Sunday, May 30, 2010

ተቃዋሚዎቹ የሚፈተኑበት ፈተና የመፈተኛዉ ወቅት አሁን ነዉ

An electoral official removes campaign posters pasted on the iron sheet fence outside a polling centre in the capital Addis Ababa, May 22, 2010. Ethiopians vote on Sunday in the first elections since a disputed 2005 poll. Voters in sub-Saharan Africa's second most populous nation will be electing 547 parliamentarians. REUTERS

ተቃዋሚዎቹ የሚፈተኑበት ፈተና የመፈተኛዉ ወቅት አሁን ነዉ

ጌታቸዉ ረዳ www.Ethiopiansemay.blogspot.com

June 30, 2010

ዉጭ አገር ያለን ተቃዋሚ ክፍሎች አገር ዉስጥ የሚኖሩት የወያነ ተቃዋሚዎች በምርጫ 2002 (ግንቦት ወር) መሳተፍ አለባቸዉ መሳተፍ የለባቸዉም በሚሉ ንትርኮች ገብተን በተቃዋሚ መሪዎች ላይ ዘላፋዎች ተካሂደዋል። በሁኔታዉ ንትርክ ገብተን አቋማቸንን መግለጻችን ይታወሳል።

እንደሚታወቀዉ ምርጫዉ በወያኔ አጭበርባሪነት ተገባድዶ የሕዝብ ድምፅ ተዘርፎ በወያኔ የዉሸት ምርጫ አሸናፊነት ተደምድሟል። ምርጫዉ በወያኔ አጭበርባሪነት ሲደመደም ትግሉ አልተደመደመም። የምርጫዉ አጭበርባሪነት የሚያመለክተዉ ለመራራ ወሳኝ የመጨረሻ የሞትና የሽረት ትግል ጥሪ ነዉ ማለት ነዉ። ከምርጫዉ በፊት ተቃዋሚዎች ሁለት ዓይነት ተቃዋሚ እና ደጋፊ ነበርዋቸዉ። ወደ ምርጫ በመሳተፋቸዉ አንዱ ክፍል ደጋፊያቸዉ ነበር ምርጫ መሳተፍ የለባቸዉም የሚሉ ደግሞ ተቃዋሚያቸዉ እና ዘላፊአቸዉ ነበር። አሁን ግን አገር ዉስጥ ያሉት ተቃዋሚዎች የምርጫዉ ዉጤት በሚያስተጋባዉ ጥሪ ምክንያት በሚወስዱት እርምጃ ለነሱ በድጋፍ የቆሙት የተቃዋሚዎቹ ደጋፊዎች ሊያጧቸዉ ወይንም ደጋፊዎቻቸዉ ሆነዉ የሚቀጥሉበትን ሁኔታ ተፈጥሯል። ግልፅ ለማድረግ፦ ምርጫዉ በወያኔ አጭበርባሪነት እንዲደመደም ካደረገ ድምጽቻዉ የተነጠቁ ተቃዋሚዎች ከባድ ፈተና ያለባቸዉ መሆኑና ፈተና የመፈተኛ ወረፋቸዉ አሁን ሆኖ ፈተናዉን በሚገባ ለማለፍ ዝግጁነታቸዉ በተግባር የሚያሳዩበት ወጣሪ የመፈተኛ ዓዉድማ ተንጣሎ እየጠበቃቸዉ ስለሆነ ሲደጉፏቸዉና ጥብቅና ቆመዉ ሲደግፏቸዉ የነበሩት ደጋፊዎቻቸዉ እንዳያጡ በብርታት ፈተናዉን ማለፍ ይጠበቅባቸዋል።

ከፊታቸዉ ተንጣሎ እየጠበቃቸዉ ያለዉ ከባድ ፈተና ካላለፉት ለታሪካቸዉ እና ለዝናቸዉ መጥፎ ስዕል ትቶ የሚያልፍ መሆኑን መረዳት ይገባቸዋል። ምርጫዉ እንዲጭበረበር መሪዎችም እኛም እናዉቅ ነበር። ሆኖም ወደ ሚጭበረበር ምርጫ እንዲገቡ የገፋፋናቸዉ ዓይነተኛ ምክንያት፤ የተጭበረበረን ምርጫ መረጃ እና ምክንያት ተጠቅሞ ሕዝቡን ለፍትሕ ጥያቄ በማነሳሳት ወያኔ ለመጨረሻ ጊዜ ከስልጣን የሚሰናበትብትን ሕዝባዊ አመጽ/ሰላማዊ አመጽ እንዲቀሰቅሱ በር ይከፍትላቸዋል በሚል ነዉ። ወቅቱ ደግሞ አሁን ነዉ። የተጭበረዉን ምርጫ ትግራይን ለምሳሌ ብንመለከት፦ ትግራይን ከሚገዙ የወያኔ ፊዉዳላዊ ቡርዧ /ተወልጄዎችና የከበርቴ ተናብልት (የከበርቴ መኳንንት) ተወካይ የሆነዉ ሃለቃ ጸጋይ በርሄ ስለምርጫዉ አንስቶ ራሳቸዉን ላሞኙት ዉጭ አገር ላሉ ገለባዎቹን ባዘጋጁለት “የ ኢንተረኔት-ፓል ቶክ” ምርጫዉን አስመልከቶ ስለ ሰጠዉ ቃለ መጠይቅ ለምርጫ የተመዘገበዉ የመራጩ ሕዝብ ብዛት 2, 017,695 (ሁለት ሚሊዬን አስራ ሰባት ሺህ ስድስት መቶ ዘጠና አምስት) ሲሆን ከዚህ ዉስጥ 1,098218 (አንድ ሚሊዮን ዘጠኝ መቶ ሰማንያ ሁለት ሺሕ አስራ ስምንት) ሕዝብ ድምፅ የሰጠ ሲሆን ከነዚህ ዉስጥ 98.6% (99%) በመለስ ዜናዊ የሚመራዉ የወያነ ትግራይ ድርጅት ድምፅ አግኝቷል ሲል በክፍለ ሃገሩ ዉስጥ 6 ድርጅቶች እና አንድ በግል የቀረበ ተወዳዳሪ በድምሩ 7 ተቃዋሚዎች ያገኙት ድምፅ 30,000 (1%) እንደሆነ ያለ ምንም ሃፍረት በመኩራራት ገልጿል። ከ7 ተቃዋሚዎች ዉስጥ 5ስቱ ያክል ምርጫዉ ያለ ምንም ማጭበርበር ሕጋዊ እና ሰላማዊ ሆኖ እንደተከናዋነ ፌርማቸዉን እንዳኖሩ ገልጿል። እነ ስየ እነ ገብሩ በዚህ ፌርማ ይኑሩበት አይኑሩበት የታወቀ ነገር የለም። የመ ኢአድ ተወካይ ወ/ሮ መሰሉ ረዳ ግን ከምርጫዉ በፊትም በምርጫዉ ወቅትም የምርቻዉ ስርዓት ሕግ የጣሰ እና ማስፈራራት እና በማጭበርብር የተከናወነ እንደነበር ከትናንት በስቲአ ማለትም በዓርብ ዕለት ከየአሜሪካ ድምፅ ራዲዬ የ አማርኛዉ ክፍል ከጋዜጠኛዋ ከ/ወ/ሮ አዳነች ፍስሃየ ጋር ባደረገቺዉ ቃለ መጠይቅ ከሰጠቺዉ መረጃ ለማረጋገጥ ይቻላል። እነ ስየ አልተጭበረበረም ብለዉ ፈርመዉ ከሆነ ምንም ማለት አይቻልምና ሂሱ ለደጋፊወፐቻቸዉ መተዉ ነዉ። ተጭበርብሯል በማለት ፀጋይ በርሄ እንዳረጋገጠዉ አሃዝ በማጭበርብር የተገኘ አሃዝ ነዉ የሚሉ ከሆነ ደግሞ ፡ ይህ አሳፋሪ በስርቆትና በማስፈራራት የተከናወነ የድምፅ ዉጠት መፈጸሙ ካመኑ ደግሞ እነ ገብሩም ሆኑ እነ ስየ ከሌሎቹ ተቃዋሚዎች ጋር የሚጠበቅባቸዉ ቀጣዩ ፈተና በምን ሁኔታ ይወጡት ይሆን የሚለዉ ወጣሪ ሁኔታ ከሚከተሉት የትግል ስልት የምናየዉ ይሆናል።

መንም እንኳ 99.9% የሕዝብ ድምጽ አገኘሁ እያለ የራሱን ሞኞቹን ቢያሞኝም ያጭበረበረ መሆኑን ዉስጡ ስለሚያዉቅና በተለይም 18 ዓመት ሙሉ በስልጣን ሲቆይ ለሕዝቡ ባዕድ በመሆኑ ፡ ራሱን በቴ/ቪዢን መስኮት ብቅ አድርጎ ከመታየት ሌላ ከሕዝቡ ጋር ወዳጅነት ስላልመሰረተ እገደላለሁ ብሎ ሰለሰጋ “ጥይት የማይበሳዉ” የነብስ መከላከያ የመስተዋት ማማ (Booth) ባደባባይ አስተክሎ በብዙ ሺህ ብር ወጪ በተሰራችለት መስተዋቷ ዉስጥ በመግባት እንደ ጥንቸል ተቆልፎበት ስለ ዘረፈዉ የህዝብ ድምፅ ለማብራራት ያዘጋጀዉን ጽሁፍ ሲያነብብ የተመለከቱ ተቃዋሚዎች የሕዝቡን መብት ለማስከበር ሕዝቡን ለሰላማዊ አመጽ በማነሳሳት መለስ ዜናዊ መስተዋት ዉስጥ ራሱን ከመሸሸግ አልፎ ሌላ ያላየነዉ አስቂኝ እና አስገራሚ የድንጉጦች እዉነተኛ ባሕሪይ በድጋሚ ተደናብሮ እንዲሸሸግ ለዓለም ሕዝብ የሚያሳዩበት ወደ ከባዱ ፈታኝ አዉድማ አሁኑኑ ዘለዉ መግባት ይህ ጸረ ኢትዬጵያ ግለሰሰብ ከተሸሸገበት መስተዋት እንዲወጣ እና ለፍትሕ እንዲያቀርቡት ይመች ዘንድ የተቃዋሚዎች ጥራት እና የትንካሬ ማንነት የሚገልጹበት ተቃዋሚዎች የሚፈተኑበት የፈተና ወቅት አሁን ነዉና ፈተናዉን በልበ ሙሉነት በመጋፈጥ በኩራት ተወጥተዉ ታሪክ በመልካም ስም እንዲያነሳቸዉ ያድርጉ። ይህ በሚያከናዉኑበት ወቅት ቅማችንን ሁሉ በመለገስ ከጎናቸዉ የምንቆም መሆናችንን በድጋሜ ቃል እንገባለን።

ገሥጾሙ፤ ለአራዊተ ሃለት።ማሕበረ አልሕምት ዉስተ ዕጓላተ፤ሕዝብ። ከመ ኢትዐጸዉ፤ እለ ፍቱናን ከመ ብሩር።ዝርወሙ፤ለአሕዛብ፤እለ ይፈቅዱ፤ቅትለ፤ ይምጽኡ ተናብልት፤ እምግብጽ። አትዮጵያ ታበጽሕ እደዊሃ ሃበ እግዚአብሔር።

(በሸንበቆ ዉስጥ ያሉትን አራዊት ፤ በአሕዛብ ዉስጥ ያሉትን የበሬዎችንና የወይፈኖችን ጉባኤ ገሥጽ። እንደ ብር የተፈተኑትን አሕዛብ እንዳይዘጉ፤ ሰልፍን የሚወዱትን አሕዛብን በትናቸዉ። መኳንንት ከግብጽ ይመጣሉ፤ ኢትዮጵያ እጆችዋን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች።) የኢትዮጵያ ሰማይ ድረ ገጽ አዘጋጅ ጌታቸዉ ረዳ www. Ethiopiansemay.blogspot.com