለሽ መንግስቶቻችነን ለማጣለት ያልሆነ ወሬ እያናፈሱ ነው ብሎ ወንጅሎን ነበር። ዘገባዎቻቸውን አስተውሱ፤ መርሳት የለባችሁም።) የወያኔ ደጋፊዎች የሚጽፉት ‘ጨረት’ እንኳ ሳይቀይሩ ልክ ጌቶቻቸው  ያስተማርዋቸውን የውሸት ቃል ነው የሚያስተጋቡት።

ወያኔ መግለጫ ባወጣ ቁጥር ሁሉንም ነገር ትከክል ነው የሚለው በሽታቸው የአሽከሮቹ ንቃተ ሕሊና በጣሙን አድርጎ ይገርመኛል። ወንጀል የፈጸመው እና በዘር ማጥፋት የተከሰሰው “ሽፈራው ሽጉጤ” የተባለው“ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር እራሱ የሰጠው መግለጫ የራሱ መልስ እንጂ “ነፃ አጣሪ ባለ ሞያ” በተለይም “ዘርን በማጥፋት የምርምር ጥናት ያካሄዱ ባለሞያዎች” እና “የድብደባ፤ የስድብ፤የሴቶች አመጽ፤ የንብረትን ቅሚያ፤ዜጎች ሲባረሩ የተወሰደው እርምጃ እና የደረሰባቸው ሁኔታ እና ተባራሪዎቹ የሰጡት እሮሮ እና አቤቱተታ ፤ክስ” የሚያጤኑ የተለያዩ ሕግ ዘርፍ  ባለሞያዎች ምርምራ ሳይጠና “ለወንጀሉ እና ለመባረራቸው ምክንያጥ ነው ተብሎ በክስ ላይ ያለው የወያኔ ባለስልጣን መግለጫ “እንደ ሃቀኛ/ፌስ ቫሊዩ ተወስዶ “የእግዚአብሔር ቃል” ነው ብለው አምነው መከራከራቸው እጅግ፤ እጅግ  አድርጎ ይገርመኛል።  ያባረርኩት፤ያፈናቀልኩት አማራ የለም የሚል ከሆነ እና የሰራሁት ስራ ወንጀል አይደለም የሚለን ከሆነ “ ከመላው ዓለም የተወጣጡ ነፃ አጣሪ የሕግ እና የወንጀል፤የስነ ኣእምሮ ተመራማሪ ባለሞያዎች፤ የበንቺ ማጂ እና በተለያዩ ቦታዎች ለ20 አመት ሙሉ በአማራው ላይ የተነጣጠረው የዘር ጥቃት እና ጉዳት እንዲጣራ ‘ሙሉ ፈቃደኛነቱን ያረጋግጥልን እና ከዚያ እውነቱን ይታወቃል። ይህ እስካልፈቀደ ድረስ ግን ወንጀሉ እንዳይመረመር ስላልተባበረ የባንዳዎቹ መሪም ሆነ የባንዳዎቹ ካልሲ አጣቢዎች በሙሉ “ወንጀለኞች” ናቸው።
ሽፈራው ሽጉጤ የተባለው የወያኔ “ካልሲ አጣቢ” በመግለጫው ላይ  የሚከተለውን የሞኝነቱ መግለጫ በየትኛው ሕግ ይህ አባባሉ ነፃ እንደሚያወጣው ይገርመኛል። እንዲህ ይላል፦

የክልሉ መንግሥት 2001. ባወጣው መመሪያ ከነሐሴ 30 ቀን 1999 ድረስ ወደ ዞኑ የገቡ ሰዎች ባሉበት ኑሯቸውን እንዲመሩ ሲደረግ ከነሐሴ 30 ቀን 1999 በኋላ ወደ ዞኑ የገቡት ደግሞ ወደቀያቸው እንዲመለሱ መወሰኑን አስታውሰዋል።

በዚሁ መሰረት በጉራፌርዳ ከሚኖሩት 22 ሺህ 46 የአማራ ክልል ተወላጆች መካከል መመሪያው ከወጣ በኋላ የገቡ 800 ሰዎች በወቅቱ ወደ ትውልድ ቀያቸው እንዲመለሱ መደረጉንም አቶ ሽፈራው አስታውቀዋል።”

መጀመሪያ ነገር “መሬት” በገዢው “የፖለቲካ ድርጅት”ሰጪ እና ከልካይነት የሚካሄድ እደላ፤ ግብይት፤ኮንትራትና ሸመታ መያዙ “ሕገ ወጥ”  ነው። መንግስት ነኝ የሚለው ደግሞ “የፖለቲካ ድርጅት” ነው።”የፓለቲካ ድርጅት’ የሚባለው ደግሞ “ወያኔ” ነው። ወያኔ ደግሞ የመላው ኢትዮጵያ መሬት “በባለቤትነት ይዞ” አከራይ በመሆን ዜጎች “የወያኔ” ጭሰኞች እንዲሆኑ አድርጓል ማለት ነው። “በሸቀጣ ሸቀጥ  ንግድ ወይንም በመሬት ንግድ” የፖለቲካ ድርጅት ጉልተኛ ሆኖ ማንም ዜጋ ከሚኖርበት ወይንም ለመኖር ከገባበት አካባቢ ማስወገድና ማስገባት እና ማባረር ከቻለ “ስልጣን ይዞ ወደ መሬት ታጁርነት በመለወጡ” በበብዙ በርካታ የወንጀል  ዓይነቶች ያስቀጣዋል”።

ባለ ስልጣን  የሚባለው ደግሞ “በሕዝብ ያልተመረጠ ፤ሕገ ወጡ፤ የወያኔ ትግራይ የፖለቲካ ቡድን ነው”። ስለሆነም የሕዝብ የግል ንብረትና መሬት ነጥቆ በቁጥጥሩ ስር አድርጎ ሲፈልግ ለቻይና፤ለሕንድ፤ ለአረቦች ሲፈልግ በሜትር እየለካ ለገበሬው አከራይቶ በፈለገበው ወቅት ደግሞ “አንተ አማራ ነህና’ “ሪሰትልመንት” ተከልከለሃል፤ ካንተ በፊት አማርኛ ተናጋሪዎች ‘ለሪ ኤንትሪ ቪዛ” ያመለከቱ ቦታውን ስለሞሉት፤ ቋንቋህ ደቡብ ስላልሆነ ተመለስ፡ ቋንቋህ የደቡብ ከሆንክ ግን “ተወላጅ” ነህ እና ‘ልናባርርህ አንችልም’፤መግባት፤መቆየት ትችላለህ፡” የሚለው በዘመነ መሳፍንት ያልታወጀ ግልጽ ዘረኛ አስተዳደር መሆኑን ቁልጭ ያለ መረጃ በዓለም ሕግ የሚያስጠይቅ ወንጀል ፈጽሟል ።
አማርኛ ተናጋሪ ካልሆንክ ካፊኛ ቋንቋ ወይንም ጉራጌኛ…… (በወያኔው ቋንቋ “ደቡብኛ” የሚባለው “ጎሳ” ወይንም “ቋንቋ”)ከተወለድክ ወይንም ተናገርክ ግን የእርሻ መሬት ምንም ቢጠብ መኖር ትችላለህ። መሬት ስለጠበበ ያለ ፈቃድ ሾልከህ ድምበር ጥሰህ ያለ ምንም ፓስፖርትና የቪዛ ፈቃድ በሕገወጥ  ወደ ባንቺ ማጂ ክልል የገባህ  “አማራ” ከሚባል ውጭ አገር  ስደተኛ ባንቺ ማጂ ዜጋ ስላልሆንክ ወደ መጣህበት አገርህ፤ ቀዬህድምበርህ ሂድ፤ ውጣ አትባልም’  ማለቱ በዜጋ መካካል ውስጥ በትውልድ፤በቀለም፤በቋንቋ፤በአካባቢ፤በጐሳ፤በሃይማኖት፤በፆታ፤በድምበር፤ መከፋፈል “ወንጀል” ነውና ያስቀጣዋል።

በቀዳሚ ነገር ፤ አንድ ዜጋ በገዛ አገሩ ውስጥ የትም ይሁን የትም ሰርቶ፤ አርሶ፤ ነግዶ እንደ “ንብ” እየዞረ ለቅሞ ለቃቅሞ ቤተሰቦቹን ማስተዳደር የመኖር መብት አለው። መቀሌ ያሉ ሲስትሮዎች/ጫማ ጠራጊዎች ብዛት ስላላቸው፤ከዚህ እስከ እዚህ አመተ ምህረት በሕገ ወጥ ድምበር ጥሳችሁ ወደ ተግራይ አገር የተሰደዳችሁ አማርኛ/ኦሮምኛ;ሶማሊኛ’፤ጉራጊኛ/ዓረብኛ ተናጋሪ ኢትዮጵያዊያኖች የሆናችሁ ስደተኞች ወደ የቋንቋ ተመሳሳዮቻችሁ ወደ አገራችሁ፤“ሂዱ!“ውጡ” እንግዲህ ወዲህ ለትግራይ ተወላጆች ብቻ ነው የሚፈቀደው፤ ከተባለ። ወያኔ ተወግዶ ሌላ ስርዓት መጥቶ “አዲስ አበባ ያሉ አማራ እና ኦሮሞ ተናጋሪ ሊስትሮዎች ወይንም ታክሲ ነጂዎች፤ስራቸውን ስለተሻማችሁባቸው፤  ወይንም በልመና የሚተዳደሩ ለማኞች ቦታ ስላጣበባችሁላቸው፤ “ትግሬ የሆናችሁ ለማኞች፤ባለ ንግድ ቤቶች፤ ወይንም፣ሊስትሮዎች ወይንም ታክሲ ነጂዎች፤ሴት አዳሪዎች፤ ከዚህ አመተምህርት ወዲህ የገባችሁ “ትግሬዎች” አዲስ አበባ ውስጥ ሰርታችሁ፤ለምናችሁ መኖር አትችሉም ላኦሮሞች እና ለአማሮች ቦታውን ለቅቃችሁ፤ንብረተታችሁን አስረክባችሁ ወደ ትግሬ ተመለሱ”  ቢባል ትግሬዎች ምን የሚል ጩኸት ባስሰማን የሚል ጥያቄ አለኝ። በበንቺ ማጂ አሁን እየተሰራ ያለው ስራ ከላይ የጠቀስኩት ተመሳሳይ ዘረኛ እርምጃ ነው የተወሰደው። እጅግ በጣም አደገኛ ነው።በጐሳውና በቋንቋ በቀለም እየለዩ እርሻ መፍቀድና አለመፍቀድ ማስገባት እና ማስወጣት፤ሕጋዊ እና ሕገወጥ ስደተኛ የሚባል ከየት መጣ? አዲስ አባበ ዩኒቨርሲቲ 120 ኤትራ ስደተኞችን በነፃ አስተምሮ ሲያስመርቅ፤ ተመራቂዎቹ በ ቪ ኦ ኤ ትግርኛ ክፍለ/ጊዜ የተናገሩት ቃለ መጠይቅ እንዲህ ሰሞኑን እንዲህ ብለው ነበር “የኢትዮጵያ መንግሥት ለኛ ለኤርትራ ስደተኞች ይህ ሁሉ ወጪ አውጥቶ ከፍተኛ ትምህርት እና ስልጠና ተምረን ወደ እዚህ ደረጃ ሲያደርሰን ከዜጎቹ ከኢትዮጵያዊያኖች በጀት “ቀምቶ” ነው ያስተማረን። ስለዚህም ለኢሕአዴግ መንግስትና መሪ የላቀ ምስጋናችን ይድረሰው” ብለዋል። ዜጎች ግን እንዲህ ያለ የነፃና ክብር እድል ሊሰጣቸው ቀርቶ “ሕጋዊ እና ሕገወጥ” እየተባሉ ከበንቺ ማጂ አከባባ በገዛ አገራቸው እየተደበደቡና እየተሰደቡ እርጉዞችና እመጫቶች፤ሽማግሌዎችና የሚያስተምራቸው ያጡ ወጣቶች ተባርረዋል።

እኔ የማውቀው እና ትግራይ ውስጥ የተደረገው የዘር አድልዎ ልነገራችሁ እና ልደምድም።፡ወያኔ ወደ ስልጣን ከመጣ መጀመሪያ አመት ላይ ዕድሜአቸው ሙሉ የወያኔ መሪዎች ከእናታቸው ማህጸን ወደ እዚህ ዓለም ከመወለዳቸው በፊት ትግራይ ውስጥ የኖሩ፤ ትግራይ ውስጥ ኖረው ወልደው ተዋልደው ሲኖሩ የነበሩ “በጡሮታ የሚተዳደሩ አማራዎች” እንግዲህ ይህ የትግራይ ተናጋሪ ክልል ተብሎ ስለተከለለ እናንተ ደግሞ “አማርኛ ተነጋሪ” ስለሆናችሁ ትግራይ አቅራቢያ ወደ አሉት የአማራ ክልላችሁ ሄዳችሁ የጡሮታ አበላችሁ እዛው ጠይቁ። “የደመወዝ መቀበያ ቡካችሁ/ሰነዳችሁ” አዛውረነዋል እና ሂዱ ተብለው በስተ እርጅናቸው ቦታውንም እንኳ ረግጠውት ወደ እማያውቁት ወደ “ወሎ’ ክፍለሃገር እና ሌሎቹም ወደ መሳሰሉት የአማራ “ክልል” በመሄድ መጠጊያ አጥተው፤በረሃብ እና በባይተዋርነት ሲንከራተቱ እንደነበሩ አወቃለሁ። ይህ ትዕዛዝ ሲተላለፍ “አገሪቱን በደማቸው ያስከበሩ መራመድ እንኳ የማይችሉ የ80 ዐመት አማራ አዛውንት ጡረተኞች ወደ ክልላችሁ ሂዳችሁ “የጡረታ አበል ጠይቁ” እያሉ የቀለዱባቸው ጉደኛ የወያኔ ሹማመንቶች በእነ ማን ጊዜ መሆኑን እናውቃለን። የዚህ ጐሰኛ ቡድን ወንጀሉ ተቆጥሮ አያልቅም።የወያኔ አሽከሮች ግን ይህ ልብ የሚሰብር አሳዛኝ ወንጀል እንደሕጋዊ እና እንደጀብድ ይቆጥሩታል።  

“ኢንዲጅነስ/ተወላጅ” የሚባለው የወያኔዎች ቋንቋ ከየት እንዳገኙት አላውቅም። ምናልባትም ከአሜሪካኖቹ ይመስለኛል። በአይሪሽ/እንጊለዞቹ እና አሜሪካ ውስጥ የመጀመሪያ ሰፋሪዎች ናቸው የሚባልላቸው “ቀይ ሕንዶች” የሚባሉት እና አሁን ኢትዮጵያ ውስጥ በአፓርታይዱ ወያኔ በቋንቋ/በጐሳ ከልሎ አማራ፤ ትገሬ፤ሶማሌ……እያለ ቅድሚያ ለ“ኢንዲጅነስ” የሚባል ጉደኛ ቃል ሲጠቀሙ የኮሎኒያሊስቶች እና የአፓርታይድ አስተዳዳር መለኪያ በኢትዮጵያ ዜግነት ውስጥ እየተጠቀሙበት እንዳሉ አውቀውት ይሆን? ቢያውቁትም እኮ እቅዳቸው ስለሆነ ያርማሉ ተብሎ አይታሰብም። ምክንያቱም “ስልፍ ዲናያል” በሚባል “የሕሊና ጽልመት” የተጋረደ ቡድን በቋንቋ በቀለም ማስተዳዳር “ወንጀል” መሆኑን እያወቀውም። ስለሆነም ነው እራሱ ለራሱ እየዋሸ የሚራመድ ፍጡር ለማሳመን ሕክምና ያስፈልገዋል።

ስለሆነም ነበር (  “ዘረኞች ሕዝብን የሚያታልሉበት ዓይነተኛ መንገድ “ውሸት”ነው። ሲዋሹ እንደ ተራ ሰው ሳይሆን ዘረኞች ሲዋሹ እስስቶች ስለሆኑ ውሸታቸው እንዳይታወቅባቸው የሚሰፍሩት ውሸትና እውነት እንደ አድማጮቹ ባሕሪ የመለዋወጥ ባሕሪያቸው ያስተካክላሉ። የዋሹትን እና የተሳደቡትን ዘረኛ ስድብም ይሁን ወንጀለኛ ፖሊሲአቸው በሌሎች ላይ በማስታከክ የገዛ ራሳቸወን ወንጀል የመጫን ችሎታቸው የላቀ ነው። ስለሆነም አድማጮች የትግል እና የንባብ ልምድ ከሌላቸው በቀላሉ የነዚህ ሰለባ ይሆናል።……..” () )ዘመን ይለወጣል ዘረኞች ትተውት የሚሄዱ አሻራ ግን አይለወጥም! ጌታቸው ረዳ Septemeber 11, 2011) በማለት አምና ልተች የቻልኩበት ምክንያት።

በበንቺ ማጂ የተፈጸመው ፖለቲካ አዘል የዘር ወንጀል ስለሆነ፤“ገለልተኛ”  (ማለትም የወያኔ ባለስልጣኖች እና የወያኔ የተቃዋሚ መሪዎች ፤የሕግ ባለሞያዎች፤የማሕበረሰብ መሪዎች፤የሴቶች ማሕበራት፣……በታዛቢነት) እና የውጭ ዜጎች እና ኢትዮጵያዊያን “አከስፐረቶች” ያቀፈ ነፃ የሆነ ዓለም አቀፍ አጣሪ አካል  ያልመረመረው ጥናት “በተከሳሹ በማቺ መንጂ ርዕሰ መስተዳድር በሽፈራው ሽጉጤ” የተሰጠው የውሸት መግለጫ  ሕጋዊነት ስለሌለው ወድቅ ነው! በጸረ አማራነታቸው ምድር እና ሰማይ ያወቃቸው “ኦነጐች እና ወያኔዎች” አማራውን ሲጨፈጭፉት የየራሳቸው የሆነ የክህደት መግለጫ ባወጡ ቁጥር ከታመኑ አማራውን የጨፈጨፈው ማነው?


2ሚሊዮን  አማራ ሕዝብ ከምደረ ገጽ ተሰውሯል ብሎ የወያኔ መንግስት እራሱ ካመነ እና የሰውረው ምክንያትም ማወቅ አልቻልኩም ብሎ እራሱ በቀጠረው  አለም አቀፍ ሙያተኛ ካረጋጋጠ፤ “ተሰወረ የተባለው ሕዝብ የት ገባ? ተጠያቂው ለምን አይኖርም? ገለልተኛ የሆነ፤ የዘር ማጥፋት አጣሪ ሙያተኛ ቡድንስ ለምን እንዲያጣራ አልተደረገም? አማራውን ወክሎ “ከሳሽ” ክፍል ስለታጣ ነው? ወይንስ ያለ የወያኔ የመግቢያ ቪዛ/ፓስፖርት “ደቡብ”

“ትግራይ ሕዝቦች፤ምዕራብ ሕዝቦች፤ ሶማሊ፤ኦሮሞ  ወዘተ” ወደ እሚባለው ሌላ ድምብርና አገር ሾልከው ድምበር ጥሰው ስለገቡ ባገሬው ኢሚግረሽን/ስደተኛ መ/ቤ/ት  “ዲፖርት” “እንዳይባረሩ” ምድር ውስጥ ታነል/ መሸሸጊያ ቆፍረው ተደብቀው እየኖሩ ነው? ይኼ ጉድ “ሊኖርም ላይኖርም” መሆኑን እና ላለመሆኑን ለምን አልተጣራም?

ስለሆነም ነው፤ የነሱን ወንጀል ወደ ተቃዋሚዎች በመለጠፍ የውሸት ባሕሪያቸው ላልተመራመሩና በራስ ክህደት ውስጥ ለሚጓዙ “የመሪያቸውን የቅንድብ ጸጉር ብዛት” ሲቆጥሩ ለሚውሉ የሕሊና ድውዮች ተከላከልሉን እያሉ ሲያሞኛቸው የምናየው። ስለሆነም ኢትዮጵያዊያን ምሁራን ሁሉ “የፖለቲካ ልዩነታችሁ” ለጊዜው ለዚህ ጉዳይ ሲባል ወደ ልዩነታችሁን ወደ ጎን አስቀምጣችሁ፤ተባብራችሁ “ሽፈራው ሽጉጤን” በዓለም አቀፍ ፍርድ ቤት ከስሳችሁ “ነፃ አጣሪ” ወደ ቦታው ድረስ ሄዶ እንዲመረምረው ያመች ዘንድ እንድትጠይቁ የኢትጵያ ሰማይ አዘጋጅ (ጌታቸው ረዳ) ይጠይቃል። የወያኔ አስካሪስ “አማራዎች ተባረሩ” ማለቱን ፈርቶ “ተፈናቀሉ” ቢልም ከዘረኛ ወንጀሉ-ነፃ-አያደርገውም! አመሰግናለሁ።