“ዛሬ” ኢ-ፍትሃዊና ሕገወጥ ውሳኔን የምንቀበል ከሆነ “ነገ” በሁሉም ዘርፍ
የአገራችን ነፃነትና ሉዓላዊነት ከነጭራሹ እንዳናጣ ምን ዋስታ አለን? (ክፍል 2)
ጌታቸው ረዳ (የ Ethiopian Semay ድረገጽ አዘጋጅ)
ይህ ጽሑፍ ካለፈው “ቪዥን ኢትዮጵያ ለኤርትራ!” ከሚለው ጽሑፌ ቀጣይ ነው። ከለይ በርዕስ የጠቀስኩት ይህ ንግግር የተናገሩት የወያኔ ፕረዚዳንት የነበሩት ነጋሶ ጊዳዳ ናቸው። ይህ ንግግር የተናገሩት በጥር 3/2005 ዓ/ም መስቀል አደባባይ/አብዮት አደባባይ የመለስ ዜናዊ የሰጥቶ መቀበል መርሕ የባድሜንና የተቀሩት ድምበሮችና ገጠሮች፤ተራሮችና ጉብታዎች…እንዲሁም እዛው የሚኖር ሕዝብና ንብረት፤ በኖርማላይዘሽን/በፕሪንስፕል ተቀብለነዋል በማለት ለሻዕቢያ አሳልፎ ለመስጠት የራሱን ፓርላማ አገልጋዮቹን ሰብስቦ ባጸደቀበት ወቅት ገብሩ አስራትና ነጋሶ ጊዳዳ አደባባይ ላይ ወደ 150,000 ሕዝብ የሚገመት ለአልጀሪስ ውሳኔ እና ለመለስ ዜናዊ ተቃውሞ ለተሰበሰበ ሕዝብ ካደረጉት ንግግር ያገኘሁት ነው።
በነገራችን ላይ ነጋሶ በዚህ ርዕስ
ላመስግን እንጂ፤ እንደምታውቁት ካሁን በፊት ነጋሶ ስለ ባድሜ ተጠይቀው የመለሱት ብታስታውሱ “ባድሜን ይስጡን ዓሰብ ይውሰዱ”
ሲሉ አንደነበረና በዛው እኔም በወቅቱ “ዜጋ” በሚባል አዲስ አበባ ሲታተም በነበረው መጽሄት ላይ ተችቻቸው እንደነበር ይታወሳል።
እነ ዶክተር ያዕቆብ ሃይለማርያምም ሆነ እነ ነጋሶ እና የመሳሰሉ ምሁራን ሕሊና ቤወቅቱ እዛም እዚህም መርገጥና የመዋዠቁ አባዜ
የለመድነው ስለሆነ፤ ይህንንም አብሮ እንዲሰመርበት ብየ ነው (ደ/ር ያቆብ ሃይለማርያምም እንዲሁ በድምበር ጉዳይም ሆነ በየዲሞክራሲ ሃሳብን የመግለጽ ነፃነት መብት በወያኔ
የተከበረ አንደሆነ አስመልክቶ ሲዋዥቀው የነበረው ቃለ መጠይቁ አንዳንዶቻችሁ ታስታውሳላችሁ)።
በመግቢያ በርዕሱ የተጠቀሰው ይህ
አባባል እኔም እስከ ባለፈው ሰሞን ጽሑፌ ደጋግሜ ለዘመናት ስናገረው የነበረ ሊሰመርበት የሚገባ ነጥብ ነው። ባለፈው ሰሞን “ቪዥን
ኢትዮጵያ” የሚል ከኢሳት/ግንቦት 7 ጋር በመተባባር ከሃዲዎች ለሻዕቢያ እጅ መንሺያ ያዘጋጁትንና
መድረክ በሚመለከት በኢትዮጵያዊያን በኩል የተደመጠው የኤርትራ ኢ’ሕጋዊ ነፃነትና ሉዓላዊነት “ሕጋዊ” አድርገው በመቀበልና ሕዝብም
እንዲቀበለው ያደረጉት የድጋፍና የጥብቅና ንግግራቸው አስመልከቼ ጽፌአለሁ። እነኚህ የባንዳ ምሁራንና ጋዜጠኞች ስብስብ አገራችንን
ካፈረሷትና ካጠቁዋት ሁለት የውጭ ሃይላት እንግዶች ጋር ሆነው፤ ሲያንጨበጭቡና ሲንጨበጨብላቸው ለታሪክ መረጃ በፊልም የተቀረጸውን
‘ዩ-ቱብ’ ላይ ተለጥፋል።
እነኚህ ክፍሎች በምሁርነትና በዲፕሎማሲ
ተሞኩሮ ሽፋን ገብተው ሲዳክሩት የነበረው የአገርን ሉዓላዊ ምድርና ሕዝብ እንዲሁም የአገርን ክብርና ዝና በጠላቶቻችን ፊት ባማዋረድ፤
የማንነታችንን መገለጫ አንኳር ክርክሮችን በማጥላላት ለባዕድ በፕሮፓጋንዳ መልክ መተባበራቸው የብዙ አገር ወዳድ ዜጎች አንጀት አስቆጥቷል።
ፕሮፌሰር መስፍን ወ/ማርያምም “ደምበር ለሱዳን ተሰጠ የሚሉ ሰዎች የተሰጠ ደምበር የለም። ካለም በማስረጃ ማሳየት አለባቸው ብለው
ባንድ የኦንላይን /ዩ ቱብ ቃለ መጠይቅ እዚህ አገር የሰጡ መሰለኝ። እኚህ ሰው ምን ነካቸው? መረጃዎች አላነበቡም? በቪኦኤ በኩል
የተደመጠው ሱዳን ድረስ ተወስደው የታሰሩ ዜጎቻችን አድምጠው አያውቁም? እነኚህ ምሁራን የአገርን ሉዓላዊ ምድርና ሕዝብ እንዲሁም
የአገርን ክብርና ዝና በጠላቶቻችን ፊት ባማዋረድ፤ የማንነታችንን መገለጫ አንኳር ክርክሮችን በማጥላላት ለባዕድ በፕሮፓጋንዳ መልክ
መተባበራቸው የብዙ አገር ወዳድ ዜጎች አንጀት አስቆጥቷል የምለው ለዚህ ነው።
ሐፍረት ምን መሆኑ የማያውቅ ንአማን
ዘለቀና፤ ዜጎቻችን ፈላሻዎችን ከሞሳድና ሲ አይ ኤ ጋር እየተነጋገረ ዜጎቻችንን በዘረኝነት እንዲሰቃዩ ወደ እስራኤል በማሸጋጋር
ግምባር ቀደም መሪ የነበረው ዩሁዳው ካሳ ከበደ፤ እንዲሁም የተቀሩት የእነ ዶክተር ዜሮዎች ስብስብ “ሻዕቢያዊት ኤርትራንና ወረባላ
መሪዋን” እያሞገሱ የተናገሩትን ንግግር ለምታስታውሱ ሁሉ እጅግ የሚገርም እና ከወያኔዎች በባሰ መልክ ሚዛን የሳቱ ቀላዋጮች ሆነው
ማድመጣችን ላንዳንዶቻችን የጠበቅነው ቢሆንም፤ ስለ ኢሳያስ አፈወርቅ ጫማና ልብስ አለባበስ እያደነቁ ያወራሉ ብለን ጭራሽ አልገመትነውም
ነበር ። ትዝ ይላችሗል፤ ተማሪዎች እያለን ‘ድሮ? ፀጉርን አሳድጎ፤ ጉርድ ሳርያን ኮት ለብሶ፤ በቅጫም እና በቅማል መበላት “የተራማጅነትና
ለሕዝብ ቤዛ ሆኖ የማለፍ ተቆርቋሪነት” ምልክት ተደርጎ እየተወሰደ በቅማልና በቅጫም በመላት ብርቅ ሆኖ ይታይ የነበረበት ጊዜ ታስታውሳላችሁ?
በላይነህ አስናቀ የተባለ የትግራይ ተወላጅ ብርቱ ተናጋሪና መቀሌ ውስጥ የተማሪዎች መሪ ከነበሩት አንዱ የነበረ ትዝ
ይላችሓል? በላይነህና ኢሳያስ ከአንድ ስሪት የተሰሩ ይመስሉኛል።
እነ ንአምን እና አንዳርጋቸው በኢሳያስ የአለባበስ ዘዴ ተማርከው
አደባባይ ላይ በደምፅ ማጉያ ለሕዝብ ሲናገሩ ማድመጥ እውነት ምሁራኖቹ ከማነስ ወደ መድቀቅ እየሄዱ ማየት ስለ እነሱ አፈርኩ። ምን
እሱ ብቻ! የኢሳቱ ጋዜጠኛ ሲሳይ አገና ለመሳይ የጠየቀው ትዝ ይላችሗል? “አስመራ ቤተመንግስት ተጋብዛችሁ ምን ዓይንት ምግብ በላችሁ?”
ብሎ የጠየቀውን ጥያቄ ትዝ ይላችሗል? ይህ የሚያስቅ ይመስላል ወንድሞቼ፤ የኼ አስፈሪ በሽታ ነው። ተቀብሮ ከሞት የተነሳ ሰው ሰማይ
ላይ መላእክት ምን ዓይንት ምግብ አንደሚመገቡ ለማወቅ የጓጓ ጠያቂ አይመስልም እንዲህ ያለ አስገራሚ ጥያቄ ጋዜጠኛ አንዲህ ብሎ ሲጠይቅ?! እኔ እያደረ እየጠበበኝ መጥቷል “ጛድ ሊቀመንበር”
ነው ያሉት አባ ቄሱ ወያኔ ወደ አዲስ አበባ ሲቃረቡ። አውነት የነዚህ ሰዎች ምንነት እየጠበበኝ መጥጧል።
እነ ዶ/ር አሰፋ ነጋሽና ዶ/ር
አበባ ፈቃደ “ትንንሽ ሕሊናዎች” የሚሉዋቸው እነኚህ ትንንሽ
ሰዎች በዛው አስገራሚ እና አሳፋሪ መድረክ ብግልጽ ያየንበት የመጀመሪያ መድረክ ነበር ቢባል የተሳሳትኩ አይመስለኝም።
መድረኩ በግልጽ ያሳየን እነዚህ
ትንንሽ ሕሊናዎች ተሸክመውት መጥተው መድረኩ ላይ ያፈሰሱት የሕሊና ጉድፍ አስቀያሚ ብቻ ሳይሆን በሚያሰዝነው መልኩ አዳራሹ ውስጥ
ከተገኙት “የሙሶሎኒ ልጆች” ጋር ግምባር ፈጥረው “ኢትዮጵያ ወገንና
ልጆች” እንደሌላት “ዘመድ አልባ” ነበር ያስቀሯት። ሁሉም በጭብጨባ አፊዘውባታል! የሙሶሎኒ ልጆች ቀን ወጥቶላቸው አዳራሹ ውስጥ
የደስ ደስ ነበር የተሰማቸው። ምስጢሩ ያልገባው “ታዳሚ” ደግሞ ጨው ለመላስ አንደተዘጋጀች ላም ‘አፉን ከፍቶ’ ማድመጡን ሳያንስ፤
ባንዳ ኢትዮጵያዊያን ከሙሶሎኒ ልጆች ጋር አብረው፤ ኤርትራንና ኢሳያስን ሲያሽሞነሙኑ እጁ እስኪ ግል ሲያንጨበጭብ ማየት እጅግ፤አጅግ፤እጅግ
ያሳዝናል። ኢትዮጵያዊያን ባድሜን ለሙሶሎኒ ልጆች ያስረክቡ ብለው የሙሶሎኒ ልጆች ሲያሾፉ፤ ያንጨበጨቡላቸው ኢትዮጵያዊያን ቪዲዮውን
ተመልሳችሁ በጥንቃቄ ተመልከቱት፡ እውቅ ሰዎች ሲያንጨበጭቡላቸው ታያላችሁ።
“መስታዎት ይገዛል ሞኝ የጫዋ ልጅ
ሁሉም የሚያሳየው መሰንበት ነው እንጂ”
ሲሉ ወላጆቻችን ነግረውናል። ገና ሉዓላዊነታችንን በሕገ ወጥ የተረገጥነውንና የተበደልነውን
አቤቱታ እነዚህ ሙራን ይወክሉናል፤ ባደባባይ በዓለም መድረኮች ይሞግትሉናል ብለን ስንጠብቃቸው ፍትሕ ለማገኘት በምናደርገው የወደፊት
ግብግብ “ገና ጦርነቱ ሳይጀመር” ተምበርካኪዎች ሆኖው እኛንም ጭምር አብረናቸው እንድንምበረከክ ያልሞከሩት አሳሳጭ የሕሊና አጣባ
አልነበረም።በቁም የሞቱተረ አስገራሚ ተምበርካኪዎች ደግሞ “ሃይለስላሴ በጉልበት ኤርትራን ወደ ኢትዮጵያ ቀላቀሏት” ሲሉም ተደምጠዋል።
የችግሩ መንስኤም ያ ነው ሲሉ፤ የእስላማዊው የቆላማው ወገን ከሱዳን እንጂ ከክርስትያን ጋር አንደባለቅም እና ከ”ፊውዳል ካልሰለጠነቺው
ኢትዮጵያ” የሰለጠነቺው “ዲሞክራቲክ” ኤርትራ መደባቅ የለባትም የሚሉ ሁለት ትምክሕታዊያን ወገኖችና ዘረኛ ባሕሪያቸውን
ግን ለመዳሰስ አልፈለጉም።
ያ ትምክሕትም በ1991 (አውሮጳዊያን ዘመን አቆጣጠር) ተደግሞ ለዛሬ ውድቀታቸው ተጋልጠው የሚያነሳቸው
አጥተው ተላልጠው “አፈር ላይ እየተንከባለሉ” አፍንጫቸው አፈር ልሶ ሃፍረት ተከናንበው ይገኛሉ። አማራ፤አማራ በደለን ሲሉ ሲቃዡ፤ሲዋሹ
ዘመን አልፎባቸው፤ “አማራ” ብለው የሚሉት፡”ኢማጂኔሪ ኤኔሚ” ከኤርትራ ሲሰወር፤ አንደገና አጋሜ የሚባል “ኢመጂኔሪ ኤኔሚ” ስለው
ብቅ አሉ፤ ያም አልሰራ ሲላቸው፤ መጨረሻ ለመላላጣቸው “መሸፈኛ” ምክንያት ሲያጡ “ኢሳያስን” ‘ብቸኛ ጥፋተኛ’ አድርገው ሲያወግዙት
ታደምጧቸዋላችሁ። ምንተሐፍረታቸውን ለመሸፈን የለበሱት እራፊ ትንታኔ ተመልከቱልኝ፦“ከኮንፌደረሺን ወደ ኮሎኒ” “ከኮሎኒ ወደ አማራ”፤
“ከአማራ ወደ አጋሜ” ፤ “ከአጋሜ ወደ ኢሳያስ” ነጋ ደግሞ ምን አንደሚለብሱ አግዚሃር ይወቀው። ከዚያ አይነት ሐፍረትና ታሪክ
ሰውረን ጌታዬ!!
በኛ አቋም ክቡር ‘ጃንሆይ’ ኤርትራን ወደ ኢትዮጵያ አንድትቀላቀል ማድረጋቸው ትክክለኛ እርምጃና ሕጋዊ ነው። እንኳንና ብዙሃኑ የሐገሬው ተወላጆች ፈቅደውና ለመቀላቀሉ ወትውተውና ተጨምረውበት ፤ ባይጨመሩበትም፤ ሕጋዊነት ነበረው። በብዙ መንገድ ንጉሡ ተሳስተዋል እያሉ የዛሬ ምሁራን ቢለፋደዱም፤ ይህ የሻዕቢያና የወያኔ ክርክር እንጂ በሕግ አንጻር ብዙ መልኩ ንጉሡ ያደረጉት ስሕትት ቢኖር አስተዳደራዊ ችግር ከሆነ እንጂ ማቀላቀላቸው “ሕግን’ ተሞርኩዘው ነው። ጣሊያን ሲሄድና ከመሄዱ በፊት የሰራቸውን ካርታዎችና ያፈረሳቸው ውሎችን መመለክተ ነው። ንጉሡ ተሳስተዋል ካልን፤ ሻዕቢያስ ማን መብቱ ሰጠውና ነው “የኮሎኒ ጥያቄ ነው” ብሎ አገርን ሊገነጥል የቻለው? የመጀመሪያው ጥያቄ “የአስር አመት የሃሳብ ማለሳለሻ ፈረሰ” ፤በጉልበት ፈረስ ከተባለ ደግሞ፤ ዛሬም መጠየቅ ካለባቸው “እንደ ጥንቱ ኢትዮጵያዊያም የይገባኛል መብቷ አንዲጠበቅ ክርክሯ አንዲደመጥ ደምፅ አንድትሰጥ የጨመረ የፌደረሽኑ ውሳኔ ድምፅ ጥያቄ ማቅረብ አንጂ፤ ጭራሽኑ ያልነበረውን “የኮሎኒ ጥያቄ ነው ብሎ” ኢትዮጵያን ያልጨመረ፤ አገርን መገንጠል ብምን መነሻና መሰረት? ኤርትራኖች ኮሎኒ ተደረጉ? ይኼ ቀልድ ነው!!!!! ኤርትራኖች ይህንን ደጋግመን ጠይቀናቸው፤ወያኔዎች ይህንን ደጋግምን ጠይቀናቸው፤ አንዳቸውም መልስ የላቸውም። አንኳን እነሱ፤ የኢትዮጵያ የፍትሕ ሚኒስቴር/የአገረቱ ፍርድ ቤቶች ዋና “አቶርኒ ጀኔራል” የነበረው አድርባዩ ዶ/ር በረከተአብ ሃብተስላሴ እንኳ ሊመልሰው አይችልም (እንደ እነሱ ኮሎኒ ነው ብሎ ሊዋሽ ይችል እንደሆነ እንጂ እኔ የኮሎኒያሊስቶች ባርያ ነበርኩ አይልም።
እነሱስ ይበሉ፤ ያው ውሸት የለመደባቸው ነው።የሚገርመው አድርባዮቹ ኢትዮጵያዊያን ባንዳዎች ደግሞ “ኤርትራዊያንና መሪያቸውና ተከታዮቹ
/ሕዝቡ ጭምር ስለ ኢትዮጵያ ክፋት አስበው አያውቁም፤ ዛሬም አያስቡም” “በእኛ ላይ ምንም ክፋት የላቸውም” ሲሉ ዋሽተዋል፤ ሰብከዋል።
ትዝታችንና ነባራዊ ሁኔታዎችን ይህንን አያመለክቱም።ትውስታዎቻችንን ወደ ሗላ ተመልሰን እናስታውስ። ዛሬ በነዚህ ከሃዲ ምሁራን ስለ
ሻዕቢያ መሪያቸውና ተከታዮቹ ደግነትና አፍቃሬ ኢትዮጵያዊነትን ይዋሹን እንጂ ማሕደራቸው “ደግነትን ሰላማዊነትን እና ክፋት
አልባንና ወንድማማችነትን” አያመለክትም።
ኤርትራኖቹ እንኳን በበጎና በወገንተኛነት ሊያዩን ቀርቶ’፤ ትግሬዎች ነን የሚሉ ወያኔዎች
እንኳ ትግሬን ከጣሊያን ባርነትና መገዛት ነፃ ያጡንን ምኒሊክን እና በተቀሩት የኢትዮጵያ መሪዎች ያለቸውን እይታ የሚከተለውን አንብቡ፦
ገብረኪዳን ደስታ በመጽሃፉ በምዕራፍ ሁለት “አጼ ዮሐንስና የግብፅ ወራሪ ሓይል” በሚለዉ ርዕስ ላይ ያገር ክህደት የፈጸሙት
ምኒሊክ ያገር አንድነት ያፈረሱት ሚኒሊክ ኤርትራን ለጠላት ሸጧታል፣ በማለት ዮሀንስ፣ ዮሃነስ በማለት ደጋግሞ የአንድነት ፣ምልክት
ምኒሊክ የክህደት ምልክት በማለት ሲከስስ ይነበባል። ባጭሩ እንዲህ ይላል
“አጼ ዮሓንስ ኢትዮጵያ የምትባልዋ ጥንታዊት ሃገር አፋራርሰዉ ለመቀራመት ያስፋፉ አራት ጠላቶች ነበሯቸዉ። እነሱም-፤
ግብፅ፤ኢጣሊድ፤ርቡሽ እና ንጉሥ ምኒሊክ ናቸዉ”
(ገ/ኪዳን ደስታ የትግራይ ህዝብና ትምክሕተኞች ሴራ ከትናነት አስከ ዛሬ ገጽ 21)
በሌላ በኩል በበራዦችና ባንዳዎች ምክንያት ተቃዋሚው ቅንጅት ከመፍረሱ በፊት፤ስለ ኤርትራ
ያወጣው ማኒፌስቶውን እንመልከት፤ማኒፌስቶው 133 ገጽ ይዟል። ማኒፌስቶው ስለ ምርጫ ያካተተው ማኒፌስቶ ነው። በገፅ 82 ላይ
“የአገር ሉአላዊነት መደፈር” በሚል ርእስ እንዲህ ይላል፦
ልጥቀስ፤-
ይህ ምንን ያመለክታል? እነ ብርሃኑ
ነጋ፤ እነ ንአመን ዘለቀ፤እነ አሰግድ ….. እና ጸረ ኢትዮጵያ አይሁዳዊው አሜሪካ ኸርመን ኰሆን ይዘው እርስ በርስ እየተሞጋገሱ
ዛሬ ስለ ኤርትራ ምን እያሉ ነው እያወሩን ያሉት? ዛሬ እነዚህ አሳፋሪዎች እንደ ወያኔ በምስጢር ሳይሆን የተደራደሩት በገሃድ በመድረክ
ወጥተው ነው ስለ ኤርትራኖች ሽንጣቸውን ገትረው እንወክላቸዋለን ብለው የነገሩን። የወያኔ “ክሎን” በየት በየት ዙሮው በየት ተፈጠሩብን?
እነ ኾኸን ዛሬ 10 ጊዜ በየመድረኩ’ለኤርትራኖች፤ እንዲሁም በኦጋዴን ነፃ አውጪና
አስገራሚው ደግሞ “ኢትዮጵያዊያንን ምን ብናደርግ ትመክረናለህ?” ብሎ የሚጠይቅ ምስኪን አዲስ የኢሳት ኩችዬ ጋዜጠኛ ደግሞ ብቅ
ብሏል። ኮሆን የተባለው የኢትዮጵያ ጠላት በግንቦት 7 ቡድኖችና በመሰሎቻቸው በክብር እየተስተናገደ እሽሩሩ እየተባለ በየመድረኩ
አስሬ ሲጋብዙት ማየት አስገራሚ ከመሆን አልፎ፤ይህ ርካሽንት ለመግለጽ ቃላት
ያጥረኛል። የሴራው መሪ ተዋናዩ ኮኸን ጠላታችን መሆኑን እያወቁ እያሽሞነሞኑ አንጀታችን እንዲቃጠል ብለው ሆን ብለው
የሚያደርጉት የግንቦት 7ና ኢሳት ጋዜጠኞችና ማኔጅመንት ድራማ/እልህ ነው። ባንዳዎቹ ኢ-ፍትሓዊ ሴራን ተቀበሉ እያሉን ነው። “ዛሬ” ኢ-ፍትሃዊና ሕገወጥ ውሳኔን የምንቀበል ከሆነ “ነገ” በሁሉም ዘርፍ የአገራችን ነፃነትና
ሉዓላዊነት ከነጭራሹ እንዳናጣ ምን ዋስታ አለን? ምንም!
መቸ የህ ብቻ፡ ኢሳያስ የኢትዮጵያ ወዳጅ ነው
ሲሉን እነ ይሁዳው ካሳ ከበደ እና ግንቦት 7 ንአማን ዘለቀ ነግረውናል፦ ኢሳያስ ኢትዮጵያን ለማበጣበጥ በባህር ወደባችን ላይ
ማንን አምጥቶ አስፍሮበታል? አንባቢዎቼ አንዳትደነግጡ! ብትደነግጡም ይገባችሗል። የተጠደመብን ጠመንጃ እጅግ አሳሳቢ ነውና፤
በጥቂቱ ልጥቀስ እና ሙሉውን ለማንበብ ርዕሱን እሰጣችሗለሁ። ካታር እና ሳውዲ አረቢያ እንዲሁም አሜሪካኖች በኢሳያስ ጋባዥነት
ምፅዋና ዓሰብ መሽገው ምን አንዳሰቡልን አንብቡ። ጥቂቱን ነው የምጠቅሰው። ሙሉውን ርዕሱን ከታች እሰጣችሗለሁ ጉጉል አድርጉት።
Recent
media reports indicate that Saudi Arabia and the UAE have contracted
Eritrea’s government for assistance in the War on Yemen, using the East African
state as a transit and logistics base for their operations, as well as 400 of
its troops for cannon fodder in Aden
‘’The GCC {the Gulf Cooperation Council}
Is Expanding ተo Eritrea, And It’s Not Good For Ethiopia…….. ‘’ The Saudis and Emiratis now have a naval
presence in Eritrea, and as South Front reported (and which was verified
separately this summer), the UAE is also seeking to open a naval base in
Berbera along the northern coast of Somalia in the breakaway Somaliland
region…………….
”To bring everything
together in a more simple understanding, Qatar has taken the lead in destabilizing the Horn
of Africa out of ideological and unipolar-loyalty reasons, and it’s using its “legal”
presence in Eritrea to facilitate this. The War on Yemen provided the other main GCC
states of Saudi Arabia and the UAE with a ‘plausible justification’ for also
‘getting in on the action’, knowing just as well as Qatar does that Eritrea is
a ‘double-hinged’ state that can be used to simultaneously project maritime and
continental influence, with the latter case being against Ethiopia.”
“By itself and
approached from a purely geopolitical standpoint, it’s theoretically possible
for Saudi Arabia and the UAE to maintain this new status quo between Eritrea
and Ethiopia (perhaps
even exploit it and each of those two states to their own advantage if shrewd
diplomacy is applied), but the presence of Qatar, the ‘loose cannon’, means that the
entire arrangement is inherently unstable and subject to sudden change. Qatar has proven itself much
more prone to impromptu outbursts of rhetorical rage than any of the other Gulf
States, and its comparatively younger leader (only 35 years old) is much less versed in the art
of statecraft
than his peers. Being so hot-headed and already harboring an inferiority complex vis-à-vis his larger
and more mature neighbors, Qatari Emir Tamim bin Hamad Al Thani is inclined to give the
full terrorist ‘go-ahead’ whenever he feels like it (or if he ‘thinks’ it
would be of strategic use for him), meaning that a Qatari-sponsored
Islamic destabilization of Ethiopia cannot at all be discounted, and must be astutely
prepared for by the country’s authorities.
“……The final section of the research
discusses the Unconventional War scenario that Qatar could help engineer
alongside Eritrea and Al Shabaab (one of its ideological ‘children’, it could
be argued) to throw Ethiopia into chaos.’’ Therefore, many layers of
intrigue blanket the possibility that Qatar may lead the GCC into a proxy
confrontation with Ethiopia, be it out of its own regard or acting on behalf of
American ‘advice’, which could see the Gulf using the country of Eritrea
alongside Al Shabaab jihadists to dislodge China from its most important
foothold in Africa.’’
The Big Picture:
“To bring everything together in a more
simple understanding, Qatar has taken the lead in destabilizing the Horn of
Africa out of ideological and unipolar-loyalty reasons, and it’s using its
“legal” presence in Eritrea to facilitate this. The War on Yemen provided the
other main GCC states of Saudi Arabia and the UAE with a ‘plausible
justification’ for also ‘getting in on the action’, knowing just as well as
Qatar does that Eritrea is a ‘double-hinged’ state that can be used to
simultaneously project maritime and continental influence, with the latter case
being against Ethiopia”
Saudi Arabia and the GCC are Expanding To Eritrea. Geopolitical Implications for Ethiopia
By Andrew Korybko
Global Research, November 18, 2015
Katehon 16 November 2015
እነ ካሳ ከበደ እና ንአምን ዘለቀ ኢሳያስ አፈወርቂ
ለኢትዮጵያ በጎ አሳቢነቱ ወሰን የለውም ሲሉ ሽንጣቸው ገትረው የሞገቱንን የሳብቨርዠን/ የባንዳዎች ሴራ ይኼውና ሳይውል ሳያድር
ውሸታቸው ሲጋለጥ።
ክፍል - 3- ይቀጥላል…….አመሰግናለሁ። ጌታቸው ረዳ (ኢትዮጵያን ሰማይ አዘጋጅ= Editor Ethiopian Semay) getachre@aol.com