Wednesday, January 27, 2021

የወያኔ ታጋዮችና የትግራይ ሕዝብ በአማራ ሕዝብ ላይ የዘር ማጥፋት ፖሊሲው በቀጥታም በተዘዋዋሪም የማይነጣጠሉ ትስስሮች አድርገዋል ጌታቸው ረዳ (ኢትዮ ሰማይ) 1/27/2021

 

የወያኔ ታጋዮችና የትግራይ ሕዝብ በአማራ ሕዝብ ላይ የዘር ማጥፋት ፖሊሲው በቀጥታም በተዘዋዋሪም የማይነጣጠሉ ትስስሮች አድርገዋል

ጌታቸው ረዳ (ኢትዮ ሰማይ)

1/27/2021

ይህ ርዕስ ለማቅረብ የተገደድኩበት መነሻ፤ ያለፈው የወያኔ እና የትግራይ ሕዝብ ቁርኝት (እስካሁንም የቀጠለው የሞቀው ድጋፍና ፍቅር) እንዳልነበረ ለማድረግ በየሚዲያው የማደምጣቸው አሽቃባጭ ምሁራን እንደ እሬት ስለመረሩኝ አውነታውን ላስቀምጥ። ያው ድሮም የሸዋ ትግሬ ወይንም ጸረ ትግሬ የሚል ስም ስለተለጠፈብኝ፤ ተቃዋሚዎቼ ለኔ አዲስ ስላልሆኑ እውነታው ዛሬም ቢመራችሁ የሆነውን ላስቀምጥላችሁ መረጥኩ።

ሁለት ጉዳዮችን እንመለከታለን ።

 

ወያኔን ወደ ሥልጣን ያመጣው ከሰማይ የመጡ ጦረኞች ሳይሆኑ፤በትግራይ ሕዝብ ትግልና አውቅና ነው። ወያኔና የትግራይ ሕዝብ በመተባበር ያካሄዱት የ17 አመት ዕድሜ ያስቆጠረው ረዢሙ ቢላዋ ያነጣጠረው ልክ የጀርመን የናዚዝም የዘር ፣ የፖለቲካ እና የግዛት ምኞቶችን በአንድ ዘር ላይ የበላይነት ለማሳካት እንዳደረገው ሁሉ በትግራይ ክ/ሃገር የተነሳው የብሔረተኛው ህወሓት ጦር ተመሳሳይ ነበር እንጂ የኢትዮጵያ ጋዜጠኞች፤ ምሁራኖችና ትግሬዎች እንደሚወሻክቱት ስለ ዲሞክራሲ እና ስለ አንድነት ጥበቃ የተደረገ ትግል አልነበረም። ስለ ዲሞክራሲ ማምጣት ትግል ተውትና ስለ አንድነትና ሉዓላዊነትን በከፋ መልኩ እንዴት እንደተከናወነና ማን እንዳከናወነው እናውቀዋለን! አደለም እንዴ? ። ኢትዮጵያን ወደብ አልባ ያደረገው ማን ነበር? “ትግሬዎች ናቸው’ አደለም እንዴ?

አሁንም የቆየው “ትግሬዎች በዘመነ ወያኔ ልዩ ተጠቃሚዎች” አልነበሩም ሕዝብና ድርጅት ለያይተን እንመልከት የመባለው የተሳሳተው መስመር በዚህ ጦርነትም ብሶበት ምሁራኑና ጋዜጠኞች ሲያሽቀብጡ እየደመጥኩ ነው።

 

በጣም የሰለቸኝ ደግሞ የትግራይ ሪፑብሊክ ለመመስረት የተነሱት የትግራይ ብሄተረኞቹ ከጦርነቱ በኋላ በለስ ቀንቷቸው ከረጅም ጊዜ በኋላ መንግሥትነት ከያዙ በሗላም ይሁን ዛሬ ከሥልጣን ከተወገዱም ቢሆን የትግራይ ሕዝብም ሆነ ተጋዮቹ በጅምላ ጭፍጨፋ እና ከወያኔ የዘር ማጥፋት ፖሊሲ ጋር በተያያዙ ሌሎች ወንጀሎች ውስጥ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ተሳትፎ አላደረገም፤ የተደረገው ፍልሚያ ለዲሞክራሲና ለአንድነት ነበር የሚል አፈታሪክ አሁንም መቀጠሉ የሚገርም ነው፡፡

አሁን እየተካሄደ ባለው ጦርነት ምክንያት በትግራይ ላይ ርሃብ መከሰቱን አስመልክቶ በተከታታይ በዜና አውዶችና ውይይቶች የሚጋበዙ ምሁራን የሚሰጡት አስተያየት የማደምጠው ይትግራይ ሕዝብ በ17 አመቱ በታላቁ ሴራ አልተካፈለም ፤ ከዚያም አልፎ የትግራይ ሕዝብ በዘመነ ወያኔ ከሌሎች “አፓርታይድ ክልሎች” የተለየ ጥቅም አልተደረገለትም ሲሉ አድምጫለሁ።  ይህ መስመር ከእውነት የራቀ ነው ፡፡ ለማን እንዳደሩ ባላውቅም “አድርባይነትም” ነው።

ምሁራኖቹ የተዘረጉት የልማትና የትምሕርት የጤና “ሱፕራ እና ኢንፍራ” የሚባሉት እስትራክቸሮች/ተቋማት/ ምን ያህል ስፋት እንዳላቸው እያወቁም ቢሆን በቅርቡ ስለተከሰተው ርሃብ ምክንያት አስታክከው ትግራይ ላይ ምንም የልማትና የጤና፤የትምህርት ስላልተደረገ ሕዝቡ ባጭር ወቅት ለርሃብ ተዳርጓል የሚል ክርክር ማስተጋባት ጀምረዋል። በየ ጉሙዝና ኦሮሞ ክልሎች እየታረደና እየተፈናቀለ ያለው የአማራ ማሕበረሰብ ይህንን ቢሰማ ምን ይል ይሆን? ዛሬም እኮ ትግሬዎች ሳይሆኑ አማራዎች ናቸው መፈናቀሉና መታረዱ በገፍ እየተፈጸመባቸው ያለው። የጀነሳይድ ተመራማሪው “ዶ/ር ግሬገሪ እስታንተን” እንደተነበዩት ቢሆን ኖሮ ዛሬ ትግሬው ነበር በየ ክልሉ የዘር ጽዳት ሊደርሰው የነበረው። አንዳንድ ክስተቶች የታዩ ቢሆንም “ያ የተተነበየውና የተፈራው ጥቃት ግን የኢትዮጵያ ሕዝብ ጨዋነት እንዳይከሰት አድርጎታል።

ትግሬዎች ወያኔ ንጉሥ በመሆኑ ትግሬዎች ከዚህ ንጉሥና ቡድን ምንም አልተጠቀሙም የሚል ክርክር ለመማፍረስ ለበርካረታ አመታት በማስረጃ በመጽሐፍ በተለያዩ ሰነዶች አቅርበን ገልጸናል። ሌላ ቀርቶ ለምሳሌ ወያኔዎች ወደ ሥልጣን ሲገቡ ኤርትራኖችና ትግሬዎች ለነገዳቸው ጥቅም ለማስጠበቅ ሲሉ ሲያደርጉት የነበረውን “አገር አቀፍ ዘረፋ”

The pillage of Ethiopia by Eritreans and their Tigrean surrogates Paperback – January 1, 1996 by Assefa Negash (Author) Amazon የሚገኘው በዶ/ር አሰፋ የተጻፈውን መጽሐፍ ማንበብ ማስረጃ ይሰጣችሗል።

 አልተጠቀመም ባዮቹ ግን እስከዚህችኛው የጦርነት የርሃብ ወቅት ምንም ተጨባጭ ሰነድ አላቀረቡም። ማስረጃ ብለው ሲናገሩ ያደመጥኩት ነገር ቢኖር፤ ለምሳሌ በቅርቡ ምኒልክ በተባለው “የዩትዩብ ሚዲያ” ቀርበው ያደመጥኳቸው የታሪክ የሕግ እና እንዲሁም ጋዜጠኞች የሚል ማዕረግ ያላቸው ምሁራን “የትግራይ ሕዝብ በወያኔ ዘመን ልዩ ጠቀሜታ ያልተደረገለት መሆኑን ማስረጃው በሁለት ሳምንት ዕድሜ ያስቆጠረው ጦርነት 4 ሚሊዮን ለርሃብ መዳረጉ “ልዩ ጠቀሜታ ሳይደረግለት ሃብት ሳያጋብት መቆየቱ ማስረጃ ነው” ሲሊ ነበር እንደ ማሰረጃ ሲያቀርቡልን የነበሩት።

በተለይ ደግሞ አበርሃ በላይ የተባለው ኢትዮ ሚዲያ ጋዜጠኛ የግብጹ ሙባረክን ለመጣል የተደረገውን ሕዝባዊ አመጽ ለሳምንታት ሲደረግ ታሕሪር እስኩየር (የነጻነት አደባባይ) በተባለው ቦታ ሕዝቡ ለሳምንት ሲመሽግ ‘ምግብና ሻይ’ በየቀኑ ከሕዝቡ ሲቀርብ የምጣኔ ሃብት ያለው ሕዝብ ስለሆነ ትግራይ/ኢትዮጵያ ግን ካንድ ቀን በላይ ማድረግ አይቻለውም ሲል ንጽጽር ሲያሰርግ ሰምቻለሁ። አብርሃ ያላወቀው ግብጸች የመጨረሻ ድሆች ናቸው። ዜጎቿ አባይ ወንዝ ላይ ከበርካታ ልጆቻቸው ጋር ዝናብና ቁር በላያቸው ላይ እየወረደ ስብርባሪ ጀልባ ሃይቁ ውስጥ እየተንሳፈፉ የሚኖሩ የምድር ድሆች ያሏት አገር ነች።፡ ያም ይሁን እና ፤ አብርሃ የዘነጋው ያለፉት የተካሄዱ ኢትዮጵያ አብዮቶች ከማአከላዊ ከተሞች ሳይሆን ድሃ ከሚባሉት ኢትዮጵያ ከተሞችና ገጠሮች ሥርዓቱን ለመቋቋም ለበርካታ ወራት እንዴት ሥርዓቱን አስጨንቆ ብዙ ለውጦች እንዳመጣ ረስቶታል። 

በዚህ ሁለት ሳምንት አጭር ጦርነት 4 ሚኪዮን የትግራይ ሕዝብ ለርሃብ የተጋለጠው ወያኔ አደህይቶት ስለነበር ተሎ ለርሃብ ተጋልጧል የሚለው የነ አብርሃ ሆነ የነዚያ ምሁራን እምነት የማልስማማበት ምክንያት 1ኛ- ወያኔ ሲኖር 4 ሚሊዮን ሕዝብ ለርሃብ አልተጋለጠም፡ አሁን የተጋለጠበት ምክንያት ብዙ ምክንያቶች አሉት “መዋቅሩ ፈራርሷል” በወያኔና በጦርነቱ ሰበብ ማለት ነው። ስለዚህም እንደ ሶሪያ እና ሊቢያ ሁሉ ጦርነት ባለበት አገር ሁሉ ርሃብ እውን ሆነ።

 ኢንፍራስትራክተሮችና ሲፈራርሱ በጣም ሃብታም ከሚባሉት ኢራቅ፤ሶሪያ እና ሊቢያ ጦርነት በተነሳ በሳምንት ውስጥ የውሃ፤የመብራት፤የስልክ ፤ የምግብ እና የባንክ አገልግሎት ተቋርጠዋል።

 

በነዚያ አገሮች እንደተከሰተው ትግራይም ውስጥም ‘ርሃብ፤ ሞት ፣ ወሲባዊ ዓመፅ ፣ የምግብ እጥረት ፣ ፣ ህመም እና መድሃኒት ዕጥረት እንዲሁም የአካል ጉዳተኝነት ተከስቷል። በነዚህ አገሮች ከጦርነቱ በሗላም ድብርት እና ጭንቀት (PTSD) የታዩ የጦርነት ውጤቶች ታይተዋል ፡፡ ስለዚህ ትግራይ ውስጥ ባጭር ወራት የጦርነት ውጤት የሆነው ርሃብ የመከሰቱ ክስተት ድሃ ስለነበር የሚለው ቁንጽል ሙግት ስሕተት ነው።

ያውም አብሮ መዘከር ያለበት “የትግራይ ሕዝብ በዘመነ ወያኔ ልዩ ጠቀሜታ ኖሮት (በመላ አገሪቷ ባለ ሃብት ሆኖ) አልፎም ያልተገራ “የሕሊና ኩራት” ፤ እንዲሁም “የበላይነት ስሜት” (ሱፕረማሲ) አያንጸባርቅም ነበር ማለት “አድራበይነት ወይንም ጅልነት” ከመሆን አያልፍም።

ሕዝብ ስንል በማንኛውም ታሪክ አጋጣሚ “ሙሉ ሕዝብ እያንዳንዱ ሰው” ማለት ንደሆነ የሚሰጠው ትርጉም እውነታውን ለመሸፈን ካልሆነ በስተቀር በታሪክ ሙሉ የሚባል ሕዝብ አይራብም፤ ጦርነት አይሳተፍም፤ ሃብት አያካብትም። ሕዝብ የሚባል በትግራይ ውስጥ ብዙውን ታይቶ በማይታወቅ ብዛት የትግራይ ነገድ/ዘውግ በተለይ “ትግርኛ ተናጋሪው” በሃብትና በሥልጣን ተጋሪነት የበላይነት ይዞ ለ27 አመታት ተጠቃሚ ነበር። ይህ ደግሞ ምሁራኖቹ የሚገልጹት ቀለል አድርገው ክብደቱን ለመሸሸግ ሲሉ የሚገልጹት “ጥቂት የወያኔ ጀሌዎች ተጠቅመዋል” በሚል ሲገልጹት እሰማለሁ።  ይህ በጣም የተሳሰተ ያሰለቸን እና ያንድ ብሔረተኛ የመነሻ ፖሊሲው ትርጉም አለማወቅ ነው።

አንድ ብሔርተኛ የሚነሳው ቆሜለታለሁ ለሚለው ነገዱ ፤መጥቀም እና ለመከላከል እንዲሁም ሥልጣን ይዞ ምጣኔ ሃብቱን ለነገዱ ለማስረከብ መሆኑን ከወያኔ ዘመን አገዛዝ ሌላ ማስረጃ ማቅርብ አይቻልም። በተግባር ያየነውም ይኸው ነው።

ዳኝነቱ፤ከላከያው፤የሚኒሰትሮች፤የመገናኛዎች፤ኢንቨየስተሮች/የንግዶች. ወዘተ…ወዘተ ባንድ ነገድ (በትግርኛ ተናጋሪው ትግሬ) ተይዞ ነበር። ዛሬም በሌሎች ባለ ተራ ዘውጌዎች ተሸጋግሮ አያየን ነው። ሃቁ ይህ ነው። የዛሬዎቹ ባለተራ ኦሮሞዎች ደግሞ ማንን እየጠቀሙት እንዳሉት በግሃድ እየታየ ነው። እነዚህ ይህንን ማድረጉን ካመናችሁ፤ እነኚህ ከማን እንደተማሩ ማወቅ አይቸግራችሁም።

በጣም የገረምኝ ደግሞ እዛው ምንልክ በተባለ ሚዲያ አንድ የሕግ ምሁር የተባለለት እንግዳ “በረሃብ የተጠቃውን የትግራይ ሕዝብ የአማራ ማሕበረሰብ ለመከላከያው በሬ እና በግ ገዝቶ ከማገዝ አልፎ ትግሬውን ከዚያ በዘለለ ማገዝ ይጠበቅበታል ሲል አስገርሞኛል። ሃሳቡ የሚከፋ ባይሆንም፡ እኔ የምለው “አማራው” ከትግሬው በምን ተሽሎት ነው ይህ ሁሉ ሃላፊነት ሊጠየቅ የበቃው። እኔ የምለው የትግራይ ሕዝብ 27 አመት እነሱ ባነገሱት የፋሺሰት ቡድን ሲቀጠቀጥ፤ሲታረድ ሲታረዝ፤ ሲባረር “ምሁራኖች” ተመሳሳይ ጥያቄ አቅርባችሁላቸው ነበር? ካላቀረባችሁላቸውስ ለምን አልጠየቃችሗቸውም? ወይንስ እራሳችሁም 27 አመት አማራ ሲንገላታ “ዝምታ ውስጥ ነበራችሁ” ።

ለመሆኑ ትግሬው ቪክተማይዝድ ተደርጎ እየቀረበ ያለው ተጠያቂው ማን ነው? ትግሬው በኢትዮጵያዊያን አልተበደለም። ሃቁ ይህ ነው። ያውም ከማንኛውም ክፍለሃገር የከፋ የብቀላ ብትር አልተሰነዘረበትም። ለዚህም ኢትዮጵያዊያን መምስገን አለባቸው። እንደ እውነታው ቢሆን ኖሮ አስቀድሜ ከላይ እንደጠቀስኩት “የጀነሳይድ ተመራማሪው “ስንታንተን” የተናገሩት መርሳት አይገባም። እሳቸው ያሉት “እኔ የምሰጋው ወያኔ ከሥልጣን ሲወገድ የማዝነው ለትግራይ ሕዝብ ነው” ነበር ያሉት። የተፈራው ባይደርስም (በሕዝብችን ደግነትና አስተዋይነት የተሰጋው ቆሟል) ፤

የሚገርመው ደግሞ “ጦሱ” ከሌላ የተቀሰቀሰ ሳይሆን ግን ባራሳቸው አካባባቢ ተለኩሶ እነሱን ራሳቸውን ተመልሶ እየለበለባቸው ነው። ይህ እንዳይደርስ ለብዙ አመታት “ወያኔ” የሚባለው ቡድን እና ፖለቲካ እንዳትቀበሉ “መጨረሻ ራሳችሁን ይበላል” እያልን ስንጮሕ ከሕዝቡ የሰማነው ምላሽ ምን እንደነበር ታውቃላችሁ።  አሁን ይህ ሁሉ መከራ ሲደርስበት ተጠያቂው ማን ነው? ተጣያቂ 1ኛ፤የትግራይ ምሁርን እና ሕዝቡ እራሱ ነው፤ 2ኛው ተጠያቂ የኦሮመዎቹ መንግሥት የሆነው አብይ አሕመድ የሚመራው ሥርዓት ነው። የተቀረው የውጭ ጦሰኛ ካለ መጀመሪያ ልጅህን ማስታገስና መስመር ማስያዝ በተገባ ነበር። ያ ሳይሆን እንደኳስ ጨዋታ “አየኹም ናይና” (የኛዎቹ አይዟችሁ) እየተባለ በየ አደባባዩ ሽማግሌና አሮጊት እናቶች ሳይቀሩ የወያኔ ባንዴራ ታጥቀው ሲዘሉና እስከስታና ፉከራ ከማየት ምን የከፋ ትዕይንት አለ?

የትግራይ ሕዝብ ከማንም በላይ ጦርነት አይቷል፤ ጉዳቱንም ያወቀዋል ተብሎ ሲነገር ነበር። አይደለም እንዴ? የጦርነት ምንነት ያወቀ ሕዝብ እንዴት በአንድ ሓላፊነት በማይሰማው፤ አገር ገንጣይ ትምሕርት ተከትሎ በጊዜው ጦርነቱን መግታት ተሳነው?

 

2ኛው ርዕስ

 የወያኔ ታጋዮች ለዲሞክራሲ ትግል ነበር በረሃ የወጡት የሚለው የተሳሳተ ትርክት በሚመለከት፡

 

የትግራይ ሕዝብ ወዶም ተገድዶም ጸረ አማራ ፖሊሲ መከተሉ ከኔ በላይ አብልጦ ወያኔን የሚያውቅ እና በምስረታው ሃ ብሎ ሲጀመር ደደቢት በረሃ የወረደው መስራች አባል የነበረው አንዱ አስገደ ግበረስላሴ የነገረንን እውነታ ይድረስ ለጎጠኛው መምህር ከሚለው ከመጽሐፌ ቀንጭቤ የሰጠውን ጥቅስ ላቅርብ፡<<ህዝባዊ ሓርነት ትግራይ አማራዎች ከድሮ፤ከጥንት ጀምሮ የትግራይ ሕዝብ ጠላቶች ናቸው። እነኚህ አህዮች ከአገራችን ይውጡ፤ትግራይ የራሳችን ነፃ አገር ነች፤ እነኚህ አማራዎች ሲፈልጉ ወደ አገራቸው ሄደው ይታገሉ!!”>> ስትል ህወሓት ኢሕአፓዎችን በትግራይ ውስጥ የመንቀሳቀስ ኢትዮጵያዊ ዜግነታቸውና መብታቸውን ገፈፈች።>> (አስገደ ገ/ስላሴ ህወሓትን ከመሰረቱ የመጀመርያው የህወሓት ታጋይ-ጋህዲ ቁጥር 2 ትግርኛው ቅጅ -ገጽ 162) 

<<ህወሓት ነፃ የሆነች የትግራይ ሪፑብሊክ ለመመስረት ነው ዋናው የትግላችን ዓላማ>> ስትል… ኢሕአፓ ደግሞ <<ትግራይ የኢትዮጵያ ሕዝብ አካል ነው ስለሆነም ትግላችሁ የኢትዮጵያን አንድነትን የሚበትን ነው።>> ሲሉ ነበር። (አስገደ ገ/ስላሴ- ጋህዲ ቁ/2 የትግርኛው ቅጅ 2001 ዓ.ም)

<<ኢህአፓ በአጋሜ አውራጃ ውስጥ በአሰፈ ሰበያ እና በወረዳ ጉሎ ሞዀዳ በወያነ ትግራይ የጠባብነት ጨረታ አሸናፊነት ተበልጦ ከትግሉ ከወጣ በሗላ።ከዚያ በሗላ የጠባብ ብሔረተኝነት በሽታ በመላዋ ትግራይ እንደ ተላላፊ በሽታ ተስፋፍቶ ወደ ሕዝቡ በመተላለፉ አብዛኛው የትግራይ ሕዝብ ፀረ አማራ ተንቀሳቀሰ።”>>

(አስገደ ገ/ስላሴ የወያኔ የመጀመሪያ መስራች አንዱ፦ ጋህዲ ቁ/2 ገጽ 155 የትግርኛው ቅጂ 2001 ዓ.ም.} ።

ልብ ልትልሉኝ የምፈልገው አስገደ ገብረስላሴ የትግራይን ሕዝብ የገለጸውን “…ከዚያ በሗላ የጠባብ ብሔረተኝነት በሽታ በመላዋ ትግራይ እንደ ተላላፊ በሽታ ተስፋፍቶ ወደ ሕዝቡ በመተላለፉ አብዛኛው የትግራይ ሕዝብ ፀረ አማራ ተንቀሳቀሰ።” የሚለውን የሚያሳይን ታጋዩም ሆነ ሕዝቡ ስለ ዲሞክራሲ ሳይሆን የታገለው አስገደ አስቀድሞ እንደነገረን ጸረ ኢትዮጵያ እና ጸረ አማራ ትግል ነበር ያካሄደው። ሕዝቡ ልጁን እየሸኘ እየመረቀ ለጦርነቱ እሳት አንዲሆን ልኬአለሁ ሲሉ በርካታ ወላጆች በቃለ መጠይቅ ሲናገሩ በጆረየ ሰምቻለሁ። ስለሆነም የወያኔ ታጋዮችና የትግራይ ሕዝብ በአማራ ሕዝብ ላይ የዘር ማጥፋት ፖሊሲው በቀጥታም በተዘዋዋሪም የማይነጣጠሉ ትስስሮች አድርገዋል የምለውም ለዚህ ነው።

ጦርነቱ እና የዘር ማጥፋት ፖሊሲው የማይነጣጠሉ ትስስሮች ነበሩ የምለው የጎንደርና የወሎ መስተዳድር የነበሩ ሕዝብና ለም መሬቶች ተነጥቀው ለትግሬዎች ሲሰጥ በዕልልታ ተቀብለው እዛው የነበረው ጥንታዊ ሕዝብ በመጤ ታጋዮች እየተገፋ “ኩንታል ለመሸከምና ዳቦ መግዣ የምትሆን የቀን ሥራ” አንኳ ለመስራት “አማራ ስለሆነንክ” አይፈቀድልህም እንባል ነበር ሲል ወልቃይት ነፃ ሲወጣ ከጉዳተኞች አንደበት ባለፈው ወር ሰምተናል።  ስለሆንም ከርዕስ መስተዳደር እስከ ሁሉም የቀገጥርና የከተማ ቅርንጫፎች ኢትዮጵያን አሁን ወዳለው አደጋ ለማስገባት በመጨረሻም በራሱ ልጆች ለችጋር መዳረጉ እራሱ የራሱን ችግር በመፍጠር ጉዳይ ሃላፊነቱ የራሱ መሆኑንም መዘንጋት የለበትም እላለሁ። ትግሬነቴን ለምትክዱም ሆነ እውነታውን በመናገሬ ለምትጠሉኝ ምሁራን ሁሉ ዛሬም እንደ ወትሮው ጠምለው ነገር ቢኖር አውነታውን ከመናገር አማራጭ የለም። በመጨረሻም ለትግራይ ሕዝብ የምለው ቢኖር፤ ወያኔንና ችግሩን ላንዴና ለመጨረሻ ለማስወገድ ከዘመተው ኢትዮጵያ መከላከያ አብሮ መበዝምት ዕድሉ ክፍት ስለሆነ፤ ያንን ትግራይ ሪፑብሊክ ቅዠት አሁን ላንዴና ለመጨረሻ የማስቆም አቅሙ ስላላችሁ፤ ያንን በወቅቱ ማከናወን ነው። ካልሆነ፤ ችግሩ ይብስ እንጂ አይሻሻልም። ፋሺዝምና ብሀየረተኛነት መቸውንም የልማትና የፍትሕ አምጪ ሆኖ ኣያውቅም። ሰላማችሁን ካስከበራችሁ በሗላ ግን አብይ የተባለው ፋሺሰት ከተቀረው የኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር ኢትዮጵያዊነታችሁን አክብራችሁ ከሥልጣን እንዲወርድ ማድረግ የግድ ነው። አብይ በሰለማዊ ሰልፍ ማውረድና ማስጨነቅ ይቻላል፤ ጦር መሰበቅም አያስፈልግም።

 አመሰግናሉ።

ጌታቸው ረዳ